Telegram Web Link
➲የሲዋክ (የመፋቂያ) ጥቅሞች ።
ሲዋክ አፍን ያፀዳል ፣ ድድን ያጠነክራል ፣ የዓይንን ፓወር ግልፅ ያደርጋል ፣


➲የጀርባን መጣመም ያስወግዳል ፣ የፀጉርን መሸበት ይከላከላል ፣ የሆድ ዕቃን ያነፃል ፣ ድምፅን ያጠራል ፣ ጨጓራ ምግብን እንዲፈጭ ያግዘዋል

➲ የንግግር መውጫ ቦታዎችን ያገራቸዋል ፣ ለቂራአት፣ ለዚክርና ለሰላት ያነቃል ፣ እንቅልፍን ያባርራል ፣ አላህን ያስወድዳል ፣ ለመላኢካዎች ያስደስታል ፣ መልካም ሥራዎችን ያበዛል ።

📚(الطب النبوي لابن القيم)

መንቁል

💎https://www.tg-me.com/qidmiylewqat
· ➪ጁመዓ!
--------------------

۞የጁምዓ እለት የሳምንቱ ምርጥ ቀን ነው።

𒊹︎︎︎የአላህ መልእክተኛ ﷺ
«አላህ ዘንድ ከቀናቶች ሁሉ በላጩ የጁምዓ እለት ነው።» ብለዋልና በዚህ እለት ስራዎቻችንን ይበልጥ ማሳመር ይገባናል።
#صححه الألباني في
السلسلة الصحيحة - رقم: (1502)
صحيح الجامع -  رقم: (1098)

➪የጁምዓ እለት በጀማዓ (በህብረት) የተሰገደ የፈጅር ሰላት ከየትኛውም ወቅት ሰላት በላጭ ነው።

𑁍የአላህ መልእክተኛ ﷺ
«አላህ ዘንድ በላጩ ሰላት በጁምዓ እለት በጀማዓ የተሰገደ የሱብህ ሰላት ነው።» ብለዋልና ከየትኛውም እለት በበለጠ ቀድሞ ለመገኘት መጣር ይበልጥ ያስመነዳል።
#السلسلة الصحيحة -
الألباني صحيح - رقم: 1566

۞የጁምዓ እለት ከሌሎች ቀናት በበለጠ በነቢዩ ﷺ ላይ ሰለዋት የማውረጃ ቀን ነው።

︎የአላህ መልእክተኛ ﷺ
«በጁምዓ ቀንና በጁምዓ ሌሊት በኔ ላይ ሰለዋትን አብዙ። በኔ ላይ አንዴ ሰለዋትን ላወረደ አላህ በሱ ላይ አስር ያወርዳል።» ብለዋልና ትንሽ ሰርተን ከአስር እጥፍ በላይ ለማግኘት ከወዲሁ እድሉን እንጠቀም።
#صحيح الجامع 
الألباني حسن - رقم: 1209

𒊹︎︎︎የጁምዓ እለት መኖሩም መሞቱም ለሙስሊሙ ፀጋ ነው።
,
𒊹︎︎︎የአላህ መልእክተኛ ﷺ
ማንኛውም ሙስሊም የጁምዓ ቀን ወይም የጁምዓ ሌሊት የሞተ እንደሆን አላህ ከቀብር ፈተና ሳያድነው አይቀርም።» ብለዋል።
 ስለዚህ በመጀመርያ የዚህ እድል ተጠቃሚ ለመሆን

☞︎︎︎አርካኑል ኢስላምን በስርዓቱ የተገበረ ሙስሊም እንሁን።

𒊹︎︎︎በማስከተልም አላህ በራህመቱ ከቀብር ፈተና እንዲጠብቀንና ለዚህ ሰበብም እንዲያበቃን ሁሌም እንለምነው።

#حسنه الألباني في صحيح الترمذي - رقم: (1074) ، تخريج مشكاة المصابيح - رقم: (1316) الألباني :إسناده حسن أو صحيح لغيره

➪የጁምዓ እለት የሳምንቱ ከኃጢኣት መንፂያ ቀን ነው።

𒊹︎︎︎የአላህ መልእክተኛ ﷺ
«ከባባድ ኃጢኣቶች ኖረው ካልጋረዱት በስተቀር አምስቱ ሰላቶች እንዲሁም ከጁምዓ እስከ ጁምዓ በመሃከላቸው ያለውን ኃጢኣት ያብሳሉ።»¹ በሌላ ዘገባም «ከባባድ ኃጢኣቶች ኖረው ካልጋረዱ በስተቀር ከጁምዓ እስከ ጁምዓ በመሃከላቸው ላለው ማበሻ ናቸው።»² ብለዋል።
,
  𒊹︎︎︎ስለዚህ ከከባባድ ወንጀሎች በመራቅ ወይም ተውበት በማድረግ፣ አምስቱን እለታዊ ሰላቶች ጠብቆ በመስገድና የሳምንቱን ልዩ የስብስብ ቀን የጁምዓን ሰላት በመስገድ ተጨማሪ ግድፈቶቻችንን እናፅዳ።

¹صحيح مسلم - رقم: (233)
²الألباني - صحيح الجامع رقم: (3110)

➪ጁምዓ የሳምንቱ ልዩ የመከባበርያ
ቀን ነው።

ሁሉም ሙስሊም ክቡር ነው። ሀብታም ከድሃ ታላቅ ከታናሽ፣ ገዢ ከተገዢ የሚለይበት ቦታ አየደለምና መስጂድ ሲደርስ ያገኘበት ክፍት ቦታ ሊቀመጥ ይገባዋል እንጂ ማንንም አስነስቶ ወይም እንዲነሳ አስደርጎ ሊቀመጥ አይገባውም። 

𒊹︎︎︎የአላህ መልእክተኛ ﷺ
«አንዳችሁ በጁምዓ ቀን ወንድሙ የተቀመጠበት ቦታ ሊቀመጥ ብሎ እንዳያስነሳው። ነገር ግን ሰፋ ሰፋ አድርጉ ይበል።» ብለዋልና ኢማሙ ኹጥባ ያልጀመሩ እንደሆነ ሰዎችን እንዲጠጋጉለትና እንዲሸጋሸጉለት በስርዓት ማግባትም ይችላል።
صحيح مسلم - رقم: (2178)

☞︎︎︎ጁምዓ የሳምንቱ ልዩ የፅዳት ቀን ነው።

𒊹︎︎︎የአላህ መልእክተኛ ﷺ
«አንዳችሁ ወደ ጁምዓ ሲሄድ ይታጠብ።» ማለታቸው ተዘግቧል።
#صحيح البخاري - رقم: (882)


𒊹︎︎︎ጁምዓ የሳምንቱ ልዩ የቁርኣን ቀን ነው።

የአላህ መልእክተኛ ﷺ ቀጣዩን
ብለዋል፣

☞︎︎︎በጁምዓ ቀን ሱረቱል ካህፍን ለቀራ ሰው በሁለቱ ጁምዓዎች መሃል ያለውን ያህል ከብርሃን ያበራለታል።»
#حسنه الألباني في
تخريج مشكاة المصابيح - رقم:(2116)

𒊹︎︎︎በሌላም ዘገባ እኛ በተለምዶ ሐሙስ ማታ በምንለው የጁምዓ አጥቢያ ምሽቱን ሱረቱል ካህፍን ለቀራ ሰው አጅሩ እጅግ በጣም ሰፊ ነው።
,
▪️ለይለቱል ጁምዓ ሱረቱል ካህፍን ላነበበ ሰው በሱ እና በበይተል ዐቲቅ (በካዕባ) መካከል ያለውን ያህል ከብርሃን ያበራለታል።» ብለዋል።
#صححه الألباني في
صحيح الترغيب -رقم: (736)
 
#اللهم صل وسلم على نبينا محمد وعلى آله وأصحابه أجمعين

•⊰✿📖✿⊱•

©«አል ኢኽላስ የሙስሊሞች ጀመዓ»


@ibnuhasen
⤵️⤵️⤵️⤵️💦📌
ኢማሙ አሽሻፊዒይ ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል፡-
“አንድ የነብዩﷺ ሱንና የተገለፀለት ሰው ለማንም ንግግር ሲል ሱንናን መተው እንደማይፈቀድለት ሙስሊሞች በሙሉ በአንድ ድምፅ ተስማምተዋል፡፡
قال الإمام الشافعي رحمه الله :
أجمع الناس على أن
من استبانت له سنة النبي
صلى الله عليه وسلم
ليس له أن يدعها لقول أحد من الناس كائناً من كان .


@ibnuhasen
➧ከሰውነታችን ላይ ማስወገድ የሚፈቀደውና የሚከለከለው ፀጉር የቱ ነው?
➛ሰውነት ላይ የሚወጣ ፀጉርን በተመለከተ ዐሊሞች ለ 3 ይከፍሉታል።

① ይወገዱ ዘንድ ሸሪዐዊ ትእዛዝ የመጣባቸው የፀጉር አይነቶች።:– ለምሳሌ
➧ የብብት ፀጉር፣
➧ የብልት አካባቢ ፀጉር፣
➧ የቀድሞ ቀመስ ፀጉር (ማሳጠር)፣
➧ በሐጅ/ በዑምራ የእራስን ፀጉር መላጨት ወይም ማሳጠር

② መወገዳቸው የተከለከሉ የፀጉር አይነቶች። ለምሳሌ:-
➧ የቅንድብን ፀጉር ማስወገድ (ከከባባድ ወንጀሎች ነው)፣
➧ ፂምን መላጨት (በኢጅማዕ የተወገዘ ነው)

③ ክልከላም ይሁን ትእዛዝ ያልመጣባቸው የፀጉር አይነቶች። ለምሳሌ:-
➧ የክንድ ላይ ፀጉር፣
➧ የእግር / የጭን ላይ ፀጉር፣
➧ የደረት ፀጉር፣
➧ የአፍንጫ ፀጉር፣ ወዘተ
በነዚህ ላይ ዐሊሞች ተወዛግበዋል። ከፊሎቹ ተፈጥሮን ከመቀየር ጋር በማያያዝ ሲከለክሉ፣ ሌሎች ግን ሸሪዐው ዝም ስላለው መሰረቱ ፍቁድነት ነው ብለዋል። ይህም በፍቃድም ይሁን በክለከላ መልክ ሸሪዐው ያልገለፀው ነገር ባለበት የመተውም ይሁን የማስወገድ ምርጫ አለው ማለት ነው። ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:–
★ "ሐላል ማለት አላህ በመፅሐፉ የፈቀደው ነው።
★ ሐራም ማለት አላህ በመፅሐፉ የከለከለው ነው።
★ ከሱ ዝም ያለው የተተወ (ያልተከለከለ) ነው።" [ሶሒሕ አትቲርሚዚ]
ስለዚህ በማስወገድም ይሁን በመተው ቁርኣንና ሐዲሥ ላይ ያልተገለፁት አይነቶች ከሶስተኛ ምድብ ላይ ያርፋሉ ማለት ነው። እናም ባለበት የመተውም ይሁን የማስወገዱ ምርጫ ለባለቤቱ የተተወ ነው።
ይህንን አቋም በርካታ ዐሊሞች መርጠውታል። ለምሳሌ ያክል የሳዑዲ ዑለማዎች ቋሚ የፈትዋ ኮሚቴ (ለጅነተ አድዳኢማህ) "ለሴት የሰውነቷን ፀጉር ማስወገድ ብይኑ ምንድን ነው?" ተብለው ሲጠየቁ እንዲህ ብለው መልሰዋል:–
"ከቅንድብና ከእራስ ፀጉር ውጭ ያለውን ማስወገድ ይፈቀድላታል። እነዚህን ግን ልታስወግዳቸው አይፈቀድላትም። …" [ፈታዋ ለጅነት አድዳኢማህ: 5/194]
በተለይ ደግሞ ፀጉሩ ባልተለመደ መልኩ የወጣ ከሆነ ለምሳሌ የሴት ፂም ወይም ቀድሞ ቀመስ ገፅታዋን ስለሚያበላሽ ማስወገድ ትችላለች።
ከተለያዩ ምንጮች የተሰበሰበ።
(ኢብኑ ሙነወር፣
⚘••..¦@TewhidTewhid
@TewhidTewhid

@ibnuhasen
📮ሀይድ ላይ ያለች ሴት ልጅ ወይንም ጀናባ ላይ ያለ ወንድ ልጅ መስጂድ መግባት ይከለከላል" የሚል ግልፅ ማስረጃ የለም‼️

ኢብኑ ሐዝም አዝዟሂሪይ رحمه الله تعالى ኒፋስ ላይ ያለች ሴት ትሁን ሀይድ ላይ ያለች ሴት፣ እንዲሁም ጀናባ ላይ ያለ ወንድ ልጅ መስጂድ ሊገቡ ይችላሉ፤ አንድም እነሱን መስጂድ ከመግባት ሚከለክል ማስረጃ የለም፤ ደግሞም መልዕክተኛውም ﷺ ሙዕሚን አይነጀስም ብለው ተናግረዋል፤

ሻፊዒይዮች ደግሞ፦
ጀናባ ላይ ላለ ሰው እና ሀይድ ላይ ላለች ሴት መስጂድ መግባት አይችሉም፤ አልፈው ካልሆነ በስተቀር ብለው ይህን የቁርዓን አንቀፅ እንደ ማስረጃ ይገለገላሉ፦

يآأيها الذين آمنوا لا تقربوا الصلاة وأنتم سكارى حتى تعلموا ما تقولون ولا جنبا إلا عابري سبيل حتى تغتسلوا. (النساء 43)

لا تقربوا الصلاة / ሰላትን አትቅረቡ
ማለት፦ (مواضع الصلاة/የሰላት ቦታዎች ማለት ነው።) ይላሉ።

ዘይድ ኢብኑ አስለም እንደፈሰሩት፦ የምትሉትን እስከምታውቁ ድረስ የሰከራችሁ ሆናችሁ እያላችሁ የሰላትን (ስፍራዎች) አትቅረቡ! ጀናባዎችም ሆናችሁም እንደዚሁ! በመንገዱ ላይም ምታልፉ/ማለት የመንገድ አላፊዎች ሆናችሁ ካልሆነ በስተቀር።
እልፍ እየተባለ ከሆነ በመስጂድ አቋርጠን ብንሄድ ችግር የለውም። ብለው ጀናባ እና ሀይድ ላይ ላሉት ሰዎች አይቻልም ይላሉ። ሻፊዒይዮች

ኢብኑ ሐዝም رحمه الله تعالى ይህንን አስመልክቶ እንዲህ ይላሉ፦
(ولا حجة في قول زيد)
ዘይድ የተናገረው ትክክል አይደለም።

لا تقربوا الصلاة/ ሰላትን አትቅረቡ
ያለውን "ስፍራ" ብለን ከፈሰርን ትርጉሙን ያበላሽብናል።

لا تقربوا الصلاة/ ሰላትን አትቅረቡ
ማለት እሱ እንደሚለው ስፍራ ሳይሆን የተፈለገበት "ሰላቱ" ነው።
ስለዚህም ተሳስቷል ይላሉ።

ኢማሙ ማሊክ رحمه الله تعالى ደግሞ፦
"በማለፍ መልኩ ሳይሆን እዛ አከባቢ እራሱ ድርሽ እንዳይሉ" ይላሉ።

አቡ ሐኒፋ رحمه الله تعالى ደግሞ
لا يمران فيه فإن اضطرا إلى ذالك تيمما.

ሀይድ ላይ ያለች ሴትና ጀናባ ላይ ያለ ሰው በመስጂድ ማለፍ ግዳጅ ከሆነባቸው፣ ሌላ አማራጭ አተው እና ማለፋቸውም አስፈላጊ ሆኖ ከሆነ ተየሙም አድርገው ማለፍ ይችላሉ።
ይላሉ።

ለማንኛውም በመከልከል የመጡት ሐዲሶች ደካማ እስከሆኑ ድረስ፣ በተለይ ደግሞ ባሁኑ ጊዜ ደም እንዳይወጣ መከላከያ እስካለ ድረስ ሓጃም ታክሎበት ሴት ልጅ መስጂድ ብትገባ የሚከለክል ግልፅ የሆነ ማስረጃ የለም።

እንደውም መልዕክተኛው ﷺ ዓኢሻን ከመስጂድ ውስጥ ለመስገድ ግንባር ማሳረፊያ ጨርቅ አቃቢይኝ ሲሏት እሷ "ሀይድ ላይ ነኝ ያለውት" ስትላቸው ሀይድሽ ያለው እጅሽ ላይ አይደለም፤ ብለዋታል።

ሸይኹል አልባኒይ፦
"ይህ ማለት ታድያ ሰትይዋ ሀይድ ስታይ የተፈራው ነገር ደሙ እንጂ ሀይዱ አይደለም ማለት ነው።" ብለው ተናግረዋል።

🔘 ስለዚህም መስጂድ መግባትን ሚከለክል አንድም ግልፅ ማስረጃ የለም።

(ሸይኽ ሙሐመድ ዐረብ)

Abu Uwais Ibnu Kasim
◈•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•◈
🔘https://www.tg-me.com/yeilmkazna



@ibnuhasen
➪የቁጣ መድሐኒት

𒊹︎︎︎በመሰረቱ ቁጣ የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ባህሪይ ሲሆን
ሲበዛና ያለበቂ ምክንያት በተደጋጋሚ የሚፈጠር ከሆነ ግን እጅጉኑ ይወገዛል

☞︎︎︎በቦታውና በመጠኑ ሲሆን ደግሞ ይመሰገናል አርአያችንና
ውዱ ነቢያችንም
(صلى الله عليه وسلم)
𒊹︎︎︎ይቆጡ እንደ ነበረ ታሪካቸው ላይ ተዘግቧል።ነገር ግን ቁጣቸው #የአላህ ድንበር ሲጣስና ዲኑ ሲነካ ብቻ ነበር ለስብእናቸው ለነፍሳቸው ብለው አንድም ቀን ተቆጥተው አያውቁም

𒊹︎︎︎በሁሉም ነገር ☞እርሳቸውን የተከተለ ምንኛ የታደለ ሰው ነው?!


➪"የቁጠኝነትን ባህሪይ ለመከላከልና በሆነ ባልሆነው #የመቆጣትን ችግር ለመቅረፍ የሚከተሉትን ምክሮች ይተግብሩ፦

1❀ቁጣቸውን ዋጥ ለሚያደርጉና ይቅር ለሚሉ ሰዎች አላህ #አኼራ ላይ ያዘጋጀውን ከፍተኛ ምንዳና ደረጃ ማስታወስ

2 ❁ አዑዙ ቢላህ ሚነሽሸይጧኒር`ረጂም ማለትና #ዚክር ማለት

3𑁍 ከንግግርና መልስ #ከመስጠት መታቀብ (ዝም ማለት)

4✰ ቁጣው የተፈጠረው #ቆመው ከሆነ መቀመጥ፣ ቁጭ ብለው ከሆነም #ጋደም ማለትና ሁኔታን መቀየር፣

5✫ ውዱእ ማድረግና ከተቻለም ሁለት ረካኣ ሰላት መስገድ
ሙሉ ውዱእ ማድረግ እንኳ ባይቻል የተወሰነ #ሰውነት ላይ ውኃ በማፍሰስ ሰውነትን ማቀዝቀዝ፣

6✩ቁጣና ንዴት የሚያስከትለውን የጤና ችግር እንዲሁም በቁጣ ጊዜ እራሳችን ላይ የሚታየውን #መጥፎና አሳፋሪ የፊት ገፅታ እና የማይገቡ እንቅስቃሴዎችን ልብ ማለትና ይህን ከሰዎች እንደምንጠላው ሁሉ ለራሳችንም መጥላት፣

7𖣔 ቁጣን መተው ነቢዩን (صلى الله عليه وسلم) መታዘዝ እንደሆነ ማወቅ፥ ምክንያቱም #ነቢዩ ("አትቆጣ!") ብለዋልና
ይህም ሊሳካ የሚችለው ለቁጣ የሚዳርጉ ነገሮችን በመራቅና የተቆጡም እንደሆነ ራስን #በመቆጣጠር ብቻ ነው

✪በሆነ ባልሆነው የሚቆጣ ሰው ቤተ-ሰቦቹንና በተለያዩ ምክንያቶች የሚገናኙትን ሰዎች አዛ ስለሚያደርጋቸው እንደሚጠሉት ማወቅና #ከቁጣ በሽታ እንዲገላግለን አላህን ዘወትር መለመን
አበቃ!

𒊹︎︎︎አላህ መልካም ባህሪያትን በሙሉ ያግራልን!እርሱ ከሚጠላቸው ባህሪያትና ድርጊቶችም ይጠብቀን

︎በኡስታዝ አሕመድ አደም
𝐓𝐞:https://www.tg-me.com/dawatulanbiya
https://www.tg-me.com/dawatulanbiya

@ibnuhasen
የውይይት ጥሪ ለአሕባሾች
~
① ጠሪ: –

አቡ ዒምራን ሙሐመድ ሲራጅ
እና
ኢብኑ ሙነወር

② የጥሪው አድማስ:–

ለሁሉም አሕባሾች። ሰሞኑን "እንወያይ" ሲሉ የነበሩትን ሀቢብ እና ወሂድን ጨምሮ እስከነ ዑመር "ኮምቦልቻ" … ባጭሩ ለሁሉም።

③ የውይይት ርእስ:–

"አላህ ከዐርሹ በላይ ነው" የሚሉ ሙስሊሞችን እያከፈራችሁ ስለሆነ የምንጀምረው በዚህ የ"ኢስቲዋእ" ርእስ ነው። ይህንን ለመቋጨት ከበቃን እንደ "ኢስቲጋሣህ" ባሉ ሌሎች ወሳኝ ርእሶች እንቀጥላለን።

④ የውይይት መስፈርት: –

ማስረጃዎች ከቁርኣን፣ ከሐዲሥ እና ነቢዩ ﷺ ምርጥነታቸውን ከመሰከሩላቸው ቀደምት ትውልዶች ንግግር ብቻ
ይሄ ከጠበበባችሁስ?! በዚህ ምክንያት እንድትሸሹ አንፈልግም። እኛ:–

👉🏾 በሰለፎች አካሄድ ተገድባችሁ መሟገት አትችሉም ብለን ስለምናምን፣
👉🏾 በዚህ ምክንያት ከውይይቱ እንድትሸሹም ስለማንፈልግ፣
👉🏾 "እንከተላቸዋለን" ከምትሏቸው አቡል ሐሰን አልአሽዐሪ ፈፅሞ እንደማትገናኙ ማጋለጥም ስለምንሻ
እስከ አቡል ሐሰን ዘመነ–ህልፈት #ድረስ ያሉ ዓሊሞችን #ብቻ እንድታጣቅሱ እንስማማለን። ከዚያ በኋላ #ፈፅሞ አይሆንም።

በዚህ ዘመን የምንገድብበት ምክንያት:–

1⃣ ውይይቱ ልጓም የለሽ ሆኖ እንዳይለጠጥ ለመወሰን፣
2⃣ እምነታችሁ ከጊዜ በኋላ የመጣ እንጂ የዚያ ምርጥ ዘመን ትውልድ እምነት እንዳልሆነ ለማሳየት፣
3⃣ ዐቂዳችሁ "ኢማማችን" የምትሉት አቡል ሐሰንም እምነት እንዳልሆነ ለማሳየት፣
4⃣ "አላህ ከዐርሽ በላይ ነው" የሚለው ዐቂዳ "የወሃቢዮች ዐቂዳ ነው" በማለት መጤ አስተሳሰብ በማስመሰል ነጭ ውሸት በመንዛት ህዝብ እያደናገራችሁ ስለሆነ

በተቃራኒው ይህ "አላህ ከዐርሹ በላይ ነው" የሚለው እምነት በቁርኣንና በሐዲሥ የፀና፣ እነዚያ ምርጥ ትውልዶች የተጓዙበት፣ እንዲሁም የነ አቡል ሐሰን አልአሽዐሪ ጭምር ዐቂዳህ እንደሆነ ለማሳየት ርእሱን መገደብ ግድ ብሏል።

⑤ የውይይቱ ቦታ:–

ቴሌግራም ላይ በዚህ ግሩፕ ይሆናል:–
👇🏾
https://www.tg-me.com/IbnuMuneworsb

🔊 መልእክቱን አዳርሱልን። ምናልባት ፈቃደኛ ሆኖ የሚቀርብ ሊኖር ይችላልና።
"በአለም ያለው የሰው ዘር አንድ ነው፡ እርሱም የ ሰው ዘር ነው። ከአንድ ዘር በቀር የሰው ዝርያ የለም። በቋንቋ፡ በነገድ፡ በብሔር ወዘተ..... መለያየት የ ዘር ልዩነት አደለም። የባህል ልዩነት እንጂ ።

የዘር ልዩነት ባዮሎጂካዊ መሰረት ያለውን መለያየት የሚያሳይ ነው። ሁላችንም ባዮሎጂካዊ ተመሳስሎሽ አለን። የምንለያየው በባህላችን ነው፡ በቁርአንም ሆነ በመልእክተኛው (ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም) መልእክቶች የምናነበው ጭብጥ ይኼው ነው። የትኛውም ሰው ለሚደርስበት ጭቆና ወይም በደል ጠበቃ ሁኖ መቆም ኢስላማዊ ግዴታ ነው።"
'ሙሀመድ አሊ (ቡርሀን) -እስልምና በ20ኛው ክፍለዘመን- ገፅ 76-77'

www.tg-me.com/ibnuhasen
ሱሰኝነት እሚባለው ቃል ራሱ ደስ አይልም!
ከሰሞኑ እየታዩ ያሉ ሱሰኝነቶች ለሌሎች ሱሶች ለየት ያለ እና አስቸጋሪ እየሆኑ ነው።
ዛሬ የ ሶሻል ሚድያ ሱሰኝነት እና ሁሉንም ነገር ሶሻል ሚድያ ላይ ማጋራት ምን እንደሆኑ ላካፍላችሁ ወደድኩ፡-
መጀመሪያ social media ያሉት መልካም ጎኖች ብዛታቸውን ሁላችንም እናውቃልን። ለንግድ ፡ ለመዝናኛነት ፡ ለፖለቲካ ፡ ለትምህርት እና መሰል ጉዳዮች እሚውለው ማህበራዊ ሚድያወች አሁን አሁን ግን ነገሩ ከረር ብሎ ወደ ሱሰኝነት ማደጉ ሁላችንም ሊያሳስብ የሚገባ ጉዳይ ሁኗል።

አንዳንዶቻችን ከ social media ለትንሽ ሰአታት ከራቅን ብዙ ነገሮች የተለወጡ ከመምሰሉ ባሻገር በድብርት እና በመሰላቸት ጊዚያችን እንድናሳልፍ ያደርገናል። ግን አንድ ሰው በ ሶሻል ሚድያ ሱስ ተጠቅቷል እምንለው መች ነው?!
ምናልባት ከታች እምጠቅሳቸው ምልክቶች እናንተ ላይ ከታየቦት ሶሻል ሚድያ ላይ ያለንን ቁርኝት ገታ ልናደርገው ይገባል የሚል ሀሳብ አለኝ።
ከታች የምጠቅሳቸው ምልክቶች በ urban balance እና health line በተደረጉ ጥናቶች የቀረቡትን ነው።

- የ ሶሻል ሚድያ አካውንትህን ማታ ስትተኛ እና ስትነቃ ገብተህ ቸክ እምታደርግ ከሆነ ሊታስብበት ይገባል።አንዳንድ ጥናቶች እንደሚሉት ከሆነ እንቅልፍ ከመተኛታችን 30 ደቂቃ በፊት ስልካችን ጋር መለያየት እንዳለብን ያትታሉ። ታድያ እኛ ይህን ጥሰን አካውንታችን እምናይ ከሆነ በትንሹ ምልክቶቹ እየተሰተዋሉብን ነው ማለት ነው።
-ፖስትህ ስንት ላይክ እንዳገኘ ለማወቅ ቶሎ ቶሎ refresh እያደረግክ እምታይም ከሆነ። ይህን ስል ላይክ የማግኘት ፍላጎት ስህተት ነው ማለቴ ሳይሆን ከልክ ካለፈ ግን አደጋ ላይ ነህ ማለት ነው።
-ስልክህ ላይ notification ድምፅ ስትሰማ ወዲያው ገብተህ እምታይ ከሆነ ።ይህን ስል ልክ የ notification ድምጿ ስትጮህ ወደ ጭንቅላትህ ትንንሽ dopamine (የ ደስተኝነት ኬሚካል በሉት ☺️) ይለቀቃል። ቀጥታ የሆነ ሽልማት እምትሸለም ያህል ይሰምሀል።

-ስራ ጊዜ ወይም የትምህርት ጊዜህም፡ሊሆን ይችላል እሚጋፋህ ከሆነ ፡-በተለይ ተማሪወች የንባብ ሰአት እሚጋፋ ከሆነ ለሱሰኝነት የቀረብን መሆኑን ራሳችን ማየት እንችላለን።

-ሶሻል ሚድያ መጠቀም በማትችልበት ጊዜ እሚደብርህ ከሆነ፡- እማትችልበት ስል ምናልባት ስልካችሁ ካርድ አልቆ መጠቀም ሳትችሉ ፣ ወይም wifi ተበላሽቶ እስኪሰራ ድረስ ሶሻል ሚድያ መጠቀም ባለመቻላችን እሚደብረን እና እሚያስጠላን ከሆነ አሁንም ይህ የሱሰኝነት አንዱ ምልክት ነው።

-ሌላው ለጓደኞቻችን ፣ ለቤተሰቦቻችን ጊዜ መስጠት ካቆምነ ዋንኛው ምልክት ነው ማለት እንችላለን። ጓደኛችን እያናገረን እኛ ፖስት የተደረግ ማንበብ እና የሱን ወሬ ከምንም አለመቁጠር(በተለይ ችክ ጋር እያወራን ከሆነ 😂) እንዲሁም ቤተሰብ ጋር ተገናኝንተን ማውራት ካቆምን ለ ሱሰኝነት መጋለጣችን ዋናወቹ ምክኒያቶች ናቸው።
("እና አንተ ሱሰኛ ነህኣ 😂" አትሉኝም ።)
ይቀጥላል....
@ibnuhasen
T.me/ibnuhasen
ክፍል ሁለት



የአንዳንዶቻችን ሱስማ ለየት ይላል። ሶሻል ሚድያ ላይ ፖስት ሳናደርግ ከዋልን እምንሞት ነው እሚመስለን። (ለምንድን ነው ግን😔) እያንዳንዷ እምናደርጋትን ነገር Facebook ላይ ወይም Instagram ላይ ካለጠፍን እንዳትውሉ የተባልን፡ነው እሚመስለን።
Psychology today እና Huffington post ባደረጉት ጥናት ሁሌም ሁሉንም ነገር ሶሻል ሚድያ ላይ እሚያጋሩ ሰወች ከታየባቸው ባህሪወች ውስጥ ከታች ያሉትን ጠቅሷል ፡-
-ማንም ስለማያውቀን እንደፈለግን መናገር ስለምንችል
-አለመታየት ስሜት ከ keyboard ጀርባ ሁነን እንደፈለግን መናገር መቻላችን እና ማንም አያየኝም የሚለው ስሜት ሲኖርብን
-ያልሆንነውን ነገር መሆን ስለምንፈልግ
- ድብርት
- በራሳችን ላይ ያለን እምነት ዝቅተኛ በመሆኑ
- ትኩረት ለመሳብ
- ራሳችን ላቅ አድርገን ከማሰብ በተጨማሪ እኛ እምናደርገው ነገር ብቻ ትክክል መስሎ እንዲሰማን ለማድረግ
-ትምህርት ነክ የሆኑ ነገሮችን ለመስጠት
-በሰሩት ስራ ላይ አስተያየት ለመቀበል

መጨረሻ ላይ የተጠቀሱት ሁለቱ ምክኒያቶች ሁሉንም፡ነገር በnegative እንዳናየው ለማድረግ እንጂ የ ፖስት ሱስ ያለበት ሰው እንዲህ አይነት ባህሪ ይኖረዋል ብየ አላስብም(እና አንተ አሰብክ አላሰብክ እንዳትሉኝ😂)።

ይህን አይነት ተግባር ብዙ ወሬ ከመውደድ የሚመጣም እንደሆነ ልንገነዘብ ይገባል።
በርግጥም ብዙ ማውራት ከመጠላቱም በተጨማሪ አላስፈላጊ ነገር ከመናገር መታቀብ እንዳለብን ነብያዊ ምክር መቀበላችን ልብ ይሏል።
ቲርሚዚ በዘገቡት ሀዲስ የአላህ መልእክተኛ (ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡-" የአላህን ስም ሳታነሱ ብዙ አታውሩ። የአላህን ስም ሳይወሳ ብዙ ማውራት ልብን ያደርቃል...."
ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ሌላ ሀዲስ ደግሞ
አቡ ሁረይራ(ረ.አ) ከረሱል (ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም) ተከታዩን ሰምቻለሁ በማለት አስተላልፈዋል፡- "አንድ ሰው ንግግርን እንደተራ ይናገራል ። በዛ ንግግሩ ምክንያት ጀሀነም ይገባል. ....."።
እንዲህ አይነት እና መሰል ሀዲሶችን እየሰማን አሁንም በዛው ባህሪያችን መቀጠላችን ደሞ ሌላ ችግራችን ነው።

እና ምን ብናደርግ ይሻላል ?!ካላችሁኝ(እንደኔ ሀሳብ)
ራሳችን ከ ሶሻል ሚድያ በቻልነው አቅም ለመገድብ መሞከር እና ለሌሎች ነገሮች ጊዜ መስጠትን ብናዳብር የተሻለ ነው።
ይህን ስል notification ከማጥፋትም ሊጀምር ይችላል። እስከ ስልካችን መቀየርም ሊደርስ ይችላል።
ከዚህ ሁሉ ግን ራሳችን ላይ ከፍተኛ መተማመን እና ጥንካሬ ካለን social media ላይ እምናጠፋውን ጊዜያችን መገደብ እና ሁኔታወችን ቀለል አድርጎ ለማየት መሞከር ጥሩ መንገድ ይመስለኛል(በ'ይመስለለኛል' ጨረስከው እንዳትሉኝ😜)።


@ibnuhasen
T.me/ibnuhasen
ፍፃሜህን አሳምር‼️
================
💢ስትተኛ በሱና ላይ ሆነህ፣ ተውበት አድርገህ፣ ወደጌታህ ተመልሰህ፣ የበደለህን አፋ ብለህ፣ እዳ ካለብህ ወይም ካለህም ፅፈህ እንዲሁም የመኝታ ዚክሮችን ብለህና ዱአ አድርገህ ቢሆን እንጂ በሰው ላይ ቂም ይዘህ፣ ሰውን በድለህ፣ ጌታህን አስቆጥተህ፣ የሰዎችን ሀቅ ይዘህና ያለሱና እንደ ከብት ዝም ብለህ እንዳትተኛ። ምክንያቱም ይህ አዳር ላንተ የመጨረሻ የዱንያ ፍፃሜህ ሊሆንና በዛው ወደ ማይቀረው ወደ ዘልአለሙ እውነተኛው ሀገር ልትሄድ ትችላለህና ኻቲማህ (ፍፃሜህ) ይስተካከል ዘንድ ጥረት አድርግ።

🔺አላህ ሆይ መጨረሻችንን አሳምርልን
🔺አላህ ሆይ ሞት ለማንም አይቀርምና እውነተኛ ባሮችህ ሆነን በታዘዝነው ላይ ቀጥ ብለን ወንጀላችንን ምረህ አንተ በምተወደው መንገድ ላይ ሆነን ግደለን
አሚን

@ibnuhasen
መፅሀፍ- ኒኣም የቀልብ በሽታወች እና መድሀኒቶቻቸው

ፀሀፊ- ሸኽ ሀሰን አዩብ

ተርጓሚ- ሀሰን ታጁ

ይዘት- መፅሀፉ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ ከሚከሰቱ ችግሮች ውስጥ የሆነውን የቀልብን ጉዳይ አንስቶ በደምብ አብራርቷል።

"አዋጅ ! ለአካል ውስጥ አንዲት ሙዳ ስጋ አለች። እርሷ ከተስተካከለች ሌሎች የሰውነት ክፍሎች ይስተካከላሉ...." ብሎ እሚጀምረው መጽሀፉ ስለ ኩራት እና ትእቢት ፣ በራስ መደነቅ ፣ ቁጣ እንዲሁም ስለ ወንድማዊ ባህሪወች ሊሆኑ የሚገቡትን ነገሮች ከመጥቀስ ባለፈ ሌሎች ጠቃሚ ርእሶች ላይ በቁርአንና በሀዲስ እንዲሁም በ ታላላቅ ሰሀባወች ንግግር ይታጨቀ ነው።

መፅሀፉ በ 2001 የታተመ ሲሆን አሁን ላለብን የልብ በሽታ ጥሩ ማሳያ የሚሆኑ ምሳሌወችን መጥቀሱ መፅሀፉን ተወዳጅ አድርጎታል።

የገፅ ብዛት - 60

ከመፅሀፉ የተወሰደ- "ወንድምን መናቅ ማለት አቃሎ እና ዋጋ እንደሌለው አድርጎ ማየት ፣ ትኩረት እና ግምት አለመስጠት ነው። ይህ ስሜት በሙስሊሞች መካከል ከተከሰተ ትስስራቸውን ክፉኛ የሚጎዳ በሽታ ነው። ምክኒያቱም በተመሳሳይ እምነት ወንድማማቾች በመልክ ፣ በሐገር ፣ በዘር ወይም በሌላ ነገር ቢለያዩም አንዱ ሌላውን ሊንቅ እና ሊያጣጥል ፈፅሞ አይገባም።" ገፅ 54

@ibnuhasen

T.me/ibnuhasen
ከጁመዓ ቀን ሱናዎች
~~~~~~~~~~~~
↩️‏سنن يوم_الجمعة

➊ الغسل
➋ الطيب
➌ السواك
➍ لبس الجميل
➎ قراءة سورة الكهف
➏ التبكير لصلاة الجمعة
➐الإكثار من الدعاء والصلاة على النبي ﷺ
🔹ገላን መታጠብ
🔹ሽቶ መቀባት
🔹ሲዋክ መጠቀም
🔹ጥሩ ልብስ መልበስ
🔹ሱረቱ ከህፍን መቅራት
🔹በጧት ለጁመዓ ሶላት መጣድ
🔹በነብዩ ﷺ ላይ ዱዓና ሰለዋት ማብዛት

@ibnuhasen
እነሆ ሳምንቱ ደረሰ

#Reading_challenge

የመፅሀፉ ስም - እስልምና በ 20ኛው ክፍለዘመን

ፀሐፊ - ሙሀመድ አሊ(ቡርሀን)

የመፅሀፉ ይዘት-

መፅሀፉ ሲጀምር ስለ ዘመናዊነት ምንነት እና ስላስከተለው ተፅእኖ በማብራራት ነበር። አሁን ላይ ዘመናዊነት ተብሎ ስለሚጠቀሰው ነገር ግልፅ አድርጎ ያስረዳል።ከዛ ስለ አንድ አይናነት። እንደ መፅሀፉ ገለፃ ከሆነ ደጃሊዝም ይለዋል።መፅሀፉ እማይነካው የታሪክ ክፍል የለም። አውሮፓውያን ከ ኦርቶዶክስ እና ካቶሊክ እምነት ውጭ ባሉ እምነቶች ላይ ያደርሱት በደል። የኦቶማን ቱርክ አመሰራረት ። ሙሀመድ አልፋትህ ኮንስታንቲኖፕልን እንዴት እንደከፈተ። ከሱ በፊት አብዱረህማን ሶስተኛ ያደረገውን ተጋድሎ። ሁለተኛው የአለም ጦርነት፣ ስለ ሆሎካውስት፣ ስለ ሳላህዲን ተምሳሌት፣ ስለ ባልካን ቀውስ፣ ስለ ኦቶማን አወዳደቅ እና አወዳደቁ ላይ የተሳተፉ እነማን እንደሆኑ ፣ የ ኺላፋው እንግዳ ተቀባይነት ፣ ሙስሊሙ አለም ላይ ስለተደቀኑ ችግሮች እና መፍትሄ ሀሳቦች፣ ኢማን እና ድል ያላቸውን ቅንጅት፣ስለ እሴት ማቆየት ፣ ባቢሎንን እንደምሳሌ ወዘተ..ምን አለፋችሁ መፅሀፉ ያልዳሰሰው ነገር የለም። ስለመፅሀፉ ይዘት ሙሉውን አልጠቀስኩም። እሱን ከመጥቀስ ራሱ ረዥም ፅሁፍ ያስፈልጋልና።

የገፅ ብዛት - 259

መጽሀፉ በ ግንቦት 2010 አ.ል የታተመ ነው

ከመፅሀፉ የተወሰደ ፡-

" እስልምናን መኖር ኃጢአት የመሰለበት ከንቱ ስርአት ውስጥ ነን፤ እስልምናን ብቻ አደለም፤ ንፁህ ምግባር የሚቀርጹ የክርስትና መርሀትም እንዲሁ ተንቀዋል። ሸሆች፣ቄሶችና ራባዮች የተገፉበት አለም ሆኗል ያለን።ይህን ማስተዋል ከሰማይ ሩቅ ነው። እልፍ የሳይንስና የከያንያን ግርዶወች ሰው ወደልቡ ውብ መስክ እንዳያርፍ አድርገውታል። የቁርአን ክብር ታላቅነትና የረዥም ዘመናት የስልጣኔ ምንጭነት እንዲካድ ዘመናዊ ትምህርት ደስ የማይል ሸክም ፈጥሯል። ሳይንሳዊነት ብቻ ልክ ብለን እንድናምን ተደርገናል።" ገፅ 10
@ibnuhasen

T.me/ibnuhasen
ብዙ ጊዜ ልክ እንደ 'think and grow rich' አይነት መፅሀፎችን ሳይ ኢስላም ለዱኣ የሰጠውን ቦታ ይገርመኛል።

ብዙ መፅሀፎች ላይ አንድን ነገር ለማድረግ ስታልም ያንን ነገር እንደምታደርገው እርግጠኛ ልትሆን ይገባል።አንዳንዱማ አንተ እንደምታደገው እርግጠኛ ሁን እንጂ ዩንቨርስ ይተባበርሀል ያላሉ።

ኢስላም ላይ ደሞ ዱኣህ ተቀባይነት ይኖረው ዘንድ አላህ እንደሚያደርግልህ እርግጠኛ መሆን አለብህ።

ሰውና ሀሳቡ የተሰኘው የጀምስ አለን መፅሀፍ ላይ እንዲሁ ይህንን ነገር ደጋግሞ ያወሳዋል።
ብዙ የሳይኮሎጂ መፅሀፎች መሆን እምትፈልገውን ነገር ፣ አላማህን ለራስህ በየቀኑ ደጋግመህ ድምጽህን ለራስህ እንድትሰማው አድርገህ ንገረው ይላሉ።

ኢስላም ደሞ እያንዳንዱን ነገር አላህን እንድትጠይቅ ያስተምርሀል። ድምፅህንም ለራስህ እንደምትሰማው አድርገህ ዱኣ እንድታደርግ ይጋብዝሀል። ጮክ ብለህ ዱኣ ማድረግ እንኳን አይጠቅብህም።

ብቻ ምን አለፋችሁ አላህን ደጋግመህ ስትጠይቅ፤ ለራስህም መሆን እምትፈልገውን ነገር እየነገርከው ነው ማለት ነው።

ለምትፈልገው ነገር ዱኣ ስታደርግ አላህ እንደሚሰጥህ እርግጠኛ ከሆንክ፤ ያንን ነገር እንደምታደርገው እርግጠኛ ትሆናለህ።

@ibnuhasen
T.me/ibnuhasen
የመፅሀፉ ስም - ተሕዚብ ተስ'ሒሉል አቂደቲል ኢስላሚያህ


ፀሀፊ- ዶ/ር አብዱላሂ ብን አብዱልአዚዝ አል ጂብሪን

ተርጓሚ- ዩሱፍ አህመድ

የመፅሀፉ ይዘት -

መፅሀፉ ሲጀምር የአቂዳ ትርጉም አጠር ባለ ትንታኔ በማቅረብ ነው። መጽሀፉ ስለተውሂድ በደምብ የሚያብራራ ነው። በስሮቹ ሙስሊሞች ስለተውሂድ ሊያውቋቸው የሚገቡ የተውሂድ ክፍሎች ተካተዋል። ከነዛም ውስጥ መፅሀፉ ስለ ተውሂድ፣ ሶስቱ የተውሂድ ክፍሎች ፣ ስለላኢላሀ ኢለሏህ የምስክርነት ቃል፣ የአምልኮ መሥፈርት እና መሰረቶች ፣ ስለአላህ መልካም ስሞች እና ባህሪያት ፣ የተውሂድ አፍራሽ ክፍሎች ፣ ስለ ሺርክ ፣ ስው ኒፋቅ፣ ስለቢድኣ ና አል'ወላእ ወል'በራእ ምን አለፋችሁ መፅሀፉ በተውሂድ ዙርያ ልናውቃቸው የሚገቡ ብዙ ነገሮችን ሸክፎ ይዟል።

የመጀመሪያው እትም ሚያዚያ 2010

የገፅ ብዛት - 278

ከመፅሀፉ የተወሰደ፡-

"ነፍሱን ከእሳት ነፃ ማድረግ እሚፈልግ ማንኛውም ሙስሊም በሌላው ሙስሊም ላይ በከሀዲነትም ይሁን በአጋሪነት ውሳኔ ለመስጠት መፍጠን የለበትም። ማንም ተራ አካላት ወይም እውቀትን ፈላጊ የሆኑ ተማሪወች በክህደት የመፈረጅን ጉዳይ ወደ ኢስላም ሊቃውንት ሳይመልሱ በግለሰብ ወይም ሙስሊም በሆኑ አንጃወች ላይ በክህደት ፍርድን መስጠት እርም ተደርጎባቸዋል። ያለ እውቀት በተክፊር ነጥቦች ዙርያ አጀንዳን ከፍተው ከሚዘባርቁ ሰወችም መራቅ አለባቸው። ምክኒያቱም ያለምንም እውቀት በዚህ አጀንዳ ውስጥ መግባት በአላህ አንቀፆች መዘባረቅ ነውና።"

@ibnuhasen

T.me/ibnuhasen
ኢማም ኢብነል ቀይም አልጀውዚ

ትክክለኛ ስማቸው አቡ አብዱላህ ሙሀመድ ኢብን አቡ በክር ኢብን ሰእድ አል ሐሪዝ አዝዙህሪይ አድ ደመሽቂይ ሲሆን ኢብን አልቀዩም አልጀውዚይ በመባል ይታወቃሉ። አልጀውዚይ በደማስቆ የምትገኝ የትምህርት ተቋም ስትሆን የኢብነልቀይም አባት የተቋሙ ምሁር እና አስተዳዳሪ ነበሩ።

ኢብን አልቀዩም የተወለዱት ሰፈር 7ቀን/691አመት ሂጅራ (1292እ.ኤ.አ) ነው። ገና በ 7 አመታቸው በጊዜው እውቅ የሆኑ ሀያ አምስት ታላላቅ ሙስሊም ምሁራን ጋር ትምህርታቸውን ተከታትለዋል። በእውቀታቸውም በመምጠቅ በተፍሲር፣ ሐዲስ፣ ፊቅህ፣ ህግ፣ ኡሱሉዲን (ስነ-አምልኮ ሳይንስ) ና ቁንቋ ሰልጥነዋል።

ስለ ኢብን አልቀይም መልካም፡ስነምግባርና ስለ አምልኮታዊ(ኢባዳ) ጥንካሬ ብዙ ሙስሊም እውቅ ሊቃውንት ፅፈዋል።


ኢብን አልቀይም 21 አመት ሲሞላቸው እንደ ሂጅራ አቆጣጠር በ712 ከሸይኹል ኢስላም ኢብን ተምይሚያህ ጋር ተገናኝተው ኢብን ተይሚያህ ከዚህ አለም በሞት እስከተለዩበት ጊዜ አብረዋቸው ቆይተዋል። ኢብን አልቀይም ከ ኢብኑ ተይሚያህ ጋር በነበራቸው ቆይታ ብዙ ነገሮችን የተማሩ ሲሆን ኢብን ተይሚያህ እስር ሲገቡም አብረው ገብተው ነበር ። እስር ቤት ውስጥ ኢብን አልቀይም ቁርአን በመቅራት እና በመረዳት ያሳልፉት እንደነበር ኢብን ረጅብ (ደረሳቸው) ይናገራል። ኢብን ተይሚያህ ሲሞቱ (አላህ ይዘንላቸውና) ኢብን አልቀይም ከእስር ተፈተዋል።

ኢብን አልቀይም በእስልምና ሀይማኖት መስኮች ዙርያ በርከት ያሉ የፅሁፍ ስራወችን አበርክተዋል። ስራወቻቸው የሰለፎችን መንገድ የተከተለና አሁንም ድረው ለዳእዋ ሰራተኞች ብርሀን በመሆን ያገለገሉ ናቸው።

ኢብን አልቀይም ከመቶ በላይ መፅሀፎችን የፃፉ ሲሆን በግጥም ችሎታቸውም ይታወቃሉ።ከኪታቦቻቸው መካከል
-ዛዱል መኣድ
-አልፈዋኢድ
-ተህዚብ ሱነን አቢዳውድ
-መዳሪጅሳሊኪን
-ሚፍታህ ዳር አሰአዳህ
-ሃዲል አርዋህ ኢላቢላዲል አፍራህ
የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ።

ኢብነልቀይም በርካታ ተማሪወችን ያፈሩ ሲሆን ከነሱም መካከል
-ኢብን ከሲር ፣ ኢብን ረጅም አልሀንበሊ፣ አዝዘሀቢ፣ ኢብን አንዱልሀዲ፣ ተቃኡዲን አቡቢኪ እና ሌሎችም ይጠቀሳሉ።

ኢብን አልቀይም አላህ ይዘንላቸውና በስልሳ (60) አመታቸው በ13ኛው ረጅብ 751 ሮብ ምሽት ወደ አኺራ ሂደዋል።ሰላተል ጀናዛ ስርአትም በንጋታው በኡመያድ መስጂድ ደማስቆ ውስጥ ተፈፀመ።

@ibnuhasen

T.me/ibnuhasen
የምር መናገር አልፈልግም ነበር ግን አልቻልኩም

ሰሞኑን world hijab day ደረሰ እያሉ ፖስት ሲያደርጉ አየሁ። ገረመኝ። "እንዲህ እሚባልም ቀን አለ" እያልኩ ተገረምኩ። ግን የታዘብኩት ነገር ቢኖር አንዳንድ ሰወች ይሄን ፖስት እሚያደርጉት ሂጃብ በትክክል እማለብሱ አሉ። እነዚህ ሰወች ምን ነካቸው አመቱን ሙሉ ሂጃብ አስተካክለው ሳይለብሱ የሂጃብ ቀን ብለው ሊያከብሩ ነው☺️። ከአላህ ጋር እምንቀርበው ትእዛዙን አስተካክለን ስንፈፅም እንጂ በአመት አንድ ቀን ሂጃብን ቀን ብለን ስላከበርን አደለም😒
አንዳንዴ ለምንድን ነው ፀጉራቸውን እሚገልጡት እያልኩ አስባለሁ።ደሞኮ ፀጉራቸውን እያሳዩ ማህበራዊ ሚድያ ላይ ይለጥፋሉ።

እስኪ ልጠይቃችሁ ምክንያታችሁ ምንድን ነው?!
(ከዚህ በታች እሚመለከተው እዚህ facebook መንደር ፀጉራችሁን ገለጥ አድርጋችሁ ፎቶ ለምትለቁት ነው)

- እንደሚከለከል አላወቅኩም ነበር ! ካላችሁ እንግዲያውስ እህቴ አላህ ይዘንልሽና እወቂ ሴት ልጅ ለሷ ያልተፈቀዱ የሆኑ ወንዶች ተገላልጣ ልትታይ አይፈቀድላትም(ሱረቱ አል ኑር 24፥31)


-ሂጃብ አስተካክሎ መልበስ ስራ ሆኖባችሁ ነውን?! ፎቶ ለምትነሺበት ስታይል ስትቀያይሪ ምንም ያልመሰለሽ ሂጃብ አስተካክሎ መልበስ ስራ ሆነብሽ¡

- ሂጃብ የጨቆናችሁ፣ ነፃነታችሁን የቀማ መስሎ ከተሰማችሁ ! ከነጅማሮው አውልቁት። እንዴት ጭቆና መስሎ የተሰማችሁን ነገር ታደርጋላችሁ።

-ውበታችሁን ማሳየት ፈልጋችሁ ከሆነም!
ወላሂ ነው እምላችሁ ፀጉራችሁን ከምታሳዩበት ፎቶ ይልቅ በሂጃብ ጥቅልል ብላችሁ እምትታዩበት ምስል ውበት አለው።

-በድንገት ፎቶ ስነሳ ነው እንጂ ፈልጌ ያደረግኩት ነገር የለም! ካላችሁ ፎቶውን ስታዩት ፀጉራችሁ የሚታይ መሆኑን አስታውላችሁ እዚህ ማህበራዊ ሚድያ ላይ አትለጥፉት
በነገራችን ላይ እንዲህ ስል ለምንድን ነው አይባችን እምትከታተል! አንተ ምን አገባህ?! ትሉ ይሆናል
Well እንግዲህ እምላችሁ ነገር ቢኖር ጥፋታችሁን ለመሸፋፈን እኔን "ምን አገባህ" ማለት የለባችሁም። እኔን "ምን አገባህ" ስላላችሁ ስራችሁ ትክክል አይሆንም አላህ ዘንድ ተፅፎ ይቀርባልና።

ሲቀጥል እኔ የናንተን ጥፋት አልተከታተልኩም ጥፋታችሁ ነው እኔን የተከታተለኝ☺️(ቀልዴን ነው)።

በነገራችን ላይ እኔ hijab day ይቻላል አይቻልም እያልኩ አደለም።

አላህ ሁላችንንም ቅኑን መንገድ ይምራን።

@ibnuhasen
T.me/ibnuhasen
እነሆ ጊዚያችን ጠብቀን ተከስተናል☺️

#Reading_challenge

ዛሬ ደሞ ለየት ያለ መፅሀፍ ነው ምጋብዛችሁ


የመፅሀፉ ስም - ጀነት መግባት ትፈልጋለህ? እና ሌሎች ኢስላማዊ ፅሁፎች

ፀሀፊ - ፀሀፊወቹ ብዙ ስለሆኑ አሳታሚውን ብናገር ይሻላል😂

አሳታሚ- ነጃሺ ማተሚያ ቤት

የመፅሀፉ ይዘት -

መፅሁፉ ሶስት የተለያዩ ክፍሎች ያሉት ሲሆን ፤ ሁለቱ የትርጉም ስራወች ሲሆን አንዱ የጥንቅር ስራውን የሰራው ሙሀመድ ሰኢድ(ABX) ነው።
በመጀመሪያ ላይ እምታገኙት "ጀነት መግባት ትፈልጋለህ?" እሚሰኘው በ ማጂድ ኢብን ኸንጀር አልባንካኒ ፤ አቢ አነስ አል ኢራቂይ የተዘጋጀ ሲሆን አብዱልፈታህ ሙሀመድ ወደ አማርኛ መልሶታል። እዚህኛው ክፍል ላይ ጀነት ምን እንደሆነ በማብራራት እሚጀምር ሲሆን ሙስሊሞች ጀነት ውስጥ ቤት ይገነባላችኋል ተብለው የተላለፉትን ሀዲሶች እና ትንተናወችን ሸክፎ የያዘ ነው።

ሁለተኛው ደግሞ ሙሀመ ሰኢድ ያጠናቀረው ሲሆን ፤ ንፁህ ቀልብ ያስፈልገናል ሲል ሰይሞታል። ቀልባችን ንፁህ ለማድረግ እሚጠቅሙ ፅሁፎችን "ፌርማታ" ብሎ በመሰየም አስራ አራት ፌርማታ ፅሁፎችን አቅርቧል።

የመጨረሻው የኢብነል ቀይምን ኪታብ በአቤል ሀይሌ ወደ አማርኛ መልሶ ስሜትን መከተል ብሎ አቅርቦታል። ስሜትህን ለምን መከተል እንደሌለብህ እያብራራ ብዙ ነጥቦችን ያነሳል።

የገፅ ብዛት - 123

ከመፅሀፉ የተወሰደ -

" እንደ አቢ ደምደም መሆን እሚችል ማን ነው?

<አቢ ደምደም ደግሞ ማን ነው?> የሚለው የብዙወቻችን ጥያቄ እንደሆነ እገምታለሁ። ተከተሉኝማ ልንገራችሁ ። አቡዳውድ እና ጦበራኒ ከአነስ ኢብኑ ማሊክ ረድየሏሁ አንሁ እንደዘገቡት የአላህ መልእክተኛ (ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም) አንድ ቀን ለሰሀቦቻቸው 'ከናንተ መካከል እንደ አቢ ደምደም መሆን እሚችል ማን ነው!' በማለት ጠየቋቸው። ሰሃቦችም 'የአላህ መልእክተኛ ሆይ! አቢ ደምደም ማን ነው?' በማለት በግርምት ጠየቋቸው 'እሱማ' አሉ ነብያችን 'እሱማ ባነጋ ቁጥር ጧት ላይ በመነሳት <ጌታየ ሆይ! እኔ ነፍሴን እና ክብሬን ሰጥቼሀለው> የሚል ሰው ሲሆን የሚሰድቡትን መልሶ አይሳደብም፤ የበደሉትን አይበድልም፣ የመቱትንም አይመታም' አሏቸው።" ገፅ ፥55


@ibnuhasen

T.me/ibnuhasen
እናስተነትን ዘንድ

እነሆ ተፈኩር እናድርግ ብለን ሀሳቡን ጀምረን አሁን ማስቀጠልን ወደድጅን። እንደ ሙስሊም አካባቢያችን ያሉ ነገሮችን እንስተነትን ዘንድ የተወደደ ነውና አካባቢያችን ስላሉ ነገሮች እያነሳን እንወያያለን።

ለዛሬ የመረጥንላችሁ አላህ በስሟ አንድ የቁርአን ምእራፍ የሰየመላትን አንድ የነፍሳት ዝርያ የሆነውን ጉንዳንን ነው።

ጉንዳን በጣም ጠንካራ ከሆኑ ነፍሳት እሚመደብ ነው። የክብደቱን 20 እጥፍ መሸከም ይችላል። ይህ ማለት አንድ ወጣት እንደ ጉንዳን ጠንካራ ቢሆን አንድ የቤት መኪናን ሊሸከም ይችላል ማለት ነው።

ጉንዳን በዳይነሶሮች ጊዜ ጀምሮ የነበረ እንደሆነ ሳይንቲስቶች ያትታሉ። ይህም ማለት ከ 100 ሚልዮን አመት በፊት ማለት ነው። ይህ ነፍሳት ከ 12,000 አይነት በላይ ዝርያወች ያሉት ነው ። ምድር ላይ እሚርመሰመሱ ብዙ ጉንዳኖችን አይተው ይሆናል። እስኪ እንጠይቅወ ምድር ላይ እሚሄዱት ጉንዳኖች ሴት ወይስ ወንድ ?!

ብዙ አያስቡ ምድር ላይ እሚያዩኣቸው ተራማጅ ጉንዳኖች በሙሉ ሴቶች ናቸው። ወንድ ጉንዳኖች ሁሉም መብረር እሚችሉ ናቸው።ቤትዎ ቁጭ ብለው ከየት መጣ ሳትሉት አንድ መንጋ ጉንዳን በሰልፍ ቤትወን ሊወሩት ይችላሉ። "ይህ ሁሉ ጉንዳን ከየት መጣ?" ብለው ከተገረሙ እንንገርዎት ። ጉንዳኖች በየቦታው ምግብ እሚፈላልግ ወታደር ይልካሉ። ጉንዳኖች ጣፋጭ ነገርን ይወዳሉ። በርግጥ እማይበሉት ነገር የለም ። ጣፋጭ ነገር ግን ምርጫቸው ነው። ያ ወታደር ቤት ውስጥ ምግብ ካገኘ ሌሎች ወታደሮችንም ይጠራና ወደ ቤትወ ዘመቻ ይከፍትበዎታል ማለት ነው።

እዚህ ምድር ላይ እስከ አስር ኳድሪሊዮን የሚደርሱ ጉንዳኖች አሉ። በቀላሉ መራባት ይችላሉ። ሴቷ ጉንዳን ወይም ንግስቲቱ ብዙ አመት መኖር ስትችል በሚልዮን የሚቆጠር ጉንዳኖችን መፈልፈል ትችላለች።

ከሰወች ጋር በ ratio ስናስቀምጥ ለአንድ ሰው አንድ ሚልዮን ጉንዳን ማለት ነው። ጉንዳኖች ይታመማሉ። ባውቨሪያ ባሲያና የተሰኘውን የፈንገስ ዘር ከነኩት ዘሩ ሰውነታቸው ላይ ተራብቶ ህመም ላይ ይጥላቸዋል። በርግጥ ጉንዳኖች ሀኪም አላቸው። ይህን ፈንገስ ግን ፈንገስን እሚገድል ጥቂት ኬሚካል ከጠጡ ይድናሉ።

ጉንዳኖች በግዛት ጦርነት ይገጥማሉ። በጦርነቱ ወቅት የቆሰሉት ጉንዳኖች የእርዳታ signal (ምልክት) ይልካሉ። ወዲያው ሀኪም ጉንዳኖች ደርሰው ያክሟቸዋል። መዳን እማይችሉ ከሆኑ ግን ሀኪሞች አይረዷቸውም።

እንደ reddit ገለፃ ከሆነ ጉንዳኖች ሲሞቱ የሰው ልጅ ሊሰማው የሚችልን ጩኸት ይጮሀሉ ወይም ድምፅ ያሰማሉ።

ለዛሬ በዚህ እናበቃለን ሌላ ጊዜ በሌላ ፍጥረት እንገናኛለን።

@ibnuhasen

T.me/ibnuhasen
2024/07/01 07:50:38
Back to Top
HTML Embed Code: