Telegram Web Link
https://youtu.be/-TVit1lMNlg
ሁልጊዜ የሰው ልጅ ቢያጠፋ ቢበድል ከሕገ እግዚአብሔር ቢወጣ እንኳ የዋህ፣ ታጋሽ፣ ቸር፣ አዛኝ የሆነ አምላክ የጠፋውን ሊፈለግ የተራበውን ሊያጠግብ የታረዘውን ሊያለብስ፣ ፍቅር ያጣውን ፍጹም ፍቅር ሊለግስ፣ ሰላም ለሌለው ፍጹም ሰላም ሊሰጥ፣ ተስፋ የሌለውን ተስፋ ሊያጐናጽፍ ከሰማይ ወረደ፤ ከድንግል ማርያም ተወለደ፤ በገዳመ ቆሮንቶስ አርባ ቀንና ሌሊት ጾመ፡፡ በጾሙም የኃጡአት ሥሮች ወይም ራሶች የተባሉትን ስስትን፣ ትዕቢትንና ፍቅረ ንዋይን ድል አደረገልን፡፡ እኛ እርሱ የጾመውን ጾም እንድናከብር እንድንጾም ምሳሌ ሆነን፡፡ ዲያብሎስን ድል አድርጐ ድል እንድንነሣው ኃይልና ምሳሌ ሆነን፡፡

https://youtu.be/-TVit1lMNlg
https://youtu.be/v9h-5TniabY
በኮከብ ተገለጠ በጠቢባን ተመለከ።. . ወደ ግብጽ ተሰደደ ነገር ግን የግብጽን አማልክት አስወገደ። በአይሁድ ዘንድ መልክና ደምግባት የለውም። ነገር ግን ለዳዊት ከሰው ልጆች ሁሉ ይልቅ ውብ ነው። በደብረ ታቦር ከጸሐይ ይልቅ እጅግ የሚያበራ፥ እንደመብረቅ የሚያንጸባርቅ ነበር፤ በዚያ እኛንም ወደ ወደፊቱ አስደናቂ ምሥጢር አስገባን። እንደ ሰው ተጠመቀ ነገር ግን እንደ እግዚአብሔር ኃጢአትን ይቅር ይላል። የተጠመቀው እርሱ መንጻት አስፈልጎት አይደለም። ነገር ግን ውኃውን ይቀድሰው ዘንድ ነው። እንደሰው ተፈተነ እንደ አምላክነቱ ግን ድል አደረገ፤ እርሱ ዓለምን አሸንፎታልና እኛን ደስ ይበላችሁ አለን፤ እርሱ ተራበ ነገር ግን ሺዎችን መገበ፤ አዎን እርሱ ሕይወትን የሚሰጥ እና ከሰማይ የወረደ ኅብስት ነውና፤ ተጠማ፥ ነገር ግን ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ ብሎ ጮኸ፤ ከሚያምኑበት ከውስጣቸው የሕይወት ውኃ ምንጭ እንደሚፈልቅ ቃል ኪዳን ሰጠ። ደከመ። ነገር ግን ለደከሙትና ቀንበር ለከበደባቸው እርሱ እረፍት ነው።
https://youtu.be/f1yFgOLPNzE
በእኛ ላይ ያለው ዓላማው ፍቅር ነውና፣ ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲቀርቡ ወዶ ይታገሳል ተብሎ ተጽፏልና (መኀ 2፡1 ፣ 2ጴጥ 3፡10) በመስቀል ላይ ሆኖ እየቆሰለና እየደማ ለበደለኞች ለኀጢዓተኞች መከራን አጽንተው ለሰቀሉት ‹‹የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው ብሎ ማለደ›› ከራሱና ከመንፈስ ቅዱስ እንዲሁም ከባሕርይ አባቱ ከአብ ጋር አስታረቀ፡፡ (2ቆሮ 5፡16-21)

ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተቀበለው ጻዋትወ መከራ ሁሉ ‹‹የድኅነታችን ተግሣጽ በእሱ ላይ ወደቀ›› (ኢሳ 53፡5) ተብሎ እንደተጻፈ ለድኀነታችን ቤዛ ነው፡፡
https://youtu.be/6tzcCtNOdos
የሰሙነ ሕማማት ዕለታት የዓመተ ኩነኔ ወይም የዓመተ ፍዳ ምሳሌዎች ናቸው፡፡ ክርስቲያኖች ክርስቶስ የዋለልንን ውለታ እያሰብን እጅግ የምናዝንበት፣ የምናለቅስበት፣ የምንሰግድበት ከሌሎች ቀናትና ጊዜያት በተለየ መልኩ አምላካችንን የምንማጸንበት፤ ጧት ማታ ደጅ የምንጠናበት፤ የክርስቶስን ተስፋ ትንሣኤ ከመቼውም ጊዜ በላይ በእምነትና በተስፋ የምንጠብቅበት  በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ የሚገኝ ልዩ ተምሣሌታዊ ምስጢራትና አዘክሮ የሚፈጸምበት ሳምንት ነው፡፡
https://youtu.be/M3wND51TxPE
ጸሎተ ሐሙስ በቤተ ክርስቲያን በርካታ ስያሜዎች አሉት፡፡ የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋን የተዋሐደ አምላክ መኾኑን ለመግለጥና ለአርአያነት ጠላቶቹ መጥተው እስኪይዙት ድረስ ሲጸልይ ያደረበት ቀን ነውና ‹ጸሎተ ሐሙስ› ይባላል (ማቴ. ፳፮፥፴፮-፶፮)፡፡ ጌታችን በዚህ ዕለት የደቀ መዛሙርቱን እግር በፍጹም ትሕትና ዝቅ ብሎ አጥቧል፡፡ ይህም ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለምን ዅሉ ኃጢአት ለማጠብ የመጣ የንጽሕና፣ የቅድስና አምላክ መኾኑን ያጠይቃል፡፡ ስለዚህም ዕለቱ ‹ሕጽበተ ሐሙስ› ይባላል፡፡
https://youtu.be/VK5nsnecsyc
ንጉሡ አንቀላፍቶአልና ዛሬ በምድር ላይ ታላቅ ጸጥታና እርጋታ አለ፣ እግዚአብሔር በሥጋ አንቀላፍቷል ለዘመናት አንቀላፍተው የነበሩትንም አስነሥቷልና፡፡ ምድር በድንጋጤና በጸጥታ ላይ ነበረች፣ እግዚአብሔር በሥጋ ሞቷል፣ የመቃብር ዓለምም ተሸብሯልና፡፡
በእውነት እርሱ የመጀመሪያውን አባታችንን እንደ ጠፋ በግ ሊፈልግ ሄደ፣ በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ ያሉትን ሊጐበኝ ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሔርና የአዳምን ልጅ የሆነው እርሱ እስረኛውን አዳምንና አብራው የታሰረችውን ሐዋንን ሊፈታ ሄደ፡፡
https://youtu.be/AR7ojgcTaA4
ጌታችን አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕያው ነውና መቃብር ይዞ አላስቀረውም፣ ትንሣኤ ነውና ሞት በእርሱ ላይ ስልጣን አልነበረውም በመሆኑም ከሦስት መዓልትና ሌሊት በኋላ መግነዝ ፍቱልኝ መቃብር ክፈቱልኝ ሳይል ሞትን ድል አድርጎ መውጊያውንም ሰብሮ በኃይሉ ተነስቷል፡፡ ‹‹ኦ መዊት አይቴ ሃሎ ቀኖትከ›› ሞት ሆይ መውጊያህ የታለ? ሲኦል ሆይ ድል መንሳትህ የታለ›› ተብሎ በትንቢት በተነገረው መሠረት ገዥውንና ኃያሉን አሸንፎ መውጊያውን ሰብሮ ጌታችን ተነስቷል፡፡
ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን ~~በዓቢይ ሃይል ወሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን ~~~ አግአዞ ለአዳም
ሰላም ~~~~ እምእዘየሰ
ኮነ ~~~ ፍሰሃ ወሰላም። አሜን!!!
+++ ትረጉም +++
ክርስቶስ በታላቅ ሃይሉና ሥልጣኑ ከሙታን መካከል ተለይቶ ተነሳ፤
ሰይጠንን አሰረው፤ አዳምን ነፃ አወጣው፤
ከእንግዲህ ወዲህ ፍሰሃ፣ ሰላም፣ ደስታ ሆነ!!! አሜን! —
https://youtu.be/aujS1Fugyd8
https://youtu.be/sQF0dZ4vetY
ከትንሣኤ እሑድ ቀጥለው ያሉት ዕለታት ‹ሰሙነ ፋሲካ› ወይም ‹ትንሣኤ› እየተባሉ የሚጠሩ ሲኾን፣ የየራሳቸው ምሥጢራዊ ስያሜም አላቸው፡፡ ስያሜአቸውንም በአጭሩ እንደሚከተለው እንመለከታለን፤
https://youtu.be/XjX6mpMUzH0
በጸሎተ ቅዳሴ ጊዜ ኅብስቱ ተለውጦ ሥጋ መለኮት ወይኑ ተለውጦ ደመ መለኮት የሚሆነው በቅዳሴው ጸሎት ነው። ሳናስቀድስ አንቆርብምና የቁርባን መሥዋዕት የሚፈጸመው በሥርዓተ ቅዳሴ ብቻ ነው፡፡ መሥዋዕቱም በቤተልሔም በተልዕኮ ፈጻምያን ይዘጋጃል። በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አምሳለ ቀራንዮ በሆነችው በቤተ-መቅደስ ውስጥ ደግሞ በካህናቱ እጅ ይታደላል፡፡
2025/02/24 22:41:07
Back to Top
HTML Embed Code: