እናስተነትን ዘንድ

ክፍል ሁለት

እነሆ ትላንት እንቅልፍ እንዳልተኛ በ ጩኸታቸው እና በንክሻቸው አላስተኛ ያሉኝ ትንኞች ነበሩ። እስኪ ስለ ቢምቢዎች ልንገራችሁ።

ቢምቢ ከ 3000 በላይ ዝርያወች ያሏት ትንኝ ናት። ከነዚህ ውስጥ ትንሾቹ ብቻ ናቸው ከ ሰው ልጅ ደም እሚመጡት። ግን ለምንድን ነው እሚመጡት?!

ደም መጣጭ የሆኑት ቢንቢወች ሴቶች ብቻ ናቸው። ወንድ ቢምቢዎች ምግባቸውን ከአበባ ብቻ ነው እሚፈልጉት። ታድያ ሴቷ ደም ምን ይሰራላታል?!ካላችሁኝ ለ እንቁላሏ እድገት ስትል ነው።

ምን አለ መሰላችሁ የ ሰው ልጅ ደም በ ፕሮቲን እና አሚኖ አሲድ የበለፀገ ስለሆነ ለእንቁላሎቻቸው እድገት ያስፈልጋቸዋል። ለዚያም ሲሉ ሴት ቢምቢወች ደም ይመጣሉ። በነገራችን ካይ ቢምቢወች ከ 1.6 - 2.3 ኪሎ ሜትር በሰአት መብረር ይችላሉ።

ታድያ ከነዚህ ውስጥ anopheles የተባሉት የቢምቢ ዝርያወች ናቸው ወባን እሚያስተላልፉት። ግን ቢምቢወች ሲነክሱን ቆዳችን ላይ እብጠት ይከሰታል ለምንድን ነው?!

መልሱ ቢምቢወች ከሰው ልጅ ደም ለመምጠጥ ቆዳችን እንደበሱ ምራቅ ነገራቸውን ወደ ውስጥ ይለቁታል! በዚህ ጊዜ የሰው ልጅ ሰውነት ወደ ውስጥ ለገባው ምራቅ ነገር ምላሽ ይሰጣል በዚህ ጊዜ እብጠት ነገር ይከሰታል።ቢምቢወች ድምፅ እሚፈጥሩት በ ክንፋቸው ውልብልብታ ነው።

እነዚህ ቢምቢወች መብራት ጠፍቶ እንኳን ሊያገኙህ ይችላሉ። ምክኒያቱ ደግሞ ቢምቢዎች ለ ካርቦን ዳይ ኦክሳይድ (CO2)፣ ለሙቀትና ለጥቁር ቀለም ልብሶች የተሳቡ መሆናቸው ነው።

እንደ healthline ገለፃ ከሆነ ቢምቢወች O blood group (የደም አይነት) ያላቸውን ሰወች ነው በደምብ እሚመገቡት። ደማችሁን እየመጠጡ ዝም ብላችሁ ብትከታተሏቸው እስከ አራት ደቂቃ ሊቆዩ ይችላሉ።

እንደ national institute of health ገለፃ ከሆነ የቢምቢ ትንኞች ከመጠን በላይ ጨውና ፈሳሽ ነገሮችን እሚያስወግድ #ኩላሊቶች አላቸው። ይህንን ቆሻሻም በሽንት መልክ ያስወግዱታል።

ወንዱ ቢምቢ ከ ሴቷ ጋር ግንኙነት ካደረጉ በኋላ በሂወት የመኖር እድል የለውም። ሴቷ ግን ብዙ ጊዜ ልታደርግ ትችላለች በሁሉም የግንኙነት ጊዜ የዘር ፈሳሹን ታጠራቅምና አንዴ ትጠቀምበታለች። ወንዶች ለጉልምስና ጊዜ በኋላ በዛ ቢባል አንድ ወይም ሁለት ሳምንት ይኖራል ሴቷ ግን እስከ መቶ ቀን መኖር ትችላለች።

ለዛሬ ይህን ይመስላል ሌላ ጊዜ በሌላ ነገር እንገናኛለን

@ibnuhasen
እናስተነትን ዘንድ

ክፍል ሶስት

እነሆ አላህ በስሟ ቁርአንን ምእራፍ የተሰየመላትን ሌላኘዋን በራሪ ነፍሳት የሆነችውን ንብን በዛሬው 'እናስተነን ዘንድ' ፕሮግራማችን ልናነሳ ወደድን።

ብዙወቻችን ስለ ንቦች እናውቃለን። ማራቸውን ማን ያልበላ አለ☺️

ንቦች ብዙ አይነት ዝርያ ያላቸው ናቸው። ከነዛ ውስጥ ግን የማር ንቦች ዝርያ ሰባት ወይም ከዛ በላይ ናቸው። እንዲህ ያልኳችሁ 'ጢንዚዛ' በመባል እሚታወቁትም የንብ ዝርያ ናቸው ተብሎ ስለሚታመን ነው።

ንቦች ሶስት አይነት መደብ አላቸው። ሰራተኛ፣ ንግስቷ እና ድሮን ተብለው እሚታወቁት ናቸው።
እስኪ አሪፍ ጥያቄወችን እናንሳ

ንቦች ለምንድን ነው ማር እሚያመርቱት?!
እኔ ልንገራችሁ ንቦች የክረምት ጊዜ ወይም አበቦች እማይገኙበት ጊዜ ሲመጣ እሚመገቡት እንዳያጡ ነው እሚያከማቹት። ማር ለንቦች ምርጥ የምግብ ምንጭ ይሆንላቸዋል። ማር በ nutreient የበለፀገ ከመሆኑ በተጨማሪ ብዙ ስኳር ስለሚኖረው ሀይል ሰጭ ምግብ ሁኖ እንዲያገለግላቸው ነው።

ሰራተኛ ንቦች በጠቅላላ ሴቶች ናቸው። ደሮን ተብለው እሚታወቁት ደግሞ ወንድ ናቸው። ስራቸው ንግስቲቱን መገናኘት ብቻ ነው። ግን ንግስቲቱም ከሀዲ ናትና ከግንኙነት በኋላ ልትገድላቸው ትችላለች።
እነዚህ ወንድ ንቦች አይናደፉም። ሰራተኛ ንቦች ደግሞ ሴት ቢሆንም መራባት አይችሉም። መራባት እምትችለው ንግስቲቱ ብቻ ናት። ንግስቲቱ ለቀናት ማየት የተሳናት ሁና ልታሳልፍ ትችላለች።ሰራተኛ ንቦች ከተናደፉ በኋላ ይሞታሉ።

አሁንም እንጠይቅዎ ንቦች ከተናደፉ በኋላ ለምን ትሞታሉ?!

መልሱ ቀላል ነው እሚናደፉበት ሰንኮፋቸው በመቀመጫቸው አካባቢ ነው ያለ። በሚናደፉበት ጊዜ ሰንኮፉ ሆዳቸው ውስጥ ያለውንም ነገር ይዞባቸው ይወጣል። ያ ማለት እሚናደፉበት ሰንኮፍ ሆዳቸው ውስጥ ያለውን ለማዋሀድ እሚጠቅማቸው እና ሆዳቸው ውስጥ ያለውን ነገር አብሮ ስለሚያወጣው መትረፍ አይችሉም።


ንቦች እሚያዘጋጁት ማር ብዙ የጤና ጥቅሞች አሉ። ከነዛ ውስጥ health line ያስቀመጣቸውን እንንገራችሁ አንቲኦክሲዳንት፣ባክተሪያን እና ፈንገስን ለማጥፋት፣ ቁስልን ለማከም፣ በሽታን የመከላከል አቅም ማሳደግ፣ ለአንጀት ጤንነት እና ለውህደት ፣ እንዲሁም የተዘጋ ጉሮሮን ለመጥረግ ይጠቅማል።

ግን በቅርብ ደግሞ የ አውስትራሊያ ዶክተሮች ከንብ መርዝ አዲስ ግኝት አግኝተናል ይላሉ።

BBC እንደዘገበው ከሆነ ተመራማሪወች ከንብ ሰንኮፍ የጡት ካንሰር ሴሎችን እንደሚገድል አስታውቀዋል። ምን ይሄ ብቻ ሜላኖዋ ተብሎ እሚታወቀውን ካንሰርም እንደሚከላከል አስታውቀዋል።

ሰራተኛ ንቦች በሚናደፉብት ጊዜ ሰውነታችን ላይ ያብጣል። ግን ሊገለን ይችል ይሆን?!
አንድ የንብ መርዝ ሊገለን አይችልም ግን እስከ አንድ ሽህ የሚደርሱ ንቦች ከተነደፍን ግን መሞታችን አይቀሬ ነው።

@ibnuhasen

www.tg-me.com/ibnuhasen
የሆነ ትልቅ ሰው ገብያ ላይ ተገናኝተን ማውራት ጀመርን።
ሰውየው ጋር ትንሽ ካወራን በኋላ እንዲህ አለ ፡- "እኔ ወደ ሻሸመኔ የሄድኩት በ 67 (1967) ነው። የዛኔ ወታደር ነበርኩ። ለግዳጅ በዛው እንደሄድኩ ኑሮየን መሰረትኩ። ልጆች ወልጃለሁ አካባቢው ላይ ሰላም ነበርን ግን ድንገት ነገሩ ሁላ ተቀያየረ አፈራውት ያልኩት ሀብት እና ንብረቴ ወደመብኝ። ለብዙ ግዜ በእርዳታ መኖር ቻልኩ ግን መዝለቅ አልቻልኩም። አሁን ይሄው እንደምታየኝ እዚህ መጥቼ እንደ አዲስ ኑሮ መስርቼ መኖር ጀምሪያለሁ። ግን ከብዶኛል። አእምሮየ ረፍት አጥቷል። በቃ ጭንቃላቴ ላይ የተቀረፀው ረብሻ እና ማፈናቀሉ። " ሰውየው መቀጠል አቃተው።


እኔም "እኔም ጂማ ነበርኩ ። የጅማ ሰው ጥሩወች ናቸው። አንዴ በብሄር ምክንያት ግቢውን ለቅቈ እንድወጣ ተደርጌ ነበር። እና እሚሰማህ ያለውን ነገር በትንሹም ቢሆን ይገባኛል የሆነው ነገር ያሳዝናል አይዞን ጋሼ!" ብየ ሸኘኋቸው።
ሙሉ ኢትዮጵያ በዘረኝነት የተበከለች ያህል ይሰማኛል። "የተፋዋ ምድር" እየተባለች ስሰማ ያደግኩት ነገር ሁሉ ውሸት እንደሆነ አወቅኩ። አንዳንዴማ "ኢትዮጵያ የተስፋዋ ሳይሆን የክፋት ምድር ናት" እያልኩ አስባለሁ።

@ibnuhasen
🚨ማሳሰቢያ🚨

ይህ ቻነል ከዛሬ ቀን ጀምሮ አገልግሎት መስጠት ያቆማል።

ባለፉት ጊዚያት ለታዳሚወቻችን ይጠቅማሉ ብለን ያሰብናቸውን ነገሮች ስናቀርብ ነበረ። ሆኖም ግን ነገራቶች እዳስብነው ሆኖ መቀጠል ስላልተቻለ ሁላችሁም ይህን የቴሌግራም ቻነል ለቅቃችሁ እንድትወጡ እንጠይቃለን።

ከምስጋና ጋር
@ibnuhasen

ለአስትያየት
@ibnuhasenadvice_bot
ኢብኑ ሀሰን pinned «🚨ማሳሰቢያ🚨 ይህ ቻነል ከዛሬ ቀን ጀምሮ አገልግሎት መስጠት ያቆማል። ባለፉት ጊዚያት ለታዳሚወቻችን ይጠቅማሉ ብለን ያሰብናቸውን ነገሮች ስናቀርብ ነበረ። ሆኖም ግን ነገራቶች እዳስብነው ሆኖ መቀጠል ስላልተቻለ ሁላችሁም ይህን የቴሌግራም ቻነል ለቅቃችሁ እንድትወጡ እንጠይቃለን። ከምስጋና ጋር @ibnuhasen ለአስትያየት @ibnuhasenadvice_bot»
Live stream started
Live stream finished (13 seconds)
አታላይ የኔ ቢጤዎች ወይም ለማኞች እንዴት ነው እሚያጭበረብሩት?!
እንዴትስ ተያዙ?! እሚለውን ለማግኘት ቪድዮውን ይመልከቱ


https://youtu.be/og2vo64kKwY
⭕️🚨በታሪክ አሰቃቂ ሰዎችን የመቅጫ መንገዶች

ሰላም ውድ ቤተሰቦቻችን እንዴት ናችሁ

ዛሬ አለም ላይ ከነበሩ ማሰቃያ መንገዶችን በደምብ እናያለን እርስዎ ቢሆኑ ምን ማድረግ እንዳለብዎት እንነግረዎታለን ይመቻችሁ። ሙሉውን ቪድዮ ተከታተሉ ላይክ ሼር እና ሰብርክራይብ ያድርጉ


https://youtu.be/nFL__kjr3HA
አዲስ አስተማሪ ቻነል ከፍተናል
እባክወን ይቀላቀሉን ይጠቀሙበታል እንጂ አይጎዱም
https://www.youtube.com/channel/UCpkMp2gtQkdm3gkI5LnVN7w?sub_confirmation=1
Sequence 02.mp4
120.7 MB
Tap On My Link Start The Bot Join All Channels And Reffer To Friends And Get Netflix Premium Account Now... https://www.tg-me.com/NetflixArenaXbot?start=user86606
2024/06/29 04:31:07
Back to Top
HTML Embed Code: