Telegram Web Link
https://youtu.be/eTzQ6285An8
አበው ሲናገሩ፡- “ሰው ኾኖ የማይበድል እንጨት ኾኖ የማይጤስ” እንዲሉ እንደየኑሮአችን ደረጃ፣ እንደየሥራችን ዓይነት ይለያይ እንደኾነ እንጂ ክርስትና ሕይወታችን ስንመላለስ አንድ ከሚያደርጉን ነገሮች ውስጥ ኃጢአት የሚስማማን መኾኑ ነው፡፡ ጥያቄአችንም ጠያቄአችን እንዳነሡት “ምን እናድርግ?” ነው፡፡ በርግጥም “ምን እናድርግ?”
https://youtu.be/raZoe3fR7-I
አንዳንድ ወገኖች በበትሩ ላይ የሚታዩት አራዊት ዘንዶ ናቸው በማለት ነገርየውን #ከ666 ጋር ለማያያዝ ሲሞክሩ ይታያሉ ። ነገር ግን በፎቶው ላይ እንደሚታየው ዘንዶ ሳይሆን የእባብ ምስል ነው ። እባቡም ደግሞ እንደምትመለከቱት ከመስቀሉ ስር ነው የሚታየው ። ምክንያቱም መስቀል የሁሉም የበላይና እባብ የተሰኘው ዲያብሎስም አናት አናቱን የተቀጠቀጠበት ነውና ።
https://youtu.be/1l6kffKE5Io
እስራኤል ለምን መሪያቸውን ትኩር ብለው መመልከት ተሳናቸው? ካህኑ አሮን እንዴት ወንድሙን መመልከት አስቸገረው? የሕዝቡ አለቆች እንደወትሮው ከሙሴ ላይ ማተኮር ለምን ተቸገሩ? ያለ ወትሮው የሙሴ ፊት ለምን አንጸባረቀ? ብለን ስንጠይቅ ሙሴ ያለማቋረጥ በደመና መካከል ከእግዚአብሔር ጋር ስለቆመና ቃል በቃል ለአርባ ቀንና ሌሊት ከአምላኩ ጋር ስለተነጋገረ ነበር፡፡ ስለተቀበለው የኦሪት ሕግ ክብር ሲባል የሙሴ ፊት በክብር አንጸባረቀ፡፡ የእግዚአብሔር ክብር በዙሪያው ስለነበር ፊቱ አንጸባረቀ
https://youtu.be/JitVvYmrJts
ልጅ ጭንጋፍ ሆኖ ሲወለድ በሥቃይ ነው:: ጤና ያጣል ይታመማል:: እናቲቱም ትታወካለች በድብታ በጭንቀት ትቸገራለች:: ባለሙያዎቹ እንደሚሉት እናት ያለ ጊዜው ከተወለደ ልጅዋ ጋር እናታዊ ትስስር ለመፍጠርና የእናትነት ፍቅርዋን ለመሥጠት ባልጠበቀችው ጊዜ የመጣ በመሆኑ ምክንያት ለጥቂት ጊዜ ትቸገራለች:: በአጭሩ ጭንጋፍ ሆኖ ሲወለድ እሱም ይሰቃያል እናቱንም ያስጨንቃል::
https://youtu.be/L_qht9du-VA
ኢያቄም:-"አቤቱ ጌታዬ ያባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለው አትጣለኝ፤ አትናቀኝ፤ ጸሎቴን ስማኝ ፈቃዴን ፈጽምልኝ፤ ለዐይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የሚሆን የተባረከ ወንድ ልጅ ስጠኝ" ብሎ ሲለምን ዋለ፡፡

#ሐናም በበኩሏ "አቤቱ ጌታዬ የአባቶቼ የእስራኤል አምላክ ሆይ እኔ ባርያህ እለምንሃለሁ፤ ስማኝ ለዐይኔ ማረፊያ ለልቤም ተስፋ የምትሆነኝ የተባረከች ሴት ልጅ የማህፀኔን ፍሬ ስጠኝ" ብላ ስትለምን ዋለች፡፡
https://youtu.be/Fd8Wclr9ijk
ዛሬም እጅዋን ወደ ፈጣሪ ትዘረጋለች የተባለላት ኢትዮጵያ ዛሬም ‘አሁንስ ተስፋዬ ማን ነው? እግዚአብሔር አይደለምን?’ ትላለች፡፡ እርግጥ ነው በዘር ተከፋፍለው እርስ በእርስ በዘር ማጥፋት ተጨራረሱ ከመባል ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት በወረርሽኝ አለቁ ቢባል ለመጪው ትውልድም ለታሪክም የተሻለ ነው፡፡ የኢራንን ምክትል የጤና ሚኒስትር ሥልጣናቸውን ሳይፈራ የያዘ ይህ ባለ ቅኔ ወረርሽኝ ለሕዝብ የማይገደውን ፣ ጥላቻ የሚዘራውን ፣ የሞት ነጋሪት የሚጎስመውን ፣ ቂም የሚሰብከውን ሁሉ ስለማያስተርፍ ምናልባት ምድሪቱን እንዳናጎሳቁል የምንነቀልበትም ይሆን ይሆን?
https://youtu.be/ndwShLSakWc
የኢትዮጵያ ክብር የሚገለጥበት፣ ገናንነቷ የሚመለስበት፣ የተሻረው የቅብዐ መንግሥቷ ክብር ተመልሶ በቅብዐ መንግሥት የከበረ በሥላሴ ኃይል የበረታ ንጉሥ የሚመራበት፣ በዮጵ ወርቋ የምታጌጥበት፣ የእምነቷ ታላቅነት በዓለም አደባባይ የሚገለጥበት ጊዜ
https://youtu.be/D1v4QPyanYE
የክርስቶስን ሰውነት በመቀበሉ ሞት ታላቅ ስኅተት ሠራ፡፡ ይህ ሰውነት በእርሱ የገዥነት ሥልጣን ሥር ያለ ተራ ሰውነት ፣ ኃጢአተኛ የሆነና የሚሞት ሰውነት መስሎት ነበር፡፡ ከሰውነታቸው ጋር የማይስማማ ምግብን የበሉ ሰዎች ሲያስመልሳቸው የሚያወጡት አልስማማ ያላቸውን ምግብ ብቻ ሳይሆን የበሉትን ነገር ሁሉ ነው፡፡ በሞትም ላይ የሆነው ይኼው ነው፡፡ ሞት ፍጹም ንጹሕና የማይሞት የሆነውን የክርስቶስን ሥጋ ዋጠ ፤ የማይሞተው ሕያዉ ክርስቶስ ለአልጠግብ ባዩ ሞትና ሲኦል የሚመር እና የማይስማማ ምግብ ሆነበት፡፡
https://youtu.be/asqL17EVmSU
አባትነት የምኞት ውጤት አይደለም ። ባሕርያዊ ትስስር ነው ። አባትነትም ብዙ ነው ። በሥጋ ፣ በእውቀት ፣ በሃይማኖት ፣ በማሳደግ ሰው አባት ይሆናል። አባት ለመሆን የሚያስፈልገው መውለድ ነው ። ልጅ ለመሆንም መወለድ ግድ ነው ። አሊያ ሽል ነው ። የእኛን አባት ስናይ የኑሮ ጥቁረቱ እንድንርቀው ያደርገን ይሆናል ። የእኛ ንጣት ግን ያለው በዚያ ጥቁረት ውስጥ ነው ።
https://youtu.be/Il0MIdNOQhw
አቤቱ ጌታዬ ሆይ የማልጠቅምና የማልረባ ሆኜ ሳለሁ እንደሚረባና እንደሚጠቅም አድርገህ ስለቆጠርከኝ፣ ወደ አንተ መምጣቴን ስለፈለግኸው፣ በፊትህ መሆኔን ስለምትወድ፣ መመለሴንም ስለምትናፍቅ ከዚህ ፍቅር ፈቀቅ እል ዘንድ እንዴት ይቻለኛል?
https://youtu.be/pHd6Ps9sDnk
እግዚአብሔር አሠራሩ እንዲህ ነው ‹‹እርሱም አይዋሽም ቢዘገይም በእርግጥ ይመጣልና ታገሠው እርሱ አይዘገይም።›› ተብሎ እንደተጻፈ እግዚአብሔር መልስ የሚሠጥበት ጊዜ በሰው ሕሊና የሚመረመር አይደለም፡፡ (ዕን. 2፡3) የለመንነውን ነገር ሳያደርግልን ልናረጅ ፣ ልንሸመግል እንችላለን፡፡ ከዚያም አልፎ የተመኘነውን ነገር ሳይሠጠን ልንሞትም እንችላለን፡፡ ፈቃዱ ከሆነ ግን የጸሎታችንን መልስ ከመቃብር ቀስቅሶ ሊሠጠን ይቻለዋል፡፡ ይህን የማያምን ሰው ሙሴን መጠየቅ ይችላል፡፡
https://youtu.be/e0Y8SnO759g
በሐዋርያት ሥራ እንደ ተጻፈው በበዓለ ጰራቅሊጦስ ማለዳ ኹሉም በአንድ ቦታ ተሰብስበው ሳሉ እንደ ዐውሎ ነፋስ ያለ ድምፅ ድንገት ከሰማይ መጣና የነበሩበትን ቤት ሞላው፡፡ ከዚያም እንደ እሳት የተከፋፈሉ የእሳት ላንቃዎች በኹሉም ላይ ተቀመጡባቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ኹላቸውም መንፈስ ቅዱስን ከተሞሉ በኋላ መንፈስ ቅዱስ ባደላቸው መጠን በየአገሩ ቋንቋዎች ኹሉ መናገር ጀመሩ /ሐዋ.፪፥፩-፬/
https://youtu.be/tOZpFwfQlSE
ሥጋችንን ከመለኮታዊ ባህርይ ተካፋይ አድርጎ ላከበረን ፥ ከድንግል ማርያም በነሳው በእኛ ሥጋ ወደ ሰማያት ላረገው ፥ በእግዚአብሔር አብ ቀኝ ለተቀመጠው ፥ በክብር እንዳረገ ከደመና ጋር ዳግም ለሚመጣው ፥ መንግሥትም ለአምላኩና ለአባቱም ካህናት እንድንሆን ላደረገ ለእርሱ ፥ ከባሕርይ አባቱና ማሕየዊ ከሆነ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ፣ ኃይል ፣ እልልታ ፣ ይባቤና ሽብሸባ ፣ ምስጋናና ውዳሴም ይሁን።
https://youtu.be/DVoztgb9nLs
"የበግ ጠቦትም በሸላቹ ፊት ዝም እንደሚል፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም›› ይላል፡፡ በእስራኤል ባሕል በግ ጠጉር ተሸልቶ ወፍራም ልብስ ይሠራበታል፡፡ ይህን ለማድረግ በጉ በሚሸለትበት ወቅት ‹‹ይበርደኛል እባካችሁን አትግፈፉኝ›› ብሎ አይከራከርም፡፡ ሸላቾቹን ከብርድ እያዳነ ያለተቃውሞ ዝም ብሎ ይኖራል፡፡ የክርስቶስ ዝምታም እንዲህ ነበር ፤ ዝምታው ግን አለመናገር ብቻ ሳይሆን ኃይል ያለው ሰውን ከእግዚአብሔር ያገናኘ ዝምታ ነበር፡፡
https://youtu.be/AYylLWRNaiI
ታናናሾችና ታላላቆችም ባለ ጠጋዎችና ድሆችም ጌታዎችና ባሪያዎችም ሁሉ በቀኝ እጃቸው ወይም በግምባራቸው ምልክትን እንዲቀበሉ፥ የአውሬውም ስም ወይም የስሙ ቍጥር ያለው ምልክት የሌለበት ማንም ሊገዛ ወይም ሊሸጥ እንዳይችል ያደርጋል። ጥበብ በዚህ አለ። አእምሮ ያለው የአውሬውን ቍጥር ይቍጠረው፤ ቍጥሩ የሰው ቍጥር ነውና፥ ቍጥሩም ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ነው። ራእይ 13፡16-18
2025/02/24 19:05:02
Back to Top
HTML Embed Code: