Telegram Web Link
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#መስከረም_5_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
1ኛ ቆሮንቶስ 11
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁷ ነገር ግን በምትሰበሰቡበት ጊዜ ለሚከፋ እንጂ ለሚሻል ስላልሆነ ይህን ትእዛዝ ስሰጥ የማመሰግናችሁ አይደለም።
¹⁸ በመጀመሪያ ወደ ማኅበር ስትሰበሰቡ በመካከላችሁ መለያየት እንዳለ እሰማለሁና፥ በአንድ በኩልም አምናለሁ።
¹⁹ በእናንተ ዘንድ የተፈተኑት እንዲገለጡ በመካከላችሁ ወገኖች ደግሞ ሊሆኑ ግድ ነውና።
²⁰ እንግዲህ አብራችሁ ስትሰበሰቡ የምትበሉት የጌታ እራት አይደለም፤
²¹ በመብላት ጊዜ እያንዳንዱ የራሱን እራት ይበላልና፥ አንዱም ይራባል አንዱ ግን ይሰክራል።
²² የምትበሉባቸውና የምትጠጡባቸው ቤቶች የላችሁምን? ወይስ የእግዚአብሔርን ማኅበር ትንቃላችሁን አንዳችም የሌላቸውን ታሳፍራላችሁን? ምን ልበላችሁ? በዚህ ነገር ላመስግናችሁን? አላመሰግናችሁም።
²³ ለእናንተ ደግሞ አሳልፌ የሰጠሁትን እኔ ከጌታ ተቀብያለሁና፤
²⁴ ጌታ ኢየሱስ አልፎ በተሰጠበት በዚያች ሌሊት እንጀራን አንሥቶ አመሰገነ፥ ቆርሶም፦ እንካችሁ ብሉ፤ ይህ ስለ እናንተ የሚሆን ሥጋዬ ነው፤ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት አለ።
²⁵ እንደዚሁም ከእራት በኋላ ጽዋውን ደግሞ አንሥቶ፦ ይህ ጽዋ በደሜ የሚሆን አዲስ ኪዳን ነው፤ በጠጣችሁት ጊዜ ሁሉ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት አለ።
²⁶ ይህን እንጀራ በበላችሁ ጊዜ ሁሉ፥ ይህንም ጽዋ በጠጣችሁ ጊዜ ሁሉ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ሞቱን ትናገራላችሁና።
²⁷ ስለዚህ ሳይገባው ይህን እንጀራ የበላ ወይም የጌታን ጽዋ የጠጣ ሁሉ የጌታ ሥጋና ደም ዕዳ አለበት።
²⁸ ሰው ግን ራሱን ይፈትን፥ እንዲሁም ከእንጀራው ይብላ ከጽዋውም ይጠጣ፤
²⁹ ሳይገባው የሚበላና የሚጠጣ የጌታን ሥጋ ስለማይለይ ለራሱ ፍርድ ይበላልና፥ ይጠጣልምና።
³⁰ ስለዚህ በእናንተ ዘንድ የደከሙና የታመሙ ብዙዎች አሉ አያሌዎችም አንቀላፍተዋል።
³¹ ራሳችንን ብንመረምር ግን ባልተፈረደብንም ነበር፤
³² ነገር ግን በተፈረደብን ጊዜ ከዓለም ጋር እንዳንኮነን በጌታ እንገሠጻለን።
³³ ስለዚህ፥ ወንድሞቼ ሆይ፥ ለመብላት በተሰበሰባችሁ ጊዜ እርስ በርሳችሁ ተጠባበቁ።
³⁴ ማንም የራበው ቢኖር ለፍርድ እንዳትሰበሰቡ በቤቱ ይብላ። የቀረውንም ነገር በመጣሁ ጊዜ እደነግጋለሁ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ያዕቆብ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ወንድሞቼ ሆይ፥ በክብር ጌታ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን እምነት ለሰው ፊት በማድላት አትያዙ።
² የወርቅ ቀለበት ያደረገና የጌጥ ልብስ የለበሰ ሰው ወደ ጉባኤአችሁ ቢገባ፥ እድፍ ልብስም የለበሰ ድሀ ሰው ደግሞ ቢገባ፥
³ የጌጥ ልብስም የለበሰውን ተመልክታችሁ፦ አንተስ በዚህ በመልካም ስፍራ ተቀመጥ ብትሉት፥ ድሀውንም፦ አንተስ ወደዚያ ቁም ወይም ከእግሬ መረገጫ በታች ተቀመጥ ብትሉት፥ ራሳችሁን መለያየታችሁ አይደለምን?
⁴ ክፉ አሳብ ያላቸውም ዳኞች መሆናችሁ አይደለምን?
⁵ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ስሙ፤ እግዚአብሔር በእምነት ባለ ጠጎች እንዲሆኑ ለሚወዱትም ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን መንግሥት እንዲወርሱ የዚህን ዓለም ድሆች አልመረጠምን?
⁶ እናንተ ግን ድሆችን አዋረዳችሁ። ባለ ጠጎቹ የሚያስጨንቁአችሁ አይደሉምን? ወደ ፍርድ ቤትም የሚጎትቱአችሁ እነርሱ አይደሉምን?
⁷ የተጠራችሁበትን መልካሙን ስም የሚሰድቡ እነርሱ አይደሉምን?
⁸ ነገር ግን መጽሐፍ፦ ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ እንደሚል የንጉሥን ሕግ ብትፈጽሙ መልካም ታደርጋላችሁ፤
⁹ ለሰው ፊት ግን ብታደሉ ኃጢአትን ትሠራላችሁ፥ ሕግም እንደ ተላላፊዎች ይወቅሳችኋል።
¹⁰ ሕግን ሁሉ የሚጠብቅ፥ ነገር ግን በአንዱ የሚሰናከል ማንም ቢኖር በሁሉ በደለኛ ይሆናል፤ አታመንዝር ያለው ደግሞ፦ አትግደል ብሎአልና፤
¹¹ ባታመነዝርም፥ ነገር ግን ብትገድል፥ ሕግን ተላላፊ ሆነሃል።
¹² በነጻነት ሕግ ፍርድን ይቀበሉ ዘንድ እንዳላቸው ሰዎች እንዲህ ተናገሩ፥ እንዲህም አድርጉ።
¹³ ምሕረትን ለማያደርግ ምሕረት የሌለበት ፍርድ ይሆናልና፤ ምሕረትም በፍርድ ላይ ይመካል።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 18
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁴ በወገኑም የእስክንድርያ ሰው የሆነ ነገር አዋቂ የነበረ አጵሎስ የሚሉት አንድ አይሁዳዊ ሰው ወደ ኤፌሶን ወረደ፤ እርሱም በመጻሕፍት እውቀት የበረታ ነበረ።
²⁵ እርሱ የጌታን መንገድ የተማረ ነበረ፥ የዮሐንስንም ጥምቀት ብቻ አውቆ በመንፈስ ሲቃጠል ስለ ኢየሱስ ይናገርና በትክክል ያስተምር ነበር።
²⁶ እርሱም በምኵራብ ገልጦ ይናገር ጀመር። ጵርስቅላና አቂላም በሰሙት ጊዜ፥ ወስደው የእግዚአብሔርን መንገድ ከፊት ይልቅ በትክክል ገለጡለት።
²⁷ እርሱም ወደ አካይያ ማለፍ በፈቀደ ጊዜ፥ ወንድሞቹ አጸናኑት፥ ይቀበሉትም ዘንድ ወደ ደቀ መዛሙርት ጻፉለት፤ በደረሰም ጊዜ አምነው የነበሩትን በጸጋ እጅግ ይጠቅማቸው ነበር፤
²⁸ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደ ሆነ ከመጻሕፍት እየገለጠ ለአይሁድ በሁሉ ፊት በጽኑ ያስረዳቸው ነበርና።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#መስከረም_5_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇

✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"ሣህል ወርትዕ ተራከባ። ጽድቅ ወሰላም ተሰዐማ። ርትዕሰ እምድር ሠረፀት"። መዝ 84፥10-11።
"ምሕረትና እውነት ተገናኙ፤ ጽድቅና ሰላም ተስማሙ። እውነት ከምድር በቀለች፥ ጽድቅም ከሰማይ ተመለከተች"። መዝ 84፥10-11።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#መስከረም_5_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ዮሐንስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁵ ዮሐንስ ስለ እርሱ መሰከረ እንዲህም ብሎ ጮኸ፦ ከእኔ በኋላ የሚመጣው እርሱ ከእኔ በፊት ነበረና ከእኔ ይልቅ የከበረ ሆኖአል፤ ስለ እርሱ ያልሁት ይህ ነበረ።
¹⁶ እኛ ሁላችን ከሙላቱ ተቀብለን በጸጋ ላይ ጸጋ ተሰጥቶናልና ሕግ በሙሴ ተሰጥቶ ነበርና፤
¹⁷ ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ሆነ።
¹⁸ መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም፤ በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ተረከው።
¹⁹ አይሁድም፦ አንተ ማን ነህ? ብለው ይጠይቁት ዘንድ ከኢየሩሳሌም ካህናትንና ሌዋውያንን በላኩበት ጊዜ፥ የዮሐንስ ምስክርነት ይህ ነው።
²⁰ መሰከረም አልካደምም፤ እኔ ክርስቶስ አይደለሁም ብሎ መሰከረ።
²¹ እንኪያስ ማን ነህ? ኤልያስ ነህን? ብለው ጠየቁት። አይደለሁም አለ። ነቢዩ ነህን? አይደለሁም ብሎ መለሰ።
²² እንኪያስ፦ ማን ነህ? ለላኩን መልስ እንድንሰጥ፤ ስለራስህ ምን ትላለህ? አሉት።
²³ እርሱም፦ ነቢዩ ኢሳይያስ እንዳለ፦ የጌታን መንገድ አቅኑ ብሎ በምድረ በዳ የሚጮኽ ሰው ድምፅ እኔ ነኝ አለ።
²⁴-²⁵ የተላኩትም ከፈሪሳውያን ነበሩና፦ እንኪያስ አንተ ክርስቶስ ወይም ኤልያስ ወይም ነቢዩ ካይደለህ፥ ስለ ምን ታጠምቃለህ? ብለው ጠየቁት።
²⁶ ዮሐንስ መልሶ፦ እኔ በውኃ አጠምቃለሁ፤ ዳሩ ግን እናንተ የማታውቁት በመካከላችሁ ቆሞአል፤
²⁷ እኔ የጫማውን ጠፍር ልፈታ የማይገባኝ፥ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ከእኔ ይልቅ የሚከብር ይህ ነው አላቸው።
²⁸ ይህ ነገር ዮሐንስ ያጠምቅበት በነበረው በዮርዳኖስ ማዶ በቢታንያ በቤተ ራባ ሆነ።
²⁹ በነገው ዮሐንስ ኢየሱስን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ፦ እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ።
³⁰ አንድ ሰው ከእኔ በኋላ ይመጣል፥ ከእኔም በፊት ነበርና ከእኔ ይልቅ የከበረ ሆኖአል ብዬ ስለ እርሱ ያልሁት ይህ ነው።
³¹ እኔም አላውቀውም ነበር፥ ዳሩ ግን ለእስራኤል ይገለጥ ዘንድ ስለዚህ በውኃ እያጠመቅሁ እኔ መጣሁ።
³² ዮሐንስም እንዲህ ብሎ መሰከረ፦ መንፈስ ከሰማይ እንደ ርግብ ሆኖ ሲወርድ አየሁ፤ በእርሱ ላይም ኖረ።
³³ እኔም አላውቀውም ነበር፥ ዳሩ ግን በውኃ አጠምቅ ዘንድ የላከኝ እርሱ፦ መንፈስ ሲወርድበትና ሲኖርበት የምታየው፥ በመንፈስ ቅዱስ የሚያጠምቅ እርሱ ነው አለኝ።
³⁴ እኔም አይቻለሁ እርሱም የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ መስክሬአለሁ።
³⁵ በነገው ደግሞ ዮሐንስ ከደቀ መዛሙርቱም ሁለት ቆመው ነበር፥
³⁶ ኢየሱስም ሲሄድ ተመልክቶ፦ እነሆ የእግዚአብሔር በግ አለ።
³⁷ ሁለቱም ደቀ መዛሙርት ሲናገር ሰምተው ኢየሱስን ተከተሉት።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
የሚቀደሰው ቅዳሴ የ #ቅዱሳን_ሐዋርያት ወይም የ #ቅዱስ_አትናቴዎስ_ቅዳሴ ነው። መልካም የአቡነ አሮን፣ የሰማዕት የቅድስት ሶፍያና የሁለቱ ልጆቿ፣ የቅዱስ ማማስ ሰማዕትና የአጼ ንብለ ድንግል የዕረፍት በዓልና ዕለተ ሰንበት ለሁላችንም ይሁንልን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#መስከረም_6

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
መስከረም ስድስት በዚች ቀን ታላቅ ነቢይ የአሞጽ ልጅ #ቅዱስ_ኢሳይያስ አረፈ፣ #የአቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ ዐፅማቸው ከዋልድባ አብረንታንት ወደ ደብረ ዓባይ የፈለሰበት ዕለት ነው፣ #ቅድስት_ሰብልትንያ በዲዮቀልጥያኖስ ዘመን በሰማዕትነት ሞተች።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ነቢዩ_ኢሳይያስ

መስከረም ስድስት በዚች ቀን ታላቅ ነቢይ የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ አረፈ። ይህም ነቢይ ለይሁዳ በነገሡ በአምስቱ ነገሥታት ዘመን አስተማረ ትንቢትም ተናገረ እሊህም አዝያን ኢዮአታም አካዝ ሕዝቅያስና ምናሴ ናቸው።

በአካዝ ዘመንም እንዲህ ብሎ ትንቢት ተናገረ። እነሆ ስለዚህ #እግዚአብሔር ምልክትን ይሰጣችኋል። እነሆ ድንግል ፀንሳ ወንድ ልጅን ትወልዳለች ስሙንም #አማኑኤል ትለዋለች። ትርጓሜውም #እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ አንድ ሆነ ማለት ነው።

እርሱም በኃጢአታቸው ከሚመጣባቸው ፍዳ ወገኖቹን የሚያድናቸው ወደ ሃይማኖቱም የሚአስገባቸው እንደሆነ የእስራኤልንም ልጆች መሥዋዕታቸውንና ክህነታቸውን እንደሚሽር ከሐዲስ ወገኖችም የሚያመሰግኑት ካህናትን እንደሚሾም ተናገረ።

የፋርስ ንጉሥ ሰናክሬምም ኢየሩሳሌምን ከቦ የስድብ ቃልን በክብር ባለቤት በ #እግዚአብሔር ላይ በተናገረ ጊዜ የፋርስ ንጉሥ ሰናክሬምን ያጠፋው ዘንድ #እግዚአብሔር እንዳለው ለሕዝቅያስ ትንቢትን ተናገረ።

በዚያች ሌሊትም #እግዚአብሔር የላከው የመላእክት አለቃ #ቅዱስ_ሚካኤል ወደ ሠናክሬም ሰፈር መጥቶ ከፋርስ ሠራዊት መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ አርበኞችን ገደለ። የለኪሶ ሰዎች ሲነጋ በተነሡ ጊዜ የሞቱትን ሰዎች ሬሳ ሁሉ አዩ።

ሕዝቅያስም ታሞ ለሞት በተቃረበ ጊዜ የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ወደርሱ መጥቶ #እግዚአብሔር ትሞታለህ እንጂ አትድንም ብሏልና ቤትህን አዘጋጅ አለው። ሕዝቅያስም ፊቱን ወደ ግድግዳው መልሶ ወደ #እግዚአብሔር ለመነ ፈጽሞ ጽኑ ልቅሶንም አለቀሰ።

ይህን ከነገረው በኋላ የ #እግዚአብሔር ቃል ወደ ነቢዩ ወደ ኢሳይያስ መጣ ሒደህ ለሕዝቅያስ የአባትህ የዳዊት ፈጣሪ #እግዚአብሔር ጸሎትህን ሰማሁ ዕንባህንም አየሁ። እነሆ በዘመንህ ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት ጨመርኩልህ አለ በለው።

ዳግመኛም ስለ እስራኤል መማረክና ከምርኮ ስለ መመለሳቸው ትንቢት ተናገረ የፈሳሽ ውኃን ምንጭ በማፍሰስ በእጆቹ ላይ #እግዚአብሔር ምልክትን ገለጠ።

ክብር ይግባውና ስለ #መድኃኒታችን_ክርስቶስ መከራ ትንቢት ተናገረ እንዲህም አለ። እርሱም በመከራው ጊዜ ነገርን አልተናገረም እንደ በግ ይታረድ ዘንድ መጣ በግ በሚሸልተው ሰው ፊት እንደ ማይናገር እንዲሁ በመከራው ጊዜ አልተናገረም።

ከዚህም በኋላ ደግሞ በሕዝቅያስ ልጅ በንጉሥ ምናሴ ላይ ትንቢት ተናገር ጣዖትን ስለማቆሙና ስለማምለኩ ገሠጸው። ስለዚህም ንጉሥ ምናሴ ተቆጥቶ በዕንጨት መሰንጠቂያ መጋዝ በራሱና በእግሮቹ መካከል ሠነጠቀው ምስክርነቱንም በዚህ ፈጸመ።

ትንቢት እየተናገረ የኖረበትም ዘመን ሰብዓ ዓመት ከዚያም በላይ ይሆናል። እርሱም ያስተማረው ክብር ይግባውና #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ከመምጣቱ በፊት በዘጠኝ መቶ ዐሥራ ሦስት ዓመት ነው።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ነብይ ኢሳይያስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አባ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ

ዳግመኛም በዚህች ቀን የዋልድባው የአቡነ ሳሙኤል ዐፅማቸው ከዋልድባ አብረንታንት ወደ ደብረ ዓባይ የፈለሰበት ዕለት ነው፡፡ አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ ትውልዳቸው ከካህናቱ ወገን አክሱም ነው አባታቸው እስጢፋኖስ እናታቸው አመተ ማርያም ይባላሉ። ለመምህር ሰጥተዋቸው ሲማሩ አድገው በኋላም ወላጆቻቸው በሞት ሲለዩአቸው ደብረ በንኰል ገዳም ገብተው ሥርዓተ ምንኩስናን ከአበው እያጠኑ ለትልቁም ለትንሹም በትሕትና እየታዘዙ ውሃ እየቀዱ እንጨት እየሰበሩ በትኅርምት በጽሞና በጸሎት ይኖሩ ነበር።

ሰይጣን በውዳሴ ከንቱ ጾር ቢመጣባቸው ከማሕበረ መነኮሳቱ ተለይተው በተባሕትዎ ለመኖር ሽተው ወጥተው ሲሔዱ ተከዜ ደረሱ። ወንዙ ሞልቶ የማያሻግራቸው ቢሆን ውሃውን በትምህርተ #መስቀል ባርከው በአንድ እጃቸው መጽሐፍ በአንድ እጃቸው መብራት እንደያዙ ገብተው መብራቱ ሳይጠፋ መጽሐፉ ሳይበላሽ ተሻግረዋል። ዋልድባ ሲደርሱ #ጌታ እዚህ ተቀመጥ ስላላቸው ገዳም መሥርተው ሥርዓተ ምንኩስናን እያስተማሩ ተቀመጡ። ዛሬ በዋልድባ የሚያመሰግኑበት #ውዳሴ_ማርያም #ቅዳሴ_ማርያምን ከተከዜ ወዲህ ያመጡ እሳቸው ናቸው። ይህንን እየጸለዩ ሲሔዱ ክንድ ከስንዝር መሬት ለቀው ይታዩ ነበር። አንድ ቀንም ይህንን ጸሎት ደግመው ውኃውን ቢባርኩት ኅብስተ ሕይወት ሆነላቸው ከነደቀ መዛሙርቶቻቸው ተመግበውታል።

#እመቤታችንም የፍቅር መግለጫ ዕጣን፣ ወርቅ፣ እንቁ ሰጥታቸዋለች። ውዳሴዬን ከቅዳሴዬ አንድ አድርጎ የደገመውን አንተ ከገባህበት መካነ ሕይወት አስገባዋለሁ ብላ ቃልኪዳን ሰጥታቸዋለች። ጊዜ እረፍታቸው ሲደርስ #ጌታን በስብሐተ መላእክት ተገልጦ በስምህ የተማጸነውን በጎ የሰራውን፣ ዜና ገድልህን የጻፈውን፣ ያስጻፈውን፣ ያነበበ፣ የተማረ፣ ያስተማረ፣ እስከ አሥር ትውልድ ድረስ ምሬልሃለሁ። በዚህ ቦታ በዋልድባ የሚሰበሰቡ ልጆችህን ከእዳ ከፍዳ እሰውርልሃለሁ አላቸው። እንኪያስ ቦታዋን ባርክልኝ ብለው እንደ መሶብ አንስተው አስባርከዋታል #ጌታችንም እህል አይብቀልብሽ ኃጢአት አይሻገርብሽ ብሎ ቃል ኪዳን ገባላት ለገዳመ ዋሊ። አባታችን አቡነ ሳሙኤል በበዓታቸው ውስጥ ጸንተው ሲኖሩ ታህሣሥ 12 ቀን ያረፉ ሲሆን ዛሬ መስከረም 6 ግን ፍልሰተ አጽማቸው የተከናወነበት እለት ነው።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጻድቁ አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅድስት_ሰብልትንያ

በዚህችም ቀን ቅድስት ሰብልትንያ በከ*ሀዲ ንጉሥ ዲዮቀልጥያኖስ ዘመን በሰማዕትነት ሞተች። ይችንም ቅድስት ዕድሜዋ ዘጠኝ ዓመት ሲሆን ከሀ*ድያን ያዙዋት እጆቿንና እግሮቿንም አሥረው ከሚነድ እሳት ውስጥ ጣሏት የክብር ንጉሥ በሆነ በ #እግዚአብሔርም ኃይል ከእሳት ዳነች።

ውኃን በተጠማች ጊዜ #እግዚአብሔርን ለምናው ውኃን አፈለቀላትና ጠጣች ክብር ምስጉን የሆነ #ጌታችንንም አመሰገነችው። ከዚህም በኋላ ነፍሷን በ #እግዚአብሔር እጅ አደራ ሰጥታ ራሷን ከእሳት ውስጥ ወረወረች ምስክርነቷንም ፈጸመች።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_መስከረም_6 እና #ከገድላት_አንደበት)
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#መስከረም_6_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሮሜ 9
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁵ እንዲሁ ደግሞ በሆሴዕ፦ ሕዝቤ ያልሆነውን ሕዝቤ ብዬ፥ ያልተወደደችውንም የተወደደችው ብዬ እጠራለሁ፤
²⁶ እናንተ ሕዝቤ አይደላችሁም በተባለላቸውም ስፍራ በዚያ የሕያው እግዚአብሔር ልጆች ተብለው ይጠራሉ ይላል።
²⁷-²⁸ ኢሳይያስም፦ የእስራኤል ልጆች ቁጥር ምንም እንደ ባሕር አሸዋ ቢሆን ቅሬታው ይድናል፤ ጌታ ነገሩን ፈጽሞና ቆርጦ በምድር ላይ ያደርገዋልና ብሎ ስለ እስራኤል ይጮኻል።
²⁹ ኢሳይያስም እንደዚሁ፦ ጌታ ፀባዖት ዘር ባላስቀረልን እንደ ሰዶም በሆንን ገሞራንም በመሰልን ነበር ብሎ አስቀድሞ ተናገረ።
³⁰ እንግዲህ ምን እንላለን? ጽድቅን ያልተከተሉት አሕዛብ ጽድቅን አገኙ፥ እርሱ ግን ከእምነት የሆነ ጽድቅ ነው፤
³¹ እስራኤል ግን የጽድቅን ሕግ እየተከተሉ ወደ ሕግ አልደረሱም።
³²-³³ ይህስ ስለ ምንድር ነው? በሥራ እንጂ በእምነት ጽድቅን ስላልተከተሉ ነው፤ እነሆ፥ በጽዮን የእንቅፋት ድንጋይና የማሰናከያ ዓለት አኖራለሁ በእርሱም የሚያምን አያፍርም ተብሎ እንደ ተጻፈ በእንቅፋት ድንጋይ ተሰናከሉ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
2ኛ ጴጥሮስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁹ ከእርሱም ይልቅ እጅግ የጸና የትንቢት ቃል አለን፤ ምድርም እስኪጠባ ድረስ የንጋትም ኮከብ በልባችሁ እስኪወጣ ድረስ፥ ሰው በጨለማ ስፍራ የሚበራን መብራት እንደሚጠነቀቅ ይህን ቃል እየጠነቀቃችሁ መልካም ታደርጋላችሁ።
²⁰ ይህን በመጀመሪያ እወቁ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም፤
²¹ ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 28
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁵ እርስ በርሳቸውም ባልተስማሙ ጊዜ፥ ጳውሎስ አንዲት ቃል ከተናገረ በኋላ ሄዱ፤ እንዲህም አለ፦ መንፈስ ቅዱስ በነቢዩ በኢሳይያስ ለአባቶቻችን፦
²⁶ ወደዚህ ሕዝብ ሂድና፦ መስማትን ትሰማላችሁና አታስተውሉም፥ ማየትንም ታያላችሁና አትመለከቱም፤
²⁷ በዓይናቸው እንዳያዩ በጆሮአቸው እንዳይሰሙ በልባቸውም እንዳያስተውሉ ተመልሰውም እንዳልፈውሳቸው፥ የዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኖአል ጆሮአቸውም ደንቁሮአል ዓይናቸውንም ጨፍነዋል በላቸው ሲል መልካም ተናገረ።
²⁸ እንግዲህ ይህ የእግዚአብሔር ድኅነት ለአሕዛብ እንደ ተላከ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን፤ እነርሱ ደግሞ ይሰሙታል።
²⁹ ይህንም በተናገረ ጊዜ አይሁድ እርስ በርሳቸው እጅግ እየተከራከሩ ሄዱ።
³⁰ ጳውሎስም በተከራየው ቤት ሁለት ዓመት ሙሉ ተቀመጠ፥ ወደ እርሱም የሚመጡትን ሁሉ ይቀበል ነበር፤
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#መስከረም_6_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇

✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"ወገሠጸ ነገሥተ በእንቲአሆሙ። ወኢትግሥሡ መሲሐንየ። ወኢታሕስሙ ዲበ ነቢያትየ"። መዝ104፥14-15።
“የቀባኋቸውን አትዳስሱ፥ በነቢያቴም ክፉ አታድርጉ ብሎ፥ ሰው ግፍ ያደርግባቸው ዘንድ አልፈቀደም፥ ስለ እነርሱም ነገሥታትን ገሠጸ።”— መዝሙር 105፥14-15
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#መስከረም_6_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ዮሐንስ 12
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³⁶ የብርሃን ልጆች እንድትሆኑ ብርሃን ሳለላችሁ በብርሃኑ እመኑ አላቸው። ኢየሱስም ይህን ተናግሮ ሄደና ተሰወረባቸው።
³⁷-³⁸ ነገር ግን ይህን ያህል ምልክት በፊታቸው ምንም ቢያደርግ፤ ነቢዩ ኢሳይያስ፦ ጌታ ሆይ፥ ማን ምስክርነታችንን አመነ? የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገለጠ? ብሎ የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ በእርሱ አላመኑም።
³⁹-⁴⁰ ኢሳይያስ ደግሞ፦ በዓይኖቻቸው እንዳያዩ፥ በልባቸውም እንዳያስተውሉ፥ እንዳይመለሱም፥ እኔም እንዳልፈውሳቸው፥ ዓይኖቻቸውን አሳወረ ልባቸውንም አደነደነ ብሎአልና ስለዚህ ማመን አቃታቸው።
⁴¹ ክብሩን ስለ አየ ኢሳይያስ ይህን አለ፥ ስለ እርሱም ተናገረ።
⁴² ከዚህም ጋር ከአለቆች ደግሞ ብዙዎች በእርሱ አመኑ፤ ነገር ግን ከምኵራብ እንዳያስወጡአቸው በፈሪሳውያን ምክንያት አልመሰከሩለትም፤
⁴³ ከእግዚአብሔር ክብር ይልቅ የሰውን ክብር ወደዋልና።
⁴⁴ ኢየሱስም ጮኸ፥ እንዲህም አለ፦ በእኔ የሚያምን በላከኝ ማመኑ ነው እንጂ በእኔ አይደለም፤
⁴⁵ እኔንም የሚያይ የላከኝን ያያል።
⁴⁶ በእኔ የሚያምን ሁሉ በጨለማ እንዳይኖር እኔ ብርሃን ሆኜ ወደ ዓለም መጥቻለሁ።
⁴⁷ ዓለምን ላድን እንጂ በዓለም ልፈርድ አልመጣሁምና ቃሌን ሰምቶ የማይጠብቀው ቢኖር የምፈርድበት እኔ አይደለሁም።
⁴⁸ የሚጥለኝ ቃሌንም የማይቀበለው እርሱ የሚፈርድበት አለው፤ እኔ የተናገርሁት ቃል እርሱ በመጨረሻው ቀን ይፈርድበታል።
⁴⁹ እኔ ከራሴ አልተናገርሁምና፤ ነገር ግን የላከኝ አብ እርሱ የምለውን የምናገረውንም ትእዛዝ ሰጠኝ።
⁵⁰ ትእዛዙም የዘላለም ሕይወት እንደ ሆነች አውቃለሁ። ስለዚህ እኔ የምናገረውን አብ እንደ ነገረኝ እንዲሁ እናገራለሁ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
የሚቀደሰው ቅዳሴ የ #ቅዱስ_ዮሐንስ_ወልደ_ነጐድጓድ ቅዳሴ ነው። መልካም የነቢዩ ቅዱስ ኢሳይያስ የዕረፍት በዓል፣ የአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ ፍልሰተ አጽም በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ነቢዩ_ኢሳይያስ

ኢሳይያስ የሚለው ስም በአይሁድ ማኅበረ ሰብ ውስጥ እጅግ የተለመደ ስም ነው፤ በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ እንኳ ብያንስ ወደ ፯ የሚኾኑ ሰዎች በዚኽ ስም ተጠርተዋል፡፡
“ኢሳይያስ፣ የሻያ” ከአራቱ ዐበይት ነቢያት አንዱ ሲኾን የስሙም ትርጓሜ “ #መድኃኒት” ማለት ነው፡፡ ሆሴዕ፣ ኢያሱ፣ ኢየሱስ ማለት መድኃኒት ማለት እንደኾነ መድኃኒት መባሉ ግን እንደ ኢያሱ ወልደ ነዌ ባጭር ታጥቆ፥ ጋሻ ነጥቆ፥ ዘገር ነቅንቆ አማሌቃውያንን አጥፍቶ እስራኤልን አድኖ፥ እንደ #ኢየሱስ_ክርስቶስ ሥጋዉን ቆርሶ፥ ደሙን አፍስሶ፥ ፲፫ቱን ሕማማተ መስቀል ታግሦ፥ አጋንንትን ድል ነስቶ ነፍሳትን አድኖ አይደለም፤ ተልእኮውን የሚገልጥ ነው እንጂ፡፡ በሌላ አገላለጽ ሊመጣ ያለው መሲሕ ማለትም #ጌታችንና_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ በድንግልና ተፀንሶ፣ በድንግልና ተወልዶ፣ ቀስ በቀስ አድጎ፣ የደቂቀ አዳምን ሕማም ተሸክሞ አጠቃላይ የሰው ልጆችን በአስደናቂ መጐብኘትን ጐብኝቶ እንደሚያድናቸው ስለሚናገር “ኢሳይያስ - መድኃኒት” የሚል ስም ተሰጥቶታል፡፡

➛ተመሳሳይ ስም ካላቸው ከሌሎች ሰዎች ለመለየትም “የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ” ተብሎ ተጠርቷል /ኢሳ.፩፡፩/፡፡ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ይኽ አሞጽ ነቢዩ እንዳልኾኑ ይስማማሉ፡፡ እናንቱም የቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት እንደሚያስረዳው ሶፊያ ትባላለች፡፡

ኢሳይያስ ይኖር የነበረው በኢየሩሳሌም ነው፡፡ ኢሳይያስ ባለትዳርና የኹለት ልጆች አባት ነበር፡፡ ሚስቱም ነቢይት እንደነበረች መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል /ኢሳ.፰፡፫/፡፡ መተርጕማን እንደሚናገሩት፡- “የኢሳይያስ ሚስት ነቢይት መባሏ የባለቤቷን መንፈሳዊ ሕይወት፣ ተጋድሎውን ትጋራ ስለነበርና በተልእኮው ኹሉ ትረዳው ስለነበረ እንጂ ራዕይን የማየት ትንቢትንም የመናገር ጸጋ ተስጥቷት ስለነበረ አይደለም” ይላሉ፡፡ ኢሳይያስ ከባለቤቱ ኹለት ልጆችን ያፈራ ሲኾን የልጆቹ ስያሜም ትንቢት አዘል ትርጓሜን የቋጠረ ነው፡፡ ታላቁ ልጅ “ያሱብ” ይባላል፡፡ “ያሱብ” ማለትም “ቅሬታዎቹ ይመለሳሉ” ማለት ነው /ኢሳ.፯፡፫/፡፡ ታናሹ ልጅ ደግሞ “ማኄር ሻላል ሐሽ ባዥ” ይባላል፡፡ ይኸውም “ምርኮ ፈጠነ ብዝበዛም ቸኰለ” ማለት ነው /ኢሳ.፰፡፫/፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስ በቤተ ሰቡ በጣም ደስተኛ ነበር፡፡ ይመካባቸውም ነበር፡፡ “እነሆ፥ እኔና #እግዚአብሔር የሰጠኝ ልጆች ለእስራኤል በጽዮን ተራራ ከሚኖረው ከሠራዊት #ጌታ#እግዚአብሔር ዘንድ ምልክትና ተአምራት ነን” ማለቱም ይኽንን ያስረዳል /ኢሳ.፰፡፲፰/፡፡

ነቢዩ ኢሳይያስ በኢየሩሳሌም ሲኖር በአካዝና በሕዝቅያስ ዘመነ መንግሥት የቤተ መንግሥት አማካሪ ነበር፡፡ በራሱ መጽሐፍ እንደነገረንም በዘመኑ የነበሩ የይሁዳ ነገሥታት ዖዝያን፣ ኢዮአታም፣ አካዝና ሕዝቅያስ ይባላሉ /ኢሳ.፩፡፩/፡፡ የነቢይነትን ሥራ የዠመረውም ወዳጁ ዖዝያን በሞተ በዓመቱ ነው፡፡ ይኸውም በ፯፻፵ ዓ.ዓ. አከባቢ ማለት ነው፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስ “ዖዝያንን ገስጽ” ሲባል ወዳጁ ስለኾነ ይሉኝታ ይዞት እምቢ ብሎ ነበር፡፡ ከዚኽም የተነሣ ከአፉ ላይ ለምፅ ወጣበት፡፡ ጌታም ተገልጦ፡- “የምትወደውና የምታከብረው ዖዝያን ሞተ፤ መንግሥቱም አለፈ፡፡ ሞት፣ ኅልፈት፣ በመንግሥቴም ሽረት የሌለብኝ እኔ አምላክኽ ብቻ ነኝ” አለው፡፡ ኢሳይያስ ይኽን ሲሰማ እጅግ ደነገጠ፡፡ ዳግመኛም #እግዚአብሔር፡- “ወደዚኽ ሕዝብ ማንን ልላክ?” አለው፡፡ ኢሳይያስም፡- “እኔ እሔድ ነበር፤ ግን በአፌ ለምፅ አለብኝ” ሲል መልአኩ በጉጠት አፉን ቀባውና ለምፁ ድኖለት ትንቢት ተናግሯል /ኢሳ.፮/፡፡

➛ነቢዩ ኢሳይያስ የነበረበት ሃይማኖታዊ፣ ማኅበራዊ፣ ግብረ ገብነታዊና ፖለቲካዊ ኹኔታ
ነቢዩ ኢሳይያስ በኢየሩሳሌም ሲኖር የቤተ መንግሥትም አማካሪ ኾኖ እንደማገልገሉ መጠን የነገሥታቱን ብዕል፣ ለመጓጓዣ የሚገለገሉባቸው ሠረገላዎች፣ ለማዕድ የሚጠቀሙባቸው ዕቃዎች፣ ሕዝቡን ንቀው የሚያዩበት ትዕቢታቸው፣ ከሚስቶቻቸው ጋር የሚያሳልፉት የቅንጦት ኑሮአቸውን ይመለከት ነበር፡፡ በየዕለቱ በሚዘጋጀው የእራት ግብዣ ልዑላኑ በከፍተኛ የወታደር፣ የሃይማኖትና የሲቪል አመራሮች ታጅበው የሚጠጡት ወይን፣ በመጨረሻም ሰክረው የሚያሳዩት አሳፋሪ ድርጊትን ያይ ነበር፡፡ ይኽ በእንዲኽ እንዳለ እነዚኽ ልዑላን ወደ ቤተ መቅደስ መጥተው የሚያቀርቡት የመሥዋዕት ብዛት፣ ከስግብግቦቹ የሃይማኖት መሪዎች የሚቀርብላቸው ውዳሴ ከንቱ፣ ከቤተ መቅደሱ መልስ በኋላ ደግሞ የሚያከናውኑትን አሕዛባዊ ግብር በአጽንዖት ይመለከት ነበር፡፡ ነቢዩ ሲመለከት የነበረው ይኽን የቤተ መንግሥቱና የቤተ ክህነቱ የቅንጦት ኑሮን ብቻ አይደለም፡፡ የመበለቶች፣ የወላጅ አልባ ሕፃናት፣ የድኾች፣ የችግረኞች ጩኸትም በነቢዩ ጆሮ ያስተጋባ ነበር፤ ወደ መንበረ ጸባዖትም ሲወጣ ያስተውል ነበር፡፡
➛ነቢዩ ራሱ “ራስ ኹሉ (የቤተ መንግሥቱ አመራር) ለሕመም ልብም ኹሉ (የቤተ ክህነቱ አመራር) ለድካም ኾኗል። ከእግር ጫማ አንሥቶ እስከ ራስ ድረስ (ከተራው ሕዝብ አንሥቶ እስከ አመራሩ ድረስ) ጤና የለውም፤ ቍስልና እበጥ የሚመግልም ነው፤ አልፈረጠም፥ አልተጠገነም፥ በዘይትም አልለዘበም” ብሎ እንደገለጠው /ኢሳ.፩፡፭-፮/ የይሁዳ ቤተ መንግሥትና ቤተ ክህነት ከነ ተራው ሕዝቡ ተበላሽቶ ነበር፡፡ ኹሉም በ #እግዚአብሔር ታምኖ ሳይኾን በሰው ክንድ ተደግፎ ይሰባሰባል፤ ግዑዛን እንስሳት እንኳ የጌታቸውን ጋጣ ሲያውቁ ሰዎች ግን ፈጣሪያቸውን ረስተዋል፡፡ አለቆች በግብዝነት፣ ጉቦን በመውደድ፣ ለድኻ አደጉ ባለመፍረድ፣ የመበለቲቱን ሙግት ባለመስማት ይታወቃሉ /ኢሳ.፩፡፳፫/፡፡ አንባቢ ሆይ! አኹን ያለውን የቤተ ክህነታችንና የቤተ መንግሥት ኹናቴ ከዚኹ ጋር ያገናዝቡ!!!

#በነቢዩ ኢሳይያስ ጊዜ የነበረውን ፖለቲካዊ ትኩሳት ስንመለከትም፥ ነቢዩ አገልግሎቱን በዠመረበት ወራት በኹለት ኃያላን መንግሥታት ማለትም በግብጽና በአሦር መካከል ውጥረት ነግሦ ነበር፡፡ ወደ አገልግሎቱ ማብቂያ አከባቢ ደግሞ በአሦርና በባቢሎን መካከል የነበረው ፍጥጫ ጣራ የደረሰበት ወራት ነበር፡፡ የእነዚኽ ኃያላን መንግሥታት መፈክር፡- “Power is the truth - እውነት ማለት ሥልጣን ነው” የሚል ነበር፡፡ በእነዚኽ ኃያላን መንግሥታት መካከል የነበረው ፍጥጫ በእስራኤልና በይሁዳን እንዴት ጫና እንዳሳደረ ለመረዳትም ፪ኛ ነገሥት ከምዕራፍ ፲፭ እስከ ፲፯ ያለውን ክፍል ማንበብ በቂ ነው፡፡ ጥቂቶቹን ለማየት ያኽልም፡-
#የእስራኤል ንጉሥ የነበረው ምናሴ የአሦር ንጉሥ ለነበረው ለፎሐ መንግሥቱን ያጸናለት ዘንድ አንድ ሺሕ ሰቅል ብር ሰጥቶታል /፪ኛ ነገ.፲፭፡፲፱-፳/፡፡
➛የዖዝያን (ይሁዳ ንጉሥ) ንግሥና ማብቂያ አከባቢ ቴልጌልቴልፌልሶር የተባለ የአሦር ንጉሥ ፋቁሔ የተባለው የእስራኤል ንጉሥ ነግሦ ሳለ ሃገሪቱን ወርሮ ነበር /፪ኛ ነገ.፲፭፡፳፱/፡፡ በይሁዳ ላይ ነግሦ በነበረው በአካዝ ላይም ዘመቱበት፡፡ ኢሳይያስም የራሱን ልጆች ምልክት እያደረገ አካዝ በ #እግዚአብሔር እንዲታመን እንጂ እንዳይደነግጥ መከረው፡፡ አካዝ ግን ጠላቶቹን እንዲቋቋምለት ለማድረግ ለአሦር ንጉሥ ግብር ይልክለት ነበር /ኢሳ.፯፡፩-፲፯፣ ፪ኛ ዜና ፳፰፡፲፮-፳፩/፡፡
#ፋቁሔም በኋላ በሆሴዕ ተገደለ፤ ሆሴዕም ነገሠ፡፡ በኋላ ላይ ግን የአሦር ንጉሥ ስልምናሶር በሆሴዕ ላይ ዘመተ፡፡ ሆሴዕም ተገዛለት፤ ግብርም አመጣለት፡፡ ነገር ግን ስልምናሶር ሆሴዕን ስላላመነው ወደ ወኅኒ አስገባው፡፡ ሰማርያንም (ሰሜናዊው ክፍል ይኸውም እስራኤል ያልነውን) ሦስት ዓመት ከበባት፤ ሕዝቡን ደግሞ ወደ አሦር አፈለሳቸው /፪ኛ ነገ.፲፯፡፫-፮/፡፡
➛እስራኤልና ይሁዳ በአምላካቸው ከመታመን ይልቅ #እግዚአብሔርን ወደሚያስቈጣ የፖለቲካ ስሌት ውስጥ ገብተው ነበር፡፡ ሰማርያ (እስራኤል) ይሁዳን ለመውጋት ከሶርያ ጋር ስትወዳጅ፣ ይሁዳ ደግሞ እስራኤልን ለመውጋት ከአሦር ጋር ተወዳጅታ ነበር፡፡ እንደዉም አካዝ፡- “እኔ ባሪያህና ልጅህ ነኝ፤ መጥተህ ከተነሡብን ከሶርያ ንጉሥና ከእስራኤል ንጉሥ እጅ አድነኝ” ብሎ ወደ አሦር ንጉሥ ወደ ቴልጌልቴልፌልሶር መልእክተኞችን ልኮ እንደነበር መጽሐፍ ቅዱሳችን ይነግረናል /፪ኛ ነገ.፲፮፡፯/፡፡ ከላይ እንደጠቀስነውም እንደ ማማለጃ ይኾን ዘንድ አካዝ በ #እግዚአብሔር ቤትና በንጉሡ ቤት መዛግብት የተገኘውን ብርና ወርቅ ወስዶ ወደ አሦር ንጉሥ ገጸ በረከት አድርጎ ሰደዶለት ነበር፡፡ የአሦር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር ግን መጥቶ አስጨነቀው እንጂ አልረዳውም /፪ኛ ዜና ፳፰፡፳-፳፩/።

➛ነቢዩ ኢሳይያስ እንግዲኽ ይኖር የነበረው በእነደዚኽ ዓይነት ውስብስብ ጊዜ ውስጥ ነበር፡፡ በአንድ በኩል የወገኖቹ ፍቅር ልቡን ያቃጥሏል፤ የእስራኤልና የይሁዳ አለመስማማት ይባስ ብሎም እርስ በርስ ለመተላለቅ ከውጭ ኃይሎች ጋር መወዳጀታቸው ውስጡን ያቆስሏል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ይሁዳ የእኅቷ የእስራኤልን ጥፋት እየተመለከተች ምንም አለመማሯ ይልቁንም ደግሞ ወደ ጥፋት ሸለቆ መንጐዷ እጅጉን አሳዘነው፡፡ አኹን ያለው የሃገራችን ኹናቴ አንባብያን ያገናዝቡት!!

➛ነቢዩ ኢሳይያስ እንደ ጠቢብ ፖለቲከኛ በመንፈሰ #እግዚአብሔር እየተመራ በጊዜው የነበረውን ፖለቲካዊ ትኩሳት ከምንጩ የሚያውቅ ነበር፡፡ የመንግሥታቱን አካሔድ አይቶም የደማስቆና የሰማርያ ውድቀት እንዲኹም የአሦር መንግሥት መካከለኛ ምሥራቁን እንደሚቈጣጠረው ተንብዮአል /ኢሳ.፯/፡፡ ከዚያ በላይ አለፍ ብሎም የባቢሎን አደገኛነት በይሁዳ ላይም የሚመጣውን መዘዝ ተናግሯል /ኢሳ.፴፱/፡፡ ጨምሮም ኹሉም ወገኖቹ (እስራኤልም ይሁዳም) ከምርኮ እንደሚመለሱ ተንብዮአል፡፡

➛ነቢዩ ኢሳይያስ የአሦር መንግሥት በኋላም የባቢሎን መንግሥት በእስራኤልና በይሁዳ ማየል #እግዚአብሔር ለቁንጥጫ የተጠቀመበት ጥበብ እንደነበር ተረድቷል፡፡ የይሁዳ ሰዎች ኢየሩሳሌም በአሦር ሰዎች ትወረራለች ብለው አልመውም አስበውም አያውቁም፤ ነቢዩ ግን ይኽ ኹሉ እንደሚኾን በትንቢት መነጽር አስረግጦ ነገራቸው፡፡ ይኽ ኹሉ የመኾኑ ምስጢርም ሕዝቡ ወደ #እግዚአብሔር እንዲመለሱና ከውጭ ኃይላት ይልቅ በእርሱ እንዲታመኑ ለማድረግ እንደኾነ ነግሯቸዋል፡፡ ለፖለቲካዊ ችግራቸው ከንስሐ ውጪ ሌላ መፍትሔ እንደሌለው ይነግራቸው ነበር፡፡

➛ነቢዩ እውነትን የማይሸፋፍን፣ ለማንም የማያዳላ መምህር ወመገስጽ ነበር፡፡ ምንም ሳይፈራና ሳያፍር አካዝን፡- “እናንተ የዳዊት ቤት ሆይ፥ ስሙ፤ በውኑ ሰውን ማድከማችሁ ቀላል ነውን? አምላኬን ደግሞ የምታደክሙ፤” ብሎታል /ኢሳ.፯፡፲፫/፡፡ ሕዝቡን “በደል የተሞላበት ሕዝብ” /ኢሳ.፩፡፬/፤ ልዑላኑን “የሰዶም አለቆች” /ኢሳ.፩፡፲/፤ በዚያ ሰዓት የነበሩት ጠላቶች (የሶርያው ንጉሥ ረኣሶንና የእስራኤሉ ንጉሥ ፋቁሔ) “ኹለት የእንጨት ጠለሸቶች” /ኢሳ.፯፡፬/ ብሎ ገስጾአቸዋል፡፡ ልቡ ደግሞ ስለ ሞዓብ ይጮኻል /ኢሳ.፲፭፡፭/፤ በባቢሎን መንግሥት ምክንያት ስለሚደርሰው ውድቀትም፡- “ፊታችሁን ከእኔ ዘንድ አርቁ፤ መራራ ልቅሶ አለቅሳለኹ፤ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ጥፋት ታጽናኑኝ ዘንድ አትድከሙ” እያለ መራራ ለቅሶን ያለቅሳል /ኢሳ.፳፪፡፬/፡፡

የነቢዩ ኢሳይያስ ልዩ ስብእናዎች
1, ታላቅ ነቢይ ነው፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስ ካደረጋቸው ግብሮችና ከጻፈው መጽሐፍ ይዘት አንጻር ታላቅ ነቢይ ልንለው እንችላለን፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስ በጽናቱ ነቢዩ ዳንኤልን ይመስላል፤ በጨዋነቱ ነቢዩ ኤርምያስን ይመስላል፤ ጸዋትወ መከራን በመቀበሉ ነቢዩ ሆሴዕን ይመስላል፤ መምህር ወመገስጽ በመኾኑ ደግሞ ነቢዩ አሞጽን ይመስላል፡፡ ከኹሉም በተለየ ግን ምንም እንኳን ከሊቅ እስከ ደቂቅ እንዲኽ ቢገስጻቸውም የድኅነት ተስፋም ይሰጣቸው ነበር፤ ተስፋውም ለእነርሱ ብቻ ሳይኾን ለደቂቀ አዳም በሙሉ የሚኾን ተስፋ ድኅነትን ነበር፡፡ ከዚኽም የተነሣ ታላቅ ነቢይ ነው፡፡
2, #እግዚአብሔር በሦስት መንገድ ኢሳይያስን አናግሮታል፡፡ በሚያስደንቅ ግርማ /ኢሳ.፮/፣ በጽኑ እጅ /ኢሳ.፰፡፲፩/፣ እንዲኹም በአባታዊ ንግግር /ኢሳ.፳፡፪/ አናግሮታል፡፡ እርሱም ይኽ ከ #እግዚአብሔር የተቀበለውን መልእክት በሦስት መንገድ አስተላልፎታል፡፡ በአደባባይ በሚደረግ ግልጽ ትምህርት፣ ለምልክትና ለተአምራት ሊኾን ራቁቱንና ባዶ እግሩን በመሔድ፣ እንዲኹም በጽሕፈት፡፡
3, ከቤተ ክህነቱ እስከ ቤተ መንግሥቱ ድረስ ኹሉም ሕይወቱ በተበላሸና አምልኮው ኹሉ ግብዝ በኾነበት ሰዓት ነቢዩ ኢሳይያስ ግን ግሩም የኾነውን መለኮታዊ ምስጢር ይካፈል ነበር፡፡ በዚኽም #እግዚአብሔር አፍቃሬ ኃጥአን እንደኾነ፣ ድካማቸውን እንደሚረዳ፣ ድኅነታቸውንም አብዝቶ እንደሚሻ ይሰብክ ነበር፡፡

#ትንቢተ_ኢሳይያስ

ትንቢተ ኢሳይያስ በዕብራይስጥ ትርጉሙ ሲታይ ከምዕራፍ ፴፮-፴፱ በስተቀር የግጥም (የቅኔ) መልክ ያለውና በአጻጻፉ እጅግ መሳጭ የኾነ መጽሐፍ ነው፡፡ በብዙ ሊቃውንት ዘንድም “የኢሳይያስ ወንጌል” እየተባለ ይጠራል፡፡ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ደግሞ “ደረቅ ሐዲስ” ይሉታል፡፡ ይኸውም እመቤታችን #ቅድስት_ድንግል_ማርያም በድንግልና ፀንሳ በኅቱም ድንግልና መውለዷን፣ #ጌታችንም በኅቱም ድንግልና ተፀንሶ በኅቱም ድንግልና መወለዱን ከፅንስ ዠምሮ እስከ ዳግም ምፅአቱ ድረስ ምስጢረ ሥጋዌን የሚናገር ስለኾነ ነው፡፡

➛ትንቢተ ኢሳይያስን የሚያነብ ሰው ሐዲስ ኪዳንን የሚያነብ ያኽል ይሰሟል፡፡ ጸሐፊውም (ኢሳይያስም) በዘመነ ሐዲስ የነበረና ከ #ጌታችን_ከመድኃኒታችን_ከኢየሱስ_ክርስቶስ እግር ስር ቁጭ ብሎ የተማረ ደቀ መዝሙር ይመስሏል፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ በድንግልና ተፀንሶ በድንግልና እንደሚወለድ /ኢሳ.፯፡፲፬/፣ አምላክነቱን /ኢሳ.፱፡፮/፣ የነገደ እሴይ ስር መኾኑ /ኢሳ.፲፩፡፩/፣ መንፈስ ቅዱስ እንደሚያርፍበት /ኢሳ.፲፩፡፪/፣ ለአሕዛብ ፍርድን እንደሚያመጣ /ኢሳ.፵፪፡፩/፣ ትሕትናው /ኢሳ.፵፪፡፪/፣ ለኹሉም ተስፋ ድኅነትን እንደሚያመጣ /ኢሳ.፵፪፡፫/፣ ወደ ግብጽ እንደሚሰደድ /ኢሳ.፲፱/፣ መከራውና ስቅለቱ /ኢሳ.፶፫/፣ በትንሣኤው ለኹሉም ተስፋ ትንሣኤን እንደሚሰጥ /ኢሳ.፴፭፡፰-፲/፣ … አምልቶና አስፍቶ ተናግሯል፡፡

➛ጀሮም የተባለ የጥንቲቱ የላቲን ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ አባት ይኽን በተመለከተ፡- “ትንቢተ ኢሳይያስን ሳነብ የ #ጌታችን_የኢየሱስ_ክርስቶስን ሕይወት የሚተርክ ወንጌላዊን አገኛለኹ፤ ከዚኹ ጐን ለጐንም ስለ መፃእያት የሚናገር ነቢይን አገኛለኹ” ማለቱም ይኽን የሚያስረዳ ነው፡፡ ➛አውግሥጢኖስ የተባለው ቅዱስ አባት ወደ ክርስትና ከተመለሰ በኋላ ቅዱስ አምብሮስን አዘውትሮ የሚያነበው መጽሐፍ ምን እንደኾነ ሲጠይቀውም “ኢሳይያስን” ብሎ መመለሱም ትንቢተ ኢሳይያስ ምን ያኽል ግልጽና የተብራራ መጽሐፍ መኾኑን ፍንተው አድርጐ የሚያሳይ ነው፡፡
2024/09/21 07:36:02
Back to Top
HTML Embed Code: