Telegram Web Link
የሀዋሳ ከተማ ስፖርት ክለብ የደጋፊዎች ማህበር የ2015 ፊዚካል እና ፋይናንሻል ሪፖርት ፣ ግምገማ ዛሬ አካሂዷል

የሀዋሳ ከተማ ስፖርት ክለብ የደጋፊዎች ማህበር በሀዋሳ ሴንትራል ሆቴል ዛሬ የፊዚኪል ሪፖርት ፋይናንሻል ሪፖርት ግምገማን አካሂዷል። የክለቡ ም/ፕሬዝዳንት እና የባህል ፣ ቱሪዝም ስፖርት መምሪያ ሀላፊ ወ/ሮ ደርጊቱ ጫሌ ፣ የክለባችን ስራ አስኪያጅ አቶ ሁቴሳ አጋሞ እና የደጋፊ ማህበር ፕሬዝዳንት ባዩ ባልጉዳ እና የማህበሩ አባላት የቴክኒክ ኮሚቴ ተወካዮች እና ከ15 አመት ጀምሮ እስከ ዋናው ድረስ ያሉ አሰልጣኞች በግምገማው ተገኝተዋል።

በማህበሩ ፀሀፊ ሀይሉ አማካኝነት ሪፖርቱ የተሰናዳ ሲሆን ጥልቅ ውይይቶች ከተካሄዱ በኃላም በቀጣይ የደጋፊዎች ጠቅላላ ጉባኤ እንደሚኖር ተጠቁሟል።
ክለባችን ሀዋሳ ከተማ በሴንትራል ሀዋሳ ሆቴል ከነሀሴ 12 ጀምሮ መቀመጫውን አድርጓል። በተከታታይ ቀናት ለቡድኑ ተጫዋቾች የህክምና ምርመራ እና የተለያዩ ስልጠናዎች ከተሰጡ በኋላ በፓላንድ ሀገር የማሻሻያ ስልጠናን ወስዶ በተመለሰው አሰልጣኝ ዘርአይ ሙሉ እየተመራ መደበኛ ልምምዱን ከነገ ሰኞ ጀምሮ ክለቡ ያከናውናል።

ክለባችን በዚህ ክረምት ያስፈረማቸው አዳዲስ ተጫዋቾች 👇

👉እንየው ካሳሁንን ከድሬዳዋ ተከላካይ
👉 አማኑኤል ጎበና ከአዳማ የመሐል ተጫዋች
👉 ፂሆን መርዕድ ከወላይታ ድቻ ግብ ጠባቂ
👉 ሚሊዮን ሰለሞን ከአዳማ ተከላካይ

ውል ያደሱ 👇

👉 መድሀኔ ብርሀኔ
👉 ተባረክ ሔፋሞ
👉 አሊ ሱለይማን
👉 አብዱልባሲጥ ከማል
👉 አቤኔዘር ኦቴ
👉 ፀጋአብ ዮሐንስ
👉 ምንተስኖት እንድሪያስ
👉 አቤኔዘር ዮሀንስ

በቀጣይ ከሀገር ውስጥ እና ከባህር ማዶ ወሳኝ ተጫዋቾችን ክለባችን የሚያስፈርም ይሆናል።
ክለባችን ሀዋሳ በጋና ፕሪሚየር ሊግ ኮከብ ተጫዋች እጩ የሆነውን ተጫዋች አስፈርሟል

በአሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ መሪነት የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን እየሰሩ የሚገኙት ሀዋሳ ከተማዎች እስከ አሁን በስብሰባቸው ውስጥ የሀገር ውስጥ አዳዲስ ተጫዋቾች በማስፈረም እና ነባሮችን በመያዝ ልምምዳቸውን ቀጥለዋል። አሁን ደግሞ የመጀመሪያ የውጪ ዜጋ ፈራሚያቸው በማድረግ በጋና ሊግ የአመቱ ኮከብ ተጫዋች ዝርዝር ውስጥ የተካተተውን ጋናዊውን የተከላካይ አማካይ ስሚካኤል ኦቶውን አስፈረመ።

አብዛኛዎቹ የእግር ኳስ ህይወቱን በሀገሩ ክለቦች ዩኒ ስታር ፣ ኢንተር አላይንስ እና ግሬት ኦሎምፒክስ ከተጫወተ በኋላ በመቀጠል ወደ ፓርቹጋል አምርቶ ለፖርትሞኔንሴ ተጫውቷል። ያለፉትን ሁለት ዓመታት ወደ ሀገሩ ጋና በመመለስ ለሊጎን ሲቲስ ግልጋሎት ሲሰጥ የነበረ ሲሆን በክለቡ ውስጥ ድንቅ ጊዜ ማሳለፍ በመቻሉ የአመቱ ምርጥ ተጫዋቾች ስድስቱ ውስጥ የተካተተ ሲሆን ለቀጣዩ የውድድር ዘመን ደግሞ ወደ ሀገራችን በመምጣት ሀዋሳን ተቀላቅሏል። Soccer Ethiopia
ኢትዮጵያ 1 - 1 ቡሩንዲ

ረድኤት አስረሳኸኝ

የክለባችን ተጫዋች ለሀገሯ ግብ አስቆጥራለች
2025/02/06 07:38:25
Back to Top
HTML Embed Code: