Forwarded from አሥራት ሚዲያ Asrat Media ®🇪🇹
በቶኪዮ ኦሎምፒክ የ5 ሺህ ሜትር የሴቶች ማጣሪያ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለፍጻሜ አለፉ
----------------------
በቶኪዮ ኦሎምፒክ የአምስት ሺህ ሜትር የሴቶች ማጣሪያ ውድድር ከመጀመሪያ ምድብ ሰንበሬ ተፈሪ 3ኛ፣ እጅጋየሁ ታዬ ደግሞ 4ኛ ሆነው ማጣሪያውን አልፈው ለፍጻሜ ደርሰዋል፡፡
ከሁለተኛው ምድብ ደግሞ አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ 1ኛ ደረጃ በመያዝ ማጣሪያውን አልፋለች፡፡
_______________________
ሐምሌ 23 ቀን 2013 ዓ.ም
@Asrat_News

2021/22 AY AAU Disability and Female Scholarship
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ከመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በቀን /መደበኛ/ ፕሮግራም ከ2006 እስከ 2013 ዓ.ም ተምረዉ ለተመረቁ አካል ጉዳተኛና ሴት ተማሪዎች የነፃ ትምህርት ዕድል (Scholarship) አዘጋጅቷል፡፡
ዝርዝር መስፈርቶች
ከመንግስት ዩኒቨርስቲ በቀን /መደበኛ /ፕሮግራም የተመረቀ/ች
የመጨረሻ የትምህርት ዉጤት (CGPA) 2.75 እና በላይ ያላቸዉ
ያለባቸዉን የወጪ መጋራት ክፍያ ከፍለዉ የጨረሱ እና ኦፊሻል ትራንስክሪፕት ከተማሩበት ዩኒቨርስቲ ማስላክ የሚችሉ
ለአካል ጉዳተኞች ከሚኖሩበት ወረዳ የተመሰከረ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
ትምህርት ክፍሉ የሚያወጣዉን የመግቢያ መስፈርት የሚያሟሉ መሆን ሲኖርባቸው
የአአዩ የድኅረ ምረቃ መግቢያ ፈተናን በተመለከተ
ለድኅረ ምረቃ ትምህርት ለማመልከት የዩኒቨርስቲዉን የድኅረ ምረቃ የመግቢያ ፈተና ቀድሞ መዉሰድ እና ፈተናዉን ማለፍ ግዴታ ነው፡፡
የፈተናዉን ግዜ እና ሌሎች መረጃዎችን በተመለከተ ከዩኒቨርስቲዉ ድረ-ገፅ ና ከትምህርት ጥናትና ምርምር ተቋም የፈተና ማእከል ማግኘት ይቻላል፡፡
የመፈተኛ ክፍያ ብር 600 በዩኒቨርስቲዉ አካዉንት 1000087392067 ገቢ ማድረግ እና ገቢ ያደረገው የተፈታኝ ስም ያለበት የባንክ ደረሰኝ ለፈተና ማዕከሉ በማስረከብ ለፈተና መመዝገብ ያስፈልጋል፡፡
የመግቢያ ፈተናው በኮምፒዩተር የሚሰጥ ሲሆን ፈተናውን በሚመለከት በ አአዩ ድረ-ገፅ አጠቃላይ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የማመልከቻና መፈተኛ ቀናት፤ ከ ሃምሌ 12 እስከ ነሃሴ 12 ቀን 2013 ዓ.ም ነው፡፡ ቀድሞ ለተመዘገቡ ቅድምያ ፈተና ይሰጣል፡፡
ከዚህ በፊት የዩኒቨርስቲዉን የድኅረ ምረቃ የመግቢያ ፈተና አልፋችሁና ባመለከታችሁበት ፕሮግራም የተማሪ የመታወቂያ ቁጥር የተሰጣችሁ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲዉን የድኅረ ምረቃ የመግቢያ ፈተና እንደገና መውሰድ ግዴታ ነው፡፡
የአአዩ የድኅረ ምረቃ ማመልከቻን በተመለከተ
የማመልከቻ ፎርሙን በዩኒቨርስቲው ድረገጽ (https://portal.aau.edu.et) መሙላት
ከማመልከቻው ፎርም የሚያገኙትን የማመልከቻ ቁጥር (Application Number) በመያዝ ብር 200 /ሁለት መቶ/ ለመመዝገቢያ ብር በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ CBE ብር ወይም በወኪሎች ወይም በቅርንጫፍ አማካኝነት በ242424 አጭር ኮድ በክፍያ መፈጸም ያስፈልጋል፡፡
ክፍያዎትን ካጠናቀቁ በኋላ ወደ ማመልከቻ ፎርሙ በመመለስ ፒዲኤፍ (PDF) ፎርማት የተለወጠ የትምህርት ማስረጃዎትን፣ የወጪ መጋራት ሰነድዎትን$፣ እንዲሁም ለቀን መርሃ ግብር የትምህርት ወጪዎን /Sponsorship/ የሚሸፍንልዎት የመንግስት መስሪያ ቤት ከሆነ የተፈረመበትና ማህተም የተደረገበት ፎርም አስገብተው እና ሌሎች መረጃዎችን በማከል የኦንላይን ምዝገባዎትን ማጠናቀቅ ይኖርብዎታል፡፡
የስፖንሰርሺፕ ፎርም ከዩኒቨርስቲው ድረ ገጽ (https://portal.aau.edu.et/ http://aau.edu.et) ማግኘት ይችላሉ፡፡
ለPhD አመልካቾች የBA/BSc ዲግሪ/ጊዜያዊ ዲግሪ እና CGPA ያለው ትራንስክሪፕት እና የMA/MSC ዲግሪና ትራንስክሪፕት ማያያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡
በተጨማሪም ለPhD አመልካቾች ትምህርት ክፍሉ የሚጠይቀውን ማያያዝ ይኖርብዎታል፡፡
ለMA/MSC አመልካቾች የBA/BSc ዲግሪ/ጊዜያዊ ዲግሪ እና CGPA ያለው ትራንስክሪፕት ማያያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡
ምዝገባዎን ለማጠናቀቅ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሬጅስትራር ቢሮ ቁጥር 203 የትምህርት እና ሌሎች ማስረጃዎችን በአካል ይዞ በመቅረብ ማስገባት ግዴታ ነው፡፡
ማሳሰቢያ
ኦፊሻል ትራንስክሪፕት ለአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሬጅስትራር ቢሮ ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1176 ያላስላከ አመልካች ቀጣይ የምዝገባ ሂደቶች እንደማይከናወኑለት እናሳስባለን፡፡
የፈተና ግዜንና የትምህርት ፕሮግራም ዝርዝሮችን በተመለከተ ከትምህርት ክፍሉ ማስታወቂያ ሰሌዳ እንዲሁም ከዩኒቨርስቲው ድረ ገፅ (https://portal.aau.edu.et /http://aau.edu.et) ማግኘት እንደምትችሉ ያሳውቃል፡፡
ጤና ላይ ለሚያመለክቱት አመልካቾች ዲግሪያቸዉን ሲጨርሱ ከጤና ጥበቃ ወይም ከተማሩበት ዩኒቨርስቲ የሚሰጣቸዉን ደብዳቤ ወይም በየሴምስተሩ የሚሰጣቸዉን Grade report ማያያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡
የተማሪዎች ቁጥር ከመቀበል አቅም በታች (ዝቅተኛ) ከሆነ የትምህርት ፕሮግራሞች የማይከፈቱ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የመመዝገቢያ ቀን ሐምሌ 26 እስከ ነሐሴ 14 2013 ዓ.ም
የማመልከቻ ቦታ አአዩ ሬጅስትራር ቢሮ ቁጥር 203
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሬጅስትራር