Telegram Web Link
ቶ መስቀል እና የሰለ(የ)ጠነው አለም/ Ankh and modern world/

ከዚህ ቀደም በየ ድህረ ገፁ የተለጠፉትን ስለ ቶ መስቀል የሚገልፁ ፅሁፎች ከራሳችን እሳቤ ጋር በማዛመድ ፅፈንላችሁ ነበር። አሁን ደግሞ ከቤተክርስቲያን ስርአት አንፃር ያለውን ለቀንላችኋል። ሀሳባችሁን ሰብሰብ፣ አዕምሯችሁን ከፈት አድርጋችሁ አንብቡና፤ ለጓደኞቻችሁ #ሼር አድርጉላቸው።

የዳቢሎስ ማህበርተኞች በአንገታቸው፣ በልብሶቻቸው፣ በቦርሳቸው፣ በንቅሳት መልክ ሲጠቀሙበት ይስተዋላል። እንደ እውነቱ ከሆነ የቶ መስቀልን እውነተኛ ምንነት መናገር እጅግ ከባድ ነው። ነገረ ግን በሰለጠነው ዘመን ፓጋኖች ምልክታየው አድርገው ሲጠቀሙበት ይስተዋላል። ክርስቶስ የተሰቀለበትን መስቀልም ቢሆን ይጠቀሙበታል። እንዲያውም በጆሮ ጌጥ እና በልብስ ማድረግ አንሷቸው በጫማ ሶል ላይ ያደርጉታል።

ክርስቶስ በወንጌሉ ዮሐ 6:47 "በኔ የሚያምን የዘለአለም ህይወት አለው" ይላል። ታዲያ የዘለአለም ህይወት ቁልፉ ቶ መስቀል ወይስ ክርስቶስ??

የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮችን በማጭበርበር ወደ ገሀነም መንገድ መምራት የጀመሩት ማህበረ ስላሴ ዘደቂቀ ኤልያስ የተሰኘው ማህበርም ቶ መስቀልን የማህበሩ መለያ አድርገውታል። አንድ በዚህ ማህበር ዋና አባል የነበሩ አባትም ከስህተታቸው ታርመው ወደ እናታቸው ቅድስት ቤተክርስቲያን መመለሳቸውን በማህበረ ቅዱሳን ቴቪ/EOTC/ ላይ ተናግረዋል።

ከአንድ ኦርቶዶክሳዊ የዩቲዩብ ቻናል የተለቀቀ ቪድዮ ላይ ደግሞ አባ ተስፋ ስላሴ ሞገስ፣ መሪ ራስ አማን በላይ እና ፕ/ሮ ፍቅሬ ቶሎሳም ስለ ቶ መስቀል በስፋት የተናገሩ ሲሆን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በሚለው ሳይሆን ተዋህዶ በሚለው ብቻ የሚያምኑ ግለሰቦች ነበሩ ይላል። ነገር ግን የታሪክ መፅሀፎቻቸውን ሪፈር ማድረግ የለብንም ማለት አይደለም። እውነት የሆነውን ታሪክ በማስረጃ እንቀበላለን።

ልብ የምትሉት ግን ሰይጣናዊ ማንነት አለውም እያልኩ አይደለም። ምክንያቱም አሁን ትልቅ ውዝግብ እየፈጠረ ያለው ይኼው ጉዳይ ነው።

ገላትያ 6:14 "አለም ለኔ ከተሰቀለበት እኔም ለአለም ከተሰቀልኩበት ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት የለም" ይለናል። ህይወታችን ክርስቶስ ነው። ትምክህታችንም በ34 ዓ.ም በእለተ አርብ በቀራንዮ አደባባይ የተሰቀለበት መስቀል እንጅ 3000 B.C ላይ በግብፃውያን ዘንድ የነበረው "ቶ" አይደለም። "ኢትኤል ቆ በትርን ወንድሙ ሀሙኤል ቶ በትርን ይይዙ ነበር" የሚለውን ታሪክ እንቀበላለን። ነገር ግን በትረ መንግስት እንጅ የድህነት ምልክት እንዳልሆነ በዘመኑ የነበሩት እነ ኢትኤል ይመሰክራሉ።

ፊልጵስዩስ 3:18-20 "ብዙዎች #ለክርስቶስ #መስቀል #ጠላቶች ሆነው ይመላለሳሉና ብዙ ጊዜ ስለ እነርሱ አልኳችሁ፤ አሁንም እንኳ እያለቀስኩ እላለሁ #መጨረሻቸው #ጥፋት ነው ሆዳቸው አምላካቸው ነው፤ ክብራቸው በነውራቸው ነውና፤ #ሀሳባቸው #ምድራዊ ነው እኛ #ሀገራችን #በሰማይ ነውና፤ ከዚያም ደግሞ የሚመጣ መድሀኒትን እርሱንም ጌታን ኢየሱስ #ክርስቶስን #እንጠባበቃለን።"

ክርስቶስ የተሰቀለበትን መስቀል በቶ መስቀል ለውጣችሁ አንገታችሁ ላይ ያደረጋችሁ፤ የድሮውን የድህነት ማዕተብ አድርጉ፤ ቶ መስቀልንም አውልቃችሁ አስቀምጡ። ቶ መስቀል ታሪካዊ ማንነት እንደሚኖረው ግልፅ ነው። ሀይማኖታዊም ማንነትም ይኖረው ይሆናል። መቼም ቢሆን ግን ክርስቶስ የተሰቀለበትን መስቀል አይተካም ዶግማ ነውና።

ሁሌም ቢሆን አባቶች ከእኛ ይበልጣሉና "መታዘዝ ከመስዋዕት ይበልጣል" የሚለውን እናስታውስ።

አዋጅ አዋጅ አዋጅ! ያልሰማህ ስማ የሰማህ ላልሰማ አሰማ!

https://www.tg-me.com/yekdset_selase_lejoch
https://www.tg-me.com/yekdset_selase_lejoch
https://www.tg-me.com/yekdset_selase_lejoch
ኢትዮጲያውያን ሊቃውንት እንዲህ የሚል #ብሒል አላቸው....

"አንድ መንገደኛ ካሰበበት በታ ሳይደረስ ቀኑ መሽበት። በጨለማ ሄጄ በአውሬ ከምበላ ስመ እግዚኣብሔርን ጠርቼ በእናቱ በቅድስት ድንግል ማርያም ስም ተማጽኜ የመሸበት እንግዳ እባካችሁ አሳድሩኝ ብዬ እለምነለሁ ብሎ ያወጣ ያወርድ ጀመር።

አስቦም አልቀረም፣ የአንድ አርሶ አደር ቤት አጋጣመው። ከበር ላይ ቆሞ ስመ እግዚአብሔርን ጠራ፡፡ አርሶ አደሩም ቤት የእግዚአብሔር ነው ብሎ #እግሩን_አጠበው#ራቱን_አበላው#መኝታ_ሰጠው። ይህ በመንገድ ሲንገላታ የዋለ መንገደኛ እግዚአብሔርን እያመሰገነ ሌሊቱን በጥሩ እንቅልፍ አሰለፈ።

ጠዋት ረፋዱ ላይ ቁርሱን በልቶ የቀረ መንገዱን ለመቀጠል ተነሣ። አባወራውም ልሸኘው ተዘጋጅ። መንገደኛውም "#ጌታዬ_ቤትዎን_ከመልቀቄ_በፊት_አንድ_ነገር_እንድናገር_ይፈቀድልኝ_አለ። አርሶ አደሩም እሺ ብሎ ፈቃዱን ገለጠ።
መንገደኛውም መቼም ውሎ ውሎ ከቤት፤ ኑሮ ኑሮ ከሞት አይቀርም። ሞት እንዳማይቀረው ሁሉ ምጽአተ ክርስቶስም አይቀርም።
*"#ያንጊዜ_ለፍርድ_በቆምን_ጊዜ_ሰይጣንን_ከሳሽ#እርስዎን_ተከሳሽ#እኔን_ምስክር_አድርጎ_ያገናኘን"🙏 ብሎ መረቀ።*

አርሶ አደሩም ነገሩ ገብቶት ኖሯልና #አሜን #ይሁን_ይደረግ ብሎ እንግዳውን ሸኘው ይባላል። 😊

===================
#ለካስ_ሲርባቸው_ያበላናቸው#ሲጠማቸው_ያጠጣናቸው#ሲታረዙ_ያለበስናቸው#ሲታመሙ_የጠየቅናቸው#ሲታሰሩ_የጎበኘናቸው_ሰዎች_በዕለተ_ምጽአት_ይመስክራሉ#ምግባራችን_ይከተለናልና#በጎ_ነገር_ማድረግ_ትርፍ_እንጂ_ኪሣራ_ከሌለው_ለጋስ_ብንሆንስ?🤔

ምንጭ ፦ ፍጹም አምልኮ (መጽሐፍ)

@yekdset_selase_lejoch
@yekdset_selase_lejoch
@yekdset_selase_lejoch
እኔ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዛሙርት ነኝ
"ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እሱን ያፈርሰዋል ፤የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ"
1ኛ ቆሮ 3፥17
የተለያዩ ኦርቶዶክሳዊ መረጃዎች
""""""""""""""""" መዝሙሮች
"""""""""""""""" ታሪኮች ያገኙበታል !!!
ለተለያዩ ሀሳብ፣አስተያየት እንዲሁም ጥያቄ


ሼር በማድረግ ኦርቶዶክሳዊ ግዴታዎን ይወጡ!!
https://www.tg-me.com/zemariyannen
#ልጅኽን_በፖለቲካዊ_ጉዳዮች_ላይ_እንዲሳተፍ_አድርገው

እንደ ችሎታው መጠን እና ከኀጢአት ነፃ በኾነው ነገር ላይ እንዲሳተፍ አድርገው፤

ወታደር ቢኾን ደመወዙ ብቻ እንዲበቃ አስተምረው፤ ለተበደሉት ኹሉ ጠበቃ እና መከታ እንዲኾንላቸው ምከረው፤ አስተምረውም።

በሌሎች የሥራ ዘርፎች ላይ ሲሰማራም ኀጢአት ባለ መሥራት፣ በአግባቡ እና በሥርዐቱ ሰዎችን ማገልገልን አስተምረው "

( ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)

[ ኦርቶዶክሳውያን እና ፖለቲካ ፤ በዳዊት ደስታ ፤ ገጽ 9 ፤ 2013 ዓ.ም. ]

@yekdset_selase_lejoch
@yekdset_selase_lejoch
@yekdset_selase_lejoch
ዕጣው #መጋቢት_26_ ይወጣል

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የቦሌ ክ/ከተማ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ሰ/ት/ቤቶች በተሻለ መልኩ ለማደራጀት እና የአገልግሎቱን አውድ ለማስፋት ታስቦ በመሸጥ ላይ የሚገኝ ትኬት ነው። ከዚህ ትኬት የሚገኘው ገቢ ቢያንስ 10 ሰ/ት/ቤቶች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ለሟቋቋም የሚረዳ ነው።

#የልዩ_ዕጣ መውጫ ቀን መጋቢት 26/2013 ።

ሁላችንም እድላችንን እየሞከርን ትኬቱን በመቁረጥና ድጋፍ በማድረግ የዚህ ታላቅ በረከት ተሳታፊ ይሆኑ ዘንድ ጥሪው ተላልፏል፤

1ኛ እጣ - #በገና
2ኛ እጣ - #ነጠላ-ጋቢ
3ኛ እጣ - #ትልቅ-ስዕል-አድህኖ(2)
4ኛእጣ - #ገድለ-ቅዱሳን(ብዛት-3)
5ኛ እጣ -# ድርሳናት (ብዛት-2)
6ኛ እጣ -# መዝሙረ -ዳዊት(2)
7ኛ እጣ - # መጸሐፍ -ቅዱስ(2)
8ኛ እጣ - # አዋልድ መጸሓፍት ለ3 ሰዎች

የያዘ የእጣ ትኬት ሲሆን ዋጋው 25 (ሃያ አምስት ብር) ነው፡፡

ቲኬቱን በክ/ከተማ ስር ባሉ ሰ/ት/ቤቶች እና በሌሎች ክ/ከተማ ሰ/ት/ቤቶች አንድነት ያገኙታል።

ለበለጠ መረጃ :-0924-37-31-33
+ ተማሪዎች ከፈተና በፊት ምን ብለው ይጸልዩ?

ቅዱስ ቄርሎስ ሳድሳዊ ከሚታወቁባቸው በርካታ በጎ ነገሮች አንዱ ለተማሪዎች የነበራቸው ልዩ ፍቅርና ቅርበት ነበረ፡፡ አባ ሚናስ ተብለው ይጠሩ ከነበረበት የምንኩስናቸው ዘመን ጀምሮ አቡኑ በተማሪዎች የተከበቡ ነበሩ፡፡ ከልዩ ልዩ ክፍለ ሀገራት ካይሮ ዩኒቨርሲቲ ሊማሩ ለሚመጡ ተማሪዎች የማደሪያ አገልግሎት በቅዱስ ሚናስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ይሰጡ ነበር፡፡ ይህ አገልግሎታቸውም በግብፅ ለዘመናዊው ቤተ ክርስቲያንን የሚያካትት የማደሪያ አገልግሎት(church- affiliated dormitory) መወለድ ምክንያት ሆኗል፡፡ የዚህ የማደሪያ አገልግሎት ተጠቃሚዎች የነበሩ ተማሪዎችም ቀሳውስትና ጳጳሳት የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ለመሆን በቅተዋል፡፡(ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ሳሙኤልና ቅዱስነታቸው አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊተጠቃሽ ናቸው፡፡) በወቅቱ መነኩሴ የነበሩት አባ ሚናስ (አቡነ ቄርሎስ) ለእያንዳንዱ የቤተ ክርስቲያኑ ካህን በተማሪዎቹ መኖሪያ ውስጥ የሥራ ድርሻ ሰጥተው ነበር፡፡ የእርሳቸውን የሥራ ድርሻ ምን እንደነበረ ግን ማንም ሰው አላወቀም ነበር፡፡ በሌሊት በድብቅ የሚሠሩት ሥራ ካህናቱና በቤተ ክርስቲያኑ የሚኖሩ ተማሪዎች የሚጠቀሙበትን መጸዳጃ ቤት ማጽዳት ነበር፡፡

ይህ ለተማሪዎች ያላቸው በጎ አመለካከት በፓትርያርክነት ዘመናቸው አልተለያቸውም፡፡ ተማሪዎች ፈተና ሲደርስባቸው ወደ እርሳቸው እየመጡ ጸልዩልን ይሉአቸው ነበር፡፡ አንዳንድ ተማሪዎች ደግሞ የሚያጠኑበትን መጽሐፍ ይዘው መጥተው ያስባርኩ ነበር፡፡ ቅዱስ አባ ቄርሎስ አንዳንዴ መጽሐፉን ገለጥ ያደርጉና ‹ይህንን አጥኑ› ብለው ይሠጡ ነበር፡፡ የፈተናውም አብዛኛው ጥያቄ ከዚያ ገጽ ይወጣ ነበር፡፡ እንዲሁም ለተማሪዎች ፈተና በሚፈተኑበት ጊዜ የሚገጥማቸውን የመንፈስ ጭንቀትና የአእምሮ ውጥረት በመረዳት የሚከተለውን ከፈተና በፊት የሚጸለይ ጸሎት አዘጋጅተውላቸዋል፡፡

+ ጸሎት +

‹‹ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ

‹‹በችግርህ ቀን ጥራኝ ፤ አድንሃለሁ አንተም ታከብረኛለህ›› ብለህ የአንተን መጠጊያነት መፈለግን ስላስተማርከኝ አመሰግንሃለሁ!

አሁንም ጌታ ሆይ! በዚህ የፈተና ሰዓት ጥበብና ማስተዋልን ትሰጠኝ ዘንድ እማጸንሃለሁ፡፡

ይህን ፈተና በሰላም አልፍ ዘንድ ጸጋን (ሞገስን) ስጠኝ፡፡ ፈተናውን በምሠራ ጊዜ ጥልቅ የሆነ ሰላምህንና በረከትህን ስጠኝ፡፡

ጌታዬ ኢየሱስ ውጤት በሚሰጡኝ ጊዜ በመምህራኖቼ ዓይን መወደድን ትሰጠኝና ልባቸውን ታለሰልስልኝ ዘንድ እለምንሃለሁ፡፡ የከበርከው ጌታእኔ ኃጢአተኛ ነኝ ፤ ዓመቱን ሙሉ አንተን ደስ አላሰኘሁህም ፤ ውስጤንም ጭምር ፤ ነገር ግን ከልቤ ደንዳናነትና ከኃጢአቶቼ የተነሣ ሳይሆን ከምሕረትህ እና ከርኅርኄህ የተነሣ እንደትረዳኝ እለምንሃለሁ፡

ጌታ ሆይ ‹‹ለምኑ ይሰጣችኋል፣ እሹ ታገኛላችሁ፤ አንኳኩ ይከፈትላችኋል›› ብለሃል፡፡ እናም እነሆኝ እየለመንኩ ነው፤ የምሕረትህንም ደጅ እያንኳኳሁ ነው፡፡ ‹‹ወደ እኔ የሚመጣውን ከቶ ከእኔ አላወጣውም›› ብለሃልና ጸሎቴን አትናቅ፡፡በቅድስት ድንግልና በመላእክትህ ሁሉ አማላጅነት መልስልኝ!! አሜን!"

ታሪክ በማይረሳው የተወሳሰበ የትምህርት ዘመን አልፋችሁ ለምትፈተኑ ለዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪዎች እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን! የልባችሁን ዓይን ያብራላችሁ! ያጠናችሁትን ይባርክላችሁ የተማራችሁትን ያስታውሳችሁ! ባለቀ ሰዓት የሚደረግ ጥናት ከጭንቀት ውጪ ምንም አያተርፍምና ራሳችሁን በጸሎት አረጋግታችሁ ተፈተኑ::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
የካቲት 27 2013 ዓ.ም

https://www.tg-me.com/yekdset_selase_lejoch
Forwarded from የቅድስት ሥላሴ ልጆች (kiya)
​​#የሳማ_ሰንበት /ደብረ ዘይት/ ቤተ- ክርስቲያን ምን ያህል ያውቃሉ።

እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የደብረ ዘይት ጾመ እኩሌታን በዓል በሳማ ሰንበት ለማክበር አስበናል። በዚህ መንፈሳዊ ጉዞ ተካፋይ የምንሆን ሰዎች ስለ ሳማ ሰንበት ትንሽ ልንላቹ ወደድን።

የሳማ ሰንበት/ደብረ ዘይት/ ቤተ- ክርስቲያን ከአዲስ አበባ በስተ ደቡብ ምስራቅ 110 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የምትገኝ በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ልዮ ስፍራ ሳማ ቀበሌ የሚገኝና በሀገራችን ብቸኛ የሆነ ትልቅ ደብር ነው።

ደብሩ/ገዳሙ/ ከ 300 ዓመት በላይ እንዳስቆጠረ ከገዳሙ የተገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ። የሳማ ሰንበት ቤተ-ክርስቲያን በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ከሚገኙ የቱሪስት መስህቦች ባልጪ አማኑኤል፣ ሸንኮራ ዮሐንስ፣ ዶፋ ሚካኤል፣ አረርቲ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም፣ ጉራምባ ማርያም መካከል አንዱ ነው።

የሳማ ሰንበት ክብረ በዓል በዓመት አንድ ግዜ ማለትም በእኩለ ፆም (ደብረ ዘይት በዓል) የሚከበር ሲሆን በክብረ በዓሉ ላይ ከሁሉም የአገሪቱ ክፍል የሚመጡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ምእመናን ይሳተፋበታል።

ከሃገር ውጭ ያሉ ቱሪስቶችም ይገኙበታል። በፈዋሽነቱ የታወቀ ጸበልም ይገኝበታል።

በሰላም ደርሰን ረድኤት በረከት ተካፍለን እንድንመለስ የእርሱ ቅዱስ ፈቃድ ይሁንልን! አሜን

#ሼር
#እንኳን #ለአቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ_በዓል_በሰላም_እና_በጤና_አደረሳችኹ፡፡
መጋቢት ፭  በዓለ ዕረፍት ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ

አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ (አቦ፥ አቡዬ)፤
* እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ብርሃነ ዓለም የኾኑ፤
* እንደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ጸጋን እና ክብርን የተሞሉ፤
* ኮከበ ገዳም፥ መናኔ ዓለም፥ ምድራዊ መልአክ፤
* ስማቸውን ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ያወጣላቸው፤
* በአክናፈ መባርቅት ተጭነው የሚጓዙ፤
* ፷ አናብስት እና ፷ አናብርት ይታዘዙላቸው የነበሩ፤ የእግራቸው ትቢያ ለአራዊቶቹ ምግብ የኾነላቸው፤
* ለብዙ አእላፍ ቅዱሳን ወላዴ የኾኑ እና በረከትን የሠጡ ታላቅ አባት (ለአብነትም፤ ለቅዱስ #ላሊበላ፥ ለአቡነ #ሳሙኤል ዘዋልድባ፥ ለአባ #አንበስ ዘደብረ ሐዘሎ፥ ለአባ ብንያም ዘግብጽ)
#ምድረ_ከብድ_፤ /ዝ_ምድር_ክቡድ_ውእቱ_/ ፤ #ዝቋላ (#ዝ_ቆላ)
    ምድረ ከብድ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ለመጀመሪያ ጊዜ ያረፉባት ቦታ ናት፤ ቀጥሎ ወደ ደብር ቅዱስ #ዝቋላ (#ዝ_ቆላ) ለጸሎት ሒደው ለሀገራችን ኢትዮጵያ እና ለዓለማችን ምሕረት እና በረከትን ከአምላካችን ለ፻ ዓመታት በባሕር ውስጥ ኾነው ለምነዋል፤

    ወደ ምድረ ከብድ ተመልሰው ለ፯ ዓመታት ጸልየዋል፤ ቊራም በሰይጣን ተመስሎ መጥቶ ዓይናቸውም ቢያጠፋውም ከ፯ ሱባዔያት በኋላ ሊቀ መላእክት ሚካኤል እና ገብርኤል ዓይናቸውን መልሰውላቸዋል፡፡

    ወደ ዝቋላ በመመለስም አጋንንትም ከምድረ ዝቋላ አጥፍተዋል፤ እንደገና ወደ ምድረ ከብድ ተመልሰው በነበሩበት ጊዜ ታላላቆቹ እና በአንበሳ ዘባን ላይ የሚሔዱት #አቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ#አባ_አንበስ_ዘደብረ_ሐዘሎ_አፋር)፣ #አባ_ብንያም_ዘግብጽ ከአባታችን ቡራኬ ለመቀበል መጡ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ተሠውረው ነበርና፤ የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አናብስት የ፫ቱን አባቶች አናብስት በሉባቸው፤ በ፯ኛው ቀን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ተገልጠው የኾነውን ነገር በማየት የተበሉትን አናብስት እንዲመልሱ የራሳቸውን አናብስት አዘዟቸው መልሰውም እንደነበሩ በተዓምራት አስነስተው ሰጧቸው፤ በደመና ጠቅሰው ቅዱስ ፋኑኤል ፫ት ሰማያዊ ኅብስትና ፫ት ጽዋዕ ይዞ ለእንግዶቻቸው ይዘው ሠረገላ በሚባለው ዋሻ አመጡላቸው እና ሰጥተው ሸኟቸው፤ እነዚኾን ቅዱሳን በሸኙ በ፯ኛው ቀን ወደ ተለያዩ ሀገራት ሔደው አስተምረዋል፡፡

    እድሜያቸው ረዥም እንደመኾኑ፤ ቅዱሱ ንጉሥ አፄ ላሊበላን ጨምሮ ሌሎችም ቅዱሳን ወደ ርሳቸው እየመጡ በረከትን ተቀብለዋል፡፡

    #በግብፅ_300_ዓመታት_#በኢትዮጵያ_ምድር_ላይ_262_ዓመታት (በዋነኛነት #በምድረ_ከብድና_በዝቋላ_ ቢኖሩም ሌሎችም የመሠረቷቸው እና የኖሩባቸው ገዳማት አሉ፤ ለአብነትም ደቡብ ወሎ የሚገኘውን #ገዘዛ_አቦን_ መጥቀስ ይቻላል)

    በድምሩ ፭፻፷፪ ዓመታት ከኖሩ በኋላ በንጉሥ ሕዝብናኝ(እንድርያስ) ዘመነ መንግሥት፤ መጋቢት ፭ ቀን ቅዳሜ ለእሑድ አጥቢያ ብዙ ቃል ኪዳንን ጌታችን ሰጣቸው፥ ፲፪ አክሊላትንም አቀዳጃቸው፤ የነበሩባት ምድረ ከብድ ገዳም ግን ራደች፥ ተንቀጠቀጠች፥ በብርሃንም ተጥለቀለች፤ ዝቅ እያለችም መንሸራተት ጀመረች፤ ጌታችንም አንቺ መሬት ኾይ ጽኚ ይኽንን ኹሉ ስለቻልሽ ምድር ክቡድ /ኋላ ምድረ ከብድ/ ተብለሽ ተጠሪ አላት፤ የጻድቁም ነፍስ ከሥጋቸው ከሌሊቱ ፮ ሰዓት ተለየች፡፡

     ይኽችውም ምድረ ከብድ ጻድቁ የኖሩባት እና የቀደሱባት፥ የመሠረቷት እና ያነጽዋት፣ ሠራዊተ መላአክት የከተሙባት፣ ታላላቅ አበው መጥተው በረከት ከአባታችን የተቀበሉባት፣ አርምሞ እና ጸጥታ የማይለያት፤ ዐጸዷና ቅጥሯ ልቡናን የሚመስጥ፤ ከአ.አ ፻፳፭ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ናት፡፡


https://www.tg-me.com/yekdset_selase_lejoch
#ትንሿ_ቤተክርስቲያን
(ቤታችን ውስጥ ያለችው የእናት የአባት እና የልጆች አንድነት፤ ኅብረት)
...የሳምንቱ መልእክታችን

ዓለም ኹሉ በንፍር ውኃ ሲጠፋ ከዚያ ጥፋት የቀረው የኖኅ ቤተሰብ ብቻ ነው - በትንሿ ቤተ ክርስቲያን !

በትንሿ ቤተክርስቲያን በደንብ ሲሠራ ከአንድ ቤተሰብ ብቻ ብዙ ቅዱሳን
ማፍራት ይቻላል፡፡ ለዚህ ጥሩ ማሳያውም የኤስድሮስ ቤተሰብ ነው። ከዚህ ቤተሰብ አምስት ቅዱሳን ተገኝተዋል፡፡ ሦስቱ ሊቃነ ጳጳሳት ናቸው፡፡ ኹለቱ ደግሞ ደናግል መነኮሳት ናቸው፡፡ ከሦስቱም ጳጳሳት መካከል ኹለቱ እጅግ የታወቁ ናቸው - ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ እና ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ !

እንደ ጲስጢስ፣ አላጲስና አጋጲስ የመሰሉ ልጆች ለማፍራት እንደ ሶፍያ የመሰሉ ወላጆች መኖር አለባቸው፡፡ እነዚህ የሚኖሩት ደግሞ ትንሿ ቤተ ክርስቲያን በአግባቡ ስትከፈት፣ ተከፍታም አገልገሎት ስትሰጥ ነው፡፡

ሰንበት ትምህርት ቤቶች ሲመሠረቱ የኢአማንያን ልጆች (ንኡሰ ክርስቲያኖችን) መሠረታዊ የቤተክርስቲያን ትምህርትን ለማስተማር እንጂ የምእመናን ልጆችን ለማስተማር አልነበረም፡፡ የምእመናን ልጆች መሠረታዊ የሃይማኖት ትምህርት መማር ያለባቸው ቤት ውስጥ ነው - ትንሿ ቤተክርስቲያን ውስጥ! ሰ/ት/ቤት መኼድ ያለባቸው ከሊቃውንት ብቻ የሚገኝ ትምህርትን ለመማር ወይም ለማገልገል ነው፡፡ ይህ ግን አሁን እየተደረገ አይደለም፡፡ ለምን? ትንሿ ቤተክርስቲያን ስለተዘጋች፡፡ እንደ ተዘጋች እንኳን የሚያስተውላት በጣት የሚቆጠር ሰው ነው፡፡

ዛሬ ትውልዱ በብዙ ነገሮች እየተፈተነ ያለው ከልጅነቱ አንሥቶ በተግባር የሚማርበት ትምህርት ቤት ስለ ተዘጋበት ነው - ትንሿ ቤተክርስቲያን !

በገጠር አብያተ ክርስቲያናት ተዘጉ ብለን የምንቆጨውን ያህል ስለዚህች ቤተክርስቲያን ብዙ ልናስተምር፣ ብዙ ልንደክም፣ ብዙ ልንለፋ ያስፈልጋል፡፡
በተለይ በተለይ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ይህቺን ቤተክርስቲያን ከተመረቁ በኋላ ለመክፈት ሰፊ ዕድል ስላላቸው ስለ ትንሿ
ቤተክርስቲያን ሰፊ ትምህርትና ግንዛቤ ሊሰጣቸው ይገባል፡፡
©ከመምህር ገብረ እግዚአብሔር ኪደ

@yekdset_selase_lejoch
@yekdset_selase_lejoch
@yekdset_selase_lejoch
Forwarded from የቅድስት ሥላሴ ልጆች (kiya)
ሀገርህም ቤተ ክርስቲያንህም ይፈልጉኻል
▫️▫️▫️▫️▫️▫️▫️
ከማንም በላይ ቤተ ክርስቲያንህ ሰው ሁሉ እኩል መሆኑን አስተምራሃለች፡፡ ቤተ ክርስቲያንህ በመጨረሻው ቀን አድልኦ በማያውቅ ፈታሔ በጽድቅ በሆነ አምላክህ ፊት እንደምትቆም እየነገረች አሳድጋሃለች፡፡ ቤተ ክርስቲያን እውነትን እውነት፣ ሐሰትን ሐሰት ማለት በሰማይ ቤት ያለውን ዋጋ ከልጅነት ጀምሮ እያስታወሰችህ አድገሃል፡፡ አትግደል፣ አትስረቅ፣ አረጋውያን አክብር፣ ወንድምህን እንደ ራስህ አድርገህ ውደድ ወዘተ… እያለች ሰብእናህን ቀርፃለች፡፡ ዓለም እንኳ ወርቃማው ሕግ ያለውን “በአንተ እንዲሆን የማትሻውን በሌላ ላይ አታድርግ፣ እንዲሆንበትም እትፍቀድ” የሚለው ሕግ ምንጭ ቤተ ክርስቲያንህ ናት፡፡
በዚሕ ሕይወት ማለፍ ወደ ልዕልና ጫፍ እንደሚያደርስ እየተማርክ ባደግኸው/ሽው በአንተ/በአንቺ ሚና ፖለቲካውን እንደገና መውለድ ይቻላል፡፡ ፖለቲካው ያንተን ፊት ዐይቶ በማያዳላ አስተሳሰብ የተሞረደ፣ በፈሪሐ እግዚአብሔር የታሸ አስተዋጽኦ ይፈልጋል፡፡ ሀገርህም ቤተ ክርስቲያንህም ይፈልጉኻል፤ ምንም እንደሌለውና እንደማይፈለግ ውጭ ቆመህ አታልቅስ፡፡ ግባና ፖለቲካውን ኢትዮጵያዊ አጨዋወት ዐሳየው፤ ሥነ-ምግባራም አድርገው፡፡ የወደድከው ብቻ፣ የመረጥከው ብቻ እንዲመራህ ምረጥ፣ ተመረጥ፤ ሐቅን ይዘህ በምርጫው ሒደት በጎ ቦታ ይኑርህ፡፡ ሕዝብህን ምራ፣ አስተዳድር፡፡ ሓላፊነት የሚሰማው መሪ ሁን፡፡ ሀገርህም ቤተ ክርስቲያንህም ይፈልጉኻል፡፡ ድምፅህ ለሀገርህም ለቤተ ክርስቲያንህም ይፈልጋታል።
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ
አምላክ አሜን!

#ታላቅ_የንግስ_በዓል_ጉዞ_ወደ_ሳማ_ሰንበት
ቤተ-ክርስትያን

#መነሻ_ቀን፦ መጋቢት 26/2013 ዓ.ም ከቦሌ አራብሳ ሰፈራ ቅድስት ማርያም ቤተ-ክርስትያን ፤

#የጉዞ_መመዝገቢያ_ዋጋ፦ መስተንግዶን ጨምሮ #280 ብር ደርሶ መልስ

#የመመዝገቢያ_ቦታ፦ ቦሌ አራብሳ ሰፈራ ኆህተ ምስራቅ ቅድስት ማርያም ቤተ-ክርስትያን።

#ለበለጠ_መረጃ፦#0922-476538
#0955-400247
#አዘጋጅ_ሐመረ_ኖህ_ሰንበት_ትምህርት_ቤት

ሰላመ እግዚአብሄር ከሁላችን ጋር ይሁን
ከእንቅልፋችሁ ንቁ አይናችሁን ግለጡ እየተባልን ነው
የዐብይ ፆምን ምክንያት በማድረግ
#ታላቅ_የንግስ_በዓል_ጉዞ_ወደ_ሳማ_ሰንበት_ቤተክርስትያን

#መነሻ_ቀን መጋቢት 25/2013
#መመለሻ_ቀን መጋቢት 26 ከሰአት በኃላ

ለመመዝገብ በ 0922_476538 ወይም 0955_400247 በመደወል ተመዝገቡ የቀረን ጥቂት ቦታዎች ብቻ ናቸዉ።
Forwarded from የቅድስት ሥላሴ ልጆች (kiya)
ምርጫና ኦርቶዶክሳውያን
🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔

👉 ለኦርቶዶክሳውያን ሀገራዊ ምርጫ መሳተፍ በ አምስት ምክንያቶች ወሳኝ ነው።

1. የሀገር ባለቤትንት መብታችንን የምናረጋግጥበት ነው።
2. ከፖለቲካዊ ተገላይነት ወደ ፖለቲካዊ ተካታችነት የምንመጣበትን ነው።
3. ብሔራዊ ተደማጭነታችንን ወደ ስፍራው መመለስ አለብን።
4. ለሥርዓታዊ እና መዋቅራዊ ጥቃቶች የዳረጉንን ርዕዮተ ዓለማዊ እና ፖለቲካዊ አሰላለፎችን የምንነቅልበት ነው።
5. ሰብአዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን በተሟላ ፖለቲካዊ ሥርዓት እንዲከበር ያለንን አቅም የምንጠቀምበት ነው።

👉 እንደ አንድ ኦርቶዶክሳዊ የምንመርጠው የፖለቲካ ፓርቲ ወይም ግለሰብ ምንድን ነው ማሟላት ያለበት?

1. በኢትዮጵያዊነት እና በኢትዮጵያ የግዛት አንድነት እና በሕዝብ አብሮነት የሚያምን መሆን መቻል አለበት
2. ለሀገራዊ ዕውቀት፣ ሃይማኖት፣ ትውፊት እና ታሪክ ክብር ያለውና እነዚህንም የፖሊሲው አካል የሚያደርግ
3. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በኢትዮጵያ ማኅበረ ፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ላበረከተችው አስተዋጽኦ እውቅና የሚሰጥ
4. ኦርቶዶክሳዊያንን ከሥርዓታዊ እና መዋቅራዊ ጥቃቶች ለማስቆም ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት ያለው መሆን አለበት።
5. በሕዝብ ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እና ተሳትፎ የሚያምን

👉 እነዚህ መስፈርቶችን እንዴት ነው ማረጋገጥ የምንችለው?

1. የፖለቲካ ፓርቲውን ድርጅታዊ ታሪክ መመርመር
2. የድርጅቶቹን የምርጫ ማኒፌስቶ እና የፖለቲካ ፕሮግራም በአግባቡ እና በጥሞና መመርመር
3. ፖሊሲዎችቸውን መመርመር፣ በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት የፖሊሲ ክርክሮቻቸውን ማድመጥ፣ የፓርቲ መሪዎች ለሚዲያዎች የሚሰጣቸውን ቃለ መጠይቆች፣ ማብራሪያዎች እና መግለጫዎችን መከታተል።
4. ስለ ቤተ ክርስቲያን እና ኦርቶዶክሳውያን ያዘጋጁትን ዕቅድ እንዲያቀርቡ በማድረግ

👉 ከእኛ ምን ይጠበቃል?

1. በእጩነትም ሆነ በመራጭነት በንቃት መሳተፍ።
2. ለእጩነትም ሆነ ለመራጭነት የሚያበቁ መስፈርቶችን ይዘን መገኘት
3. በአስመራጭነት አና በታዛቢነት በንቃት መሳተፍ
4. ፖለቲካ ፓርቲዎች ፕሮግራሞቻቸውን ሲያስተዋውቁ ተገኝቶ መሞገት
5. ኦርቶዶክሳውያን በምርጫ እንዲሳተፉ መቀስቀስ
6. ምርጫውን ከሚያውኩ ማንኛውም ነገሮች ኦርቶዶክሳዊያን መጠበቅ መቻል አለብን።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን።
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡፡ አሜን

በወቅታዊ ጉዳዮች ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
የተሰጠ መግለጫ

“ወበየውሀትክሙ ወበፍርሐተ እግዚአብሔር አሠንዩ ግእዘክሙ-
በቅንነታችሁ እግዚአብሔርን በመፍራት ሁናችሁ ግብራችሁን አሳምሩ፡፡” (1ኛ ጴጥ 3፡16)

ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ከጥንት ጀምሮ የሰው ልጆች ሰላምና አንድነት፣ የሀገር ሉዓላዊነትና የሕዝቦቿን ሁለንተናዊ ደኅንነት እያስጠበቀች ማንኛውም የተፈጥሮና ሰው ሠራሽ አደጋ ሲፈጠር በጾምና በጸሎት በመትጋት ማኅበራዊ ችግሮች እንዲወገዱ ግንባር ቀደም ሆና ስትሰለፍ ኖራለች፤ ሃይማኖታዊና ማኅበራዊ፣ መንፈሳዊና ሕዝባዊ ግዴታዋን በየዘመኑ በመወጣት ሐዋርያዊ ተልእኳን ስትፈጽም ቆይታለች፤ ዛሬም የሚጠበቅባትን ሐዋርያዊና ማኅበራዊ ተልእኮ ለመፈጸም የሚቻለውን ሁሉ እያደረገች ትገኛለች፡፡

እነዚህ ተግባራትም የሚመነጩት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ከጌታችን ከመድኀኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ከተሰጣት ሐዋርያዊ ተልእኮ መንፈሳዊ አደራ ነው፡፡ ይኽ እንደተጠበቀ ሆኖ በአሁኑ ጊዜ በሀገራችን የተከሰቱ የተፈጥሮም ሆነ ሰው ሠራሽ ችግሮች ከዕለት ወደ ዕለት እየተባባሱ ሲሄዱም ቤተ ክርስቲያን የሚጠበቅባትን ከማድረግ አልተቆጠበችም ፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ የቤተ ክርስቲያናችንን አስተዋጽኦ ለመግለጽና ለወደፊቱም የሚጠበቅባትን እንደምትፈጽም ለመግለጽ ያህል በቅርቡ በመላው ሀገራችን በተለይም በሰሜኑ ክፍል የተፈጠረውን ችግር ለመቅረፍ ገና ከጅምሩ በርካታ ጥረቶችን ስታከናውን ቆይታለች ለመጥቀስ ያህል፡-

1. በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ የሰላምና የአንድነት ዐቢይ ኮሚቴ በማቋቋም፣ ከራስዋ ቋት በጀት በመመደብ፣ የማስተማሪያ መመሪያ በማዘጋጀት፣ አባቶችን፣ ሊቃውንትንና ሰባክያንን በማደራጀት በመላው ሀገሪቱ ሁለት ጊዜ የሰላም ሥምሪት አድርጋለች፤

2. በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉበኤ ስለ ሀገር ሰላምና አንድነት፣ ስለመላው ሕዝብ ደኅንነት አጀንዳ ቀርጾ በመነጋገር፤ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የሕዝብ መሪዎች ልዩነታቸውን በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲፈቱ ተደጋጋሚ ጥሪዎችን በማቅረብ ለሰላም፣ ለአንድነት፣ ለፍቅር፣ ለሕዝብ ዘላቂ ትሥሥር እና ለሀገራዊ መረጋጋት የሚጠቅሙ ውሳኔዎችን በመወሰን፣ መግለጫዎችን እና ጥሪዎችን በማስተላለፍ የበኩሏን ተወጥታለች፤

3. የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የተከሰቱ የሰላም ዕጦትና አለመረጋጋት በእግዚአብሔር ቸርነት እንዲፈቱ ሕዝቡ በጸሎትና በምሕላ በአንድነት ሆኖ ወደ እግዚአብሔር እንዲጮኽ መመሪያዎችን በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት በማስተላለፍ በጥንታውያን አድባራት፣ ገዳማትና አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት በአደባባይ ሳይቀር ሊቃውንት፣ ካህናት፣ መነኰሳት፣ ምእመናንና ወጣቶች በአንድነት ያለማቋረጥ ጸሎትና ምሕላ ሲያደርሱ ቆይተዋል፤ አሁንም እያደረጉ ይገኛሉ፤

4. በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዓበይት በዓላት፣ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የመክፈቻና የመዝጊያ መግለጫዎቸ ዓለም አቀፍ ዲፕሎማቶች በተገኙባቸው መድረኮች ሳይቀር እስከ መስከረም 16 ቀን 2013 ዓ/ም በዓለ መስቀልና ጥቅምት 23 ቀን 2013 ዓ/ም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መዝጊያ ድረስ በቀጥታ በመላው ዓለም በሚዲያ ሥርጭቶች የሰላም፣ የአንድነት፣ የመግባባትና ችግርን በውይይት የመፍታት ጥረት እንዲደረግ መግለጫ ሲተላልፍ ቆይተዋል፤

5. ቤተ ክርስቲያናችን በቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በልዑክነት የተሳተፉባቸው በአካል ችግሮች በነበሩባቸው ቦታዎች በመጓዝና በሌሎችም አካባቢዎች በመዘዋወር ልዩነቶች በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት መጠነ ሰፊ ጥረቶች ተደርገዋል፤

6. በኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አስተባባሪነት ከሌሎች የሃይማኖት ተቋማት እና የሀገር ሽማግሌዎች ጋር በመሆን ወደ ለምሳሌ ወደ መቀሌ፣ ባህርዳር፣ ሐዋሳ፣ ኦሮሚያና በኢትዮጵያ ሶማሌ በመሰሉ የሀገራችን ክፍሎች በመጓዝ እንዲሁም አዲስ አበባ ከተማ ላይ ተደጋጋሚ የሰላምና የዕርቅ መድረክ በማዘጋጀት ችግሮችን በተከበረው የሀገራችን የሽምግልና ባህል ለመፍታት ያልተቋረጠ ሥራ ተሠርቷል፤

7. የቤተ ክርስቲያናችን ታሪካውያን ገዳማት አበው መነኰሳት፣ የአብነት መምህራን የሆኑ ሊቃውንት በአንድነት ሁነው ካለባቸው መንፈሳዊ ግዴታ አንፃር በፈቃደ እግዚአብሔር ተነሣስተው መቀሌና ሌሎች አካባቢዎች ድረስ በመሄድ ችግሮችን በሽምግልና ለመፍታት ያለመሰልቸት ጥረት አድርገዋል፤

8. ከብዙ ድካም በኋላም ቢሆን ችግሮቹ ወደ ጦር ሜዳ ሲያመራ በጊዜው የቤተ ክርስቲያናችን መግለጫ በቂ የሚዲያ ሽፋን ባያገኝም ከሌሎች የሃይማኖት ተቋማት ጋር በመሆን ድምጽ አሰምታለች፤

ቤተ ክርስቲያናችን የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነት እና የዘለዓለማዊ ሕይወት መማጸኛ ቤት ናትና ለመላው ሕዝብ መልካም አኗኗር ለኢትዮጵያ ሰላምና አንድነት፣ በጸሎት፣ በምኅላ፣ በትምህርትና በማኅበራዊ ተልእኮ የድርሻዋን ያልተወጣችበት ጊዜ በታሪክ የለም፡፡

ችግር ተፈጥሮ በርካታ ጉዳት ከደረሰም በኋላ ቢሆን በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጅ መመሪያ የጠቅላይ ጽ/ቤቱን ኃላፊዎችን እና መላውን የቤተ ክርስቲያን መዋቅር በማንቀሳቀስ ሁሉን አቀፍ ድጋፍና ሰብዓዊ እርዳታ፣ ትምህርትና መንፈሳዊ ማጽናኛ እንዲደረግ ዓቢይ ኮሚቴ አቋቁማ በመላው ዓለም እየተንቀሳቀሰች ትገኛለች፤

ዛሬም ቢሆን ይኽች ጥንታዊት ታሪካዊትና ዓለም አቀፋዊት ቤተ ክርስቲያን በማንኛውም የሰው ልጅ ችግር ውስጥ የሚጠበቅባትን ታደርጋለች እያደረገችም ትገኛለች፤

ስለሆነም በድጋሜ ማስተላለፍ የምንፈልገው ዓቢይ ጉዳይ ቢኖር መንግሥትና የሀገር ጉዳይ ያገባናል የምትሉ አካላት በሙሉ ለሀገር ሰላምና ሉዓላዊነት፣ ለሕዝብ አንድነትና መተሳሰብ፣ ለዜጎች ሁለንተናዊ ደኅንነትና የሕይወት ዋስትና ቅድሚያ በመስጠት ችግሮችን በሰላማዊ እና በሠለጠነ መንገድ እንድትፈቱ ዛሬም ወደፊትም ለሚሆነው በአጽንዖት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፤

በሀገራችን ልዩ ልዩ አካባቢዎች በአሰቃቂና ኢሰብዓዊ በሆነ መንገድ ሕይወታቸውን እያጡ ያሉ ንፁሐን ዜጎች ሁኔታ አሳሰቢ ስለሆነ መንግሥት ከእስከዛሬው የበለጠ የዜጎች ሕይወት ይጠበቅ ዘንድ ድርሻውን እንዲወጣ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፤

በተለይም መጭው ጊዜ የምርጫ ወቅት በመሆኑ ተፎካካሪ ፓርቲዎችና መንግሥት ከቅስቀሳው እስከ ፍጻሜው ያለው ሂደት በሰላማዊ መንገድ እንዲፈጸም ታደርጉ ዘንድ በድጋሜ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፤

አገራችንን ኢትዮጵያን ለከፍተኛ ዕድገት እንደሚያደርስና ሕዝባችንንም ከዘመናት ድህነት እንደሚያላቅቅ የታመነበት የሕዳሴ ግድብ ፍጻሜ ሊያገኝ እየተቃረበ መሆኑ ይበልጥ ለፍጻሜው ግንባታ እንድንነሳሳ ተስፋ ሰጭ በመሆኑ መላው ዜጎች አሁንም ካለፈው በበለጠ የሚጠበቅብንን ድጋፍ እንድናደርግ የሁላችንንም ርብርቦሽ እንደሚያስፈልግ ቤተ ክርስቲያናችን አሁንም አጥብቃ ታሳስባለች፤

ውድና ክቡር ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን ልዑል አምላካችን እግዚአብሔር ነፍሶቻቸውን እንዲምርልን ለቤተሰቦቻቸውም መጽናናትን እንዲሰጥልን እየተማጸንን በሁሉም አካባቢዎች ንብረት ለወደመባቸው፣ ከመኖሪያ ቀያቸው ለተፈናቀሉና ሰብዓዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው በሙሉ አቅም የፈቀደውን ሃይማኖታዊና ወገናዊ ድጋፍ እንዲደረግ ቤተ ክርስቲያናችን ታሳስባለች፤
🕯• ┈••●◉ ✞✟✞ ◉●••┈ •🕯
                  ሚያዝያ ፲ወ፪
እንኳን ለአቡነ ሳሙኤል ዘቆየጻ (ኢትዮጵያዊ)፣ ለቅዱስ ኤርምያስ ነቢይ፣ ለቅዱስ አቤሜሌክ (ኢትዮጵያዊ)፣ ለቅዱስ ባሮክ እንዲኹም ለቅዱስ እለእስክንድሮስ ዘኢየሩሳሌም ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችኹ 🙏
🕯• ┈••●◉ ✞✟✞ ◉●••┈ •🕯

ዳግመኛም ዛሬ ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት፣ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ፣ ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ፣ ቅዱስ ቴዎድሮስ ምሥራቃዊ ሰማዕት፣ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ፣ አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ እንዲኹም ቅዱስ ድሜጥሮስ ወርኃዊ መታሰቢያቸው ነው 🙏🙏🙏

አምላከ ቅዱሳን በቃልኪዳናቸው ይማረን 🤲 አሜን!
🕯• ┈••●◉ ✞✟✞ ◉●••┈ •🕯

https://www.tg-me.com/yekdset_selase_lejoch
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን

ሠላም የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦች እንደምን ሰነበታችሁ? አሜን ስሙ ለዘለአለሙ የተመሠገነ ይሁን በእለተ ሀሙስ ሚያዝያ 21ቀን 10:30 ላይ ፀሎተ ሀሙስን ምክንያት በማድረግ ውሉደ ብርሀን አና ሐመረ ኖህ ሰ/ት/ቤት አንድ ላይ በመሆን የፀሎት እና የትምህርት መርሀግብር ስላዘጋጀን በአራብሣ ሠፈራ ቅድስት ማርያም እንድትገኙልን በቅድስት ሥላሴ ስም ጠርተኖታል።


ማሳሰቢያ፡ ለብቻ መምጣት ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አይጠበቅምና የኔ ሚሉትን ሠው ይጋብዙ የበረከቱም ተሳታፊ ይሁኑ።

አዘጋጅ የሐመረ ኖህ እና የዉሉደ ብርሀን ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፋሎች📚
Forwarded from የቅድስት ሥላሴ ልጆች (kiya)
#_ታላቅ_የስቅለት_እና_ከሲኦል_ነፍሳትን_የማውጫ_ጸሎት!

ዛሬ አርብ ይህንን ታላቅ ጸሎት ሳትጸልዩ አትዋሉ!

እጅግ ግሩም የስቅለት እና የሁል ጊዜ ጸሎቶ!

ኦርቶዶክሳውያን እባካችሁ ይህንን ጸሎት እየጸለያችሁ አንድ እልፍ /አሥር ሺ/ ነፍሳትን ከሲኦል አውጡ። የመድኃኔዓለም ቸርነት ከምናውቀው መጽሐፍ ቅዱስ በላይ ነው።

አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ይህን ጸሎት ሲጸልዩ ነፍሳትን ከሲኦል በቀን ሰባት ጊዜ በሌሊት ሰባት ጊዜ ያወጡበት ነበር!

ይህ ታላቅ ጸሎት የጌታችንን ሰቅለት እና የደረሰበትን መከራ በሰላምታ የሚያመሰግን ልዩ ጸሎት ነውና ጸልዩት!

በቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

ሼር በማድረግ ለምዕመናኑ አድርሱ፣የቃል-ኪዳኑን በረከት ተቋደሱ!

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ይህን ጸሎት በእግዚአብሔር አጋዥነት እጀምራለሁ፡፡ ኃጢአትን የምታስተሰርይ ንስሐን የምትቀበል በደልን ይቅር የምትል ለኃጥአን ተስፋ የአብ የባሕርይ ልጁና የሕይወት ቃል የዓለምን ኃጢአትን የምታሰተሰርይ የካህናት አለቃ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የእኔ ኃጢአትና የወገኖቼን ኃጢአት ይቅር በል፡፡

ጸሎትና ልመና ወደ እግዚአብሔር ምልጃ ለነፍስና ለሥጋ የሚጠቅም ነው፡፡ በሕይወተ ሥጋ ያሉ ሰዎች ይህንን ጸሎት በሚጸልዩነት ጊዜ አባቶቻቸውን፣እናቶቻቸውን፣ዘመዶቻቸውንና ወዳጆቻቸውን በአንዲት ጊዜ ከሲኦል ያወጡበታል፡፡

የእሾህ አክሊል ጎንጉነው ያቀዳጁሽ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ እራስ ሆይ ላንቺ ሰላምታ ይገባሻል፡፡ ሥጋችንን ለማንጻትና ነፍሳችንን ለመቀደስ እስከ መመታት ደርሰሽ ንጹሕ ደምን አፈሰስሽ፡፡ /ከቤተሰባችሁ የሞቱትን ሰዎች ክርስትና ስም አስገቡና ….. ማርልን ብላችሁ አባታችን ሆይ በሉ …../

ሰይጣን የተፋውን የኃጢአት ምርቅ ከእኛ ለማስወገድ ስለእኛ አይሁድ ርኩስ ምራቃቸውን የተፉብሽ የዓለም ቤዛ የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የከበርሽ ፊት ሆይ ላንቺ ሰላምታ ይገባሻል፡፡ ዛሬም የእኔን ኃጢአት አስወግጂ፡፡ /አባታችን ሆይ በል …../

አላዋቂ በሆኑ በሰቃልያን አይሁድ እጅ በጥፊ የተመታችሁ የዓለም ቤዛ የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጉንጮች ሆይ ለእናንተ ሰላምታ ይገባችኋል፡፡ በእናንተ ምክንያት ፈጽሞ የተዘጋ ገነት ተከፈተ፡፡ እንዲሁም የልቦናዬ በር ፈጽሞ ይከፈትልኝ፡፡ /አባታችን ሆይ በል …./

የነፍሳችንንና የሥጋችንን መድኃኒት ትሰጭን ዘንድ የመረረ ሐሞትና ከርቤ ትጠጪ ዘንድ የወደድሽ የዓለም ቤዛ የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የከበርሽ አፍ ሆይ ላንቺ ሰላምታ ይገባሻል፡፡ እንደዚሁ ለእኔ የሕይወት መጠጥ አጠጪኝ፡፡ /አባታችን ሆይ በል …../

ስለ እኛ በአደባባይ የሞት መስቀልን የተሸከምሽ የዓለም ቤዛ የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የከበርሽ ከፍ ከፍ ያልሽ ክንድ ሆይ ላንቺ ሰላምታ ይገባሻል፡፡ ሁላችን የእጅሽ ፍጥረቶች ነንና የኃጢአቴን ሸክም ተሸከሚልኝ፣የበደሌን ሸክም አቅልይልኝ፡፡ /አባታችን ሆይ በል …../

ስለ እኛ ስለ ፍጥረቶሽ የመስቀል ግንድ የተላከብሽ የዓለም ቤዛ የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልዩ የሆንሽ ጀርባ ሆይ ላንቺ ሰላምታ ይገባሻል፡፡ ዛሬም የኃጢአቴን ግንድ አንሽልኝ፡፡ /አባታችን ሆይ በል …../

የተረገሙ አይሁድ በችንካር ይቸነክሩሽ ዘንድ የወደድሽ የመድኃኒታችን የፈጣሪያችን የኢየሱስ ክርስቶስ የከበርሽ ቀኝ እጅ ሆይ ላንቺ ሰላምታ ይገባሻል፡፡ እንደዚሁ በስንፍናዬ የሠራሁትን በደሌን አጥፊልኝ፡፡ /አባታችን ሆይ በል …../

አስቀድመሽ ስለበደላችን ከሐድያን አይሁድ በችንካር ይቸነክሩሽ ዘንድ የወደድሽ ያለመለወጥ ፍጹም እግዚአብሔር ፍጹም ሰው የሚሆን የመድኃኒታችን የፈጣሪያችን የኢየሱስ ክርስቶስ ግራ እጅ ሆይ ላንቺ ሰላታ ይገባሻል፡፡ እንደዚሁ የእኔን በደል ቸንክሪ፡፡ የሞት ችንካር ከሚሆን ከዲያቢሎስ አድኚኝ፡፡ /አባታችን ሆይ …../

ስለ ኃጢአታችን ክፉዎች አይሁድ ይቸነክሩሽ ዘንድ ፈጽመው ያሰሩሽ የፈጣሪያችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የከበርሽ ቀኝ እግር ሆይ ላንቺ ሰላምታ ይገባሻል፡፡ እንደዚሁ ኃጢአቴን አስተስርይልኝ፡፡ /አባታችን ሆይ በል …../

በእውነት የታመነ እውነተኛ ቅን ንጉሥ የሚሆን የዓለም ቤዛ የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የከበርሽ ግራ እግር ሆይ ላንቺ ሰላምታ ይገባሻል፡፡ ያለ በደል በቅዱስ መስቀል ላይ ተቸነከርሽ፡፡ እንዲሁ ኃጢአቴን ቸንክሪልኝ፣የበደሌን መጽሐፍ ደምስሽልኝ፡፡ /አባታችን ሆይ ……/

ኃጢአታችንን የምንታጠብበትና የምናተሰርይበት ውኃና ደምን ከጎንሽ እስከምታፈሺ ድረስ በመስቀል ላይ ሳለሽ በጦር ጎንሽን የተወጋሽ የጌታችን የአምላካችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልዩና የከበርሽ ጉን ሆይ ላንቺ ሰላምታ ይገባሻል፡፡ ተዘግቶ የነበረው የሰማይ ምስጢር ባንቺ ምክንያት ተገለጠ፣ተከፈተ፡፡ እንደዚሁም ሁሉ የልቤ በር ይከፈትልኝ፡፡ /አባታችን ሆይ በል …../

በመስቀል ላይ መከራን ለተቀበሉ ለጌታችን ለፈጣሪያችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ አካላት ሁሉ ሰላምታ ይገባቸዋል፡፡ የጌቶች ጌታ፣የንጉሦች ንጉሥ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ላንተ ክብር ምስጋና ይገባሃል፡፡ በታላላቅ ችንካሮች ይቸነክሩህ ዘንድ ለእኛ ስትል የወደድክ ዛሬም በፍቅርህ ትቸነክረኝ ዘንድ እለምንሃለሁ፡፡ ከእኛ ጋር መከራን ስለተቀበልክ እኛም ካንተ ጋር መከራን እንቀበላን፡፡ በመስቀል ላይ የተቀበልከው የመከራህ ተሳታፊዎች አድርገኸናልና በመከራ ስለመሰልንህ እንደዚሁ በጌትነትህ በምትመጣበት ጊዜ በዕለተ ምጽአት ከአገልጋዮችህ ከቅዱሳን ጋራ ክብርን አድለን፡፡ /አባታችን ሆይ በል ……/

ታዖስ ወዖ አልፋ ቤጣ የምትባል ጌታዬ ኢየሱስ ክርቶስ ሆይ የባሕርይ አባትህ አብ መጠግያ ኃይል ይሁነኝ፡፡ እግዚአብሔር ዕድል ፈንታዬ ጽዋዕ ተርታዬ ነው፡፡ አቤቱ እንደ ቸርነትህ ጎዳናዬን አስተካክልልኝ፡፡ አንተ ለወደድከው መራራው ከማር ወለላ ይልቅ ጣፋጭ ይሆናል፡፡ እኔም ይህን እወደዋለሁ፡፡ እግዚአብሔር ሆይ አንተን መውደድ ስጠኝ፡፡ ፈጣሪዬ አስመልክተኝ፣አስተዋይ ልቦና ስጠኝ፣ፈጣሪዬ ጥበበኛ አድርገኝ፣ፈጣሪዬ አድነኝ፡፡ በውስጥና በውጭ ያለው የሚታየውንና የማይታየውን አበሳ የምታውቅ አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ አውግዮን፣ አውሎግሶን ልቦናዬንና ሰማያዊውን ቤት ክፈትልኝ፣ዐይነ ልቦናዬንም አብራልኝ፡፡ ኃጢአቴንም ይቅር በለኝ፡፡ .አባታችን ሆይ …../

መሐሪ የሆን አምላክ ሆይ፣ ይቅር ባይ አምላክ ሆይ፣ ቸር አምላክ ሆይ የእኔን የበደለኛውን ኃጢአት ይቅር በል፡፡ /አባታችን ሆይ በል/

ዓለም ሳይፈጠር አስቀድመህ የነበርክ ዛሬም ያለህ ዓለምን አሳልፈህ የምትኖር የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ልባቸው አብ ሆይ ላንተ ሰላምታ ይገባሃል፡፡ ዓለም ሳይፈጠር አስቀድመህ የነበርክ ዛሬም ያለህ ዓለምን አሳልፈህ የምትኖር የአብ የመንፈስ ቅዱስ ቃላቸው ወልድ ሆይ ላንተ ምስጋና ይገባሃል፡፡ ዓለም ሳይፈጠር አስቀድመህ የነበርክ ዛሬም ያለህ ዓለም አሳልፈህ የምትኖር የአብና የወልድ ሕይወታቸው እስትንፋሳቸው መንፈስ ቅዱስ ሆይ ላንተ ስላምታ ይገባሃል፡፡ /ሦስት ጊዜ በል/ አቤቱ ፈጣሪዬ ሥጋዬንና ነፍሴን ባርክ፡፡ አባቴ ፈጣሪዬ ሕይወቴንና ሞቴን ባርክ፡፡ አቤቱ ፈጣሪዬ ጸሎቴንና ልመናዬን ባርክ የእኔን የኃጥኡን የ ……….. /አባታችን ሆይ በል ……./

ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የሚያስጨንቅ ለአንተ ቀላል ነው፡፡ የራቀ ላንተ ቅርብ ነው፡፡ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ይቅርታህን ከእኔ አታዘግይብኝ አታርቅብኝ፡፡ የሚያደንቁህን ክፍ ከፍ አድርጋቸው፡፡ ላንተ ቀላል
Forwarded from የቅድስት ሥላሴ ልጆች (kiya)
ነውና ኃጢአቴን አስተስርይልኝ አንተ መከራ በደሌን ይቅር በለኝ፡፡

እግዚአብሔር ፈጣሪዬ ሆይ በሦስትነትህ ተማፀንኩህ፣ በትክክል ሥልጣንህ ተማፀንኩህ፣ በአንድነትህ ተማፀንኩህ፣ አንተን በወለደችህ በድንግል ማርያም እናትህ ተማፀንኩህ፣ በቅዱስ መስቀልህ ተማፀንኩህ፣ በምትወደው በወዳጅህ በቅዱስ ዮሐንስ ተማፀንኩህ፣ አንተን በአጠመቀህ በቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ተማፀንኩህ፣ መልአከ ምክርህ በሆነ በቅዱስ ሚካኤል ተማፀንኩህ፣ ያንተን መወለድ ለድንግል ማርያም የደስታ ብሥራትን በነገራት በቅዱስ ገብርኤል ተማፀንኩህ፣ እኔ ኃጢአተኛው በወዳጅህ በእስትንፋሰ ክርስቶስ ተማፀንኩህ፡፡ የእኔንም የሕዝቡንም ኃጢአት ይቅር በል፡፡ /አባታችን ሆይ በል ……/

የዚህች ጸሎት ክብር ፈጽሞ በሰማይም ቢሆን በምድርም ቢሆን አይገኝም፡፡ በአምላክ ልቦና፣ በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ በጸናች አምላክን በወለደች በድንግል ማርያም ልቦና፣ በደጋጎቹ በጻድቃን፣ በሰማዕታት፣ ፍጹማን በሚሆኑ በመነኮሳት፣ በደናግል ልቦና፣በተመረጡ በዘጠና ዘጠኙ ቅዱሳን መላእክት ልቦና፣ በቅዱስ ሚካኤልና በቅዱስ ገብርኤል ልቦና ይገኛል እንጅ፤እነርሱም ይህችን ጸሎት በጸለዩ ጊዜ ሁለት መቶ አርባ ሺህ ነፍሳትን ከሲኦል ያወጣሉ፡፡ እመቤታችን እግዝእትነ ማርያምም በየዕለቱ ፵፻፼ ነፍሳትን ታወጣለች፡፡ ንስሐ የገባ ኃጢአተኛ እንኳን በጸለየባት ጊዜ አንድ እልፍ ነፍሳትን ያወጣል፡፡ ይህችን ጸሎት አታወጣም ብሎ የሚጠራጠር ቢኖር መንግሥተ ሰማያትን አያያትም፡፡ /አባታችን ሆይ በል ……/

ተወዳጆች ሆይ ይህንንታ ታለቅ ጸሎት ዘወትር ብትጸልዩት በሥጋ ላላችሁ ለእናንተም እንዲሁም ንስሐ ሳይገቡ፣ቅዱስ ቁርባን ሳይቀበሉ ለሞቱ ቤተሰቦቻችሁና ወገኖቻችሁ ትተርፉበታላችሁ፡፡ ከሲኦል ሲወጡን አምላከ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ በሕልም ክብራቸውንና ያሉበትን ቦታ ያሳያል።

ምንጭ፦ የታላቁ የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ የሐሙስ ገድል ገጽ 39 ቁጥር 1 እስከ ገጽ 43 ቁጥር 19!
2025/02/22 14:52:49
Back to Top
HTML Embed Code: