Telegram Web Link
ከጥቂት ወራትም በኋላ ገዳማትን ሊያጠፋ ምርኮንም ሊማርክ ሠራዊቱን ሰብሰቦ ወደ ግብጽ አገር ዘመተ ወደ አባ ጳኵሚስም ገዳም በደረሰ ጊዜ አበ ምኔቱ ወደርሱ ወጥቶ እኔ ነኝ አለው ቅፍሮንያም ሰምቶ አበምኔቱን ለብቻው አግልሎ እንዲአጠምቀውና የምንኵስናንም ልብስ እንዲአለብሰው ለመነው አበ ምኔቱም እሺ በጎ አለው።

ከዚህም በኋላ ሠራዊቱ ወደ ሀገራቸው በተመለሱ ጊዜ ብቻውን ቀረ በዚያንም ጊዜ የምንኵስናን ልብስ ለበሰ ተጋድሎውንም በመጾምና በመጸለይ ጀመረ። ሰይጣንም በእርሱ ላይ ቀንቶ ነገረ ሠሪ አስነሣበት በመኳንንቱም ዘንድ ወነጀለው እነርሱም አገራችንን ያጠፋ የመኰንን ልጅ ከዚህ አለ ብለው ገዳሙን ከበቡ #እግዚአብሔርም ሠወረው በአጡትም ጊዜ ነገረ ሠሪውን ገደሉት።

ይህም ቅዱስ በገድል ተጠምዶ ኖረ በየሰባት ቀንም ይጾማል ያለ መራራ አደንጓሬ አይመገብም። በዚያም ወራት የምድር አውሬ እንስሶቻቸውን እየገደለ በገዳሙ ላይ ጥፋትን አደረሰ አባ ቅፍሮንያም ወደርሱ መጥቶ እንደ በግ ይዞ አሠረው ዐሥር ዓመትም ቆይቶ ሞተ።

ቅዱስ ቅፍሮንያም የ #እግዚአብሔር መልአክ እየመራው ወደ ኢየሩሳሌም ሔደ በአንዲትም ቀን ደረሰ በዚያም ታላቅ ምሥጢርን አየ ከከበሩ ቦታዎችም ተባርኮ ወደ መኖሪያው ተመልሶ በሰላም አረፈ።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ኪሩቤል፣ በቅዱሳን መላዕክት እና ሰማዕታት አማላጅነት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን ።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ኅዳር_8#ከዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ እና #ከገድላት_አንደበት)
"በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።

እንኳን #ለዘመነ_አስተምህ(ሕ)ሮ_የመጀመርያ_ሳምንት ለዕለተ እሑድ እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።

#የዚህ_ሳምንት_መዝሙር፦ ሃሌ ሉያ በ፰ " #ኢትዘኪሮ_አበሳነ ዚአነ ፍጹመ ኢኀደገነ ፍጹመ ንማስን #ኄር_እግዚአብሔር_አዘዞሙ_ሙሴ ለሕዝብ ያክብሩ ሰንበተ ጽድቅ"። ትርጉም፦ #ቸር_እግዚአብሔር በደላችንን ሳያስብ ፈጽሞ እንጠፋ ዘንድ አልተወንም፤ በእውነት ሕዝብህ #ሰንበትን_ያክብሩ_ብሎ_ሙሴን አዘዘው። #ሊቁ_ቅዱስ_ያሬድ_በድጓው_ላይ

#ዘመነ_አስተምሕሮ፦ ይህ ዘመን አስተምሕሮ ከኅዳር ፮ (6) እስከ ታኅሣሥ 7 (13) ፯ (፲፫) ያለው ወቅት ሲሆን አስተምሕሮ ማለት ኹለት ትርጉም አለው፤ ይኸውም በመሐሩ "ሐ" (አስተምሕሮ) በሚለው ከተጻፈ ምሕላ፣ ምልጃና፣ ልመና፣ ይቅርታ ማለት ነው። ይህም "መሐሪ" ይቅር አለ በደልን ተወ፤ ወይም አስተምሕሮ ስለ #እግዚአብሔር ቸርነትና ርኅራኄ የምንመሰክርበት እርሱ በደላችንን ሁሉ ይቅር ብሎ ሊታረቀን በሰማይ መውረዱን ከድንግል #ማርያም መወለዱን የምናዘክርበት እንዲሁም እርሱ ይቅር እንዳለን ተገንዝበን እኛም እርስ በእርሳችን ይቅር መባባል እንደሚገባን ትምህርት የሚሰጥበት ወቅት ነው። በተለይ ይህ ዘመነ አስተምሕሮ ቤተ ክርስቲያን ስለ ልጆቿ ምልጃ የምታቀርብበት ምዕመናንንም ስለ በደላቸው ይቅርታ የሚጠይቁበት ዘመን ነው።

በሃሌታው "ሀ" (አስተምህሮ) በሚለው ከተጻፈ ትምህርት ሥርዓት ማለት ነው፤ አስተምህሮ የሚለው ቃል "መሀረ" አስተማረ፣ መከረ፣ ዘከረ ከሚለው ሥርወ ግሥ የተገኘ ነው ይኸውም የ #እግዚአብሔር ቸርነት፣ ርኅራኄ፣ ትዕግሥትና የማዳን ሥራው በቤተ ክርስቲያን በስፋት የሚሰበክበት ጊዜ ስለኾነ ወቅቱ ዘመነ አስተምህሮ ተብሏል የሥርዓትና የትምህርት ወቅት ማለት ነው። "ፊደል አይቀነስም" ብለው ሊቃውንቱ የሚሟገቱት ከዚህ የተነሣ ነው፤ እነዚህ ተመሳሳይ ድምጽ ያላቸው ፊደላት በአገባባቸው ሰፊ የትርጉም ለውጥ ሊያመጡ ይችላሉና። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ዘመነ አከፋፈል መሠረት ከኅዳር ፮ (6) እስከ ታኅሣሥ 7 (13) ፯ (፲፫) ቀን ድረስ ያለው ወቅት ዘመነ አስተምሕሮ ተብሎ ይጠራል።

በዘመነ አስተምሕሮ የ #እግዚአብሔርን ቸርነት፣ ታጋሽነት፣ ይቅር ባይነት በየጊዜው የሰዎችን በደል ሳይመለከት የቸርነቱን ሥራ መሥራቱን፣ ለሰዎች የዕረፍት ቀን እንዲሆን ሰንበትን መቀደሱ ይታሰባል። በተለይ ደግሞ ቅዱሳን ነቢያት ስለ #ክርስቶስ መምጣት የቆጠሩት ሱባኤ፣ የመሰሉት ምሳሌ፣ የተናገሩት ትንቢት፣ የጸለዩት ጸሎት የጾሙት ጾም የሚዘከርበት ሰሞን ነው።
#ኅዳር_8_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇🌹
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ማቴዎስ 6
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵ ስትጸልዩም እንደ ግብዞች አትሁኑ፤ ለሰው ይታዩ ዘንድ በምኩራብና በመንገድ ማዕዘን ቆመው መጸለይን ይወዳሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋቸውን ተቀብለዋል።
⁶ አንተ ግን ስትጸልይ፥ ወደ እልፍኝህ ግባ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል።
⁷ አሕዛብም በመናገራቸው ብዛት እንዲሰሙ ይመስላቸዋልና ስትጸልዩ እንደ እነርሱ በከንቱ አትድገሙ።
⁸ ስለዚህ አትምሰሉአቸው፤ ሳትለምኑት አባታችሁ የሚያስፈልጋችሁን ያውቃልና።
⁹ እንግዲህ እናንተስ እንዲህ ጸልዩ፦ በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፥
¹⁰ ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፤
¹¹ የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን፤
¹² እኛም ደግሞ የበደሉንን ይቅር እንደምንል በደላችንን ይቅር በለን፤
¹³ ከክፉም አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን፤ መንግሥት ያንተ ናትና ኃይልም ክብርም ለዘለዓለሙ፤ አሜን።
¹⁴ ለሰዎች ኃጢአታቸውን ይቅር ብትሉ፥ የሰማዩ አባታችሁ እናንተን ደግሞ ይቅር ይላችኋልና፤
¹⁵ ለሰዎች ግን ኃጢአታቸውን ይቅር ባትሉ፥ አባታችሁም ኃጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም።
¹⁶ ስትጦሙም፥ እንደ ግብዞች አትጠውልጉ፤ ለሰዎች እንደ ጦመኛ ሊታዩ ፊታቸውን ያጠፋሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋቸውን ተቀብለዋል።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ 🌹
"በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።

                         
#የዕለቱ_አንገርጋሪ_ግእዝ_ዜማ፦ ሃሌ ሉያ "#ሶበሰ_ይወርዱ_መላእክት እምሰማይ ዲበ ምድር አልቦሙ ድምጽ ወኢይሰማዕ ድምጸ ክነፊሆሙ፤ አልቦ አሠር ለምክያዳተ እገሪሆሙ፤ ይቀልል ሩጸቶሙ እምነፋሳት"። ትርጉም፦ #መላክት_ከሰማይ ወደ ምድር በሚወርዱበት ጊዜ ጽምጽ የላቸውም፤ የክንፎቻቸውን ድምጽ አይሰማም፤ ለእግሮቻቸውም አረጋገጥ ኮቴ ፍለጋ የለውም፤ ሩጫቸው ከነፋሳት ይፈጥናል"። #ሊቁ_ቅዱስ_ያሬድ_በድጓው_ላይ

"በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።

                            
"#ሰላም_ለ፬እንስሳሁ_ለአብ_እለ_ይጸውሩ መንበሮ እለ ስሞሙ #አግርሜስ_ገጸ_አንበሳ#አግርሜጥር_ገጸ_ሰብእ#ባርቲና_ገጸ_ላሕም#አርጣን_ገጸ_ንስር። ለቀዳማዊ ገጹ ከመ አንበሳ፤ በአምሳለ #ፈጣሪሁ_ዘውእቱ_አብ። ለካልዕ ገጹ ከመ ሰብእ #በአምሳለ_ወልድ፤ ዘውእቱ ነሥአ ፍጹመ ስባኤ። ለሣልስ ገጹ ከመ ንስር #በአምሳለ_መንፈስ_ቅዱስ ዘውእቱ አስተርአየ በርእየተ ርግብ በሥጋ። ወራብእ ገጹ ከመ ላሕም #በአምሳለ_ቅድስት_ቤተ_ክርስቲያን፤ እስመ ፬ቱ መኣዝኒሃ"። ትርጉም፦ #የአብ_ዙፋኑን_ለሚሸከሙና ስማቸው #የአንበሳ_መልክ_ያለው_አግርሜስ#የሰው_መልክ_ያለው_አግርሜጥር#የላም_መልክ_ያለው_ባርቲና#የንስር_መልክ_ያለው_አርጣን ለተባሉ #ለአራቱ እንስሳ ሰላምታ ይገባል፤ የመዠመርያው ፊት እንደ_አንበሳ_ነው፤ ያውም #በፈጣሪው_በአብ ምሳሌ ነው፤ የኹለተኛውም ፊቱ ያውም ፍጹም ሰውነትን ገንዘብ ባደረገ #በወልድ_አምሳል_እንደ_ሰው_ነው፤ የሦስተኛውም ፊቱ ያውም አካል ባለው #ርግብ_አምሳል_በተገለጠ_መንፈስ_ቅዱስ_አምሳል እንደንስር ነው፤ ያራተኛውም ፊቱ እንደ ላም ነው፤ #በቅድስት_ቤተ_ክርስቲያን_ምሳሌ፤ መኣዝኗ አራት ናቸውና። #ሊቁ_አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ_በተአምኆ_ቅዱሳን_ላይ
   
#ኅዳር_9

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ኅዳር ዘጠኝ በዚህችም ቀን ሃይማኖታቸው የቀና #318ቱ_ቅዱሳን_አበው_ሊቃውንት_በኒቅያ አርዮስን ያወገዙበት ዕለት ነው፤ የእስክንድርያ አገር አርባ አንደኛ ሊቃ ጳጳሳት #ቅዱስ_አባት_ይስሐቅ አረፈ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ጉባኤ_ኒቅያ

ኅዳር ዘጠኝ በዚህችም ቀን የሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት ኤጲስቆጶሳት ስብሰባ በኒቅያ ከተማ በጻድቅ ንጉሥ በቈስጠንጢኖስ ዘመን ሆነ። ከእርሳቸውም ጋራ አራቱ ሊቃነ ጳጳሳት አሉ እሊህም አባ እለእስክንድሮስ የእስክንድርያ አባ ዮናክንዲኖስ የሮሜ አገር አባ ሶል ጴጥሮስ የቊስጥንጥንያና የአንጾኪያም ሊቀ ጳጳሳት አባ ኤዎስጣቴዎስ ናቸው። ስብስባቸውም የሆነበት ምክንያት በእስክንድርያ አገር ቄስ ሁኖ ስለ ነበረው ስለ አር*ዮስ ነው። እርሱ ስቶ የክብር ባለቤት #ወልድን በመለኮቱ ፍጡር ነው በማለቱ ነው።

ከእሊህም ቅዱሳን ተጋዳዮች አባቶች ከውስጣቸው እንደ ሐዋርያት ሙታንን ያስነሡ በሽተኞችን የሚፈውሱ ድንቆች ተአምራትን የሚያደርጉ አሉ ብዙ ዘመናትም ስለ ቀናች ሃይማኖት የተሠቃዩ አሉ። ከእርሳቸውም የእጃቸውንና የእግራቸውን ጥፍሮች ያወለቋቸው አሉ ዳግመኛም እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን የቆረጧቸው አሉ። ጥርሶቻቸውን የሰበሩአቸውና ጐናቸውን የሠነጠቋቸውም አሉ።

ከውስጣቸውም ስሙ ቶማስ የሚባል የሀገረ መርዓስ ኤጲስቆጶስ አለ ከሀድ*ያንም ሃያ ሁለት ዓመት አሥረው ርኅራኄ የሌለውን ሥቃይ አሠቃዩት በየዓመቱም ወደርሱ በመግባት ከሕዋሳቱ አንዱን ይቆርጣሉ እንዲሁም በማድረግ እጆቹን እግሮቹን ከንፈሮቹን አፍንጫውን ጆሮዎቹንም ቆርጠው ጨረሱ። ጥርሶቹንም ሰበሩ በእሳትም ተለብልቦ እንደ ጠቆረ ግንድ አደረጉት የርሱ ወገኖችም እንደሞተ አስበው እንደ ሌሎች ሰማዕታት በየዓመቱ መታሰቢያውን አደረጉ።

እሊህ አባቶችም ወደ ኒቅያ ከተማ በደረሱ ጊዜ ንጉሥ ቁስጠንጢኖስ ታላቅና ሰፊ የሆነ መሰብሰቢያ አዳራሽ አዘጋጀላቸው በውስጡም ለየአንዳንዳቸው ወንበሮችን አኖረ የእርሱንም ወንበር ከእነርሱ ወንበሮች ዝቅተኛ አደረገ መሳለምን በመርዓስ ኤጲስቆጶስ በቅዱስ ቶማስ ጀመረ ሰገደለት ሕዋሳቶቹ ከተቆረጡበት ላይ ተሳለመው። እንዲሁም አባቶችን ሁሉንም ተሳለማቸው። ከዚህም በኋላ በትረ መንግሥቱን ሰይፉን ቀለበቱን ሰጣቸውና እንዲህ አላቸው እነሆ አሁን በካህናት ሁሉና በመንግሥት ላይ ሃይማኖቱ እንደናንተ የቀና ከሆነ ታኖሩት ዘንድ ሃይማኖቱ የቀና ካልሆነ ግን ከምእመናን ለይታችሁ ታሳድ*ዱት ዘንድ ሥልጣንን ሰጠኋችሁ።

እነርሱም ሕግንና ሥርዓትን ሠሩ ክብር ይግባውና #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስም በመካከላቸው ይቀመጥ ነበር ልቡናቸው በ #መንፈስ_ቅዱስ የበራላቸው ሰዎች አይተውታልና በሚቆጥሩአቸው ጊዜ ግን ሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት ቁጥር ሁነው ያገኙአቸዋል።

ከዚህም በኋላ ለካህናትና ለሕዝባውያን ለነገሥታት ለመሳፍንት ለሚገዙና ለሚሸጡ ነጋዴዎች ለድኆችም ለሽማግሎችና ለጐልማሶች ለሙት ልጆችም ለወንድና ለሴት ሥርዓትን ሠሩ። ከዚህም በኋላ #ወልድ በመለኮቱ ከ #አብ ጋር ትክክል እንደሆነ እያስረዱ የቀናች ሃይማኖትን አስተማሩ የተረገመ አርዮ*ስንና በረከሰች ትምህርቱ የሚያምነውን አው*ግዘው ለዩ።

የሠሩዋት ያስተማሩዋትም የሃይማኖት ትምህርት ይቺ ናት እንዲህ ብለው ሁሉን በያዘ ሰማይና ምድርን የሚታይና የማይታየውን በፈጠረ በአንድ አምላክ በ #እግዚአብሔር_አብ እናምናለን። ዓለም ሳይፈጠር ከእርሱ ጋር በነበረ የ #አብ አንድ ልጁ በሚሆን በአንድ #ጌታ_በኢየሱስ_ክርስቶስም እናምናለን።

ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ከእውነተኛ አምላክ የተገኘ አምላክ የተፈጠረ ያይደለ የተወለደ በመለኮቱ ከ #አብ ጋር የሚተካከል። ሁሉ በርሱ የሆነ ያለ እርሱ ግን ምንም ምን የሆነ የሌለ በሰማይም ያለ በምድርም ያለ። ስለእኛ ስለ ሰው ስለ መዳናችን ከሰማይ ወረደ በግብረ #መንፈስ_ቅዱስ ከቅድስት ድንግል #ማርያም ፈጽሞ ሰው ሆነ።

ሰው ሆኖ በጰንጤናዊ ጲላጦስ ዘመን ስለ እኛ ተሰቀለ ታመመ ሞተ ተቀበረም በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ በቅዱሳት መጻሕፍት እንደተጻፈ። በክብር ወደ ሰማይ ዐረገ በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ ዳግመኛም ሕያዋንንና ሙታንን ይገዛ ዘንድ በጌትነት ይመጣል ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም።

ከዚህም በኋላ የ #መንፈስ_ቅዱስ ጠላት ስለሚሆን ስለመቅ**ዶንዮስ በቊስጥንጥንያ ከተማ መቶ ሃምሳው ኤጲስቆጶሳት በተሰበሰቡ ጊዜ ከዚህ የቀረውን ሠሩ። እንዲህም አሉ #ጌታ ማሕየዊ በሚሆን ከ #አብ በሠረፀ በ #መንፈስ_ቅዱስም እናምናለን እንሰግድለት እናመሰግነውም ዘንድ ከ #አብና#ወልድ ጋራ በነቢያት የተናገረ። ከሁሉ በላይ በምትሆን ሐዋርያት በሰበሰብዋት በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም እናምናለን። ኃጢአትን ለማስተሥረይ በአንዲት ጥምቀትም እናምናለን ። የሙታንንም መነሣት የሚመጣውንም ሕይወት ተስፋ እናደርጋለን።

እሊህም አባቶቻችን ይችን የሃይማኖት ትምህርት ምእመናን ሁሉ በቀንም በሌሊትም በጸሎታቸው ጊዜ እንዲአነቡዋት በቅዳሴም ጊዜ እንዲጸልዩባት አዘዙ ወንዶችና ሴቶች ሽማግሎችና ልጆች አገልጋዮችም ሁሉ እንዲማሩዋት አዘዙ። ሠርተው ወስነው ለቤተ ክርስቲያን የሃይማኖትን ፋና ከአቆሙላት በኋላ ወደ የሀገራቸው በፍቅር አንድነት ተመለሱ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_አባት_ይስሐቅ

ዳግመኛም በዚህች ዕለት ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት አርባ አንደኛ የእስክንድርያ አገር ሊቃ ጳጳሳት ቅዱስ አባት ይስሐቅ አረፈ።

ይህም ቅዱስ ቡርልስ ከሚባል አገር ነው ወላጆቹም #እግዚአብሔርን የሚፈሩ እጅግም ባለጸጎች ናቸው ከረጅም ዘመንም በኋላ ይህን ቅዱስ በወለዱት ጊዜ በታላቅ ደስታ ደስ ተሰኙበት። ከዚህም በኋላ ያጠምቀው ዘንድ ወደ ኤጲስቆጶስ በአቀረቡት ጊዜ ኤጲስቆጶሱም ሲያጠምቀው በሕፃኑ ራስ ላይ የብርሃን #መስቀልን አየ በዚያንም ጊዜ የሕፃኑን እጅ ይዞ በራሱ ላይ አኖረ። እንዲህም ብሎ ትንቢት ተናገረለት ይህ ሕፃን በ #እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ላይ ይሾማል አባቱንም እንዲህ አለው ይህን ልጅ ጠብቀው እርሱ ለ #እግዚአብሔር የተመረጠ መሣሪያ ይሆናልና።

ጥቂትም በአደገ ጊዜ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርትና ጽሕፈትን አስተማሩት የቅዱሳንንም ዜና የሚያነብ ሆነ ወላጆቹንም ትቶ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሔደ በአበ ምኔቱ በአባ ዘካርያስም ዘንድ መንኩሶ በገድል ተጠመደ።

በአንዲትም ዕለት አንድ ጻድቅ ሰው በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አየው በእርሱም ላይ ይስሐቅ በ #ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ላይ ይሾም ዘንድ አለው ብሎ ትንቢት ተናገረ።

በዚያም ወራት ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሐንስ ጸሐፊ የሚሆነውና የሚረዳው ብልህ ሰው ፈለገ ስለ አባ ይስሐቅም ነገሩት እርሱም መልእክተኞችን ልኮ ወደርሱ አስመጣው ይጽፍለትም ዘንድ ደብዳቤ ሰጠው እርሱ ግን አባ ይስሐቅ እያወቀ ጽሕፈቱን አበላሽ ሊቀ ጳጳሳቱ እንዲተወውና ወደ አስቄጥስ ገዳም እንዲመለስ ነበር የዚህን ዓለም ክብር ይጠላልና።

ሊቀ ጳጳሳቱም እንዲተወውና እንዲአሰናብተው አውቆ ማበላሸቱን በአወቀ ጊዜ በጥሩ ጽፈሃል ከዚህም እንድትሔድ እኔ አልተውህም አለው አባ ይስሐቅም እንደማይለቀው አውቆ የሚያውቀውን ሁሉ ጥበቡን ያማረ ጽሕፈቱንም ገለጠለት ሊቀ ጳጳሳቱም በእርሱ እጅግ ደስ አለው ።
ከጥቂት ወራትም በኋላ አባ ይስሐቅ ወደ አስቄጥስ ገዳም ተመለሰ አባ ዮሐንስም የሚያርፍበት ቀን በደረሰ ጊዜ ስለርሱ ሊቀ ጵጵስና የሚሾም ማን እንደሆነ ያስረዳው ዘንድ ክብር ይግባውና #ጌታችንን_ኢየሱስ_ክርስቶስን ለመነው #ጌታም በራእይ ከአንተ በኋላ ለዚች ሹመት የሚጠቅም ረዳትህ ይስሐቅ ነው አለው።

ከዚህም በኋላ ሕዝቡን ጠራቸውና ከእርሱ በኋላ ሊቀ ጳጳሳት ሁኖ የሚሾም ረዳቱ ይስሐቅ እንደሆነ አስረዳቸው ከዚህም በኋላ አባ ዮሐንስ በአረፈ ጊዜ ይህን ቅዱስ አባት ይስሐቅን ይዘው በእስክንድርያ አገር ላይ ሊቀ ጳጳሳት አድርገው ሾሙት በዘመኑም ቤተ ክርስቲያን ብርሃን ሆነች ብዙዎች አብያተ ክርስቲያንንም አደሳቸው ይልቁንም የወንጌላዊ ማርቆስን ቤተ ክርስቲያን አሳምሮ አደሳት የሊቀ ጵጵስናውንም ቤት አደሰ ።

ይህንንም አባት ብዙ ችግርና መከራ ደርሶበታል በወንጌላዊ ማርቆስ መንበርም ሰባት ዓመት ተኩል ኑሮ አረፈ። በዚህም ቅዱስ አባት በመጽሐፈ ገድሉ ከእሑድ ቀን በቀር ሊቀ ጳጳሳት እንዳይሾም የሚያዝ ጽሑፍ አለ።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን አባቶች ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ኅዳር_9)
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ኅዳር_9_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ቆላስይስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵ በሥጋ ምንም እንኳ ብርቅ፥ በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝና፥ ሥርዓታችሁንም በክርስቶስም ያለውን የእምነታችሁን ጽናት እያየሁ ደስ ይለኛል።
⁶ እንግዲህ ጌታን ክርስቶስ ኢየሱስን እንደ ተቀበላችሁት በእርሱ ተመላለሱ፤
⁷ ሥር ሰዳችሁ በእርሱ ታነጹ፥ እንደ ተማራችሁም በሃይማኖት ጽኑ፥ ምስጋናም ይብዛላችሁ።
⁸ እንደ ክርስቶስ ትምህርት ሳይሆን፥ እንደ ሰው ወግና እንደ ዓለማዊ እንደ መጀመሪያ ትምህርት ባለ በፍልስፍና በከንቱም መታለል ማንም እንዳይማርካችሁ ተጠበቁ።
⁹ በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤
¹⁰ ለአለቅነትና ለሥልጣንም ሁሉ ራስ በሆነ በእርሱ ሆናችሁ ተሞልታችኋል።
¹¹ የሥጋንም ሰውነት በመገፈፍ፥ በክርስቶስ መገረዝ፥ በእጅ ባልተደረገ መገረዝ በእርሱ ሆናችሁ ደግሞ ተገረዛችሁ፤
¹² በጥምቀትም ከእርሱ ጋር ተቀብራችሁ፥ በጥምቀት ደግሞ፥ ከሙታን ባስነሣው በእግዚአብሔር አሠራር በማመናችሁ፥ ከእርሱ ጋር ተነሣችሁ።
¹³ እናንተም በበደላችሁና ሥጋችሁን ባለመገረዝ ሙታን በሆናችሁ ጊዜ፥ ከእርሱ ጋር ሕይወትን ሰጣችሁ፤ በደላችሁን ሁሉ ይቅር አላችሁ፤
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
2ኛ ዮሐንስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁶ እንደ ትእዛዛቱም እንሄድ ዘንድ ይህ ፍቅር ነው፤ ከመጀመሪያ እንደ ሰማችሁ፥ በእርስዋ ትሄዱ ዘንድ ትእዛዙ ይህች ናት።
⁷ ብዙ አሳቾች ወደ ዓለም ገብተዋልና እነርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የማያምኑ ናቸው፤ ይህ አሳቹና የክርስቶስ ተቃዋሚው ነው።
⁸ ሙሉ ደመወዝን እንድትቀበሉ እንጂ የሠራችሁትን እንዳታጠፉ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።
⁹ ለሚወጣ ሁሉ በክርስቶስም ትምህርት ለማይኖር ሰው አምላክ የለውም፤ በክርስቶስ ትምህርት ለሚኖር አብና ወልድ አሉት።
¹⁰ ማንም ወደ እናንተ ቢመጣ ይህንም ትምህርት ባያመጣ በቤታችሁ አትቀበሉት ሰላምም አትበሉት፤
¹¹ ሰላም የሚለው ሰው በክፉ ሥራው ይካፈላልና።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 15
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²² ያን ጊዜ ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ከቤተ ክርስቲያኑ ሁሉ ጋር ከእነርሱ የተመረጡትን ሰዎች ከጳውሎስና ከበርናባስ ጋር ወደ አንጾኪያ ይልኩ ዘንድ ፈቀዱ፤ እነርሱም በወንድሞች መካከል ዋናዎች ሆነው በርስያን የተባለው ይሁዳና ሲላስ ነበሩ።
²³ እንዲህም ጽፈው በእነርሱ እጅ ላኩ። ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ወንድሞችም በአንጾኪያና በሶርያ በኪልቅያም ለሚኖሩ ከአሕዛብ ወገን ለሆኑ ወንድሞች ሰላምታ ያቀርባሉ።
²⁴ ያላዘዝናቸው ሰዎች ከእኛ ወጥተው፦ ትገረዙ ዘንድና ሕግን ትጠብቁ ዘንድ ይገባችኋል ብለው ልባችሁን እያወኩ በቃል እንዳናወጡአችሁ ስለ ሰማን፥
²⁵-²⁶ ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነፍሳቸውን ከሰጡት ከምንወዳቸው ከበርናባስና ከጳውሎስ ጋር የተመረጡትን ሰዎች ወደ እናንተ እንልክ ዘንድ በአንድ ልብ ሆነን ፈቀድን።
²⁷ ራሳቸውም ደግሞ በቃላቸው ያንኑ ይነግሩአችሁ ዘንድ ይሁዳንና ሲላስን ልከናል።
²⁸-²⁹ ለጣዖት ከተሠዋ፥ ከደምም፥ ከታነቀም፥ ከዝሙትም ትርቁ ዘንድ ከዚህ ከሚያስፈልገው በቀር ሌላ ሸክም እንዳንጭንባችሁ እኛና መንፈስ ቅዱስ ፈቅደናልና፤ ከዚህም ሁሉ ራሳችሁን ብትጠብቁ በመልካም ትኖራላችሁ። ጤና ይስጣችሁ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#ኅዳር_9_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇

✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"ወነበቡ ዓመፃ ውስተ ዓርያም።  ወአንበሩ ውስተ አፉሆሙ። ወአንሶሰወ ውስተ ምድር ልሳኖሙ"። መዝ. 72፥8-9።
"አስበው ክፉ ነገርን ተናገሩ፤ ከፍ ከፍ ብለውም በዓመፃ ተናገሩ። አፋቸውን በሰማይ አኖሩ፥ አንደበታቸውም በምድር ውስጥ ተመላለሰ"። መዝ. 72፥8-9።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#ኅዳር_9_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ዮሐንስ 10
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁵ ኢየሱስም መለሰላቸው፥ እንዲህ ሲል፦ ነገርኋችሁ አታምኑምም እኔ በአባቴ ስም የማደርገው ሥራ ይህ ስለ እኔ ይመሰክራል፤
²⁶ እናንተ ግን እንደ ነገርኋችሁ ከበጎቼ ስላልሆናችሁ አታምኑም።
²⁷ በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ እኔም አውቃቸዋለሁ ይከተሉኝማል፤
²⁸ እኔም የዘላለም ሕይወትን እሰጣቸዋለሁ፥ ለዘላለምም አይጠፉም፥ ከእጄም ማንም አይነጥቃቸውም።
²⁹ የሰጠኝ አባቴ ከሁሉ ይበልጣል፥ ከአባቴም እጅ ሊነጥቃቸው ማንም አይችልም።
³⁰ እኔና አብ አንድ ነን።
³¹ አይሁድ ሊወግሩት ደግመው ድንጋይ አነሡ።
³² ኢየሱስ፦ ከአባቴ ብዙ መልካም ሥራ አሳየኋችሁ፤ ከእነርሱ ስለ ማናቸው ሥራ ትወግሩኛላችሁ? ብሎ መለሰላቸው።
³³ አይሁድም፦ ስለ መልካም ሥራ አንወግርህም፤ ስለ ስድብ፤ አንተም ሰው ስትሆን ራስህን አምላክ ስለ ማድረግህ ነው እንጂ ብለው መለሱለት።
³⁴ ኢየሱስም እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፦ እኔ፦ አማልክት ናችሁ አልሁ ተብሎ በሕጋችሁ የተጻፈ አይደለምን?
³⁵ መጽሐፉ ሊሻር አይቻልምና እነዚያን የእግዚአብሔር ቃል የመጣላቸውን አማልክት ካላቸው፥
³⁶ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ስላልሁ እናንተ አብ የቀደሰውን ወደ ዓለምም የላከውን፦ ትሳደባለህ ትሉታላችሁን?
³⁷ እኔ የአባቴን ሥራ ባላደርግ አትመኑኝ፤
³⁸ ባደርገው ግን፥ እኔን ስንኳ ባታምኑ አብ በእኔ እንደ ሆነ እኔም በአብ እንደ ሆንሁ ታውቁና ታስተውሉ ዘንድ ሥራውን እመኑ።
³⁹ እንግዲህ ደግመው ሊይዙት ፈለጉ፤ ከእጃቸውም ወጣ።
⁴⁰ ዮሐንስም በመጀመሪያ ያጠምቅበት ወደ ነበረው ስፍራ ወደ ዮርዳኖስ ማዶ እንደ ገና ሄደ በዚያም ኖረ።
⁴¹ ብዙ ሰዎችም ወደ እርሱ መጥተው፦ ዮሐንስ አንድ ምልክት ስንኳ አላደረገም፥ ነገር ግን ዮሐንስ ስለዚህ ሰው የተናገረው ሁሉ እውነት ነበረ አሉ።
⁴² በዚያም ብዙዎች በእርሱ አመኑ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ የሚቀደሰው ቅዳሴ የ #ሠለስቱ_ምዕት_ቅዳሴ ነው። መልካም የሠለስቱ ምዕት በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"#ሠለስቱ_ምዕት_ዐሠርቱ_ወሰመንቱ_ሃይማኖተ እለ ከሠቱ መጋብያነ ምሥጢር #ለመንፈስ_ቅዱስ_ቤቱ፣ በሲኖዶሶሙ ጥቅመ ኃጢአት ነሠቱ፣ ዐላውያን አእትቱ"። ትርጉም፦ #የመንፈስ_ቅዱስ_ማደርያው_ሃይማኖታዊ ምስጢርን የሚመግቡ፣ ሃይማኖትን ገልጠው ያብራሩ #ሦስት_መቶ_ዐሥራ_ስምንት_ሊቃውንት፣ በጉባኤያቸው የኑፋቄ ሕንጻን አፈረሱ መንናፍቃንንም አስወገዱ። #ሊቁ_ቅዱስ_ያሬድ_በድጓው
  
#ኅዳር_10

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ኅዳር ዐሥር በዚህች ቀን ቅዱሳት ንጹሐት መነኰሳይያት ደናግል እናታቸው #ቅድስት_ሶፍያም በሰማዕትነት አረፉ፤ ቅዱሳን አባቶቻችን ስለ ጾም ሥርዓት የአንድነት ስብሰባ አድርገው #የቅዱስ_ዲሜጥሮስን_ቀመር_አቡሻህርን በሁሉም ዘንድ እንዲጠቀሙበት በጉባኤ ወሰኑ፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅድስት_ሶፍያ

ኅዳር ዐሥር በህች ቀን ቅዱሳት ንጹሐት መነኰሳይያት ደናግል እናታቸው ሶፍያም በሰማዕትነት አረፉ። እሊህም ቅዱሳት ከተለያዩ አገሮችና ቦታዎች ሲሆኑ መለኮታዊ ፍቅር በአንድነት ሰበሰባቸው የምንኲስናንም ልብስ ለበሱ ይኸውም የመላእክት ልብስ ነው። በሮሜ አገር ከአሉ ገዳማትም በአንዱ የሚኖሩ ሆኑ ቅድስት ሶፍያም በእነርሱ ላይ እመ ምኔት ሆነች።

እርሷም ጸጋንና ዕውቀትን የተመላች ናት የቅዱሳን መነኰሳትን ገድል በማንበብ እየጾሙ እየጸለዩ በምድር ላይ እንደ መላእክት እስከ ሆኑ ድረስ መንፈሳዊ ዕድገትን አሳደገቻቸው ከእነርሱም በአንድ ገዳም ውስጥ ሰባ ዓመት ያህል የኖሩ አሉ ከውስጣቸውም ልጅ እግሮች የሆኑ አሉ።

ከሀዲ ንጉሥ ዑልያኖስም ከፋርስ ንጉሥ ከሳቦር ጋር ሊዋጋ በሮሀ ሀገር በኩል በሚያልፍ ጊዜ እርሱ ሳቦር ሊወጋው ወደርሱ እንደሚመጣ ሰምቷልና አልፎ ሲሔድም በውስጡ እሊህ ደናግል ያሉበትን ገዳም አይቶ ይህ ምንድን ነው ብሎ ጠየቀ ሰዎችም ይህ የደናግሎች ገዳም ነው አሉት።

በዚያንም ጊዜ ወደዚያ ገዳም ገብተው ደናግሎችን እንዲገድሏቸው በገዳሙ ውስጥም ያለ ገንዘባቸውን ሁሉ እንዲዘርፉ ወታደሮቹን አዘዘ ወታደሮችም ገብተው እሊያን ደናግል በሰይፍ ገደሏቸው ገዳሙንም አጠፉ የገዳሙን ገንዘብ ሁሉንም ዘረፉ።

ከሀዲውን ንጉሥ ግን ስለ መንጋዎቹ በቀል #እግዚአብሔር ተበቀለው ይህም እንዲህ ነው ያጠፋው ዘንድ ሰማዕት መርቆሬዎስን አዘዘው መርቆሬዎስም በአካለ ነፍስ ሒዶ በጦር ወጋውና በክፉ አሟሟት ሙቶ ወደ ዘላለም ሥቃይ ሔደ። እሊህ ቅዱሳት ደናግል ግን ወደ ዘላለም ተድላ ደስታ ገቡ።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በእሊህ ደናግል ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ባሕረ_ሐሳብ

በዚችም ዕለት በእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት በድሜጥሮስ ዘመን ስለ ጾም ሥርዓት ቅዱሳን ሊቃነ ጳጳሳትና የኤጲስቆጶሳት የአንድነት ስብሰባ ተደረገ። በዚህም የአንድነት ጉባኤ የመሰብሰባቸው ምክንያት እንዲህ ነው የክርስቲያን ወገኖች በጥር ዐሥራ አንድ ቀን በከበረች በጥምቀት በዓል ተጠምቀው በማግሥቱ የከበረች የአርባ ቀንን ጾም መጾም ይጀምራሉ እስከ የካቲት ሃያ ሁለት ቀንም ጾመው ጾምን ይፈታሉ።

ከዚህም በኋላ በመጋቢት በሃያ ሦስት የሕማማትን ሰሞን መጾም ይጀምራሉ በዚህም ወር በሀያ ሰባት የስቅለቱን በዓል ያከብራሉ በሃያ ዘጠኝም ክብር ይግባውና የ #መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስን የትንሣኤውን በዓል ያክብሩ ነበር።

ይህ ድሜጥሮስም በእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት ሁኖ በተሾመ ጊዜ በእርሻ የሚተዳደር መጻሕፍትን የማያውቅ ጨዋ ሰው ሲሆን #እግዚአብሔር በመለኮታዊ ስጦታው ልቡን ብሩህ አድርጎለት የብሉይንና የሐዲስ መጻሕፍትን የቤተ ክርስቲያንንም ሕግ አወቀ ከእርሳቸውም ብዙዎችን ተረጎመ።

ከዚህም በኋላ በ #መንፈስ_ቅዱስ ገላጭነት ባሕረ ሐሳብ የተባለ የዘመን ቁጥርን ጻፈ ይህም ክብር ይግባውና የ #መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ አጽዋማትና በዓላቶቹ የሚታወቁበት እሊህም የከበረች የአርባ ቀን ጾም የሆሣዕና ዑደት ስቅለቱ ትንሣኤው በአርባ ቀን ዕርገቱ ከትንሣኤውም በኋላ በኀምሳኛው ቀን #መንፈስ_ቅዱስ የወረደበት ናቸው።

ይህንንም ጽፎ ወደ ሮሜ አገር ሊቀ ጳጳሳት አባ ፊቅጦር ላከ ሁለተኛም ወደ አንጾኪያ አገር ሊቀ ጳጳሳት አባ መክሲሞስ ላከ ዳግመኛም ወደ ኢየሩሳሌም አገር ሊቀ ጳጳሳት አባ አጋብዮስ ላከ እነርሱም በአነበቧት ጊዜ እጅግ ደስ ተሰኙባት።

የሮሜ አገር ሊቀ ጳጳሳት አባ ፊቅጦርም በሮሜ አገሮች ሁሉ ያሉትን ኤጲስቆጶሳቶቹን አዋቂዎችን ብዙዎች ሊቃውንትንም ሰበሰባቸው ይህንንም የዘመን ቁጥር አስነበበላቸው እጅግ በጣም ጥሩ ሁኖ አግኝተውት ደስ ተሸኙበት በደስታም ተቀበሉት አባዝተውም በመጻፍ ለሁሉ አገሮች ላኩት እስከዚች ዕለትም ጸንቶ ተሠርቶ ኖረ። ከዚህም በኋላ ልዩ ሦስት የሆነ አንድ #እግዚአብሔርን ፈጽሞ እያመሰገኑት ወደየሀገራቸው ገቡ።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም ሥርዓትን በሰሩልን አባቶች ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ኅዳር_10)
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ኅዳር_10_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇🌹
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሮሜ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ስለዚህ፥ አንተ የምትፈርድ ሰው ሁሉ ሆይ፥ የምታመካኘው የለህም፤ በሌላው በምትፈርድበት ነገር ራስህን ትኰንናለህና፤ አንተው ፈራጁ እነዚያን ታደርጋለህና።
² እንደዚህም በሚያደርጉት ላይ የእግዚአብሔር ፍርድ እውነተኛ እንደ ሆነ እናውቃለን።
³ አንተም እንደዚህ በሚያደርጉ የምትፈርድ ያንም የምታደርግ ሰው ሆይ፥ አንተ ከእግዚአብሔር ፍርድ የምታመልጥ ይመስልሃልን?
⁴ ወይስ የእግዚአብሔር ቸርነት ወደ ንስሐ እንዲመራህ ሳታውቅ የቸርነቱንና የመቻሉን የትዕግሥቱንም ባለጠግነት ትንቃለህን?
⁵ ነገር ግን እንደ ጥንካሬህና ንስሐ እንደማይገባ ልብህ የእግዚአብሔር ቅን ፍርድ በሚገለጥበት በቍጣ ቀን ቍጣን በራስህ ላይ ታከማቻለህ።
⁶ እርሱ ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው ያስረክበዋል፤
⁷ በበጎ ሥራ በመጽናት ምስጋናንና ክብርን የማይጠፋንም ሕይወት ለሚፈልጉ የዘላለምን ሕይወት ይሰጣቸዋል፤
⁸ ለዓመፃ በሚታዘዙ እንጂ ለእውነት በማይታዘዙትና በአድመኞች ላይ ግን ቍጣና መቅሠፍት ይሆንባቸዋል።
⁹ ክፉውን በሚያደርግ ሰው ነፍስ ሁሉ መከራና ጭንቀት ይሆንበታል፥ አስቀድሞ በአይሁዳዊ ደግሞም በግሪክ ሰው፤
¹⁰ ነገር ግን በጎ ሥራ ለሚያደርጉ ሁሉ ምስጋናና ክብር ሰላምም ይሆንላቸዋል፥ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው።
¹¹ እግዚአብሔር ለሰው ፊት አያዳላምና።
¹² ያለ ሕግ ኃጢአት ያደረጉ ሁሉ ያለ ሕግ ደግሞ ይጠፋሉና፤ ሕግም ሳላቸው ኃጢአት ያደረጉ ሁሉ በሕግ ይፈረድባቸዋል፤
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
1ኛ ጴጥሮስ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹-² እንዲሁም፥ እናንተ ሚስቶች ሆይ፥ ከባሎቻችሁ አንዳንዱ ለትምህርት የማይታዘዙ ቢኖሩ፥ በፍርሃት ያለውን ንጹሑን ኑሮአችሁን እየተመለከቱ ያለ ትምህርት በሚስቶቻቸው ኑሮ እንዲገኙ ተገዙላቸው።
³ ለእናንተም ጠጕርን በመሸረብና ወርቅን በማንጠልጠል ወይም ልብስን በመጎናጸፍ በውጭ የሆነ ሽልማት አይሁንላችሁ፥
⁴ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ።
⁵ እንዲህ በቀድሞ ዘመን በእግዚአብሔር ተስፋ ያደረጉት ቅዱሳት ሴቶች ደግሞ ለባሎቻቸው ሲገዙ ተሸልመው ነበርና፤
⁶ እንዲሁም ሣራ ለአብርሃም፦ ጌታ ብላ እየጠራችው ታዘዘችለት፤ እናንተም ከሚያስደነግጥ ነገር አንዳች እንኳ ሳትፈሩ መልካም ብታደርጉ ልጆችዋ ናችሁ።
⁷ እንዲሁም፥ እናንተ ባሎች ሆይ፥ ደካማ ፍጥረት ስለ ሆኑ ከሚስቶቻችሁ ጋር በማስተዋል አብራችሁ ኑሩ፤ ጸሎታችሁ እንዳይከለከል አብረው ደግሞ የሕይወትን ጸጋ እንደሚወርሱ አድርጋችሁ አክብሩአቸው።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 17
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³⁰ እንግዲህ እግዚአብሔር ያለማወቅን ወራት አሳልፎ አሁን በየቦታቸው ንስሐ ይገቡ ዘንድ ሰውን ሁሉ ያዛል፤
³¹ ቀን ቀጥሮአልና፥ በዚያም ቀን ባዘጋጀው ሰው እጅ በዓለሙ ላይ በጽድቅ ሊፈርድ አለው፤ ስለዚህም እርሱን ከሙታን በማስነሣቱ ሁሉን አረጋግጦአል።
³² የሙታንንም ትንሣኤ በሰሙ ጊዜ እኵሌቶቹ አፌዙበት፥ እኵሌቶቹ ግን፦ ስለዚህ ነገር ሁለተኛ እንሰማሃለን አሉት።
³³ እንዲሁም ጳውሎስ ከመካከላቸው ወጣ።
³⁴ አንዳንዶች ወንዶች ግን ተባብረው አመኑ፤ ከእነርሱ ደግሞ በአርዮስፋጎስ ያለው የፍርድ ቤት ፈራጅ ዲዮናስዮስ ደማሪስ የሚሉአትም አንዲት ሴት ሌሎችም ከእነርሱ ጋር ነበሩ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#ኅዳር_10_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇🌹

✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"ወቀጻዕክዋ በጾም ለነፍስየ። ወኮነኒ ጽዕለተ። ለበስኩ ሠቀ ወኮንክዎሙ ነገረ"። መዝ 68፥10-11።
"ነፍሴን በጾም አስመረርሁአት፥ ለስድብም ሆነብኝ። ማቅ ለበስሁ ምሳሌም ሆንሁላቸው"። መዝ.68፥10-11።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#ኀዳር_10_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇🌹
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ማቴዎስ 25
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ በዚያን ጊዜ መንግሥተ ሰማያት መብራታቸውን ይዘው ሙሽራውን ሊቀበሉ የወጡ አሥር ቆነጃጅትን ትመስላለች።
² ከእነርሱም አምስቱ ሰነፎች አምስቱም ልባሞች ነበሩ።
³ ሰነፎቹ መብራታቸውን ይዘው ከእነርሱ ጋር ዘይት አልያዙምና፤
⁴ ልባሞቹ ግን ከመብራታቸው ጋር በማሰሮአቸው ዘይት ያዙ።
⁵ ሙሽራውም በዘገየ ጊዜ ሁሉ እንቅልፍ እንቅልፍ አላቸውና ተኙ።
⁶ እኩል ሌሊትም ሲሆን፦ እነሆ፥ ሙሽራው ይመጣል፥ ትቀበሉት ዘንድ ውጡ የሚል ውካታ ሆነ።
⁷ በዚያን ጊዜ እነዚያ ቆነጃጅት ሁሉ ተነሡና መብራታቸውን አዘጋጁ።
⁸ ሰነፎቹም ልባሞቹን፦ መብራታችን ሊጠፋብን ነው፤ ከዘይታችሁ ስጡን አሉአቸው።
⁹ ልባሞቹ ግን መልሰው፦ ምናልባት ለእኛና ለእናንተ ባይበቃስ፤ ይልቅስ ወደሚሸጡት ሄዳችሁ ለራሳችሁ ግዙ አሉአቸው።
¹⁰ ሊገዙም በሄዱ ጊዜ ሙሽራው መጣ፥ ተዘጋጅተው የነበሩትም ከእርሱ ጋር ወደ ሰርግ ገቡ፥ ደጁም ተዘጋ።
¹¹ በኋላም ደግሞ የቀሩቱ ቈነጃጅት መጡና፦ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ፥ ክፈትልን አሉ።
¹² እርሱ ግን መልሶ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ አላውቃችሁም አለ።
¹³ ቀኒቱንና ሰዓቲቱን አታውቁምና እንግዲህ ንቁ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
✝️✝️✝️ 🌹
 የሚቀደሰው ቅዳሴ የ #ቅዱስ_ዮሐንስ_ወልደ_ነጎድጓድ ነው። መልካም የሠላሳ ስድስቱ ቅዱሳት አንስት በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።
🌹
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
2025/01/04 03:23:40
Back to Top
HTML Embed Code: