Telegram Web Link
ከት/ቤቱ የተሰጠ ማሳሰቢያ
@kawgms_portal
የ 8ኛና የ12ኛ ክፍል ሞዴል ፈተናዎች ተጠናቀዋል፡፡
@wwwAddisAbabaeducationburau
@wwwAddisAbabaeducationburau
@kawgms_portal
የሚኒስትሪ ፈተና አሰጣጥን በሚመለከት ውሳኔ ላይ አልተደረሰም!

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ዳኜ ገብሩ ለአዲስ ማለዳ እንዳስታወቁት፣ በዘንድሮው የትምህርት ዘመን የስምንተኛ ክፍልን ክልላዊ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች 12 ሺሕ ቢሆኑም ፈተና አሰጣጡ እንዴት እና መቼ ይሰጥ የሚለው ጉዳይ ላይ ግን ውሳኔ ላይ መድረስ አልተቻለም። እንደ ዳኜ ገለጻ ከሆነ፣ የ12ኛ ክፍልም ይሁን የስምንተኛ ክፍል ፈተና እንዴት እና በምን መንገድ ይሁን የሚለውን ከፌዴራል ባለድርሻ አካላት ጋር በሚደረግ ንግግር የሚወሰን ይሆናል። እስከ አሁን ግን ምንም የተገለጸ ነገር የለም ሲሉ ምክትል ቢሮ ኃላፊው ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

Via Addis Maleda

@kawgms_portal
KAWGMS pinned «Click your grade below»
🎲 ኢትዮቴሌኮም ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች እና መምህራን ትምህርታዊ መረጃዎችን ከ http://ndl.ethernet.edu.et/ በነፃ ማግኘት እንዲችሉ አደረገ።
@Ethiostudente
በዚሁ መሰረት ከዛሬ ጀምሮ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያዘጋጀውን የዲጂታል ላይበራሪ ተማሪዎችና መምህራን ገብተው ሲጎበኙ ከከፍያ ነፃ ወይም ዜሮ ሬቲንግ መደረጉ ተገልጿል፡፡
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ኢትዮ ቴሌኮም ላደረገው ከፍተኛ ድጋፍ እያመሰገነ የከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ማህበረሰቡ በ http://ndl.ethernet.edu.et/ ገብታችሁ የነፃ አገልግሎቱን እንድታገኙ እየጋበዘ ተማሪዎችና መምህራን የኦንላይን በመማር ማስተማሩን ሂደቱ በዚሁ አግባቡ እንድትቀጥሉ ያሳስባል፡፡
@Ethiostudente
ቤተመፃህፍቱ ከ80 ሺህ በላይ ማጣቀሻ መፃፍህት፣ የመጀመሪያ ዓመት የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ሞጁሎች፣ በምስል የተደገፉ አጋዥ ማብራሪያዎች እንዲሁም የሁሉም የትምህርት አይነቶች ኮርስ ማቴሪያሎችን ይዟል፡፡


@kawgms_portal
ለቀኝ አ/አንዳርጌ ወ/ጊዮርጊስ መታሰቢያ ት/ቤ
8 ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ


በአዲስ አበባ ት/ቢሮ ተዘጋጅቶ የነበረውን ፈተና መፈተናችሁ ይታወሳል። ስለሆነም መልሶቹ ስለተላኩ በየክፍላችሁ በመግባት መልሶቹን በማየት እራሳችሁን በመመዘን የበለጠ ጠንክራችሁ እንድታጠኑ እና የተሻለ ውጤት እንድታመጡ ት/ቤቱ ያበረታታል።

በቤታችሁ ቆዪ
እራሳችሁን ጠብቁ
ለቀኝ አ/አንዳርጌ ወ/ጊዮርጊስ መታሰቢያ ት/ቤ
8 ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ


ከመጪው ሐሙስ ሰኔ 11 2020 ጀምሮ የትምርትቤቱ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች የሞዴል ፈተና በጉለሌ ክ/ከተማ ት/ቢሮ በቴሌግራም ሰለተዘጋጀ ከወዲሁ በማጥናት እራሳችሁን እንድታዘጋጁ ት/ቤቱ ያሳስባል።

የፈተና ቀን

8ኛ ክፍል ፠ ሐሙስ እና አርብ
12ኛ ክፍል ፠ ሐሙስ፣ አርብ እና ቅዳሜ



በቤታችሁ ቆዪ
እራሳችሁን ጠብቁ
KAWGMS pinned «ለቀኝ አ/አንዳርጌ ወ/ጊዮርጊስ መታሰቢያ ት/ቤ 8 ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ ከመጪው ሐሙስ ሰኔ 11 2020 ጀምሮ የትምርትቤቱ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች የሞዴል ፈተና በጉለሌ ክ/ከተማ ት/ቢሮ በቴሌግራም ሰለተዘጋጀ ከወዲሁ በማጥናት እራሳችሁን እንድታዘጋጁ ት/ቤቱ ያሳስባል። የፈተና ቀን 8ኛ ክፍል ፠ ሐሙስ እና አርብ 12ኛ ክፍል ፠ ሐሙስ፣ አርብ እና ቅዳሜ በቤታችሁ…»
ቀን 11/10/2012 ዓ/ም
በጉለሌ ክ/ከተማ የተዘጋጀ የ 12ኛ እና 8ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና በየክፍላችሁ የቀረበ ሲሆን ተማሪዎች እራሳችሁን እንድትፈትሹበትና ወላጆችም ተገቢዉን እገዛ እንድታደርጉላቸዉ እና በአግባቡ ፈተናዉን መውሰዳቸዉን እንድታረጋግጡ እንጠይቃለን፡፡

ት/ቤቱ
መልካም ፈተና!!https://www.tg-me.com/guleleeducationoffice
@kawgms_portal
ለ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች
ነገ ማክሰኞ ሰኔ 16/ 2012 ዓ.ም የትምህርት ቤቱ የሞዴል ፈተና በትምህርት ቤቱ የቴሌግራም ቻናል በኩል የሚደርሳችው መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡
ለ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች
ሰኔ 16/ 2012 ዓ.ም የትምህርት ቤቱ የሞዴል ፈተና በትምህርት ቤቱ የቴሌግራም ቻናል በኩል እነደተላከላችሁ የሚታወስ ነው ።ስለሆነም ት/ቤቱ ለምዘና እና ለምደባ ስለሚጠቀምበት የጥያቄውን መልስ በ24/10/2012 ዓ. ም ዕረቡ ክፍያ ካጠናቀቃችሁበት ደረሰኝ ኮፒ ጋር በማያያዝ ለትምህርት ሴክተር ሀላፊዊች በአካል ቀርባችሁ እንድታስረከቡ ት/ቤቱ ያሳስባል፡፡
ማሳሰቢያ
የ2012 ውጤት ወላጆች ብቻ በተገኙበት የሚሰጠው ከ21 /11/2012 - 24/11/2012 ድረስ ባሉት ቀናት ከ 3 ሰዓት እስከ 6 ሰዓት ብቻ ትምህርት ቤቱ ያስተናግዳል፡፡ (ቀናቱ ሽግሽግ የተደረገበት ምክንያት የኮቪድ19 ሁኔታን በማገናዘብ ነው)
የቀጣይ አመት የትምህርት ምዝገባ ከነሃሴ 20 ጀምሮ እንደሚጀመር ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ
--------------------------------------------------
ሚኒስቴሩ ትምህርት ቤቶች የቀጣይ አመት የትምህርት ምዝገባን ከነሃሴ 20 ጀምረው ማካሄድ ይችላሉ ብሏል።

የትምህርት ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ወ/ሮ ሃረጓ ማሞ ትምህርት ቤቶች ምዝገባውን ሲያካሂዱ የኮቪድ 19 ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በዓለም የጤና ድርጅትና በጤና ሚኒስቴር የተቀመጡ መከላከያዎችን በሚገባ በመተግበር መሆን እንዳለበት አሳስቧል።

ትምህርት የሚጀመርበት ቀን በቀጣይ እንደሚወሰንና ይፋ እንደሚደረግም የገለፁት ዳይሬክተሯ የቀጣዩ አመት የትምህርት ሂደት ስኬታማ እንዲሆንም ተማሪዎች ፥ መምህራን ፥ ወላጆችና መላው የትምህርት ማህበረሰብ ይህን አስቸጋሪ ወቅት ለማለፍ የሚተላለፉትን ገዢና አስፈላጊ መልእክቶች ብቻ በመከታተልና ቫይረሱ ሊተላለፍ የሚችልባቸውን መንገዶች ከውዲሁ በማስወገድ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚያስፈልግም አሳስበዋል።

አካላዊ ርቀትን ጠብቆ ለማስተማር፣ የንፅህና መጠበቂያዎችን ከማዘጋጀትና መሰል የኮሮና መከላከል ተግባራትን ተግባራዊ ለማድረግ በሚያስችል መልኩ ቀድመው ዝግጅት የሚደረግባቸው ተግባራትም እንደሆኑ አክለው ገልጸዋል።

በምን አይነት መልኩ ትምህርት መጀመር እንዳለበት የተለያዩ አማራጮችን ለማመላከት ሰፊ ውይይት እየተደረገባቸው ሲሆን ውሳኔ ሲያገኝ ይፋ ይደረጋል።

የ8ኛና የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ጊዜን በተመለከተ ሚኒስቴሩ በቅርብ የሚያሳውቅ ሲሆን ተማሪዎች ራሳቸውን እያዘጋጁ እንዲቆዩ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።
2024/09/29 02:21:10
Back to Top
HTML Embed Code: