Telegram Web Link
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ነሐሴ_6_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
1ኛ ቆሮንቶስ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁰ የእግዚአብሔር ጸጋ እንደ ተሰጠኝ መጠን እንደ ብልሃተኛ የአናጺ አለቃ መሠረትን መሠረትሁ፥ ሌላውም በላዩ ያንጻል። እያንዳንዱ ግን በእርሱ ላይ እንዴት እንዲያንጽ ይጠንቀቅ።
¹¹ ከተመሠረተው በቀር ማንም ሌላ መሠረት ሊመሠርት አይችልምና፥ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
¹² ማንም ግን በዚህ መሠረት ላይ በወርቅ ቢሆን በብርም በከበረ ድንጋይም በእንጨትም በሣርም ወይም በአገዳ ቢያንጽ፥ የእያንዳንዱ ሥራ ይገለጣል፤
¹³ በእሳት ስለሚገለጥ ያ ቀን ያሳያልና፥ የእያንዳንዱም ሥራ እንዴት መሆኑን እሳቱ ይፈትነዋል።
¹⁴ ማንም በእርሱ ላይ ያነጸው ሥራ ቢጸናለት ደመወዙን ይቀበላል፤
¹⁵ የማንም ሥራ የተቃጠለበት ቢሆን ይጎዳበታል፥ እርሱ ራሱ ግን ይድናል ነገር ግን በእሳት እንደሚድን ይሆናል።
¹⁶ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን?
¹⁷ ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ።
¹⁸ ማንም ራሱን አያታልል፤ ከእናንተ ማንም በዚች ዓለም ጥበበኛ የሆነ ቢመስለው ጥበበኛ ይሆን ዘንድ ሞኝ ይሁን።
¹⁹-²⁰ የዚህች ዓለም ጥበብ በእግዚአብሔር ፊት ሞኝነት ነውና። እርሱ ጥበበኞችን በተንኰላቸው የሚይዝ፤ ደግሞም፦ ጌታ የጥበበኞችን አሳብ ከንቱ እንደ ሆነ ያውቃል ተብሎ ተጽፎአልና።
²¹ ስለዚህም ማንም በሰው አይመካ። ነገር ሁሉ የእናንተ ነውና፤
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
1ኛ ጴጥሮስ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹-² እንዲሁም፥ እናንተ ሚስቶች ሆይ፥ ከባሎቻችሁ አንዳንዱ ለትምህርት የማይታዘዙ ቢኖሩ፥ በፍርሃት ያለውን ንጹሑን ኑሮአችሁን እየተመለከቱ ያለ ትምህርት በሚስቶቻቸው ኑሮ እንዲገኙ ተገዙላቸው።
³ ለእናንተም ጠጕርን በመሸረብና ወርቅን በማንጠልጠል ወይም ልብስን በመጎናጸፍ በውጭ የሆነ ሽልማት አይሁንላችሁ፥
⁴ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ።
⁵ እንዲህ በቀድሞ ዘመን በእግዚአብሔር ተስፋ ያደረጉት ቅዱሳት ሴቶች ደግሞ ለባሎቻቸው ሲገዙ ተሸልመው ነበርና፤
⁶ እንዲሁም ሣራ ለአብርሃም፦ ጌታ ብላ እየጠራችው ታዘዘችለት፤ እናንተም ከሚያስደነግጥ ነገር አንዳች እንኳ ሳትፈሩ መልካም ብታደርጉ ልጆችዋ ናችሁ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 16
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹³ በሰንበት ቀንም ከከተማው በር ውጭ የጸሎት ስፍራ በዚያ መሆኑን ስላሰብን ወደ ወንዝ አጠገብ ወጣን፤ ተቀምጠንም ለተሰበሰቡት ሴቶች ተናገርን።
¹⁴ ከትያጥሮን ከተማም የመጣች ቀይ ሐር ሻጭ እግዚአብሔርን የምታመልክ ልድያ የሚሉአት አንዲት ሴት ትሰማ ነበረች፤ ጳውሎስም የሚናገረውን ታዳምጥ ዘንድ ጌታ ልብዋን ከፈተላት።
¹⁵ እርስዋም ከቤተ ሰዎችዋ ጋር ከተጠመቀች በኋላ፦ በጌታ የማምን እንድሆን ከፈረዳችሁልኝ፥ ወደ ቤቴ ገብታችሁ ኑሩ ብላ ለመነችን፤ በግድም አለችን።
¹⁶ ወደ ጸሎት ስፍራም ስንሄድ፥ የምዋርተኝነት መንፈስ የነበረባት ለጌቶችዋም እየጠነቈለች ብዙ ትርፍ ታመጣ የነበረች አንዲት ገረድ አገኘችን።
¹⁷ እርስዋ ጳውሎስንና እኛን እየተከተለች፦ የመዳንን መንገድ የሚነግሩአችሁ እነዚህ ሰዎች የልዑል አምላክ ባሪያዎች ናቸው ብላ ትጮኽ ነበር።
¹⁸ ይህንም እጅግ ቀን አደረገች። ጳውሎስ ግን ተቸገረና ዘወር ብሎ መንፈሱን፦ ከእርስዋ እንድትወጣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አዝሃለሁ አለው፤ በዚያም ሰዓት ወጣ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#ነሐሴ_6_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇

✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"ወይሰግዳ ሎቱ አዋልደ ጢሮስ በአምኃ። ወለገጽኪ ይትመሀለሉ ኵሎሙ አሕዛብ ብዑላነ ምድር። ኵሉ ክብራ ለወለተ ንጉሥ ሐሴቦን"። መዝ 44፥12-13።
"የጢሮስ ሴቶች ልጆች እጅ መንሻን ይዘው ይሰግዱለታል። የምድር ባለጠጎች አሕዛብ በፊትህ ይማለላሉ። ለሐሴቦን ንጉሥ ልጅ ሁሉ ክብርዋ ነው፤ ልብስዋ የወርቅ መጐናጸፊያ ነው"። መዝ 44፥12-13።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#ነሐሴ_6_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ማርቆስ 16
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁹ ከሳምንቱም በመጀመሪያው ቀን ማልዶ በተነሣ ጊዜ፥ አስቀድሞ ሰባት አጋንንት ላወጣላት ለመግደላዊት ማርያም ታየ።
¹⁰ እርስዋ ሄዳ ከእርሱ ጋር ሆነው ለነበሩት ሲያዝኑና ሲያለቅሱ ሳሉ አወራችላቸው፤
¹¹ እነርሱም ሕያው እንደ ሆነ ለእርስዋም እንደ ታያት ሲሰሙ አላመኑም።
¹² ከዚህም በኋላ ከእነርሱ ለሁለቱ ወደ ባላገር ሲሄዱ በመንገድ በሌላ መልክ ተገለጠ፤
¹³ እነርሱም ሄደው ለሌሎቹ አወሩ፤ እነዚያንም ደግሞ አላመኑአቸውም።
¹⁴ ኋላም በማዕድ ተቀምጠው ሳሉ ለአሥራ አንዱ ተገለጠ፥ ተነሥቶም ያዩትን ስላላመኑአቸው አለማመናቸውንና የልባቸውን ጥንካሬ ነቀፈ።
¹⁵ እንዲህም አላቸው፦ ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ።
¹⁶ ያመነ የተጠመቀም ይድናል፥ ያላመነ ግን ይፈረድበታል።
¹⁷ ያመኑትንም እነዚህ ምልክቶች ይከተሉአቸዋል፤ በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ፤ በአዲስ ቋንቋ ይናገራሉ፤ እባቦችን ይይዛሉ፥
¹⁸ የሚገድልም ነገር ቢጠጡ አይጎዳቸውም፤ እጃቸውን በድውዮች ላይ ይጭናሉ እነርሱም ይድናሉ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
የሚቀደሰው ቅዳሴ የ #እመቤታች_የማርያም_ቅዳሴ ነው። መልካም የሱባኤ የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
አኵሱም ጰንጠሌዎን ገዳም ውስጥ የሚገኘው የማርያም መግደላዊት ቤተ ክርስቲያን!
ነሐሴ 6 ዓመታዊ የዕረፍት በዓሏ በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ይውላል። ከበዓለ ዕረፍቷ በረከት ይክፈለን!!!
#ነሐሴ_7

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ነሐሴ ሰባት በዚች አምላክን የወለደች #የእመቤታችን_የድንግል_ማርያምን ፅንስቷ ነው፣ የሐዋርያት አለቃ የከበረ #ሐዋርያው_ቅዱስ_ጴጥሮስ በዓል ነው፣ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት #አባ_ጢሞቴዎስ አረፈ፣ የራኄል ልጅ #ቅዱስ_ዮሴፍ ተወለደ፣ ዳግመኛ በዚህች ቀን #እግዚአብሔርን የሚወድ የኢትዮጵያ ንጉሥ #ናዖድ ዕረፍቱ ነው።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#በዓለ_ጽንሰታ_ለእግዝእትነ_ማርያም

ነሐሴ ሰባት በዚች ቀን እግዚአብሔር የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤልን ወደ ከበረና ከፍ ከፍ ወዳለ ጻድቅ ኢያቄም ላከው አምላክን የወለደች የእመቤታችን የድንግል ማርያምን ፅንስቷንና ልደቷን በእርሷም ለዓለሙ ሁሉ ድኅነትና ተድላ ደስታ እንደሚሆን ነገረው።

ይህ ጻድቅም ሰው ኢያቄምና የከበረች ሚስቱ ሐና ልጅ ሳይወልዱ ሸመገሉ የከበረች ሐና መካን ሁናለችና ስለዚህም እጅግ ያዝኑ ነበር የእስራኤል ልጆች ልጅ ያልወለደውን ከእግዚአብሔር በረከትን ያጣ ነው እያሉ ያቃልሉት ነበርና። እነርሱም ልጅን ይሰጣቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ዘወትር ፈጽሞ ይለምኑ ነበር። ከዚህም በኋላ ወንድ ልጅን ወይም ሴት ልጅን ቢወልዱ ለእግዚአብሔር ቤት አገልጋይ ሊያደርጉ ስለትን ተሳሉ።

የከበረ ኢያቄምም በተራራ ላይ ሳለ ሲጸልይና ሲማልድ እነሆ በላዩ እንቅልፍ እንቅልፍ ብሎት አሸለበ ያን ጊዜ ከእግዚአብሔር የተላከ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ተገለጸለት እንዲህም አለው ሚስትህ ሐና ትፀንሳለች ዓለሙ ሁሉ ደስ የሚሰኝባትን የብዙዎችም ዐይነ ልቡ ናቸው በእርሷ የሚበራላችውን በእርሷም ድኅነት የሚሆንባትን ሴት ልጅን ትወልድልሃለች።

በነቃ ጊዜም ወደ ቤቱ ሒዶ ለሚስቱ ለቅድስት ሐና ነገራት ራእይዋን እውነት እንደሆነች አመኑዋት ከዚህም በኋላ ነሐሴ ሰባት በዚች ቀን የከበረች ሐና ፀነሰች ለዓለም ሁሉ መመኪያ የሆነች በሁለት ወገን ድንግል የሆነች የአምላክ እናት እመቤታችንን ማርያምን ወለደቻት።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ጴጥሮስ_ሐዋርያ

በዚህችም ቀን የሐዋርያት አለቃ የከበረ ሐዋርያ ጴጥሮስ በዓል ነው። በዚች ቀን ጌታችን የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ እርሱ እንደሆነ በሐዋርያት መካከል ታምኗልና።

በከበረ ወንጌል እንደተባለ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ፊልጶስ ቂሣርያ አገር በደረሰ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል ብሎ ጠየቃቸው እርሱ ልብን ኲላሊትን የሚመረምር ሰዎች የሚያስቡትን ሁሉ የሚያውቅ ሲሆን።

ያን ጊዜ ሐዋርያት ተጠራጣሪዎች ስለነበሩ ስለዚህ ያሰቡትን በልባቸው ያለውን እንዲናገሩ ከከተማ ውጭ አወጣቸው። ከእርሳቸውም ኤልያስ እንደሆነ የሚአስቡ አሉ ወይም ከቀደሙት ነቢያት አንዱ እንደሆነ የሚሉም ነበሩ። ጴጥሮስም በእነርሱ ላይ ተቆጥቶ ለምን እንዲህ ታስባላችሁ እርሱ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ነው እንጂ አላቸው።

ስለዚህም የጴጥሮስን ሃይማኖት በመካከላቸው ይገልጥ ዘንድና ግልጥ ሊያደርግ ወደ ውጭ አወጣቸው። እንዲሁም በጠየቃቸው ጊዜ ኤልያስ እንደሆንክ ወይም ከቀደሙት ነቢያት አንዱ እንደሆንክ ሰዎች ይናገራሉ በማለት እነርሱ የልባቸውን ተናገሩት። ጴጥሮስ ግን አንተ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ነህ ብሎ በእውነት ምስክርን ሆነ።

ስለዚህም ጌታችን አመሰገነው የመንግሥተ ሰማያትንም ቊልፍ ሰጠው ። ከዚያች ቀን ወዲህ የሐዋርያት ሁሉ አለቃ ሆነ በእርሱም የሊቃነ ጳጳሳት የኤጲስቆጶሳት የቀሳውስትና የዲያቆናት ሹመት ተሰጠ። የቤተ ክርስቲያንም መሠረት ተባለ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አባ_ጢሞቴዎስ_ሊቀ_ዻዻሳት

በዚህችም ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሃያ ስድስተኛ የሆነ የከበረ አባት የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ጢሞቴዎስ አረፈ። ይህንንም ቅዱስ በእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት ይሆን ዘንድ የክብር ባለቤት ጌታችን መርጦት ተጋዳይ የነበረ አባ ዲዮስቆሮስ በደሴተ ጋግራ ከአረፈ በኋላ ሊቀ ጵጵስና ተሾመ።

ይህም አባት ጢሞቴዎስ ብዙ መከራ ደርሶበታል። ንጉሥ መርቅያን ለእስክንድርያ አገር ሌላ መናፍቅ ሊቀ ጳጳሳት ሹሞ አባት ጢሞቴዎስን አስቀድሞ አባ ዲዮስቆሮስ ተሰዶባት ወደ ነበረች ደሴተ ጋግራ አጋዘው። መርቅያንም ከሞተ በኋላ የእስክንድርያ ሰዎች ተነሥተው መርቅያን የሾመውን ሊቀ ጳጳሳት ገደሉት አባት ዲዮስቆሮስ እንዳዘዘ አባ ጢሞቴዎስን መልሰው ሾሙት።

ከዚህም በኋላ የመርቅያን ልጅ ልዮን ነገሠ ያን ጊዜ አባ ጢሞቴዎስን ሁለተኛ ወደ ደሴተ ጋግራ አጋዘው በዚያም ዐሥር ዓመት ኖረ ልዮን እስከ ሞተ ድረስ ከእርሱም ኋላ ዘይኑን ነገሠ። ያን ጊዜም አባ ጢሞቴዎስን ወደ መንበረ ሢመቱ በታላቅ ክብር መለሰው ሕዝቡንም እያስተማራቸውና እየመከራቸው በቀናች ሃይማኖትም እያጸናቸው ኖረ።

በወንጌላዊ ማርቆስ ወንበርም ሃያ ሁለት ዓመት ኖረ እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም አረፈ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ዮሴፍ_ጻድቅ

በዚህችም ቀን የራኄል ልጅ ዮሴፍ ተወለደ። አባቱ ያዕቆብ እናቱ ራኄል ይባላሉ፡፡ ለአባቱ 11ኛ ልጅ ነው፡፡ አባቱ ያዕቆብ የወንድሙን የኤሳውን በረከት ከአባቱ ከወሰደ በኋላ ከኤሳው ሸሽቶ ወደ አጎቱ ላባ ዘንድ ተሰዶ 14 ዓመት ለላባ ተገዝቶ ራሄልንና ርብቃን አግብቶ ብዙ ልጆችን ወለደ፡፡ ሀብት ንብረትም ካፈራ ከ21 ዓመት በኋላ ወደ አባቱ አገር ተመልሶ ከወንድሙ ጋር ታረቀ፡፡ ያዕቆብም በምድረ በዳ አቅራቢያ ባለች አብርሃም ይቀመጥባት ከነበረ አገር ከአባቱ ከይስሐቅ ዘንድ ደረሰ፡፡ ይህችውም በከነዓን ያለችው ኬብሮን ናት፡፡ አባቱ ይስሐቅ አብርሃም ይቀመጥባት በነበረችው የወይራ ዛፍ ሥር ተቀምጦ አገኘው፡፡ ከዚህም በኋላ ይስሐቅ አርጅቶ ዘመኑን ጨርሶ ሞተ፡፡ ያዕቆብም አባቱ ይስሐቅ ይኖርባት በነበረች አገር ኖረ፡፡ ያንጊዜም ልጁ ዮሴፍ 17 ዓመት ሆኖት ነበር፡፡ እርሱም ከአባቱ ከያዕቆብ ሚስቶች ከዘለፋ ልጆችና ከባላ ልጆች ጋር የአባቱን በጎች ይጠብቅ ነበር፡፡ ያዕቆብም በእርጅናው ዘመን ወልዶታልና አብልጦ ይወደው ነበር፡፡

ወንድሞቹም በዚህ ምክንያት ጠሉት፡፡ ዮሴፍም ሕልም አልሞ ሕልሙን ለወንድሞቹ ነገራቸው፡፡ ዮሴፍም ያየው ሕልም 11ዱ ወንድሞቹና አባቱም ጭምር ለዮሴፍ እንደሚገዙለትና እንደሚሰግዱለት የሚያሳይ ነበር፡፡ ይህንንም ሕልሙን ሲሰሙ ወንድሞቹ ይበልጥ ጠሉት፡፡

የዮሴፍም ወንድሞች የአባታቸውን በጎች ይዘው ወደ ሴኬም ጎዳና ሄዱ፡፡ አባቱም ዮሴፍን ‹‹ወንድሞችህን አይተሃቸው ና›› ብሎ ስንቃቸውን ቋጥሮ ወደ ቆላው ላከው፡፡ ሴኬምም እንደደረሰ አንድ ሰው ወንድሞቹ ያሉበትን አሳይቶት ወደ ዶታይን ወረደ፤ በዶታይንም አገኛቸው፡፡ እነርሱም በሩቅ ሳለ አዩትና ወደ እነርሱ ገና ሳይቀርብ ይገድሉት ዘንድ በእርሱ ላይ ተማከሩ፡፡ ‹‹እንግደለውና በአንድ ጕድጓድ ውስጥ እንጣለው፡፡ ክፉ አውሬም በላው እንላለን›› ብለው ሲመካከሩ ከእነርሱ ውስጥ ሮቤል ይህን ሲሰማ ‹‹ሕይወቱን አናጥፋ፣ ደም አታፍስሱ፤ በዚህች ምድረ በዳ ባለችው ጕድጓድ ጣሉት፣ ነገር ግን እጃችሁን አትጣሉበት›› አላቸው፡፡ ሮቤልም እንዲህ ማለቱ ከእጃቸው ሊያድነውና ወደ አባቱ ሊመልሰው ነው፡፡ ዮሴፍንም ቀሚሱን ገፈው ወስደው ወደ ቀበሮ ጕድጓድ ጣሉት፡፡ ጉድጓዱንም በድንጋይ ገጥመው በላይ ተቀምጠው ዮሴፍ ያመጣላቸውን እንጀራ እየተመገቡ ሳለ የእስማኤላውያን ነገዶች ወደ ግብፅ ለመውረድ ከገለዓድ ሲመጡ አይተው በይሁዳ ምክር ወንድማቸውን ከጕድጓድ አውጥተው ለእስማኤላውያን በሀያ ብር
ሸጡት፤ እስማኤላውያንም ዮሴፍን ወደ ግብፅ ወሰዱት፡፡ የፈርዖን ጃንደረባ የዘበኞቹም አለቃ የሚሆን የግብፅ ሰው ጲጥፋራ ዮሴፍን ወደ ግብፅ ካወረዱት ከእስማኤላውያን እጅ ገዛው፡፡ እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋር ነበረ፣ ሥራውም የተከናወነለት ሰው ሆነ፡፡ ጌታውም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር እንዳለ፣ እርሱ የሚሠራውንም ሁሉ እግዚአብሔር በእጁ እንዲያከናውንለት አየ፡፡ ዮሴፍም በጌታው ፊት ሞገስን ስላገኘ በቤቱ ላይ ሾመው፣ ያለውንም ሁሉ በእጁ ሰጠው፡፡ በቤቱ ባለውም ሁሉ ላይ ከሾመው በኋላ እግዚአብሔር የግብፃዊውን ቤት ስለ ዮሴፍ ባረከው፤ የእግዚአብሔር በረከት በውጪም በግቢም ባለው ሁሉ ላይ ሆነ፡፡ ጲጥፋራም ያለውን ሁሉ ለዮሴፍ አስረከበ። የዮሴፍም ፊቱ መልከ መልካምና ውብ ነበረ፡፡ ይኸውም ምሳሌ ነው፡፡ ዮሴፍ የጌታችን፣ ወንድሞቹ ደግሞ የአይሁድ ምሳሌ ናቸው፡፡ ዮሴፍ ምግባቸውን ይዞላቸው ቢሄድ ከበው እንደደበደቡት ሁሉ ጌታችንም ‹‹እኔ ግን እላችኋለሁ…›› እያለ የነፍሳቸውን ምግብ ቢያስተምራቸው አይሁድ ጠልተውት ገድለውታል፡፡ ዮሴፍ እንዲሸጥ ሀሳብ ያመጣው ይሁዳም ጌታችንን የሸጠው የይሁዳ ምሳሌ ነው፡፡ ዮሴፍ በግብፅ ሕያው በከነዓን ግን ምውት እንደሆነ ሁሉ ጌታችንም በመለኮቱ ሕያው ሲሆን በትስብእቱ ግን ምውት ሆኗል፡፡

ወንድሞቹም የዮሴፍን ቀሚስ ወስደው የፍየል አውራም አርደው ቀሚሱን በደም ነክረው ወደ አባታቸው ሄደው ‹‹ይህንን አገኘን፣ ይህ የልጅህ ልብስ እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ እስኪ እየው›› አሉት፡፡ ያቆዕብም ‹‹ይህ የልጄ ቀሚስ ነው፤ ክፉ አውሬ በልቶታል›› ካለ በኋላ ልብሱን ቀዶ በወገቡም ማቅ ታጥቆ ለልጁ ብዙ ጊዜ አምርሮ ስላለቀሰ ዐይኑ ጠፋ፡፡

ዮሴፍም ጌታውን በቅንነት እያገለገለ ሲኖር የጌታው ሚስት ባሏ በሌለበት ጠብቃ በዮሴፍ ላይ የዝሙት ዐይኗን ጣለችበትና ‹‹ከእኔ ጋር ተኛ›› አለችው፡፡ ዮሴፍም ‹‹እነሆ ጌታዬ በቤቱ ያለውን ምንም ምን የሚያውቀው የለም፣ ያለውንም ሁሉ ለእኔ አስረክቦኛል፤ ለዚህ ቤት ከእኔ የሚበልጥ ሰው የለም፤ ሚስቱ ስለሆንሽ ከአንቺም በቀር ያልሰጠኝ ነገር የለም፤ እንዴት ይህን ትልቅ ክፉ ነገር አደርጋለሁ? በእግዚአብሔር ፊት እንዴት ኃጢአትን እሠራለሁ?›› አላት፡፡ እርሷ ግን ስለዚህ ነገር በየጊዜው ትጨቀጭቀው ነበር፡፡ አንድ ቀን ወደ ቤቱ በገባ ጊዜ በቤት ውስጥ ከቤት ሰዎች ማንም ስላልነበረ ወደ እርሱ ገብታ ከእኔ ጋር ተኛ ስትል ልብሱን ተጠማጥማ ያዘች፤ እርሱም ልብሱን በእጅዋ ትቶላት ሸሽቶ ወደ ውጭ ወጥቶ ሄደ፡፡ የጲጥፋራ ሚስት ግን የቤቷን ሰዎች ጠርታ ‹‹እዩ ዕብራዊው ሰው ከእኔ ጋር ሊተኛ ወደ እኔ ገባ፣ እኔም ድምፄን ከፍ አድርጌ ስጮኽ ቢሰማ ልብሱን በእኔ ዘንድ ጥሎ ሸሸ ወደ ውጭም ወጣ›› ብላ በሐሰት ከሰሰችው፡፡ ባሏም ሲመጣ እንዲሁ ብላ ነገረችው፡፡ ባሏም የእርሷን ቃል በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ፡፡ ዮሴፍን ይዞ እስር ቤት ጣለው፡፡ እግዚአብሔርም ከዮሴፍ ጋር ነበረ፣ ምሕረትንም አበዛለት፥ በግዞት ቤቱም አለቃ ፊት ሞገስን ሰጠው፡፡ የሚያደርገውንም ሁሉ እግዚአብሔር ያቀናለት ነበር፡፡

የጲጥፋራ ሚስት የኃጢአት ምሳሌ ስትሆን ዮሴፍ የንጽሕና ምሳሌ ነው፡፡ ኃጢአት ደርሳ ሥሩኝ ሥሩኝ ስትላችሁ የንጽሕናን የቅድስናን ነገር አስባችሁ ፈጥናችሁ ከእርሷ ተለዩ ሲል ነው፡፡ ንጽሕናችሁን በኃጢአት አታቆሽሹ አለ፡፡ አንድም የጲጥፋራ ሚስት የዚህ ዓለም ዮሴፍ የመናንያን ምሳሌ ነው፡፡ ዮሴፍን የጲጥፋራ ሚስት ሽንገላ ሳያታልለው ጥሏት እንደሸሸ ሁሉ መናንያንም የዚህ ዓለም ሀብት፣ ንብረት፣ ቤት፣ ልጅ፣ ባል፣ ሚስት… ሳያታልላቸው የዓለምን ጣዕም ሸሽተው ገዳም ይገባሉና ነው፡፡

ዮሴፍ ከታሰረ ከሁለት ዓመት በኋላ ንጉሡ ፈርዖን ሕልም አየ፡፡ በነጋም ጊዜ ነፍሱ ታውካ የግብፅን ሕልም ተርጓሚዎችና ጠቢባንን ሁሉ ሰብስቦ እንዲተረጉሙለት ሕልሙን በዝርዝር ነገራቸው፡፡ ነገር ግን ሊተረጉሙለት አልቻሉም ነበር፡፡ የንጉሡም የጠጅ አሳላፊ አስቀድም ከዮሴፍ ጋር ታስሮ ሳለ እርሱ ያየውን ሕልም ዮሴፍ ተርጉሞለት እንደነገረው ሆኖለት ስለነበር በዚህ ጊዜ የጠጅ አሳላፈው ለንጉሡ ስለ የሴፍ ነገረው፡፡ ፈርዖንም ዮሴፍን አስመጥቶ ሕልሙን ነግሮት ተረጎመለት፡፡ በፈርዖንም ሕልም መሠረት ሰባት ዓመታት ጥጋብ እንደሚሆንና ከዚያም በኋላ ሰባት የርኃብ ዓመታት እንደሚመጡ ነገረው፡፡ ፈርዖንም ዮሴፍን ‹‹እኔ በዙፋኔ ብቻ ከአንተ እበልጣለሁ›› ብሎ በቤቱና በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ ሾመው፡፡ ቀለበቱንም አውጥቶ አሰረለት፡፡ ይህም የሆነው በ30 ዘመኑ ነው፡፡ ዮሴፍ በእናት በባቱ ቤት 17 ዓመት፣ በጲጥፋራ ቤት 10 ዓመት፣ በእስር ቤት ሁለት ዓመት ተቀምጦ ባጠቃላይ ልክ 30 ዓመት ሲሆነው በፈርዖን ፊት ለሹመት ቆመ፡፡ ይኸውም ምሳሌ ነው፡፡ ዮሴፍ በ30 ዘመኑ ለሹመት በፈርዖን ፊት እንደቆመ ሁሉ ጌታችን መድኃኔዓም ክርስቶስም በጲላጦስ ፊት ለፍርድ የቆመው በ30 ዘመኑ ነው፡፡

ዮሴፍም በግብፅ ምድር ዞሮ የሰባቱን ዓመት እጅግ ብዙ እህል ሰበሰበ፡፡ ሰባቱም የጥጋብ ዘመን ሲያልፍ ሰባቱ የርኃብ ዘመን በጀመረ ጊዜ በሀገሩ ሁሉ ታላቅ ርኃብ ሆነ ነገር ግን በግብፅ ምድር ብቻ እህል ነበር፡፡ ንጉሡም ከየሀገሩ ሁሉ ወደ እርሱ የሚመጡትን ወደ ዮሴፍ እየላካቸው ዮሴፍም እህል ከጎተራ እያወጣ ይሸጥላቸው ነበር፡፡ የዮሴፍ አባት ያዕቆብ በግብፅ እህል እንዳለ በሰማ ጊዜ ልጆቹን እህል እንዲሸምቱ ወደ ግብፅ ላካቸው፡፡ ነገር ግን ክፉ እንዳያገኘው ብሎ የዮሴፍን ወንድም ብንያምን ከእነርሱ ጋር አላከውም ነበር፡፡ ዮሴፍም ዐሥሩ ወንድሞቹ ከሕዝቡ ጋር ገብተው ሲሰግዱለት አይቶ ዐወቃቸው፣ እነርሱ ግን የሰገዱለት የሀገሩ ገዥ ስለነበረ ነው እንጂ ወንድማቸው እንደሆነ ዐላወቁትም ነበር፡፡ ዮሴፍም በልጅነቱ ከእነርሱ ጋር ሳለ ያየውን ሕልም አሰበ፡፡ እነርሱም ስለራሳቸው በነገሩት ጊዜ ‹‹እቤት የቀረውን ወንድማችሁን አምጡ›› ብሎ ለርኃባቸው እህሉን ሰጥቶ አንዱን (ስምዖንን) ለይቶ አስቀርቶ ዘጠኙን ስንቃቸውን ጭኑ ወደ አባታቸው ቤት ወደ ከነዓን ላካቸው፡፡ ሄደውም የሆነውን ለያዕቆብ ነገሩት፡፡

እርሱም ከወንድማቸው ጋር ድጋሚ ወደ ግብፅ ላካቸውና ድጋሚ በዮሴፍ ፊት ሰግደው ሰላምታ አቅርበው እጅ መንሻን አመጡለት፡፡ ዮሴፍም የእናቱን ልጅ ብንያምን ባየው ጊዜ ወደ ውስጥ ገብቶ አለቀሰ፡፡ ዮሴፍ ቆይቶ ራሱን ገለጠላቸው፡፡ ያደረጉበትንም ነገራቸው፡፡ የርኃቡም ዘመን ገና 5 ዓመት ይቀረው ነበርና ዮሴፍ ወንድሞቹን ‹‹ስለሸጣችሁኝ አትዘኑ እነሆ ሕይወታችሁን ለማዳን እግዚአብሔር አስቀድሞ ከእናንተ በፊት ወደ ግብፅ ልኮኛል›› አላቸው፡፡ አባቱንም ወደ እርሱ እንዲያመጡት ላካቸው፡፡ ያዕቆብም ከነቤተሰቡ ንብረቱንም ሁሉ ሰብስቦ ወደ ግብፅ ወረደ፡፡ ልጁን ዮሴፍንም ባየው ጊዜ እያለቀሰ አቅፎ ከሳመው በኋላ ሞቱን ተመኘ፡፡

በግብፅ የያዕቆብ የልጅ ልጆቹ ቁጥር 66 ሆነ፡፡ ከዮሴፍም ልጆች ጋር አንድ ላይ 70 ሆኑ፡፡ ያዕቆብም ፈርዖንን ገብቶ ከባረከው በኋላ በግብፅ ጌሤም ምድር 17 ዓመት ተቀመጠ፡፡ ዘመኑም 140 በሆነ ጊዜ በሞት ማረፉን ዐውቆ ልጁን ዮሴፍን ጠርቶ በአባቶቹ መቃብር ቤት ውስዶ እንዲቀብረው ነገረው፡፡ የዮሴፍንም ሁለቱን ልጆች ምናሴንና ኤፍሬምን ባረካቸው፡፡ ‹‹አባቶቼ አብርሃምና ይስሐቅ በፊቱ የሄዱለት እርሱ እግዚአብሔር፣ ከታናሽነቴ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኔን የመገበኝ እግዚአብሔር፣ ከክፉ ነገር ሁሉ ያዳነኝ መልአክ እርሱ እነዚህን ብላቴኖች ይባርክ፤ ስሜም የአባቶቼ የአብርሃምና የይስሐቅ ስም በእነርሱ ይጠራ፤
በምድርም መካከል ይብዙ›› ብሎ ባረካቸው፡፡ ያዕቆብም ልጆቹን ጠርቶ ወደፊት የሚሆነውን ሁሉ ይልቁንም የጌታችንን የመወለዱን ነገር በምሳሌ እያደረገ ነገራቸው፡፡ እያንዳንዳቸውንም እንደ በረከታቸው ባረካቸውና በአብርሃምና በይስሐቅ ሣራም በተቀበረችበት መቃብር ወስደው እንዲቀብሩት ከነገራቸው በኋላ በ137 ዕድሜው እግሮቹን በአልጋው ላይ ሰብስቦ በሰላም ዐረፈ፡፡ የግብፅ ሰዎችም 70 ቀን አለቀሱለት፡፡ ዮሴፍም አባቱን ባዘዘው ቦታ በእነ አብርሃም መቃብር ከቀበረው በኋላ ወደ ግብፅ ተመለሰ፡፡

የዮሴፍም ወንድሞች አባታቸው እንደ ሞተ ባዩ ጊዜ ‹‹ምናልባት ዮሴፍ ይጠላን ይሆናል፣ ባደረግንበትም ክፋት ሁሉ ብድራት ይመልስብን ይሆናል›› ብለው ፈርተው ወደ ዮሴፍ መልዕክት ልከው ‹‹አባትህ ገና ሳይሞት ‹ዮሴፍን እባክህ የወንድሞችህን በደል ኃጢአታቸውንም ይቅር በል፣ እነርሱ በአንተ ከፍተውብሃልና፤ አሁንም እባክህ የአባትህ አምላክ ባሪያዎች የበደሉህን ይቅር በል› ብሎሃል›› ብለው ላኩለት፡፡ ወንድሞቹም መጥው በፊቱም ሰግደው ‹‹እነሆ እኛ ለአንተ ባሪያዎችህ ነን፣ በአባቶችህ አምላክ ባሮችህን ኃጢአታችንን ይቅር በለን›› አሉት፡፡ ዮሴፍም እንዲህ ሲሉት አለቀሰ፡፡ እርሱም ‹‹ሁሉም ነገር በእግዚአብሔር ፈቃድ የተደረገ ስለሆነ አይዟችሁ አትፍሩ›› እያለ እንዳይፈሩ አጽናናቸው፤ደስም አሰኛቸው፡፡ ዮሴፍም በግብፅ ተቀምጦ 110 ዓመት ኖረ፡፡

የኤፍሬምን ልጆች እስከ ሦስት ትውልድ ካየ በኋላ ወንድሞቹን ጠርቶ ‹‹እኔ እሞታለሁ፤ እግዚአብሔርም መጎብኘትን ይጎበኛችኋል፣ ከዚህችም ምድር ያወጣችኋል፤ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም ወደማለላቸው ምድር ያደርሳችኋል፡፡ እግዚአብሔር ሲያስባችሁ አጥንቴን ከዚህ አንሥታችሁ ከእናንተ ጋር ውሰዱ እንጂ ከዚህ አትተውት›› ብሎ አማላቸው፡፡ ዮሴፍም በ110 ዕድሜው በሰላም ዐረፈ፡፡ በሽቱ አሽተው በግብፅ ምድር በሣጥን ውስጥ አኖሩት፡፡ ዮሴፍም ‹‹እግዚአብሔር ሲያስባችሁ አጥንቴን ከዚህ አንሥታችሁ ከእናንተ ጋር ውሰዱ እንጂ ከዚህ አትተውት›› ማለቱ አንድም ከግብፅ ምድር እንደሚወጡና የአባቶቻቸውን ርስት ከነዓንን እንደሚወርሱ ሲነግራቸው ነው፡፡ ፍጻሜው ግን ግብፅ የመቃብር ከነዓን የትንሣኤ ምሳሌ ናቸው፡፡ አንድም ግብፅ የገሃነም ከነዓን የመንግሥተ ሰማይ ምሳሌ ናቸው፡፡ ያዕቆብም እንዲሁ ብሏልና ዮሴፍም እንዲህ ያለ ስለምን ነው ቢሉ አባቶቻችን እንዲህ ማለታቸው መውጣታችንን ቢያውቁ ነው ብለው እንዲነቁ፣ እንዲተጉ፣ አንድም ለማጸየፍ ነው፣ ‹‹አባቶቻችን አጥንታችን እንኳን ከዚህ አይቅር›› ብለዋል ብለው እንውጣ እንዲሉ ነው፡፡

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ነሐሴ_7 እና #ከገድላት_አንደበት)
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ነሐሴ_7_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ዕብራውያን 9
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ፊተኛይቱም ደግሞ የአገልግሎት ስርዓትና የዚህ ዓለም የሆነው መቅደስ ነበራት።
² የመጀመሪያይቱ ድንኳን ተዘጋጅታ ነበርና፥ በእርስዋም ቅድስት በምትባለው ውስጥ መቅረዙና ጠረጴዛው የመስዋዕቱም ኅብስት ነበረባት፤
³ ከሁለተኛውም መጋረጃ ወዲያ ቅድስተ ቅዱሳን የምትባለው ድንኳን ነበረች፥
⁴ በዚያም ውስጥ የወርቅ ማዕጠንት ነበረ ሁለንተናዋም በወርቅ የተለበጠች የኪዳን ታቦት፤ በእርስዋም ውስጥ መና ያለባት የወርቅ መሶብና የበቀለች የአሮን በትር የኪዳኑም ጽላት ነበሩ፥
⁵ በላይዋም ማስተስሪያውን የሚጋርዱ የክብር ኪሩቤል ነበሩ፤ ስለ እነዚህም ስለ እያንዳንዳቸው ልንናገር አሁን አንችልም።
⁶ ይህም እንደዚህ ተዘጋጅቶ ሳለ፥ ካህናት አገልግሎታቸውን እየፈጸሙ ዘወትር በፊተኛይቱ ድንኳን ይገቡባታል፤
⁷ በሁለተኛይቱ ግን ሊቀ ካህናት ብቻውን በዓመት አንድ ጊዜ ይገባባታል፥ እርሱም ስለ ራሱና ስለ ሕዝቡ ስሕተት የሚያቀርበውን ደም ሳይዝ አይገባም፤
⁸ ፊተኛይቱም ድንኳን በዚህ ገና ቆማ ሳለች፥ ወደ ቅድስት የሚወስደው መንገድ ገና እንዳልተገለጠ መንፈስ ቅዱስ ያሳያል።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
1ኛ ጴጥሮስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁶ በመጽሐፍ፦ እነሆ፥ የተመረጠና የከበረን የማዕዘን ራስ ድንጋይ በጽዮን አኖራለሁ በእርሱም የሚያምን አያፍርም ተብሎ ተጽፎአልና።
⁷ እንግዲህ ክብሩ ለእናንተ ለምታምኑት ነው፤ ለማያምኑ ግን አናጢዎች የጣሉት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ የዕንቅፋትም ድንጋይ የማሰናከያም ዓለት ሆነ፤
⁸ የማያምኑ ስለ ሆኑ በቃሉ ይሰናከሉበታልና፤ ለዚህ ደግሞ የተመደቡ ናቸው።
⁹ እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤
¹⁰ እናንተ ቀድሞ ወገን አልነበራችሁም አሁን ግን የእግዚአብሔር ወገን ናችሁ፤ እናንተ ምሕረት ያገኛችሁ አልነበራችሁም አሁን ግን ምሕረትን አግኝታችኋል።
¹¹ ወዳጆች ሆይ፥ ነፍስን ከሚዋጋ ሥጋዊ ምኞት ትርቁ ዘንድ እንግዶችና መጻተኞች እንደ መሆናችሁ እለምናችኋለሁ፤
¹² ስለሚመለከቱት ስለ መልካም ሥራችሁ፥ ክፉ እንደምታደርጉ በዚያ እናንተን በሚያሙበት ነገር፥ በሚጎበኝበት ቀን እግዚአብሔርን ያከብሩት ዘንድ በአሕዛብ መካከል ኑሮአችሁ መልካም ይሁን።
¹³ ስለ ጌታ ብላችሁ ለሰው ሥርዓት ሁሉ ተገዙ፤ ለንጉሥም ቢሆን፥ ከሁሉ በላይ ነውና፤
¹⁴ ለመኳንንትም ቢሆን፥ ክፉ የሚያደርጉትን ለመቅጣት በጎም የሚያደርጉትን ለማመስገን ከእርሱ ተልከዋልና ተገዙ።
¹⁵ በጎ እያደረጋችሁ፥ የማያውቁትን ሞኞች ዝም ታሰኙ ዘንድ እንዲህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነውና፤
¹⁶ አርነት ወጥታችሁ እንደ እግዚአብሔር ባሪያዎች ሁኑ እንጂ ያ አርነት ለክፋት መሸፈኛ እንዲሆን አታድርጉ።
¹⁷ ሁሉን አክብሩ፥ ወንድሞችን ውደዱ፥ እግዚአብሔርን ፍሩ፥ ንጉሥን አክብሩ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 10
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ በቂሣርያም ኢጣሊቄ ለሚሉት ጭፍራ የመቶ አለቃ የሆነ ቆርኔሌዎስ የሚሉት አንድ ሰው ነበረ።
² እርሱም ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር እግዚአብሔርን የሚያመልክና የሚፈራ ለሕዝብም እጅግ ምጽዋት የሚያደርግ ወደ እግዚአብሔርም ሁልጊዜ የሚጸልይ ነበረ።
³ ከቀኑም ዘጠኝ ሰዓት ያህል፦ ቆርኔሌዎስ ሆይ የሚለው የእግዚአብሔር መልአክ ወደ እርሱ ሲገባ በራእይ በግልጥ አየው።
⁴ እርሱም ትኵር ብሎ ሲመለከተው ደንግጦ፦ ጌታ ሆይ፥ ምንድር ነው? አለ። መልአኩም አለው፦ ጸሎትህና ምጽዋትህ በእግዚአብሔር ፊት ለመታሰቢያ እንዲሆን አረገ።
⁵ አሁንም ወደ ኢዮጴ ሰዎችን ልከህ ጴጥሮስ የሚባለውን ስምዖንን አስመጣ።
⁶ እርሱ ቤቱ በባሕር አጠገብ ባለው በቍርበት ፋቂው በስምዖን ዘንድ እንግድነት ተቀምጦአል፤ ልታደርገው የሚገባህን እርሱ ይነግርሃል።
⁷ የተናገረውም መልአክ በሄደ ጊዜ፥ ከሎሌዎቹ ሁለቱን፥ ከማይለዩትም ጭፍሮቹ እግዚአብሔርን የሚያመልክ አንዱን ወታደር ጠርቶ፥
⁸ ነገሩን ሁሉ ተረከላቸው ወደ ኢዮጴም ላካቸው።
⁹ እነርሱም በነገው ሲሄዱ ወደ ከተማም ሲቀርቡ፥ ጴጥሮስ በስድስት ሰዓት ያህል ይጸልይ ዘንድ ወደ ጣራው ወጣ።
¹⁰ ተርቦም ሊበላ ወደደ፤ ሲያዘጋጁለት ሳሉም ተመስጦ መጣበት፤
¹¹ ሰማይም ተከፍቶ በአራት ማዕዘን የተያዘ ታላቅ ሸማ የሚመስል ዕቃ ወደ ምድር ሲወርድ አየ፤
¹² በዚያውም አራት እግር ያላቸው ሁሉ አራዊትም በምድርም የሚንቀሳቀሱት የሰማይ ወፎችም ነበሩበት።
¹³ ጴጥሮስ ሆይ፥ ተነሣና አርደህ ብላ የሚልም ድምፅ ወደ እርሱ መጣ።
¹⁴ ጴጥሮስ ግን፦ ጌታ ሆይ፥ አይሆንም፤ አንዳች ርኵስ የሚያስጸይፍም ከቶ በልቼ አላውቅምና አለ።
¹⁵ ደግሞም ሁለተኛ፦ እግዚአብሔር ያነጻውን አንተ አታርክሰው የሚል ድምፅ ወደ እርሱ መጣ።
¹⁶ ይህም ሦስት ጊዜ ሆነ፥ ወዲያውም ዕቃው ወደ ሰማይ ተወሰደ።
¹⁷ ጴጥሮስም ስላየው ራእይ፦ ምን ይሆን? ብሎ በልቡ ሲያመነታ፥ እነሆ፥ ቆርኔሌዎስ የላካቸው ሰዎች ስለ ስምዖን ቤት ጠይቀው ወደ ደጁ ቀረቡ፤
¹⁸ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው፦ ጴጥሮስ የተባለው ስምዖን በዚህ እንግድነት ተቀምጦአልን? ብለው ይጠይቁ ነበር።
¹⁹ ጴጥሮስም ስለ ራእዩ ሲያወጣ ሲያወርድ ሳለ፥ መንፈስ፦ እነሆ፥ ሦስት ሰዎች ይፈልጉሃል፤
²⁰ ተነሥተህ ውረድ፥ እኔም ልኬአቸዋለሁና ሳትጠራጠር ከእነርሱ ጋር ሂድ አለው።
²¹ ጴጥሮስም ወደ ሰዎቹ ወርዶ፦ እነሆ፥ የምትፈልጉኝ እኔ ነኝ፤ የመጣችሁበትስ ምክንያት ምንድር ነው? አላቸው።
²² እነርሱም፦ ጻድቅ ሰው እግዚአብሔርንም የሚፈራ በአይሁድም ሕዝብ ሁሉ የተመሰከረለት የመቶ አለቃ ቆርኔሌዎስ ወደ ቤቱ ያስመጣህ ዘንድ ከአንተም ቃልን ይሰማ ዘንድ ከቅዱስ መልአክ ተረዳ አሉት።
²³ እርሱም ወደ ውስጥ ጠርቶ እንድግድነት ተቀበላቸው። በነገውም ተነሥቶ ከእነርሱ ጋር ወጣ፥ በኢዮጴም ከነበሩት ወንድሞች አንዳንዶቹ ከእርሱ ጋር አብረው ሄዱ።
²⁴ በነገውም ወደ ቂሣርያ ገቡ፤ ቆርኔሌዎስም ዘመዶቹንና የቅርብ ወዳጆቹን በአንድነት ጠርቶ ይጠባበቃቸው ነበር።
²⁵ ጴጥሮስም በገባ ጊዜ ቆርኔሌዎስ ተገናኝቶ ከእግሩ በታች ወደቀና ሰገደለት።
²⁶ ጴጥሮስ ግን፦ ተነሣ፤ እኔ ራሴ ደግሞ ሰው ነኝ ብሎ አስነሣው።
²⁷ ከእርሱም ጋር እየተነጋገረ ገባ፥ ብዙዎችም ተከማችተው አግኝቶ፦
²⁸ አይሁዳዊ ሰው ከሌላ ወገን ጋር ይተባበር ወይም ይቃረብ ዘንድ እንዳልተፈቀደ እናንተ ታውቃላችሁ፤ ለእኔ ግን እግዚአብሔር ማንንም ሰው ርኵስና የሚያስጸይፍ ነው እንዳልል አሳየኝ፤
²⁹ ስለዚህም ደግሞ ብትጠሩኝ ሳልከራከር መጣሁ። አሁንም በምን ምክንያት አስመጣችሁኝ? ብዬ እጠይቃችኋለሁ አላቸው።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#ነሐሴ_7_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇

✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"ብፁዕ ብእሲ ዘአንተ ገሠፅኮ እግዚኦ። ወዘመሀርኮ ሕገከ። ከመ ይትገኃሥ እመዋዕለ እኩያት።" መዝ 93፥12-13
“ለኃጢአተኛ ጕድጓድ እስኪቈፈር ድረስ ከክፉዎች ዘመናት ይወገድ ዘንድ፥ አቤቱ፥ አንተ የገሠጽኸው ሕግህንም ያስተማርኸው ሰው ምስጉን ነው።” መዝ. 93፥12-13
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ነሐሴ_7_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ማቴዎስ 16
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹³ ኢየሱስም ወደ ፊልጶስ ቂሣርያ አገር በደረሰ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን፦ ሰዎች የሰውን ልጅ ማን እንደ ሆነ ይሉታል? ብሎ ጠየቀ።
¹⁴ እነርሱም፦ አንዳንዱ መጥምቁ ዮሐንስ፥ ሌሎችም ኤልያስ፥ ሌሎችም ኤርምያስ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው ይላሉ አሉት።
¹⁵ እርሱም፦ እናንተስ እኔን ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ? አላቸው።
¹⁶ ስምዖን ጴጥሮስም መልሶ፦ አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ አለ።
¹⁷ ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ።
¹⁸ እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም።
¹⁹ የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል።
²⁰ ያን ጊዜም እርሱ ክርስቶስ እንደ ሆነ ለማንም እንዳይነግሩ ደቀ መዛሙርቱን አዘዛቸው።
²¹ ከዚያን ቀን ጀምሮ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ይሄድ ዘንድ ከሽማግሎችና ከካህናት አለቆች ከጻፎችም ብዙ መከራ ይቀበልና ይገደል ዘንድ በሦስተኛውም ቀን ይነሣ ዘንድ እንዲገባው ለደቀ መዛሙርቱ ይገልጥላቸው ጀመር።
²² ጴጥሮስም ወደ እርሱ ወስዶ፦ አይሁንብህ ጌታ ሆይ፤ ይህ ከቶ አይደርስብህም ብሎ ሊገሥጸው ጀመረ።
²³ እርሱ ግን ዘወር ብሎ ጴጥሮስን፦ ወደ ኋላዬ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን፤ የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን አታስብምና ዕንቅፋት ሆነህብኛል አለው።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
የሚቀደሰው ቅዳሴ የ #እመቤታች_የማርያም_ቅዳሴ ነው። መልካም የእመቤታችን የጽንሰት በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
Audio
ሃና እና እያቄም በስለት ያገኙሽ:
ድንግል እናታችን በጣም ደስ ይበልሽ።

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
#ነሐሴ_8

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ነሐሴ ስምንት በዚህች ቀን #ቅዱስ_አልዓዛር_ካህን ከሚስቱ እና ልጆቹ ጋር በሰማዕትነት ሞቱ፣ ዳጋ እስጢፋኖስን የመሠረቱት ታላቁ #ጻድቅ_አቡነ_ኂሩተ_አምላክ ዕረፍታቸው ነው፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_አልዓዛር_ካህን

ነሐሴ ስምንት በዚች ቀን አልዓዛርና ሚስቱ ሰሎሜ አንኤም አንጦኒኃስ ዖዝያ አልዓዛር አስዮና ስሙና መርካሎስ የሚባሉ ልጆቻቸውም ሰባቱ በሰማዕትነት ሞቱ።

ይህም አረጋዊ አልዓዛር ከመምህራነ ኦሪት አንዱ ነው እርሱም ለሕዝቡ አለቃና ሊቀ ካህናትም ነው በፈሪሀ #እግዚአብሔርም ሁኖ ያስተዳድራቸው ነበር። ከዚህም በኋላ ዳታንና አቤሮን በሙሴና አሮን ላይ እንደተነሡባቸው ከዘመዶቹ ወገን ሦስት ካህናት በእርሱ ላይ ቀንተው ተነሡበት።

የእሊህም ስማቸው ስምዖን አልፍሞስ መባልስ ይባላል ሹመቱንም እንዲለቅላቸው ፈለጉ ሕዝቡ ግን የአልዓዛር ሹመቱ ከ #እግዚአብሔር እንጂ ከሰው አይደለም ብለው ከለከሉአቸው።

ስለዚህም ነገር ወደ ግሪክ አገር ወርደው ንጉሥ አንጥያኮስን አነሳሡት መጥቶም የእስራኤልን መንግሥት እንዲወስድ ቀሰቀሱት። በመጣ ጊዜም ወደ ከተማቸው በተንኮል እንዲገባ አደረጉት።

በገባ ጊዜም ሊቀ ካህናቱ አልዓዛርን ይዞ የእሪያ መሥዋዕትን ለሕዝቡ እንዲሠዋ አዘዘው እምቢ ባለውም ጊዜ ሰባቱን ልጆቹን ገደላቸው። እርሱንና ሚስቱን በእሳት በአጋሉት ብረት ምጣድ ላይ አስተኙአቸው እንዲህም ምስክርነታቸውን ፈጸሙ።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በእሊህ ቅዱሳን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አቡነ_ኂሩተ_አምላክ_ዘጣና

ዳግመኛም በዚህች ቀን ዳጋ እስጢፋኖስን የመሠረቱት ታላቁ ጻድቅ አቡነ ኂሩተ አምላክ ዕረፍታቸው ነው፡፡

አቡነ ኂሩተ አምላክ ሰባቱ ከዋክብት ከተባሉት ቅዱሳን አንዱ አቡነ ኂሩተ አምላክ ሲሆኑ እሳቸውም ታላቁን ገዳም ዳጋ እስጢፋኖስን የመሠረቱት ናቸው፡፡ እርሳቸውም የዐፄ ይኩኖ አምላክ የወንድም ልጅ ናቸው፡፡ ከደብረ ሊባኖሱ አቡነ ተክለሃይማኖት ጋር ሆነው በሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም ከአባ ኢየሱስ ሞዐ ሥርዓተ ምንኩስናን ተምረዋል፡፡ ንጉሡ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን ለመላዋ ኢትዮጵያ ሊቀ ካህናት፣ አቡነ ኂሩተ አምላክን ደግሞ ዓቃቤ ሰዓት አድርገው ሾሟቸው፡፡

አቡነ ኂሩተ አምላክም በዓቃቤ ሰዓትነት ለጥቂት ጊዜ ካገለገሉ በኋላ በዓለም በመንግሥት ተቀምጦ ከማገልገል ይልቅ ከከተማ ወጥቶ ከሰው ተለይቶ #እግዚአብሔርን ማገልግል ይበልጣል በማለት የተቀበሉትን መዓርገ ሢመት ንቀው በመተው አልባሌ መስለው ታቦተ እስጢፋኖስን ከሐይቅ ይዘው መልአክ እየመራቸው ወደ ጣና ባሕር ዳርቻ ደረሱ፡፡ ሁለት ድንጋዮችንም በተረአምራት እንደ ታንኳ አድርገው በመጠቀም ባሕሩን በበትረ መስቀላቸው እየቀዘፉ ዳጋ ወደተባለው ደሴት ገብተው ጥቂት ዕረፍትን አድርገዋል፡፡ እሳቸው ያን ጊዜ ያረፉበት ቦታ ዛሬም ድረስ ‹‹ዓቃቤ ሰዓት›› እየተባለ በመዓርግ ስማቸው ይጠራል፡፡

የጣናን ባሕር እንደ ታንኳ ተጠቅመው የተሻገሩባቸው እነዚያ ሁለት ትላልቅ ድንጋዮችም ዛሬ በገዳሙ ውስጥ የጻድቃን ማረፊያ (ምዕራፈ ጻድቃን) ተብሎ በሚጠራው ቦታ ላይ በክብር ተቀምጠው ይገኛሉ፡፡ አቡነ ኂሩተ አምላክ በቦታው ላይ ሥርዓቱን አጽንተው ተጋድሎአቸውን ጨርሰው ነሐሴ 8 ቀን በክብር ዐርፈዋል፡፡

ዳጋ እስጢፋስ ገዳምን ከዐፄ ዳዊት ጀምሮ እስከ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ድረስ የተነሡት ነገሥታት እየተሳለሙት የከበሩ ቅርሶችንና የወርቅ ዘውዳቸውን በስጦታ አበረክተውላታል፡፡ 900 ዓመት ያስቆጠሩ የብራና መጻሕፍትና ሌሎች አስደናቂ ቅርሶች የሚገኙበት ገዳም ነው፡፡ የዐፄ ዳዊት፣ የዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ፣ የዐፄ ፋሲልና የሌሎቹም ቅዱሳን ነገሥታት ዐፅም በዚህ ገዳም በክብር ተቀምጦ ይገኛል፡፡ የዐፄ ሱስንዮስም ዐፅም በዚሁ በታላቁ ገዳም ዳጋ እስጢፋኖስ ከብዙ ቅዱሳን ነገስታት ዐፅም ጋር ይገኛል፡፡ ዐፄ ሱስንዮስ የፖርቱጋልን እርዳታ ለማግኘት ሲሉ የካቶሊክን የክህደት እምነት አምነው በሀገራችንም ላይ አውጀው ከ8 ሺህ በላይ ካህናት ምእመናንን ካስገደሉ በኋላ ምላሳቸው ተጎልጉሎ በክፉ አሟሟት ሊሞቱ ሲሉ ልጃቸው ፋሲል ቅዱሳን አባቶችን በመለመን በጸሎታቸው እንዲፈወሱ አድርጓቸዋል፡፡ እነ አቡነ ምእመነ ድንግል እና አቡነ ዓምደ ሥላሴ ጋር በጸሎታቸው የንጉሡን የተጎለጎለ ምላሳቸውን መልሰውላቸው ከሕመማቸውም ፈውሰዋቸዋል፡፡ ‹‹ፋሲል ይንገስ ካቶሊክ ይፍለስ…ተዋሕዶ ይመለስ…የዐፄ ሱስንዮስ ምላስ ይመለስ…እግዚአብሔር ይፍታ›› ሲል ተጎልግሉ የነበረው ምላሳቸው ተመልሰ፡፡ በዚያን ጊዜ ዐፄ ሱስንዮስ ‹‹ብቆይ ዓመት ብበላ ገአት/ገንፎ›› ብለው በመናገር ማላሳቸው እንደቀድሞው ሆነላቸው። ለንስሐ ሞት በቅተው መንግስታቸውን ለልጃቸው አውርሰው በክብር አርፈዋል፡፡ ለዚህም ነው የዐፄ ሱስንዮስ ዐፅም በታላቁ ገዳም ዳጋ እስጢፋኖስ ከብዙ ቅዱሳን ነገስታት ዐፅም ጋር አብሮ መገኘቱ፡፡

አቡነ ኂሩተ አምላክ የጌታችንን ቅዱስ መስቀል ወደ ሀገራችን ለማምጣት ብዙ የደከሙ አባት ናቸው፡፡ ንጉሡ ዐፄ ዳዊት በዘመናቸው ርሀብ ስለነተሳ የዘደብረ ቢዘኑን ታላቁን ጻድቅ አቡነ ፊሊጶስን ከገዳማቸው አስጠርተው ‹‹ምን ባደርግ ይሻለኛል?›› ብለው አማከሯቸው፡፡ እኚህም የዘደብረ ቢዘኑ አቡነ ፊሊጶስ የዐፄ ዘርዐ ያዕቆብን መወለድ በትንቢት የተናገሩ ናቸው፡፡ ንግሥቲቱ የዐፄ ዳዊት ሚስት የአቡነ ፊሊጶስን እግራቸውን አጥባቸው ስትጨርስ የእግራቸውን እጣቢ በእምነት ጠጣችው፡፡ በዚህም ጊዜ አቡነ ፊሊጶስ ንግሥቲቱን ‹‹ከማኅፀንሽ ፍሬ ታላቅ ጻድቅ ልጅ ይወጣል›› ብለው ትንቢት ከነገሯት በኋላ በትንቢታቸው መሠረት ታላቁ ጻድቅ ንጉሥ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ተወልደዋል፡፡ ዐፄ ዳዊትም በዘመናቸው ስለተነሣው ርሀብ አቡነ ፊሊጶስን ሲያማክሯቸው ጻድቁ ሱባዔ ገብተው በጸሎት ከጠየቁ በኋላ ‹‹የ #ጌታችንን_መስቀል ያስመጡ›› ብለው ንጉሡን መከሯቸው፡፡ ንጉሡ ዐፄ ዳዊትም ከኢየሩሳሌም፣ ከቁስጥንጥንያና ከእስክንድርያ መንግሥታት ጋር ተጻጽፈው ዓሥሩን ታላላቅ የሀገራችንን ቅዱሳን ይዘው ሄደው መስቀሉን መስከረም 10 ቀን አምጥተውታል፡፡ ቅዱስ መስቀሉን ካመጡት ዓሥሩ ታላላቅ ቅዱሳን ውስጥም አንዱ የጣና ደሴቱ አቡነ ኂሩተ አምላክ ናቸው፡፡ የተቀሩት ዘጠኙ ደግሞ የደብረ ቢዘኑ አቡነ ፊሊጶስ፣ የጣና ደሴቱ አቡነ እንድርያስ፣ አቡነ በትረ ማርያም፣ አቡነ ዮሐንስ፣ አቡነ ታዴዎስ፣ አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ፣ አቡነ ዘካርያስ፣ አቡነ ያሳይና አቡነ ቶማስ ናቸው፡፡

አቡነ ኂሩተ አምላክ ወደ ግብፅ ሄደው ግማደ መስቀሉን ይዘው ከግብፅ ስለመጡ አንዳንድ ሰዎች ግብፃዊ ናቸው ይሏቸዋል ነገር ግን ለሀገራቸው ለቅድስት ኢትዮጵያ ትልቅ ውለታ የዋሉ ታላቅ ጻድቅ ናቸው፡፡ የትውልድ ሀገራቸውም ወሎ ልዩ ቦታው መርጦ እንደሆነ ታሪካቸው ያስረዳል፡፡

#ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ነሐሴ_8 እና #ከገድላት_አንደበት)
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ነሐሴ_8_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሮሜ 9
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁴ የምሕረቱ ዕቃዎችም ከአይሁድ ብቻ አይደሉም፥ ነገር ግን ከአሕዛብ ደግሞ የጠራን እኛ ነን።
²⁵ እንዲሁ ደግሞ በሆሴዕ፦ ሕዝቤ ያልሆነውን ሕዝቤ ብዬ፥ ያልተወደደችውንም የተወደደችው ብዬ እጠራለሁ፤
²⁶ እናንተ ሕዝቤ አይደላችሁም በተባለላቸውም ስፍራ በዚያ የሕያው እግዚአብሔር ልጆች ተብለው ይጠራሉ ይላል።
²⁷-²⁸ ኢሳይያስም፦ የእስራኤል ልጆች ቁጥር ምንም እንደ ባሕር አሸዋ ቢሆን ቅሬታው ይድናል፤ ጌታ ነገሩን ፈጽሞና ቆርጦ በምድር ላይ ያደርገዋልና ብሎ ስለ እስራኤል ይጮኻል።
²⁹ ኢሳይያስም እንደዚሁ፦ ጌታ ፀባዖት ዘር ባላስቀረልን እንደ ሰዶም በሆንን ገሞራንም በመሰልን ነበር ብሎ አስቀድሞ ተናገረ።
³⁰ እንግዲህ ምን እንላለን? ጽድቅን ያልተከተሉት አሕዛብ ጽድቅን አገኙ፥ እርሱ ግን ከእምነት የሆነ ጽድቅ ነው፤
³¹ እስራኤል ግን የጽድቅን ሕግ እየተከተሉ ወደ ሕግ አልደረሱም።
³²-³³ ይህስ ስለ ምንድር ነው? በሥራ እንጂ በእምነት ጽድቅን ስላልተከተሉ ነው፤ እነሆ፥ በጽዮን የእንቅፋት ድንጋይና የማሰናከያ ዓለት አኖራለሁ በእርሱም የሚያምን አያፍርም ተብሎ እንደ ተጻፈ በእንቅፋት ድንጋይ ተሰናከሉ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
1ኛ ጴጥሮስ 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹² ወዳጆች ሆይ፥ በእናንተ መካከል እንደ እሳት ሊፈትናችሁ ስለሚሆነው መከራ ድንቅ ነገር እንደ መጣባችሁ አትደነቁ፤
¹³ ነገር ግን ክብሩ ሲገለጥ ደግሞ ሐሤት እያደረጋችሁ ደስ እንዲላችሁ፥ በክርስቶስ መከራ በምትካፈሉበት ልክ ደስ ይበላችሁ።
¹⁴ ስለ ክርስቶስ ስም ብትነቀፉ የክብር መንፈስ የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ ላይ ያርፋልና ብፁዓን ናችሁ።
¹⁵ ከእናንተ ማንም ነፍሰ ገዳይ ወይም ሌባ ወይም ክፉ አድራጊ እንደሚሆን ወይም በሌሎች ጒዳይ እንደሚገባ ሆኖ መከራን አይቀበል፤
¹⁶ ክርስቲያን እንደሚሆን ግን መከራን ቢቀበል ስለዚህ ስም እግዚአብሔርን ያመስግን እንጂ አይፈር።
¹⁷ ፍርድ ከእግዚአብሔር ቤት ተነሥቶ የሚጀመርበት ጊዜ ደርሶአልና፤ አስቀድሞም በእኛ የሚጀመር ከሆነ ለእግዚአብሔር ወንጌል የማይታዘዙ መጨረሻቸው ምን ይሆን?
¹⁸ ጻድቅም በጭንቅ የሚድን ከሆነ ዓመፀኛውና ኃጢአተኛው ወዴት ይታይ ዘንድ አለው?
¹⁹ ስለዚህ ደግሞ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መከራን የሚቀበሉ፥ መልካምን እያደረጉ ነፍሳቸውን ለታመነ ፈጣሪ አደራ ይስጡ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 16
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³⁵ በነጋም ጊዜ ገዢዎቹ፦ እነዚያን ሰዎች ፍታቸው ብለው ሎሌዎቻቸውን ላኩ።
³⁶ የወኅኒውም ጠባቂ፦ ትፈቱ ዘንድ ገዢዎቹ ልከዋል፤ እንግዲህ አሁን ወጥታችሁ በሰላም ሂዱ ብሎ ይህን ቃል ለጳውሎስ ነገረው።
³⁷ ጳውሎስ ግን፦ እኛ የሮሜ ሰዎች ስንሆን ያለ ፍርድ በሕዝብ ፊት ደብድበው በወኅኒ ጣሉን፤ አሁንም በስውር ይጥሉናልን? አይሆንም ራሳቸው ግን መጥተው ያውጡን አላቸው።
³⁸ ሎሌዎቹም ይህን ነገር ለገዢዎች ነገሩ። የሮሜ ሰዎችም እንደ ሆኑ በሰሙ ጊዜ ፈሩ፤
³⁹ መጥተውም ማለዱአቸው፥ አውጥተውም ከከተማ ይወጡ ዘንድ ለመኑአቸው።
⁴⁰ ከወኅኒውም ወጥተው ወደ ልድያ ቤት ገቡ፥ ወንድሞችንም ባዩ ጊዜ አጽናኑአቸውና ሄዱ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#ነሐሴ_8_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇

✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"ወድቀት እሳት ወኢርኢክዋ ለፀሐይ። ዘእንበለ ይትዐወቅ ሦክክሙ ሕለተ ኮነ። ከመ ሕያዋን በመዓቱ ይውኅጠክሙ"። መዝ 57፥8-9።
"እንደሚቀልጥ ሰም ያልቃሉ፤ እሳት ወደቀች፥ ፀሐይንም አላዩአትም። እሾኻችሁ ሳይታወቅ በትር ሆነ፤ ሕያዋን ሳላችሁ በመዓቱ ይነጥቃችኋል"። መዝ 57፥8-9።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#ነሐሴ_8_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ማቴዎስ 7
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹² እንግዲህ ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትወዱትን ሁሉ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉላቸው፤ ሕግም ነቢያትም ይህ ነውና።
¹³ በጠበበው ደጅ ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚወስደው ደጅ ሰፊ፥ መንገዱም ትልቅ ነውና፥ ወደ እርሱም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው፤
¹⁴ ወደ ሕይወት የሚወስደው ደጅ የጠበበ፥ መንገዱም የቀጠነ ነውና፥ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው።
¹⁵ የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ።
¹⁶ ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ። ከእሾህ ወይን ከኩርንችትስ በለስ ይለቀማልን?
¹⁷ እንዲሁ መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬ ያደርጋል፥ ክፉም ዛፍ ክፉ ፍሬ ያደርጋል።
¹⁸ መልካም ዛፍ ክፉ ፍሬ ማፍራት፥ ወይም ክፉ ዛፍ መልካም ፍሬ ማፍራት አይቻለውም።
¹⁹ መልካም ፍሬ የማያደርግ ዛፍ ሁሉ ይቆረጣል ወደ እሳትም ይጣላል።
²⁰ ስለዚህም ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ።
²¹ በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም።
²² በዚያ ቀን ብዙዎች፦ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል።
²³ የዚያን ጊዜም፦ ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።
²⁴ ስለዚህ ይህን ቃሌን ሰምቶ የሚያደርገው ሁሉ ቤቱን በዓለት ላይ የሠራ ልባም ሰውን ይመስላል።
²⁵ ዝናብም ወረደ ጎርፍም መጣ ነፋስም ነፈሰ ያንም ቤት ገፋው፥ በዓለት ላይም ስለ ተመሠረተ አልወደቀም።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
የሚቀደሰው ቅዳሴ የ #እመቤታች_የማርያም_ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ነሐሴ_9

#አባ_ኦሪ

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ነሐሴ ዘጠኝ በዚች ቀን ስጥኑፍ ከሚባል አገር የከበረ ቄስ አባ ኦሪ ምስክር ሁኖ ሞተ። ይህ ቅዱስ ብዙ ርኅራኄ ያለው በሥጋው በነፍሱም ንጹሕ የሆነ ነው ብዙ ጊዜም አምላካዊ ራእይን ያያል። ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ በመሠዊያው ላይ ታይቶ ብዙ ምሥጢራትን ገለጠለት።

ከዚህም በኋላ የአባ ኦሪ ዜናው በኒቅዮስ አገር መኰንን ዘንድ ተሰማ ወደርሱም አስቀርቦ ለአማልክት ዕጣን አቅርብ አለው እርሱም ለረከሱና ለተሠሩ አማልክት አልሠዋም ብሎ እምቢ አለው።

መኰንኑም ተቆጥቶ በብዙ ሥራ አስፈራራው ቅዱስ ኦሪም ሥቃዩን ምንም ምን አልፈራውም ጹኑ ሥቃይንም አሠቃየው። ከዚህም በኋላ ወደ እስክንድርያ አገር ላከው በዚያም ጽኑዕ የሆነ ሥቃይን አሠቃይተው በወህኒ ቤት ጣሉት። በዚያም ድንቆች ተአምራቶችን በማድረግ በሽተኞችን ፈወሳቸው ።

ዜናውም በተሰማ ጊዜ ደዌ ያለባቸው ሁሉ ከየአገሩ ብዙዎች ሰዎች ወደርሱ መጥተው አዳናቸው። ይህንንም መኰንኑ ሰምቶ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ በመንግስተ ሰማያትም የሰማዕትነትን አክሊል ተቀበለ።

ከዚህም በኋላ የከበረ ዮልዮስ ሥጋውን አንሥቶ ገንዘው ወደ ሀገሩ ስጥኑፍም ላከው። የመከራውም ወራት ካለፈ በኋላ ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያን ሠርተውለት ሥጋውን በውስጧ አኖሩ ከሥጋውም ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ። በማመንም ለሚመጡ በሽተኞች ሁሉ ታላቅ ፈውስ ሆነ።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሱ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ነሐሴ_9)
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ነሐሴ_9_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ፊልጵስዩስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹² ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ይህ የደረሰብኝ በእውነት ወንጌልን ለማስፋት እንደ ሆነ ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ።
¹³ ስለዚህም እስራቴ ስለ ክርስቶስ እንዲሆን በንጉሥ ዘበኞች ሁሉና በሌሎች ሁሉ ዘንድ ተገልጦአል፥
¹⁴ በጌታም ካሉት ወንድሞች የሚበዙት ስለ እስራቴ ታምነው የእግዚአብሔርን ቃል እንዲነግሩ ያለ ፍርሃት ከፊት ይልቅ ይደፍራሉ።
¹⁵ አንዳንዶች ከቅንአትና ከክርክር እንኳ ሌሎች ግን ከበጎ ፈቃድ የተነሣ ክርስቶስን ይሰብኩታል፤
¹⁶ እነዚህ ወንጌልን መመከቻ ለማድረግ እንደ ተሾምሁ አውቀው በፍቅር ይሰብካሉ፥
¹⁷ እነዚያ ግን በእስራቴ ላይ መከራን ሊያመጡብኝ መስሎአቸው፥ ለወገናቸው የሚጠቅም ፈልገው በቅን አሳብ ሳይሆኑ ስለ ክርስቶስ ያወራሉ።
¹⁸ ምን አለ? ቢሆንም በሁሉ ጎዳና፥ በማመካኘት ቢሆን ወይም በቅንነት ቢሆን፥ ክርስቶስ ይሰበካል ስለዚህም ደስ ብሎኛል።
¹⁹ ወደ ፊትም ደግሞ ደስ ይለኛል፤ ይህ በጸሎታችሁና በኢየሱስ ክርስቶስ መንፈስ መሰጠት ለመዳኔ እንዲሆንልኝ አውቃለሁና፥
²⁰ ይህ ናፍቆቴ ተስፋዬም ነውና፤ በአንድ ነገር እንኳ አላፍርም ነገር ግን በሕይወት ብኖር ወይም ብሞት፥ ክርስቶስ በግልጥነት ሁሉ እንደ ወትሮው አሁን ደግሞ በስጋዬ ይከብራል።
²¹ ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ፥ ሞትም ጥቅም ነውና።
²² ነገር ግን በስጋ መኖር ለእኔ የሥራ ፍሬ ቢሆን፥ ምን እንድመርጥ ኣላስታውቅም።
²³ በእነዚህም በሁለቱ እጨነቃለሁ፤ ልሄድ ከክርስቶስም ጋር ልኖር እናፍቃለሁ፥ ከሁሉ ይልቅ እጅግ የሚሻል ነውና፤
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
2ኛ ዮሐንስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁶ እንደ ትእዛዛቱም እንሄድ ዘንድ ይህ ፍቅር ነው፤ ከመጀመሪያ እንደ ሰማችሁ፥ በእርስዋ ትሄዱ ዘንድ ትእዛዙ ይህች ናት።
⁷ ብዙ አሳቾች ወደ ዓለም ገብተዋልና እነርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የማያምኑ ናቸው፤ ይህ አሳቹና የክርስቶስ ተቃዋሚው ነው።
⁸ ሙሉ ደመወዝን እንድትቀበሉ እንጂ የሠራችሁትን እንዳታጠፉ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።
⁹ ለሚወጣ ሁሉ በክርስቶስም ትምህርት ለማይኖር ሰው አምላክ የለውም፤ በክርስቶስ ትምህርት ለሚኖር አብና ወልድ አሉት።
¹⁰ ማንም ወደ እናንተ ቢመጣ ይህንም ትምህርት ባያመጣ በቤታችሁ አትቀበሉት ሰላምም አትበሉት፤
¹¹ ሰላም የሚለው ሰው በክፉ ሥራው ይካፈላልና።
¹² እንድጽፍላችሁ የምፈልገው ብዙ ነገር ሳለኝ በወረቀትና በቀለም ልጽፈው አልወድም፥ ዳሩ ግን ደስታችሁ ፍጹም እንዲሆን ወደ እናንተ ልመጣ አፍ ለአፍም ልናገራችሁ ተስፋ አደርጋለሁ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 15
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁹ ስለዚህ ከአሕዛብ ወደ እግዚአብሔር የዞሩትን እንዳናስቸግራቸው፥
²⁰ ነገር ግን ከጣዖት ርኵሰትና ከዝሙት ከታነቀም ከደምም ይርቁ ዘንድ እንድንጽፍላቸው እቈርጣለሁ።
²¹ ሙሴስ ከቀደሙት ትውልድ ጀምሮ በሰንበት በሰንበት በምኵራቦቹ ሲያነቡ በየከተማው እርሱን የሚሰብኩ አሉት።
²² ያን ጊዜ ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ከቤተ ክርስቲያኑ ሁሉ ጋር ከእነርሱ የተመረጡትን ሰዎች ከጳውሎስና ከበርናባስ ጋር ወደ አንጾኪያ ይልኩ ዘንድ ፈቀዱ፤ እነርሱም በወንድሞች መካከል ዋናዎች ሆነው በርስያን የተባለው ይሁዳና ሲላስ ነበሩ።
²³ እንዲህም ጽፈው በእነርሱ እጅ ላኩ። ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ወንድሞችም በአንጾኪያና በሶርያ በኪልቅያም ለሚኖሩ ከአሕዛብ ወገን ለሆኑ ወንድሞች ሰላምታ ያቀርባሉ።
²⁴ ያላዘዝናቸው ሰዎች ከእኛ ወጥተው፦ ትገረዙ ዘንድና ሕግን ትጠብቁ ዘንድ ይገባችኋል ብለው ልባችሁን እያወኩ በቃል እንዳናወጡአችሁ ስለ ሰማን፥
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#ነሐሴ_9_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇

✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"ወትቀውም ንግሥት በየማንከ። በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኊብርት። ስምዒ ወለትየ ወርእዪ ወአጽምዒ ዕዝነኪ"። መዝ 44፥9-10።
"የንጉሦች ሴት ልጆች ለክብርህ ናቸው፤ በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች። ልጄ ሆይ፥ ስሚ እዪ ጆሮሽንም አዘንብዪ፤ ወገንሽን ያባትሽንም ቤት እርሺ"። መዝ 44፥9-10።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#ነሐሴ_9_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ዮሐንስ 10
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ወደ በጎች በረት በበሩ የማይገባ በሌላ መንገድ ግን የሚወጣ እርሱ ሌባ ወንበዴም ነው፤
² በበሩ የሚገባ ግን የበጎች እረኛ ነው።
³ ለእርሱ በረኛው ይከፍትለታል፤ በጎቹም ድምፁን ይሰሙታል፥ የራሱንም በጎች በየስማቸው ጠርቶ ይወስዳቸዋል።
⁴ የራሱንም ሁሉ ካወጣቸው በኋላ በፊታቸው ይሄዳል፥ በጎቹም ድምፁን ያውቃሉና ይከተሉታል፤
⁵ ከሌላው ግን ይሸሻሉ እንጂ አይከተሉትም፥ የሌሎችን ድምፅ አያውቁምና።
⁶ ኢየሱስ ይህን ምሳሌ ነገራቸው፤ እነርሱ ግን የነገራቸው ምን እንደ ሆነ አላስተዋሉም።
⁷ ኢየሱስም ደግሞ አላቸው፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ እኔ የበጎች በር ነኝ።
⁸ ከእኔ በፊት የመጡ ሁሉ ሌቦችና ወንበዴዎች ናቸው፤ ዳሩ ግን በጎቹ አልሰሙአቸውም።
⁹ በሩ እኔ ነኝ፤ በእኔ የሚገባ ቢኖር ይድናል፥ ይገባልም ይወጣልም መሰማርያም ያገኛል።
¹⁰ ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ።
¹¹ መልካም እረኛ እኔ ነኝ። መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል።
¹² እረኛ ያልሆነው በጎቹም የእርሱ ያልሆኑ ሞያተኛ ግን ተኵላ ሲመጣ ባየ ጊዜ በጎቹን ትቶ ይሸሻል፤ ተኵላም ይነጥቃቸዋል በጎቹንም ይበትናቸዋል።
¹³ ሞያተኛ ስለ ሆነ ለበጎቹም ስለማይገደው ሞያተኛው ይሸሻል።
¹⁴-¹⁵ መልካም እረኛ እኔ ነኝ፥ አብም እንደሚያውቀኝ እኔም አብን እንደማውቀው የራሴን በጎች አውቃለሁ የራሴም በጎች ያውቁኛል፤ ነፍሴንም ስለ በጎች አኖራለሁ።
¹⁶ ከዚህም በረት ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤ እነርሱን ደግሞ ላመጣ ይገባኛል ድምፄንም ይሰማሉ፥ አንድም መንጋ ይሆናሉ እረኛውም አንድ።
¹⁷ ነፍሴን ደግሞ አነሣት ዘንድ አኖራለሁና ስለዚህ አብ ይወደኛል።
¹⁸ እኔ በፈቃዴ አኖራታለሁ እንጂ ከእኔ ማንም አይወስዳትም። ላኖራት ሥልጣን አለኝ ደግሞም ላነሣት ሥልጣን አለኝ ይህችን ትእዛዝ ከአባቴ ተቀበልሁ።
¹⁹ እንግዲህ ከዚህ ቃል የተነሣ በአይሁድ መካከል እንደ ገና መለያየት ሆነ።
²⁰ ከእነርሱም ብዙዎች፦ ጋኔን አለበት አብዶአልም፤ ስለ ምንስ ትሰሙታላችሁ? አሉ።
²¹ ሌሎችም፦ ይህ ጋኔን ያለበት ሰው ቃል አይደለም፤ ጋኔን የዕውሮችን ዓይኖች ሊከፍት ይችላልን? አሉ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
የሚቀደሰው ቅዳሴ የ #እመቤታች_የማርያም_ቅዳሴ ነው። መልካም የእመቤታችን የጽንሰት በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
2024/09/22 09:38:31
Back to Top
HTML Embed Code: