Telegram Web Link
Forwarded from የቅድስት ሥላሴ ልጆች (kiya)
በባታችን ሰቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ገፅ 39 - 43 ያለው ፀሎት በማለት ሲፀልዩ ነፍሳትን በቀን 7 ጊዜ በሌሊት 7ጊዜ ያወጡ ነበር። አቡነ ዘበሰማያት ከሰላመ ገብርኤል ከእቀበኒ ጋር ሲጸልይ 24 እልፍ ነፍሳትን ከሲኦል ያወጣሉ።

ይህችን ፀሎት አታወጣም ብሎ የሚጠራጠር ቢኖር መንግስተ ሰማያትን አያያትም።
https://www.tg-me.com/yekdset_selase_lejoch
https://www.tg-me.com/yekdset_selase_lejoch
Forwarded from የቅድስት ሥላሴ ልጆች (kiya)
ቶ መስቀል እና የሰለ(የ)ጠነው አለም/ Ankh and modern world/

ከዚህ ቀደም በየ ድህረ ገፁ የተለጠፉትን ስለ ቶ መስቀል የሚገልፁ ፅሁፎች ከራሳችን እሳቤ ጋር በማዛመድ ፅፈንላችሁ ነበር። አሁን ደግሞ ከቤተክርስቲያን ስርአት አንፃር ያለውን ለቀንላችኋል። ሀሳባችሁን ሰብሰብ፣ አዕምሯችሁን ከፈት አድርጋችሁ አንብቡና፤ ለጓደኞቻችሁ #ሼር አድርጉላቸው።

የዳቢሎስ ማህበርተኞች በአንገታቸው፣ በልብሶቻቸው፣ በቦርሳቸው፣ በንቅሳት መልክ ሲጠቀሙበት ይስተዋላል። እንደ እውነቱ ከሆነ የቶ መስቀልን እውነተኛ ምንነት መናገር እጅግ ከባድ ነው። ነገረ ግን በሰለጠነው ዘመን ፓጋኖች ምልክታየው አድርገው ሲጠቀሙበት ይስተዋላል። ክርስቶስ የተሰቀለበትን መስቀልም ቢሆን ይጠቀሙበታል። እንዲያውም በጆሮ ጌጥ እና በልብስ ማድረግ አንሷቸው በጫማ ሶል ላይ ያደርጉታል።

ክርስቶስ በወንጌሉ ዮሐ 6:47 "በኔ የሚያምን የዘለአለም ህይወት አለው" ይላል። ታዲያ የዘለአለም ህይወት ቁልፉ ቶ መስቀል ወይስ ክርስቶስ??

የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮችን በማጭበርበር ወደ ገሀነም መንገድ መምራት የጀመሩት ማህበረ ስላሴ ዘደቂቀ ኤልያስ የተሰኘው ማህበርም ቶ መስቀልን የማህበሩ መለያ አድርገውታል። አንድ በዚህ ማህበር ዋና አባል የነበሩ አባትም ከስህተታቸው ታርመው ወደ እናታቸው ቅድስት ቤተክርስቲያን መመለሳቸውን በማህበረ ቅዱሳን ቴቪ/EOTC/ ላይ ተናግረዋል።

ከአንድ ኦርቶዶክሳዊ የዩቲዩብ ቻናል የተለቀቀ ቪድዮ ላይ ደግሞ አባ ተስፋ ስላሴ ሞገስ፣ መሪ ራስ አማን በላይ እና ፕ/ሮ ፍቅሬ ቶሎሳም ስለ ቶ መስቀል በስፋት የተናገሩ ሲሆን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በሚለው ሳይሆን ተዋህዶ በሚለው ብቻ የሚያምኑ ግለሰቦች ነበሩ ይላል። ነገር ግን የታሪክ መፅሀፎቻቸውን ሪፈር ማድረግ የለብንም ማለት አይደለም። እውነት የሆነውን ታሪክ በማስረጃ እንቀበላለን።

ልብ የምትሉት ግን ሰይጣናዊ ማንነት አለውም እያልኩ አይደለም። ምክንያቱም አሁን ትልቅ ውዝግብ እየፈጠረ ያለው ይኼው ጉዳይ ነው።

ገላትያ 6:14 "አለም ለኔ ከተሰቀለበት እኔም ለአለም ከተሰቀልኩበት ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት የለም" ይለናል። ህይወታችን ክርስቶስ ነው። ትምክህታችንም በ34 ዓ.ም በእለተ አርብ በቀራንዮ አደባባይ የተሰቀለበት መስቀል እንጅ 3000 B.C ላይ በግብፃውያን ዘንድ የነበረው "ቶ" አይደለም። "ኢትኤል ቆ በትርን ወንድሙ ሀሙኤል ቶ በትርን ይይዙ ነበር" የሚለውን ታሪክ እንቀበላለን። ነገር ግን በትረ መንግስት እንጅ የድህነት ምልክት እንዳልሆነ በዘመኑ የነበሩት እነ ኢትኤል ይመሰክራሉ።

ፊልጵስዩስ 3:18-20 "ብዙዎች #ለክርስቶስ #መስቀል #ጠላቶች ሆነው ይመላለሳሉና ብዙ ጊዜ ስለ እነርሱ አልኳችሁ፤ አሁንም እንኳ እያለቀስኩ እላለሁ #መጨረሻቸው #ጥፋት ነው ሆዳቸው አምላካቸው ነው፤ ክብራቸው በነውራቸው ነውና፤ #ሀሳባቸው #ምድራዊ ነው እኛ #ሀገራችን #በሰማይ ነውና፤ ከዚያም ደግሞ የሚመጣ መድሀኒትን እርሱንም ጌታን ኢየሱስ #ክርስቶስን #እንጠባበቃለን።"

ክርስቶስ የተሰቀለበትን መስቀል በቶ መስቀል ለውጣችሁ አንገታችሁ ላይ ያደረጋችሁ፤ የድሮውን የድህነት ማዕተብ አድርጉ፤ ቶ መስቀልንም አውልቃችሁ አስቀምጡ። ቶ መስቀል ታሪካዊ ማንነት እንደሚኖረው ግልፅ ነው። ሀይማኖታዊም ማንነትም ይኖረው ይሆናል። መቼም ቢሆን ግን ክርስቶስ የተሰቀለበትን መስቀል አይተካም ዶግማ ነውና።

ሁሌም ቢሆን አባቶች ከእኛ ይበልጣሉና "መታዘዝ ከመስዋዕት ይበልጣል" የሚለውን እናስታውስ።

አዋጅ አዋጅ አዋጅ! ያልሰማህ ስማ የሰማህ ላልሰማ አሰማ!

https://www.tg-me.com/yekdset_selase_lejoch
https://www.tg-me.com/yekdset_selase_lejoch
https://www.tg-me.com/yekdset_selase_lejoch
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ(አንድ) አምላክ አሜን::

እንኳን ለጾመ ነብያት (ለገና ጾመ) ፣ ለጾመ አዳም ፣ ለጾመ ስብከት ፣ ለጾመ ሐዋርያት ፣ ለጾመ ፊልጶስ ፣ ለጾመ ማርያም እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን!::

የጾመ ነብያት የሳምንት ስያሜዎች:-

* ከኅዳር ፮ 6 እስከ ፲፪ 12 => አስተምህሮ (ጾመ የለውም (ያለ ጾመ ያለፈ))

በጾመ ነብያት ጊዜ የሚውሉት ሳምንታት ባጠቃላይ ፯ (7) ናቸው:: እነርሱም:-
* ከኅዳር ፲፫ 13 እስከ ኅዳር ፲፱ 19 => ቅድስት (የመጀመሪያው እሁድ ሳምንት ሱባኤውን የምናገኝበት)
* ከኅዳር ፳ 20 እስከ ኅዳር ፳፮ 26 => ምኩራብ (አምላካችን እየሱስ ክርስቶስ የሃይማኖት ቃል ያስተማረበት)
* ከኅዳር ፳፯ 27 እስከ ታህሳስ ፫ 3 => መጻጉ (ሰው የለኝም የሚል ትርጉዋሜ አለው)
* ከኅዳር ፬ 4 እስከ ፮ 6 => ደብረ ዘይት
* ከታህሳስ ፯ 7 እስከ ፲፫ 13 => ዘመነ ስብከት
* ከታህሳስ ፲፬ 14 እስከ ፳ 20 => ዘመነ ብርሃን
* ከታህሳስ ፳፩ 21 እስከ ፳፯ 27 => ዘመነ ኖላዊበ; መባል ይታወቃል::
የተቀሩት ቀናት÷ ታህሳስ ፳፰ (28) አማኑኤል ታህሳስ ፳፱ (29) ልደት በመባል ይታወቃል::

ይምራን ይቆየን
Forwarded from የቅድስት ሥላሴ ልጆች (kiya)
† ጾመ ነቢያት ፡ [ የገና ጾም ]
#Ethiopia | ዛሬ - ኅዳር 15 ቀን ተጀምሮ እስከ ልደት ለአርባ ሦስት ቀናት የሚጾም ጾም ነው
† - ከ7ቱ አጽዋማት (ዐቢይ ጾም፣ ጾመ ፍልሠታ፣ ጾመ ሐዋርያት፣ ጾመ ነቢያት፣ ጾመ ድኅነት፣ ጾመ ነነዌ ና ጾመ ገሃድ) መካከል አንዱ ነው፡፡
ይህ ጾም የእግዚአብሔርን ሰው መሆን ሲጠባበቁ የኖሩት ትንቢትና ጸሎት በጌታችን መወለድ ፍጻሜ ያገኘበት ወቅት በመሆኑ «ጾመ ነቢያት (የነቢያት ጾም) » እየተባለ ይጠራል።
ለአዳም የተነገረውን የድኅነት ተስፋ ስለ ተፈጸመበትም «ጾመ አዳም (የአዳም ጾም)» ይባላል። ስለ እግዚአብሔር ሰው መሆን በስፌት ትምህርት ወንጌል የሚሰጥበት ወቅት በመሆኑም «ጾመ ስብከት (የስብከት ጾም)»፤ የጾሙ መጨረሻ (መፍቻ) በዓለ ልደቱ በመሆኑ ደግሞ «ጾመ ልደቱ (የልደት ጾም)» በመባል ይታወቃል።
ይህንን ጾም በዘመነ ብሉይና በዘመነ ሐዲስ ብዙ ቅዱሳን ጾመውታል፤ በዚህም ምክንያት የሚከተሉት ስያሜዎች አሉት፡፡ እነርሱም፦
† ፩. ጾመ አዳም፦
አዳም ዕፀ በለስን በልቶ ከገት ከተባረረ በኋላ; በፈጸመው በደል አዝኖ ፥ ተክዞ፤ አለቀሰ (እንባ ቢያልቅበት እዥ እስከሚያፈስ፤ እዥ ቢያልቅበት ደም በዓይኑ እስከሚፈስና ዓይኑ ይቡስ ወይም ደረቅ እስከሚሆን ድረስ አለቀሰ) ፥ ጾመ፣ ጸለየ፡፡ ከልብ የሆነ ጸጸቱን፣ ዕንባውን፣ በራሱ መፍረዱንም እግዚአብሔር አይቶ ተስፋ ድኅነት ሰጠው፡፡ ‹‹ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ፣ በደጅህ ድኼ፣ በዕፀ መስቀል ተሰቅዬ፣ ሞቼ አድንሃለሁ፡፡›› የሚል ነው፡፡ /ገላ. ፬፥፬፣ መጽ.ቀሌምንጦስ/ ስለዚህ ጾሙ የተሰጠው ተስፋ ፥ የተቆጠረው ሱባኤ ስለተፈጸመበት ‹‹ጾመ አዳም›› ይባላል፡፡
† ፪. ጾመ ነቢያት፦
ነቢያትም የምሥጢረ ሥጋዌ ነገር ተገለጦ ስለታያቸው፣ ክርስቶስ ለሰው ልጅ የሚከፍለውን የፍቅር ዋጋ በትንቢ
@yekdset_selase_lejoch
@yekdset_selase_lejoch
ሐመረ ኖኅ ሰንበት ት/ቤት
ይህ ቻናል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን በቦሌ አራብሳ ሰፈራ ኀህተ ምስራቅ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ሐመረ ኖኅ ሰ/ት/ቤት የተመሰረተ ቻናል ነው።
#ቻናሉ
•ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ጋር የተያያዙ የተለያዩ ፁሁፎችን እና መረጃዎች ይቀርቡበታል።
•ሰ/ት/ቤቱን የሚደግፍ የተለያዩ ሀሳብ አስተያየት ወይም ዉይይት ለማድረግ @kiya17 @dhwbm11 ያናግሩንየ፨
https://www.tg-me.com/hamernoh
ሐመረ ኖህ ሰንበት ት/ቤት አዲስ ያሰፋዉ የአገልግሎት አልባስ
https://www.tg-me.com/hamernoh
Forwarded from የቅድስት ሥላሴ ልጆች (kiya)
ሰላም የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እደምን ቆያቹ?

ትንሽ ነው ጨርሰን እናንብበው ለንተም ላንቺም ለሀገራችንም ለቤተክርስትያን ጠቃሚ ነው።
👇👇👇

አሁን ስላለንበት ወቅታዊ እና ነባራዊ ሁኔታ ጥቂት ልበላቹ። አሁን በዚህ ባለንበት ወቅት ሀገራችን ቅድስት ኢትዮጵያ ስላሟ እና ጤናዋ ታውኮ ፡ ፍቅሯ ደብዝዞ ፡ ጠላት እና መናፍቅ እየፈነጨባት ነው። እቺም ቅድስት ምድር ንጹሀን ልጆቿን በማያውቁት እና ኦርቶዶክስ ወይም code name ( አማራ ) በማለት እየተገደሉ እሷም ወደ ሆዷ እያስገባች ነው።

ለምንድነው ይሄ የሆነው?

1- ትንቢት ነው። የኢትዮጵያ የመከራዋ ትንቢት የተነገረው የዛሬ 500 አመት ነው። ግን ይሄን ትንቢት በአንዴ አልተሰጣትም በዮዲትጉዲት ፡ በአህመድ ግራኛ ፡ በጣልያን ፡ ደርቡሽ ፡ በእንግሊዞች , , , , በእንደነዚህ ጊዜያቶች እየተቀነሰ ተሰጥቷታል። አሁን ግን የዚህ ትንቢት ፍጻሜው ነው። እዴት ለሚል? ልብ ያለው አሁንም ቢሆን ያየዋል። ልብ ያላለ ግን ሲደርስበት ያየዋል።

ፍጻሜው እንዴት ነው ቢሉ፡ በአባቶች እንደተመገረው በሀገራችን በ2 ሀያላን እና በ7የሀረብ ሀገራት የሚመራ የጦር ሀይል እደሚገባ እና ባለ ማህተቤውን እና ቤተከርስትያን ተኮር ጥቃት አይቀሬው እደሆነ አስገንዝበዋል። ይሄን ለማያምን ግልጽ የሆነ ማስረጃ አለ ያውም በሚዲያ በቲቪ የተላለፈ። ከታች ተመልከቱት።

2- የአለም መሰረት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት እና የአባቶቻችን እና የእናቶቻችን በጥበብ እና በፈሪሀ እግዚአብሔር የተመሰረተ ስለሆነ ነው።

የምድር ጥበብ በአባታችን አዳም በኩል ተሰጥቶ በጥበብ እና በሀያልነት የገዢነት እና የበላይነት እዳለን ስለምያውቁ እና እርግጠኛም ስለሆኑ የምዕራቡ ሀገራት እቺን የከበረች ሚስጥራዊ ሀገር ካላጠፉ እንቅልፍም አይወስዳቸም። ግን አይሆንላቸውም።

3- ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት እውነተኛዋ እና ፍጹም የሆነች እምነት ናት።ስለዚ ጠላት ዳቢሎስ ለሰከንድም ቢሆን አይተኛላትም የክፋት ድግስ ሲደግስ ነው ሚውለው ሚያድረው።

4- አፍሪካን እስላማዊ ሀገር ማድረግ።
ይሄስ እንዴት ነው ቢሉ? የአረቦች የ100 አመት እቅዳቸው ነው። አፍሪካን እስላም ሀገር የማድረግ። ይሄም እዳይሆን ማነቆ የሆነችባቸው ይችው ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ ናት። ስለዚ ያላቸው አማራጭ ማጥፋት ነው። ለዚ ተብሎ የተመደበው ብር ይዘገንናል የአለም ህዝብ እያንዳንዱን ለተወሰን አመታት ዘና አድርጎ የሚያኖር ነው።

ለምድነው ግን አለም እንዲ ያተኮረባት? መልሱ ቀላል ነው እኛ ያላየነው እነሱ ያዩት ነገር አለ ማለት ነው። እሱን አንድ ቀን እናወራታለን።


ታድያ እኛ ምን እናድርግ?

ቀላል ነው። ንስሀ ፡ ጸሎት ፡ ፆም ፡ ስግደት ፡ ቅዱስ ስጋው ክቡር ደሙን መቀበል።

በስሜ የተጠሩት ሕዝቤ ሰውነታቸውን አዋርደው ቢጸልዩ፥ ፊቴንም ቢፈግሉ፥ ከክፉ መንገዳቸውም ቢመለሱ፥ በሰማይ ሆኜ እሰማለሁ፥ ኃጢአታቸውንም ይቅር እላለሁ፥ ምድራቸውንም እፈውሳለሁ።
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 7 : 14

ይሄን ምናደርገው ለመትረፍ ሳይሆን ክርስትያናዊ ግዴታችንም ነው። አንድ ክርስትያን ከነዚህ ውጪ ከሆነ ክርስትያን ሊባል አይችልም። እነኚህን ቱርፋቶች አድርገን ብንሞት ደማችን ደመ ሰመዕት ይሆንልናል። ከተረፍንም ከዚ ሁሉ መአት ሚያተርፈው እግዚአብሔር ነውና መትርፊያ ቦታዎች ገዳማት አሉ የመረጣቸውን ትዕዛዛቱን ህጉን የጠበቁትን ያተርፋቸዋል ያድናቸዋል።

ሩቅ አደለም ቅርብ ነው። አይናችን ገልጠን አይናችን የታወረብን አይናችንን እንግለጥ። መልዕክቴ ነው።

ሚኪያስ
እኛም ልብ ብለን ሌላውም ልብ እዲል #ሼር እናድርገው ቢይንስ አንድ ሰው ንስሀ ሲገባ በሰማይ ትልቅ ደስታ ይሆናል ይሄን እያሰብን ለወገኖቻችን እንድናጋራ በትህትና እጠይቃለው። 🙏🙏🙏
https://www.tg-me.com/yekdset_selase_lejoch
https://www.tg-me.com/yekdset_selase_lejoch
Forwarded from የቅድስት ሥላሴ ልጆች (kiya)
#ትንቢተ_ኢትዮጵያ

#በ1212 ጀርመን የሚገኝ ብራና መጽሀፍ
ነፍሳቸውን ይማርና አለቃ ታምሩ በኢትዮጵያ ከሰሩት ታላላቅ ሥራዎች አንዱና ዋነኛው ነው።

ትንቢተ-ኢትዮጵያን በ 1212 በግዕዝ የተጻፈውን ወደ አማረኛ በ1949 ዓ/ም ተርጉመው ማተማቸው ነው።

#1ኛ,……#ጊዮርጊስ በፈረስ ሆኖ አድዋ ላይ ይዋጋል።
እውን ሆኖል።

2ኛ,በቋራ አንበሳ ተነፈሰ >> ይልና የአጼ ቴዎድሮስን መምጣት ቀድሞ ትንቢቱ ተናግሮል።

3ኛ, ዘመነ ጎንደር እያለቀ ንግሥናው ወደ ሽዋ ሊመጣ ሲል < ፋሲል ግንብ የቁራ ማደሪያ ይሆንል ይለዋል።

4ኛ, ስለ ንጉሥ አጼ ኃይለስላሴ ደግሞ <<... ፈረሳቸው ሳይቀር ይከዳቸዋል >> ይላል።

5ኛ, ልጅ ኢያሱን ያወሳል ።

#ኢያሱን ላለመካድ መኳንንቶች ተማምለው ነበር።
በኃላ ግን እሱን ክደው የጣይቱ ብጡልን ወንድም ራስ ጉግሳ ገድለው። በዚህ የተነሳ መኮንንቱና ተፈሪ መኮነን << ጥቁር ውሻ ይውልዳሉ.. >> ይላል ፣ ይህ ደግሞ የመንግሥቱ ኃይለማርያምን መምጣት ቀደም ብሎ ተናግሮል ። ታዲያ በዚህ ዘመን << ወላድ እናት ደረቶን ትመታለች ይላል።

6ኛ<<ከስሜን መረብን ከተሻገሩ ዝም በሎቸው >> አባይንና ተከዜን ከተሻገሩ በኃላ ግን እርስ በርሳቸው ይተላለቃሉ >> ይላል ።

ትንቢት ስለ እንቶኔ እሱም እንዲህ ይላል
“ይሄ መንግስትም እንደ አመድ ቡን ብሎ ይጠፋል:: ብዙዎቹም ሀብታቸውን እንኳን የትም ይዘው ለመሄድ እድሉን አያገኙም:: “ምነው” የሚሉበት ግዜም ይመጣል:: ኤርትራውያንም ኢትዮጵያ ውስጥ እህል ውሃ አላቸው ።

ግፍ የሰሩ ሰዎችም “ምነው” ብለው እስኪጸጸቱ ድረስ ፍርዳቸውን ይቀበላሉ ይላል ።
ትንቢት ከውድቀት በኋላ
“በዚያን ግዜ የአህዛብ ንጉስ ይነግሳል:: ለቤተ ክርስትያንና ለክርስትያኖችም መልካም ያልሆነ ግዜ ይሆናል።
ደም ይፈሳል፣ ብዙ በዳር ሀገር ያሉ ክርስትያኖች መክራ ያገኛቸዋል፣ ሰማዕትነት ይቀበላሉ፣ ትልቅ ክብርም ያገኛሉ፣ ከሰማዕትነት ይቆጠርላቸዋል ። ብዙ ወጣቶችም ይሄን ክብር ይቋደሳሉ:: እንደ ቅዱስ ጊዮርጊስ እንደ ቅዱስ መርቆርዮስ ሰማዕትነት ይቆጠርላቸዋል። የኑሮ ውድነቱም የከፋ ይሆናል:: የኤድስ በሽታም የሚመሰገንበት ግዜ ይመጣል:: ኤድስ ምናልባትም ለንስሓ ግዜ የማይሰጥ አጣድፎ የሚገድል በሽታ ሳይሆን አይቀርም የሚቆመው መንግስት ለዓለም መንግስታትም ያስቸገረ ይሆናል:: ነገር ግን ስለ ቅዱሳን ጸሎትና ምልጃ እድሜው አጭር ይሆናል”

#ትንቢት_ስለ_ንጉሥ_ቶዎድሮስ
” ኢትዮጵያን በዘንግ አርባ አመት የሚገዛ ንጉሥ( ቶዎድሮስ ይሉታል) ይነግሳል። የሚነሳውም ከምስራቅ ነው:: በሱ ዘመን ስደት ወደ ኢትዮጵያ ይሆናል። አንድ እንጀራ ለአስር ሰው ያጠግባል። በሱ ዘመን እንኳን የሰው የንጨት ጠማማ አይኖርም፣ ኤርትራም ወደ እናት ሀገሯ ትመለሳለች:: ፍቅርና አንድነት ይሆናል:; ኢትዮጵያ እጅግ ታላቅ ሀገር ትሆናለች::በሱ ዘመን የሚነሱትም ፓትርያርክ እጅግ የበቁና ገቢረ ተአምር የሚያደርጉ ይሆናሉ:: “በዚህ ሰው ንግሥና ዘመን በኢትዮጵያ ፍጹም ሰላም ይሆናል:: በሀገሪቱም በረከት ይዘንባል:: ከሌላው ሀገር ተለይታም የጥጋብና የበረከት ሀገር ትሆናለች:: የበርካታ ሀገር ስደትኞችንም የምታስተናግድ የስደተኞች መጠለያና ማረፍያ ትሆናለች:: ለዘመናት ደም ሲቃቡ የነበሩት ኤርትራና ኢትዮጵያም አንድ ይሆናሉ:: ሁለቱ ወንድማማች ህዝቦች ወንድማማችነታቸውን አድሰው በሰላም በፍቅር ይኖራሉ::

በዛ ዘመን የሚሾሙትም ፓትርያርክ ሕዝብን ከአምላኩ የሚያስታርቁ : ሀገርን በጸሎት የሚጠብቁ ተአምር የማድረግ ጸጋ የተሰጣቸው ትልቅ አባት ናቸው።

ሼር

ጥያቄ አስተያየት👇👇
@frye18
@frye18


https://www.tg-me.com/yekdset_selase_lejoch
https://www.tg-me.com/yekdset_selase_lejoch
https://www.tg-me.com/yekdset_selase_lejoch
Forwarded from የቅድስት ሥላሴ ልጆች (😰😱😨😣😤😬😣😕😐😯) via @like
ኢትዮጲያ ግን እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር እምትዘረጋበት ቀን እጅግ ቀርቧል:: አሁን የጦር ዛቻ እያየንበት ያለው መዘዘኛው አባይንም በተመለከተ በአንድ በኩል እንደሚያጋድለን በትንቢቱ :~
" አባይ ደፈረሰ ጣናንም ያ'ሙታል:
እንዳትከተሉት ሙት ይዞ ይሞታል" ብለው: ሼህ ሁሴን ተናግረውለታል::

ወደፊት ምን እየተካሄደ እንዳለ እንኳን እንደዚህ ሀሳብ እምንለዋወጥበት እድል እማይኖርበት ግዜ ይመጣል::ዛሬ የተጋራነው ሀሳብ በመጭው ግዜ ትዝታ ይሆናል :: የብሔርና የሃይማኖት ጦርነት የተነሳ ግዜ ያኔ ሁሉ እንዳልነበር ይሆናል:: ከዚህ እሚያድነን አንድ እና አንድ መፍትሄ አሁንም ዛሬ ላይ ሆነን ተግተን እምናረገው ፀሎት እና የእግዚያብሔር ምህረት እንጂ የታጠቅነው የጦር መሳሪያ አይደለም::

አባ ዘወንጌል ስለ አንበጣውም ሆነ ስለጦርነቱ ተናግረውት ያለፉትን ከዚህ ትንቢት ጋር እሚጋራውን ብዙ ነጥቦች አስታውሱ::

ይህን ፖስት ያረኩት የቅርብ ሩቁን ነገን እያሰብክና/እያሰብሽ ጭንቀት ውስጥ ገብተህ/ሽ መኖር እንድታቆም/ሚ አይደለም::ይልቁንም ግዜው እየጠበበ እየጠበበ እንደሄደ አስተውለን ቦታው
ላይ ሲደርስ የተዘጋጀ ልብ እንዲኖረን :ግዜው
እንደ ወጥመድ ድንገተኛ እንዳይሆንብን መጭውን አውቀን ህፀፃችንን እያረምን ራሳችንን እያስተካከልን በፀሎት ከመፃኢው መከራ አትርፎ ለትንሳኤዋ ዘመን እንዲያበቃን እየተማፀንን ኑሮዋችንን እንድንቀጥል ነው::

ምክንያቱም የኛ አይን መጨፈን እሚሆነውን ከመካሄድ አያስቆመውም : ጆሮዋችንን መድፈን እሚነገረውን ከመነገር አይከለክለውም::ይልቁንም አውቀነው መፀለያችን ነገሩን እንደነነዌ ያረግልናል ሊያስቀርልን ይችላል::"

እግዚአብሔር የኢትዮጲያችንን መከራ ያሳጥርልን :ከመፃዒው ጥፋትም ያድንልን!
መድሃኔአለም ኢየሱስ ክርስቶስ ከዘላለም እስከዘላለም ያው ነው:: መንገድም እውነትም ህይወትም መድሃኒትም እርሱ ነው!!! ወደርሱ እንመለስ ።

አንባቢ ሆይ ሼር በማረግ ግዴታህን ተወጣ

https://www.tg-me.com/yekdset_selase_lejoch
https://www.tg-me.com/yekdset_selase_lejoch
https://www.tg-me.com/yekdset_selase_lejoch
እንኳን ለመዳህኒአለም ወርሃዊ በአል አደረሰን
አስፈሪው የኢትዮጲያ ቀን!!!
ትንቢተ ኢትዮጲያ!

ካልጨረሳችሁ አትጀምሩ

ራሺያ በምስራቅ :ጀርመን እና ጣሊያን በሰሜን : የአረብ ጦርም ሁሉ ወደ ኢትዮጲያ
ይገባል: ምድሯን ባዶ ያረጋል!

ቅዱስ መፅሃፉ ደግሞ ይህን ይላል :~
"እናንተ ኢትዮጲያውያን ደግሞ በሰይፌ ትገደላላችሁ::እርሱም በሰሜን ላይ እጁን ይዘረጋል::..."
ትንቢተ ሶፎኒያስ 2(12)

ምን ያህሎቻችን እንዳስተዋልን ባላውቅም
በ2017 ላይ RT ኒውስ :~
** አፍሪካውያን የውጪ ጦር ሰራዊት ወደ አሃጉራቸው ያስገቡ ግዜ ትልቅ ተሸናፊዎች ይሆናሉ!
ብሎ የዘገበው በወቅቱ ቀልቤን የያዘውን ዘገባ አሁን ላስታውሳችሁ ግድ አለኝ::ይህ ለሚገባው ትልቅ ማንቂያ ደውል ነው::

እሚያስፈራው መስዋዕትነት ቢጠይቅም
በትንቢቱ ላይ ስለ ወያኔ :~
የአስመራ ጦርነት ሲጀመር ወያኔ
ይሞታል ተብሎ የተፃፈለት በርግጠኝነት
በኢትዮጲያ ጦርመደምሰሱ የማይቀረው ዛሬ ላይ ያለው የህወሓት ሰራዊት ሳይሆን: ሊፈፀም እየተቃረበ ያለው ትንቢት ላይ የተፃፈው ጥምር የውጪ ጦር በሰላም ማስከበር ስም ወደፊት መግባት እና በቅርብ የሚሆነው የኢትዮጲያ ትንሳኤው ቅድመ መከራ ነው::

ይህ የወያኔ እና የኢትዮጲያ ጦርነት ጥቅምት እንደሚጀምር የተናገረው የሼህ ሁሴን ትንቢት እንደተባለው አሁን ከህወሀት ጋር የተጀመረው ጦርነት ጥቅምት መሆኑ ስናይ ትንቢቱ ዝንፍ አለማለቱን ልብ ያለው ልብ እንዲል ከዚህ ቀደም ፖስት አድርጌው ነበር::

በብልፅግና ወንጌል የሰከሩ በየቸርቹ የፈሉ 2013 የሰላም ግዜ ነው እያሉ እግዚአብሔር ያላላቸውን በስሙ እየዋሹ ከአባታቸው ከዳቢሎስ የሆነ ሆነብሽ ሆነልህ እያሉ ዛሬም ድረስ እማያስተውለውን መንጋ አሜን እያስባሉ እሚነዱ የሀሰት ትንቢት ሲነዙ የነበሩ የመንደር ውርጋጦች አንድም ትንቢታቸው በስህተት ሲፈፀም አላየንም: ይልቁንም ይሄኛው ቃል በቃል ሲሆን እያየነው ነው::

ቅዱስ መፅሃፉም ትንቢትን አትናቁ ሁሉን ፈትኑ
እንዳለ ማሰብ ግድ ይለናል::በክርስቶስ ያላመነው ቀያፋም የተናገረው ትንቢት መፈፀሙን አንዘንጋው::ቀጣዩ ምጥ በቅርቡ ወደፊት ወያኔ በእባባዊ ፍኖቱ ዘርቶት የሄደው የጎጠኝነት መርዝ የብሄር ፖለቲካ :ለሁሉም ግዜ አለውና በጊዜው ሲገነፍል :

ለማናችንም የማይጠቅመው አሁን ላይ ቆሞ ለመራመድ ድክድክ እያለ የታዘብነው የእርስ በእርስ በዘር የመባላታችን ነገር ለይቶለት የጀመረ እለት የሚሆነው ሀገራዊ መዳከምና ለውጪ ጥንተ ጠላቶቻችን ለነጮቹ: ለአረቦቹ (ለግብፅም )ይሁን ወይ ድርቡሽ: ወይ ለአሸባሪው አልሻባብ እና አይሲስ ይሁን ለሌላ የሚያደርገው በር መክፈት ነው::

**********************
**********************
ልክ በትንቢቱ ላይ እንደተፃፈው ሁሉ:~
ይህ ሰበብ በርግጠኝነት አሸባሪነትን ለመደምሰስ ሰላም ለማስከበር በሚል ሰበብ ኢትዮጲያ ውስጥ እነ ራሺያ : አረብ ኢምሬትስ ጀርመን እና ጣሊያን እንዲገቡ እና ሀያላኑ ሀገራት እስካሁን በሶሪያ:የመን:አፍጋኒስታን: ሊቢያ እና ሌሎችም ላይ ሀገር ሲያፈርሱ ምድራዊ ገሀነብ ሲፈጥሩ እንዳየነው የራሳቸውን ሀገር ላለመጉዳት በሰው ሀገር እየገቡ የጡንቻቸውን ልክ የሚያሳዩበትን መንገድ ይከፈታል::ለዚህም RT news
የነጮቹን አላማ ፍንጭ ቀድሞ ነግሮናል:
ማገናዘብ የኛ የአፍሪቃውያኑ ፋንታ ነው::

የትንቢቱን እውነተኝነት የምትጠራጠሩ
እስኪ ራሺያ እስከዛሬ ያላረገችውን ከቅርብ ግዜ ወዲህ አሁን ላይ የጦር ሰፈርዋን ለማቋቋም ከሱዳን በቅርቡ የተስማማችው ለምን ይመስላችሁዋል?
ይህ ትንቢት መፈፀሚያው ባይደርስ ነው?
አሜሪካና ቻይና ዱባይስ/አረብ ኢምሬትስ/ በምፅዋ: በጅቡቲ እና በበርበራ /ሱማሌ ወደብ ዙሪያ ከ3 በላይ የጦር ሰፈር እየገነቡ የከበቡን ለምን ይመስላችሁዋል?

በኢትዮጲያ ውስጥስ አይተነው በማናቀው ሁኔታ ተከባብሮና ተዋዶ ሲኖር የነበረው ወንድማማች ህዝብ ተጨካክኖ በማይካድራ በጉሊሶ በመተከል ወዘተ ሲቀራደድ የባእዳኖቹ በተለይም የግብፅ ስውር እጅ እገዛ ባንድም ሆነ በሌላ መልኩ የሌለበት ይመስላችሁዋል?

ይህንን የሚሊተሪ ቤዝ/ጦር ሰፈር ከቦን ስናይ እንዴት ነው አይተን እማናውቀው አይነት አደጋ ከፊታችን እንደተጋረጠ እማይሸተን::ከታች ፖስት የተደረጉትን ዜናና ምስሎች አስተውሏቸው::ከዚህ ቀደም ፖስት ካደረኩት የትንቢቱ ክፍል በዚ ትንቢት ተፅፎ እስካሁን በእድሜያችን ያየነው ስለ ቻይና: ስለ ወያኔ : ስለአስመራ : ስለወልቃይት ...ወዘተ አሁን ድረስ የተፃፈው መፈፀሙን እስካየን ድረስ ቀጣዩም እንደሚፈፀም ጥርጥር የለውም::

ይህ ደግሞ በትንቢቱ እንደተፃፈው ኢትዮጲያን ከሶሪያ ያልተናነሰ ቀውስ ውስጥ ከቶ ይገድላታል:ብዙ ልጆቿ ጥለዋት ይሰደዳሉ: ብዙ ደም ይፈሳልም::ይህ ሁሉ ግን እሚሆነው :ዛሬ ላይ ያለው መንግስት የፈጠረው ችግር ስለሆነ አይደለም::ዛሬ ላይ ባለው የዶ/ር አብይ መንግስትም ቆይታ ላይ ላይሆንም ሊሆንም ይችላል::ብቻ ወደፊት ማንም እቺን አገር ቢመራ ሊሆን ያለው ከመሆን ስለማይቀር ነው::

ምክንያቱም በክርስትና እምነትም/በፍካሬ ኢየሱስ/ ሆነ በእስልምና ይፈፀም ዘንድ የተባለለት :ከአምላኳ ጉያ ርቃ እማታቀው ኢትዮጲያ ዛሬ ስለፋነነች ለዚህም የእግዚአብሔር የቁጣው ሰአት ስለደረሰ :~በክፋት በጭካኔ
በመከዳዳት: በገንዘብ ወዳድነት :በአስማት በሌዝቢያን እና በጌይነት: እየተዘፈቀ በሁሉ ቅጥ አጥቶ ከፈሪሀ እግዚአብሔር እየተለየና

ከፈጣሪ መንገድ እያፈነገጠ ሃዋሪያው ጳውሎስ ለጢሞቲዮስ በፃፈው 2ተኛ መልእክት 3ተኛ ምእራፍ ላይ የተዘረዘረውን የሃጥያት አይነት ሙሉ ለሙሉ እያሟላ
የሄደው እና የከፋው የኛ ዘመን ትውልድ ላይ ቅጣቱ ሊሆንበት ይህ ትንቢት ሊፈፀም ግድ ስለሆነ ነው::
ምናልባትም በምህረቱ ቢያስበን ሁላችንም ራሳችንን ልንመረምር እና ከፈጣሪ ልንታረቅ ግድ ይለናል::

ለቁጣ የታዘዙት ባእዳን ከላይ በጦራቸው እየደቆሱ ከታች ሀብቷን በሰበቡ ሊቦቡጡ ለጡትዋ እንደ መዥገር ሊሆኑ ልጆችዋን በጦርነትና ስደት ሊጨርሱ ከፈጣሪም የተሰጣቸው ግዜ ያልቅና ኢትዮጲያ ተመልሳ እንደምታገግም ከዛ በሁዋላ እንደምትባረክም እንዲሁ በሌላ ቦታ ተፅፎላታል:: ስለ አጥፊዎችዋ መግቢያ ግን በትንቢቱ ይህ ተነግሯል :~

በምስራቅ ኢትዮጲያ በሀረርጌ በኩል የሚገባው የራሺያ ጦር እንደሆነ
በሰሜን የሚመጣው ብዙም ሳይቆይ የሚመለሰው የጀርመንና ጣልያን ጦር::
**ሌላው ደሞ አረብ ኢምሬትን ጨምሮ የያዘ የ7 አረብ ሀገራት ጥምር 1 ጦር ወደ ኢትዮጲያ ይገባል::

ምእራባዊያኑ ሲቪል ዋር እያሉ በየሚዲያዎቻቸው እየለፈፉ የጦር ነጋሪት እሚጎስሙብን ዛሬ ላይ መንግስት ነገሩን
ተቆጣጥሮ ማረጋጋት ቢችል ራሱ : ነጮቹ ግን
መተራመሳችንን አጥብቀው የሚሹት ነገር በመሆኑ በዛም በዚህም ብለው ነገሩን ወደፊትም ቢሆን ከመፈጠር ወደሁዋላ አይሉም::

ኢትዮጲያ ሞታ እምትነሳበት እየመጣ ያለው ግዜ ከባድ ይሆናል::ሀያላኑ ሀገራት ሶሪያን ግራና ቀኝ አቅማቸውን ሲፈታተሹ ዱቄት አድርግዋት እንደሄዱ ኢትዮጲያንም ቀጣይዋ ሶርያ ከማረግ ወደ ሁዋላ አይሉም::
ይህን ክፉ ጊዜ እሚያሳጥረውም ይትረፍ ያለውንም የሚያተርፈው የእግዚያብሔር ምህረት እና ፀሎታችን ብቻ ነው::ይህን እውነታ መዋጥ የማንፈልግ ካለን መጭውን ሁላችን አብረን የምናየው በመሆኑ አይይሳስብም።
https://www.tg-me.com/yekdset_selase_lejoch
Forwarded from የቅድስት ሥላሴ ልጆች (kiya)
ሰላም የቅድስት ሥላሴ ልጆች በሙሉ
ከአሁን ሰአት ጀምሮ ስለ covid 19 ክትባት እና ስለ microchip መነጋገርም ሆነ መወያየት የምትፈልጉ አባላት በግሩፓችን 👉 @enamsgen እና እኔንም በግል ማናገር የምትፈልጉ 👉 @frye18 ማናገር ትችላላችሁ።
ሙሉ መረጃዉን ዛሬ ማታ ይለቀቃል።

ድንግል ማርያም ከልጆዋ ታስታርቀን
አሜን
#ኮድ_11

ከምስሎችህ ሁሉ

ከኢየሱስ ክርስቶስ ከምስሎቹ ሁሉ
ከቤቴ ግድግዳ ከተሰቃቀሉ
እኔን የሚገርመኝ
በቤተልሔሙ በከብቶቹ ግርግም
ከእናትህ ማህፀን ከድንግል ማርያም
በአጭር ቁመት
በጠባብ ደረት ተወስነህ አዝነህ
ስትመጣ አይደለም

ከኢየሱስ ክርስቶስ ከምስሎቹ ሁሉ
ከቤቴ ግድግዳ ከተሰቃቀሉ
እኔን የሚገርመኝ

ዮሴፍ ከሚባለው ከቅዱስ ዳዊት ዘር
ከእናትህ ከእናቴ ከእመብርሀን ጋር
ሽሽት ነበርና ከሄሮድስ ወታደር

በዚያ በበረሀ በፀሀይ ሀሩር
ለህዝቦችህ ሁሉ ባሳየኸው ፍቅር
የስደትህ ምስሉ እንደሱም አይደለም

ከኢየሱስ ክርስቶስ ከምስሎቹ ሁሉ
ከቤቴ ግድግዳ ከተሰቃቀሉ
እኔን የሚገርመኝ

በዮርዳኖስ ባህር በቅዱስ ዮሐንስ
በ ፴ አመትህ ተጠምቀህ ስትፈውስ
አብ ከሰማይ ሆኖ ቃሉን ሲተነፍስ
መንፈስ ቅዱስ በእርግብ ተመስሎ
ከቤቴ ግድግዳ ጥግ ላይ ተስሎ
የሚገኘው አይደለም

ከኢየሱስ ክርስቶስ ከምስሎቹ ሁሉ
ከቤቴ ግድግዳ ከተሰቃቀሉ
እኔን የሚገርመኝ


መራራ ሀሞት የጠጣበት
በመስቀል ላይ የዋለበት
ለሰው ልጆች የሞተበት
እሱ ምስልም አለኝ
እኔን ግን አያስገርመኝ


ከኢየሱስ ክርስቶስ ከምስሎቹ ሁሉ
ከቤቴ ግድግዳ ከተሰቃቀሉ
እኔን የሚገርመኝ


ከቤቴ ግድግዳ መሀል ላይ የዋለው
ኢየሱስ ክርስቶስ ከበሬ የቆመው
ክፈት ልጄ እያለ እያንኳኳ ያለው
ከምስሎቹ ሁሉ ይሄ ነው ሚገርመው


እንደው ክርስቶስ ሆይ ብከፍት ምንትል ይሆን
ከሀጢያቴ ብዛት ቅዱስ ሰው የማልሆን

"ና ልጄ ወደኛ "
ወይስ " ሀጢያተኛ "
" ና ወደ ገነት "
ወይስ" ሲዖል ውሰዱት "

እባክህ ጌታዬ እኔን ይቅር በለኝ
ከልጆችህ መሀል አንድ ልጅ አድርገኝ
ከሲዖል ሳይሆን ከገነት እንድገኝ!!!

#kiya

Join & share
👇👇👇👇
@sinekal
@sinekal
@sinekal
ሰላም የቅድስት ሥላሴ ልጆች
ይህንን መንፈሳዊ ግጥም በ linku በመግባት like በማድረግ እንድትተባበሩኝ
ወንድም እህቶች ከላይ ያለዉን ግጥም like በማድረግ እንዳሸንፍ አርዱኝ
የእያንዳዳቹ ድጋፍ ዋጋ አለዉ 👍

አመሰግናለሁ
ሰላም የሐመረ ኖህ ሰንበት ት/ቤት አባላት🙏

ነገ የጌታችን የመዳህኒታችን የእየሱስ ክርስቶስ በአለ ልደቱን በሰንበት ት/ቤታችን በደማቅ ሁኔታ ስለምናከብር ማንም የ ሰ/ት/ቤቱ አባላት እንዳንቀር አሳስባለ።

መልካም በአል🙏
#ጌና_እና_ልደት

ጌና እና ልደት ዋዜማ እና ክብረ በዓል /የተለያዩ ቀናት/ ቢኾኑም ከቅርብ ጊዜያት ወዲኽ ግን ጌና ልደትን እየተካ እንጠቀምበታለን፤ ነገር ግን ይኽ ሊስተካከል ይገባዋል፡፡ ልዩነት ስላለውም የኢትዮጵያ ብርሃን የተባለው አፈ ጳዝዮን አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ለጌና እና ለልደት ለ፪ቱም በዓላት ለየብቻቸው በመጽሐፈ ምሥጢር ድርሰት ደርሶላቸዋል፡፡
#ጌና፤ የልደት በዓል ዋዜማ ቀን ሲኾን በዚኽ ቀን ‹‹በገና ጨዋታ አይቆጡም ጌታ›› የተባለለትን ‹‹የገና ጨዋታ›› እንጫወታለን፤ የምንጫወትበት የኳሱ ስያሜ ‹‹ሩር›› ሲባል ስያሜውን ያገኘው፤ ሰብአ ሰገል እልፍ እልፍ ሠራዊት አስከትለው የተወለደውን አይሁድ ንጉሥ ፍለጋ ወደ ንጉሡ ሔሮድስ ደርሰው ነበርና፤ ሔሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ፈልጎ እና በውስጡ ሸሽጎ ለሰብአ ሰገል "ሒዱ ሕፃኑን ፈልጉ ስታገኙትም ንገሩኝ" ብሎ ሰድዷቸዋል፤ ነገር ግን በዚያው ሳይነግሩኝ እንዳይሔዱ በማለት እነርሱ ሳያውቁ ‹‹ሩር›› የተባለ ሰላይ በመሃላቸው አስገብቶ ነበርና ሰብአ ሰገልን ይመራቸው የነበረው ኰከብ ተሠውሮባቸዋል፤ ሰብአ ሰገል ሠራዊታቸውን ቢያጣሩ ከመሃከላቸው የተቀላቀለ ሩር የተባለ የሔሮድስን ሰላይ አገኙ ይኽንንም ሰላይ የሰብአ ሰገል ሠራዊት አንገቱን በሰይፍ ቀልተውታል እና ያን ለማስታወስ ዛሬ በገና ጨዋታ ላይ ሩር የተባለው ኳስ የሔሮድስ ሰላይን ‹‹ሩር›› እንዲያስታውስ አባቶች ሥርዓትን ሠሩ፡፡

#ልደቱ_ለእግዚእነ_ኢየሱስ_ክርስቶስ
#‹‹#ቤዛ_ኵሉ_ዓለም_ዮም_ተወልደ::›› /#ቅዱስ_ያሬድ/

ጌታችን ለሰው ልጆች ብሎ፤ የሰው ልጆች ፍቅር አገብሮት ንጽሕት እና ቅድስት ከኾነች ከእመቤታችን ያለ ወንድ ዘር በመጋቢት ፳ወ፱ ተጸንሶ ታኅሣሥ ፳ወ፱ በ፩ ዓ.ም. (ዓለም ከተፈጠረ፥ ዘመን ከተቈጠረ በ፶፻፭፻ ዓመት) በበረት ተወልደ፡፡ ሰማይ እና ምድር የማይወስኑትን በረት ቻለው፤ ወሰነውም በሌሊት መንጋቸውን የሚጠብቁ እረኞች ነበሩ፡፡ መልአኩ መጥቶ እንዲኽ አላቸው፡- ‹‹እነኾ! ለሕዝቡ ኹሉ የሚኾን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለኹና አትፍሩ፤ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኀኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የኾነ ተወልዶላችኋልና፡፡ ይኽም ምልክት ይኾንላችኋል፤ ሕፃን ተጠቅልሎ በግርግምም ተኝቶ ታገኛላችኹ›› አላቸው፡፡ ሉቃ2፡10-12፡፡ ከመልአኩም ጋራ ሠራዊተ መላእክት መጥተው ‹‹ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ለዕጓለ እመሕያው ሥምረቱ /ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይኹን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ/›› አሉ፡፡ ቅዱሳን መላእክትም ከእነርሱ ተለይተው ወደ ሰማይ በወጡ ጊዜ እረኞቹ እርስ በርሳቸው ‹‹እንግዲኽ እስከ ቤተ ልሔም ድረስ እንሒድ፣ እግዚአብሔርም የገለጠልንን ይኽን የኾነውን ነገር እንይ›› ተባባሉና ፈጥነው መጡ፡፡ ማርያምን እና ዮሴፍን ሕፃኑንም በግርግም ተኝቶ አገኙ፡፡ አይተውም ስለዚኽ ሕፃን የተነገረላቸውን ነገር ገለጡ፤ የሰሙትን ኹሉ እረኞቹ በነገሯቸው ነገር አደነቁ፤ የብርሃን እናቱ እመ አምላክ ግን ይኽን ነገር ኹሉ በልቧ እያሰበች ትጠብቀው ነበር፡፡ ሉቃ ፪፡፲፫-፲፱፡፡
መላእክትም ሰማይ መንበሩ ምድር የእግሩ መረገጫ የኾኑለት አምላክ በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወስኖ በጎል ተኝቶ በጨርቅ ተጠቅልሎ አይተውት ደስ ብሏቸው ወደ ሰማይ ቢያርጉ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በዕሪና ከመንበሩ አይተውት ‹‹ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት›› ብለው አመስግነውት በጣዕም ላይ ጣዕም፤ በጸጋ ላይ ጸጋ ተጨምሮላቸው ደስ ብሏቸዋል፡፡ ልደቱን ይሹታልና፤ መላእክትም ብቻ አይደሉም እንስሳትም አራዊትም ደስ ብሏቸዋል፡፡ #ይህም_ሊታወቅ_አንድ_ባሕታዊ_በቋራ_/_ኋላ_ማኅበረ_ሥላሴ_ገዳም/_ቋርፍ_ሲምስ_ቶራ_ሚዳቋ_ዮም_ተወልደ_ መድኀኔ_ዓለም_ዮም_ተወልደ_ቤዛ_ኵሉ_ዓለም_ዮም_ተወልደ_ከሣቴ_ብርሃን እያለች ስትዘል አይቷል። በጌታችን በልደቱ የባሕር ውኃ ወተት እና ማር ተራሮች እንጀራ እንጨቶችም የበረከት ፍሬ ሆነዋል፡፡ ልደቱንም በኮከብ ተረድተው ሰብአ ሰገል (የጥበብ ሰዎች) ስማቸውም ማንቱሲማር፣ ሜልኩ በዲዳስፋ የተባሉ የፋርስ ነገሥታት ከገነት የተገኘ ወርቅ፣ ዕጣን ከርቤ አምጥተው ገብረውለታል፡፡ /ዘኅ ፳÷፲፯፡፡
‹‹ሰው ሆይ! ፈጽመኽ ደስ ይበልኽ፣ እግዚአብሔር ዓለሙን ወዶታልና አንድ ልጁንም የሚያምንበት ኹሉ እስከ ዘለዓለም ፈጽሞ ይድን ዘንድ አሳልፎ ሰጥቷልና ልዑል ክንዱን ሰደደልን፡፡››

https://www.tg-me.com/yekdset_selase_lejoch
2025/02/23 05:52:44
Back to Top
HTML Embed Code: