Telegram Web Link
https://youtu.be/daFGPxR5PAk
ጌታችን የይሁዳን ስርቆት ያላጋለጠውና በሹመቱ ያቆየው በተጣለበት አመኔታና በጌታው ትእግሥት ልቡ ተነክቶ እንዲመለስ መንገድ ሊሰጠው ነበር፡፡ ገንዘብ ያዥነቱ ጌታውን ለመሸጥ የሚያስገድድ የገንዘብ እጥረት የማያጋጥመው ሰው ስለሚያደርገው ይሁዳን ምንም ምክንያት ሊያቀርብ የማይችል ያደርገዋል፡፡ የይሁዳ ችግር የገንዘብ እጥረት ሳይሆን የገንዘብ ፍቅር ነበር፡፡ ‹‹ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነውና›› ይሁዳም ‹‹ይህን ሲመኝ ከሃይማኖት ተሳስቶ በብዙ ሥቃይ ራሱን ወጋ›› (፩ጢሞ. ፮፥፲)
https://youtu.be/VwFbqx2dncM
ከሁሉም ልብ የሚሰብረው ሐሙስ ምሽት የሆነው ነገር ነው፡፡ ጌታችን ‹‹ከእራት ተነሣ ልብሱንም አኖረ፥ ማበሻም ጨርቅ ወስዶ ታጠቀ ፤ በኋላም በመታጠቢያው ውኃ ጨመረ፥ የደቀ መዛሙርቱንም እግር ሊያጥብና በታጠቀበትም ማበሻ ጨርቅ ሊያብስ ጀመረ›› የእግር ሹራብ በማይደረግበትና ክፍት ጫማ በሚደረግበት በዚያ ዘመን ቀኑን ሙሉ ሲጓዙ የዋሉበትን የሐዋርያቱን በአቧራ ያደፉ እግሮች ሊያጥብ ተነሣ፡፡ (ዮሐ.፲፫፥፬) በእስራኤል ባህል እግር ማጠብ የሎሌዎች ሥራ ቢሆንም የሰማይና የምድር ንጉሥ ግን በትሕትና እንደ ሎሌ ሆነ፡፡ (፩ሳሙ. ፳፭፥፵፩)
https://youtu.be/lX2CpJVhmvA
ጌታችን የሚያዝበትን ዕቅድ የነደፈውና ለወታደሮቹ የቅድሚያ ትእዛዝና የምሥጢር ‹ኮድ› የሠጣቸውም ራሱ ይሁዳ ነበር፡፡ ‹‹የምስመው እርሱ ነው ፣ ያዙት ተጠንቅቃችሁም ውሰዱት› የሚል ዝርዝር መመሪያም አስቀድሞ አስተላልፎ ነበር፡፡ (ማር. ፲፬፥፵፬) ስለዚህ ቃል በገባው መሠረት ወደ ጌታችን ቀርቦም ‹‹መምህር ሆይ ፣ መምህር ሆይ ሰላም ለአንተ ይሁን ብሎ ሳመው›› (ማር. ፲፬፥፵፬ ፣ማቴ.፳፮፥፵፰}
https://youtu.be/SlBBCfBAsiU
ሊሸጠው እንደመጣ እያወቀ ይሁዳ በሐሰት ፍቅር ሲያቅፈው ጌታችን ልቡን ምንኛ አሳዝኖትና አምሞት ይሆን? እርሱ ግን ይህንን ሕመም ታገሦ ተቀበለ፡፡ ይሁዳም እንደ ጠላቱ እየሸጠው እንደ ወዳጁ አቅፎ ሳመው፡፡ ጌታችን ‹‹በሩ እኔ ነኝ ፤ በእኔ የሚገባ ይድናል›› ብሎ ሲናገር ቢሰማም ይሁዳ ግን በሩን ጌታን ስሞ ተሳልሞ ወደ ውስጥ በመግባትና በመዳን ፈንታ ወደ ሲኦል ገሠገሠ፡፡ ከውጪ ተሳልሞ መመለስ ይኼው ነው ትርፉ! (ዮሐ. ፲፥፱)
https://youtu.be/S2_AYPLtFI8
ከዚህ በኋላ ይሁዳ በራሱ ላይ ፈረደና ታንቆ ሊሞት ወሰነ፡፡ የይሁዳ ትልቁ ኃጢአት ጌታን አሳልፎ መሥጠቱ ሳይሆን ጌታ ይቅር አይለኝም ማለቱ ነው፡፡ ‹‹የወደቀስ አይነሣምን? የሳተስ አይመለስምን?›› ይላል መጽሐፉ፡፡ (ኢሳ. ፰፥፬) እግዚአብሔር ሊፈርድ ሲመጣ ለምን ኃጢአት ሠራህ? ብሎ አይጠይቅም ፤ የፈጣሪ ጥያቄ ለምን ንስሓ አልገባህም? ነው፡፡ ይሁዳ ግን ይቅር በለኝ በማለት ፈንታ በራሱ ላይ ፈረደ፡፡ ፈራጅ እግዚአብሔር ነውና እንደ ጲላጦስ ለራስ ይቅርታ ማድረግም ሆነ እንደ ይሁዳ በራስ መፍረድ የሰው ልጅ ሥልጣን አይደለም፡፡
Forwarded from የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች (ነጠላ ሰረዝ)
ይህ ኀብረት የንባብን ልምድ ለማዳበር እና ሃሳብ ለማጋራት በተመረጡ የ ሃይማኖት፣ የ ታሪክ እና የልብ-ወለድ መጽሐፍት ላይ ግምገማ የሚከውን ሐገር አቀፍ ኅብረት ነው::


መልዕክት ለመላክ ፣ ለአስተያየት እና ለመመዝብ @Endalk9
https://www.tg-me.com/TheEthiopianJandereba
https://youtu.be/Cgfj6bADZTE
ምንም እንኳን ትንቢቶች ቢነገሩም ይሁዳ እስከተመለሰ ድረስ እግዚአብሔር የኃጥኡን መመለስ ይወድዳልና ስለማይወድቅ ፍቅሩ ሲል ትንቢቶቹን ይሽራቸው ነበር፡፡ ‹‹ፍቅር ለዘላለም አይወድቅም ፤ ትንቢትም ቢሆን ይሻራል›› ተብሎ ተጽፎአልና፡፡ (፩ቆሮ. ፲፫፥፰) ለነነዌ ሰዎች ስለ ፍቅሩ ሲል ዮናስን አስከፍቶ የተነገረባቸውን የጥፋት ትንቢት የሻረ አምላክ ይሁዳም ቢመለስ ኖሮ የተነገረውን ትንቢት እስካልተፈጸመ ድረስ ነቢያቱ እንደ ዮናስ ቢከፉም እንኳን ይሽረው ነበር፡፡ (ዮና. ፫፥፲)
https://youtu.be/D74UzOIEs0I
ጌታችን ከመያዙ በፊት ለወታደሮቹ አንድ ነገር አሳሰባቸው፡፡ የሚይዙት ኃይል ስለሌለው ሳይሆን ፈቅዶ መሆኑን ካስረዳ በኋላ ልትይዙኝ ከሆነ ‹‹እንግዲህ እኔን ትፈልጉ እንደሆናችሁ እነዚህ ይሒዱ ተዉአቸው›› አለ፡፡ ወደ መከራ እየሔደ ስለ ተማሪዎቹ የሚያስብ መምህር ፣ ወደ መታረድ እየሔደ ስለ በጎቹ የሚጨነቅ መልካሙ እረኛ ክርስቶስ እኔን ያዙኝና ‹‹እነዚህ ይሒዱ ተዉአቸው›› ብሎ ‹‹ነፍሱን ስለበጎቹ አሳልፎ ሰጠ›› (ዮሐ. ፲፰፥፰) የደቀ መዛሙርቱን አቅማቸው ያውቃልና ‹ከሚቻላቸው በላይ› ተፈትነው እንዳይጠፉ ፣ ባልጸና እምነታቸው በመከራ እንዳይወድቁ ያስባልና በአንዲት ገረድ ፊት የሚክዱት ሐዋርያት በወታደር ፊት እንዲጋፈጡ አላሰናበታቸውም፡፡ ‹‹ይሒዱ ተዉአቸው›› አለ፡፡
https://youtu.be/uiNBVJ1KXnQ
ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታችን እንዳይሞት የነበረው ቁርጠኝነት ጌታችን እስከተያዘባት ሐሙስ ምሽት ድረስ የቀጠለ ነበር፡፡ ለጌታ ካለው ጽኑ ፍቅር የተነሣም ጌታችንን ሊይዙ ከመጡት ወታደሮች ጋር ለመዋጋት ሰይፍ ይዞም ነበር፡፡ እርግጥ ነው ጌታችን ‹‹ሰይፍን ያዙ›› ብሎ ነግሮአቸው ነበር፡፡ ሁለት ሰይፍ እንዳላቸው ሲነግሩትም ‹‹ይበቃል›› ብሏቸው ነበር፡፡ ጌታችን ይበቃል ያለው ግን ሰይፉን ሳይሆን ንግግራቸውን ነበር፡፡ ለውጊያ ሰይፍ ሁለት ሊበቃ አይችልም ፤ ጌታም ጎኑን በጦር ሊወጋ እንጂ ሰዎችን ሊያዋጋ ሰው የሆነ አምላክ አይደለም፡፡ ሊቃውንት እንዳብራሩት ያዙ የተባሉት ሰይፍ ደግሞ ‹‹ነፍስና መንፈስን ጅማትና ቅልጥምን እስኪለይ ድረስ የሚወጋውን የመንፈስ ሰይፍ›› ሲሆን እርሱም ሦስት ዓመት ያስተማራቸውን የመከራ ቀን ስንቅ የሚሆን የእግዚአብሔር ቃልን ነበር (ኤፌ. ፮፥፲፯ ዕብ. ፬፥፲፪)
Forwarded from ፍቁረ እግዚእ ሚዲያ Fikure Egzi Media – FEM (ፍቁረ እግዚእ ሰንበት ት/ቤት)
ታላቅ የበረከት በዓለ ንግሥ ጥሪ
ጥር 4 ቀን 2013 ዓ.ም
በደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ እና መካነ ጎልጎታ ቅድስት ድንግል ማርያም ቤ/ክ
በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ በድምቀት የሚከበረውን የሐዋርያው ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ በዓለ ንግስ ተገኝተው የበረከት ተሳታፊ ይሁኑ።
https://youtu.be/1RkmbxZJ9hg
የሚመጸውት ሰው በፍጹም ቸርነት መመጽወት አለበት እንጂ በሚለምነው ሰው ላይ ግምገማ ማካሔድ የለበትም፡፡ ወዳጄ የሚለምንህ ሰው በንዝነዛ ፋታ አሳጥቶህ ይሆናል ፣ እንግዲህ እሱንም ረሃብ እንዲህ ፋታ አሳጥቶት ነው፡፡ አነጋገሩ ለዛ የለው ይሆናል ፣ ለዛ ያሳጣው ግን ድህነት ነው፡፡ የሚነግርህ ታሪክ አሳማኝ ላይሆን ይችላል ፣ ምንም ቢልህ መቸገሩ ግን እውነት ነው፡፡ ይኼን ሁሉ ርቀት ሔዶ አንተን ለማሳመን የሚጣጣረው ፣ አጠያየቁን የሚለዋውጠው ስለጨከንክበት ነው እንጂ መቸገሩ እውነት ነው፡፡ ፈጣሪ ይህንን ደሃ ከፊትህ ያቆመው እንድትረዳው ነው እንጂ የልመና ተሰጥኦ ውድድር ዳኛ እንድትሆንለት አይደለም፡፡
Forwarded from ፍቁረ እግዚእ ሚዲያ Fikure Egzi Media – FEM (ፍቁረ እግዚእ ሰንበት ት/ቤት)
✞✞✞ጉባኤ ፍቁረ እግዚእ ✞✞✞
ሳምንታዊ የሰንበት ት/ቤታችን ጉባኤ አርብ ምሽቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ በሰንበት ት/ቤቱ አዳራሽ ይካሔዳል።
በእለቱ በመገኘት የመርሐ ግብሩ ተሳታፊ ይሁኑ!!!
🍃🍂🍃🍂🍃🍂🍃🍂🍃🍂🍃🍂🍃🍂🍃🍂
https://youtu.be/QIPhpizuPwA
ጌታችንን በመከተል የነገሩን ፍጻሜ ያዩ ዘንድ እስከ ሊቀ ካህናቱ ግቢ የዘለቁት ደግሞ ቅዱስ ዮሐንስና ቅዱስ ጴጥሮስ ነበሩ፡፡ የጌታ ፍቅር ጸንቶባቸው እንጂ በዚያች አስጨናቂ ሌሊት እስከ ሊቀ ካህናቱ ግቢ ድረስ ዘልቀው መሔዳቸው ትልቅ አደጋ ላይ የሚጥላቸው ውሳኔ ነበር፡፡ በጎች ሆነው ወደ ተኩላዎች ግቢ ዘልቀው መግባታቸው ብቻ ‹ፍቅር ፍጹም ፍርሃትን አውጥቶ እንደሚጥል› ያሳያል፡፡ ከሸሸ ተዋግቶ የቆሰለ ይሻላልና የጴጥሮስን በፈተና መውደቅ ብቻ ከማየት እንደ ልማዱ ‹ጌታ ሆይ ወደ ማን እንሔዳለን?› ብሎ እንደ ጓደኞቹ ሳይሸሽ ጌታውን በፍቅር መከተሉን ልናመሰግን ይገባናል፡፡ ‹ጴጥሮስ በፍቅሩ ምክንያት ከፍርሃታቸው የተነሣ ከሸሹት ጓደኞቹ ጋር አብሮ አልሸሸም› ‹‹ወበእንተ አፍቅሮቱ ጴጥሮስ ኢጐየ ምስለ አብያጺሁ እለ ጐዩ እምፍርሃቶሙ›› እንዲል፡፡[
https://youtu.be/YOKkBJLJi9w
በዚህ ብዙ የማያስቀምጥ የሥልጣን ቦታ ላይ ሐናም ሆነ ቀያፋ ለብዙ ዓመታት መቀመጣቸው የሮማውያን ገዢዎችን ገንዘብ ወዳድነት ሊቋቋሙ የሚችሉ ባለሀብቶች መሆናቸውንም የሚያሳይ ነው፡፡ በዚያ ላይ በሊቀ ካህናትነታቸው ዘመን በእስራኤል ሕዝብ ላይ በሮማውያን እጅ አስከፊ የመብት ጥሰት ቢደርስም መንበረ ሥልጣናቸው እስካልተነካባቸው ድረስ ከቅኝ ገዢዎቻቸው ጋር ተስማምተው የሚኖሩ መስሎ አዳሪዎች ነበሩ፡፡ እንደ ሊቀ ካህናትነታቸውም ለቤተ መቅደሱ ክብር የሚጨነቁና ፈሪሐ እግዚአብሔር ያላቸው አልነበሩም፡፡ የሚያሳዝነው ድፍረት ከቤተ መቅደስ ሊወጣ የማይገባው የሊቀ ካህናቱ ልብሰ ተክህኖ እንኳን በሮማውያን ገዢዎች ቤት (Castle Antonia) ይቀመጥ የነበረ ሲሆን ሊቀ ካህናቱ በክብረ በዓል ወቅት የሚለብሰው ገዢው ሲፈቅድለት ነበር፡፡
https://youtu.be/egjHnenN15g
ከእኛ ከኢትዮጵያውያን ክብር ጓድሏል መተማመን ጠፍቷል ወንድም በወንድሙ ላይ እተነሣ ፍቅር በመካከላችን ቅዝቅዟል ፍርድ ተጓድሏል ደሀ ተበድሏል በገዛ ሀገራችን ሳይቀር እንደ መጻተኛ የሰሜኑ፣ በደቡብ፣ የምስራቁ ከምዕራብ ተዘዋውሮ እንዳይሰራ ጎጆ ቀልሶ ኑሮ መሥርቶ ወልዶና ከብዶ እንዳይኖር በዘረኝነት አጥር ተከልሎ በገዛ ሀገሩ ስደተኛ በባዕድም ሀገር በአሕዛብም ምድር ሳይቀር ከርታታና ተስፋ ቢስ ሆነናልና፡፡
2025/02/24 12:53:24
Back to Top
HTML Embed Code: