Telegram Web Link
Audio
ስንክሳር ዘወርሃ ጥር አሥራ ሁለት
https://www.tg-me.com/SinkisarZekidusan2
Audio
ድርሳን ዘቅዱስ ሚካኤል ዘወርሃ ጥር
https://www.tg-me.com/SinkisarZekidusan2
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈሰ ቅዱስ ስም አሜን
ጥር 15-በሁለት ዓመት ከዘጠኝ ወሩ የከበረች ወንጌልን ሰብኮ ጣዖት አምላኪዎችን በተአምራቱ ያሳመነውና ብዙ አሰቃቂ መከራዎችን የተቀበለው ሕፃኑ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ዕረፍቱ ነው፡፡ ማኅበርተኞቹ የሆኑ ዓሥራ አንድ ሺህ አራት ሰዎችም አብረው በሰማዕትነት ዐርፈዋል፡፡
+ በግራኝ ዘመን ከአንድ ቤተ ክርስቲያን ጋር በእሳት ተቃጥሎ በሰማዕትነት ያረፈው አቡነ ቄርሎስ ዕረፍቱ ነው፡፡
+ የሶርያ ክርስቲያኖች በዚህች ዕለት በዓሉን በድምቀት የሚያከብሩለት የኑሲሱ አቡነ ጎርጎሪዮስ መታሰቢያ በዓሉ ነው፡፡
+ ነቢዩ ቅዱስ አብድዩ ዕረፍቱ ነው፡፡

አቡነ ቄርሎስ ኢትዮጵያዊ፡- አባታቸው ሳይንቱ እናታቸው ወለቃት ሲባሉ የመጀመሪያ ስማቸው መብዓ ሥላሴ ነው፡፡ በባሕታዊነታቸው መላ ገዳማቱ ሁሉ ያደንቋቸው የነበሩ ሲሆን እንደ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ 60 አንበሶችና 60 ነብሮች የተሰጣቸው ታላቅ አባት ናቸው፡፡ ጻድቁ በክፉው ግራኝ ዘመን ከአንዲት ቤተ ክርስቲያን ጋር አብረው ተቃጥለው ነው በሰማዕትነት ያረፉት፡፡ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን በጸሎታቸው ይማረን!
+++

ነቢዩ ቅዱስ አብድዩ፡- የስሙ ትርጓሜ ‹‹የእግዚአብሔር አገልጋይ›› ማለት ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ 1ኛ ነገ 18፡3 ላይ ‹‹አብደዩ እግዚአብሔርን እጅግ ይፈራ ነበር›› ተብሎ የተነገረለት እውነትም ‹‹የእግዚአብሔር አገልጋይ›› የሆነ የነቢዩ ኤልያስ ደቀመዝሙር የነበረ ታላቅ ነቢይ ነው፡፡ ይህም ቅዱስ ነቢይ ከጠረፍ በረሃ አቅራቢያ ካለች ሱሳም በምትባል አገር ካሉ ሰዎች ወገን ነው፡፡ አባቱ ሐናንያ ይባላል፡፡ ለነቢዩ ኤልያስ ደቀ መዝሙሩ ሆኖ በንጉሡ በአክዓብምና በንግሥቲቱ በኤልዛቤል ምክንያት በእርሱ ላይ የመጣውን መከራ ሁሉ ታግሷል፡፡ ታላቁ ነቢይ ኤልያስ ከእነ ኤልዛቤል ሸሽቶ ወደ ተራራ ላይ ወጥቶ በዋሻ ተሸሽጎ ምግቡን አሞራ እያመጣለት በኖረበት ጊዜ እንኳን ነቢዩ አብድዩ ግን ብቻውን የእግዚአብሔርን ነቢያት ይንከባከብ ነበር፡፡ አብድዩ የንጉሥ አክዓብ የቤቱን አዛዥ የነበረ ቢሆንም ንግሥት ኤልዛቤል የእግዚአብሔርን ነቢያት ባስገደለች ጊዜ አብድዩ መቶውን ነቢያት ወስዶ ሃምሳ ሃምሳውን በዋሻ ውስጥ ሸሽጎ እንጀራና ውኃ ይመግባቸው የነበረ ታላቅ ባለውለታ ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ታሪኩ እንዲህ ተብሎ ነው የተጻፈው፡-
‹‹ከብዙ ቀንም በኋላ በሦስተኛው ዓመት ‹‹ሂድ ለአክዓብ ተገለጥ፥ በምድር ላይም ዝናብ እሰጣለሁ›› የሚል የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤልያስ መጣ፡፡ ኤልያስም ለአክዓብ ይገለጥ ዘንድ ሄደ፤ በሰማርያም ራብ ጸንቶ ነበር፡፡ አክዓብም የቤቱን አዛዥ አብድዩን ጠራ፤ አብድዩ እግዚአብሔርን እጅግ ይፈራ ነበር፡፡ ኤልዛቤልም የእግዚአብሔርን ነቢያት ባስገደለች ጊዜ እርሱ መቶውን ነቢያት ወስዶ አምሳ አምሳውን በዋሻ ውስጥ ሸሽጎ እንጀራና ውኃ ይመግባቸው ነበር፡፡ አክዓብም አብድዩን ‹‹በአገሩ መካከል ወደ ውኃው ምንጭ ሁሉና ወደ ወንዝ ሁሉ ሂድ፤ እንስሶችም ሁሉ እንዳይጠፉ ፈረሶችንና በቅሎችን የምናድንበት ሣር ምናልባት እናገኛለን›› አለው፡፡ ሁለቱም የሚመለሱበትን አገር ተካፈሉ፤ አክዓብም ለብቻው በአንድ መንገድ አብድዩም ለብቻው በሌላ መንገድ ሄዱ፡፡
አብድዩም በመንገድ ሲሄድ እነሆ ኤልያስ ተገናኘው፤ አብድዩም አወቀው፣ በግምባሩም ተደፍቶ ‹‹ጌታዬ ሆይ! ኤልያስ አንተ ነህን? አለ፡፡ ኤልያስም ‹‹እኔ ነኝ ሄደህ ለጌታህ ‹ኤልያስ ተገኝቶአል› በል›› አለው፡፡ አብድዩም ‹‹እኔን ባሪያህን እንዲገድል በአክዓብ እጅ አሳልፈህ ትሰጠኝ ዘንድ ምን ኃጢአት አድርጌአለሁ? አምላክህ ሕያው እግዚአብሔርን! ጌታዬ ይፈልግህ ዘንድ ያልላከበት ሕዝብ ወይም መንግሥት የለም፤ ሁሉም ‹‹በዚህ የለም›› ባሉ ጊዜ አንተን እንዳላገኙ መንግሥቱንና ሕዝቡን አምሎአቸው ነበር፡፡ አሁንም እነሆ ‹ሂድ ኤልያስ ተገኘ ብለህ ለጌታህ ንገር› ትለኛለህ፡፡ እኔም ከአንተ ጥቂት ራቅ ስል የእግዚአብሔር መንፈስ አንሥቶ ወደማላውቀው ስፍራ ይወስድሃል፤ እኔም ገብቼ ለአክዓብ ስናገር ባያገኝህ ይገድለኛል፤ እኔም ባሪያህ ከትንሽነቴ ጀምሬ እግዚአብሔርን እፈራ ነበር፡፡ ኤልዛቤል የእግዚአብሔርን ነቢያት ባስገደለች ጊዜ መቶውን የእግዚአብሔር ነቢያት ወስጄ አምሳ አምሳውንም በዋሻ ውስጥ ሸሽጌ እንጀራና ውኃ የመገብኋቸው ነበር፡፡ ይህ ያደርግሁት ነገር በውኑ ለጌታዬ አልታወቀህምን? አሁንም ‹ሄደህ ኤልያስ ተገኘ ብለህ ለጌታህ ንገር ትላለህ› እርሱም ይገድለኛል›› አለው፡፡
ኤልያስም ‹‹በፊቱ የቆምሁት የሠራዊት ጌታ ሕያው እግዚአብሔርን! እኔ ዛሬ ለእርሱ እገለጣለሁ›› አለ፡፡ አብድዩም አክዓብን ሊገናኘው ሄደ፣ ነገረውም፤ አክዓብም ኤልያስን ሊገናኘው መጣ፡፡ አክዓብም ኤልያስን ባየው ጊዜ ‹‹እስራኤልን የምትገለባብጥ አንተ ነህን?›› አለው፡፡ ኤልያስም ‹‹እስራኤልን የምትገለባብጡ፣ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ትታችሁ በኣሊምን የተከተላችሁ፣ አንተና የአባትህ ቤት ናችሁ እንጂ እኔ አይደለሁም›› አለው፡፡ 1ኛ ነገ 18፡1-20፡፡
ቅዱስ አብድዩ የንጉሥ አክዓብ የቤቱን አዛዥነቱን ትቶ የኤልያስ ቀደ መዝሙሩ ሆኖ በነቢይነት እግዚአብሔርን ሲያገለግል ኖረ፡፡ በንጉሥ ኢዮሳፍጥ ዘመንም ትንቢትን ተናገረ፡፡ እግዚአብሔርም ስለ ትንሣኤና ስለ ፍርድ ቀን በቃሉ ነገረው፡፡ ሁለተኛም ከእስራኤል ልጆች የሚሆነውን ከአሕዛብም ለቀሩት አጸናቸው፣ አብዝቶ መከራቸው፣ ገሠጻቸውም፡፡ የትንቢቱም ወራት ሲፈጸም በዚህች ዕለት በሰላም በፍቅር አንድነት ዐርፏል፡፡ የትንቢቱም ወራት ሃያ ዓመት ነው፡፡ ይኸውም ከጌታችን ሥጋዌ በፊት በ900 ዓመት ነው፡፡
+ + +

ዳግመኛም በዚህች ዕለት የሶርያ ክርስቲያኖች የኑሲሱን የአቡነ ጎርጎሪዮስን የዕረፍቱን በዓል በደማቅ ሁኔታ ያከበራሉ፡፡ በእኛ አቆጣጠር ግን ዕረፍቱ ጥር 21 ቀን ነው፡፡ (የጥር ሃያ አንዱን ይመለከቷል፡፡)
+ + +

ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣ፡- ሦስት ዓመት እንኳን ሳይሞላው በሁለት ዓመት ከዘጠኝ ወሩ ታላቅ ሰማዕትነትን የተቀበለው ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ አባቱ ቆዝሞስ (ስምዖን) እናቱ ኢየሉጣ ይባላሉ፡፡ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ በኅዳር 15 ቀን የተወለደ ሲሆን ሀገሩ በታችኛው እስያ ልዩ ስሙ ሀንጌቤን ይባላል፡፡ ዘመኑ ዘመነ ሰማዕታት ነበርና መምለኬ ጣዖት የሆነው ንጉሥ እስክንድሮስ ቅድስት ኢየሉጣን ‹‹ለጣዖቴ ስገጂ›› ብሎ አስገደዳት፡፡ እርሷም ‹‹ሕፃኑ ልጄ መጥቶ ይመስክር›› ብላ ስትናገር ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ተጠራና ተጠየቀ፡፡ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስም ‹‹ለጣዖት አንሰግድም፣ ዘላለማዊ የሆነ የማይሻር አምላክ ስላለ ለእርሱ ነው የምንሰግደው›› ብሎ የአምላኩን ክብር በሕፃን አንደበቱ መሰከረ፡፡ ሕፃኑም ይህንን በመሰከረ ጊዜ ዕድሜው ገና ሁለት ዓመት ከዘጠኝ ወሩ ነበር፡፡

ነቢዩ ቅዱስ ዳዊትም ‹‹ከልጆችና ከሚጠቡት አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ›› ሲል እንደተናገረ (መዝ 10፡2፣ 118፡130) መድኃኔዓለም ክርስቶስም በቅዱስ ወንጌሉ ላይ ‹‹አባት ሆይ፣ የሰማይና የምድር ጌታ ይህን ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግንሃለሁ›› ያለውን ቃል በሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ሕይወት ተግባራዊ ሆኖ አይተነዋል፡፡ ማቴ 11፡27፡፡ በነቢዩም ትንቢት መሠረት በበዓለ ሆሣዕና ዕለት በእናታቸው እቅፍና ጀርባ ላይ የነበሩ እምቦቀቅላ ጨቅላ ሕፃናት ‹‹ሆሣዕና፤ በጌታ ስም የሚመጣ የእስራኤል ንጉሥ የተባረከ ነው›› በማለት ጌታችንን አመስግነውታል፡፡
እንደዚሁ ሁሉ ቅዱስ ቂርቆስም በከሃዲው ንጉሥ ፊት የጌታችንን ክብር በመሰከረ ጊዜ ንጉሡ እጅግ ተቆጥቶ 40 ጋን ውኃ የሚይዝ በርሜል አስጥዶ 40 ቀን ሙሉ እሳት አስነድዶ ቅንጭብ፣ ዘይት፣ ዝፍጥና ሌላም በእጅጉ የሚጎዱ ነገሮችን በውስጡ ጨምሮ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱን ቅድስት ኢየሉጣን ወደዚያ እቶኑ እሳት እንዲከቷቸው አዘዘ፡፡ ንጉሡ እስክንድሮስ ጭፍሮቹን "ሰም፣ ጨው፣ ባሩድ፣ሙጫ፣ እርሳስ፣ ብረትን፣ ቅንጭብ፣ ቁልቋል ጨምሩበት" ብሎ አዘዛቸው፡፡ ጭፍሮችም ያዘዛቸውን ከፈጸሙ በኀላ መጥተው "ያዘዝከንን ሁሉ ጨምረንበት ነዶ ፈልቷል" አሉት፡፡ "ድምፁም እንደ ነጎድጓድ ይሰማል፤ ወላፈኑም እንደ ፀሐይ ያንፀባርቃል፡፡ የፍላቱም ኃይል 14 ክንድ ያህል እየዘለለ ይወጣል፡፡ በውስጡ የሚጣሉትን ሰዎች እዘዝ" አሉት፡፡ ያንጊዜም ህፃን ቂርቆስንና እናቱን ኢየሉጣን ይዘው ከእስር ቤት አወጧቸው፡፡ በክርስቶስ ስም ስላመኑ በእስር ቤት አግብተው አስረዋቸው ነበርና ፍላቱ ወደ ላይ በሚዘል በብረት ጋን ውስጥ ለመጨመር ሲወስዷቸው በዚያን ጊዜም እልፍ ከአንድ ሺህ አራት መቶ ሰዎች እንዲወጡና በፈላው የብረት ጋን ውስጥ የቅዱሳንን አሟሟት እንዲያዩ ሹሙ አዘዘ፡፡ ቅድስት ኢየሉጣም የፍላቱን ግርማ ባየች ጊዜ ተሸበረች፡፡ ተጠብቆላት ያለውንም ዋጋ ትታ ልትክድ ፈለገች፡፡ ቅዱስ ቂርቆስም ይህን ባወቀ ጊዜ "እናቴ ሆይ ከብረት ጋን ግርማ የተነሳ አትፍሪ፤ ድንጋፄም አይደርብሽ" እያለ ከብሉይና ከሐዲስ እየጠቀሰ እንድትጸና አስተማራት፡፡

"ነገር ግን እናቴ ሆይ አናንያንና አዘርያን፣ ሚሳኤልንም እግዚአብሔር ከዕቶን እሳት እንዳወጣቸው እወቂ፤ እኛንም ከዚህ ከብረት ጋን ውስጥ ሊያድነን ይችላል፡፡ እናት ሆይ ከሚያልፈው ከዚህ ዓለም ጭንቅ ልታመልጭ በሚያልፈው በዘለዓለም እሳት ልትቀጭ ትሻለች፡፡ እናት ሆይ ይህን አትሺ፤ ይቅርብሽ አሁን እግዚአብሔር በመካከላችን አለና ይረዳናል፡፡ ሶስናን ከሀጢያተኞች እጅ ያዳናት እኛንም ከብረት ጋን ያድነናል፡፡ ዳንኤልን ከአንበሶች አፍ ያዳነ እርሱ ያድነናል፡፡ እግዚአብሔር በዚህ ብረት ጋን ውስጥ ግዳጃችን ልንፈፅም ፈቅዶም እንደሆነ የኢዮብን ነፃነት (ትእግስት) ልናገኝ ይገባናል፡፡ እርሱ ልጆቹንና ሚስቱን ያገኘው ገንዘብ ሁሉ አጥቶ በመጨረሻው ሰውነቱን አጥቶ ነበርና ምንም ምንም የቀረበለት አልነበረምና እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ ከማለት በቀር ያለው ነገር የለም እግዚአብሔር ሰጠ፤ እግዚአብሔርም ወሰደ አለ፡፡ የእግዚአብሔር ስሙ ለዘለዓለም ይመስገን አለ፡፡ እኛም ይህንን መከራ ልንታገስና የተጠበቀልንን ልንከተል ይገባናል..." እያለ አብዝቶ መከራት፡፡ ነገርግን በዚህም ምክር እናቱን መመለስና ለሰማዕትነት ማዘጋቸት አልቻለም፡፡ ከዚህ በኋላ ቂርቆስ ዓይኖቹን ወደሰማይ አቅንቶ መጸለይ ጀመረ፡፡ "እግዚአብሔር ሆይ ይህች ባርያህ ከምትክድ ከህይወት መፅሐፍ እኔን ፋቀኝ አለ፡፡ አቤቱ ይህነን ነገር ልታደርግ አይገባህም፤ አቤቱ እርሻውን ልታቃጥል ፍሬውንም ልትባርክ ትወዳለህን፡፡ አቤቱ እንጨቱን ቁረጡና አንድዱት ቅጠሉን ጠብቁ ብለህ ልታዝ አይገባህም፡፡ እንጨቱንም ቅጠሉንም ጠብቁ ብለህ እዘዝ እንጂ ይህ አይገባህም ያመነብህ ሁሉ ይህን ያየ ዘንድ፡፡ ማዳን የሚችል አምላክ ኑሮአቸው ቢሆን ከዚህ ከእሳት ባልሸሹም ነበር ብሎ እንዳይጠራጠር፡፡ ዲያብሎስ ከባለስልጣኑ ይልቅ እኔ በረታሁ ቅዱሳኑም ድል ነሳኋቸው ብሎ እንዳይመካ፣ ከመንጋውም አንድ በግ ቀማሁ እንዳይል አቤቱ የኃይል መንፈስ ለእናቴ ስጣት አበርታት..." ብሎ ጸለየ፡፡ በዚያን ጊዜ ዲያብሎስ ከእርሷ ሸሽቶ ሄደ፡፡ ከዚህ በኋላ ቅድስት እናቱ እንዲህ አለች፡- በመንግስተ ሰማያት አባት የሆንከኝ ልጄ ሆይ ጌታህ ኃይል ስጠኝ፡፡ የሚጠብቀንን ገድላችንን እንፈፅምና ድል እንነሣ" አለችው፡፡ የብረት ጋኑን ሲነድ ሳየው በምንጭ ላይ በዝቶ እንደሚወርድ ጠል ሁኖ አየዋለሁና፡፡ ቅዱሳንም ይህንን ሲነጋገሩ አንስተው ከብረት ጋኑ ውስጥ ጨመሯቸው፡፡ በውስጡም አንገትን የሚቆለምም ልብን የሚያጣምም ሆድን የሚሰነጥቅ ሥርንም የሚበጥስ መሣሪያ ነበረበት፡፡ ወዲያውም የራማው ልዑል ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል እንደ ዐይን ጥቅሻ ፈጥኖ ከሰማይ ወረደና የብረት ጋኑን እሳት ፈጽሞ አበረደው፡፡ ከቅዱሳንም አንዱን እንኳን ሳይነካው የብረት ጋን ማቃጠሉና መፍላቱ ፀጥ አለ፡፡ እንደ ውኃም ሆነ፡፡

ንጉሡም እሳቱ እንዳልጎዳቸው ሲያውቅ ከዚያ አውጥቶ በሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ አፍና አፍንጫ መርዝ ከተተበት፣ ነገር ግን መርዙ ምንም አልጎዳውም እንዳውም ምግብ ሆነው፡፡ ዳግመኛም ጨውና በርበሬ በዐይኑ አነደደበት፡፡ አሁንም ምንም አልነካውም፡፡ ከዚህም በኀላ ሹም እስክድሮስም አስራ አራት የተሳሉና የጋሉ ብረቶች ያመጡ ዘንድ ዳግመኛ አዘዘ፡፡ ሰባቱን በእናቱ አካል ሰባቱን በሱ አካል ውስጥ ይተክሉ ዘንድ ከነዚሁም ሁለቱን በጆሮዎቹ ሁለቱን በዓይኖቹ ሁለቱን በአፍንጫዎቹ አንዱን በልቡ ይተክሉ ዘንድ አዘዘ፡፡በሕፃኑም ላይ ሹሙ እንዳዘዘው አደረጉበት፡፡ አሁንም ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወረደና ፈወሳቸው፡፡
ዳግመኛም የሕጻኑን እራስ ከነቆዳው ገፈው በእሳት ውስጥ ይጨምሩ አንድ ሹም አዘዘ፡፡ እንዲሁም አደረጉበት፡፡ ዳግመኛም ቅዱስ ገብርኤል እንደ ዐይን ጥቅሻ ፈጥኖ መጥቶ ይህንን መከራ ከሕፃኑ አራቀለት፡፡ ዳግመኛም ሹሙ በመቃን ውስጥ ጨመረው በገመድ እንዲሰቅሉት አዘዘ፡፡ ከዚህም መከራ መልአኩ አዳነው፡፡ ሐምሌ 19 ቀን በዓሉን በታላቅ ድምቀት የምናከብረው ይህንን ሁሉ የሊቀ መላእክት የቅዱስ ገብርኤልን ተራዳኢነት በማሰብ ነው፡፡

ንጉሡም በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ በብዙ ጭንቅና ሥቃይ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣን ለ3 ዓመታት አሠቃያቸው፡፡ እነርሱም መከራን እየተቀበሉ በከሀዲው ንጉሥ ፊት የአምላካቸውን ስም እየጠሩ መሰከሩ፡፡ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና ክብሩን ይመሰክሩለት ዘንድ የቢታንያን ድንጋዮችና የበለዓምን አህያ አንደበት ከፍቶ ያናገረ አምላክ ሦስት ዓመት እንኳን ባለሞላው በሁለት ዓመት ከዘጠኝ ወር ሕፃን ልጅ ላይ አድሮ በወቅቱ የነበሩ ዓላውያን ነገሥታት ክብሩን እንዲያውቁ አደረገ፡፡
ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ሄሮድስ ላስፈጃቸው 144,000 የቤቴልሔም ሕፃናት አለቃቸው ነው፡፡ ይህስ እንደምን ነው ቢሉ ሄሮድስ ያስፈጃቸው እነኚያ እልፍ የቤቴልሔም ሕፃናት የተገደሉት ጌታችንን ለማግኘት በተደረገው ፍለጋ ምክንያት ስለሆነ ቅዱስ ቂርቆስን በመሞት ይተካከሉታል እርሱ ግን የአምላኩን ስምና ክብር በማስተማርና በመመስከር ሰማዕትነትን ስለተቀበለ በዚህ ይበልጣቸዋልና ለእነኚያ እልፍ የቤቴልሔም ሕፃናት አለቃ አድርጎ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሾሞታል፡፡ ቅዱስ ገድሉም እንደሚናገረው ‹‹መንገድ ጠራጊ ከተባለ ከዮሐንስ መጥምቅ በቀር ሴቶች ከወለዱዋቸው እንደ አንተ ያለ አልተገኘም›› በማለት ጌታችን በማይታበል ቅዱስ ቃሉ ታላቅ የሆነ ቃልኪዳኑን በመሐላ አጽንቶለታል፡፡ በመጨረሻም ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ተጋድሎውን ፈጽሞ ጥር 15 ቀን በ3 ዓመት ከ1 ወር ከ3 ቀኑ አንገቱን በሰይፍ ተቆርጦ ሰማዕትነትን ተቀብሏል፡፡ ሲሰየፍም ከአንገቱም ደም፣ ውኃና ወተት የወጣ ሲሆን ሦስት አክሊላትም ወርደውለታል፡፡ ጌታችንም የመከራውን ጽናት የትዕግስቱን ብዛት አይቶ ከመከራ ሊያሳርፈው ፈቀደና ተገልጾለት ‹‹ሰላም ለከ ኦ ፍቁርየ ቂርቆስ›› አለው፡፡ ‹‹ሰላም ላንተ ይሁን፤ የመከራህን ጽናት፣ የትዕግስትህን ብዛት አይቼ ከዚህ ዓለም ድካም ላሳርፍህ መጣሁ›› ብሎ ብዙ ቃልኪዳን ሰጠው፡፡ ‹‹…ስምህ
በተጠራበት፣ ቤተመቅደስህ በታነጸበት፣ ስዕልህ ባለበት ቦታ ሁሉ የሕፃናት እልቂት፣ የከብት በሽታ፣ የእህል እጦት ርሀብ፣ ቸነፈር አይደርስም›› የሚል አስደናቂ ቃልኪዳንም ገብቶለታል፡፡ ሕፃኑም በምድር ላይ አልተቀበረም ይልቁንም ጌታችን በኤልያስ ሰረገላ ሥጋውን አሳርጎለታል፡፡ እናቱ ቅድስት ኢየሉጣም በጥር 16 ቀን ሰማዕትቷን በክብር ፈጽማለች፡፡ የቅዱስ ቂርቆስ ማኅበርተኞች የሆኑ ዓሥራ አንድ ሺህ አራት ሰዎች የጌታችንን ክብር እየመሰከሩ በሰማዕትነት ዐርፈዋል፡፡
የቅዱስ ቂርቆስና ማኅበርተኞች የሆኑ የቅዱሳን ሰማዕታት ረድኤት በረከታቸው ይደርብን በጸሎታቸው ይማረን!
+ + +
እንኩዋን ለአበው ቅዱሳን "አባ ዳንኤል" : "አባ ዸላድዮስ" : ወቅዱስ "ፊላታዎስ ሰማዕት" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ

+*" ማር ዳንኤል "*+

=>"ዘዓምድ" በሚል ስም ከሚታወቁ የቤተ ክርስቲያን አበው መካከል 4ቱ ቅድሚያውን ይይዛሉ:: እነዚህም:-
1.ቅዱስ ስምዖን ዘዓምድ:
2.ቅዱስ አጋቶን ዘዓምድ:
3.ቅዱስ ዳንኤል ዘዓምድ እና
4.ቅዱስ ሉቃስ ዘዓምድ ናቸው::

+"ዘዓምድ" የሚለውን ቃል ምሥራቃውያን በልሳናቸው 'THE STYLITE' ይሉታል:: የእኛው ቃል ደግሞ ከግዕዝ የተወረሰ ነውና በቁሙ ቢተረጐም "የምሰሶው" የሚል ትርጉምን ይይዛል:: ይህም በ2 ምክንያቶች ነው::

+አንደኛው ቅዱሳኑ ተጋድሏቸውን የፈጸሙት ከረዥም ምሰሶ ላይ ወጥተው በመጸለይ ስለሆነ ነው:: ሌላኛው ምክንያት ደግሞ እነዚህ አባቶች በዘመኑ ለነበሩ ምዕመናንና መነኮሳት አጽናኝ: አስተማሪ: መሪና ፈዋሽ በመሆናቸውና እንደ ምሰሶ ተተክለው ሳይነቃነቁ በመጸለያቸው ነው::

+ልክ ከዓለም ሃገራት ብዙ ስውራንን እና ቅዱሳን ነገሥታትን በመያዝ ሃገራችን ቀዳሚ እንደ ሆነችው ሁሉ ምሰሶ ላይ ወጥተው የሚጋደሉ ቅዱሳንም ሶርያውያንና ምሥራቃውያን ናቸው:: በዚህ ዕለትም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የታላቁን ቅዱስ ማር ዳንኤልን በዓል ታከብራለችና ከዜና ሕይወቱ ለበረከት ጥቂት እንካፈል::

=>ይህ ቅዱስ ሰው (በስዕሉ የሚታየው) ሶርያዊ ሲሆን ተወልዶ ያደገባት አካባቢ በቀድሞው አጠራር "ሃገረ ዓምድ" ይሏታል:: "ማር" የሚለው ቃል በቤተ ክርስቲያን ቅድስናንና አለቅነትን የሚገልጽ ስም ነው:: በዚህ ስም ጥቂቶች ብቻ ሲጠሩበት ለሊቃውንትም: ለሰማዕታትም: ለጻድቃንም አገልግሏል::

+ቅዱሱ "ማር" ብቻ ሳይሆን "ዘዓምድ" ተብሎም ተጠርቷል:: ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ እርሱም በፊት እንደ ጠቀስናቸው አበው ምሰሶ ላይ ተጠግቶ (ቆሞ): ትኩል ከመ ዓምድ ሆኖ በመጸለዩ ነው::

+ማር ዳንኤል በምድረ ሶርያ ስመ ጥር ጻድቅ ነው:: በዘመነ ጻድቃን መጨረሻ አካባቢ ከክርስቲያን ወገኖቹ ተወልዶ: በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አድጐ: ገና በልጅነቱ ለቤተ እግዚአብሔር ተሰጥቷል::

+የወቅቱ የሃገረ ዓምድ ዻዻስ (አባ ዼጥሮስ) ለማር ዳንኤል ፍኖተ ጽድቅን (የሕይወት - የእውነትን ጐዳና) በማሳየት ከፍ ያለውን አስተዋጽኦ አበርክቷል:: አስተምሮም ለመዓርገ ክህነት አብቅቶታል::

+ቅዱሱ በእድሜው እየበሰለ ሲሔድ ግን ምርጫው ምናኔ ሆኖ በመገኘቱ በፈቃዱ ወደ በርሃ ሔደ:: በዚያም መዓርገ ምንኩስናን ተቀብሎ በጾም: በጸሎትና በትሕርምት ይጋደል ገባ::

+ማር ዳንኤል በበዓቱ ተወስኖ ሲጾም: ሲጸልይና እግዚአብሔርን ሲያመልክ ከጸጋ (ከብቅዓት) ደረሰ:: ብዙ ተአምራትንም በመሥራቱ ስም አጠራሩ በአካባቢው ተሰማ:: እርሱ ግን ከሰው: ይልቁንም ከሴቶች ይርቅ: ላለማየትም ራሱን ይከለክል ነበር::

+ለአንድ መናኝ በሰዎች መካከል: ይልቁንም በተቃራኒ ጾታ ጐን መኖር ያልተፈቀደ: ፈታኝም ድርጊት ነውና ከፈጣሪው ጋር እንዲህ የሚል ቃልን ገባ:: "ከዚህ በሁዋላ ሴት ልጅን አላይምም" አለ:: በእንዲህ ያለ የቅድስና ሕይወት ሳለ ወላጅ እናቱ ልታየው ተመኘች::

+ወደ ገዳሙ መጥታም "ልጄ! ላይህ ሽቻለውና ልግባ : ወይ ብቅ በል" ስትል ላከከችበት:: ቅዱሱ ግን "እናቴ! ሴትን አላይም ብየ ቃል ስለ ገባሁ አልችልም" ሲል መለሰላት:: በጣም አዝና "እኔ ወልጄ: አዝዬ: አጥብቼ: አሳድጌ እንደ ሌሎች ሴቶች አስመሰልከኝ? በል ፈጣሪ 2 ሴቶች በአንድ ልብስ ሆነው ይዩህ!" ብላ ረግማው ወደ ቤቷ ተመለሰች::

+የሚገርመው ማር ዳንኤል በበርሃ የበቃውን ያህል እናቱ በዓለም ሳለች በጐ ሰርታለችና እርሷም ጸጋውን አብዝቶላታል:: በምን ይታወቃል ቢሉ:- ያቺ የተናገረቻት ነገር ሁሉ ደርሶበታልና::

+አንድ ቀን ለገንዘብ ሲል አንድ ሰው የገደለውን አምጥቶ በቅዱሱ በር ላይ ጣለው:: ቅዱሱም ያለ አበሳው ታሥሮ ወደ ከተማ ሲወሰድ መታጠቢያ (shower) ቤት ውስጥ የነበሩ ሴቶች ሊያዩት ቸኩለው: አንድ ልብስ ለብሰው ወጥተዋል:: ማር ዳንኤል ይህንን ሲያይ የእናቱ ነገር ትዝ ብሎት ሳቅ ብሏል::

+በታሠረበት ቦታ ግን የሞተውን ሰው በጸሎቱ በማስነሳቱ በክብር ወደ በዓቱ ተመልሷል:: የከተማዋ ንጉሥም ገዳምን አንጾለታል:: በተረፈ ዘመኑም ለብዙ ቅዱሳን አባት ሆኖ እስከ እርጅናው አገልግሏል:: በዚህች ቀንም በክብር ዐርፏል::

+*" አባ ዸላድዮስ "*+

=>አባ ዸላድዮስም በተመሳሳይ የዘመነ ጻድቃን ፍሬ ነው:: በርሃ ከገባባት ቀን ጀምሮ ጾምን: ጸሎትን አዘውትሮ ክርስትናውን አጽንቷል:: ሙሉ እድሜውን በጐ በመሥራት በማሳለፉ ፈጣሪውን ሲያስደስት ለብዙዎች አንባ: መጠጊያ መሆን ችሏል::

+በጸሎቱ አካባቢውን በደህንነት ይጠብቅ ነበር:: ምዕመናን እንኩዋን ወደ እርሱ መጥተው ተባርከው ባሉበት ቦታ ሁነው ተማጽነው እንኩዋ መሻታቸውን አያጡም ነበር:: ምንም ያህል ኃጢአተኞች ይሁኑ እግዚአብሔር ስለ አባ ዸላድዮስ ሲል ይለመናቸው ነበር::

+አንድ ቀን አንድ ነጋዴ ሰው በባሕር ላይ ሲሔድ ድንገት ማዕበል ይነሳበታል:: ብቻውን ነበርና ጨነቀው:: እሱ ያለባት ጀልባም ትንሽ በመሆኗ ልትሠበር ደረሰች:: መዳን እንደ ማይችል ሲያውቅ ተስፋ ቆረጠ::

+ድንገት ግን አባ ዸላድዮስ ትዝ ብሎት ቀና ብሎ "ጌታየ! ስለ ቅዱሱ አባት ብለህ ብትምረኝ ለወዳጅህ መቶ ዲናር ወርቅ እሰጣለሁ" ሲል ተሳለ:: ቃሉን ተናግሮ ሳይጨርስ አባ ዸላድዮስ በጀልባው ላይ ቁጭ ብሎ ታየው:: ማዕበሉም ጸጥ እንዲል አድርጐ ከወደብ አድርሶ ተለየው::

+ነጋዴውም ፈጣሪውን ስለ ድኅነቱ እያመሰገነ 100 ዲናር ወርቁን ይዞ አባ ዸላድዮስን ፍለጋ ወጣ:: የሚያውቀው በዝና ብቻ ነበርና:: መንገድ ላይም ሞሪት የሚባል መሪ አግኝቶ ከአባ ዸላድዮስ በዓት ደረሰ::

+ከቅዱሱ ተባርኮ ወርቁን ቢያቀርብለት "ልጄ! እኔ ይህን አልፈልገውም:: ለነዳያን በትነው" አለው:: ነጋዴው ሲወጣ ግን ሞሪት (መሪው) ገንዘቡን ፈልጐ ገደለውና ከጻድቁ በር ላይ ጣለው:: ሃገረ ገዢውም ሲሰማ አባ ዸላድዮስን አሠረው::

+ጻድቁ ግን የሞተውን ባርኮ አስነሳውና "ማን ገደለህ" ቢለው "ሞሪት" ሲል መልሷል:: መኮንኑ ሞሪትን ሊገድለው ቢልም "የለም" ብሎ ነጋዴውን በደስታ: ሞሪትን ደግሞ በንስሃ ሸኝቷቸዋል:: አባ ዸላድዮስ ግን ተረፈ ዘመኑን በቅድስና ሲጋደል ኑሮ በክብር ዐርፏል::

+*" ቅዱስ ፊላታዎስ ሰማዕት "*+

=>"ፊላታዎስ" ማለት "መፍቀሬ እግዚአብሔር - እግዚአብሔርን የሚወድ: እርሱም የሚወደው" ማለት ነው:: ቅዱሱ የዘመነ ሰማዕታት (3ኛው መቶ ክ/ዘመን) ፍሬ ሲሆን ለየት ያለ ታሪክ ያለው ቡሩክ ወጣት ነው::

+እርሱ የባለ ጸጐች ልጅ: ስለ ክርስትና ምንም ሰምቶ የማያውቅ ሕጻን ነበር:: ወላጆቹ የሚያመልኩት ላምን ሲሆን የአካባቢው ሰው ደግሞ ለጸሐይ ይንበረከክ ነበር:: ቤተሰቦቹ ስለ አምልኮ ሲጠይቁት "እናንተ የምታመልኯቸው ፍጡራን ስለ ሆኑ አልፈልግም" አላቸው::

+ሕጻን ቢሆንም ስለ ፈጣሪው ተመራመረ:: በመጨረሻውም ፀሐይን "አንተ ምንድነህ?" ቢለው "እኔ ፍጡር ነኝ" ሲል መልሶለታል:: በዚያች ዕለት ግን ቅዱስ መልአክ ወርዶ: ሁሉን ነገር አስተምሮ የክርስቶስ ወታደር አድርጐታል::
+ወደ ቤቱ ተመልሶም የወላጆቹን ላም "እውነትን ተናገር" ብሎ ገስጾታል:: ላሙም ሰይጣን እንዳደረበት በሰው ልሳን ተናግሮ: የቅዱሱን ወላጆች ወግቶ ገድሏቸዋል:: ቅዱስ ፊላታዎስ ግን ላሙን አስገድሎ: ወላጆቹን ከሞት አስነስቶ ከአካባ

ቢው ሰው ጋር በስመ ሥላሴ አስጠምቁዋቸዋል::

+በድንግልና ኑሮም ዘመነ ሰማዕታት ሲጀምር በርጉም ዲዮቅልጥያኖስ እጅ ብዙ ተሰቃይቷል:: በጸሎቱም ጣዖታቱን (እነ አዽሎንን) ከነ አገልጋዮቻቸው ወደ ጥልቁ አስጥሟቸዋል:: እርሱም በዚህች ቀን በሰይፍ ተከልሎ ለክብር በቅቷል:: ለእኛ ለኃጥአን የሚሆን ቃል ኪዳንንም ከጌታው ተቀብሏል::

=>የቅዱሳን አባቶቻችን አማናዊት ርስት ድንግል ማርያም አትለየን::

=>ጥር 16 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ፊላታዎስ ሰማዕት
2.አባ ዸላድዮስ ገዳማዊ
3.ማር ዳንኤል ሶርያዊ
4.አባ ዮሐንስ መሐሪ (ሊቀ ዻዻሳት)
5.11,004 ሰማዕታት (የቅ/ቂርቆስ ማሕበር)
6.11,503 (የቅ/ፊላታዎስ ማሕበር)
7.አባ ጽሕማ (ከተስዓቱ ቅዱሳን አንዱ)

=>ወርሐዊ በዓላት
1.በዓለ ኪዳና ለድንግል
2.ቅዱስ አኖሬዎስ ንጉሥ
3.ቅዱስ ገብረ ማርያም (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
4.ቅድስት ኤልሳቤጥ
5.አባ ዳንኤል
6.አባ አቡናፍር ገዳማዊ
7.አባ ዮሐንስ ወንጌሉ ዘወርቅ

=>+"+ ጻድቅ እንደ ዘንባባ ያፈራል::
እንደ ሊባኖስ ዝግባም ያድጋል::
በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ተተክለዋል::
በአምላካችንም አደባባይ ውስጥ ይበቅላሉ::
ያን ጊዜ በለመለመ ሽምግልና ያፈራሉ::
ደስተኞችም ሆነው ይኖራሉ:: +"+ (መዝ. 91:12)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
#ጌታችን #ፍቅር ለሚገባው ፍቅርን፥ #ጅራፍ ለሚገባው ጅራፍን አሳይቷል!

(አንተ ግን ሁለቱንም ጥለሃቸዋልና በከንቱ ታለቅሳለህ)

❖ልብ በል ጅራፍ ጥላቻ አይደለም! ፍትሕ እንጂ!

☞አባቶቻችን ጅራፍን ባያነሱ ኖሮ #ኢትዮጵያም #ቤተክርስቲያንም እስከ ዛሬ አይኖሩም ነበር!

➋ሰማዕትነት ጥሩ ነው፤ ግን ሃገርና ቤተ ክርስቲያን ጨርሰው ከጠፉ ምን ዋጋ አለው? (ሰሜን አፍሪቃን፥ ምስራቅ አውሮፓን፥ ቱርክን፥ መካከለኛው ምሥራቅን  ተመልከት)

➌መፍትሔ ከፈለግህ፦
•ራስህን ካላስፈላጊ መንገዶችህ አንጻ፤
•ንስሃ ግባ
•አተኩረህ (ከልብ) ጸልይ
•ከቻልክ የቤተሰብ/የማኅበር ጸሎትን አዘውትር
•ሌሎች አጀንዳዎችህን አውልቀህ ጥለህ፥ ሃገርና ቤተ ክርስቲያን ላይ አተኩር
•ዘር፥ ቡድን . . . የመሳሰለውን ከእውነት የራቀ ተግባር ከአንተ አራግፍ
•ከዚህ በኋላ ወንድም/እህቶችህን ሰብሰብ አድርገህ ምከር!

"አኃዊነ ምንተ ንግበር - ወንድሞቻችን ምን እናድርግ" (ሐዋ. ፪:፴፯)
የሚለው የምክክር ርዕስ ነው!

☞ይህንን ካደረግህ ቸሩ እግዚአብሔር ካንተ ጋር ነውና ሰውነትህ ለመፍትሔው ሁሉ ዝግጁ ይሆናል!

በማጠቃለያው መጽሐፍ ምን እንደሚል ልነግርህ አስቤ ነበር! ግን ያልኩህን እንደሰማኸኝ እርግጠኛ አይደለሁምና እስከዚህ ይብቃኝ!

@ DnYordanos Abebe

https://www.tg-me.com/zikirekdusn
✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞

✞✞✞ ጥር 17 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ✞✞✞

" አበዊነ መክሲሞስ ወዱማቴዎስ "

=>እኒህ ቅዱሳን የሥጋ ወንድማማቾች ሲሆኑ በቤተ
ክርስቲያን ታሪክ እጅግ ተወዳጅ አባቶች ናቸው::
ስንጠራቸውም "አበዊነ
ቅዱሳን: ወክቡራን: ሮማውያን: መስተጋድላን:
ወከዋክብት ብሩሃን" ብለን ነው::

+ይኸውም "እንደ ንጋት ኮከብ የምታበሩ: ተጋዳይ:
ቅዱሳንና ክቡራን የሆናችሁ ሮማውያን አባቶቻችን" ማለት
ነው:: ሃገረ
ሙላዳቸው ሮም ሁና አባታቸው ንጉሥ ለውንድዮስ
ይባላል::

+ይህ ንጉሥ ሮምን በምታክል ታላቅ ሃገር በ4ኛው መቶ
ክ/ዘመን ነግሦ ሳለ መልካም ሰው ሆኖ ተገኝቷል::
ከመልካም ሚስቱ
(ንግሥቲቱ) ከወለዳቸው መካከልም 2ቱ ከዋክብት
ይጠቀሳሉ:: 2ቱ ቅዱሳን በአጭር የጊዜ ልዩነት የተወለዱ
በመሆናቸው
እንደ መንትያ ይቆጠራሉ::

+ንጉሡ ለውንድዮስም ከእግዚአብሔር ዘንድ ላገኛቸው
ልጆቹ ስም ሲያወጣ ታላቁን መክሲሞስ: ታናሹን ደግሞ
ዱማቴዎስ
ብሎታል:: ቅዱሳኑ በንጉሥ አባታቸው መልካም ፈቃድ
ክርስትናን ተምረዋል::

+ምንም እንኳ የንጉሥ ልጆች እና ልዑላን ቢሆኑም
ተቀማጥለው አላደጉም:: ምቾት ብዙዎችን አጥፍቷልና::
ይህንን የተረዳ
አባታቸው ሞገስን በፈጣሪያቸው ዘንድ እንዲያገኙ እንዲህ
በበጐ ጐዳና አሳደጋቸው::

+ቅዱሳን መክሲሞስና ዱማቴዎስ ካደጉና ለአካለ መጠን
ከደረሱ በኋላ ቅዱሳት መጻሕፍትን ለማንበብ ይተጉ ነበር::
በተለይ
ዜና ቅዱሳንን ከማንበብ አይጠግቡም ነበር::
እግዚአብሔርንም በፍቅር እያመለኩ በጾምና በጸሎት
ይገዙለት ነበር::

+ቅዱሳኑንም ለየት የሚያደርጋቸው አንዱ ይሔው ነው::
ወርቅና ብር በፊታቸው ፈሶ: በእግራቸው እየረገጡት:
አገሩና ምድሩ
እየሰገደላቸው: የላመ የጣመ ምግብ እየቀረበላቸው:
የሞቀ የደመቀ መኝታ እየተነጠፈላቸው . . . ሁሉንም ስለ
ፍቅረ
ክርስቶስ መናቃቸው ይደነቃል::

+እነርሱ በክርስቶስ ፍቅር ሆነው የዚህን ዓለም ጣዕም
ንቀዋልና የአባታቸውን ቤተ መንግስት ሊተዉ አሰቡ::
አሳባቸው
ደግሞ በመመካከር ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ መሪነት:
እንደ አንድ ልብ መካሪ: እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ እንዲሉ
አበው
በጌታ መሪነት ነው::

+ወደ በርሃ ሔደው ለፈጣሪ ለመገዛት ሲያስቡ መውጫ
መንገዳቸውን ይሹ ነበርና አንድ ጐዳና ተገለጠላቸው::
ከዚያም ለንጉሥ
አባታቸው ሔደው "አባ! እኛ ወደ ኒቅያ (ታናሽ እስያ)
ሔደን መባረክ እንፈልጋለን" ሲሉ ጠየቁት::

+ወቅቱ ቦታዋ ስለ 318ቱ ቅዱሳን ሊቃውንት ሞገስን
ያገኘችበት ጊዜ ነበር:: አባታቸውም መንፈሳዊ ሰው ነበርና
ደስ
እያለው ፈቀደላቸው:: ብዙ ወርቅን ሰጥቶ: ሸልሞ ከብዙ
ሠራዊት ጋር ሸኛቸው::

+ቅዱሳኑ መክሲሞስና ዱማቴዎስም ለጥቂት ጊዜ
በኒቅያ ሲጸልዩና ሲባረኩ ሰነበቱ:: ቀጥለውም
የአባታቸውን ሰራዊት ሰብስበው
"እኛ ሱባኤ ልንይዝ ስለ ሆነ እንመጣለን" የሚል
ደብዳቤን ሰጥተው ወደ ሮም ሸኟቸው::

+ወታደሮችን ከሸኙ በኋላ ቅዱሳኑ በአካባቢው ወደ ሚገኝ
አንድ ገዳም ሒደው ለአንድ ደግ መናኝ ምሥጢራቸውን
ገለጹለት::
ልክ የንጉሡ ለውንድዮስ ልጆች መሆናቸውን ሲያውቅ
'አመንኩሰን' ያሉትን እንቢ አላቸው::

+"ለምን?" ሲሉት "ደጉን አባታችሁን ማሳዘን
አልፈልግም:: ግን ፈቃዳችሁ እንዲፈጸምላችሁ ወደ ሶርያ
ዝለቁ:: በዚያ
አባ አጋብዮስ የሚባል ጻድቅ ገዳማዊ ሰው ታገኛላችሁ"
ብሎ ወደ ሶርያ አሰናበታቸው::

+በምድረ ሮም: በተለይም በቤተ መንግስቱ አካባቢ የ2ቱ
ልዑላን መጥፋት (መሰወር) ሲሰማ ታላቅ ሐዘንና ለቅሶ
ተደረገ::
ንጉሡ አባታቸው በወታደሮቹ ዓለምን ቢያካልልም
ሊያገኛቸው አልቻለም:: እርሱ ፈጽሞ ሲያዝን እናታቸው
ፈጽማ መጽናናትን
እንቢ አለች::

+መክሲሞስና ዱማቴዎስ ግን ምድረ ሶርያ ገብትው
የጻድቁ አባ አጋብዮስ ደቀ መዛሙርት ሆኑ:: በእርሱም
ዘንድ ለምናኔ
የሚያስፈልጉ በጐ ምግባራትንና ትሩፋትን ከተማሩ በኋላ
2ቱንም አመነኮሳቸው:: በዚያ ቦታም እየታዘዙ: ፈጣሪን
እያመለኩ:
በጾም: በጸሎትና በትህትና ኖሩ::

+አንድ ቀን ግን አባ አጋብዮስ ጠርቶ "ልጆቼ! ተባረኩ!
በእናንተ ምክንያት ደስ ብሎኛልና:: በዚህች ሌሊት
የመነኮሳት
ሁሉ አለቃ ታላቁ ቅዱስ መቃርዮስ በራዕ ተገልጦ: ልጆች
እንዲሆኑኝ ስጠኝ ብሎኛልና እኔ ሳርፍ ወደ ግብጽ ገዳመ
አስቄጥስ
እንድትሔዱ" አላቸው::

+አባ አጋብዮስ ካረፈ በኋላ ግን እንደ ትዕዛዙ
አልሔዱም:: ውዳሴ ከንቱን ይፈሩ ነበርና:: በዚያው
በምድረ ሶርያ ግን
በጥቂት ጊዜ: ገና በወጣትነት ከብቃት መዓርግ ስለ ደረሱ
በርካታ ተአምራትን ሠሩ:: በሰው ዘንድም ፍጹም ተወዳጅ
ሆኑ::

+ስም አጠራራቸውም ሶርያን መላት:: በዘመኑ
በአካባቢው አንድ ግዙፍ ዘንዶ ተነስቶ ሰውንም
እንስሶችንም ፈጃቸው::
ሕዝቡም ሒደው በቅዱሳኑ ፊት አለቀሱ:: ያን ጊዜ ቅዱስ
መክሲሞስ (ትልቁ) ክርታስ አውጥቶ "አንተ ዘንዶ ይህ
ክርታስ
ወደ አንተ ሲደርስ ከማደሪያህ ውጣ: ሙት: ወፎችም
ይብሉህ" ሲል ጻፈበት::

+"ሒዳችሁ በበሩ ጣሉት" አላቸው:: አንድ ደፋር ሰው
ተነስቶ ሰዎች ሁሉ እያዩት ወስዶ በዘንዶው መውጫ ላይ
ጣለው::
በቅጽበትም ዘንዶው ወጥቶ ሞተ:: አሞሮችም ተሰብስበው
በሉት:: ከዚህ ድንቅ ተአምር የተነሳ ሕዝቡ የቅዱሳኑን
አምላክ አከበረ::

+ከዚህ በተረፈም በቅዱሳኑ ስም ታላላቅ ተአምራት
ተደረጉ:: ርኩሳት መናፍስት ሁሉ ስማቸውን እየሰሙ
ይሸሹ ነበርና::
ድውያን እነሱ በሌሉበት ስማቸው ሲጠራላቸው ይፈወሱ
ነበር:: የአካባቢው ሰው ስማቸውን እየጠራ: በእነርሱም
እየተማጸነ
ከመከራው ሁሉ ይድን ነበርና ለሕዝበ ክርስቲያኑ ሞገስ
ሆኑ::

+መርከበኞች ደግሞ ከማዕበል ለመዳን የቅዱሳኑን ስም
በጀልባዎቻቸው ላይ ይጽፉ ነበር:: አንድ ቀን ግን የንጉሡ
ለውንድዮስ ባለሟል ይህንን ጽሑፍ ተመልክቶ ስለ
ጠረጠረ መርከበኛውን በንጉሡ ፊት አቀረበው::

+ንጉሡም መርከበኛውን "የጻፍከው የማንን ስም ነው?"
ቢለው "በሶርያ የሚገኙ 2 ወንድማማች ቅዱሳን ስም
ነው" አለው::
ልጆቹ እንደ ሆኑ ገምቶ በመርከበኛው መሪነት
ንግሥቲቱንና ሴት ልጁን ላካቸው:: እነርሱ በሐዘን
ተሰብረው ነበርና::

+ወደ ሶርያ ወርደው ባገኟቸው ጊዜም ከናፍቆትና ደስታ
የተነሳ ታላቅ ጩኸትን እየጮሁ አለቀሱ:: "እንሒድ ወደ
ሮም"
ሲሏቸው ግን ቅዱሳኑ "የለም! እኛ የክርስቶስ ነን" ብለው
እንቢ ስላሏቸው እያዘኑ ተመለሱ:: ንጉሡ ግን ይህንን
ሲሰማ
ደስ አለው:: "እነርሱ የዚህን ዓለም ኃላፊነት ተረድተዋል"
ሲልም አወደሳቸው::

+በኋላ ግን "የሮሜ ሊቀ ዻዻሳት መሆን አለባችሁ"
የሚል ነገር ሲሰማ ቅዱሳን መክሲሞስና ዱማቴዎስ
ከሶርያ ወጥተው ወደ
ግብጽ ወረዱ:: የከታላቁ ቅዱስ መቃርስ ዘንድ ደርሰውም
ልጆቹ እንዲሆኑ ለመኑት::

+"ልጆቼ! በርሃ አይከብዳችሁም?" ቢላቸው "ግዴለም!"
አሉት:: በዚያም ከተራራው ሥር በዓት ሠርቶላቸው ለ3
ዓመታት
በአርምሞ ቆዩ:: አንድ ቀንም ቅዱሳኑ እየጸለዩ ከአፋቸው
የወጣ የብርሃን ምሰሶ ከመንበረ ጸባኦት ሲደርስ አይቶ
ታላቁ
መቃርስ አደነቀ::
+በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን መጀመሪያ አካባቢም ጥር 14
ቀን ታላቁ ቅዱስ መክሲሞስ ዐረፈ:: በዕለቱም የሰማይ
ቅዱሳን ሁሉ
ወርደው እየዘመሩ ወሰዱት:: ከ3 ቀን በኋላ ደግሞ ቅዱስ
ዱማቴዎስ ዐረፈ::+በተመሳሳይ ቅዱሳኑ ሲወስዱት 2ቱንም ቅዱሳን ታላቁ
መቃርስ በበዓታቸው ቀብሯቸዋል:: ቦታውም ደብረ
ብርስም (በርሞስ)
ተብሏል:: ትርጉሙም የሮማውያኑ ቅዱሳን ደብር እንደ
ማለት ነው::

✞አምላከ ቅዱሳን በእነርሱ ላይ የበዛች ፍቅሩን ለእኛም
ያድለን:: ፍሬ ትሩፋት: ፍሬ ክብር እንድናፈራም ይርዳን::
ክብራቸውንም አያጉድልብን::

✞ጥር 17 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱሳን እና ክቡራን የሚሆኑ አባቶቻችን "መክሲሞስ
እና ዱማቴዎስ"

በ 17 የሚከበሩ ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት (ቀዳሜ ሰማዕት)
2.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ ዘብዴዎስ)
3.ቅዱሳን አበው መክሲሞስና ዱማቴዎስ
4.አባ ገሪማ ዘመደራ
5.አባ ዸላሞን ፈላሢ
6.አባ ለትጹን የዋህ
7.ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ሊቅ (ዘደሴተ ቆዽሮስ)

++"+ ፍቅር ያስታግሳል:: ፍቅር ያስተዛዝናል:: ፍቅር
አያቀናናም::ፍቅር አያስመካም:: ፍቅር አያስታብይም::
ብቻዬን
ይድላኝ አያሰኝም:: አያበሳጭም:: ክፉ ነገርን
አያሳስብም:: ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ
ደስ
አይለውም:: ሁሉን ይታገሣል:: ሁሉን ያምናል:: ሁሉን
ተስፋ ያደርጋል:: በሁሉ ይጸናል:: +"+ (1ቆሮ. 13:4)

✞✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞✞
2024/09/30 21:39:43
Back to Top
HTML Embed Code: