Telegram Web Link
Forwarded from የቅድስት ሥላሴ ልጆች (kiya)
ከቀብር መልስ

ከቀብር መልስ እጅህን ታጥበህ ተስተናግደህ ታውቃለህ? ንፍሮስ ቀምሰህ ታውቃለህ? ንፍሮውን ስትበላ እኔ እንደማደርገው ሽንብራ ሽንብራውን ለቅመህ በልተህ ስንዴውን ለሌላ ሰው ትመርቃለህ ወይስ ሁለቱንም ትበላለህ? በሆድህ "ለምንድን ነው ግን ጨዉን የሚያሳንሱት" እያልክ ተመራምረህ ይሆን?

እኔ ደግሞ ዛሬ ከቀብር መልስ ካልጠፋ እህል ስንዴ ለምን እንደሚቀርብ ልነግርህ ነው:: ነገሩ ባሕል ብቻ ሳይሆን ሃይማኖትም ነው::

ከቀብር መልስ በንፍሮ መልክ የምንበላው ስንዴ ኀዘንተኞችን የሚያጽናና ትልቅ መልእክት ይዞአል::

ቀብረን ከተመለስን በኁዋላ ስንዴ ስንበላ የንፍሮውን ጣዕም ማሰላሰል ትተን ይህንን የጌታችን ቃል እናስታውስ :-

"እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የስንዴ ቅንጣት በምድር ወድቃ ካልሞተች ብቻዋን ትቀራለች፤ ብትሞት ግን ብዙ ፍሬ ታፈራለች" ዮሐ 12:24

ክርስቶስ ስንዴ የሚያፈራው ሞቶ በምድር ሲቀበር ነው ብሎ ስንዴን ለእኛ ሞትና ትንሣኤ ምሳሌ አድርጎታል:: ቀብረህ ስትመለስ በእጅህ የዘገንከው ስንዴ ቀብረኸው የመጣኸው ወንድምህ ትንሣኤ እንዳለው እየነገረ ያጽናናሃል:: በምድር የወደቀ ስንዴን ያልረሳ አምላክ የሞተውን አይረሳም::

ቀብረነው መጣን ብለህ አትዘን:: ዘርተኸው እንደመጣህ አስብ:: በመዋረድ ብትዘራውም በክብር ይነሣል:: በድካም ብትዘራውም በኃይል ይነሣል:: ለመበስበስ ብትዘራውም ባለመበስበስ ይነሣል ይልሃል ሐዋርያው (1 ቆሮ 15:42-43)

ነፍሳችን ከሥጋችን በተለየች ጊዜ በምድር አስከሬናችን ይቀራል:: አስከሬን (በግሪክ ስክሪኒዉም) ኮሮጆ መያዣ ማኅደር ማለት ነው:: "ንዒ ማርያም ለእግዚአብሔር አስከሬኑ" "የእግዚአብሔር ማደሪያው ማርያም ሆይ ነይ" እንዲል:: የነፍሳችን ማደሪያ የሆነው ሥጋ ከአዳሪዋ ነፍስ ሲለይ አስከሬን (ማደሪያ) የነፍስ ሳጥን የሚል ስም ይሠጠዋል:: ሬሳ የሚለው ቃል የበሰበሰ ነገር ምሥራቃውያኑ የቡድሃና ሂንዱ ተከታዮች ሥጋን የነፍስ እስር ቤት አድርገው ስለሚያምኑ ሥጋ ሲቃጠል ነፍስ ነፃ ይወጣል ብለው አስከሬን ያቃጥላሉ:: በዳግም ሥጋዌ (reincarnation) የሚያምኑ በመሆናቸውም አንድ ሰው ድጋሚ ሲፈጠር የተሻለ አካል ይዞ እንዲወለድ አሮጌው ሥጋው መቃጠል አለበት ብለው ያስተምራሉ::

እኛ ግን እንቀብራለን እንጂ በፍጹም አስከሬን አናቃጥልም:: የሚቀበር ነገር ዋጋ ያለውና በኁዋላ የሚፈለግ ነገር ነው:: ገንዘብ የምትቀብረው ሌላ ጊዜ ልታወጣው ካሰብክ ነው:: የምታቃጥለው ግን የማትፈልገውን ነው:: የምንቀበረው እንደምንወጣ ስለምናምን ነው:: የመለከት ድምፅ ሰምተን እንደምንነሣ ተስፋ ስላለን ምንም ብንሞትም በተስፋ እንቀበራለን:: እንደምንበቅል ተስፋ አድርገን እንዘራለን:: ሌላው ቢቀር በእሳት ተቃጥለን ብንሞት እንኳን አመዱንምና የከሰለውን አጥንትም ቢሆን በተስፋ እንቀብረዋለን::

"የሙታንን መነሣት ተስፋ እናደርጋለን የሚመጣውንም ሕይወት ለዘለዓለሙ አሜን!"

#ዲያቆን_ሄኖክ_ኃይሌ
ቻናላችንን ለመቀላቀል ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑት
👇👇👇👇👇👇👇
https://www.tg-me.com/yekdset_selase_lejoch
Forwarded from የቅድስት ሥላሴ ልጆች (kiya)
ትችት 👉 በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ

"መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከንቱ ንግግርን ማስወገድ እንዳለብን ሲነግረን፦ 'ሰዎች ስለተናገሩት ከንቱ ንግግር መልስ ይሰጡበታል' ብሎናል። (ማቴ 12፥36)

ከንቱ ንግግር ማለት ፌዝ፣ ቧልት፣ ሥላቅ ሲሆኑ እነዚህም ትችት፣ ነቀፋ፣ አሽሙር አዘል መልእክት ያላቸው ናቸው። ከእነዚህ ዋነኛው ትችት ነው። ከጦዘ ወንጭፍ ላይ በቅጽበት ተወንጭፎ ነፍሳትን እንደሚያጠፋ ድንጋይ (ሩር) እንዲሁ የትችት መንፈስ ከተዋረሰው ሰው አንደበት የሚወጡ ቃላት ስሜትን የሚጎዱና ሕሊናን የሚያቆስሉ ናቸው።

ምናልባት ይህ የትችት መንፈስ የተጸናወተው ሰው ትችቱን በለሰለሰ ቃላት ሊያብራራው ቢችልም እንኳ ንግግሩ ሁሉ እንዲህ ነበረ እንጂ እንዲህ አይደለም የሚል ስለሆነ የትችቱ መርዛማነት እንዳለ ነው።

ይህ የትችት ሰው ምንጊዜም በሰዎች ዕድገትና በሁኔታዎች መስተካከል ስለማይደሰት በማይመለከተውና ባልተረዳው ጉዳይ ሳይቀር ይበሳጫል። በዚች ምድር ላይ የማያውቀው ነገር ያለ ስለማይመስለው የማይተቸው ነገር የለም። ከሆነለት ይተቻል ካልሆነለት ደግሞ አጉረምራሚ ስለሚሆን የራሱን ሰላምና መረጋጋት ያጣል።"

👉 ይህን መንፈሳዊ ምክር ለወዳጅዎ ያካፍሉልን

https://www.tg-me.com/yekdset_selase_lejoch
Forwarded from የቅድስት ሥላሴ ልጆች (kiya)
ካቴድራል(የካቴድራል ቤተክርስትያን)

@yekdset_selase_lejoch

ካቴድራል ማለት ቃሉ ግዕዝ ወይም አማርኛ ሳይሆን ጥሬ ቃሉ ግሪክ ሲሆን ወደ ላቲን ሲተረጎም (cathedra) ካቴድራል ይላል፡፡  ይህም የጳጳስ መቀመጫ (ዙፋን) ማለት ሲሆን በጥንታዊያን ክርስቲያኖች አመለካከት ካቴድራል ማለት የሥልጣን ምልክት ማለት ነው፡፡  የካቴድራል ሕንጻዎች መሠራት ያለባቸው በትልልቅ ከተማዎች ነው እንጂ በአነስተኛ መንደር መሠራት የለበትም፡፡  የካቴድራል ቤተክርስቲያን በጣም ትልቅ ግዙፍ ሕንጻ ነው፡፡ 

@yekdset_selase_lejoch

ጥንታዊያን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ካቴድራል ተብሎ የተሰጣቸው ስያሜ የለም፡፡  ይህም ቃሉ ያልተለመደ የባዕድ ቃል በመሆኑ ለመጀመሪያ ጊዜ በ1924 ዓ.ም የተሰራውን የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን እጅግ በሥፋቱ ትልቅ በመሆኑና ውበትን የተላበሰ ዘመናዊ ሕንጻ በመሆኑ ይህን በማየትና በማድነቅ በግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ ቤተክርስቲያኑ ለመጀመሪያ ጊዜ የካቴድራል ስም ተሰጠው፡፡

@yekdset_selase_lejoch

ከላይ እንደተገለፀው ካቴድራል ሲባል ብዙ ምዕመናን የሚይዝ ትልቅና ውበት የተላበሰ በሕንጻ አሠራሩም ካሉት ሦስት ዓይነት የቤተክርስቲያን አሠራር ውስጥ ከምኩራብ (አራት መአዘን)፤ ከክብ ቤተንጉሥ ከዋሻ አሠራር ዓይነቶች ውስጥ ካቴድራል የምኩራብ ከኦሪቱ ትውፊት የተወሰደውን ዓይነት ቅርፅ የያዘ ነው፡፡  ካቴድራል ተብሎ የሚሰየመው ይህ ታላቅ ቤተክርስቲያን ብዙ ምዕመናንን አካቶ ከመያዙም በላይ ሦስት መንበር በቤተ መቅደሱ ወስጥ ሊኖረው ይገባል፡፡  ይህም በክብረ በዓል ጊዜ በሦስቱ መንበር የቅዳሴው ሥነ-ሥርዓት ተከናውኖ ምዕመናን በሥርዓት እንዲስተናገዱ ይረዳቸዋል፡፡ በተለይ የካቴድራል ቤተክርስቲያን ስያሜ መጥቶ በከተማችን ውስጥ ያሉት አብያተ ክርስቲያናት ከጊዜ ወደ ጊዜ በቁጥር እየጨመረ የመጣውን የምዕመናን ቁጥር በሥርዓት ለማስተናገድ የቤተክርስቲያኑ ስፋት ታላቅ ድርሻ አለው፡፡

@yekdset_selase_lejoch

በአጠቃላይ በጥንት ጊዜ የሌለው እና አሁን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የመጣው ካትድራል ብሎ ቤተክርስቲያንን መሰየም ዛሬ እየተለመደና ጠቃሚነቱ እየታወቀ በመምጣቱ በከተማችን በአዲስ አበባ በርካታ ታላላቅ ዘመናዊ ካቴድራሎች ታንፀዋል፡፡

@yekdset_selase_lejoch
Forwarded from የቅድስት ሥላሴ ልጆች (kiya)
🙏ቅዳሴ ማለት ምን ማለት ነው ⁉️

​​💠 ቅዳሴ ማለት ምን ማለት ነው ???
💠 በቅዳሴ ጊዜ 5ቱ ምሥዋዕቶች ምን ምን ናቸው?
💠 14ቱ ፍሬ ቅዳሴያት እነማን ይሆኑ?
💠ካህናት በቅዳሴ ወቅት 2: 3: 4: 5: 7: 12: ወይም 24: ሆነው ከቀደሱ ምሳሌነቱ ምን ምን ይሆን?
💠 እኛ ክርስቲያኖች ቅዳሴን ባስቀደስን ቁጥር 4 ነገሮች እናገኛለን ምን ይሆኑ?
💠 አምስቱ የስሜት ሕዋሳት በፀሎተ ቅዳሴ ጊዜ ያስቀድሳሉ እንዴት?


በእነዚህ ትምህርቶች ዙሪያ እየተማማርን እንገኛለን እርሶም እውቀቱ እዲኖሮዎ ከፈለጉ ይህን ማስፈንጠሪያ ይጫኑት ⁉️


👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://www.tg-me.com/yekdset_selase_lejoch
Forwarded from የቅድስት ሥላሴ ልጆች (kiya)
#በዓለ_ቅዱስ_ገብርኤል (ሐምሌ 19)
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
ይህ ዕለት መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ቅድስት ኢየሉጣንና ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስን ከእቶን እሳት ያዳነበት ነው፡፡ ቅዱስ ቂርቆስ ሀገሩ ሮም ሲሆን አባቱ ቆዝሞስ እናቱ ኢየሉጣ ይባላሉ፡፡ እናቱ ቅድስት ኢየሉጣ በትውልዷ ከአዝማደ ነገሥት ወገን ናት፡፡ ዲዮቅልጥያኖስ በነገሠ በ20 ዓመት በአባ ባጋግዮስ ምክንያት ‹‹የጣዖታት ቤቶች ይከፈቱ አብያተ ክርስቲያናት ይዘጉ›› ብሎ አሳወጀ፤ በዚህ ጊዜ ግማሾቹ ተሰደዱ ቅድስት ኢየሉጣም ልጇ የ3 ዓመት ሕፃን ነበርና ለርሱ ብላ ወደ ኢቆንዮን ሸሸች፡፡
በዚያም ሀገረ ገዢው ‹‹ክርስቶስን ካጂ ለጣዖት ስገጂ›› ቢላት ‹‹ዓይን እያለው ለማያይ ጆሮ እያለው ለማይሰማ በቃልህ አዘህ በእጅህ ሠርተህ ላቆምከው ምስል አልሰግድም›› ብላ መለሰችለት፡፡ እርሱም መልሶ ‹‹እምቢ ካልሽ በሰይፍ እቀጣሻለሁ›› ብሎ ቢያስፈራራትም እርሷ ግን ‹‹ይህን ሕፃን ጠይቀው›› አለችው፡፡ ከዚያም ሕፃኑን ‹‹ወርቅ እሰጥሃለሁ ለዚህ ጣዖት ስገድ›› አለው፡፡ ሕፃኑ ቂርቆስ መንፈስ ቅዱስ አድሮበታልና ‹‹ራሳቸውን እንኳ ማዳን ለማይችሉ ጣዖታትህ አልሰግድም›› ብሎ በመለሰለት ጊዜ ንጉሡ ተበሳጭቶ ‹‹በብረት ጋን ውኃ አፍልታችሁ ከዚያ ውስጥ ጣሏቸው›› ብሎ አዘዘ፡፡ የውኃው ፍላት እንደ ክረምት ነጎድጓድ 42 ምዕራፍ ድረስ ይሰማ ነበር፡፡ የንጉሡ አገልጋዮች ሊከቷቸው ሲወስዷቸው የቅድስት ኢየሉጣ ልቧ በፍርሃት ታወከባት፤ ቅዱስ ቂርቆስ ግን የእናቱን ፍርሃት እንዲያርቅላት ይጸልይ ነበር፤ እርሷንም ሁለተኛ ሞት አያገኘንምና እናቴ ሆይ በርቺ ፣ ጨክኚ፤ አናንያ፣ አዛርያና ሚሳኤልን ያዳነ እኛንም ያድነናል›› በማለት እያጽናናት ልብሷን እየጎተተ ከእሳቱ ቀረቡ፡፡ ከዚህ በኋላ ቅድስት ኢየሉጣ ጨክና በፍጹም ልብ ሆነው ተያይዘው ከእሳቱ ገብተዋል፡፡ እግዚአብሔርም መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልን ልኮ በበትረ መስቀሉ እሳቱን አጥፍቶ የፈላውን ውኃ አቀዝቅዞ አውጥቷቸዋል፡፡ ቅድስት ኢየሉጣ እና ቅዱስ ቂርቆስ በወጡም ጊዜ ልብሳቸውና ሰውነታቸው ሳይቃጠል ተመልክተው ከአሕዛብ ብዙዎቹ አምነው ሰማዕትነት ተቀብለዋል፡፡ ቅዱስ ገብርኤል ከሚፈላ ውኃ ያወጣቸው ሐምሌ 19 ቀን ሲሆን ሰማዕትነት የተቀበሉት ግን ጥር 15 ቀን ነው፤ (ስንክሳር ዘጥር 15 ይመልከቱ)፡፡ የቅድስት ኢየሉጣ እና የቅዱስ ቂርቆስ በረከታቸው ይደርብን አሜን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
ምንጭ፦ ስንክሳር ዘሐምሌ 19 ፣ መድበለ ታሪክ ፣ መዝገበ ታሪክ

https://www.tg-me.com/yekdset_selase_lejoch
Forwarded from የቅድስት ሥላሴ ልጆች (kiya)
🙏ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን የቅድስት ሥላሴ ልጆች በሙሉ🙏
ቀጣዩ ትምህርታችን የሚሆነው👇

💠ህንጻ ቤተክርስቲያን ምንድን ነው?
💠የቤተክርስቲያን ውስጣዊ ክፍሎች ምን ምን ናቸው?
💠የቤተክርስቲያን ውጫዊ ክፍሎች እና አገልግሎቶቹስ?
💠በቤተ ክርስቲያን ማድረግ ስለ ሚገባን እና ስለ ማይገባን ነገሮች?
💠ቤተክርስቲያን እንዴት መጠበቅ አለብን?
የሚሉትን ተከታታይ ትምህርቶች #የቅድስት_ሥላሴ_ልጆች_ማህበር በተሰኘው ኦርቶዶክሳዊ ቻናላችን እናቀርባለን።
ቤተሰብ ለመሆን👇👇👇
https://www.tg-me.com/yekdset_selase_lejoch
Forwarded from የቅድስት ሥላሴ ልጆች (kiya)
✞✞ ፆመ ፍልሰታ✞✞

(ጾመ ፍልሰታ) የፍልሰታ ፆም(ጾመ ማርያም) ሞት በጥር በነሀሴ መቃብር።

የፍልሰታ ፆም ከነሐሴ 1 እስከ 15 ነው።

በቤተ ክርስቲያናችን እደሚገለፀው "እመቤታችን ያረፈችው ጥር 21ቀን ነው።

ሐዋርያት በድኗን ሊቀብሯት ወደ ጌተሰማኒ ይዘዋት ሲሄዱ አይሁድ አይተዋቸው በተኗቸው፤ በዚህ ጊዜ መላእክት የእመቤታችንን አስክሬን ወስደው በገነት አኑረውታል።
ከ8ወር በኋላ በነሐሴ ሐዋርያት አስክሬኗን እንደገና ከጌታ ተቀብለው በፀሎትና በምህላ ቀብረዋታል። በዚህ የቀብር ሥነ-ስርዓት ላይ ከ12 ሐዋርያት አንዱ ቶማስ አልነበረም።

ቅዱስ ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ በደመና ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመጣ ያገኛታል፤ በዚህ ጊዜ ትንሳኤዋን ሌሎች ሐዋርያቶች አይተው ለእሱ የቀረበት መስሎት ተናዶ በፊት የልጅሽን ትንሳኤ ሳላይ ቀረው አሁን ደግሞ የአንቺን ትንሳኤ ሳላይ ቀርቼ ነበር ብሎ ከደመና ሊወረወር ቃጣው በዚህ ጊዜ
እመቤታችን ቶማስን አፅናንታ ከእሱ በቀር ሌላ ትንሰኤዋን እንዳላየ ነገረችው።

ቶማስም ሐዋርያት ወዳሉበት ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ እመቤታችንን ቀበርናት ብለው ነገሩት እሱም አውቆ ምስጥሩን ደብቆ አይደረግም ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር? አላቸው። ለማሳየትም መቃብር ሲከፍቱ አጧት በዚህ ጊዜ "አታምኑኝም ብዬ ነው እንጂ እመቤታችን ተነስታ አርጋለች።'' ብሎ ሁኔታውን ተረከላቸው ለምስክርም ይሆናል ብሎ የሰጠችውን ሰበኗን (መቀነቷን) አሳያቸው። ሰበኗንም ለበረከት ቆራርጠው ተከፋፍለው ወደ ሀገረ ስብከት ተበታተኑ። በዓመቱም ትንሳኤሽን ቶማስ አይቶ እንዴት እኛ ይቀርብናል? ብለው ከነሐሴ 1 ጀምሮ ሱባኤ ገቡ በነሐሴ14 ቀንም ጌታችን ትኩስ በድን አድርጕ አምጥቶ ሰጣቸው። ከቀበሯትም በኋላ በነሐሴ16 ተነስታለች። በዚህ ቀን ጌታ ቀድሶ እመቤታችንም በልጇ እጅ ቆርባለች። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የሐዋርያት ቤተክርስቲያን የእመቤታችንን በረከት ለማግኘት ይህችን ጊዜ ትፆማለች።
የእመቤታችን በረከቷ አማላጅነቷ ከሁላችንም ጋር ይሁን እናትነቷ ይብዛብን አሜን አሜን አሜን መልካም የፍልሰታ ፆም ይሁንልን ሀገራችንን ሰላም ታድርግልን አሜን ።

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
<< ወለወላዲተ ድንግል >>
<< ወለመስቀሉ ክቡር >>

https://www.tg-me.com/yekdset_selase_lejoch
Forwarded from የቅድስት ሥላሴ ልጆች (kiya)
+ አባቶቻችን እንዲህ አሉ +

"እሳትና ውኃን ማዋሐድ እንደማይቻል በሌሎች ኃጢአት መፍረድም በራስ ኃጢአት ከመጸጸት ጋር አብሮ አይሔድም" ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው

"የማያማትብ እጅ ቀኙም ግራውም አንድ ነው" አባ ፓስዮስ ዘደብረ አቶስ

"እግዚአብሔር ለኃጢአተኛ ሰው ያለው ፍቅር
ጻድቅ ሰው ለእግዚአብሔር ካለው ፍቅር ይበልጣል"
አባ አርሳኒ

"ሕፃን ልጅ እናቱ ስታጥበው ያለቅሳል:: ሕፃን እምነት (ትንሽ እምነት) ያላቸው ሰዎችም ነፍሳቸውን የሚያጥብ መከራ ሲመጣባቸው እግዚአብሔርን ያማርራሉ" አባ ስምዖን

"ዕለትን የሠጠህ እርሱ ለእለት የሚበቃህንም ይሠጥሃል" ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ

"እጅግ ምርጡ ጸሎት "ጌታ ሆይ አንተ ሁሉን ታውቃለህ የፈቀድከውን አድርግልኝ" ማለት ነው"
ባሕታዊ ቴዎፋን

"ሲያመነዝር ያየኸውን ሰው አንተ ንጹሕ ብትሆንም አትናቀው:: ምክንያቱም አታመንዝር ያለው ጌታ አትፍረድም ብሏል" አባ ቴዎዶር

"አንድ ሰው ኃጢአት ሲሠራ ብታይ እንኳን አትፍረድበት:: አንዳንዴ ዓይንህም ሊሳሳት ይችላል"
ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው

"ለኃጢአተኛው ክንፍህን ዘርጋለት:: ኃጢአቱን ልትሸከምለት ባትችል እንኳን ሸፍንለት"
ቅዱስ ይስሐቅ ሶርያዊ

ከአበው አንዱን ትሕትና ምንድርን ነው? ብለው ጠየቁት:: እርሱም "ትሕትና ማለት ወንድምህ በበደለህ ጊዜ እርሱ ይቅርታ ሳይጠይቅህ በፊት ቀድመህ ይቅር ማለት ነው" አለ::

"ይቅር ካላልክ ገነትም ይቅርብህ" አባ ኤፍሬም አረጋዊ

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
መስከረም 22 2013 ዓ ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ዘንድ ጸልዩ! ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Share ያድርጉ


channel > https://www.tg-me.com/yekdset_selase_lejoch

Group > https://www.tg-me.com/enamsgen
Forwarded from የቅድስት ሥላሴ ልጆች (kiya)
፠ሀጢያታችንን ለምን በቀጥታ
ለእግዚአብሄር ብቻ አንናዘዝም??፠
--------------------------------
• ሀጢያትን ለካህን መናዘዝ ለእግዚአብሄር አለመናዘዝ አይደለም፡፡ ሀጢያትን ለካህን መንገር ለእግዚአብሄር መናዘዝና ክብር መስጠት ነው፡፡ እያሱ እንዳለ “ልጄ ሆይ ለአምላክ ክብርን ስጥ፡ ለእርሱም ተናዘዝ፡ ያደረግከውንም ንገረኝ
አትሸሽገኝ” ኢያሱ 7-19፡፡
ኢያሱ “ክብርን ስጥ” ያለው ለእግዚአብሄር: “ተናገር”
ያለው ግን ለራሱ መሆኑ ሀጢያትን ለካህን መናዘዝ ለእግዚአብሄር ክብር
መስጠት እንደሆነ ያሳየናል፡፡ አበዉ ካሀናትም ኑዛዜን ከተቀበሉ በኋላ
“እግዚአብሔር ይፍታህ” እንጂ ”ፈትቼሃለሁ ” አይሉም፡፡ ይህም ምንም በእሱ ፊት ብንናገርም ሰሚዉም ሆነ በእነርሱ እጅ ስርየት የሚሰጠዉ እርሱ ባለቤቱ ስለሆነ ነው፡፡ ”ሁለት ወይም ሶስት በሚሆኑበት በዚያ በመካከላችሁ እገኛለሁ” ብሎ ቃል የገባ አምላክ በአናዛዡ ካህንና በተናዛዡ ምእምን መካከል ሆኖ ይሰማል፡ ስርየትንም ይሰጣል፡፡
• ሰው ሲታመም ሀኪም ቤት ሄዶ በሀኪሙ ፊት ”ቆረጠኝ ወጋኝ. . . ” እያለ
ህመሙን እንደሚያብራራው ሁሉ፡ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ያሉት ካህናትም የነፍስ ሀኪሞች ናቸውና እያንዳንዱን የነፍስ በሽታ (ሀጢያት) በዝርዝር በእነርሱ ፊት ልንናዘዝ ይገባል፡፡ በሀኪሙ ፊት ምንናዘዘው የእግዚአብሔርን ፈዋሽነት ክደን
እንዳልሆነው ሁሉ በካህናት ፊት የምንናዘዘውም የእግዚአብሔርን ሰሚነት ክደን አይደለም፡፡
• ለምን በቀጥታ ለእግዚአብሔር አልናዘዝም ማለት በራሱ ትዕቢት ነው፡፡ ንስሃ የሚገባ ሰው ሊል የሚገባው ”ከበደሌ ብዛት የተነሳ ቀና ብዬ የሰማይን ርዝመት አይ ዘንድ እንኩዋ አገባቤ አይደለም” ነው(ፀሎተ ምናሴ)፡፡
• በወንጌል እግዚአብሔር ”እርስ በርሳችሁ ሀጢያታችሁን ተናዝዙ” ያለው የሰው ልጅ ከፈጣሪ ይልቅ ሰውን ስለሚፈራና ስለሚያፍር በሃጢያቱ እንዲሳቀቅ ስለፈለገ ነው፡፡
እግዚአብሔር ያየኛል ይሰማኛል ሳይል የሰራውን ሀጢያት እንዴት
እግዚአብሔር ያየኛል ይሰማኛል ብሎ ይናዘዛል? እነዚህ ከእግዚአብሔር ይልቅ
ሰውን የሚፈሩትን መጽሐፍ እንዲህ ይላቸዋል ”እስመ ዐይነ ሰብእ ያፈርሆሙ
ወኢየአምሩ ከመ አይነ እግዚአብሔር ያበርህ እምእዕላፍ ፀሀይ” ”የሰው ዐይን
ያስፈራቸዋል፡ የእግዚአብሔር አይን ግን ከብዙ አእላፍ ፀሀያት ይልቅ
እንደሚያበራ አያውቁም!!!”
@rituaH

፠ስለ ንስሃ ሊያውቁአቸው የሚገቡ አንኳር ጉዳዮች፠
-------------------------------
☞አንድ ምእመን ንስሃ በሚገባበት ጊዜ ሃጢያቱን ሳያድበሰብስ በዝርዝር ለካህኑ
በሚገባ መልኩ መናዘዝ አለበት ፡፡ እንዳው በደፈናው “እኔ ያልሰራሁት ሃጢያት የለም ” ”አድርጉ ከተባለው ውስጥ ያደረግኩት አንድም መልካም ነገር የለም!” እያሉ የብልጠት ኑዛዜ መናዘዝ አይገባም፡፡ አንድ በሽተኛ በሃኪም ፊት ”ታምሜአለሁ! ” ”በሽታ የተባለ ሁሉ አለብኝ!” በማለት መድሃኒት እንደማያገኝ ሁሉ ሃጢያቱን በዝርዝር እና በግልፅ ያልተናገረም በትክክል ስርየት አያገኝም፡፡

☞አንድ ምእመን ስለ ሃጢያቱ በግልፅ ሊናገር እና ሊዘረዝር ይገባል ሲባል ግን
በሆነው ባልሆነው ”እኔ ሃጢያተኛ ነኝ” ሊል ይገባል ማለት አይደለም፡፡ ”ድሃ
ድህነቱን በአፉ ይጠላታል” ሲራ 13-24 እንዳለ ”እንደኔ ሃጢያተኛ ማን አለ?”
እያሉ ሃጢያትን በአፍ መጥላት ገና ከሀጢያት ፍቅር ያለመላቀቅ ምልክት ነው፡፡ ሃጢያትን የሚጠላት በንስሃ ይርቃታልና፡፡ ሃጢያተኛ ነኝ እያሉ በማወጅ ንጹሃን ትሁታን የሚመስላቸው አሉ፡፡ ትሁታን ግን ቅዱስ ዮሃንስ አፈወርቅ እንዳለው: #ሃጢያተኛ_ነኝ_የሚሉት_ሳይሆኑ_ሃጢያተኛ_ሲባሉ_የሚታገሱት_ናቸው፡፡

☞በኑዛዜ ወቅት ትንኝን እያጠሩ ግመልን እንደመዋጥ ታላላቅ ሃጢያቶቻችንን
ከጎን ትተን ጥቃቅኑን ብቻ መናገር ስህተት ነው፡፡ ሲሰሩት ያልፈሩትን ሃጢያት
ሲናገሩት መፍራት አይገባምና፡፡ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በአርጋኖን ዘረቡዕ 7-5 እንዲህ እንዳለ ”ሃጢያቴን ለመናገር ለምን አፍራለሁ? አለመናዘዜስ ለምንድን
ነው? እኔ ሀጢያቴን ብሰውረው ሃጢያቴ ራሱ ሊከሰኝ ይጮሃል፡፡ እንኪያስ
እንዳልበደለ ለምን ዝም እላለሁ? የሰራሁትን ክፉ ስራዬ ያሳጣኛል እኔ
እንዳልሰራ ለምን እሆናለሁ? የሚዘልፈኝ አልሻም፡ እኔ ራሴ ለራሴ የራሴን ዘለፋ
አነባለሁ እንጂ::”

☞በኑዛዜ ወቅት ለሀጢያት ምክንያት መደርደርና የሌሎችን ሀጢያት አክሎ
መናገር አይገባም ”እገሌ እንዲህ አድርጎ ስለገፋፋኝ እንዲህ አድርጌ ነበር”
አያሉ ሌላውን መክሰስና ምክንያት መስጠት ይቅር ሳይሉ ይቅርታ መሻት ነውና፡፡ ጌታችንም በወንጌል ”ከሳሾችሽ ወዴት አሉ?” ያላትን ሴት ”አኔም
አልፈርድብሽም” ብሎ በይቅርታ ያሰናበታት ስለ ከሳሾችዋ አንዳች ባለመናገሩዋ ነበር (ዮሀ 8-11)፡፡

☞ሰው ሆኖ የማይበድል እንጨት ሆኖ የማይጨስ የለምና እንዲሉ ሰው ሁልጊዜ
ከበደል ንጹህ ይሆን ዘንድ አይችልም በንስሃ ሃጢያቱን የሚናዘዝ ሰው ዳግመኛ
አይበድልም ማለት አይደለም፡፡ ከንስሃ በሁዋላ በሃጢያት ተፈትነን ብንወድቅ
ተስፋ ሳንቆርጥ ወዲያው ንስሃ ልንገባ ይገባል፡፡ ”መልሼ ልበድል ለምን ንስሃ
እገባለሁ” ማለት ግን ”መልሶ ለሚርበኝ ለምን እበላለሁ” ”መልሼ ለምቆሽሽ
ለምን እታጠባለሁ” እንደ ማለት ነው:: ቅዱስ ዮሃንስ አፈወርቅ ”መውደቅ
አዳማዊ ነው ወድቆ አለመነሳት ግን ዲያቢሎሳዊ ነው” እንዳለው ተሰፋ ቆርጦ በንስሃ መነሳት ይኖርብናል እግዚአብሄር ይቅር ማለት ሳይሰለቸዉ ሰው ይቅር በለኝ ማለት ሊሰለቸው አይገባም::
ይቆየን።

Join 👇👇👇

ይዩ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ 👇 ለማግኘት // 👇
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼🌼 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

https://www.tg-me.com/yekdset_selase_lejoch
Forwarded from የቅድስት ሥላሴ ልጆች (kiya)
የፕሮቴስታንት መልስ

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን ውድ የተዋሕዶ አማኞች እነሆ ዛሬ የብዙዎች ጥያቄ የሆነውን "ኃይለ ቃል" አንስተን ረድኤተ እግዚአብሔርን አጋዥ አድርገን እንማማራለን

ብዙዎች የተጣመሩባት ለእምነታቸው መሠረት ያደረጓት እንደ ጥያቄ እንደ መልስም የሚጠቅሷት ብቸኛ ጥቅስ ናት ሮሜ 8÷34 :: ቃሉ “የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሣው በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው ደግሞ ስለእኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው” ይላል::

“የሚማልደው” የሚለውን ቃል ይዘው ኢየሱስ አማላጅ ነው የሚሉ ሰዎች አሉ:: ( ሎቱ ስብሐት) አለማስተዋል ካልሆነ በቀር በዚህ የሚሳሳት ሰው አለ ለማለት አያስደፍርም ምክንያቱም ከላይ ስናነብ የምናገኘው የዚህ ተቃራኒ ነውና::

ከዛ በፊት.........
📌በ1938 ዓ.ም የተጻፈው መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል "ክርስቶስ ኢየሱስ ሞተ ከሙታንም ተለይቶ ተነሳ በአብ ቀኝ ተቀምጧል ስለእኛ #ይፈርዳል"

📌 በ 1975 ዓ.ም ከግዕዝ ወደ አማርኛ የተተረጎመው እንዲህ ይላል "የሚፈርደው ማንነው? ክርስቶስ ኢየሱስ ሞተ ከሙታንም ተለይቶ ተነሳ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጧል ስለእኛም #ይፈርዳል

በአሁን ሰዓት የተሰራጨው መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ግን እንዲህ ይላል "የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሳው በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው ደግሞ ስለእኛ #የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው"

በዚህ ጥቅስ ላይ በተያዩ ዘመናት የተጻፉ መጽሐፍቶች ክርስቶስን #ፈራጅ ሲያደርጉት በአሁን ሰዓት ላይ ግን ያሉ መጽሐፍት #አማላጅ ይሉታል።

ትክክለኛው የቅዱስ ጳውሎስ ቃል የቱ ነው ብለን ስንጠይቅ መረዳት የምንችለው ከምንባቡ ሐሳብ ነው። ቁጥር 33 ላይ ከፍ ብለን ስንመለከት እንዲህ ሲል ይጀምራል

" እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል?"
👉 ይህ ማለት እግዚአብሔር ተከተሉኝ ብሎ በመጥራት የመረጣቸውን አይ እነርሱ አንተን ሊከተሉ አይገባቸውም ሊመረጡም አይችሉም ብሎ የሚከሳቸው ማነው በማለት ይጠይቃል በመቀጠልም " የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው" በማለት የመረጣቸውን ሰዎች መንግስቱን ለማውረስ እናንተ የአባቴ ብሩካን ብሎ የሚያጸድቃቸው እግዚአብሔር ነው አለ" እንዲሁም "የሚኮንን (የሚፈርድ) ማነው በማለት ይጠይቃል

#መኮነን ከግእዙ ሳይተረጎም ቀጥታ የተወሰደ ቃል ሲሆን መኮነን ማለት " #ኮነነ " ከሚለው የግእዝ ሥርወ ቃል የወጣ ሲሆን #መፍረድ ማለት ነው

✴️ እንግዲህ ማጽደቅና መኮነን የአማላጅነት ሥራ ሳይሆን የፈራጅነት ሥራ እንደሆነ ልብ እንበል።

በመቀጠል "የሚኮንንስ ማንነው" ብሎ ለጠየቀው ጥያቄ መልስ ሲሰጥ ቁጥር 34 ላይ "የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሳው በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው" በማለት አሁን ያለበትን ሥፍራ ይገልጻል።

💮 የሞተውና ሞትን ድል አድርጎ በሥልጣኑ የተነሳው ኢየሱስ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ አለ ማለት ነው። መቼም እግዚአብሔር ቀኝና ግራ ፊትና ኋላ የለውም እርሱ ስፍራ ማይወስነው ረቂቅ ነው።

ለመለኮት ወርድና ቁመት፣ ላይና ታች፣ ቀኝና ግራ ያለው አይደለም፣ በሁሉ የመላ ነው እንጂ
(ቅዳሴ ማርያም)
ታድያ በእግዚአብሔር ቀኝ ሲል ምን ማለቱ ነው? ብለን ስንጠይቅ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ቀኝ የተለያየ ትርጉም ቢኖረውም በዚህ ምዕራፍ ላይ ግን #ክብርን #ስልጣንን ያመለክታል

"በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው" ማለቱ በሥልጣንና በክብር በሰማያት ያለው ማለቱ ነው። ይህም ማለት ክርስቶስ ቀድሞ ሥጋ ከመልበሱ በፊት ክብር የሌለው ሆኖ በኋላ ክብር አገኘ ለማለት አይደለም ክብርና ሥልጣኑ ቅድመ ተዋሕዶና ድህረ ተዋሕዶ ከባሕርይ አባቱ ከአብ፣ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ትክክል ነው።

ከላይ በዝርዝር እንዳየነው ጥቅሱ የሚያመለክተው ፈራጅነቱን እንጂ አማላጅነቱን በፍጹም አይደለም። ማጽደቅና መኮነን ከቻለ እንዲሁም በእግዚአብሔር ቀኝ (ክብር) ካለ እርሱ ክርስቶስ ፈራጅ እንጂ አማላጅ አይሆንም "የሚኮንን ማን ነው?"የሚለውና "ስለ እኛ የሚማልደው" የሚሉት ሁለት ሐሳቦች እርስ በእርሳቸው እንዳይጋጩ አስማምቶ መተርጎም ያስፈልጋል።

#ይቀጥላል………


https://www.tg-me.com/yekdset_selase_lejoch
Forwarded from የቅድስት ሥላሴ ልጆች (kiya)
🔑የፕሮቴስታንቱ ቸርች የማይፈታው እንቆቅልሽ!🔑

#መፅሐፍ #ቅዱስን ልዩ ከሚያረጉት ነገሮች መካከል አንዱ ዕድሜው ነው ከሱ ቀድሞ ወይም ከሱ በፊት የተፃፈ መፅሐፍ የለም የመጀመሪያው መፅሐፍ መፅሐፈ ሄኖክ ሲሆን የተፃፈውም ከአዳም ጀምሮ #ሰባተኛ #ትውልድ በሆነው በሄኖክ በ 1486 ዓመተ ዓለም ወይም ከክርስቶስ ልደት 4014 ዓመት በፊት ነው " #የአምላካችን #ቃል #ግን #ለዘላለም #ፀንታ #ትኖራለች " ት.ኢሳ 40 ፥ 8 እንደተባለ
መፅሐፍ ቅዱስ ታሪክ የማይሽረው ዘመን የማይገታው የማያረጅ #ዘላለማዊ #ነው

መፅሐፍ ቅዱስን #ከአርባ #ስምንት በላይ የሆኑ ጻሕፍት

💠 እረኛ የነበሩ {ሙሴ ፣ አሞፅ }
💠 ነገሥታት የነበሩ {ዳዊት ፣ ሰለሞን}
💠 ካህን የነበሩ { ሕዝቅኤል }
💠ቀራጭ የነበሩ {ማቴዎስ }
💠 ዓሳ አጥማጅ የነበሩ {ጴጥሮስ ፣ ዮሐንስ }
💠 ሐኪም የነበሩ { ሉቃስ }
ከተለያየ የሥራ መስክ ተጠርተው ፤
በተለያየ ቦታ ማለትም ፦
➡️በሲና ምድረ በዳ ፣
➡️በኢየሩሳሌም ፣
➡️በተለያዮ የእስራኤል ክፍሎች
➡️በስደት አገር በባቢሎን ፣ በፋርስ ፣በሮም ከተማ ፣ በፍጥሞ ደሴት በወህኒ ቤት ሆነው በተለያዩ ዘመናት የጻፉት የቅዱሳት መጻሕፍት ስብስብ ቢሆንም መልዕክቱ ግን ያልተዛባ ርቱዕ {ቀጥተኛ} የሆነ #እርስ #በርሱ #የማይጋጭ #ነው

#ይቀጥላል ……………

https://www.tg-me.com/yekdset_selase_lejoch
Forwarded from የቅድስት ሥላሴ ልጆች (kiya)
የቀጠለ...

▪️ ወዳጄ አንድ ነገር ብቻ ልጨምርልህና ላብቃ አስተውለህዋል ? አራቱም ወንጌላውያን በጻፉት ወንጌል ላይ ጌታ ተወለደ ብለው ብዙም ሳይነግሩን በ30 ዓመቱ ሊጠመቅ ወደ ዮሐንስ ዘንድ መሄዱን ነው የሚነግሩን እዚህ ላይ አንድ ጥያቄ እስቲ ልጠይቅህ ጌታ በ 7 ዓመቱ፣ በ 14 ዓመቱ ፣ በ 21 ዓመቱ .........ምን ይሰራ ነበር ? ምን ያረግ ነበር ? አንተ ይሄን ልታስረዳን ትችላለህ ? ይሄን ጥያቄ የሚመልሰውንና የሚያስረዳውን ተዓምረ ኢየሱስ የተባለውን የቤተ ክርስቲያን መጽሐፍስ ትቀበለዋለህ ? ታዲያ ስትጠየቅ የማትመልስ ፣ ሲያስረዱህ የማትቀበል ምን ዓይነት ፍጥረት ነህ ? ዝም ብሎ መጥላት መቃወም ለማን ይጠቅማል ማንንስ ያስተምራል ? ወዳጄ በራዕ 22 ፥ 18 ላይ አንዳች የጨመረ የቀነሰ የሚለው ቃል የተጠቀሰው ለዮሐንስ ራዕይ እንጂ ለሌሎቹ ቅዱሳት መጻሕፍት አይደለም ይህን ቃል ያላግባብና ያለቦታው እየጠቀሱ የሁሉም መጽሐፍት ማጠቃለያ አስመስለው የሚያቀርቡልህ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ መቼ ተሰብስቦ ባንድ ጥራዝ እንደተዘጋጀ የማያውቁ ፤ መጻሕፍትን ሳይመረምሩና በቃሉ ሳይፈትኑ በአርእስታቸውና በሽፋናቸው ብቻ የሚጠሉ ናቸው ፤ አንተ ግን በተማርህበትና በተረዳህበት ነገር ጽና ፤ የመናፍቃኑን የክህደትና የኑፉቄ መረብ የምትበጣጥስበትን የመንፈስ ቅዱስ ሰይፍ ያዝ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው ፤ ቃሉ ለአንተ የዲያቢሎስን ሽንገላ የምትቃወምበት
የእግዚአብሔር ዕቃ ጦር ፤ ለሚቃወሙህ ደግሞ ድንጋዩን የሚያደቅ መዶሻ ነው ። ኤር 23 ፥ 29 እንደ ቃሉ ዉጣ እንደ ቃሉ ግባ ዘሁ 27 ፥ 21 ብዙ ምርኮ እንዳገኝ
በቃልህ ደስ አለኝ ያልክ እንደ ቅዱስ ዳዊት ዘምር መዝ 119 ፥ 162 ቃሉ ለእግርህ መብራት ለመንገድህም
ብርሃን ነው መዝ 119 ፥ 106 በእግዚአብሔር ቤት ተተክለሃል በአምላክህ አደባባይ ውስጥ ትበቅላለህ መዝ 92 ፥ 13 አንተም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለች፥ ፍሬዋን በየጊዜዋ እንደምትሰጥ፥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ትሆናለህ ። መዝ 1 ፥ 3 ወዳጄ ለዚህ ክብር ያበቃን ዘንድ ላንተም ለኔም ለደካማው ወንድምህ ጸልይ ።

ወስብሀት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀለሉ ክቡር!!!!

https://www.tg-me.com/yekdset_selase_lejoch
Forwarded from የቅድስት ሥላሴ ልጆች (kiya)
+ ልጅሽ ደጅ ላይ ቆሟል +

ከመስከረም 26-እስከ ሕዳር 6 ባሉ አንድ ቅዳሜ ማታ ከ3 ሰዓት በኋላ ማሕሌተ ጽጌን ለመቆም ወደየካ ደብረ ሳሕል ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን እየሄድኩ ነው . . . መንገዱ ጭር ብሏል፤ አንድ ሱቅ ላይ ግን ደምበኛ (ገዢ) ቆሟል፤ እኔ መንገዴን እየቀጠልኩ ነው፡፡ ደንበኛው ቀጥ ብሎ ወደኔ መጣ እና ‹‹አባ ይበርኩኝ?›› አለኝ። ‹‹ካህን አይደለሁም›› አልኩት፣ በለበስኩት ነጠላ ጋቢና በእጄ የያዝኩት የጸሎት መጽሐፍ ወደ ቤተ ክርስቲያን እንደምሄድ አውቆ ነው፡፡ ‹‹አውቃለሁ›› አለኝ እና ‹‹ወደየትኛው ቤተ ክርስቲያን ነው የምትሄደው?›› ጠየቀ መለስኩለት፤ ‹‹እባክህን ልሸኝህ?›› አለኝ አዲስ ቪ 8 መኪና እያሳየኝ፣ ‹‹ብዙም ሩቅ ስላልሆነ በእግሬ ነው የምሄደው›› አልኩት . . .

ግለሰቡ የጠጣ ይመስላል፣ በእርግጥም የመጠጥ ሽታ ሸትቶኛል፤ በእጁ ፓኬት ሲጋራ ይዟል፣ ከሱቁ ሲመጣ ከፓኬቱ ውስጥ አንዱን አውጥቶ ከንፈሩ ላይ አድርጎ ነበር ሲቀርበኝ በጣቶቹ መሃል ያዘው፣ ምልከታዬን አስተውሎ ነው መሰለኝ የያዘውን ሲጋራ በሙሉ ጣለና በእግሩ ረጋገጠው፡፡ ‹‹አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ ልትል ነው አይደል?›› አለኝ

ከዚህ ንግግር በኋላ ስካሩ ሙሉ ለሙሉ ሲጠፋ በግልጽ ይታያል፡፡ ሁሉንም የመኪናውን በሮች ከፈተና ‹‹እንዲናፈስ ፈልጌ ነው . . . በሲጋራና በመጠጥ ሽታ የታጠነ መኪና ውስጥ እንዳትገባ›› አለኝ፤ በግርምት ቆምሁ፤

‹‹እባክህ አሁን እንሂድ?›› የጋቢናውን በር ብቻ ትቶ ሌሎቹን ዘጋጋና መኪናውን ለመንዳት ተዘጋጀ፤ በእምነት ገባሁና ተቀመጥኩ። መንገድ ስንጀምር በጣም ባዘነ ድምጸት

‹‹ሽሮ ሜዳ ነው ያደግሁት . . . ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን . . . ጽጌን በፍቅር ቆሜ ነው ያደግኩት . . . ለረጅም ዓመታት . . . አክሊለ ጽጌ ብዬ . . . ክበበ ጌራ ወርቅ ብዬ ›› ዓይኖቼን ከመንገዱ ነቅዬ ወደርሱ ሳዞር መንታ መንታ ሆነው የሚወርዱ እንባዎቹን ይጠርጋል፤ ምን ማለት እንዳለብኝ አላውቅም መስማት ብቻ

‹‹ዲግሪዬን ከያዝኩ በኋላ አንድ ዓለም አቀፍ ኤን ጂ ኦ ገባሁ . . . በከፍተኛ ደመወዝ በቃ ከቤተ ክርስቲያን ጋር ተለያየሁ. . . አልሳለም፣ ኪዳን አላደርስ፣ አላስቀድስ፣ አላድር፣ አላነግስ ከሀገር ሀገር መዞር ከጓደኞቼ ጋር መጠጣት፣ ሲጋራ ማጨስ . . . ይኸውልህ ሚስትና ልጆች እያሉኝ ነው እዚህ ያገኘኸኝ፣ የመጠጥና የሲጋራ ጓደኞቼ በልጠውብኝ ነው ያገኘሁህ. . . ውስኪአቸውን ይዘው እየጠበቁኝ ነው ›› ያለቅሳል፣ እንባዎቹን ይጠርጋል፤ ግን በሥርዓት ረጋ ብሎ ይነዳል፤ መናገሩን ይቀጥላል

‹‹ተረጋግቼ ማሰብ አልፈልግም . . . ምክንያቱም ከተረጋጋሁ ልጅነቴን ማሰብ እጀምራለሁ . . . ልጅነቴን ማሰብ ከጀመርሁ ቤተ ክርስቲያንን ማሰብ እጀምራለሁ . . . ደጀ ሰላሟን ማሰብ እጀምራለሁ. . . መቅደሷን ማሰብ እጀምራለሁ፣ . . . የዕጣኑን ሽታ ማሰብ እጀምራለሁ . . . ማልቀስ እጀምራለሁ . . . ፍቅሯን አስባለሁ . . . የጸናጽሉ፣ የከበሮው ድምጽ ይሰማኛል፣ በመሃል ሰይጣኔ ይመጣና እውነቴን ነው ስጠራው ነዋ የሚመጣው. . . ለጓደኞችህ ደውል ይለኛል . . . በመጠጥ ራስህን ደብቅ ይለኛል እታዘዘዋለሁ ልጆቼንና ሚስቴን ጥዬ እወጣለሁ››

አሁን ወደ ቤተክርስቲያን ታጥፈናል፤ ወደ ግቢው የሚያስገባ በር ጋር ስንደርስ ቆመ፣ ወደውስጥ ለመግባት በሮቹ የተከፈቱ ቢሆንም አልገባም፤
‹‹ወደውስጥ ገብተህ ትንሽ ቆይተህ አትሄድም?›› አልኩ ሀዘኑ ተጋብቶብኝ ‹‹አልገባም ግን ድሮ የሚወድሽ ልጅሽ ደጅ ቆሟል በላት›› አለና ሳግ ተናንቆት መሪውን ተደግፎ ድምጽ አሰምቶ አለቀሰ፣ ቅዱስ ጴጥሮስ ለምን እንዳለቀሰ፣ እንዴት እንዳለቀሰ በዓይኔ ያየሁ መሰለኝ፤
‹‹እባክህን ግባና አልቅስ›› አልኩ፣ የቻለውን ያህል አልቅሶ እንዲወጣለት ፈለግሁ፣

‹‹ማን . . . እኔ? አልገባም ግን ንገርልኝ አሁንም ይወድሻል በልልኝ . . . እዚህ በር ላይ ቆሟል በልልኝ›› አለኝ፣ እያለቀሰ ወረድሁ
ቅዱስ ዳዊት ‹‹በኃጥአን ድንኳኖች ከመቀመጥ ይልቅ በእግዚአብሔር ቤት እጣል ዘንድ መረጥሁ›› መዝ 84፣10 ያለው ለምን እንደሆነ ይበልጥ ገባኝ። ሳላውቀው የእኔም እንባ መንገዱን ጀምሯል፤ ‹‹ማን ስለሆንኩ ነው እንዲህ በፍቅርህ የተሸከምከኝ››አልኩ አምላኬን፣
በላዔ ሰብዕ ትዝ አለኝ በልጅነቱ የሚያስታውሳትን የድንግልን ድንቅ ስሟን ሲሰማ ከክህደት እንደተመለሰና ለመዳን ምክንያት እንደሆነችው፡፡ እናም ‹‹በልጅነቱ ይወድሽ የነበረውን ልጅሽን አስቢው ከልጅሽ ዘንድ አሳስቢለት›› አልኳት

ዲያቆን ዶ/ር ቢኒያም ዘክርስቶስ

ትምህርቱ ለሌሎች ይዳረስ ዘንድ Share እና Like ያድርጉ።

Channel: https://www.tg-me.com/yekdset_selase_lejoch

Group: @enamsgen
Forwarded from የቅድስት ሥላሴ ልጆች (kiya)
ሰላም የቅድስት ድንግል ማርያም ልጆች በሙሉ

🔔በብዙዎቻችሁ ጥያቄ መሰረት ""የሚያየኝን አየሁት"" የተሰኘ ኦርቶዶክሳዊ ይዘት ያለውን መንፈሳዊ ታሪክ በድጋሜ በቴሌግራም ቻናላችን ለማቅረብ እየተዘጋጀን መሆኑን እየገለፅን እርሶም ከታሪኩ እንዲማሩ እየጋበዝን የመጀመሪያው ክፍል ሐሙስ ማታ 2:00 ሰዓት ላይ በቻናላችንና በግሩፓችን የምንለቅ መሆንን እናሳውቃለን።

Channal 👇
🔑 @yekdset_selase_lejoch 🔑
Group👇
🔑 @enamsgen 🔑

"የልዑል እግዚአብሔር ቃል ለሁሉም ይተላለፍ ዘንድ ሼር /Share ያድርጉ።
Forwarded from የቅድስት ሥላሴ ልጆች (kiya)
ሰላም የቅድስት ድንግል ማርያም ልጆች በሙሉ

🔔በብዙዎቻችሁ ጥያቄ መሰረት ""የሚያየኝን አየሁት"" የተሰኘ ኦርቶዶክሳዊ ይዘት ያለውን መንፈሳዊ ታሪክ በድጋሜ በቴሌግራም ቻናላችን ለማቅረብ እየተዘጋጀን መሆኑን እየገለፅን እርሶም ከታሪኩ እንዲማሩ እየጋበዝን የመጀመሪያው ክፍል ሐሙስ ማታ 2:00 ሰዓት ላይ በቻናላችንና በግሩፓችን የምንለቅ መሆንን እናሳውቃለን።

Channal 👇
🔑 @yekdset_selase_lejoch 🔑
Group👇
🔑 @enamsgen 🔑

"የልዑል እግዚአብሔር ቃል ለሁሉም ይተላለፍ ዘንድ ሼር /Share ያድርጉ።
Forwarded from የቅድስት ሥላሴ ልጆች (kiya)
ለምን #ቀዳሚት_ሥዑር_ (#ሥዑር_ቅዳሜ) (የስቅለት ማግስት ) ላይ ቄጤማ ይታደላል ወይንም ይደረጋል ???
ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ
ይህቺ ቅዳሜ በእነዚኽ ስሞች ትታወቃለች
#ቀዳሚት_ሥዑር_ (#ሥዑር_ቅዳሜ)፤ #ገብረ_ሰላመ_፤ (#ለምለም_ቅዳሜ)
#ሰንበት_ዐባይ #ቅዱስ_ቅዳሜ#ቀዳሚት_ሰንበት
ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ
#ቀዳሚት_ሰንበት፤ እግዚአብሔር ፍጥረታትን ፈጥሮ ከፈጸመ በኋላ ያረፈባት ስለኾነች፤ የእግዚአብሔር የዕረፍት ዕለት፤ ቀዳሚት ሰንበት (የዕረፍት ቀን) ትባላለች፡፡
#ሰንበት_ዐባይ (ታላቋ ሰንበት)፤ የመጀመሪያዋ ሰንበት በመኾኗ ታላቋ ሰንበት ትባላላች፡፡
#ቀዳሚት_ሥዑር_ (#ሥዑር_ቅዳሜ)፤ እግዚአብሔር ሥነ ፍጥረትን ከመፍጠር ዕረፍት እንዳደረገባት ኹሉ፣ የፍጥረት ርእስ የኾነውን አዳምን ለማዳን ሕማም እና ሞት የተቀበለው አምላካችን ክርስቶስ በከርሠ መቃብር አርፎባታል፡፡ (ማቴ. ፳፯፥፷፩)፡፡

፠ ‹ሥዑር› የተባለችበት ምክንያትም በዓመት አንድ ቀን ስለምትጾም (የጾም ቀን በመኾኗ) ነው፡፡

የጌታችን እናት ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ወዳጆቹ ቅዱሳን ሐዋርያት እና ሌሌችም የጌታ ወዳጆች ጌታችን ተላልፎ ከተሰጠበት ዕለት ጀምሮ ብርሃነ ትንሣኤውን እስኪያዩ ድረስ እህል ውኃ በአፋቸው አልዞረም፡፡ ይመኩበትና ተስፋ ያደረጉት የነበረ አምላካቸው በመቃብር ስላረፈ ዕለቷን ሞቱን በማሰብና ትንሣኤውን በመናፈቅ በጾም አክብረዋታል፡፡

፠ የቻልን ሕዝበ ክርስቲያንም ይኽን መነሻ በማድርግ ከዓርብ ጀምረን በማክፈል (በመጾም) እህል ውኃ ሳንቀምሱ ለኹለት ቀናት እናድራለን (እንካፍላለን)፡፡ እንደ ዋልድባ እና ማኅበረ ሥላሴ ባሉ ገዳማት ያሉ ታላላቅ አባቶችና ወንድሞች ደግሞ ከሆሣዕና አንዳንዶችም ከዕለተ ረቡዕ ጀምረው ለ7ት ቀናት ወይም ለ3ት ቀናት ያከፍላሉ፡፡

#ገብረ_ሰላመ_፤ (#ለምለም_ቅዳሜ)
ቅዳሜ የጠዋቱ ጸሎት ሲፈጸም ካህናቱ ‹‹ገብረ ሰላመ በመስቀሉ፤ (በመስቀሉ ሰ
ላምን አደረገ፥ መሠረተ)›› እያሉ በቤተ ክርስቲያን ለተሰበሰቡ ምእመናን የምሥራች ቄጠማ ያድላሉ፡፡

፠ ቄጠማው በኖኅ ዘመን በንፍር ውኃ ምድር በተጠለቀለቀች ጊዜ፤ ኖኅ ወደ መርከብ ይዟቸው ከገባው እንስሳት መካከል የውኃውን መጉደል ለመረዳት ርግብን በመርከብ መስኮት አሾልኮ ልኮ እርሷም ቄጠማ በአፏ ይዛ በመመለስ የምሥራች ምልክት፥ የውኃውን መድረቅ እንደተነገረችውና እንደተደሰተ ሁሉ (ዘፍ. ፱፥፩-፳፱)፡፡ ‹‹በክርስቶስ ሞት፤ ሞተ ነፍስ ከሰው ልጆች ተወገደ፤›› ስንል ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቅዳሜ ጠዋት ደባትር መዘምራን ዝማሬን ካቀረቡ በኋላ ለልጆቿ ቄጠማ ታድለናለች፡፡ የምሥራች ተምሳሌት የኾነውን ቄጠማም፤ ከሲኦል ቃጠሎ ወደ ጥንተ ማኅደራችን ገነት መመለሳችንን ለመመስከር በግንባራችን እናስረዋለን፡፡
(ፍኖተ ሕይወት)
#ቅዱስ_ቅዳሜ፤ ለ5500 በሲኦል ሲማቅቁ የነበሩ ነፍሳትን ሰላም ለኹላችኹ ይኹን ብሎ ወደ ገነት አስገብቷቸዋልና፤ ይኽች ቅዳሜ ቅዱስ (የተለየች) ቅዳሜ ትባላለች፡፡
አውረድዎ፥ አውረድዎ፥ አውረድዎ እምዕፅ፤
ወአምጽኡ አፈዋተ ከርቤ ሕዉስ፡፡

https://www.tg-me.com/yekdset_selase_lejoch
🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔

ግንቦት 5/2014 ዓ.ም ቀድሞ በተያዘ መርሐግብር ብጹአን አባቶቻችን ለማነጋገር ቤተክህነት ተገኝተው የነበሩት
#ኢዮኤል_ግርማ እና #ዳዊት_አሰፋ ከቦሌ ክፍለ ከተማ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ከእስር በመታወቂያ ዋስ ተፈትተዋል።

#ቃለአብ_ታመነ እና #ዓለምነህ_ዳኘው ከኮልፈ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት በ200 ብር ዋስ እንዲወጡ ቢወሰንም ይግባኝ ተጠይቆባቸው ልደታ ፍርድ ቤት ውሳኔ በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ።

እነዚህን ምንም ጥፋት ያላጠፉ ቀሪ ሁለት ወንድሞቻችንን መንግሥት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ ከእስር እንዲፈታቸው አበክረን እየጠየቅን ይህንኑ ጉዳይ መላው ሰንበት ት/ቤቶች በማሕበራዊ ገጻችሁ በማጋራት ለወንድሞቻችሁ ያላችሁን ድጋፍ እንድታሳዩ እናሳስባለን።

#የአዲስ_አበባ_ሰንበት_ትምህርት_ቤቶች_አንድነት
🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔
Forwarded from 📸 kiya pictures 📸
ለፕሮፋይል የሚሆኑ ኦርቶዶክሳዊ ፎቶዎች ለማግኘት 📸 https://www.tg-me.com/kiya_pictures1
2025/02/21 11:43:18
Back to Top
HTML Embed Code: