https://youtu.be/daFGPxR5PAk
ጌታችን የይሁዳን ስርቆት ያላጋለጠውና በሹመቱ ያቆየው በተጣለበት አመኔታና በጌታው ትእግሥት ልቡ ተነክቶ እንዲመለስ መንገድ ሊሰጠው ነበር፡፡ ገንዘብ ያዥነቱ ጌታውን ለመሸጥ የሚያስገድድ የገንዘብ እጥረት የማያጋጥመው ሰው ስለሚያደርገው ይሁዳን ምንም ምክንያት ሊያቀርብ የማይችል ያደርገዋል፡፡ የይሁዳ ችግር የገንዘብ እጥረት ሳይሆን የገንዘብ ፍቅር ነበር፡፡ ‹‹ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነውና›› ይሁዳም ‹‹ይህን ሲመኝ ከሃይማኖት ተሳስቶ በብዙ ሥቃይ ራሱን ወጋ›› (፩ጢሞ. ፮፥፲)

YouTube
ሕማማት ( ይሁዳ የመረጠው ጌታ ) ክፍል ሁለት....ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ እንደጻፈው....ቢንያም ብርሐኑ እንዳነበበው
ጌታችን የይሁዳን ስርቆት ያላጋለጠውና በሹመቱ ያቆየው በተጣለበት አመኔታና በጌታው ትእግሥት ልቡ ተነክቶ እንዲመለስ መንገድ ሊሰጠው ነበር፡፡ ገንዘብ ያዥነቱ ጌታውን ለመሸጥ የሚያስገድድ የገንዘብ እጥረት የማያጋጥመው ሰው ስለሚያደርገው ይሁዳን ምንም ምክንያት ሊያቀርብ የማይችል ያደርገዋል፡፡ የይሁዳ ችግር የገንዘብ እጥረት ሳይሆን የገንዘብ ፍቅር ነበር፡፡ ‹‹ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነውና››…
https://youtu.be/VwFbqx2dncM
ከሁሉም ልብ የሚሰብረው ሐሙስ ምሽት የሆነው ነገር ነው፡፡ ጌታችን ‹‹ከእራት ተነሣ ልብሱንም አኖረ፥ ማበሻም ጨርቅ ወስዶ ታጠቀ ፤ በኋላም በመታጠቢያው ውኃ ጨመረ፥ የደቀ መዛሙርቱንም እግር ሊያጥብና በታጠቀበትም ማበሻ ጨርቅ ሊያብስ ጀመረ›› የእግር ሹራብ በማይደረግበትና ክፍት ጫማ በሚደረግበት በዚያ ዘመን ቀኑን ሙሉ ሲጓዙ የዋሉበትን የሐዋርያቱን በአቧራ ያደፉ እግሮች ሊያጥብ ተነሣ፡፡ (ዮሐ.፲፫፥፬) በእስራኤል ባህል እግር ማጠብ የሎሌዎች ሥራ ቢሆንም የሰማይና የምድር ንጉሥ ግን በትሕትና እንደ ሎሌ ሆነ፡፡ (፩ሳሙ. ፳፭፥፵፩)

ሕማማት ( የይሁዳ እግሮች ) ክፍል ሦስት....ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ እንደጻፈው....ቢንያም ብርሐኑ እንዳነበበው
ከሁሉም ልብ የሚሰብረው ሐሙስ ምሽት የሆነው ነገር ነው፡፡ ጌታችን ‹‹ከእራት ተነሣ ልብሱንም አኖረ፥ ማበሻም ጨርቅ ወስዶ ታጠቀ ፤ በኋላም በመታጠቢያው ውኃ ጨመረ፥ የደቀ መዛሙርቱንም እግር ሊያጥብና በታጠቀበትም ማበሻ ጨርቅ ሊያብስ ጀመረ›› የእግር ሹራብ በማይደረግበትና ክፍት ጫማ በሚደረግበት በዚያ ዘመን ቀኑን ሙሉ ሲጓዙ የዋሉበትን የሐዋርያቱን በአቧራ ያደፉ እግሮች ሊያጥብ ተነሣ፡፡ (ዮሐ.፲፫፥፬)…
https://youtu.be/lX2CpJVhmvA
ጌታችን የሚያዝበትን ዕቅድ የነደፈውና ለወታደሮቹ የቅድሚያ ትእዛዝና የምሥጢር ‹ኮድ› የሠጣቸውም ራሱ ይሁዳ ነበር፡፡ ‹‹የምስመው እርሱ ነው ፣ ያዙት ተጠንቅቃችሁም ውሰዱት› የሚል ዝርዝር መመሪያም አስቀድሞ አስተላልፎ ነበር፡፡ (ማር. ፲፬፥፵፬) ስለዚህ ቃል በገባው መሠረት ወደ ጌታችን ቀርቦም ‹‹መምህር ሆይ ፣ መምህር ሆይ ሰላም ለአንተ ይሁን ብሎ ሳመው›› (ማር. ፲፬፥፵፬ ፣ማቴ.፳፮፥፵፰}

ሕማማት ( የጦር መሪው ይሁዳ ) ክፍል አራት....ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ እንደጻፈው....ቢንያም ብርሐኑ እንዳነበበው
ጌታችን የሚያዝበትን ዕቅድ የነደፈውና ለወታደሮቹ የቅድሚያ ትእዛዝና የምሥጢር ‹ኮድ› የሠጣቸውም ራሱ ይሁዳ ነበር፡፡ ‹‹የምስመው እርሱ ነው ፣ ያዙት ተጠንቅቃችሁም ውሰዱት› የሚል ዝርዝር መመሪያም አስቀድሞ አስተላልፎ ነበር፡፡ (ማር. ፲፬፥፵፬) ስለዚህ ቃል በገባው መሠረት ወደ ጌታችን ቀርቦም ‹‹መምህር ሆይ ፣ መምህር ሆይ ሰላም ለአንተ ይሁን ብሎ ሳመው›› (ማር. ፲፬፥፵፬ ፣ማቴ.፳፮፥፵፰}
https://youtu.be/SlBBCfBAsiU
ሊሸጠው እንደመጣ እያወቀ ይሁዳ በሐሰት ፍቅር ሲያቅፈው ጌታችን ልቡን ምንኛ አሳዝኖትና አምሞት ይሆን? እርሱ ግን ይህንን ሕመም ታገሦ ተቀበለ፡፡ ይሁዳም እንደ ጠላቱ እየሸጠው እንደ ወዳጁ አቅፎ ሳመው፡፡ ጌታችን ‹‹በሩ እኔ ነኝ ፤ በእኔ የሚገባ ይድናል›› ብሎ ሲናገር ቢሰማም ይሁዳ ግን በሩን ጌታን ስሞ ተሳልሞ ወደ ውስጥ በመግባትና በመዳን ፈንታ ወደ ሲኦል ገሠገሠ፡፡ ከውጪ ተሳልሞ መመለስ ይኼው ነው ትርፉ! (ዮሐ. ፲፥፱)

ሕማማት ( ከማቁሰል የከፋ ቁስል ) ክፍል አምስት....ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ እንደጻፈው....ቢንያም ብርሐኑ እንዳነበበው
ሊሸጠው እንደመጣ እያወቀ ይሁዳ በሐሰት ፍቅር ሲያቅፈው ጌታችን ልቡን ምንኛ አሳዝኖትና አምሞት ይሆን? እርሱ ግን ይህንን ሕመም ታገሦ ተቀበለ፡፡ ይሁዳም እንደ ጠላቱ እየሸጠው እንደ ወዳጁ አቅፎ ሳመው፡፡ ጌታችን ‹‹በሩ እኔ ነኝ ፤ በእኔ የሚገባ ይድናል›› ብሎ ሲናገር ቢሰማም ይሁዳ ግን በሩን ጌታን ስሞ ተሳልሞ ወደ ውስጥ በመግባትና በመዳን ፈንታ ወደ ሲኦል ገሠገሠ፡፡ ከውጪ ተሳልሞ መመለስ ይኼው…
Forwarded from የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች (ነጠላ ሰረዝ)
YouTube
"እመቤታችን ማማለድ አይደለም አፍርሳ ልትሰራን ትችላለች" በዲ/ን ሔኖክ ኃይሌ | በኛ ቤት | ክፍል 2
የመምህር ዲ/ን ሔኖክ ኃይሌ ዩቱብ ቻናል ነው ግቡና ሰብስክራይብ አድርጉት : https://youtube.com/channel/UCOaVsWC05aUjeqIEW3fWj7g
follow me on social media;
facebook: https://www.facebook.com/lijbinu
Instagram: https://www.instagram.com/?hl=en

https://youtu.be/S2_AYPLtFI8
ከዚህ በኋላ ይሁዳ በራሱ ላይ ፈረደና ታንቆ ሊሞት ወሰነ፡፡ የይሁዳ ትልቁ ኃጢአት ጌታን አሳልፎ መሥጠቱ ሳይሆን ጌታ ይቅር አይለኝም ማለቱ ነው፡፡ ‹‹የወደቀስ አይነሣምን? የሳተስ አይመለስምን?›› ይላል መጽሐፉ፡፡ (ኢሳ. ፰፥፬) እግዚአብሔር ሊፈርድ ሲመጣ ለምን ኃጢአት ሠራህ? ብሎ አይጠይቅም ፤ የፈጣሪ ጥያቄ ለምን ንስሓ አልገባህም? ነው፡፡ ይሁዳ ግን ይቅር በለኝ በማለት ፈንታ በራሱ ላይ ፈረደ፡፡ ፈራጅ እግዚአብሔር ነውና እንደ ጲላጦስ ለራስ ይቅርታ ማድረግም ሆነ እንደ ይሁዳ በራስ መፍረድ የሰው ልጅ ሥልጣን አይደለም፡፡

ሕማማት ( የይሁዳ ትልቁ ኀጢአት ) ክፍል ስድስት....ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ እንደጻፈው....ቢንያም ብርሐኑ እንዳነበበው
ከዚህ በኋላ ይሁዳ በራሱ ላይ ፈረደና ታንቆ ሊሞት ወሰነ፡፡ የይሁዳ ትልቁ ኃጢአት ጌታን አሳልፎ መሥጠቱ ሳይሆን ጌታ ይቅር አይለኝም ማለቱ ነው፡፡ ‹‹የወደቀስ አይነሣምን? የሳተስ አይመለስምን?›› ይላል መጽሐፉ፡፡ (ኢሳ. ፰፥፬) እግዚአብሔር ሊፈርድ ሲመጣ ለምን ኃጢአት ሠራህ? ብሎ አይጠይቅም ፤ የፈጣሪ ጥያቄ ለምን ንስሓ አልገባህም? ነው፡፡ ይሁዳ ግን ይቅር በለኝ በማለት ፈንታ በራሱ ላይ ፈረደ፡፡…
Forwarded from የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች (ነጠላ ሰረዝ)
ይህ ኀብረት የንባብን ልምድ ለማዳበር እና ሃሳብ ለማጋራት በተመረጡ የ ሃይማኖት፣ የ ታሪክ እና የልብ-ወለድ መጽሐፍት ላይ ግምገማ የሚከውን ሐገር አቀፍ ኅብረት ነው::
መልዕክት ለመላክ ፣ ለአስተያየት እና ለመመዝብ @Endalk9
https://www.tg-me.com/TheEthiopianJandereba

https://youtu.be/Cgfj6bADZTE
ምንም እንኳን ትንቢቶች ቢነገሩም ይሁዳ እስከተመለሰ ድረስ እግዚአብሔር የኃጥኡን መመለስ ይወድዳልና ስለማይወድቅ ፍቅሩ ሲል ትንቢቶቹን ይሽራቸው ነበር፡፡ ‹‹ፍቅር ለዘላለም አይወድቅም ፤ ትንቢትም ቢሆን ይሻራል›› ተብሎ ተጽፎአልና፡፡ (፩ቆሮ. ፲፫፥፰) ለነነዌ ሰዎች ስለ ፍቅሩ ሲል ዮናስን አስከፍቶ የተነገረባቸውን የጥፋት ትንቢት የሻረ አምላክ ይሁዳም ቢመለስ ኖሮ የተነገረውን ትንቢት እስካልተፈጸመ ድረስ ነቢያቱ እንደ ዮናስ ቢከፉም እንኳን ይሽረው ነበር፡፡ (ዮና. ፫፥፲)

ሕማማት ( የይሁዳ ዕጣ ፈንታ ) ክፍል ሰባት....ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ እንደጻፈው....ቢንያም ብርሐኑ እንዳነበበው
ምንም እንኳን ትንቢቶች ቢነገሩም ይሁዳ እስከተመለሰ ድረስ እግዚአብሔር የኃጥኡን መመለስ ይወድዳልና ስለማይወድቅ ፍቅሩ ሲል ትንቢቶቹን ይሽራቸው ነበር፡፡ ‹‹ፍቅር ለዘላለም አይወድቅም ፤ ትንቢትም ቢሆን ይሻራል›› ተብሎ ተጽፎአልና፡፡ (፩ቆሮ. ፲፫፥፰) ለነነዌ ሰዎች ስለ ፍቅሩ ሲል ዮናስን አስከፍቶ የተነገረባቸውን የጥፋት ትንቢት የሻረ አምላክ ይሁዳም ቢመለስ ኖሮ የተነገረውን ትንቢት እስካልተፈጸመ ድረስ…
https://youtu.be/D74UzOIEs0I
ጌታችን ከመያዙ በፊት ለወታደሮቹ አንድ ነገር አሳሰባቸው፡፡ የሚይዙት ኃይል ስለሌለው ሳይሆን ፈቅዶ መሆኑን ካስረዳ በኋላ ልትይዙኝ ከሆነ ‹‹እንግዲህ እኔን ትፈልጉ እንደሆናችሁ እነዚህ ይሒዱ ተዉአቸው›› አለ፡፡ ወደ መከራ እየሔደ ስለ ተማሪዎቹ የሚያስብ መምህር ፣ ወደ መታረድ እየሔደ ስለ በጎቹ የሚጨነቅ መልካሙ እረኛ ክርስቶስ እኔን ያዙኝና ‹‹እነዚህ ይሒዱ ተዉአቸው›› ብሎ ‹‹ነፍሱን ስለበጎቹ አሳልፎ ሰጠ›› (ዮሐ. ፲፰፥፰) የደቀ መዛሙርቱን አቅማቸው ያውቃልና ‹ከሚቻላቸው በላይ› ተፈትነው እንዳይጠፉ ፣ ባልጸና እምነታቸው በመከራ እንዳይወድቁ ያስባልና በአንዲት ገረድ ፊት የሚክዱት ሐዋርያት በወታደር ፊት እንዲጋፈጡ አላሰናበታቸውም፡፡ ‹‹ይሒዱ ተዉአቸው›› አለ፡፡

ሕማማት ( እነዚህ ይሒዱ ተዉአቸው ) ክፍል ስምንት....ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ እንደጻፈው....ቢንያም ብርሐኑ እንዳነበበው
ጌታችን ከመያዙ በፊት ለወታደሮቹ አንድ ነገር አሳሰባቸው፡፡ የሚይዙት ኃይል ስለሌለው ሳይሆን ፈቅዶ መሆኑን ካስረዳ በኋላ ልትይዙኝ ከሆነ ‹‹እንግዲህ እኔን ትፈልጉ እንደሆናችሁ እነዚህ ይሒዱ ተዉአቸው›› አለ፡፡ ወደ መከራ እየሔደ ስለ ተማሪዎቹ የሚያስብ መምህር ፣ ወደ መታረድ እየሔደ ስለ በጎቹ የሚጨነቅ መልካሙ እረኛ ክርስቶስ እኔን ያዙኝና ‹‹እነዚህ ይሒዱ ተዉአቸው›› ብሎ ‹‹ነፍሱን ስለበጎቹ አሳልፎ…
https://youtu.be/uiNBVJ1KXnQ
ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታችን እንዳይሞት የነበረው ቁርጠኝነት ጌታችን እስከተያዘባት ሐሙስ ምሽት ድረስ የቀጠለ ነበር፡፡ ለጌታ ካለው ጽኑ ፍቅር የተነሣም ጌታችንን ሊይዙ ከመጡት ወታደሮች ጋር ለመዋጋት ሰይፍ ይዞም ነበር፡፡ እርግጥ ነው ጌታችን ‹‹ሰይፍን ያዙ›› ብሎ ነግሮአቸው ነበር፡፡ ሁለት ሰይፍ እንዳላቸው ሲነግሩትም ‹‹ይበቃል›› ብሏቸው ነበር፡፡ ጌታችን ይበቃል ያለው ግን ሰይፉን ሳይሆን ንግግራቸውን ነበር፡፡ ለውጊያ ሰይፍ ሁለት ሊበቃ አይችልም ፤ ጌታም ጎኑን በጦር ሊወጋ እንጂ ሰዎችን ሊያዋጋ ሰው የሆነ አምላክ አይደለም፡፡ ሊቃውንት እንዳብራሩት ያዙ የተባሉት ሰይፍ ደግሞ ‹‹ነፍስና መንፈስን ጅማትና ቅልጥምን እስኪለይ ድረስ የሚወጋውን የመንፈስ ሰይፍ›› ሲሆን እርሱም ሦስት ዓመት ያስተማራቸውን የመከራ ቀን ስንቅ የሚሆን የእግዚአብሔር ቃልን ነበር (ኤፌ. ፮፥፲፯ ዕብ. ፬፥፲፪)

ሕማማት ( የዮና ልጅ ስምዖን እና የማልኮስ ጆሮ ) ክፍል ዘጠኝ....ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ እንደጻፈው....ቢንያም ብርሐኑ እንዳነበበው
ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታችን እንዳይሞት የነበረው ቁርጠኝነት ጌታችን እስከተያዘባት ሐሙስ ምሽት ድረስ የቀጠለ ነበር፡፡ ለጌታ ካለው ጽኑ ፍቅር የተነሣም ጌታችንን ሊይዙ ከመጡት ወታደሮች ጋር ለመዋጋት ሰይፍ ይዞም ነበር፡፡ እርግጥ ነው ጌታችን ‹‹ሰይፍን ያዙ›› ብሎ ነግሮአቸው ነበር፡፡ ሁለት ሰይፍ እንዳላቸው ሲነግሩትም ‹‹ይበቃል›› ብሏቸው ነበር፡፡ ጌታችን ይበቃል ያለው ግን ሰይፉን ሳይሆን ንግግራቸውን ነበር፡፡…
Forwarded from ፍቁረ እግዚእ ሚዲያ Fikure Egzi Media – FEM (ፍቁረ እግዚእ ሰንበት ት/ቤት)
ታላቅ የበረከት በዓለ ንግሥ ጥሪ
ጥር 4 ቀን 2013 ዓ.ም
በደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ እና መካነ ጎልጎታ ቅድስት ድንግል ማርያም ቤ/ክ
በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ በድምቀት የሚከበረውን የሐዋርያው ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ በዓለ ንግስ ተገኝተው የበረከት ተሳታፊ ይሁኑ።

https://youtu.be/1RkmbxZJ9hg
የሚመጸውት ሰው በፍጹም ቸርነት መመጽወት አለበት እንጂ በሚለምነው ሰው ላይ ግምገማ ማካሔድ የለበትም፡፡ ወዳጄ የሚለምንህ ሰው በንዝነዛ ፋታ አሳጥቶህ ይሆናል ፣ እንግዲህ እሱንም ረሃብ እንዲህ ፋታ አሳጥቶት ነው፡፡ አነጋገሩ ለዛ የለው ይሆናል ፣ ለዛ ያሳጣው ግን ድህነት ነው፡፡ የሚነግርህ ታሪክ አሳማኝ ላይሆን ይችላል ፣ ምንም ቢልህ መቸገሩ ግን እውነት ነው፡፡ ይኼን ሁሉ ርቀት ሔዶ አንተን ለማሳመን የሚጣጣረው ፣ አጠያየቁን የሚለዋውጠው ስለጨከንክበት ነው እንጂ መቸገሩ እውነት ነው፡፡ ፈጣሪ ይህንን ደሃ ከፊትህ ያቆመው እንድትረዳው ነው እንጂ የልመና ተሰጥኦ ውድድር ዳኛ እንድትሆንለት አይደለም፡፡

ባለጸጋ ነዳያን....ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ እንደጻፈው....ቢንያም ብርሐኑ እንዳነበበው
የሚመጸውት ሰው በፍጹም ቸርነት መመጽወት አለበት እንጂ በሚለምነው ሰው ላይ ግምገማ ማካሔድ የለበትም፡፡ ወዳጄ የሚለምንህ ሰው በንዝነዛ ፋታ አሳጥቶህ ይሆናል ፣ እንግዲህ እሱንም ረሃብ እንዲህ ፋታ አሳጥቶት ነው፡፡ አነጋገሩ ለዛ የለው ይሆናል ፣ ለዛ ያሳጣው ግን ድህነት ነው፡፡ የሚነግርህ ታሪክ አሳማኝ ላይሆን ይችላል ፣ ምንም ቢልህ መቸገሩ ግን እውነት ነው፡፡ ይኼን ሁሉ ርቀት ሔዶ አንተን ለማሳመን…
Forwarded from ፍቁረ እግዚእ ሚዲያ Fikure Egzi Media – FEM (ፍቁረ እግዚእ ሰንበት ት/ቤት)
✞✞✞ጉባኤ ፍቁረ እግዚእ ✞✞✞
ሳምንታዊ የሰንበት ት/ቤታችን ጉባኤ አርብ ምሽቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ በሰንበት ት/ቤቱ አዳራሽ ይካሔዳል።
በእለቱ በመገኘት የመርሐ ግብሩ ተሳታፊ ይሁኑ!!!
🍃🍂🍃🍂🍃🍂🍃🍂🍃🍂🍃🍂🍃🍂🍃🍂

https://youtu.be/QIPhpizuPwA
ጌታችንን በመከተል የነገሩን ፍጻሜ ያዩ ዘንድ እስከ ሊቀ ካህናቱ ግቢ የዘለቁት ደግሞ ቅዱስ ዮሐንስና ቅዱስ ጴጥሮስ ነበሩ፡፡ የጌታ ፍቅር ጸንቶባቸው እንጂ በዚያች አስጨናቂ ሌሊት እስከ ሊቀ ካህናቱ ግቢ ድረስ ዘልቀው መሔዳቸው ትልቅ አደጋ ላይ የሚጥላቸው ውሳኔ ነበር፡፡ በጎች ሆነው ወደ ተኩላዎች ግቢ ዘልቀው መግባታቸው ብቻ ‹ፍቅር ፍጹም ፍርሃትን አውጥቶ እንደሚጥል› ያሳያል፡፡ ከሸሸ ተዋግቶ የቆሰለ ይሻላልና የጴጥሮስን በፈተና መውደቅ ብቻ ከማየት እንደ ልማዱ ‹ጌታ ሆይ ወደ ማን እንሔዳለን?› ብሎ እንደ ጓደኞቹ ሳይሸሽ ጌታውን በፍቅር መከተሉን ልናመሰግን ይገባናል፡፡ ‹ጴጥሮስ በፍቅሩ ምክንያት ከፍርሃታቸው የተነሣ ከሸሹት ጓደኞቹ ጋር አብሮ አልሸሸም› ‹‹ወበእንተ አፍቅሮቱ ጴጥሮስ ኢጐየ ምስለ አብያጺሁ እለ ጐዩ እምፍርሃቶሙ›› እንዲል፡፡[

ሕማማት ( በፈተና ግቢ ውስጥ ) ክፍል አስር....ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ እንደጻፈው....ቢንያም ብርሐኑ እንዳነበበው
ጌታችንን በመከተል የነገሩን ፍጻሜ ያዩ ዘንድ እስከ ሊቀ ካህናቱ ግቢ የዘለቁት ደግሞ ቅዱስ ዮሐንስና ቅዱስ ጴጥሮስ ነበሩ፡፡ የጌታ ፍቅር ጸንቶባቸው እንጂ በዚያች አስጨናቂ ሌሊት እስከ ሊቀ ካህናቱ ግቢ ድረስ ዘልቀው መሔዳቸው ትልቅ አደጋ ላይ የሚጥላቸው ውሳኔ ነበር፡፡ በጎች ሆነው ወደ ተኩላዎች ግቢ ዘልቀው መግባታቸው ብቻ ‹ፍቅር ፍጹም ፍርሃትን አውጥቶ እንደሚጥል› ያሳያል፡፡ ከሸሸ ተዋግቶ የቆሰለ…
https://youtu.be/YOKkBJLJi9w
በዚህ ብዙ የማያስቀምጥ የሥልጣን ቦታ ላይ ሐናም ሆነ ቀያፋ ለብዙ ዓመታት መቀመጣቸው የሮማውያን ገዢዎችን ገንዘብ ወዳድነት ሊቋቋሙ የሚችሉ ባለሀብቶች መሆናቸውንም የሚያሳይ ነው፡፡ በዚያ ላይ በሊቀ ካህናትነታቸው ዘመን በእስራኤል ሕዝብ ላይ በሮማውያን እጅ አስከፊ የመብት ጥሰት ቢደርስም መንበረ ሥልጣናቸው እስካልተነካባቸው ድረስ ከቅኝ ገዢዎቻቸው ጋር ተስማምተው የሚኖሩ መስሎ አዳሪዎች ነበሩ፡፡ እንደ ሊቀ ካህናትነታቸውም ለቤተ መቅደሱ ክብር የሚጨነቁና ፈሪሐ እግዚአብሔር ያላቸው አልነበሩም፡፡ የሚያሳዝነው ድፍረት ከቤተ መቅደስ ሊወጣ የማይገባው የሊቀ ካህናቱ ልብሰ ተክህኖ እንኳን በሮማውያን ገዢዎች ቤት (Castle Antonia) ይቀመጥ የነበረ ሲሆን ሊቀ ካህናቱ በክብረ በዓል ወቅት የሚለብሰው ገዢው ሲፈቅድለት ነበር፡፡

ሕማማት ( ሐና እና ቀያፋ ) ክፍል አስራ አንድ....ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ እንደጻፈው....ቢንያም ብርሐኑ እንዳነበበው
በዚህ ብዙ የማያስቀምጥ የሥልጣን ቦታ ላይ ሐናም ሆነ ቀያፋ ለብዙ ዓመታት መቀመጣቸው የሮማውያን ገዢዎችን ገንዘብ ወዳድነት ሊቋቋሙ የሚችሉ ባለሀብቶች መሆናቸውንም የሚያሳይ ነው፡፡ በዚያ ላይ በሊቀ ካህናትነታቸው ዘመን በእስራኤል ሕዝብ ላይ በሮማውያን እጅ አስከፊ የመብት ጥሰት ቢደርስም መንበረ ሥልጣናቸው እስካልተነካባቸው ድረስ ከቅኝ ገዢዎቻቸው ጋር ተስማምተው የሚኖሩ መስሎ አዳሪዎች ነበሩ፡፡ እንደ…
https://youtu.be/egjHnenN15g
ከእኛ ከኢትዮጵያውያን ክብር ጓድሏል መተማመን ጠፍቷል ወንድም በወንድሙ ላይ እተነሣ ፍቅር በመካከላችን ቅዝቅዟል ፍርድ ተጓድሏል ደሀ ተበድሏል በገዛ ሀገራችን ሳይቀር እንደ መጻተኛ የሰሜኑ፣ በደቡብ፣ የምስራቁ ከምዕራብ ተዘዋውሮ እንዳይሰራ ጎጆ ቀልሶ ኑሮ መሥርቶ ወልዶና ከብዶ እንዳይኖር በዘረኝነት አጥር ተከልሎ በገዛ ሀገሩ ስደተኛ በባዕድም ሀገር በአሕዛብም ምድር ሳይቀር ከርታታና ተስፋ ቢስ ሆነናልና፡፡

አቤቱ የሆነብንን አስብ