✝ ✝ ✝
🌹 #የዕለቱ_አንገርጋሪ_ግዕዝ_ዜማ፦ ሃሌ ሉያ "#በከመ_አቡነ_አብርሃም ኢሐነጸ ቤተ ወከማሁ #አባ_ዮሐኒ ነበረ አድባረ ወበዓታተ #ገብ_ኄር ዘወውኁድ ምዕመነ ኮንከ ዲበ ብዙኅ አሰይመከ"። ትርጉም፦ #አባታችንን_አብርሃምን ቤትን እንዳልሰራ እንዲሁ #አባ_ዮሐኒ በበዓትና በተራራ ተቀመጠ #ቸር_ባርያ_አገልጋይ በጥቂት የታመንህ ሆንክ በብዙ እሾምሀለሁ"። ።
✝ ✝ ✝
🌹 "#አባ_ዮሐኒ_ጸገየ_ሕይወተ። ፈረየ ሠላሳ ወስሳ ወምእተ። #ብሔረ_ሕያዋን ተመሥጠ ግብተ። ዘዐይን ኢርዕየ ነሥአ ዕሤተ"። ትርጉም፦ #አባ_ዮሐኒ ሕይወትን አብቦ፤ ሠላሳ፣ ስሳንና፣ መቶን አፈራ፤ #ወደ_ሕያዋን አገር በድንገት ተነጥቆ ዐይን ያላየውን ዋጋ አገኘ። #ሊቁ_ቅዱስ_ያሬድ_በድጓው_ላይ
✝ ✝ ✝
🌹 "#ሶበ_ዴገነኪ_አርዌ_በሊዐ_ሕፃንኪ_ዘኀለየ። በዘትሠርሪ ገዳመ ወታፈጥኒ ጐዪየ። አመ ጸገይኪ #አክናፈ_ከመ_ዮሐኒ_ጸገየ። ብእሲተ ሰማይ #ማርያም_ዘትለብሲ_ፀሓየ። ተአምረኪ ጸሐፈ #ዮሐንስ_ዘርእየ"። ትርጉም፦ #ፀሐይን_የምትለብሺ (እውነተኛ ፀሐይ የተባለ ጌታን የወለድሽ) የሰማይ እመቤት ማርያም ሆይ ልጅሽን ለመግደል ያሰበ አውሬ ሄሮድስ በተከተለሽና ወደ በረሀ ፈጥነሽ በምትሸሺበት ጊዜ #ክንፍን_እንዳወጣ_እንደ_አባ_ዮሐኒ ክንፍን ስታወጪ ያየ #ዮሐንስ_ተአምርሽን_ጻፈ። #ሊቁቆቹ_አባ_ጽጌ_ድንግልና_አባ_ገብረ_ማርያም_በማኅሌተ_ጽጌ_ላይ።

#ኅዳር_6
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ኅዳር ስድስት ቀን ክብርት #እመቤታችን_ከተወደደ_ልጇ ጋር ደብረ ቁስቋም ገብተው ካገኛቸው ድካም ያረፉበት፣ የአረጋዊ #ቅዱስ_ዮሴፍ፣ #የቅድስት_ሰሎሜ፣ #የአባ_ጽጌ_ድንግል መታሰቢያቸው ነው፤ የሮሜ አገር ሊቀ ጳጳሳት #ቅዱስ_ፊልክስ እረፍቱ ነው።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ደብረ_ቁስቋም
ኅዳር ስድስት በዚህች ዕለት ክብርት #እመቤታችን ከተወደደ ልጇ ጋር ከስደት በሚመለሱበት ጊዜ ደብረ ቁስቋም ገብተው ካገኛቸው ድካም ዐረፉ፡፡
አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች ክብርት #እመቤታችን ከስደት በተመለሰች ጊዜ እንዲህ ሆነ፡- የብርሃን እናቱ ክብርት #እመቤታችን ልጇን ይዛ ከእነ ዮሴፍ ጋር ወደ ምድረ ግብፅ ስትሰደድ ግብፅ ደርሰው በዚያ ቢቀመጡም ነገርን ግብፅ አልተመቸቻውም፡፡ ሕዝቡም በሰላም አልተቀበላቸውም፡፡ እንዲያውም በምድረ ግብፅ ብዙ ተሠቃይተዋል፡፡ ከግብፅም ተነሥተው ወደ ኢትዮጵያ በመጡ ጊዜ ግን ኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ በሰላምና በፍቅር ተቀበላቸው፡፡ ከመንገዱና ከርሃብ ጥሙ ጽናት የተነሣ እጅግ ደክማለችና የኢትዮጵያ ሰዎች #እመቤታችንን አይተው እጅግ አዘኑላት፡፡ ‹‹ይህችስ የነገሥታት ዘር ትመሥላለች ነገር ግን አንዳች ችግር አጋጥሟት ተሰዳ ወደ ሀገራችን መጥታለች..›› ብለው እንክብካቤን አደረጉላት፡፡ እግራቸውን አጥበው በክብር ማረፊያዎች ላይ አሳረፏቸው፡፡ መልካም መስተንግዶም አደረጉላቸው፡፡ #እመቤታችንም ከድካሟ ካረፈች በኋላ ሀገሪቱን በእጅጉ ወደደቻትና የተወደደ ልጇን ‹‹ይህን ሀገርና ሕዝቧን በመላ ወድጃቸዋልሁና በዚህ እስከ መጨረሻው እንኑር›› አለችው፡፡ #ጌታችንም ክብርት እናቱን ‹‹ይህች ቅድስት ሀገር ናት፣ በኋለኛው ዘመን የቅዱሳን መነኮሳት ቦታ ትሆናለች፡፡ በውስጧም እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ እመሰገንባታለሁ፤ የአንቺም ስም ሳይጠራ አይውልባትም›› አላት፡፡
ከዚህም በኋላ #ጌታችን ደመና ጠቅሶ በእርሷ ላይ ተቀመጡ፡፡ መልአኩ ቅዱስ ዑራኤልም መጣና እየመራቸው መላ ኢትዮጵያን ጎበኟት፡፡ #እመቤታችንም ሀገሪቱንና ሕዝቦቿን ወዳቸዋለች ደስም ተሰኝታባቸዋለችና #ጌታችን ለክብርት እናቱ ‹‹ይህችን ቅድስት ሀገር አሥራት አድርጌ ሰጠሁሽ›› አላት፡፡ #እመቤታችንም እጅግ ተደስታ ‹‹ልጄ አምላኬ›› ብላ አመሰገነችው፡፡ ከዚህም በኋላ ከአንዱ ቦታ ወደ አንዱ ቦታ እየተዘዋወሩ መላዋ ኢትዮጵያን በኪደተ እግራቸው ባረኳት፡፡ #ጌታችንም ‹‹በዚህ ቦታ እንዲህ ዓይነት ቤተ ክርስቲያን ይታነጻል፤ እከሌ የሚባል እንዲህ ዓይነት ቅዱስ ይነሣል…›› እያለ ብዙ ምሥጢራትን ለክብርት እናቱ ነገራት፡፡ ከዚህም በኋላ የስደቱ ዘመን ሲያልፍ ሄሮድስም በመጨረሻ ክፉ አሟሟትን ሲሞት መልአኩ ወደ ገሊላ አውራጃ እንዲመለሱ ነገራቸው፡፡ #እመቤታችንም ‹‹ከዚህች ሀገርስ ባንሄድ እመርጣለሁ›› ስትለው የተወደደ ልጇ ግን ‹‹እናቴ ሆይ ጽድቅንና ፈቃድን ሁሉ ልንፈጽም ይገባናል›› ብሎ አጽናናትና ወደ ሀገራቸው ተመልሰው ሄዱ፡፡
ተመልሰውም ሊሄዱ ሲነሡ የኢትዮጵያ ሰዎች ልዩ ልዩ አምሐ እጅ መንሻ ሰጧቸው፡፡ ልዩ ልዩ ልብሶች፣ ወርቅ፣ ዕጣን፣ ከርቤ፣ ሽቱ እና ሥንቀቸውን በግመሎች ላይ ጭነው #እመቤታችንንና የተወደደ ልጇንም በበቅሎ ላይ አስቀምጠው በክብር ሸኟቸው፡፡ #እመቤታችንም ልጇን ታቅፋ በበቅሎ ተቀምጣ በበረሃው በመጓዝ ወደ መጣችበት አገር ሄደች፡፡ ኢትዮጵያንም የሰጧትን ብዙ እጅ መንሻዎች በግመሎች ጭና ይዛ ወደ አገሯ በተመለሰች ጊዜ ከአንድ ባሕር ዳር ደረሰች፡፡ ከዚያም የጀልባውን ባለቤት ‹‹ #እግዚአብሔርን ስለመውደድ አሻግረኝ›› ብላ ለመነችው፡፡ ባለጀልባውም ‹‹እነሆ ዕቃ የተጫኑ አምስት ግመሎችና ከአንቺ ጋር ከዚህም ሕፃን ጭምር አምስት ሰዎች እመለከታለሁ፣ አንቺ የተቀመጥሽባት በቅሎም አለች፡፡ ጀልባዋም ታናሽ ናት፣ የመቀመጫ ክፍሏም በውስጧ የተሳፈሩት ሰዎችም ተጨናንቀው ነው ያሉት፡፡ ስለዚህ እንዴት ላሻግርሽ እችላለሁ? ነገር ግን #እመቤቴ_ሆይ! ይቅርታ አድርጊልኝ ይህን በክፋት አላደረግሁትምና›› አላት፡፡
ክብርት #እመቤታችንም የጀልባው ባለቤት ሊያሻግራት እንዳልቻለ በተረዳች ጊዜ ‹‹ልጄ ሆይ የ #እግዚአብሔር ልጅ እንደመሆንህ ይህን ትልቅ ወንዝ ለመሻገር የአምላክነትህን ሥራ ትሠራ ዘንድ እለምንሃለሁ›› ስትል ማለደችው፡፡ ያንጊዜም #ጌታችን ክብርት እናቱን ‹‹የወለደሽኝ እናቴ ሆይ! አትዘኝ›› ብሎ አረጋጋት፡፡ ዳግመኛም ‹‹በእኔ ፈቃድ በ #አባቴ ፈቃድ በ #መንፈስ_ቅዱስ ፈቃድ ካንቺ ሰው ሆኛለሁና ሰው መሆኔንም ከ #አባቴ በቀር መስተፍሥሒ ከሚሆን ከ #መንፈስ_ቅዱስም በቀር ያወቀ የለም፡፡ ዳግመኛም በሕያዋንና በሙታን ለመፍረድ ለሁሉም እንደየሥራው እከፍለው ዘንድ እመጣለሁ፡፡ ያችንም ሰዓት የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ የአዳም ልጆችም ቢሆኑም ከእኔና ከ #አባቴ ከ #መንፈስ_ቅዱስም በቀር የሚያውቃት የለም፡፡ ያንጊዜ ‹ዐመፅን የሚናገር አንደበት ሁሉ ይዘጋል› ብሎ አባትሽ ዳዊት እንደተናገረ እከራከራለሁ የሚል አንደበት እንደድዳ ምላሽ ያጣል›› አላት፡፡
ክብርት #እመቤታችን_ማርያምም ይህንን ሁሉ ምሥጢር የተወደደ ልጇ የነገራትን ታስተውለው በልቧም ትጠብቀው ነበር፡፡ #ጌታችንም_አምላካችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስም ለክብርት እናቱ ይህንን ከነገራት በኋላ ቀኝ እጁን ዘርግቶ ከወንዙ ማዶ ጢር በሚባል ተራራ ያሉትን ድንጋዮች ጠቀሳቸው፡፡ ያንጊዜም እነዚህ ድንጋዮች እየተገለባበጡ መጥተው እንደ ጀልባ ሆነው በወራጁ ወንዝ ላይ ተንሳፈፉ፡፡ ከዚያም #እመቤታችንን ከሕፃኑ ጋር ከነቤተሰቧና ከነጓዟ አሻገረሯት፡፡
እነዚህንም ድንጋዮች ያዩ ሰዎች ሁሉ እጅግ አድንቀው ‹‹ብቻውን ድንቅ ተአምራት ያደረገ፣ እስራኤልን የፈጠረ #እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን የጌትነቱም ስም የተመሰገነ ነው›› እያሉ አመሰገኑ፡፡ እነዚህም የተባረኩ ሰዎች ወንዙን ከተሻገሩ በኋላ በዚህች አገር ለስምንት ቀን ተቀመጡ፡፡ ከዚህም በኋላ አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች ክብርት #እመቤታችን ስለደረገላት መልካም ሥራ ሁሉ #እግዚአብሔርን ፈጽማ እያመሰገነች ወደ አባቷ ወደ ዳዊት አገር ተመለሰች፡፡
ዳግመኛም በኋለኛው ዘመን #ጌታችን በዚህ በ #ደብረ_ቍስቋም ቅዱሳን ሐዋርያቶቹን ሰበሰባቸውና ታቦትንና ቤተ ክርስቲያንን አክብሮ የቍርባን መሥዋዕትንም ሠርቶ #ቅዱስ_ሥጋውንና #ክቡር_ደሙን ለወገኖቹ ሰጣቸው፡፡ ለዚህም ነገር የእስክንድርያ አገር ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱሳን አባቶቻችን ቄርሎስና ቴዎፍሎስ ምስክሮቹ ሆኑ፡፡
#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን አምላክን የወለደች የእመቤታችን የቅድስት #ድንግል_ማርያም በረከቷ ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አረጋዊ_ቅዱስ_ዮሴፍ እና #ቅድስት_ሰሎሜ
ዳግመኛም በዚህች ቀን የአረጋዊ ቅዱስ ዮሴፍ እና የቅድስት ሰሎሜም መታሰቢያቸው ነው።
#አረጋዊ_ቅዱስ_ዮሴፍ፦ መልካም ሽምግልና የነበረው የእመቤታችን #ድንግል_ማርያም እጮኛዋ ድካሟን ለመሳተፍ ክብር ይግባውና ለ #ጌታችንም አሳዳጊው ለመሆን የተገባው መታሰቢያው ነው።

እርሱም #እምቤታችንን በርሱ ዘንድ ካስጠበቋት ጀምሮ በሁሉ ነገር ያገለግላት ነበር። በመከራዋም ሁሉ አልተለያትም። በወለደችም ጊዜ በቤተ ልሔም ከርሷ ጋራ ነበረ። ወደ ግብጽም በተሰደደች ጊዜ ከእርሷ ጋራ ብዙ መከራ ደረሰበት። ከዚህም ዓለም የሚለይበት ጊዜው በደረሰ ጊዜ ወንዶችና ሴቶች ልጆቹን ተሰናበታቸው እጆቹንም ዘርግቶ ነፍሱን በ #እግዚአብሔር እጅ ሰጠ። የዘላለምንም ሕይወት ወረሰ። በአረፈበትም ጊዜ #ጌታችን ወደርሱ መጥቶ እጆቹን በላዩ ጫነ ለሥጋውም መፍረስና መበስበስ እንዳያገኘው ኃይልን ሰጠው በአባቱ በያዕቆብም መቃበር አኖሩት።
#ቅድስት_ሰሎሜ፦ አምላክን የወለደች የቅድስት #ድንግል_የእመቤታችን የአክስቷ ልጅ መታሰቢያዋ ነው። እርሷም የማጣት ልጅ የሌዊ ልጅ የሚልኪ ልጅ የካህን አሮን ልጅ ናት። ለማጣት ሦስት ሴቶች ልጆች አሉት የታላቂቱ ስም ማርያም ነው የሁለተኛዪቱ ስም ሶፍያ የሦስተኛዪቱም ሐና ነው ይቺም ማርያም ሰሎሜን ወለደቻት ሶፍያም ኤልሳቤጥን ወለደቻት ሐናም አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት #ድንግል_ማርያምን ወለደቻት።
#እመቤታችንም ድንግል ስትሆን የክብር ባለቤት #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስን በወለደችው ጊዜ ይቺ ቅድስት ሰሎሜ የ #እመቤታችንን አወላለድ እንደ ሴቶች ሁሉ አወላለድ መስሏት ተጠራጠረች ከዚህም በኋላ የድንግል #እመቤታችን ገላዋን ዳሠሠቻት ያን ጊዜ እጇ ተቃጠለ ሕፃኑን በዳሠሠችው ጊዜ ደግሞ ዳነች።
በዚህም በኅቱም ድንግልና አምላክን እንደወለደች አወቀች። ከተረገመ ኄሮድስ ፊት #እመቤታችን በሸሸች ጊዜ ከዮሴፍ ጋራ በመሆን አብራ በመሰደድ የ #እመቤታችንን ድካሟን ተካፍላ አገለገለቻት ከስደት እስከ ተመለሱ ድረስ ሕፃኑን ታዝለዋለች የምታጥብበትም ጊዜ አለ።
#መድኃኒታችን ሰው በሆነበት ወራት ሁሉ አልተለየችም በመከራውም ቀን ከ #እመቤታችን ጋራ ከከበሩ ሁሉ ሴቶች በትምህርቱ ወራት ከተከተሉት ጋራ እያለቀሰች ነበረች።
በተነሣባት ዕለት ወደ መቃብር ገሥግሣ ከሐዋርያት ቀድማ ያየች ናት። በኃምሳኛውም ቀን #መንፈስ_ቅዱስ በወረደ ጊዜ ከባልንጆሮቿ የከበሩ ሴቶች ጋራ ሰማያዊ ሀብትን ተቀብላ በክብር ባለቤት #መድኃኒታችን ስም ሰበከች ብዙዎችንም አሳመነች። ከአይሁድም ብዙ ስድብና ሽሙጥ አገኛት ከዚያም አረፈች።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አባ_ጽጌ_ድንግል_ዘወለቃ
ጻድቁ አቡነ ጽጌ ድንግል በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበሩ ሊቅና ገዳማዊ ናቸው። የዘር ሐረጋቸው ምንም ከቤተ እሥራኤል እንደሚመዘዝ ቢታወቅም ኢትዮዽያዊ ናቸው። አስቀድመው አይሁዳዊ በመሆናቸው #ኢየሱስ_ክርስቶስንና #ድንግል እናቱን አያምኑም ነበር።
የተማሩትም ብሉይ ኪዳንን ብቻ ነበር። በጊዜውም " #ክርስቶስ አልተወለደም ትክክለኛው እምነት ይሁዲ ነው" እያሉ ከክርስቲያኖች ጋር ይከራከሩ ነበሩ። አንድ ቀን ግን ከታላቁ ሊቅና ገዳማዊ አቡነ ዜና ማርቆስ ጋር ተገናኙ።
ጻድቁን ስላልቻሏቸው ተሸንፈው በ #ክርስቶስ አመኑ። አቡነ ዜና ማርቆስም አስተምረው ክርስትና ሲያነሷቸው/ሲያጠምቁዋቸው 'ጽጌ ድንግል' አሏቸው። ሲመነኩሱም 'ጽጌ ብርሃን' ተብለዋል። ቀጥለውም በጾምና በጸሎት ሲጋደሉ #እመቤታችንንም ሲለምኑ ምሥጢር ተገለጠላቸው።
የእመ ብርሃንን ስዕለ አድኅኖ በአበባ ተከባ: በብርሃንም ተውጣ ተመለከቱ። በዚህ ምክንያትም ዛሬ በጣፋጭነቱ የሚታወቀውን ማኅሌተ ጽጌን 150 ዓርኬ አድርግው ደረሱ። እስከ ዕለተ ዕረፍታቸውም #እመቤታችንና ልጇን በገዳማቸው (ወለቃ አካባቢ የሚገኝ) ሲያመሰግኑ ኑረዋል። ጻድቁ ያረፉት ጥቅምት 27 ሲሆን ዛሬ የቃል ኪዳን በዓላቸው ነው።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_አባ_ፊልክስ
ዳግመኛም በዚህች ቀን የሮሜ አገር ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባት ፊልክስ አረፈ። የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ ክርስቲያኖች ናቸው የቤተክርስቲያንንም ትምህርት አስተማሩት የሮሜ ሊቀ ጳጳሳት አንስጣስዮስም ዲቁና ሾመው ደግሞ የሮሜ ሊቀ ጳጳሳት ዮስጦስም ጠባዩን የጽድቁንና የትሩፋቱን ደግነት አይቶ ቅስና ሾመው።
ከእርሱ በፊት የነበረ ሊቀ ጳጳሳት አባ ዲዮናስዮስ በአረፈ ጊዜ ይህን አባት ፊልክስን መረጡት በ #እግዚአብሔርም ፈቃድ በሮሜ ሀገር ላይ ሊቀ ጵጵስና ሾሙት የ #ክርስቶስንም መንጋዎች በመልካም አጠባበቅ ጠበቀ።
ትሩስ ቄሣርም ከሞተ በኋላ ቴዎድሮስ ቄሣር ነገሠ ። እርሱም በምእመናን ላይ ታላቅ መከራ አምጥቶ ጭንቅ በሆኑ ሥቃዮች አሠቃያቸው። ብዙዎችም በእርሱ እጅ በሰማዕትነት ሞቱ። ይህም አባት ከዚህ ከሀዲ ታላቅ መከራና ኀዘን ደረሰበት። ስለርሱም ወደ #እግዚአብሔር ማለደ ክብር ይግባውና #ጌታችንም ልመናውን ተቀብሎ ይህንን ከሀዲ በሁለተኛ ዘመነ መንግሥቱ አጠፋው።
ከዚህም በኋላ ከሀዲ ዲዮቅልጥያኖስ በነገሠ ጊዜ ክርስቲያኖችን አብዝቶ ማሠቃየትን ጀመረ ይህም አባት ፊልክስ የክርስቲያኖችን ሥቃይ እንዳያይ ክብር ይግባውና ወደ #እግዚአብሔር ጸለየ በዲዮቅልጥያኖስም በመጀመሪያው ዘመነ መንግሥቱ አረፈ።
ይህም አባት ብዙዎች ድርሳናትንና ተግሣጾችን ደርሶአል ከእርሳቸውም ስለ ውግዘትና ስለ ቀናች ሃይማኖት የተመላለሱበት አለ እሊህም ለክርስቲያን ወገን እጅግ የሚጠቅሙ በጎዎች ናቸው።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም ከስደቱ በረከትም ያድለን። በቅዱሳኑም ጸሎቱ ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኅ_ኅዳር_6_ግንቦትና_ሐምሌ፣ #ከዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ እና #ከገድላት_አንደበት)

✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ኅዳር_6_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇🌹
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
2ኛ ቆሮ 8
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ወንድሞች ሆይ፥ ለመቄዶንያ አብያተ ክርስቲያናት የተሰጠውን የእግዚአብሔርን ጸጋ እናስታውቃችኋለን፤
² በብዙ መከራ ተፈትነው ሳሉ የደስታቸው ብዛትና የድህነታቸው ጥልቅነት የልግስናቸውን ባለ ጠግነት አብዝቶአል፤
³ እንደ ዓቅማቸው መጠን ከዓቅማቸውም የሚያልፍ እንኳ ወደው እንደ ሰጡ እመሰክርላቸዋለሁና።
⁴ ለቅዱሳን በሆነው አገልግሎት እንዲተባበሩ ይህን ቸርነት በብዙ ልመና ከእኛ ይለምኑ ነበር፥
⁵ አስቀድመውም በእግዚአብሔር ፈቃድ ራሳቸውን ለጌታ ለእኛም ሰጡ እንጂ እንዳሰብን አይደለም።
⁶ ስለዚህም ቲቶ አስቀድሞ እንደ ጀመረ እንዲሁ ደግሞ ይህን ቸር ሥራ ደግሞ በእናንተ ዘንድ ሊፈጽም ለመንን።
⁷ ነገር ግን በነገር ሁሉ፥ በእምነትና በቃል በእውቀትም በትጋትም ሁሉ ለእኛም በፍቅራችሁ እንደ ተረፋችሁ፥ በዚህ ቸር ሥራ ደግሞ ትረፉ።
⁸ ትእዛዝ እንደምሰጥ አልልም፥ ነገር ግን በሌሎች ትጋት በኩል የፍቅራችሁን እውነተኛነት ደግሞ ልመረምር እላለሁ፤
⁹ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ቸር ስጦታ አውቃችኋልና፤ ሀብታም ሲሆን፥ እናንተ በእርሱ ድህነት ባለ ጠጎች ትሆኑ ዘንድ ስለ እናንተ ድሀ ሆነ።
¹⁰ በዚህም ነገር ምክር እሰጣለሁ፤ ከአምና ጀምራችሁ ለማድረግ ብቻ ያይደለ ነገር ግን ለማሰብ ደግሞ አስቀድማችሁ የጀመራችሁት ይህ ይጠቅማችኋልና፤
¹¹ አሁንም ለማሰብ በጎ ፈቃድ እንደ ነበረ፥ እንዲሁ እንዳላችሁ መጠን መፈጸም ደግሞ ይሆን ዘንድ፥ ማድረጉን ደግሞ ፈጽሙ።
¹² በጎ ፈቃድ ቢኖር፥ እንዳለው መጠን የተወደደ ይሆናል እንጂ እንደሌለው መጠን አይደለም።
¹³ ለሌሎች ዕረፍት ለእናንተም መከራ እንዲሆን አይደለም፥ ትክክል እንዲሆን ነው እንጂ፤
¹⁴ የእነርሱ ትርፍ ደግሞ የእናንተን ጉድለት እንዲሞላ በአሁኑ ጊዜ የእናንተ ትርፍ የእነርሱን ጉድለት ይሙላ፤ በትክክል እንዲሆን፥ እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፦
¹⁵ ብዙ ያከማቸ አላተረፈም፥ ጥቂትም ያከማቸ አላጎደለም።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
2ኛ ዮሐንስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁹ ለሚወጣ ሁሉ በክርስቶስም ትምህርት ለማይኖር ሰው አምላክ የለውም፤ በክርስቶስ ትምህርት ለሚኖር አብና ወልድ አሉት።
¹⁰ ማንም ወደ እናንተ ቢመጣ ይህንም ትምህርት ባያመጣ በቤታችሁ አትቀበሉት ሰላምም አትበሉት፤
¹¹ ሰላም የሚለው ሰው በክፉ ሥራው ይካፈላልና።
¹² እንድጽፍላችሁ የምፈልገው ብዙ ነገር ሳለኝ በወረቀትና በቀለም ልጽፈው አልወድም፥ ዳሩ ግን ደስታችሁ ፍጹም እንዲሆን ወደ እናንተ ልመጣ አፍ ለአፍም ልናገራችሁ ተስፋ አደርጋለሁ።
¹³ የተመረጠችው የእኅትሽ ልጆች ሰላምታ ያቀርቡልሻል።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹² በዚያን ጊዜ ደብረ ዘይት ከሚባለው ተራራ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፥ እርሱም ከኢየሩሳሌም የሰንበት መንገድ ያህል የራቀ ነው።
¹³ በገቡም ጊዜ ወደሚኖሩበት ሰገነት ወጡ፥ ጴጥሮስና ዮሐንስም፥ ያዕቆብም፥ እንድርያስም፥ ፊልጶስም፥ ቶማስም፥ በርተሎሜዎስም፥ ማቴዎስም፥ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብም፥ ቀናተኛ የሚባለው ስምዖንም፥ የያዕቆብ ልጅ ይሁዳም።
¹⁴ እነዚህ ሁሉ ከሴቶችና ከኢየሱስ እናት ከማርያም ከወንድሞቹም ጋር በአንድ ልብ ሆነው ለጸሎት ይተጉ ነበር።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ኅዳር_6_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇🌹
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"ርኢክዎ ለኃጥእ ዐብየ ወተለዐለ ከመ አርዘ ሊባኖስ። ወሶበ እገብእ ኀጣእክዎ። ኀሠሥኩ ወኢረከብኩ መካኖ"። መዝ 36፥35።
"ኃጥአን ከፍ ከፍ ብሎ እንደ ሊባኖስ ዝግባም ለምልሞ አየሁት። ብመለስ ግን አጣሁት፤ ፈለግሁት ቦታውንም አላገኘሁም"።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ኅዳር_6_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇🌹
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ማቴዎስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁹ ሄሮድስም ከሞተ በኋላ፥ እነሆ፥ የጌታ መልአክ በግብፅ ለዮሴፍ በሕልም ታይቶ፦
²⁰ የሕፃኑን ነፍስ የፈለጉት ሞተዋልና ተነሣ፥ ሕፃኑን እናቱንም ይዘህ ወደ እስራኤል አገር ሂድ አለ።
²¹ እርሱም ተነሥቶ ሕፃኑንና እናቱን ያዘና ወደ እስራኤል አገር ገባ።
²² በአባቱም በሄሮድስ ፈንታ አርኬላዎስ በይሁዳ እንደ ነገሠ በሰማ ጊዜ፥ ወደዚያ መሄድን ፈራ፤ በሕልምም ተረድቶ ወደ ገሊላ አገር ሄደ፤
²³ በነቢያት፦ ናዝራዊ ይባላል የተባለው ይፈጸም ዘንድ፥ ናዝሬት ወደምትባል ከተማ መጥቶ ኖረ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ 🌹
የሚቀደሰው ቅዳሴ #ቅዳሴ_እግዚእነ ነው። መልካም የቊስቋም ማርያም በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#ኅዳር_7
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ኅዳር ሰባት በዚህችም ቀን #የቅዱስ_ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕት ቅዳሴ ቤቱ፣ ከእስክንድርያ አገር የሆነ #ቅዱስ_ጊዮርጊስ በሰማዕትነት አረፈ፣ #አቡነ_ገብረ_እንድርያስ_ዘወለቃ የእረፍታቸው መታሰቢያ ነው፣ #አባ_ናህርው በሰማዕትነት አረፈ፣ #የአባ_ሚናስ_ዘተመይ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው፣ #ቅዱሳን_ዘኖቢስ እና እናቱ #ቅድስት_ዘኖብያ እንዲሁም #ቅዱስ_ሐዲስ_መርቆሬዎስ እና ወንድሙ #ቅዱስ_ዮሐንስ በሰማዕትነት አረፉ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ጊዮርጊስ_ሊቀ_ሰማዕት
ኅዳር ሰባት በዚህችም ቀን የልዳ ሀገር የሆነ የሰማዕታት አለቃ የታላቁ መስተጋድል የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የከበረችበት ነው ዳግመኛም #ጌታችን በውስጧ ላደረገው ድንቅ ተአምር መታሰቢያ ሆነ።
ይህም እንዲህ ነው በውስጧ ድንቆች ተአምራት እንደሚሠሩ ከሀዲ ዲዮቅልጥያኖስ በሰማ ጊዜ ሊአፈርሳት አሰበ ስሙ አውህዮስ የሚባለውንም መኰንን ከብዙ ሠራዊት ጋር ላከው፤ ያም መኰንን በደረሰ ጊዜ የቅዱስ ጊዮርጊስ ሥዕል ወዳለበት አዳራሽ በትዕቢት ሆኖ ገባ። በሥዕሉም ፊት በብርጭቆ መቅረዝ መብራት ነበረ በቤተ ክርስቲያኒቱና በቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ እየዘበተ በእጁ በያዘው በትር የመብራቱን መቅረዝ መትቶ ሰበረው የመቅረዙም ስባሪ ወደ ከሀዲው ራስ ደርሶ መታው ራሱንም ታመመ ፍርሃትና እንቅጥቅጥም መጣበት ወድቆም ተዘረረ ባልንጀሮቹም ወደ አገሩ ሊወስዱት ተሸከሙት በክፉ አሟሟትም ተጐሳቊሎ ሞተ ወስደውም ከባሕር ጣሉት ወገኖቹም ወደ ሀገራቸው አፍረው ተመለሱ።
ከሀዲ ዲዮቅልጥያኖስም ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ በልዳ ሀገር ያለች የቅዱስ ጊዮርጊስን ቤተ ክርስቲያን ያፈርሳት ዘንድ ራሱ ተነሥቶ ሔደ በዚያንም ጊዜ ከ #እግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ መታው ሰባት ዓመት ያህልም ዐይኖቹ ታውረው አእምሮውንም አጥቶ ቁራሽ እንጀራም እየለመነ ኑሮ ሞተ።
ክብር ይግባውና #ጌታችንም የቤተ መንግሥቱን ሰዎች አስነሣበት እርሱን አስወግደው ጻድቅ ሰው ቁስጠንጢኖስን በ #እግዚአብሔር ፈቃድ አነገሡት እርሱም በአዋጅ የጣዖታትን ቤቶች ዘግቶ አብያተ ክርስቲያናትን ከፈተ ለክርስቲያን ወገኖችም በሁሉ ዓለም ተድላ ደስታ ሆነ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ጊዮርጊስ_እስክንድርያ
በዚህች ቀን የእስክንድርያ አገር የሆነ ቅዱስ ጊዮርጊስ በሰማዕትነት አረፈ።
የዚህም ቅዱስ አባቱ በእስክንድርያ አገር በንግድ ሥራ የሚኖር ነው ልጅም አልነበረውም የልዳዊው ቅዱስ ጊዮርጊስም ቤተ ክርስቲያኑ የከበረችበት የበዓልዋ መታሰቢያ ኅዳር ሰባት በደረሰ ጊዜ ልጅን ይሰጠው ዘንድ ወደ #እግዚአብሔር እንዲማልድለት ቅዱስ ጊዮርጊስን ለመነው #ጌታችንም ልመናውን ተቀብሎ ይህን ልጅ ሰጠው ስሙንም በታላቁ ሰማዕት ስም ጊዮርጊስ ብሎ ስም አወጣለት።
የዚህም ልጅ እናቱ ለእስክንድርያ አስተዳዳሪ ለአርማንዮስ እኅቱ ናት ከዚህም በኋላ እናትና አባቱ አረፉ እርሱም ከእናቱ ወንድም ዘንድ ተቀመጠ ሃያ አምስት ዓመትም በሆነው ጊዜ በጎ ሥራ የሚሠራ ሆነ ድኆችን እጅግ ይረዳቸው ይወዳቸውም ነበረ የሚራራና የሚመጸውት ሆነ ወደ ቤተክርስቲያን መገሥገሥንም ይወዳል። ለመኰንን አርማንዮስም አንዲት ብቻዋን ሴት ልጅ አለችው ቦታዎችንም በመጐብኘት ደስ ይላት ዘንድ ከባልንጀሮቿ ጋር ወጣች ወደ ደብረ ቊስቋምም ስትደርስ ጣዕም ባለው ድምጽ በመዘመር ሲያመሰግኑ የተሰበሰቡ መነኰሳትን አገኘቻቸው ምስጋናቸውና መዝሙራቸውም ወደ ልቡዋ ገብቶ ተቀረጸ።
የአባቷ እኅት ልጅ የሆነ ጊዮርጊስንም መነኰሳቱ ስለሚዘምሩት ያስረዳት ዘንድ ጠየቀችው እርሱም ወደማይጠፋ ዕረፍትና ተድላ እንደሚያደርሳቸው ትርጓሜውንና ጥቅሙን ሊያስረዳትና ሊያስገነዝባት ጀመረ።
ወደ አባቷም አርማንዮስ በተመለሰች ጊዜ በፊቱ ቁማ ክብር ይግባውና በ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ታመነች አባቷም ሊሸነግላት ጀመረ ልጄ ሆይ ይህን አታድርጊ አላት ነገሩን ባልተቀበለች ጊዜ ራሷን በሰይፍ አስቆረጠ በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለች።
ከዚህም በኋላ ልጅህን ያሳታት የእኅትህ ልጅ ጊዮርጊስ ነው ብለው ለመኰንኑ ነገሩት እርሱም ሰምቶ ቅዱስ ጊዮርጊስን ይዞ ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃየው ጭካኔውንም አይቶ ወደ ሀገረ እንጽና ሰደደው በዚያም ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃይተው ቅድስት ራሱን በሰይፍ ቆረጡ የሰማዕትነትንም አክሊል ተቀበለ።
በዚያም ሳሙኤል የሚባል ዲያቆን ነበር የቅዱስ ጊዮርጊስንም ሥጋ አንሥቶ ወደ ሀገረ መኑፍ ወሰደው። የአርማንዮስም ሚስት በአወቀች ጊዜ መልእክተኞችን ልካ አስመጣችው ከልጅዋም ሥጋ ጋር በአንድነት በእስክንድርያ አገር አደረገችው።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አቡነ_ገብረ_እንድርያስ_ዘወለቃ
ዳግመኛም በዚህች ቀን አቡነ ገብረ እንድርያስ ዘወለቃ የእረፍታቸው መታሰቢያ ነው። የትውልድ ሀገራቸው ወሎ ቦረና ጋስጫ ነው፡፡ አባታቸው ተንሥአ ክርስቶስ እናታቸው አርሴማ ይባላሉ፡፡ ሁለቱም ደጋግ ቅዱሳን ናቸው፡፡ ዕድሜአቸው ለትምህርት ሲደርስ ለመምህር ሰጧቸው፡፡ መምህሩም ጸጋ #እግዚአብሔር እንዳደረባቸው ዐውቀው ‹‹ብዙዎችን የምታድን ጻድቅ ትሆናለህ›› ብለው ትንቢት ነግረዋቸዋል፡፡ የመጻሕፍትንም ትርጓሜ በሚገባ ካስተማሯቸው በኋላ ንፍታሌም ይባል የነበረውን ስማቸውን ለውጠው ገብረ እንድርያስ አሏቸው፡፡
ጻድቁ በአቡነ ዮሐንስ ከማ ገዳም ለረጅም ጊዜ በታላቅ ተጋድሎ አገልግለዋል፡፡ አባታችን ሙታንን በማስነሣትና ድውያንን በመፈወስ ብዙ ተአምራትን ሲያደርጉ ኖረዋል፡፡ ብዙ አባቶች ሱባኤ ይይዙበት በነበረው በሰኮሩ #ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ጸሎት ሲያደርጉ ቅዱስ ዑራኤል በወርቅ ጽዋ ሰማያዊ ወይንና ኅብስት መግቧቸዋል፡፡ #እመቤታችንም ሦስት ጽዋ ማየ ሕይወት ሰጥታቸው በእርሱ ብዙ ሕሙማንን ፈውሰውበታል፡፡
ጻድቁ በስማቸው የፈለቀው ጸበል እጅግ አስገራሚ ነው፡፡ ጸበሉ ውስጥ እንጨት ሲነከርበት እንጨቱ በተአምራት ነጭ መቁጠሪያ ሆኖ ይወጣል፡፡ ይህም እስከዛሬ ድረስ በግልጽ ይታያል፡፡ ጸበሉ ውስጥ ማታ የነከሩትን እንጨት ጠዋት ላይ መቁጠሪያ ሆኖ ያገኙታል፡፡ እጅግ አስገራሚ ነው በእውነት! መቁጠሪያውም ለእንቅርትና ለልዩ ልዩ ሕመሞች መድኃኒት ነው፡፡ ነገር ግን ጸበሉ ያለበት አካባቢው በመርዛማና አደገኛ እባቦች የተሞላ ነው፡፡ ሆኖም ግን እባቦቹ የጻድቁ ግዝት ስላለባቸው በገዳሙ ውስጥ ብቻ ማንንም አይነኩም፡፡ ጸበሉ ደግሞ የሚገኘው ከገዳሙ የአንድ ሰዓት ተኩል መንገድ ርቀት ላይ ነው፡፡
አባታችን #እግዚአብሔር ኃጥአንን እንድምርላቸው ጣቀት ወንዝ ከተባለው ቦታ በአንገታቸው ላይ በጣም ትልቅ ድንጋይ እየተሸከሙ ይጸልዩ ነበር፡፡ በዚህ ይጸልዩበት ከነበረው ወንዝ ውስጥ ነው በተዓምራት መቁጠሪያ የሚሠራው ጸበል የፈለቀላቸው፡፡ ደቡብ ወሎ ወግዲ ወረዳ የሚገኘው አቡነ ገብረ እንድርያስ ገዳም ከአባ ጽጌ ድንግል ገዳም በእግር የ3 ሰዓት መንገድ ያስኬዳል፡፡
ጻድቁ አቡነ ገብረ እንድርያስ ዓርብ ዓርብ የ #ጌታችንን_ቅዱስ_ሥጋውንና #ክቡር_ደሙን ለመቀበል ወደ ኢየሩሳሌም ይመላለሱ የነበረው በትልቅ ድንጋይ ላይ እንደ ደመና ተጭነው ነበር፡፡
ጻድቁ በአየር ላይ ሲጓዙ ድንጋዩን እንደ ሠረገላ ዋርካውን እንደ ጥላ ይጠቀሙበት ነበረ፡፡ ያ እንደ ሠረገላ ሆኖ ያገለግላቸው የነበረው ትልቅ ድንጋይ ዛሬም ድረስ በገዳማቸው ውስጥ ይገኛል፡፡ ታሪኩም በቅዱስ ገድላቸው ላይ ተጽፎ ይገኛል፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_አባ_ናህርው

በዚህችም ቀን ዳግመኛ ከግብፅ አገር ከፍዩም መንደር አባ ናህርው በሰማዕትነት አረፈ። ይህም ቅዱስ #እግዚአብሔርን እጅግ የሚፈራው ነው በእስክንድርያ ሀገር የሚሠቃዩ የሰማዕታትን ዜና በሰማ ጊዜ ክብር ይግባውና ስለ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ስለ ስሙ ሊሞት ወደደ በራእይም ወደ አንጾኪያ ሀገር ሒደህ በዚያ ትሞት ዘንድ አለህ አለው።
ወደዚያ መድረስ እንዴት ይቻለኛል በማለት የሚያስብ ሆነ ሊሳፈርም መርከብን ፈለገ በዚያን ጊዜ #እግዚአብሔር መልአኩን ቅዱስ ሚካኤልን ላከለት በክንፎቹም ተሸክሞ ወደ አንጾኪያ ሀገር አደረሰው።
በዲዮቅልጥያኖስም ፊት ቀርቦ በ #እግዚአብሔር ታመነ ንጉሡም ስሙንና አገሩን ጠየቀው እርሱም ከግብጽ አገር እንደሆነ አስረዳው ንጉሡም ቃሉን ሰምቶ ለጣዖታቱ ቢሠዋለት ብዙ ገንዘብና የግምጃ ልብሶችን ሊሰጠው ማለለት እርሱ ግን ቃሉን አልሰማም ንጉሱም እኔ ታላቅ ሥቃይን አሠቃይሃለሁ የሚል ቃልን ደግሞ ተናገረው ከሥቃዩም የተነሳ አልፈራም ትእዛዙንም አልሰማም።
ከዚህም በኋላ ቅዱስ ናህርውን በብዙ አይነት ስቃይ እንዲአሰቃዩት ንጉሱ አዘዘ አንድ ጊዜ ለአንበሶች ጣሉት አልነኩትም አንድ ጊዜ ከእሳት ጨመሩት አልተቃጠለም ሌላ ጊዜም በወጭት ቀቀሉት ከማሠቃየትም በሰለቸ ጊዜ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ ንጉሡ አዘዘ።
ይህ አባ ናህርውም በግብጽ አገር በሰማዕትነት ስለሞቱ ስለ አንጾኪያ አገር ሰማዕታት ፈንታ በአንጾኪያ አገር በሰማዕትነት አረፈ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አባ_ሚናስ_ዘተመይ
በዚህችም ቀን ከገምኑዲ አውራጃ የሀገረ ተመይ ኤጲስቆጶስ የአባ ሚናስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ሆነ። የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ ደጎች #እግዚአብሔርን የሚፈሩ ዜናቸውም በቅዱሳን አባቶች ዘንድ እስከ ተሰማ ድረስ በጾማቸው በጸሎታቸው በገድል በመጸመዳቸው የመነኰሳትን ሥራ የሚሠሩ ናቸው።
እነርሱም ያለ ፈቃዱ ልጃቸውን ሚስትን አጋቡት ሙሽራዪቱም ወዳለችበት የጫጒላ ቤት ገባ ድንግልናቸውንም ሳያጠፉ ሥጋቸውን በንጽሕና ይጠብቁ ዘንድ ከእርሷ ጋር ተስማሙ ሁለቱም በበጎ ተጋድሎ እየተጋደሉ በአንድነት ኖሩ።
ከዚህም በኋላ ቅዱስ ሚናስ የምንኲስና ልብስ ሊለብስ ወዶ ሚስቱን እንዲህ አላት በዓለም እያለን የምንኲስና ሥራ ልንሠራ ለእኛ አግባብ አይደለም እነርሱ ከልብሳቸው ውስጥ ማቅ በመልበስ በ #እግዚአብሔር_መንፈስ የተደረሱ መጻሕፍትን በማንበብና ለጸሎት በመትጋት ሌሊቱን ሁሉ ይቆሙ ነበርና ከዚህም በኋላ ሰላምታ ሰጥታ ሸኘችው አሰናበተችውም።
እርሱም ወደ አባ እንጦንዮስ ገዳም ሔደ ከወላጆቹ ሊርቅ ወዶአልና እነርሱ ወደ ሚስቱ ይመልሱት ዘንድ በንጉሥ ትእዛዝ በቦታ ሁሉ እየፈለጉት ነበርና #እግዚአብሔር ሠውሮታልና ከቶ አላገኙትም በዚያም ገዳም በገድል ተጠምዶ ብዙ ጊዜ ኖረ በእስክንድርያም ሊቀ ጳጳሳት የሆነው አባ ሚካኤል ከእርሱ ጋር በምንኵስና ነበር።
ከዚህም በኋላ ሁለቱ ብሩሃን ከዋክብት አባ አብርሃምና አባ ገዓርጊ በነበሩበት ወራት ከነበረበት ወጥቶ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሔደ። ይህ ቅዱስ አባ ሚናስም ተወዳጅ ልጅን ሆናቸው ከእርሳቸውም ዘንድ በበዓታቸው የሚኖርና የሚያገለግላቸው ሆነ የምንኲስናንም ሥራ ጨመረ ከእርሳቸውም ትምህርታቸውን ተጋድሏቸውን በመማር ከብዙዎች በተጋድሎውና በአምልኮቱ ከፍ ከፍ አለ አባ አብርሃምና አባ ገዓርጊ ሌሎችም አባቶች ከእርሱ ተጋድሎ የተነሣ ያደነቁ ነበር።
ሰይጣን ግን በእርሱ ቀንቶ በታላቅ አመታት እግሮቹን መታው ሁለት ወርም በምድር ላይ ወድቆ ኖረ ። ከዚህም በኋላ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ያለ ጥፋት በጤና አሥነሣው።
ከዚህም በኋላ ክብር ይግባውና #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ኤጲስቆጶስ ይሆን ዘንድ መርጦ ጠራው የሊቀ ጳጳሳቱም መልእክተኞች ወደርሱ መጡ ከመነኰሳት የሚለይ በመሆኑ ታላቅ ኀዘንን አዘነ ቅዱሳን አባቶችም ይህ ሥራ ከ #እግዚአብሔር ነው አትዘን አሉት።
እርሱም ለ #እግዚአብሔር ትእዛዝ ራሱን ዝቅ አድርጎ ከሊቀ ጳጳሱ መልክተኞች ጋር አብሮ ሔደ ሊቀ ጳጳሱም ተመይ በሚባል አገር ላይ ኤጲስቆጶስነት ሾመው ሀብተ ፈውስም ተሰጥቶት በሽተኞችን የሚፈውሳቸው ሆነ በሽታ ያለባቸውም ሁሉ ወደርሱ ይመጣሉ እርሱም ክብር ይግባውና ወደ #እግዚአብሔር በመጸለይ ይፈውሳቸዋል።
ሁለተኛም የተሠወረውን የማወቅ ሀብተ ጸጋ #እግዚአብሔር ሰጠው በሰው ልቡና የታሰበውንም የሚያውቅ ሆነ ኤጲስቆጶሳቱም ሁሉ ከየሀገሮቻቸው በመምጣት ራሳቸውን ዝቅ አድርገው የሚታዘዙለትና ትምህርቱን የሚቀበሉ ሆኑ አሕዛብም ሁሉ ትምህርቱን ይሰሙ ዘንድ ይመጡ ነበር እርሱም ለአራት ሊቃነ ጳጳሳት አባት ሆነ። በሚሾሙ ጊዜ እጁን በላያቸው ጭኖአልና እሊህም በእስክንድርያ አገር ሊቃነ ጳጳሳት የሆኑ እለእስክንድሮስ፣ ቆዝሞስ፣ ቴዎድሮስ፣ ሚካኤል ናቸው።
ክብር ይግባውና #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ከዚህ ከኃላፊው ዓለም ሊለየው በፈቀደ ጊዜ የሚለይበትን ቀን በ #መንፈስ_ቅዱስ አውቆ በሀገረ ስብከቱ ያሉትን ሕዝቡን ሁሉ ልኮ አስመጣቸው። በቀናች ሃይማኖት እንዲጸኑ የከበረ የወንጌልንም ትእዛዝ እንዲጠብቁ አዘዛቸው ከዚህም በኋላ ለእውነተኛው ጠባቂያቸው ለ #ጌታችንና_ለመድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ሰጣቸውና ከዚህ ከኃላፊው ዓለም ተለይቶ ወደ ወደደው #ክርስቶስ ሔደ ሕዝቡም አለቀሱለት ቸር ጠባቂያቸውም ከእርሳቸው በመለየቱ እጅግ አዘኑ እንደሚገባም ገንዘው እርሱ ራሱ በአዘዛቸው ቦታ አኖሩት።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱሳን_ዘኖቢስና_እናቱ_ዘኖብያ
በዚህችም ቀን ቅዱሳን ዘኖቢስና እናቱ ዘኖብያ በሰማዕትነት አረፉ እሊህም ቅዱሳን ተበይስ ከምትባል አገር ከታላላቆቿ ናቸው። እነርሱ ክርስቲያን እንደሆኑ በንጉሥ ዘንድ ወነጀሏቸው ንጉሥም ወደርሱ እንዲአቀርቧቸው አዘዘና ሲቀርቡ እንዲህ አላቸው የምትጠበቁት ከምንድን ነው አገራችሁስ ወዴት ነው እነርሱም እንዲህ ብለው መለሱለት እኛ ጣዖታትን ከማምለክ እንጠበቃለን እምነታችንም በ #ክርስቶስ ነው ሀገራችንም ተበይስ ይባላል።
መኰንኑም ለአማልክት ሠዉ አላቸው ቅዱሳንም እኛ ለ #ኢየሱስ_ክርስቶስ እንሠዋለን እንጂ ለጣዖታት አንሠዋም አሉት መኰንኑም ተቆጣ ልብሳቸውንም ገፈው በራሳቸው ጠጒር ሰቅለው ይደበድቧቸው ዘንድ አዘዘ ወደ #እግዚአብሔርም ጸለዩ በዚያንም ጊዜ ማሠሪያቸው ተፈታ የብርሃንንም ልብሶች ለብሰው ሕዝቡ አዩአቸው መኰንኑም ወንበሩን ተሸክሞ በኋላቸው ሲከተል ነበር ። ሕዝቡም ይህን በአዩ ጊዜ እንዲህ እያሉ ጩኸው አመሰገኑ ልዩ ጽኑዕ ምስጉን አሸናፊ #እግዚአብሔር የጌትነትህ ክብር በሰማይና በምድር የመላ የ #ክርስቲያን_አምላክ_ኢየሱስ_ክርስቶስ ኃይልህ ታላቅ ነው።
ከዚህም በኋላ መኰንኑ ተቆጣ እርስበርሳቸው እንዲተያዩ አድርገው በሁለት መስቀሎች እንዲሰቅሏቸው አዘዘ ያን ጊዜም ደመና መጥቶ ጋረዳቸው በማግሥቱም የ #እግዚአብሔርን ቃል ሲያስተምሩ መኰንኑ አገኛቸው ሕዝቡም አይተው እኛ በክርስቲያኖች አምላክ እናምናለን እርሱ ታላቅ ነውና እያሉ በአንድ ቃል ጮኹ።
ሁለተኛም እንዲህ ብሎ አዘዘ ሁለት ወንበሮችን እንዲሠሩ በውስጣቸውም ብረቶችን እንዲተክሉ እሊህንም ቅዱሳን በላዩ አስተኝተው ከእሳት ምድጃ ውስጥ እንዲጨምሩአቸው አዘዘ #ጌታችን_ኢየሱስም አዳናቸው በእነዚያ ወንበሮችም ላይ ተቀምጠው ሕዝቡን ሲያስተምሩ አገኙአቸው።

መኰንኑም በአየ ጊዜ ቁጣን ተመላ ቁመቱና ጐኑ ሃያ ሃያ ክንድ የሆነ ጒድጓድን ቆፍረው እሳትን እንዲአነዱበትና በውስጡ እንዲጨምሩአቸው አዘዘ ወደ #እግዚአብሔርም በጸለዩ ጊዜ ያ እሳት ጠፋ ጒድጓዱም እንደተሸለመ ቤት ሆነላቸው።
መኰንኑም የውሽባ ቤት ጠባቂውን ጠርቶ እሳትን እንዲያነድ አዘዘው ቅዱሳኑንም ከውስጡ እንዲጨምሩአቸው። ወደ #እግዚአብሔርም በጸለዩ ጊዜ የውሽባ ቤቱ ውኃ ሆነ መኰንኑም ውኃ የተመላበትን ጋን ተሸክሞ ነበር ይህንንም ድንቅ ሥራ ሕዝቡ በአዩ ጊዜ እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ በሚሠራው ሥራ የተደነቀ ነው እያሉ እግዚአብሔርን አመሰገኑት።
መኰንኑም ምን እንደሚያደርጋቸው በተቸገረ ጊዜ እንዲገድሏቸውና እስከ ነገ ድረስ በድናቸውን ጠብቀው በእሳት እንዲአቃጥሏቸው በነፋስም ውስጥ እንዲበትኑአቸው አዘዘ። በገደሏቸውም ጊዜ ነጐድጓድ መብረቅ ንውጽውጽታና ዝናም ሆነ በዚያ ንውጽውጽታም ብዙዎች ኃምሣ አራት ያህል ሰዎች ሞቱ በሌሊትም ምእመናን መጥተው በሥውር ሥጋቸውን ወስደው ቀበሩአቸው።
በማግሥቱም መኰንኑ በድናቸውን በፈለገ ጊዜ የሆነውን ሁሉ ተአምር ነገሩት ያም መኰንን አደነቀ በጌታችንም አምኖ ክርስቲያን ሆነ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱሳን_መርቆሬዎስና_ዮሐንስ
በዚህችም ቀን ቅዱሳን ሐዲስ መርቆሬዎስና ወንድሙ ዮሐንስ በሰማዕትነት አረፉ። እነዚህ ቅዱሳን #እግዚአብሔርን ለሚፈሩና ለሚያመልኩ ክርስቲያኖች ሰዎች ልጆች ናቸው የታላቁም ስሙ "መናሂ" ነበር የምንኲስና ልብስ በለበሰ ጊዜ መርቆሬዎስ ብለው ሰየሙት የታናሹም ስሙ "አቡፈረዥ "ነበር እርሱንም በሚመነኲስ ጊዜ ዮሐንስ ብለው ሰየሙት።
በአደጉም ጊዜ ወደ ሊቀ ሰራዊት ቅዱስ ቴዎድሮስ ገዳም ሔዱ በዚያም #እግዚአብሔርን ለሚያገለግል አረጋዊ ጻድቅ ሰው የሚታዘዙ ሁነው ኖሩ ለገዳሙ በሚአሻው ስራ መነኰሳቱንም በማገልገል የክረምቱን ቅዝቃዜና የበጋ ቃጠሎ ታግሠው የምድሩን ፍሬዎች የሚሰበስቡና ወደዚያች ገዳም የሚያመጡ ሆኑ።
ለራሳቸው ግን በዓለም ውስጥ ምንም ምን ጥሪትን አላደረጉም ዳግመኛም በዓለም ውስጥ ጣዕም ካላቸው ከመብል ከመጠጥ ከእንቅልፍ የራቁ ናቸው በየሁለትና በየሶስት ቀን ይጾማሉ። ዳግመኛም በቅብጢና በዓረብ ቋንቋ ጽሕፈት ተማሩ የምንኲስናንም ሕግና ሥርዓት ፈጸሙ።
በአንዲት ቀንም በአንድነት እያሉ ከ ##እግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ወደ እነርሳቸው መጥቶ እነርሱ ወደ ምስክርነት አደባባይ እንደሚደርሱ ነገራቸው ያን ጊዜ ደስ አላቸው በ #መንፈስ_ቅዱስም በረቱ ተነሥተውም በችኰላ ተጒዘው ወደ አገራቸው ደረሱ። የአገራቸውም ሰዎች በአገሩ ገዥ ዘንድ ወነጀሏቸው እርሱም ለብህንሳው ገዥ አሳልፎ ሰጣቸው እርሱም በውኑ እናንተ ጣዖትን የምታመልኩ ናችሁን ብሎ ጠየቃቸው ። ቅዱሳን ግን ይህ በእኛ የሚነገር አይደለም እኛ በግልጥ ክርስቲያን የሆን የረከሱ ጣዖታትን የማናመልክ ነንና እውነተኛውን #አምላክ_ጌታችንን_ኢየሱስ_ክርስቶስን እናመልከዋለን እንጂ አሉት።
መኰንኑም ይህን በሰማ ጊዜ ቊጣን ተመላ በአንገቶቻቸውም ሰንሰለት አስገብተው ከተማውን ሁሉ አዙረው ከዚያ በኋላ በወህኒ ቤት እንዲአስሩአቸው አዘዘ በዚያም ሳሉ የ #እግዚአብሔር መልአክ ብዙ ጊዜ የሚጐበኛቸው ሆነ።
ከአምስትም ወር በኋላ መኰንኑ ከእስር ቤት አውጥቶ በፊቱ አቆማቸውና ሃይማኖታችሁን ተዉ አላቸው። አይሆንም በአሉትም ጊዜ ሥጋችሁን በእሳት አቃጥላለሁ ብሎ አስፈራራቸው እነርሱ ግን ምንም አልፈሩትም የልባቸውን ጥንክርና አይቶ ወደ ወህኒ ቤት መለሳቸው።
ከብዙ ወራት በኋላ ሌላ መኰንን መጣ እርሱም ሊአድናቸውና ሊተዋቸው ወደደ የአገር ሰዎች ግን ተቃወሙት እነዚህን ካልገደልካቸው በንጉሥ ዘንድ እንከስሃለን አሉት ያንጊዜም ሊአስፈራራቸው እሳትን ያነዱ ዘንድ አዘዘ እነርሱ ግን ወደ እሳቱ ለመግባት ተደፋፈሩ ዳግመኛም ራርቶላቸው ወደ ወህኒ ቤት መለሳቸው ሁለተኛም አምጥተው በተሳሉ ሰይፎች ያስፈራሩአቸው ዘንድ አዘዘ የእዚህ ቅዱሳን ልብ ግን አልደከመም ቃላቸውም አልተለወጠም።
ከዚህም በኋላ ህዝቡን ከመፍራት የተነሳ ራሳቸውን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ በመጀመሪያም የዮሐንስን ራስ ቆረጡ ያን ጊዜም ራሱ ከሥጋዋ ላይ ዘለለች ከእርሷም እንደ ደስታ ቃል ያለ የሰሙ ሁሉ እስኪያደንቁ ድረስ ታላቅ ድምፅ ወጣ።
ዳግመኛም የቅዱስ መርቆሬዎስን ራስ ቆረጡ ሥጋቸውንም ከእሳት ውስጥ ጨመሩ በዚያንም ጊዜ እሳቱ ጠፋ ሥጋቸውንም ልብሳቸውንም አልነካም መኰንኑም በአየ ጊዜ ክርስቲያኖች እንዳይሰርቋቸው ጠብቁ ብሎ አዘዘ በማግስቱም የዐዘቅት ውኃ በአገኙ ጊዜ ከውስጧ ጨመሩአቸው ከዚህም በኋላ ከእርሳቸው ብዙዎች ተአምራት ተገለጡ።
#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ሰማዕታት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ኅዳር_7 እና #ከገድላት_አንደበት)

#ኅዳር_8
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ኅዳር ስምንት በዚች ቀን ሥጋ የሌላቸው #የአርባዕቱ_እንስሳ በዓላቸው ነው፣ ሊቀ መላእክት #ቅዱስ_አፍኒን የተሾመበት ነው፣ #ለንጉሥ_ቈስጠንጢኖስም መስቀል የተገለጸበት ነው፣ የአረማዊ መኰንን ልጅ የነበረ #ቅዱስ_አባ_ቅፍሮንያ ያረፈበት ቀን ነው።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አርባዕቱ_እንስሳ
ኅዳር ስምንት በዚች ቀን ሥጋ የሌላቸው የአርባዕቱ እንስሳ በዓላቸው ሆነ።
እሊህም መንበሩን የሚሸከሙ የ #እግዚአብሔር ሠረገላዎቹ ናቸው። ስለ እሳቸውም ወንጌልን የጻፈ ዮሐንስ እንዲህ ሲል እንደመሰከረ በዚያ ዙፋን ፊት በረድ የሚመስል ባሕር አለ በዙፋኑም ዙሪያ አራት እንስሶች አሉ በፊትም በኋላም ዐይንን የተመሉ ናቸው።
የፊተኛው አንበሳ ይመስላል ሁለተኛውም ላም ይመስላል ሦስተኛውም የሰው መልክ ይመስላል አራተኛውም የሚበር አሞራ ይመስላል።
የእሊህም የአራቱ እንሰሶች እያንዳንዱ ክንፋቸው ስድስት ስድስት ነው ሁለንተናቸውም ዐይኖችን የተመሉ ናቸው። የነበረ የሚኖር የአማልክት አምላክ #እግዚአብሔር ጽኑዕ ክቡር ልዩ ነው እያሉ በመዓልትና በሌሊት ዕረፍት የላቸውም።
ሁለተኛውም ስለእርሳቸው ኢሳይያስ እንዲህ አለ ከዚህም በኋላ ንጉሡ ኦዝያን በሞተ ጊዜ አሸናፊ #እግዚአብሔርን ሰፊ በሆነና ከፍ ከፍ ባለ ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ብርሃኑም ቤቱን መልቶ ሱራፌልም በዙሪያው ቁመው አየሁት።
የአንዱም የአንዱም ክንፋቸው ስድስት ነው በሁለቱ ክንፋቸው ፊታቸውን በሁለቱ ክንፋቸው እግሮቻቸውን ይሸፍናሉ በሁለቱ ክንፎቻቸው ከጽንፍ እስከ ጽንፍ ይበራሉ። አንዱም አንዱም ከአንዱ ጋራ ፍጹም አሸናፊ የሆንክ #እግዚአብሔር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ተብለህ የምትመሰገነው ምስጋናህ በምድርና በሰማይ የመላ ነው እያሉ ያመሰግናሉ።
ነቢይ ዳዊትም በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ አለ ሁለተኛም በኪሩቤል ላይ የተቀመጠ እርሱ ምድርን አናወጻት አለ። ሕዝቅኤልም እንዲህ አለ ከወደ ሰሜን እነሆ ጥቅል ነፋስ ሲመጣ አየሁ ታላቅ ደመና አለ በዙሪያውም ብርሃን አለ ከእሱም እሳት ቦግ ብሎ ይወጣል።
በደመናውም መካከል ባለ በእሳቱ ውስጥ እንደ አራት ራስ አሞራ መልክ የሚመስል አለ በመካከሉም እንደ አራቱ ኪሩቤል መልክ ያለ አለ። መልካቸውም እንዲህ ነው በውስጣቸው የሰው መልክ አላቸው የአንዱም የአንዱ ፊቱ አራት ነው ክንፉም አራት ነው።
እግራቸውም የቀና ነው ከእግራቸውም ክንፍ አላቸው ሰኮናቸው ግን እንደ ላም ሰኮና ነው ከሱም እሳት ቦግ ይላል እንደጋለ ብረት ፍንጣሪም ይበራል።
ወንጌላዊ ዮሐንስም ዳግመኛ እንዲህ አለ በዚያው ዙፋን ዙሪያ የብዙ መላእክትን ድምፅ የእንስሶቹንም የእነዚያ አለቆችንም ቃል ሰማሁ ቁጥራቸውም እልፍ አለቆች ያሉአቸው ብዙ የብዙ ብዙ ነው።
ለዚያ ለተገደለው በግ ኃይልን፣ ባለጸግነትን፣ ጥበብን፣ ጽናትን፣ መንግሥትን፣ ክብርን፣ ጌትነትን፣ ምስጋናን ገንዘብ ሊያደርግ ይገባዋል ብለው በታላቅ ቃል ተናገሩ።
በሰማይና በምድር ከምድር በታች በባሕር ውስጥ በእነዚያም ውስጥ የተፈጠረው ፍጥረት ሁሉ ጌትነት ክብር ኃይል በረከት በዙፋኑ ለተቀመጠው ለሱ ለበጉም ለዘላለሙ ይገባዋል አሉ። በእውነት ይገባዋል። እሊህም አራቱ እንስሶች አሜን ይላሉ። እሊያም አለቆች ይሰግዳሉ።
ስለ ልዕልናቸውና ስለ ክብራቸው ለእሊህ አርባዕቱ እንሰሳ ከብሉይና ከሐዲስ ብዙ መጻሕፍት መስክረዋል መሐሪና ይቅር ባይ #እግዚአብሔርም ስለ ሁሉ የሰው ፍጥረት ይለምኑት ዘንድ ቀራቢዎቹ አደረጋቸው። ዳግመኛም እንዲህ ተባለ ገጸ ሰብእ ስለ ሰው ፍጥረት ይለምናል። ገጸ አንበሳ ስለ አራዊት ይለምናል ገጽ ላሕም ስለ እንስሳ ይለምናል ገጸ ንስርም ስለ አዕዋፍ ይለምናል ከሰማይ ሠራዊት ሁሉ እነርሱ በ #እግዚአብሔር ዘንድ በባለሟልነት እጅግ የቀረቡ ናቸውና።
ስለዚህም በዓለሙ ሁሉ በስማቸው አብያተ ክርስቲያን እንዲታነፁ በዚችም ቀን መታሰቢያቸው እንዲደረግ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አዘዙ እነርሱ ስለ ሰው ወገን በ #እግዚአብሔር ዘንድ ይማልዳሉና።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_አፍኒን_ሊቀ_መላእክት
ዳግመኛም በዚህች ዕለት ሊቀ መላእክት ቅዱስ አፍኒን የተሾመበት ዓመታዊ በዓሉ ነው፡፡ ይህም ሱራፌልና ከኪሩቤል ጋር የልዑልን የጌትነቱን ዙፋን የሚጠብቅ ነው፡፡ ስለዚህም ክቡር መልአክ ሄኖክ እንዲህ አለ፡- "…ያንን ቤት ሱራፌልና አፍኒን ዙሪያውን እየዞሩ ይጠብቁታል፣ እነርሱም የልዑልን የጌትነቱን ዙፋን ሲጠብቁ የማያንቀላፉ ናቸው፡፡" ቅዱስ ዮሐንስ በራእዩ "በ #እግዚአብሔር ፊት የሚቆሙ 7 መላእክትን አየሁ" (ራዕ 8፥2) እንዳለ ሊቃነ መላእክት በቁጥር 7 ናቸው፡፡ እነርሱም፡- ቅዱስ ሚካኤል፣ ቅዱስ ገብርኤል፣ ቅዱስ ሩፋኤል፣ ቅዱስ ራጉኤል፣ ቅዱስ ዑራኤል፣ ቅዱስ ፋኑኤልና ኅዳር 8 ቀን የተሾመበትን ዓመታዊ በዓሉን የምናከብርለት ቅዱስ አፍኒን ናቸው፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ታላቁ_ቅዱስ_ቆስጠንጢኖስ
በዚህችም ቀን ለንጉሥ ቈስጠንጢኖስም #መስቀል ተገለጸለት።
ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ለቤተ ክርስቲያን የፈፀመውን መልካም ተግባር ያህል መሥራት የቻለ ንጉሥ በሐዲስ ኪዳን የለም። ጻድቁ ንጉሥ ከቅድስት እናቱ እሌኒና ከአረማዊ አባቱ ቁንስጣ በበራንጥያ ተወለደ።
ዘመኑ ዘመነ ዐጸባ /የመከራ ጊዜ/ ወይም የሰማዕታት ዘመን በመሆኑ ክርስቲያኖች በግፍ የሚጨፈጨፉበት ወቅት ነበር። ክርስቲያኖችን ከምድረ ገፅ ለማጥፋት በተደረገው የ40 ዓመታት ዘመቻ አብያተ-መቃድስና መጻሕፍት ተቃጠሉ። ብዙዎቹ በየበርሃው ተሰደዱ። ሚሊየኖች በግፍ አለቁ።
የዚሕን ዘመን መከራ በውል ያልተረዳ ሰው ቅዱስ ቆንጠንጢኖስን ሊያከብር አይችልም። ምክንያቱም ምክንያቱም ይህን የመከራ ዘመን በፈቃደ #እግዚአብሔር አስቁሞ ቀርነ-ሃይማኖት የቆመው፣ ብዙ ሥርዓት የተሠራው፣ ቤተ ክርስቲያንም ያበራችው በዘመኑ ነውና።
ቅዱሱ ንጉሥ ለሁሉም ነቢያት ሐዋርያትና ሰማዕታት አብያተ ክርስቲያናትን ራሱ በመሠረታት በቁስጥንጥንያ አንጿል። በዘመኑ ቤተ ክርስቲያን በሰላም ኖራለት፡ በኃይለ #መስቀሉ ጠላት ጠፍቶለት ኑሮ በዚህች ቀን አርፏል።
ይህቺ ቀን ታላቁ ንጉሥ በፈለገ ኮቦር ቅዱስ #መስቀልን የተመለከተባት ናት። መክስምያኖስን ሊወጋ ወደ ሮም በተጓዘ ጊዜ በሰማይ ላይ መድኅን #መስቀል ተዘርግቶ በላዩ ላይ "ኒኮስጣጣን" የሚል በዮናኒ ልሳን ተጽፎበት ተመልክቷል።
ይህንንም "በዚህ ጠላትህን ድል ታደርጋለህ" ማለት ነው ብለው ተርጉመውለታል። እርሱም በጋሻው፣ በጦሩ፣ በሰይፉ፣ በፈረሱ ላይ የ #መስቀል ምልክትን አድርጐ ማሕደረ ሰይጣን መክስምያኖስን ድል ነስቶታል። እኛንም በሞገሰ #መስቀሉ ይጠብቀን።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_አባ_ቅፍሮንያ
በዚህችም ቀን የአረማዊ መኰንን ልጅ የነበረ አባ ቅፍሮንያ አረፈ። ከዕለታትም በአንዲቱ ስሙ መርቆሬዎስ የሚባል መነኰስ ከአባ ጳኵሚስ ገዳም ወደ ሀገሩ መጣ እርሱ ክርስቲያን እንደሚሆን በእርሱ ላይ ትንቢት ተናገረ።