ለክለባችን የልዑካን አባላት አሸኛኘት ተደረገላቸው
በ2015 የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ለሚካፈለው አንጋፋው ክለባችን ሀዋሳ ከተማ እግር ኳስ ክለብ በሴንትራል ሀዋሳ ሆቴል ሽኝት ተደረገለት፡፡ ለውድድሩ ወደ ባህርዳር ለሚያመራው ስብስቡ የክለበቡ የበላይ ጠባቂ እና የከተማው ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ እና ከፍተኛ የመንግስት አካላት ፡ የቦርድ አመራሮች ፡ አሰልጣኞች ፡ ተጫዋቾች እና አጠቃላይ የቡድኑ የልዑካን አባላት በተገኙበት ነው ሽኝቱ ዛሬ ማምሻውን መደረግ የቻለው፡፡
ክለባችን የፊታችን ሰኞ ነሀሴ 16 ወደ ባህርዳር የሚያመራ ይሆናል፡፡

ክለባችን ሀዋሳ ከተማ ወሳኝ ድል አስመዝግቧል
በኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት ጨዋታ አንጋፋው ክለባችን ሀዋሳ ከተማ በአሰልጣኝ ዘርአይ ሙሉ እየተመራ በዛሬው ዕለት ቀን 10 ሰአት በባህርዳር ስታዲየም ኢትዮጵያ ቡናን ገጥሞ፡፡ በአብዱልባሲጥ ከማል እና ተባረክ ሂፋሞ ድንቅ ጎሎች 2ለ1 አሸንፏል፡፡ የክለባችን የቀድሞው ተጫዋች ብሩክ በየነ አንዷን ጎል ለኢትዮጵያ ቡና አስቆጥሯል፡፡
ክለባችን በለገጣፎ ለገዳዲ የመጀመሪያው ሳምንት ላይ ቢሸነፍ የዛሬው ድል ለቀጣይ ጉዟችን ትልቅ የድል ሀብት ይሆንልናል፡፡ በሶስተኛው ሳምንት ጨዋታ አዳማ ከተማን የምንገጥም ይሆናል፡፡
እንኳን ደስ አላችሁ የሀይቆቹ ደጋፊዎች !

የክለባችን የደጋፊዎች ማህበር ፕሬዝዳንት ባዩ ባልጉዳ ትላንት በፕሪሚየር ሊጉ ሀዋሳ ከተማ ኢትዮጵያ ቡናን ሲረታ ያሳየው የደስታ አገላለፅ !