Telegram Web Link
ይህን_ብስራት_ሁሉም_ይስማ_seid_jemal_.128
<unknown>
ይህን ብስራት ሁሉም ይስማ

በ (seid jemal) 👆👂👂👈

„እህቴ ሆይ ሳትፈለጊና ሳትመርጭ አካልሽ ከፈን ከመገነዙ በፊት በፈላጎትና ምርጫሽ ሸፍኝዉ ሰዉነት የሚሸፈነዉ በኢማን ልክ ነዉ...
Share 🙏🙏🙏
➡️telegram chanal⬅️

@HALALI_TUBE
@HALALI_TUBE
🛤በውስጥ መስመር የተላከልኝ ማስታወሻ
- ስሞት አላስብም፣ አልጨነቅም፣

- ገላዬ ፈራሽ ነውና ምን አሳሰበኝ

ሙስሊም ወንድሞቼ መደረግ ያለበትን ሁሉ ያደርጉልኛል፡፡

1- ልብሴን ያወልቃሉ፣

2- ያጥቡኛል፣

3- ይከፍኑኛል፣

4- ከቤቴ ይዘውኝ ይወጣሉ፣

5- ወደ አዲሱ ቤቴ (መቃብር) ይወስዱኛል፣

6- ብዙዎች ጀናዛዬን ለመሸኘት ይመጣሉ፣

7- እኔን ለመቅበር ሥራቸውንና ቀጠሯቸውን ሁሉ ትተው የሚመጡ አሉ፡፡

ከነኚህ መካከል ምናልባት ላንዳፍታ እንኳን ስለኔ አስበው የማያውቁ ብዙ ናቸው፡፡

8- ቤተሰቦቼ እኔን ላለማስታወስ ያለኝን ነገር ሁሉ አውጥተው ይጥሉ ይሆናል፤ አሊያም በኔ ሥም ይመፀውቱ ይሆናል

- ቁልፎቼ 🔑🗝

- መጽሐፎቼ 📚

- ጫማዎቼ 👟

- ልብሦቼ 👖👔…..

በአንድ ነገር ግን እርግጠኛ ሁኑ፡፡

- በመሞቴ ይህች ዱንያ ሐዘኗ አልበዛም፣ አለች አልፈረሠችም፣

- የዓለም 🌍 እንቅስቃሴም ላፍታ አልቆመም፣

- የኢኮኖሚው 💰 ቀውስም አልተፈጠረም፣

- በሥራ ቦታዬ ላይ ሰው ለመቅጠር ማስታወቂያ🧾 ይወጣል፣

- ንብረቴ 💸🏠🚘 የወራሾቼ ይሆናል፣ በትንሽ በትልቁም ኦዲት የምደረገው ግን እኔ ነኝ፣

- ስሞት መጀመሪያ ከኔ የሚገፈፈው ስሜ ነው፡፡ በሥሜ መጠራቴ ይቀራል፤

- ጀናዛው የታለ እባላለሁ፡፡ ጀናዛውን ዉሰዱ፣ አምጡ እንስገድበት፣ ጀናዛውን እንቅበር … ይባላል

- ሥልጣኔ፣ ከተከበረ ቤተሰብ መሆኔ፣ ጎሳዬ … ሁሉ ዋጋ ያጣል፤



ዱንያ ይህን ያህል ቀላልና ተራ ነገር ነች፤ የምንሄድበት ዓለም ግን አቤት ክብደቱ! ማስፈራቱ! …

በሕይወት ያለህ ወዳጄ ሆይ! በመሞትህ ሦስት ዓይነት ሐዘን አለ

1- የሚያውቁህ ዋ ያ ሚስኪን እኮ ሞተ! ይላሉ

2- ባልደረቦችህ ለሰዓታት አለያም ለቀናት ያዝኑና ወደ ሳቅና ጨዋታቸው ይመለሳሉ፣

3- ትልቁ ሐዘን ያለው ቤትህ ነው፣ ቤተሰብህ ጋ … ሁሌም ያስታውሱህ ይሆናል፣

የዱንያ ታሪክህ በዚህ መልኩ አበቃ ፤ የመጨረሻው ዓለም ታሪክህ ተጀመረ

ሁሉ ነገርህ ተወሰደ፣ ፈረሠ፣ አለፈ፣ ጠፋ!!!

1- መልክህ፣

2- ሀብትህ፣

4- ጤናህ፣

5- ልጅህ፣

6- ቪላህ፣

7- ዝናህ፣

8- ሚስትህ/ባልሽ

ካንተ ጋር ሥራህ ብቻ ቀረ

እውነተኛው ሕይወት ተጀመረ፡፡

እዚህ ላይ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ/ሽ

ለአኺራህ ምን አዘጋጀህ!! እስቲ በጥልቀት አስብ፡፡

እናም በርታ፣ በርቺ እህቴ

1- በግዴታዎች፣

2- በሱንና ነገሮች፣

3- በድብቅ መፅውት፣

4- መልካም ሥራ አብዛ፣

5- ሌሊት ተነስተህ ስገድ፣

ትድን ዘንድ ጠንክር፣ ይሳካልህ ዘንድ በርታ፡፡

መልካም ንግግር ምጽዋት ነው፡፡ ምንም የለኝም አትበል፡፡ ሌላ ነገር ብታጣ ይህችን በእጅህ የገባችውን ፅሑፍ መጽውት፣ ምንም ጉልበትና ጊዜ አይወስድብህምና አታመንታ፡፡

ለወዳጅ ዘመዶ ሼር ሼር ሼር .....✔️

@Halali_tube_bot 👈ለአስተያየት ይጠቀሙ

@HALALI_TUBE
@HALALI_TUBE
#ሴት_ልጅ_የታላቁና የምርጡ ነቢይዐለይሂ አፍዶሉ ሶላቱ ወሰላም አማና ናት፡፡
ረሱሉ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም በተከበረዉ ሐዲሳቸዉ ላይ እንድህ ሲሉ ይናገራሉ፦
"إنِّي أُحَرِّجُ حَقَّ الضَّعِيفَينِ: اليَتِيم وَالمَرْأةِ."

የሁለት ደካሞችን መብት የየቲምንና የሴትን መብት ጥብቅ አድርጌባችኃለሁኝ፡፡
"أكْمَلُ المُؤمِنِينَ إيمَانًا أحْسَنُهُمْ خُلُقًا، وخِيَارُكُمْ خياركم لِنِسَائِهِمْ."
ከሙእሚኖች ኢማኑ ሙሉ የሆነ፣ከመካከላችሁ መልካም ስነ ምግባር ያለዉ፣ ከእናንተ ዉስጥ በላጮቹ ለሴቶቻቸዉ ምርጥ የሆኑት ናቸዉ፡፡
ባል ከሚስቱ ጋር የሚያደርገዉ ግንኙነት በብሩሕ ፈገግታ የታጀበና ትዕግስት ያልተለየዉ እንድሁም ሚስቱን በመንከባከብ ፅኑ መሰረት ላይ የቆመ ከሆነ ከሁሉም በላጭ እንደሆነ ረሱሉ አሚንዐለይሂ አፍዶሉ ሶላቱ ወሰላም በተከበረዉ ሐዲሳቸዉ ገልጸዋል፡፡የእኛ ሞደል ረሱሉ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ከማንምና ከምንም በላይ ለቤተሰቦቻቸዉ ብሎ ለሚስቶቻቸዉ እጅግ አዛኝ፣ትሁት ተናናሽና ደግ ነበሩ፡፡

ሼር🙏
ለተጨማሪ ትምህርቶች

#በቴሌግራም_አድራሻችን👇👇


@HALALI_TUBE
@HALALI_TUBE
የፎዚያ መልክት:
ፎዚያ እባላለው፣ ሁለት ልጆች አሉኝ፣ 26 አመቴ ነው
ይህንን መልክቴን ለሁሉም ጓደኞቻቹ በስፋት እንድታሰራጬልኝ እንደ አንድ
ሙስሊም እጠይቃቹሀለው!
ዱዐ እንድታደርጉልኝ እጠይቃቹሀለው ምክንያቱም የCancer በሽተኛ
ሆኛለው፤ አላህን የምትወዱት ከሆነ ለሁሉም page መልክቴን አድርሱልኝ፤
በሀቅ የሚገዙት አምላክ የለም ከሙሀመድ/ሰዐወ/ ጌታ ውጪ እሱም
የአላህ መልክተኛ ነው!
በአላህ እጠይቃቹሀለው በሁሉም group አሰራጭታቹ ዱዐ እንድታረጉልኝ፤
አላህ እንዲፈውሰኝ፣ እንዲአዝንልኝ ዱዐ አርጉልኝ!!!
ለ አላህ ብላቹ ለ እህታች ዱዐ አድርጉላት ።🙏🙏🙏😭😭 አላህ አፊያ ያርግሽ ፎዚ። አላሁመ አሚን😭🙏🙏
@HALALI_TUBE
@HALALI_TUBE
@HALALI_TUBE
💥::::::::::ዱንያ ውስጥ::::::::💥

#ዱንያ ውስጥ ሆነን ቤት በቀየርን ቁጥር ከሱ የተሻለን ቤት እንመኛለን ።

#አኺራ ላይ ግን ጀነት ከገባህ ከሷ ውጪ ወደ ዉጪ ነው የምትለው።

( إِنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ كَانَتْ لَهُمْ جَنَّٰتُ ٱلْفِرْدَوْسِ نُزُلًا )

☞እነዚያ ያመኑና መልካም ሥራዎችን የሠሩ
የፊርደውስ ገነቶች ለእነሱ መስፈሪያ ናቸው ፡፡"
( خَٰلِدِينَ فِيهَا لَا يَبْغُونَ عَنْهَا حِوَلًۭا )

☞በእርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ከእርሷ መዛወርን የማይፈልጉ ሲኾኑ (መስፈሪያቸው ነው) ፡፡"

[ከህፍ 107 - 108]

☞ አላህ ከጀነት ሰዎች ያድርገን
አሚንንንን🤲🤲

share your friends

@HALALI_TUBE
@HALALI_TUBE
🚫:::::::::::::::ሙሲባ:::::::::::::🚫

ኡሙ ሰለማ አላህ ስራዋን ይውደድላትና የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ሲሉ ሰማሁ አለች:

☞ሙሲባ ሲደርስበት

إنا لله وإنا إليه راجعون
اللهم آجرني في مصيبتي
واخلف لي خيرا منها

"እኛ የአላህ ነን! ወደእርሱም ተመላሾች ነን!
አላህ ሆይ በደረሰብኝ ነገር ምንዳን ፃፍልኝ! ከእርሱ የተሻለም ተካልኝ"
ያለ ሰው አላህ ደግሞ በደረሰበት ነገር ምንዳን ፅፎለትና ከእርሱ የተሻለም ቢተካለት እንጂ አይተወውም አሉ።

☞አስከትላም ኡሙ ሰለማ እንዲህ ትላለች:
አቡ ሰለማ (ባለቤቴ) በሞተ ግዜ " ወደመልክተኛው ﷺ በመጀመሪያ የተሰደደው ቤት ሆኖ ሳለ ከአቡ ሰለማ የተሻለ ከሙስሊሞች ማን አለና (አላህ ማንን ይተካልኛል?) " አልኩ!

አላህ ደግሞ ከእርሱ (አቡ ሰለማ) የተሻለ የአላህ መልክተኛን ﷺ ተካልኝ።"

ሙስሊም፣ አቡ ዳውድ እና ነሲ ኢ ዘግበውታል

ሼር🙏🙏🙏

@HALALI_TUBE
@HALALI_TUBE
አሏህ እውነት በዘይል(ጂራት)ይገለፃልን ?
አሏህን በ ذيل(ጭራ)ለገፀው ወሀቢ መልስ
① አሏህን በሃላ ጭራ (ጂራት) መግለፅ አይችልም
② መጠነኛ እና በቂ መልስ አሏህን በዘይል ለገለፀው ወሀቢ

③ ድብቅ መርዝ ወደ ህዝቡ ይፋ ወጣ
④ ቁሸይሪይ ስለ ሙጀሲሞች ምን አሉ
⑤ ከአረበኛ ወደ አማርኛ በቅጥታ የተሰጠ መልስ
በ ሀቢብ ኑሩ

Share 🙏🙏🙏

@HALALI_TUBE
@HALALI_TUBE
አስተያየት ፣
ወቀሣ፣
ከስህተት ርምት ፣
ወንድማዊ ምክር፣
ቅሬታ ፣
የግል ምልከታ…………ወዘተ
#በአጠቃላይ_ይጠቅማል_የምትሉትን ሀሣብ ለመቀበል ዝግጁ ነኝና በቦቱ ገብታችሁ …………

#ገስፁኝ
#አርሙኝ
#ኮርኩሙኝ
#ተቆጡኝ
#ምከሩኝ ወሏህ ከስህተቴ እመለሣለሁ።
ተራ ከእውቀት ነፃ የሆንኩ ወንድማችሁ ነኝ።

አደራ ግን ወሏሂ ሱመ ወሏህ ኡስታዝ አይደለሁም፡፡
እኔ አንድ ተራ ሙስሊም ወጣት ብቻ ነኝ።

ስለዚህ ሣትፈሩ የመሰላችሁን የተሰማችሁን ሹክ በሉኝ ጀግኖቼዋ
👇👇👇👇👇👇👇
@HALALI_TUBE_BOT
@HALALI_TUBE_BOT
@HALALI_TUBE_BOT
#👇ሙስሊም ከሆንክ ይሄንን በሚገባ አንብብ

• ለምንድን ነው በመስጂድ ውስጥ እየተኛን በፓርቲዎች ላይ ነቃ የምንለው
• ለምንድነው ከአላህ ጋር ማውራት እየከበደን አሉባልታ ወሬዎችን ለማውራት የሚቀለን
• ለምንድነው ለጌታችን የመፅሐፍ መልእክት (የቁርአን መልእክት) ችላ ለማለት እየቀለለን አስቀያሚ መልእክቶችን ለመመለስ የሚቀለን
• አንተ ወይም አንቺ ይሄንን መልእክት ለጓደኞችህ(ሽ) ታስተላልፈለህ ወይስ ችላ ትለዋለህ
• አላህ እንዲህ ብሏል "አንተ እኔን ከጋደኞችህ ፊት ብታስተባብለኝ እኔ አንተን የትንሳኤ ቀን አስተባብልሀለው (ነፍግሀለው)
• እያንዳንዱ ሙስሊም አሁኑኑ "አስተግፊሩላህ ወአቱቡ ኢለይህ" 3 ጊዜ ይበልና ይህንን መልእክት በcontact ላይ ለሚገኙ ሙስሊሞች ያስተላልፍ
• ኢንሻአላህ በትንሽ ደይቃ ውስጥ በቢሊየን የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ይሉት እና የአላህ ቁጣ ይበርድልናል
• ✿እስካሁን ያለውን በማንበብህ(ሽ) ያጣሀው(ሽው) ምንም ነገር የለም ስለዚህ ቀጣዩንም እንብብ(ቢ)
• የአዛን ጥሪ ስትሰማ(ሚ) ቶሎ ተነስተህ(ሽ) መልስ(ሽ) (ለሰላትም ተቻኮል(ይ)) የስልክህ(ሽ)ን ጥሪ ስትሰማ(ሚ) ለማንሳት እንደምትቻኮለው(ይው)🏃
• ቁርአንን በተመስጦ አንብብ(ቢ) የተላከልህን መልእክት እንደምታነበው(ቢው)
• አላህን ፍራ(ሪ) ሞትን እንደምትፈራው(ሪው)
• ሞትን አስታውስ(ሽ) ስምህን(ሽን) እንደምታስታውሰው(ሽው)
አንድ ሰጋጅ ምንያህል ደይቃ ነው ለሰላት የሚወስደው?

"ፈጅር" 4-6 ደቂቃ
"ዝሁር" 6-8 ደቂቃ
"አስር" 6-8 ደቂቃ
"መግሪብ" 5-7 ደቂቃ
"ኢሻ" 7-10 ደቂቃ
በአጠቃላይ 28-39 ደቂቃ ከ24 ሰአት ውስጥ
እኛ ለአላህ ብለን እምንጠቀመው ሰአት አለን?
80% ሰዎች ይህንን መልእክት አያስተላልፉም አንተ ወይም አንቺ ከሚልኩት እንድትሆን(ኚ) አመኛለው


የቂያማ ምልክቶች
• ግብረ ሰዶም
• ሰዎች ስለሌሎች አያት ቅድመ አያት ክፋት እና ቂም ማውራት
• ልብሶች አብዛኛውን የሰውነት ክፍል የሚያሳዩ መሆናቸው
• በሰማይ ላይ ብዙም ከዋክብት አይኖሩም
• ትላልቅ ህንፃዎች መብዛት
• የደጃል መምጣት
• የኢማም አህመድ መምጣት
• የኢሳ አለይሂሰላም መውረድ
• የእጁጅ እና መእጁጅ መምጣት
• ፀሀይ በገባች መውጣት( የይቅርታ በር በተዘጋ ጊዜ)
• ከመሬት ውስጥ አንዲት ፍጡር መውጣት እና ትክክለኛ አማኞችላይ ምልክት ማድረጓ
• ለ40 ቀናት ጉም መነሳት እና በዛምክንያትም እውነተኛ አማኞች ምንም እውቀትም ሆነ ስሜት ሳይሰማቸው መሞት
• ከባድ እሳት መነሳት በዛም ብዙ ነገሮች መውደም
• የካአባ መፍረስ
• ቁርአን ከሰውም ልብ ከወረቀትላይ መነሳት
• የጡሩንባ መነፋት በመጀመርያው እንስሳዎች አና ሰዎች መሞት
• በሁለተኛው ሲነፋ የአላህ ፍጥረት በሙሉ እንደገና ይነሳሉ ለፍርድ በአረፈት መሬት ላይ ይሰበሰባሉ
• ፀሀይ ወደ ምድር በጣም ትቀርባለች
• ነብዩ ሙሀመድ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰም እንዳሉት" ይህንን ዜና ለአንድ ሰውያደረሰ ( ያስተላለፈ) በፍረዱ ቀን ጀነት ላይ ቦታ ይዘጋጅለታል
• ይህንን መልእክት በስልካችሁ contact ላይ ላሉ ሙስሊሞች በሙሉ ላኩ ይህን መልእክት ችላ ካልከው(ሽው) የረሱልን ንግግር አስታውስ
• ይህንን መልእክት ለሌሎች አስተላልፍ(ፊ)
• እኛም የተከበረው የአላህ ቃል 250,000,000 ጊዜያት እንዲታወስ መላክ ጀምረናል
"ላኢላሀ ኢላ አንተ ሱብሀነከ ኢኒ ኩንቱ ሚነ ዟሊሚን" አላህ ኮሮናን ከአለማችን ያጠፋልን ዘንድ በሱ እንጠበቅ
ይህንን መልእክት አንዴ አንብበህ(ሽ) ለሁሉም በcontact ላይ ለሚገኝ ሙስሊም አስተላልፍ(ፊ) j
✿እባካችሁ እንዳታቋርጡት

አላህ ሁላችንንም ወደሱ ይመልሰን
ሼር 🙏🙏🙏
የፃፍኩት ትርጉም ስለሆነ ስህተት ካለው በዚ አስተካክሉኝ👇👇👇👇
@Halali_tube_bot
@Halali_tube_bot

@HALALI_TUBE
@HALALI_TUBE
ሙሉዉን አንብቢዉ ከዚያም በመጨረሻ ላይ ያለዉን ቁጥር እይ
ከዚያም ወስኚ
የአላህ መልእክተኛ ሰለላህ አለይህ ወሰለም እንዲህ ብለዋል ⇣
በሚዛን ላይ ከባድ የሆነች አላህ ዘንድ የተወደደች ንግግር ⇣
ሱበሃን አላህ ወቢ ሃምዲህ ሱበሃን አላህ አል አዚም
ሱበሃን አላህ ወቢ ሃምዲህ ሱበሃን አላህ አል አዚም
ሱበሃን አላህ ወቢ ሃምዲህ ሱበሃን አላህ አል አዚም
ሱበሃን አላህ ወቢ ሃምዲህ ሱበሃን አላህ አል አዚም
ሱበሃን አላህ ወቢ ሃምዲህ ሱበሃን አላህ አል አዚም
ሱበሃን አላህ ወቢ ሃምዲህ ሱበሃን አላህ አል አዚም
ሱበሃን አላህ ወቢ ሃምዲህ ሱበሃን አላህ አል አዚም
ሱበሃን አላህ ወቢ ሃምዲህ ሱበሃን አላህ አል አዚም
ሱበሃን አላህ ወቢ ሃምዲህ ሱበሃን አላህ አል አዚም
ከዚያም ቢያንስ ለ30 ሰዎች ላክላቸዉ ቢሉትም(ቢያነቡትም)
አምስመቶ ሺ ሚሊዮን ሃሰናትን በአላህ ፈቃድ ታገኛለህ
እንደዚሁ ደግሞ ከላክላቸዉም ሰዎች እያንዳንዳቸዉ ቢያንስ ለ30
ሰዎች ከላኩ አሁንም 4.680.000.000 ሃሰናትን ታገኛለህ
አታዉቅም መቼ እንደምትሞት ስለዚህ ሰደቀተል ጃሪያ አድርጋት
አሰራጫት ደቂቃ እንኳን ያህል አትወስድብህም የዉመል ቅያማ

#Share_share 🙏🙏

@HALALI_TUBE
@HALALI_TUBE
As wr wb ደረቅ መሬት በውሃ ነፍስ እንደምትዘራ ሁሉ ደረቅ ልብም በዚክርና በቁርአን ነፍስ ትዘራለች 🍂🍂

#ኢንሻአላህ_ሼር_በማድረግ #የአባሎቻችንን_ቁጥር_እናብዛ🙏🙏🙏

@HALALI_TUBE
@HALALI_TUBE
አንድ ሰው የ አስር ሶላት ከሚያልፈው ሀብት ንብረቱ ቤተሰቡ በአጠቃላይ ቢወድሙበት ይሻላል ብለዋል ነብዩ ሙሀመድ(ሰ.ዐ.ወ)

በሌላ ሀዲስ እንደተወራው ነብዩ ሙሀመድ ሰ.ዐ.ወ እንዲህ ብለዋል ፦ አንድ ሰው ሶላት ሲያመልጠው ጀሀነም ላይ 83 አመት (የአኼራ) ስሙ ይፃፋል

ቀብር ላይ ባመለጠው ወቅት እባብ እየመጣ ይነድፈዋል የእባቡ መርዝ ዱንያ ላይ ቢረጭ አረንጓዴ ተክል ሚባል አይበቅልም ነበር ብለዋል።


ሁለት ብርዳማ ወቅቶችን የሰገደ ጀነት ገባ ብለዋ ሰይዳችን ሰ.ዐ.ወ።(ብርዳማ ሰላት የተባሉት ሱብሂ እና ዐስር ናቸው።)


ሙስሊም ወንድም እህቶቼ የሶላትን ነገር አደራ አደራ።🙏
#share 🙏🙏🙏
@HALALI_TUBE
@HALALI_TUBE
❤️በአንድ ወቅት ነብዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ቢላል ኢብኑ ረባህን ከሗላው በፍቅር ስሜት እቅፍ አደረገው ይይዙትና።

ድምፃቸውን ቀይረው "እኔ ማን ነኝ ?" ብለው ይጠይቁታል.....
ቢላልም
"ኡመር ነህ ?"
"አይደለሁም።"
"አቡበክር መሆን አለብህ?"
"አሁንም ተሳስተሃል።"
"በቃ ኡስማን ነህ።"
"አላወቅከኝም።"
"አሊ ነህ ማለት ነው?"
....እያለ ያቀፈውን ሰው ማንነት ሲጠይቅ ይቆያል።
°
ከዚያ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ለቅቅ አደረጉትና ከፊት ለፊቱ በመምጣት
"ቢላል ሆይ! በእውነት እኔ መሆኔን አላወቅክም ነበር እንዴ ?" ሲሉ ጠየቁት።
°
ቢላልም “የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! በደንብ አውቄዎታለሁኝ ነገር ግን ለረጅም ጊዜ
እንዳቀፉኝ መቆየትን ስለፈልግኩኝ እንጂ"
ሲል
አይነት ፍቅር ነው? ያ ረብ!
ፊዳክ አቢ ወኡሚ ወደሚ ወነፍሲ ያረሱሉሏህ!!
ያአሏህ የእሳቸውን ፊት በጀና ለማየት አብቃን!!!
አሚንንንን.......

❤️❤️❤️

#ኢንሻአላህ_ሼር_በማድረግ #የአባሎቻችንን_ቁጥር_እናብዛ🙏🙏🙏

@HALALI_TUBE
@HALALI_TUBE
⭕️ አሰተማሪ ቂሳ

እዴት ያለ ባል

👉ባልና ሚስት ከተጋቡ አራት አመታት ተቆጥረዋል ግን ልጆችን መውለድ አልቻሉም ነበርና ወደ ሀኪም ቤት ችግሩን ለማወቅ ይሄዳሉ አስፈላጊውንምርመራ ማድረግ እንዳለባቸው ተነግሯቸው ወደ ቤታቸው ይመለሳሉ፣ የምርመራውን ውጤት ለመስማት ባል ወደ ሃኪም ቤት ቀድሞ ያመራል ዶክተሩ ጋር ሲገባ የተነገረው ውጤት እጅጉን አሳዛኝ ነበር ባለቤቱ መውለድ አትችልም መሃን ናት ባል የሰማውን ዋጥ በማድረግ አላህን ያመሰግናል ፣ ለዶክተሩም እንዲህ ይለዋል ባለቤቴን ይዜ እመጣለው ግን ስትመጣ መውለድ እንደማትችል አትንገራት ይልቁንስ እኔ መውለድ እንደማልችል አሳውቃት በማለት ለምኖ ያሳምነዋል፡

ዶክተሩም ባል ያለውን እሺ በማለት ለሚስት ባለቤትዋ መውለድ እንደማይችል እና ተስፋቹ አንድ አላህን ብቻ መማፀን ነው ሲል ከምክር ጋር ውጤቱን ያሳውቃታል ብዙም አልቆየ ይህ ወሬ በባልና ሚስት ቤተሰቦች ዘንድ ይሰራጫል፣ በዚህ መልኩ ለአምስት አመታት ያህል ከኖሩ በኋላ ሚስት ለባል ከዛሬ ጀምሮ ከሱ ጋር መኖር እንደማትችል እና ዘር ፍሬዋን ልጆችዋን ወልዳ ማየት እንደምትፈልግ ትነግረዋለች ፣ባል በጣም ሀዘን እየተሰማው ይህ የአላህ ውሳኔ ነው እባክሽ በአላህ ላይ ያለሽ ተስፋ የጠነከረ ይሁን በማለት ነገሩን ለማርገብ ይሞክራል እሷም ጥሩ ይህንንአመት እታገሳለው ከዛ በኌላ ግን ከኔ ጋር ትቆያለች ብለህ እንዳታስብ ትለዋለች እሱም በአላህ ተስፋውን አስጠግቶ ይስማማል ፡ሱብሃነሏህ የአላህ ውሳኔ ሆኖ በዛው አመት ሚስት በኩላሊት በሽታ ትጠቃለች ሀኪሞችም ግዴታ ኩላሊቷ መቀየር እንዳለበትና ካልሆነ ነገሮች ሊከብዱ እንደሚችሉ ይነግሯታል።

ሚስትም ይህንን ስትሰማ ወቀሳዋን በባል ላይአጠናክራ
ቀጠለች ሰበቡ አንተው ነህ ፍታኝ ኑሮዬን ልኑርበት ስልህ እምቢ ብለህ ብዙ ወቀሰችው በዚህ ወቅት ባል ባለቤቱን አስፈቅዶ ኩላሊት በፍቃደኝነት ለባለቤቱ የሚሰጥ ሰው ለማፈላለግ ከሀገር ውጭ እንደሚሳፈር ይነግራት እና ተሰናብቶ ከሆስፒል ይወጣል ብዙም አልቆየ ከሳምንት ቦኌላ ይደውላል አልሃምዱሊላህ ኩላሊት የሚሰጥ ሰው አግኝቻለው አብሽሪ በማለት ያበስራታል አንድ የአረብ ሀገረ ተወላጅ ወጣትም ያለችበት ሆስፒታል ድረስ መጥቶ ኩላሊቱን ሊሰጣት ፍቃደኛ መሆኑን ይነግራታል፡ ቤተሰብ ሁሉ
ተደሰተ ዱአው ዘነበበት ለነገሩ ኩላሊቱን የሚሰጠው በእርግጥ ባል እንጂ ይህ ወጣት አልነበረም። ሚስት እና ቤተሰብ እንዳያውቁ የተጠቀመው ዘዴ ነበር ፡ባልም አስፈላጊው የቀዶ ጥገና ከተደረገለት በኌላ ኩላሊቱን ለሚስት ይሰጥና የኩላሊት ዝውውሩ በተሳካ መልኩ ይጠናቀቃል ፡

አልሀምዱሊሏህ!!! ሚስትም ጤንነትዋ ሙሉ ለሙሉ ይመለስላታል ። መቼም ይህንን ከፍተኛ ክፈያ የከፈለን ባል ድካምና በአላህ ላይ ያለውን ተወኩል እና ኢማን ብሎም ተስፋ አላህ በከንቱ አይተወውም አይደል !!! ብዙም አልቆዪ ሚስት የመጀመርያ ልጅዋን መፀነስዋን ታውቃለች አላሁ አክበር !!! በ ዘጠነኛው ወር የመጀመረያው ልጅ ተወለደ ቤተሰብ ሁሉ በደስታ ተዋጠ ፥ ይህንን ሁሉ በቀን ውሎው መዘገብ ላይ ግን ከማስፈር ባል አልተዘናጋም ነበር በዚህ ሁኔታ ላይ ሳሉ አንድ ቀን በቤት ውስጥ ካለ ጠረጴዛ ላይ ይህንን መዘገቡን ረስቶ ጥሎት ከቤት ይወጣል ሚስትም አንስታ ማንበብ ትጀምራለች ያኔ ነበር እውነታው ሁሉ የተብራራላት በለቅሶ ተዋጠች ወዲያው

ባል ጋር 📲ደውላ ተንሰቅስቃ እውነታውን እንዳወቀች አስረዳችው እሱም እያለቀሰ ምን ያህል እንደሚወዳት ነገራት ፡፡ ታሪኩን ፀሀፊው ባልም ሚስቱ ለሱ ካላት ክብር እና ከፍተኛ ወዴታ የተነሳ ከዛ ቀን ጀምሮ ቀና ብላ በሙሉ አይኗ ደፍራ እንዳላየችውበመግለፅ ለባለፉት አስር አመታት ብቻውን ያለቅስ እንደነበር እና እምባውን ይጠርግለት የነበረ ሰው እንዳልነበረ እና ዛሬ ባለቤቱ ስታለቅስ አይዞች በማለት እምባዋን እንደሚያብስላት ይናገራል ፣፣ ይሄው ነው የሰብር
ውጤቱ መጨረሻው ጣፋጭ እና አስደሳች ነው።

አላህስ ከታጋሾች ጋር አይደል ?!!! አላህ ከታጋሾቹ ያድርገን አሚን🙏

#ኢንሻአላህ_ሼር_በማድረግ #የአባሎቻችንን_ቁጥር_እናብዛ🙏🙏🙏

@HALALI_TUBE
@HALALI_TUBE
ለዘፈን_አፍቃሪያን_መገሠጫ_ትሆን_ዘንዳ_ይህችን_ታሪክ_አንብቧት
👇👇👇
ታሪኩ እንዲህ ነው፦
*ልጁ በጣም ሙዚቃ ማዳመጥ ይወዳል። ጠዋት፣ ማታ፣ቀን፣ለሊት፣ሁልም ጆሮው ላይ ኤርፎን ሰክቶ፣ አላህ ለቁርአን፣እንዲሁም ለተግሰጽ የለገሰውን ጆሮ ለሃራም እናለማይወደው ድርጊት ይጠቀማል።


ታዲያ ከዕለታት አንድ ቀን ት/ቱን ጨርሶ፣ ቤት ይገባል። ልቡ የሚገኘው ዛሬ ምን አይነት ዘፈን አውርጄ ላዳምጥ ነው ።
ከዚያም ፍራሹ ላይ ጋደም ብሎ፣ ሞባይሉን ከፍቶ፣በማዳመጥ ላይ ሳለ የክፍሉ መብራት ድንገት በኃይል ድርግም ብሎ ይጠፋል ።
ደንግጦ የሞባይሉን ፍላሽ በማብራት፣ ኤርፎኑን ለመንቀል ቢሞክር እንቢ ይለዋል።
ከጆሮው ውስጥ የተጣበቀው ኤርፎን፣አልነቀልም ብሎ ብዙ አታገለው። በመጨረሻም ስላልቻለ ለቤተሰቡ ተናገረ።


ቤተሰቡ ሙዚቃ በማዳመጡ ቢናደዱም፣አሁን ለችግሩ መፍትሔ እንፈልግ በማለት በፍጥነት ወደ አቅራቢያው ከአንገት በላይ እስፔሽላይስት ህክምና ወሰዱት።ዶክቶሮች በድንጋጤ እንዲሁም በመገረም እንዲህ አይነት ሁኔታ አጋጥሟቸው እንደማያውቁና ከአቅም በላይ ስለሆነባቸው ወደ ሌላ የሕክምና ማዕከል ሪፈር ይጽፋለታል። ቤተሰብ በጣም ተጨንቋል።
ልጁ ምንም አያወራም፣ ዝምታን ተከናንቦ አይኑን ያቁለጨልጫል።በአብዋራ የተሞላ ፀጉሩን እያከከ በዙሪያው ያሉ ሰዎች የሚያወሩትን ለማዳመጥ ይሞክራል። ነገር ግን ምንም ነገር አይሰማውም። ጆሮው ደን ቁሯል።
አላህ የሰጠውን ጆሮ ቁርአንን ለማዳመጥ ሳይጠቀም ሙዚቃ አዳምጦበታል። በዚህም የፀፀተው ይመስላል።


ወደ ሌላ ሕክምና ማዕከል ተጉዘው ከከባድ የ 2፡00ሠዓት ቀዶ ጥገና ሕክምና በኃላ ኤርፎኑ ለብቻው መወገድ ስላልቻለ ሁለቱ ጆሮዎች፣ከቦታቸው ተነቅለው የማዳመጥ ፀጋን አሳጥቶት ከሕክምና ማዕከሉ ወደ ቤት ተመለሰ። ከዚያ በኃላም ጤና እያለው ያልቀራውን ቁርአን ለማንበብ ይታገላል።
ሕይወቱንም በፀፀት እና በማልቀስ ለመግፋት ተገዷል።

ኢኽዋኒ ወ አኽዋቲ አላህ የሰጠንን ፀጋ እሱን ለማመስገን እንጂ፣እሱን ለማስቆጣት አንጠቀመው። ሙዚቃን ከመስማት ርቀው፣ ቁርአንን በማዳመጥ ከሚረኩት ያድርገን!!!
አላሁመ አሚን!

Share ማድረጎን አይዘንጉ 1 ሰው በኛ ሰበብ ሊመለስ ይችላል እናም share ለማድረግ አንሰስት ።
በተቻለን አቅም ለሌሎች በማድረስ ከሀራም ነገራቶች እንዲርቁ ሰበብ እንሁናቸው ።

@HALALI_TUBE
@HALALI_TUBE
#ቁርአን ትልቅ ስጦታና እርጋታ ነው
•ልቡ ውስጥ የቁርአንን ፍቅር አኑሮ ያተለቀ ሰው.....
×አላህ በሰዎች መካከል ደረጃውን ከፍ ያደርግለታል።


join join join
👇👇👇👇👇👇👇👇
@HALALI_TUBE
          
አንዲት ታላቅ እናት ለፈጅር ሶላት ልጆቿን እንዲህ እያለች ትቀሰቅሳቸው ነበር፦
"ለሰላት ተነሱ! … ጀነት ውስጥ ከመሀከላችን አንድም ሰው እንዲጎል አንፈልግም!"
ውብ ተርቢያ ፤ በአላህም ላይ የተጣለ ያማረ ተስፋ!
#share 🙏🙏🙏

@Halali_tube
↪️ኢብራሂም ኢብኑ አድሀም የገጠመውን አስገራሚ ክስተት እንዲህ ሲል ያጫውተናል :–
《ሀጅ ለማድረግ በመጓዝ ላይ ሳለሁ ምግብ የያዘ ምሳቃዬን አንድ አሞራ ይዞብኝ ከነፈ ፆሜን መዋሌ አሳስቦኝ እከተለው ጀመር ከርቀትም ወደ አንድ ዋሻ ምሳቃዬን ይዞ ሲገባ አየሁት ተከትዬው ገባሁ አንድ ሰውዬ በዛ በረሀ ብቻውን እግርና እጁ ታስሮ የኔን ምግብ አቀርቅሮ በአፉ እንደ ዶሮ ሲመገብ ተመለከትኩት ማን እንዳሰረውና ለምን እንደታሰረም ጠየኩት እሱም 《 ሀጅ ለማድረግ በወጣሁበት ሽፍቶች ንብረቴን ዘርፈው እጅና እግሬን ጠፍረው አስረው ሜዳ ላይ ጥለውኝ ሄዱ
ጌታዬ ሆይ! አንተኑ ለመገዛት ከቤቴ ወጥቻለሁና የሪዝቄን ነገር አደራ በማለት ተማፀንኩት ይሄው እንደምታየው አላህ ይህን አሞራ ሰበብ አርጎልኝ ቁርሴንም ምሳዬንም እያመጣ ይመግበኛል።》

እናም ወዳጃችን አላህ የከፈተውን ጉሮሮ ሳይዘጋው አያድርምና ተወኩል ላይ አደራ🙏

#ኢንሻአላህ_ሼር_በማድረግ #የአባሎቻችንን_ቁጥር_እናብዛ🙏🙏🙏

@HALALI_TUBE
@HALALI_TUBE
▪️ፈተና መብዛቱ ለኸይር ነው

🔻አብሽር አሏህ ፈተናን ባንተ ላይ ማፈራረቁ ስለጠላህ አይደለም። ነብያችን - ﷺ - የቲም ነበሩ። እናታቸውን በ6አመታቸው አጥተዋል ፤ ርቧቸው ድንጋይ ሆዳቸው ላይ አስረዋል ፤ ሌላም ብዙ ፈተና ደርሶባቸዋል። ታዲያ አሏህ ጠልቷቸው ነው ብለህ ታስባለህን? በጭራሽ.
°
🔻እንደውም በተቃራኒው እንደሚወድህ አመላካች ነው። ነብያችን - ﷺ - ይህን ስላሉ ፦ [ አሏህ ህዝቦችን ከወደደ ይፈትናቸዋል። ] (ሙስነድ ኢማሙ አሕመድ ፥ 23623). በሌላም ሐዲስ ላይ [ ከሰዎች ሁሉ በላእ የሚበረታባቸው ነብያቶች ናቸው ከዛም ደጋግ የአሏህ ባሪያዎች ናቸው። ] (ሲልሲለት አስሶሒሓህ ፥ 144).
°
🔻አማኝ በሆነ ሰው ላይ ፈተና መብዛቱ አሏህ ለሱ መልካምን ነገር እንዳሰበለትም አመላካች ነው። ረሱል - ﷺ - እንዲህ ብለዋል ፦ [ አንድን ሙስሊም ከድካምም ይሁን ከበሽታ ከጭንቅም ይሁን ከሓዘን ከችግርም ይሁን ከጭንቀት ሙሲባ አይደርስበትም ከምትወጋው የሆነች እሾህም ብትሆን አሏህ በሷ አማካኝነት ከወንጀሉ ቢያፀዳው እንጂ። ] (ሶሒሁል ቡኻሪ ፥ 5641). አሏህ ፈተናን ታግሰው እሱ ከሚወዳቸው ባሪያዎቹ ያድርገን አሚንንን🙏🙏🙏

#ኢንሻአላህ_ሼር_በማድረግ #የአባሎቻችንን_ቁጥር_እናብዛ🙏🙏🙏
@HALALI_TUBE
@HALALI_TUBE
#ከጀናዛ_ማጠቢያ_ክፍል

ከሴቶችን የጀናዛ ማጠቢያ ክፍል አንዲት እህት ደወለችልኝ ጀናዛዋን ለሰባት ሆነንም ማንሳት አልቻልንም።
«ምን እናድርግ እንዴት ወደ ማጠቢያዉ ሳጥን ላይ እናስቀምጣት?» አለችኝ በጥያቄዋ ትንሽ ግራ ተጋባሁና "ሰዉ ጨምሪ" አልኳት ከተወሠነ ደቂቃ ቦኋላ መልሳ ደወለችልኝ አላነሳችኋም አልኳት "ከብብቷ ስር ወገቧ ላይና ሁለት እግሮቿ ላይ ገመድ አስረን 12 ሆነን አነሳናት የሚገርም ነገር እየተመለከትኩ ነዉ። ጀናዛዉ ይንቀሳቀሳል ውዱዕ ላደርግላት ስል እጄን እየያዘችኝ አስቸገረችኝ ወዱዕ ላደርግላት አልቻልኩም። " አለችኝ "አረ እህቴ በጣም ተጋኗል ሙት እንዴት ይንቀሳቀሳል አልኳት በአላህ ይሁንብኝ የሆነዉን ነዉ የነገርኩህ አጠገቤ ያሉትን ልጆቿን ቤተሠቦቿን መጠየቅ ትችላለህ አለችኝ እስቲ ጠብቂ ዶክተሮች ይምጡና መሞቷን ያረጋግጡልን አልኳት።
ደወልንላቸዉ ጀናዛዉ ሲታጠብ እንደሚንቀሳቀስ ነገርናቸዉ 4ሴት ዶክተሮችን ላኩልን መሞቷን ካረጋገጡ በኋላ በሚያዩት ነገር በጣም ተገረሙ የሴትየዋ ልጅ እየጮኸች ታለቅስ ጀመር ደወልኩላት እናትሽ ትሠግድ ነበር ? ብዬ ጠየቅኳት አዎ ሶላት አምልጧት አያዉቅም ሆኖም ግን ሠዉና ሠዉን ሳታጣላ ዉላ አታዉቅም በየሠርግቤቱ በየለቅሶ ቤቱ እየሄደች ሠዉን ከሠዉ ታባላለች ብዙ ጊዜ መከርናት አስታወስናት ልትመከር ግን አልቻለችም
ሡብሀነላህ አልኩ አላህ በዱንያ ላይ በልጇ አስመሠከረባት ነቢያችን (صلى الله عليه وسلم) እናንተ በምድር ላይ የአላህ ምስክሮች ናችሁ ባሉ ግዜ እዉነት ተናገሩ እንደዚያዉ እያለች ያለ ጠሀራ ቀበርናት ይላሉ።

ለወዳጅ ዘመድዎ ሼርና ፎርዋርድ በማድረግ ያዳርሱ
በእርስዎ ሰበብ አንድ ሰው ቢቶብት ወይም ባለበት ጠንካራ አቋም ላይ ቢፀና ከፍተኛ አጅርን ይጎናፀፋሉ
በቻናላችን በሚሰጡ ትምህርቶች ተሳታፊ ለመሆን ይህን ይጫኑና ጆይን ይበሉ👇
@HALALI_TUBE

#ኢንሻአላህ_ሼር_በማድረግ #የአባሎቻችንን_ቁጥር_እናብዛ🙏🙏🙏

@HALALI_TUBE
@HALALI_TUBE
2025/02/05 20:45:48
Back to Top
HTML Embed Code: