Telegram Web Link
✞✞✞ ልዩ መንፈሳዊ ጉባኤ ✞✞✞
የቅዱስ ቁርባን ትርጉም፣ ሥርዐትና አፈጻጸም እንዲሁም
ቅዱስ ቁርባንን የተመለከቱ ጥያቄዎች ካልዎት
ይዘው ይምጡ በአባቶች ምላሽ ይሰጥባቸዋል ።
መጋቢት 13 – 15 ከ12:00 ሰዓት ጀምሮ ቀጠርዎ ከኛጋር ይሁን ።
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
https://youtu.be/QzYfyN1KOcw
ወዳጄ ሆይ! አንተ በሰውነትህ ላይ ፈትተህ የለቀቅከው ማንን ነው? በርባንን ነው ወይንስ ጌታን ነው? በርባንን ፈትተኸው ከሆነ ዛሬውኑ በንስሓ ተመልሰህ ፈጣሪህን በሰውነትህ ውስጥ አክብረው፡፡ ‹በርባንን የፈታሁት እኮ ወድጄ አይደለም! ሁኔታዎች አስገድደውኝ ነው› ብለህ እንደ ጲላጦስ ለራስህ ይቅርታ ማድረግና እጅህን መታጠብ አይበጅህም፡፡ ይልቅስ አሁኑኑ ጌታህን ፈትተህ በርባንን የተባለ ኃጢአትን ስቀለው! ያን ጊዜ የክርስቶስ መሆንህ ይታወቃል፡፡ ‹‹የክርስቶስ ኢየሱስ የሆኑቱ ሥጋን ከክፉ መሻቱና ምኞቱ ጋር ሰቀሉ›› ተብሎ ተጽፎአልና፡፡ (ገላ. ፭፥፳፬)
https://youtu.be/ysBuJzN9v_I
አይሁድ የጲላጦስን የአቋም መዋዠቅ ሲያዩ ኃይላቸው እየበረታ ሔደ፡፡ ከዚህ በኋላ ወጥቶ በርባን ይፈታ ላሉት ሰዎች ‹‹ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን እንግዲህ ምን ላድርገው?›› አላቸው፡፡ ይህንን ያለው አሁንም በሕዝቡ ላይ ተስፋ ስላልቆረጠ ‹እውነት ይህ ሰው ይመጣል የተባለው መሲሑ ቢሆንስ› ብለው እንዲከብዳቸው ነበር፡፡ እነርሱ ግን ፡- ይሰቀል ይሰቀል አሉ፡፡ ‹‹እርሱም ፡- ምን ነው? ያደረገው ክፋት ምንድር ነው? አለ ፤ እነርሱ ግን ፡- ይሰቀል እያሉ ጩኸት አበዙ›› (ማቴ. ፳፯፥፳፫) ‹‹ይህንስ ብትፈታው የቄሣር ወዳጅ አይደለህም ፤ ራሱን ንጉሥ የሚያደርግ ሁሉ የቄሣር ተቃዋሚ ነው›› እያሉ ጮኹ (ዮሐ. ፲፱፥፲፪)
Forwarded from Addis ዕቃዎች
አምስተኛው የመጻሕፍት ጉባኤ ደረሰ - የፊታችን እሑድ
በአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል በዕለተ ደብረ ዘይት

በዕለቱ ማስክ አድርገን - ከበር ውጪ በተዘጋጀው ነፋሻማ ቦታ ላይ ርቀታችንን ጠብቀን እንድንታደም ሙሉ ዝግጅቱ ተጠናቅቆአል።
https://youtu.be/gBBTAU3luTs
በሦስቱ ቀናት ጉዞ ወቅት አብርሃም ምን ያስብ ይሆን የሚለውን እኛ ከመጠየቅ በቀር እንዲህ ነው ለማለት አንችልም፡፡ ይህ ጻድቅ ሰው የልቡን ሰውሮ በዝምታ ባሳለፋቸው በእነዚያ ቀናት ፣ ልጁን በሕሊናው ውስጥ ሠውቶ በከረመበት ወቅት በልቡ ምን ያስብ እንደነበር ግን ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹እግዚአብሔር ከሙታን እንኳን ሊያስነሣው እንዲቻለው አስቧልና›› ብሎ በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ ነግሮናል፡፡ የእምነት ምሳሌ የሆነው አብርሃም የተስፋውን ቃል የማያጥፈው አምላክ ልጄን እንድሠዋው ቢያደርገኝም እንኳን ልጄን ከሞት አስነሥቶም ቢሆን ቃሉን ይፈጽምልኛል የሚል እምነት በልቡ ውስጥ ነበረ፡፡ (ዕብ. ፲፩፥፲፱)
https://youtu.be/1OhGCaWfws0
ለነገሩ የካህናት አለቃ ኢየሱስ ክርስቶስ በተሰቃየባት በዚያች ዕለት ምን ክህነት አለን ብለው ያጥናሉ? ሊቀ ቀዳስያን በሞተባት ዕለትስ ምን ዓይነት ቅዳሴ ሊቀድሱ ይችላሉ? ስለዚህ እየተወዘወዘ ከጥናው የሚወጣው ጢስ በበጎ መዓዛ ክፉ ሽታን እንደሚያርቅ የሁላችንን የኃጢአት ሽታ ለማራቅ የተንገላታውን ጌታ እያሰቡ ቀሳውስት ከሚያራራ ዜማ ጋር ‹ኦ ዘጥዕመ ሞተ በሥጋ› ‹በሥጋ ሞትን የቀመስከው ሆይ!› እያሉ ማዕጠንቱን ይወዘውዛሉ፡፡
https://youtu.be/KaOIFAgEuSM
‹‹ከሽማግሌዎቹም አንዱ መልሶ ፡- እነዚህ ነጩን ልብስ የለበሱ እነማን ናቸው? ከወዴትስ መጡ? አለኝ፡፡ እኔም ፡- ጌታ ሆይ አንተ ታውቃለህ አልሁት፡፡ አለኝም ፡- እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ ናቸው፡፡ ልብሳቸውንም አጥበው በበጉ ደም አነጹ ፤ ስለዚህ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት አሉ፡፡ ሌሊትና ቀንም በመቅደሱ ያመልኩታል ፤ በዙፋኑም ላይ የተቀመጠው በእነርሱ ላይ ያድርባቸዋል፡፡ ከእንግዲህ ወዲህ አይራቡም ፤ ከእንግዲህም ወዲህ አይጠሙም፡፡ ፀሐይም ትኩሳትም ሁሉ ከቶ አይወርድባቸውም ፤ በዙፋኑ መካከል ያለው በጉ እረኛቸው ይሆናልና ወደ ሕይወት ውኃ ምንጭ ይመራቸዋል ፤ እግዚአብሔርም ዕንባዎችን ሁሉ ከዓይናቸው ያብሳል›› ራእይ ፯፥፲፫
https://youtu.be/Ew1OMFsLLsA
አንድ ላይ ኃጢአት መሥራት ቀላል ነው ፤ አንድ ላይ ንስሓ መግባት ግን ይከብዳል፡፡ በሀገር ደረጃ ንስሓ መግባት ግን እጅግ ያስደንቃል፡፡ ‹ነነዌ የምትገለበጥ ከሆነ ሀገር እንቀይር› አላሉም ፤ ሀገር ከመቀየር ይልቅ ራሳቸውን መቀየር እንደሚሻል ተረድተው ነበር፡፡ ሁሉም እኩል ልቡ ተሰበረ ፤ ሁሉም ማቅ ለበሰ፡፡

የሰባኪው ስብከት ጣዕም የለውም ብለው አላማረሩም ፣ ‹ተስፋ የሚሠጥ ስብከት መቼ ሰማን› አላሉም፡፡ ሰባኪው እያዋዛ አላስተማራቸውም ፣ ምሳሌ አልነገራቸውም ፣ ቅኔ አልተቀኘላቸውም ፣ ቅዱስ ኤፍሬም እንዲህ ይላል ‹‹የተላከላቸው ጨካኝ ሐኪም ነበር ፤ የያዘው መድኃኒትም የሚያቃጥል ነበር ፤ እንደ ሰይፍ የሚቆራርጥ ቃል ተናገራቸው ፤ እነርሱ ግን አቁስሏቸው ተፈወሱ››
https://youtu.be/a7PZc-4-E0s
የክርስቶስን አምላክነትና በሞቱ የተገኘውን ድኅነት ያልተረዱ ሰዎች ግን ስለ ጌታችን ሞት ቢያለቅሱም እንኳን ‹ለእኛ ብሎ ተሰቃየ› ብለው ትርጉሙ ገብቷቸው ሳይሆን በሰብአዊ ስሜት ሆነው ብቻ ነው፡፡ ጌታችን በቀራንዮ መንገድ እየተከተሉት ያለቀሱለትን የኢየሩሳሌም ሴቶች ወደ እነርሱ ዘወር ብሎ ‹እናንተ የኢየሩሳሌም ልጆች ለእኔ አታልቅሱልኝ› ያላቸውም ለዚህ ነበር፡፡ እነርሱ ያለቀሱት ‹ንጹሑ አምላክ ለእኛ ሲል ተሠቃየ› ብለው ሳይሆን የደረሰበትን ግፍ በማየት ‹አዬ! መጨረሻው ይኼ ይሆን?› እያሉ ተስፋ በመቁረጥ ነበር፡፡
https://youtu.be/28IG6mVEi9M
ያዕቆብ ከወንድሙ ጋር ተጣልቶ ከቤርሳቤህ ወደካራን ሲሔድ በእጁ ከጨበጠው በትር በቀር ሌላ ምን የያዘው ነገር ነበረው? የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር እየተከተለ በነገር ሁሉ ይባርካቸውና ያከብራቸው ካልነበር በስተቀር በእውነት በእጃቸው ላይ ምንም አልነበረም። ብዙ ግዜ ባዶነት ለእግዚአብሔር ድንቅ ስራ ምቹ ሁኔታ ነው።
https://youtu.be/beni_nCyGjQ
መስቀል ማሰር ለብቻው እርሱ ሊልቅ የሚለውን የቅድስና ከፍታ አያስገኝም፡፡ በቤተመቅደስ ግቢ ትሕትናን መልበስ እኔ ግን ላንስ ያስፈልጋል ያስባለን መለኮታዊ ፍቅር አያስተረጉምም፡፡ ነጠላ በማሸረጥ የዓለም ክፉ ተራራ አይደረመስም፡፡ ንግሥ እየጠበቁ ሻማ ማብራት የነፍስ ጨለማን አያበራም፡፡ ትናንትም፣ አሁንም፣ ነገም የማይወሐዱት ተዋሕዶ ከሕዝብ ቆጠራ የዘለለ ትሩፋት የለውም፡፡
2025/02/23 22:20:27
Back to Top
HTML Embed Code: