Telegram Web Link
በቀጣይ ዓመት የትምህርት ዘመን ተማሪዎች ለኮሮና ተጋላጭ እንዳይሆኑ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 19 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በ2013 የትምህርት ዘመን ተማሪዎች ለኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ እንዳይሆኑ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ÷ የቀጣዩ ዓመት ትምህርት ምዝገባ ከነገ ነሐሴ 20 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ በመንግሥት እና በግል ትምህርት ቤቶች እንደሚጀመር ገልጸዋል።

ትምህርት ቤቶች የኮሮና ቫይረስ መከላከያ መንገዶችን በመተግበር ምዝገባ እንዲያከናውኑ ተፈቅዷል ብለዋል።

የበሽታው ሁኔታ እየተስፈፋ ቢሆንም የትምህርት ዝግጅት እና እንቅስቃሴ መጀመር አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን ነው ሚኒስትሩ የተናገሩት።

ሚኒስትሩ አያይዘውም ወደ መማር ማስተማር ተግባር በሚገባበት ወቅት ለተማሪዎች ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር እንደሚሠራ ጠቁመው÷ ማስክ፣ የእጅ ማፅጃ እና መሰል አቅርቦቶችን ከባላድርሻ አካላት ጋር በመሆን ለማቅረብ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በግልም ሆነ በመንግሥት ትምህርት ቤቶች የኮሮና ቫይረስ ስርጭት እንዳይከሰት ተማሪዎች ማስክ በማድረግ፣ አካላዊ ርቀትን በመጠበቅ እና እጅን በመታጠብ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚኖርባቸው ሚኒስትሩ አሳስበዋል።

ከቅድመ መደበኛ ጀምሮ እስከ 12ኛ ክፍል ላሉት ተማሪዎች በ2012 የትምህርት ዘመን በ2ኛ ሴሚስተር ያለፋቸውን ትምህርቶች ማካካሻ ለመስጠት መታሰቡንም ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ከኢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።

#FBC
የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማስጀመር የሚያስችሉ ሁኔታዎችን እያጤንኩ ነው አለ ትምህርት ሚኒስቴር፡፡
----------------------------------------
የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሚሊዮን ማቲዎስ የ2013 አ.ም.የትምህርት ሂደትን ለማስቀጠል የሚያስችሉ ከትምህርት ቤቶች አከፋፈት ጋር ተያይዞ ባሉ ወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

የኮሮና ቫይረስ በኢትዮጵያ መከሰቱን ተከትሎ ከ42 ሺ በላይ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ይማሩ የነበሩ ከ26 ሚሊየን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ ሆነዋል፡፡

የ2013 ዓመት ትምህርትን ለመጀመር የሚስችሉ ሁኔታዎችን ለመቃኘት የጥናት ቡደን ተቋቁሞ ጥናት እያደረገ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል፡፡

በጥናቱ መሰረት ትምህርት ቤቶች በአንድ ክፍል ውስጥ ከ20 እስከ 25 ተማሪዎችን ለማስተማር የሚያስችል አቅም ስለመኖርና አለመኖራቸው ልየታ እየተካሄድ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

የተማሪዎችን ርቀት ለማስጠበቅ በአንድ ወንበር አንድ ተማሪ እንዲቀመጥ የሚደረግ ሲሆን በፈረቃ ትምህርት መስጠት፣ ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎች መገንባት፣ የማህበረሰብ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትን ለማስተማሪያነት መጠቀም እንደ አማራጭ ጥቅም ላይ እንደሚውሉ ተገልጧል፡፡

ይህንን ታሳቢ በማድረግ አንዳንድ ክልሎች አስቀድመው ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎችን የገነቡ ቢሆንም ሁሉም ክልሎች በየትምህርት ቤቱ ተጨማሪ ክፍሎችን እንዲገነቡ እየተደረገ ነው።

በትምህርት ቤቶች ውስጥ ውሃ እንዲኖር ማድረግ፣ የእጅ ማፅጃ ሳኒታይዘርና ማስክ የማቅረብ ስራዎችም እንደሚሰሩ ተነስቷል፡፡

የኮረና ቫይረስ ስርጭት ያለበት ሁኔታ እየተገመገመ ደረጃ በደረጃ ትምህርት ቤቶችን ለመክፈት የሚያስችሉ ሁኔታዎች እየተጤኑ ነው ያሉት ሚስትር ዴኤታው ሚሊዮን ማቲዎስ ለስኬቱ ወላጆችና ባለድርሻ አካላት ከመንግስት ጎን እንዲቆሙ ጠይቀዋል፡፡

Fana

@KAWGMS_portal
#የ2013 ዓመት ትምህርትን ለመጀመር የሚስችሉ ሁኔታዎችን ለመቃኘት የጥናት ቡደን ተቋቁሞ ጥናት እየተደረገ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሚሊዮን ማቲዎስ ተናግረዋል፡፡

📌በጥናቱ መሰረት ትምህርት ቤቶች በአንድ ክፍል ውስጥ ከ20 እስከ 25 ተማሪዎችን ለማስተማር የሚያስችል አቅም ስለመኖርና አለመኖራቸው ልየታ እየተካሄድ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

📌የተማሪዎችን ርቀት ለማስጠበቅ በአንድ ወንበር አንድ ተማሪ እንዲቀመጥ የሚደረግ ሲሆን በፈረቃ ትምህርት መስጠት፣ ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎች መገንባት፣ የማህበረሰብ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትን ለማስተማሪያነት መጠቀም እንደ አማራጭ ጥቅም ላይ እንደሚውሉ ተገልጧል፡፡

📌ይህንን ታሳቢ በማድረግ አንዳንድ ክልሎች አስቀድመው ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎችን የገነቡ ቢሆንም ሁሉም ክልሎች በየትምህርት ቤቱ ተጨማሪ ክፍሎችን እንዲገነቡ እየተደረገ መሆኑም ነው የተነገረው።#አዲስ_ነገር #Whatsnew_ebs
የጤና ሚኒስቴር ትምህርት ለመጀመር የሚስችል ሁኔታ መኖሩን ሲያረጋጥልን ትምህርት እንጀምራለን - የትምህርት ሚኒስቴር

የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ያለበት ደረጃ ተገምግሞ ትምህርት ለመጀመር የሚያስችል ሁኔታ መኖሩን የጤና ሚኒስቴር ማረጋግጫ ሲሰጥና መንግስት ውሳኔ ሲያሳልፍ ትምህርት እንደሚጀመር የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ከትምህርት ገበታ ውጪ ያሉ ህፃናት በከፍትኛ ሁኔታ እየተጎዱ በመሆኑ ለእነሱ ቅድሚያ እንደሚሰጥም ነው ያብራሩት፡፡

ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ለ6 ወር ከትምህርት ገበታ ውጭ የሆኑ ህፃናት ከዚያ በፊት ለሁለት አመታት ያክል ይዘውት የነበረውን እውቀት ሊያሳጣቸው ይችላል፡፡

በዚህ ምክንያት ለህፃናት ቅድሚያ ለመስጠት እቅድ ተይዟል፡፡

የዓለም የጤና ድርጅት መረጃ እንደሚያሳየውም ህፃናት በኮሮና ቫይረስ የመያዝና የማስተላለፍ ባህሪያቸው ከሌሎቹ የቀነሰ በመሆኑ ድርጅቱ የሚያስቀምጣቸውን የቫይረሱን መከላከያ መንገዶች ሙሉ ለሙ በመተግበር ትምህርት ለመጀመር ጥረት ይደረጋል፡፡

በትምህርት አከፋፈት ዙሪያ የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ በተስፋፋባቸው እንደ አዲስ አበባ ባሉ ትላልቅ ከተሞች ትምህርት በ3 ፈረቃ ለመጀመር እቅድ ተይዟል፡፡

ከትላልቅ ከተሞች እርቀው የሚገኙና የቫይረሱ ስርጭት ስጋት በሌለባቸው አካባቢዎችም የኮሮና ቫይረስ መከላከያ መንግዶችን በመተግብር ትምህርት እንደሚጀመር ዶ/ር ጌታሁን መናገራቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በትምህርት ቤቶች አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ትምህርት ለመጀመር ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ ነው:-ትምህርት ሚኒስቴር
-------------------------------------------------
በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ለ 7 ወራት የተቋረጠውን መደበኛ ትምህርት ለማስቀጠል ትምህርት ሚኒስቴር አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉን አስታወቀ፡፡

መንግስት በትምህርት ቤቶች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል፣ የውሃ እና የእጅ ማፅጃ አቅርቦቶችን በማሟላት እንዲሁም ትምህርት ቤቶችን የማፅዳት ስራዎችን በማከናወን መደበኛ ትምህርት እንደሚጀመር ተገልጿል፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር ኢንጂ.) ትምህርት ቤቶች ሲከፈቱ ተማሪዎች እንደየ ደረጃው ወደ ክፍል ገብተው ትምህርታቸውን እንደሚከታተሉ የገለፁ ሲሆን ትምህርት ሲጀመርም በአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች የሚጀመር መሆኑን እና በቀጣይም ሌሎች የትምህርት ክፍሎች ወደ መደበኛ ትምህርቱ እንደሚገቡ ተናግረዋል፡፡

በትምህርት ቤቶች የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የተቀመጡ ጥንቃቄዎች ሙሉ በሙሉ የሚተገበሩ መሆኑን እና የትምህርት አሰጣጡ ሂደትም በፈረቃ የሚሰጥ መሆኑንም ሚኒስትሩ አብራርተዋል፡

የፈረቃ ስርዕቱም እንደየአካባቢው ሁኔታ ከ 2 እስከ 3 ሊሆን እንደሚችልም ተገልጿል፡፡

የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል በትምህርት ቤት ውስጥ መምህራኖች ትልቁን ሃላፊነት ሊወጡ እንደሚገባ የተገለፀ ሲሆን ወላጆችም ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት ሲልኩ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

መደበኛ ትምህረቱም መንግስት ውሳኔ እንዳሳለፈ እንደሚጀምር ተገልጿል፡፡

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስፈላጊውን የጥንቃቄ እርምጃዎችን በመተግበር ትምህርት ቤቶችን መክፈት እንደሚቻል ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ምክረ ሃሳብ ማቅረቡ ይታወሳል፡፡
የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ቀን በነገው ዕለት ይፋ ይሆናል -ትምህርት ሚኒስቴር
~
በሀገር አቀፍ ደረጃ ትምህርት የሚጀመርበት ቀን ነገ ከቀኑ 9 ሰአት ላይ ይፋ ይደረጋል

አስፈላጊውን ቅድመ ጥንቃቄ በማድረግ በሀገር አቀፍ ደረጃ የመማር ማስተማር ስራው በቅርብ ቀን እንደሚጀመር የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

"ትምህርት ቤቶች በምን መልኩ እና እንዴት ይጀምሩ?" በሚለው ዙሪያ ከሁሉም ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ጋር ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡

ውይይቱ ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት የሚካሄድ ሲሆን ነገ ከቀኑ 9 ሰአት ላይ በሀገር አቀፍ ደረጃ ትምህርት የሚጀመርበት ቀን ይፋ ይደረጋል ተብሏል፡፡

በተጨማሪም የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ቀንም በነገው ዕለት ይገለፃል ተብሏል፡፡
ትምህርት ቤቶች በሶስት ዙር ትምህርት እንዲጀምሩ ሊደረግ ነው፡፡
==================
ትምህርት ቤቶችን ዳግም መክፈት በሚቻልበት የውሳኔ ሃሳብ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በተገኙበት በጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ውይይት እየተካሄደ ነው።

በውይይቱ የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፋዎችና ሌሎች ሚኒስትሮችም ተገኝተዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ትምህርት ቤቶችን ዳግም ለመክፈት ስለቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ገለፃ አድርገዋል።

የትምህርት ቤቶች ትምህርት ማስጀመር ሂደት በሶስት ዙር እንደሚከናወን የሚል ምክረ ሃሳብ ቀርቧል፡፡

በገጠር ወረዳና ቀበሌ ከተሞች የሚገኙ ትምህርት ቤቶች በመጀመሪያው ዙር ጥቅምት 9 ቀን 2013 ዓ.ም ትምህርት እንዲጀምሩ የውሳኔ ምክረ ሃሳብ ቀርቧል።

በሁሉም የዞንና የክልል ከተሞች የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ደግሞ በ2ኛ ዙር ጥቅምት 16 ቀን 2013 ዓ.ም ትምህርት እንዲጀምሩ ነው ምክረ ሃሳብ የቀረበው።

በአዲስ አበባና ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን የሚገኙ ትምህርት ቤቶችም ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ትምህርት እንዲጀምሩ የውሳኔ ምክረ ሀሳብ ቀርቧል።

የ8ኛና የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን አስመልክቶም ሁሉም ተፈታኞች ለፈተና እንዲቀመጡ የሚል የውሳኔ ምክረ ሃሳብ መቅረቡ ተገልጿል።

የ8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ሕዳር 22 እና 23 ቀን 2013 ዓ.ም የሚሰጥ ሲሆን ፈተና ላይ መቀመጥ የሚችሉት 7ኛ ክፍልን ተምረው ያጠናቀቁና የ8ኛ ክፍልን የአንደኛ ሴሚስተር ትምህርት የተከታተሉ ብቻ ናቸው።

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መውሰድ የሚችሉት የ11ኛ ክፍል ትምህርት ያጠናቀቁና የ12ኛ ክፍልን የመጀመሪያ ሴሚስተር ትምህርት የተከታተሉ ብቻ ናቸው ተብሏል።

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሕዳር 28 እስከ ታህሳስ 1 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚሰጥም በምክረ ሀሳቡ ላይ ተጠቅሷል።

የትምህርት አሰጣጥ ሂደቱን በተመለከተ ለመንግስት ትምህርት ቤቶች የሚወጣው መመዘኛ በግል ትምህርት ቤቶችም ተፈጻሚ ይሆናል ተብሏል፡፡

በቀረበው ምክረ ሃሳብ ላይ የሚደረገው ውይይት አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡
ኮቪድ 19ኝን ለመከላከል የተቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎችን በ3 ሳምንታት ውስጥ ያሟሉ ትምህርት ቤቶች ትምህርት እንዲጀምሩ ተወሰነ፡፡
------------------------------------------------------------

የዓለም የጤና ድርጅትና የጤና ሚኒስቴር ወረርሽኙን ለመከላከል ባስቀመጡት ቅድመ ሁኔታ መሰረት ትምህርት ቤቶች ከመከፈታቸው በፊት በመድሃኒት ማፅዳት፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብልና የእጅ ማፅጃ ማሟላት እንዲሁም አካላዊ ርቀትን ማስተግበር ይጠበቅባቸዋል፡፡

ለሌላ አገልግሎት ውልው የነበሩ ትምህርት ቤቶችም አስፈላጊውን የማስተካከያ ስራ ሊሰራላቸው እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡

እንደየ ትምህርት ቤቶቹ ነባራዊ ሁኔታ ትምህርት በፈረቃ እና አንድ ቀን በመዝለል ተራ ሊያስተምሩም ይችላሉ፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር ባስቀመጠው መስፈርት መሰረት በአንድ ክፍል ውስጥ ከ20 እስከ 25 ተማሪ ማስተማር የሚችሉ መሆንም ይጠበቅባቸዋል ተብሏል፡፡

የተቀመጠው መስፈርት እንዳለ ሆኖ፡-

በገጠር ወረዳና ቀበሌ ከተሞች የሚገኙ ትምህርት ቤቶች በመጀመሪያው ዙር ጥቅምት 9 ቀን 2013 ዓ.ም፤

በሁሉም የዞንና የክልል ከተሞች የሚገኙ ትምህርት ቤቶች በ2ኛ ዙር ጥቅምት 16 ቀን 2013 ዓ.ም፤

በአዲስ አበባና አዲስ አበባ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ደግሞ በ3ኛ ዙር ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ትምህርት እንዲጀምሩ የውሳኔ ምክረ ሀሳብ መቅረቡ ይታዋሳል፡፡

በዚህ መሰረት ኮቪድ 19ኝን ለመከላከል በ3 ሳምንታት ውስጥ አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ ያሟሉ ትምህርት ቤቶች በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ትምህርት መጀመር ይችላሉ ተብሏል፡፡
የትምህርት ቤቶችን ዝግጁነትን የሚያጣራ ኮሚቴ ወደ ስራ ገብቷል።
------------------------------------------------

የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ ( ዶ/ር ኢንጂ.) ትምህርት ለማስጀመር የ ቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገለፀዋል።

የትምህርት ቤቶችን ዝግጁነት ለ ማረጋገጥ ከተለያዩ ዘርፎች የተወጣጣ ኮሚቴ መዋቀሩን እና ኮሚቴውም ስራዎችን በባለቤትነት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

ኮሚቴውም ከጤና ፣ ከትምህርት ፣ ከአስተዳደር ዘርፍ እንዲሁም ከወላጆች የተወጣጡ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን በተለይ ወላጆች በአብላጫው የሚሳተፉበት ነው፡፡

የተዋቀረው ኮሚቴ በሚቀጥሉት 3 ሳምንታት ውስጥ ትምህርት ቤቶች ያሉበትን ሁኔታ የሚገመግም፣ ከትምህርት ሚኒስቴር የሚላኩ ቁሳቁሶች መድረሳቸውን የሚያጣራ ፣ ሌሎች ድጋፎችን የሚያስተባብር ፣ በትምህርት ቤቶች አስፈላጊው ግብዕቶች መኖራቸውን የሚመለከት እንዲሁም ትምህርት ቤቱ በአጠቃላይ ትምህርት ማስኬድ የሚችልበት ሁኔታ ላይ ስለመሆኑ ይገመግማል፡፡

የተዋቀረው ኮሚቴ የትምህርት ቤቶችን ነባራዊ ሁኔታ ገምግሞ ውሳኔ ሲያስልፍ ትምህርት ቤቶች የሚከፈቱ ሲሆን ትምህርት ቤቶችን የመክፈት ሁኔታም የሚወሰነው የትምህርት ቤቶች ተማሪዎቹን ለመቀበል የሚያስችል ዝግጁነቱ ሲኖር መሆኑን ተነግሯል፡፡

በግል ትምህርት ቤቶችም የወላጅ ኮሚቴዎች የትምህርት ቤቱ ዝግጁነቱን ካላረጋገጡ እና ካላመኑበት ትምህርት ቤቱ ትምህርት መጀመር እንደማይችል ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡
ትምህርት ሲጀመር ማስክ ያላደረገ ማንኛውም ተማሪ ወደ ትምህርት ቤት እንደማይገባ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

በለይቶ ማቆያነት ሲያገለግሉ የነበሩ ትምህርት ቤቶች የኬሚካል ርጭት ሳይደረግላቸው ትምህርት እንደማይጀምሩ ተገልጿል

የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ የተቋማቸውን የ3 ወራት የስራ አፈጻፀም የተመለከተ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በዚህም የኮቪድ 19 ወረሽኝን በመከላከል የመማር ማስተማር ስራውን ለማስጀመር የተለያዩ ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑን አብራርተዋል።

መንግስት ለተማሪዎች የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል የማቅረብ ስራ እየሰራ መሆኑንና ትምህርት ሲጀመር ማስክ ያላደረገ ማንኛውም ተማሪ ወደ ትምህርት ቤት እንደማይገባ ተናግረዋል።

የኮሮና ቫይረስ መከሰቱን ተከትሎ ለኮሮና ቫይረስ ህሙማን ማቆያ ጥቅም ላይ ሲውሉ የነበሩ ትምህርት ቤቶች የኬሚካል ርጭት ሳይደረግላቸው ትምህርት እንደማይጀምሩ ሚኒስትሩ አመልክተዋል፡፡

የኬሚካል ርጭቱን ለማካሄድ አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን እና በቀጣይ ሳምንታት እንደሚጀመርም ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ ገልጸዋል፡፡

ይህንን አስቸጋሪ ወቅት በድል ለመወጣት መምህራንና ወላጆች ርብርብ እንዲያደርጉም ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የ12ኛ ክፍል ፈተናን በኦላይን ለመፈተን የሚያደርገውን ዝግጅት እያጠናቀቀ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ፡፡
--------------------------------------------------
ትምህርት ሚኒስቴር የ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ፈተና በኦላይን ለመፈተን የሚያስችለውን አስፈልጊ ዝግጅት ማድረጉን አስታውቋል፡፡

ለባለሙያዎች ስልጠናዎችን መስጠት የተጀመረ ሲሆን በትምህርት ቤቶችም ፈተናውን ለመስጠት የሚያስችል በቂ የመብራት እና የኔትዎርክ አቅርቦት እንዲኖር እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በኦላይን የሚሠጠው ፈተናም ኩረጃን ሙሉ በሙሉ የሚያስቀር ከመሆኑም ባሻገር ለወረቀትና ፈተናውን ለማረም የሚወጣውን ወጪና ጊዜ ይቆጥባል ነው የተባለው፡፡

ቴክኖሎጂው የተለያዩ ሲስተሞች የተጫኑበት ሲሆን ተማሪዎች ፈተናውን በሚወስዱበት ጊዜ የራሳቸው ታብሌት ላይ ብቻ ትኩረት እንዲያደርጉ የሚያስችል ሲስተም አለው ተብሏል።

ፈተናው የሚሰጥባቸው ታብሌቶችም በቅርቡ ለተማሪዎች እንደሚሰራጩ ተገልጿል።

ተማሪዎችም ከቴክኖሎጂው ጋር እንዲተዋወቁ ከሦስት ሣማንት ያላነሰ ጊዜ የሚሰጣቸው ሲሆን ምንም ሳይጨናነቁ ለፈተና እንዲዘጋጁ ሚኒስቴሩ ጥሪ አቅርቧል።
የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ለሁሉም ትምህርት ቤቶች በነፃ ይሰጣል- ትምህርት ሚኒስቴር
----------------------------------------
የትምህርት ሚኒስቴር መደበኛ ትምህርት ለመጀመር አስፈላጊ ዝግጅቶችን እያጠናቀቀ እና በትምህርት ቤቶች አስፈላጊ ግብዕቶች ለማሟላት ስራዎችን እየሰራ መሆኑን አስታወቋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ወ/ሮ ሃረጓ ማሞ ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት ከመጀመሩ በፊት ለሁሉም የመንግስት እና የግል ትምህርት ቤቶች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ በነፃ እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡

የአፍና አፍንጫ መሸፈኛውም አዲስ አበባ እና ሀዋሳን ማዕከል በማድረግ ለክልል እና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ እንደሚከፋፈሉ ዳይሬክተሯ አስታወቀዋል፡፡

የአለም የጤና ድርጅት መስፈርቶችን የሚያሟሉ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛዎችም ሀገር ውስጥ ካሉ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ግዢ የመፈፀም ስራ እየተከናወነ እና በቅርቡ ወደ ትምህርት ቤቶች እንደሚደርሱ ተገልጿል፡፡

ለተማሪዎች የሚከፋፈለው የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ በተደጋጋሚ ታጥቦ ዳግም አግልግሎት መስጠት የሚችል እንደሆነም ተነግሯል፡፡
መልዕክት
ትምህርት ቤት እስከሚከፈት ድርስ ተማሪዎችን ለማትጋት አጫጭር ኖትና መልመጃ ስለምንልክ ወላጆች ይህንኑ በመረዳት ልጆችን እንድትረዷቸው እናሳስባለን፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ለ2013 የትምህርት ዘመን የተዘጋጀ የክፍለ ጊዜ ድልድል፡፡

Share via
https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAEgabybI4yOcFps7Mw
2024/09/29 00:32:23
Back to Top
HTML Embed Code: