Telegram Web Link
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
"ሰውን ስትረዳው ጎሳውን፣ ጾታውን፣ ሃይማኖቱን ብለህ አትርዳው ስለ ክርስቶስ ስም ብለህ እርዳው።"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

@Finote_tsidk
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ትዕቢት የነበረንን መልካም ምግባር ሁሉ የሚያሳምም ደግሞም የሚገድል ክፋ ደዌ ነው፡፡"
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)

@finote_tsidk
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
“እንደ እባብ ልባሞች ኹኑ” ማቴ.10÷16

እባብ ራሱን (ጭንቅላቱን) ለማዳን ሲል ሌላው ሰውነቱን ለአደጋ እንደሚያጋልጥ ኹሉ አንተም እንዲህ አድርግ፡፡ ሃይማኖትህን ለመጠበቅ ስትል ሀብትህን ወይም ሰውነትህን ወይም የዚህ ዓለም ሕይወትህን ወይም ያለህን ኹሉ እንኳን መስጠት ካለብህ ይህን በማድረግህ በፍጹም አትዘን!

አንተ ሃይማኖትህን ይዘህ ወደ ወዲያኛው ዓለም ስትሔድ እግዚአብሔር ደግሞ ኹሉም ነገር እጅግ ውብ አድርጎ ይመልስልሃል፤ ሰውነትህን በታላቅ ክብር ያስነሣልሃል፤ ከሀብት ከንብረት ይልቅም ከመግለጽ ኃይል በላይ የኾኑ በጎ በጎ ነገሮችን ይሰጥሃል፡፡ ኢዮብ ዕራቁቱን ኾኖ በአመድ ላይ ከሞት እልፍ ጊዜ የሚከፋ ሕይወትን እየመራ የተቀመጠ አይደለምን? ነገር ግን ሃይማኖቱን ስላልጣለ አስቀድሞ የነበረው ኹሉ እጅግ በዝቶ ተመልሶለታል፤ ጤናውና ውብ የኾነ ሰውነቱ፣ ልጆችን፣ ሀብቱን፣ ከዚህ ኹሉ የሚበልጥ ደግሞ አክሊለ ትዕግሥትን አግኝቷል፡፡

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ - #ገብረ_እግዚአብሔር_ኪደ)

@finote_tsidk
@finote_tsidk
#ይቅር_በለኝ ...

የምህረት ባለቤት፣ የይቅርታ ምንጩ፣ የርህራሄ ባህሩ፣ የአዛኝነት ልኩ፣ የተቀባይነት ሚዛኑ እግዚአብሔር ሆይ ምህረትህ ጥላ ይሁነኝ። አንተን በመበደል መትጋቴን ይቅር በል። አንተን በማሳዘን መዝለቄን እኔም ጠልቼዋለሁና ምህረት አድርግልኝ።

አንተን አውቄ እንዴት እንዲህ እኖራለሁ? የአንተ ልጅ መሆኔ በግብሬ እንዲገልጥ አቅም ሁነኝ። የኔ ጌታ እኔ ምንም አቅም እንደሌለኝ ገብቶኛል አቅሜ አንተ ሁን። በራሴ ስጋ ስለለበስኩኝ ይህም ስጋ የኃጢአት ዝንባሌ በውስጡ በመኖሩ ከስጋዬ ጋር ትግል ገጥሜ አንተን እንዳላሳዝንህ ደግፈኝ። አንተን የሚያከብር የአንተ ጸጋ ይብዛልኝ።

ስጋ ለእግዚአብሔር ህግ መገዛት ተስኖታል ተብሎ በቃልህ እንደተጻፈው በስጋ ሳይሆን በመንፈስ ተገዝቼልህ ስጋዬ ደግሞ እንዲታዘዝህ እርዳኝ። ሁሌ ለነፍሴ ማድላት እንዲሆንልኝና ስጋዬን መጎሰም የምችልበት አቅም የምትሰጠኝ ጌታዬ ጸጋህን በውስጤ አፍስስልኝ።

ለቁጥር ለሚታክቱ ጊዜያት በአንተ ላይ መሸፈቴን አውቀዋለሁ፣ ብዙ ማጥፋቴን እና መበደሌን ተረድቻለሁ። ይቅር እንድትለኝ በፊትህ ቀርቢያለሁኝና የማይነጥፍ የምህረት ባለቤት እግዚአብሔር ሆይ ይቅር በለኝ። 

አንተን በድዬ ደስ ቢለኝ ምን ይርባኛል? አንተ በእኔ ተከፍተህ እኔ በድሎት ነኝ ብል ምንስ ይጠቅመኛል? ለአንተ ጀርባ ሰጥቼህ ፊቴ ለሌላው ቢገለጥ ትርፌ ምንድን ነው? ምን ይጠቅመኛል አንተ ካሳዘንኩኝ? ምንስ ይረበኛል ፍቃድህን አልፌ በፍቃዴ ብራመድ? ምንስ እረብ አገኛለሁ ከምትጠቅመኝ ከአንተ ሸሽቼ የስጋ መሻቴን ብከተል? ..... ምንም ምንም አልጠቀምም። ምንም ....

ልለይ እስኪ ከማይረባኝ አልሂድ በቃ ትላንት በሄድኩበት ጎዳና። በሰጠኸኝ በአዲሱ ቀን እኔም አዲስ ሆኜ መኖር እንድችል በጸጋህ ደግፈኝ። ትላንቴን ይቅር ልትል ታማኝ የሆንከው አምላኬ እግዚአብሔር ሆይ በማይበጠስ የምህረት ሰንሰለት አጥረህ የምታኖረኝ አንተ ነህና ዛሬዬን በምክርህ እንድኖር ምህረትህን አብዛልኝ።

አድርጌው የማዝንበት ነገር አንተን አያከብርምና ክብርህ በሌለበት ህይወት ውስጥ እንዳልገኝ እግሮቼን እና ሃሳቤን ጠብቅ።  የማላዝንበት ነገር በማድረግ እንድኖር እና ልክ ላልሆነ ነገር ተሰልፌ ልክ እንደሆንኩኝ እንዳይሰማኝ ማስተዋልን አድለኝ።

ከላይ ስታይ መንፈሳዊ ውስጤ ሲታይ አለማዊ አልሁን፣ ሰዎች ሲያዩኝ ጥሩ ነገሬ አንተ ስታየኝ ግን መጥፎ ሆኜ አልገኝ፣ በአደባባይ መልካም በጓዳዬ መጥፎ አልሁን፣  ከጸጋህ የተነሳ አንተን በመምሰል ልምምድ ውስጥ አሳድገኝ። 

“እግዚአብሔርን መምሰል እጅግ ማትረፊያ ነው፤” 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፥6

ዲያቆን ተስፋ መሠረት
📆 ሐምሌ 20 2016 ዓ.ም ተጻፈ

  ➟ @finote_tsidk
  ➟  @finote_tsidk
#ልንናደድ_የሚገባን_ማን_ላይ_ነው?

ብዙ ኃጢአቶችንና ወንጀሎችን የሠራ አንድ ሰው ለሠራው ኃጢአትና ወንጀል ሳይቀጣ ሲቀር አይተን ብዙዎቻችን እንበሳጫለን፡፡ ያ ሰው እንዲጠየቅና እንዲቀጣ እንፈልጋለን፡፡ ይህ ሳይኾን ከቀረ ግን ቅር እንሰኛለን፤ እንናደዳለን፡፡

እንዲህ የምንኾነው ግን የገዛ ራሳችንን ግብር ስለማንመለከት ነው፡፡ መበሳጨትና መናደድ ቅርም መሰኘት የሚገባን በገዛ ራሳችን ላይ ነውና፡፡ እያንዳንዳችን ለራሳችን እንዲህ ብለን ልንጠይቅ ይገባናል፦ "በሌሎች ሰዎች ላይ ስንት በደል ፈጸምሁ? ለዚህ በደሌስ ስንቴ ሳልቀጣ ቀረሁ?"

በራሳችን ላይ ብዙ ምሳሌዎችን እንደምናገኝ ጥርጥር የለውም፡፡ ይህን ማወቃችን ደግሞ በሌሎች ሰዎች ላይ የተቆጣነው ቁጣና የተበሳጨነው ብስጭት እንደ ጢስ ተኖ እንደ ትቢያ በንኖ እንዲጠፋ ያደርጓል፡፡ ከዚህም በላይ ፊታችንን ወደ እግዚአብሔር እንድናዞር ስለ በደልነውም በደል ይቅርታንና ቸርነትን እንድንለምን ያደርገናል፡፡

እንዲያውም እኛ በበደልነው በደልና ሌሎች ሰዎች በሠሩት ኃጢአት ልዩነቱን እናስተውለው ይኾናል፡፡ ምናልባት የእኛ በደል የተሰወረና ለሌሎች ሰዎች የማይታይ ሕቡዕ ይኾናል፤ በአንጻሩ ደግሞ የሌሎች ሰዎች ኃጢአት በግልጽ የሚታይ ይኾናል፡፡

ታዲያ በዚህ ኹኔታ የእኛ በደል ንኡስ፥ የሌሎች ሰዎች ኃጢአት ግን ዐቢይ እንደ ኾነ ልናስብ ይገባናልን? በጭራሽ! ምክንያቱም በስውር የሚሠ'ራና ሌላ ሰው የማያየው በደል ብዙውን ጊዜ እጅግ አደገኛ ነው፡፡ ስርቆትንና ቀማኛነትን የመሳሰሉ በግልጽ የሚታዩ ኃጢአቶች ኃጢአት መኾናቸው በቀላሉ ይታወቃሉ፡፡ መታወቃቸው ብቻም ሳይኾን በቀላሉ ንስሐ ሊገባባቸውና ሊወገዱ የሚችሉ ናቸው፡፡ ውሸትን፣ ሐሜትንና በስውር ማታለልን የመሳሰሉ በስዉር የሚሠሩ በደሎች ግን በደል መኾናቸውን ለማወቅም ስለ እነዚህ ንስሐ ገብቶ ለማስወገድም እጅግ ክቡዳን ናቸው፡፡

(#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ - አምስቱ የንስሐ መንገዶች ገጽ 98-99)

@finote_tsidk
በፈተና ጊዜ፥ ደካማው ሰው "እንደዚህ የደረሰብኝ'ኮ" እያለ የሚያመካኝበት ሌላ ሰውን ይፈልጋል፤ ብርቱው ሰው ግን በፈተናው ይጸና ዘንድ እግዚአብሔርን ይፈልጋል፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

@finote_tsidk ♻️ @finote_tsidk
ሰው ሆኖ ሰው አደረገኝ
<unknown>
▬▬▬▬▬▬    ▬▬▬▬▬▬
▬ ●#ሰው_ሆኖ_ሰው_አደረገኝ  ● ▬
▬▬▬▬   ▬▬▬▬   ▬▬▬▬

🎤 ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን

ሰው ሆኖ ሰው አደረገኝ
በዱር በገደሉ ፈለገኝ
ሲራራልኝ ታማኝ ያለበሰኝ ግርማ
እልልታ ለስሙ ላዳነኝ በደሙ

ከድካም ሊፈታኝ ደክሞት አረፍ አለ
ከእሳት ሊነጥቀኝ ምን ያልሆነው አለ
ዳግመኛ እንዳልመጣ ከያዕቆብ ጉድጓድ
ፈሰሰ በልቤ የመዳኔ መውደድ (2)

በገዢዎች ግቢ የደም ላብ አላበው
ቆስሎልኝ ጌታዬ ውበቴን መለሰው
የገዳሙ ማዕድ የአለቱ ውሃ
ስትመገብ ዳነች ነፍሴ ከበረሃ (2)

በአላዛራዊው ፍቅር ለኔ አለቀሰ
የመዳኒቴ አምላክ እንዴት ቢወደኝ ነው
ዮም ፍስሃ ኮነ ተገኝቷል ድሪሙ
ሰማይና ምድር እልልታን አሰሙ (2)

ግሩም ርህራሄ ከልብ የመነጨ
የጠፋን ሚፈልግ ለመንግስቱ ያጨ
የማፅናናቱ አቅም ስብራቴን ሰብሮ
እንደሰው አቆመኝ መከራዬን ሽሮ (2)

መቃብር አልቀረም ሞቴን ሊገል ሞቶ
በገሊላ ቀድሞኝ አየሁት ተነስቶ
የትንሣኤው ተስፋ የልቤን እጅ ይዞ
እግሬ ተመልሷል ከኤማውስ ጉዞ (2)

  🇸 🇭 🇦 🇷 🇪 👇 👇 👇 👇

@finote_tsidk 💠 @finote_tsidk
@finote_tsidk 💠 @finote_tsidk
"ለነዲያን ምጽዋት ስትሰጡአቸው በዚያው ጥቂት መልካም ቃል ጨምሩበት"

ቅዱስ ኤፍሬም ሶሪያዊ
"ለወፎች ክንፍ የተሰጣቸው"
   
ለወፎች ክንፍ የተሰጣቸው በወጥመድ እንዳይያዙ ነው። ሰዎችም የማሰቡ ኃይልን የተሰጣቸው ኃጢአትን እንዲያስወግዱ ነው። እንግዲህ እንዲህ የማሰብ ኃይል ተሰጥቶን ሳለ ይባስ ብለን ከምድር አራዊት በታች የማናስተውል ከኾንን ሊደረግልን የሚችል ምህረት ወይም ይቅርታ እንደምን ያለ ምሕረት እንደምንስ ያለ ይቅርታ ነው?

በወጥመድ ተይዛ የነበረች ወፍ ድንገት ከወጥመዱ ብታመልጥ፤ ወደ ወጥመድ ገብቶ የነበረ አጋዘን ወጥመዱን በጣጥሶ ቢሄድ ከእንግዲህ ወዲህ በተመሳሳይ ወጥመድ እነዚህን መያዝ ከባድ ነው። የሕይወት ተሞክሮ ለሁለቱም ጥንቃቄን አስተምሯቸዋልና። እኛ ግን ምንም እንኳ በተመሳሳይ ወጥመድ ብንያዝም ተመልሰን ወደዚያ ወጥመድ እንወድቃለን፣ ምንም እንኳን በለባዊነት የከበርን ብንኾንም አእምሮ  እንደሌላቸው እንሰሳት እንኳን ቀድመን አናስብም፤ አንጠነቀቅም!

ሴትን በማየት እልፍ ጉዳቶችን ተቀብለን ወደ ቤታችን የተመለስነው፤ በዝሙት ተመኝተንም ስናበቃ ለአያሌ ቀናት ያዘንነው ስንቴ ነው? ነገር ግን ከዚያ በኋላም ቢሆን በዚሁ ጉዳይ ላይ ጠንቃቆች አልኾንም፤ አንዱን ቁስል ሳናገግም ወደዚያ ክፉ ጠባይ እንወድቃለን፣ በተመሳሳይ መንገድ እንያዛለን፤ እጅግ ጥቂት ለኾነች የደስታ ሽርፍራፊ ብለንም ረጅምና ተደጋጋሚ ሥቃይን እንቀበላለን።

ዘውትር "በወጥመዶች መካከል እንደምትኼድ በገደልም መካከል እንደምትመላለስ  ዕወቅ" የሚለውን ኃይለ ቃል ደጋግመን ለራሳችን ብንነግረው ግን ከእነዚህ ጉዳቶች ኹሉ እንጠበቃለን (ሲራ 9:13)

~ በእንተ ሐውልታት

@finote_tsidk ♻️ @finote_tsidk
@finote_tsidk ♻️ @finote_tsidk
#ጭማሪ

ዋና ነገር በሌለበት ጭማሪ ሊኖር አይችልም። የጭማሪ ህልውና ያለው ዋና የሚባለው ነገር ሲኖር ብቻ ነው። ጨምር ልንል የምንችለው ኖሮ የጎደለ ነገር ሲኖር ነውና ምንም በሌለበት ጨምር ወይም ጨምሪ ስንል ብንገኝ ከእብድ ሳንሻል እንቀራለን።

እስኪ አንድ ምሳሌ እናንሳ። ሻይ ቡና ለማለት አንድ ስፍራ ብትገኙ ልትጠጡ ያሰባችሁት ነገር ከፊታችሁ ሳይቀርብ ስኳር ጨምሪ ትሉ ይሆን? በጭራሽ አትሉም። ስኳር ይጨመር ከማለታችሁ በፊት የምትጠጡትን ቀርቦ ማየት እና ቀምሳችሁ ማጣጣም ግድ ይላል። ስለዚህ ቀዳሚው ነገር ጭማሪ የሚደረግበት ያ ዋናው ነገር ነው ማለት ነው።

መጽሐፍ ምንን ቀዳሚ ማድረግ እንዳለብን በግልጽ ያስረዳል። ጭንቀታችን ምን መሆን እንዳለበትም እንዲሁ። ስለምግብ እና ስለመጠጥ ወይም ስለልብስ ተጨንቀን ይሆን? በመጽሐፍ እንደተጻፈው እነዚህ ለእኛ አስፈላጊ እንደሆኑ የሰማይ አባታችን እግዚአብሔር ያውቃል።

ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። (ማቴ 6:33) ተብሎ በመጽሐፍ እንደተጻፈ ቀዳሚው ነገር ጽድቁን እና የእግዚአብሔርን መንግስቱን መሻት ነው። የእግዚአብሔርን መንግስት ባለመሻት ውስጥ ያለ የቱም ትርፍ የኪሳራ መሰረት ነው።

ሰው የእግዚአብሔርን መንግስት ሳይፈልግ ለስጋው ቢደክም፣ ለሚበላው ቢለፋ፣ ለሚጠጣው ቢጥር፣ ለምቾቱ ቢታገል በከንቱ እንደሚታገል ሰው ነው ምክንያቱም ከጋሪው ፈረሱን አስቀድሟልና። የሚከተለንን መከተል እድለቢስነት ነው። ከእኛ የሚጠበቀው ማስከተል ሆኖ ሳለ ከዚህ በተቃሳኒ ቆመን መከተል ከጀመርን አደጋ ላይ ነን።

ገንዘብን መከተል፣ በረከትን መከተል፣ ሀብትን መከተል፣ ብልጽግናን መከተል፣ እድገትን መከተል፣ ምቾትንና ድሎትን መከተል ሳይሆን ልኩ መንግስቱን እና ጽድቁን መከተል ነው። እኛ መንግስቱን እና ጽድቁን ስንከተል ይሄ ሁሉ ደግሞ እኛ ይከተለናል።

ይህን መርህ የሚስቱ ሰዎች አተርፍ ባይ አጉዳይ ለሚለው አባባል አይነተኛ ምሳሌ ይሆናሉ። ሰው የሚሮጠው የሚለፋውም ለማትረፍ ነው ነገር ግን የእግዚአብሔርን መንግስት ሳይኖረው ሰው ለዚህ ሁሉ ነገር ቢታትር ለማትረፍ ደክሞ እያጎደለ ነው ማለት ነው።

ለማትረፍ ሮጦ ኪሳራን መዝገን በእርግጥም አለመታደል ነው። እስኪ ያለ እግዚአብሔር መንግስት ሰው ምን ቢኖረው አትራፊ ይባላል? ያለ እግዚአብሔር ጽድቅ ሰው የቱ ከፍታ ላይ ቢሆን አትራፊ ይባላል? ሁሉ የሞላላቸው የአለማችን ቅንጡ ሰዎች እንኳን የእግዚአብሔር መንግስት ከሌላቸው ትተው የሚሄዱት ሀብታቸው ምን ሊረባቸው አይችልም? ምንም

“ሰው ዓለምን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል?” (ማርቆስ 8፥36) ተብሎም በመጽሐፍ የተጻፈው የነፍሳችን ጥያቄ የእግዚአብሔር መንግስት ስለሆነ ነው። ስለዚህ ከኋላ አትጀምሩ። ቤት ከጣሪያ እንደማይጀምር እንዲሁ የህይወታችሁን ግንባታ ከገንዘብ እና ከቁስ አትጀምሩ።

መሠረት የሌለው ቤት እንደማይጸና እንዲሁ የእግዚአብሔር መንግስት የሌላት እና የእግዚአብሔርን ጽድቅ ያለበሰች ነፍስ በዬትኛውም ስጋዊ ልብስ የኃጢአትን ብርድ ልትቋቋም አትችልም።  በጎደለች ነፍስ ስጋ ምንም አይነት ትርፍ ውስጥ ቢኖር ጉድለቱ አይሞላም። ምክንያቱም ከዋናው ጉድለት ካለ ጭማሪው ምንም ቢሆን ዋናው ስለማይሞላ ነው።

የነፍሱ ጥያቄ ሳይመለስ ሰው በስጋው ላለው ክፍተት ሙላትን ቢያገኝ ማግኘቱ ሁሉ የማጣቱ ምልክት ነው የሚሆነው። እና የህይወታችሁን ዋና ነገር የእግዚአብሔርን መንግስት እና ጽድቅ መፈለግ ላይ አድርጉ ሌላው የምትፈልጉት ነገር የሚከተላችሁ ይሆናል።

የሚከተላችሁን ስትከተሉ ብትኖሩ ግን ያ ነገር በረከታችሁ መሆኑ ቀርቶ እግዚአብሔር ከሰበላችሁ እረፍት የምትጎድሉበት መጥፊያችሁ ይሆናል። ማንም ሰው እንዲጠፋ የማይሻውን የእግዚአብሔር ጽድቁን እና መንግስቱን የመለግ አቅም እና ማስተዋል ይሁንልን። አሜን

ዲያቆን ተስፋ መሠረት
📆 ሐምሌ 25 2016 ዓ.ም ተጻፈ

ይቀላቀሉ  ➟ @finote_tsidk
ለሌሎች ያጋሩ  ➟  @finote_tsidk
"ከንስሐ አባትህ ጋር ስትሆን ጥያቄህን እንጂ ውሳኔህን አታቅርብላቸው፤ በልብህ ካሰብከው ጋር እንዲስማሙ ሳይሆን በሀሳብህ ላይ ሀሳባቸውንና ምክራቸውን እንዲሰጡህ አድርግ።"

ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሣልሣዊ

@finote_tsidk
ጾመ ፍልሰታ/ጾመ ማርያም/ 
  
   🌺ፍልሰታ ማለት ፈለሰ፤ ተሰደደ፤ ተጓዘ፤ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ሄደ ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ቃል ሲሆን ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ «ፈለሰት ማርያም እምዘይበሊ ኀበኢይበሊ፤ ድንግል ማርያም ከሚያልፈው ዓለም ወደማያልፈው ዓለም፣ ከምድር ሕይወት ወደ ሰማያዊ ሕይወት፣ ተሻገረች» በማለት ፍልሰታ የሚለውን ቃል ትርጓሜ አመሥጥሮ ገልጾታል፡፡

  🌺ጾመ ፍልሰታ ከእመቤታችን ድንግል ማርያም የዕረፍት ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ እመቤታችን በዚህ ዓለም ፷፬ ዓመታትን በሕይወተ ሥጋ ከቆየች በኋላ ጌታችን የእናቱን ተድላ ነፍሷን እንጂ ተድላ ሥጋዋን አይወድምና ጥር ፳፩ ቀን ፵፱ ዓመተ ምሕርት አረፈች፡፡ ዕረፍቷም እንደሌላው ሰው በሕማምና በድካም አይደለም፡፡ በገነት ዕፀዋት መዓዛ ተመስጣ ቅድስት ነፍሷ ከሥጋዋ ተለይታለች፡፡

  🌺ታሪኩ በነገረ ማርያም እንደተጻፈው ሐዋርያት እመቤታችንን በአጎበር አድርገው አክብረው ወደጌቴሴማኒ መካነ መቃብር ይዘዋት ሲሄዱ አይሁድ ለምቀኝነት አያርፉም ነበርና ቀድሞ ልጇን ተነሣ ዐረገ እያሉ ሲያውኩ ኖረዋል፤  እርሷን ደግሞ ተነሣች ዐረገች እያሉ ሊያውኩን ነውና «ኑ የማርያምን ሥጋ በእሳት እናቃጥለው» ብለው በምቀኝነት ተነሱ፡፡ ከመካከላቸው አንድ ታውፋንያ የሚባል አይሁዳዊ ከሐዋርያት እጅ ለመንጠቅ ዘሎ ሄዶ የአልጋውን ሸንኮር ሲይዝ የታዘዘ መልአክ በረቂቅ ሰይፉ እጆቹን ቆረጠው፡፡ እጆቹም በአልጋው ሸንኮር ላይ ተንጠልጥለው ቀሩ፡፡ የምሕረት እናት የሆነችው ድንግል ማርያም ቅዱስ ጴጥሮስ ጸልዮ እጆቹን እንዲመልስለት ነግራው እንደነበረ አድርጎለታል፡፡

  🌺የእመቤታችን ሥጋዋን መላእክት ከዮሐንስ ወንጌላዊ ጋር በገነት ከዕፀ ሕይወት ሥር ወስደው አስቀምጠውታል፡፡ ሥጋዋ ያለበትን ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ አይቶ እነርሱ ባለማየታቸው እመቤታችን ባረፈች በ፮ኛው ወር ከነሐሴ ፩ ቀን እስከ ፲፬ ቀን ድረስ ከጾሙ በኋላ በ፲፬ኛው ቀን ሥጋዋን እንደገና ከጌታ ተቀብለው በጌቴሴማኒ ባለው መቃብር ቀብረውታል፡፡

  🌺ከዚህ በኋላ እንደ ልጇ በ፫ኛው ቀን ተነሥታ መላእክት እየዘመሩላት ወደሰማያት ስታርግ፤ ሐዋርያው ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ በደመና ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለሰ ዕርገቷን በማየቱ መላእክት «እመቤትህ እርሷ ናት፤ስገድላት» አሉት፤ እርሱም «ወፈቀደ ይደቅ እምደመናሁ ይላል፤ከደመናው ሊወድቅ ወደደ» ምክንያቱም ቀድሞ የልጇን ትንሣኤ፤ ዛሬ ደግሞ የእርሷን ትንሣኤ ለማየት ብሎ ነው፡፡ እመቤታችንም «ትንሣኤየን ያየህ አንተ ነህ ሌሎቹ አላዩም» ብላ ሐዋርያት ገንዘው የቀበሩበትን የሐር ግምጃ ሰጥታ አጽናንታ ሰደደችው፡፡

  🌺ቅዱስ ቶማስ ኢየሩሳሌም ሲደርስ የእመቤታችን ነገር እንዴት ሆነ ብሎ ጠየቃቸው፤እነርሱም አግኝተው እንደቀበሯት ነገሩት፤ እርሱም ያየውን ምሥጢር በልቡ ይዞ «ሞት በጥር፤ በነሐሴ መቃብር፤ ለሰሚውም አያምር፤ይህ እንዴት ይሆናል?»፤ ቢላቸው ቅዱስ ጴጥሮስ «ድሮም አንተ ተጠራጣሪ ነህ፤ማን ያርዳ የቀበረ፤ ማን ይናገር የነበረ እንዲሉ፤ ገንዘን የቀበረን እኛ እያለን እንዴት ትጠራጠራለህ» ብለው ወደ መቃብሯ ሄደው መቃብሯን ቢከፍቱት ባዶ ሆኖ አገኙት፡፡ በዚህ ተደናግጠው ተያዩ፤ በዚህ ጊዜ ቅዱስ ቶማስ «አታምኑኝም ብዬ ነው እንጂ እመቤታችን ተነሣች፤ዐረገች፤ ይኸው ምልክቱ» ብሎ ገንዘው የቀበሩበትን ሰበን አሳያቸው፤ እነርሱም አምነው ሰበኗን ለበረከት ተካፈሉት፡፡

  🌺በዓመቱ ነሐሴ ፩ ቀን ሐዋርያት በመንፈሰዊ ቅናት ተነሳስተው «ቶማስ ትንሣኤዋን አይቶ እኛ ሳናይ እንዴት ይቀርብናል» በማለት ነሐሴ ፩ ቀን ሱባኤ ጀምረው በ፲፮ኛው ቀን የሐዋርያትን ሱባኤ ተቀብሎ እመቤታችንን መንበር ጴጥሮስን ተራዳኢ፣ ካህን እስጢፋኖስን ሠራዔ ዲያቆን አድርጉ ቀድሶ አቁርቧቸዋል፡፡ ከዚያ ጊዜ በኋላም ከነሐሴ ፩ እስከ ፲፭ ቀን  ጾመ ፍልሰታ ተብሎ ሁሉም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታይ ይጾመዋል፡፡

💛የጾሙ እና የትንሣኤዋ በረከት ተካፋይ ያድረገን፤ አሜን💛

🇯 🇴 🇮 🇳    ♻️  🇸 🇭 🇦 🇷 🇪

⋆⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⋆⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⋆
@finote_tsidk  ♻️  @finote_tsidk
@finote_tsidk  ♻️  @finote_tsidk
@finote_tsidk  ♻️  @finote_tsidk
⋆⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⋆⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⑉⋆

𝕕𝕠𝕟'𝕥 𝕗𝕠𝕣𝕘𝕖𝕥 𝕣𝕖𝕒𝕔𝕥 𝕚𝕟 𝕠𝕦𝕣 𝕡𝕠𝕤𝕥
"ጽንዕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ሆይ ልጅሽ ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኚልን፡፡ አእምሮውን ጥበቡን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን፡፡"

@finote_tsidk
@finote_tsidk
#ተወዳጁ_ልጅሽ_እንዲመግበኝ_ትለምኝልኝ_ዘንድ_እማጸንሻለሁ

እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ። የመድኃኒት እናት ሆይ በመዓልትም በሌሊትም አማላጅ ትሆኝኝ ዘንድ እሰግድልሻለሁ። እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ከእርሱ የሚገኘውን ኃይልን ይሰጠኝ ዘንድ ከአንቺ ወደ ተወለደው ልጂሽ እንድትለምኝልኝ እማጸናለሁ። በመወለዱ ድኅነት የተገባሽ ሆነሻልና። በሔዋን ውድቀት ሆነ። አብ በመላእክት አለቃ በቅዱስ ገብርኤል አማካኝነት ሰላምን የላከልሽ እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ። ሰላምታን ሰጠሽ ሰገደልሽም። ጸጋን የተመላሽ ሆይ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነውና ሰላምታ ይገባሻል። እነሆ ትጸንሻለሽ ልጅም ትወልጃለሽ፣ ስሙንም አማኑኤል ትይዋለሽ። የልዑል ኃይል ይጸልልሻል፤ ከአንቺ የሚወለደውም ቅዱስ ነው፤ እርሱም የልዑል ልጅ ይባላል አለሽ።

በተቀደሰው ስሙ ኅሊናዬን ልቡናዬን እንዲቀድስ ትለምኝው ዘንድ እማጸንሻለሁ። ንጽሕት ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ። የሕይወት ቃል ከአንቺ ሰው ይሆን ዘንድ በሥጋ ከአንቺ ይወለድ ዘንድ የተገባሽ የመድኃኒት እናት እመቤታችን ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ። ከአንቺ በመዋሐዱም እኛ ዳንን። እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ። በእናታቸው ማሕፀን ሕፃናትን የሚስላቸው ከአባቱ እና ከመንፈስ ቅዱስ ጋርም ሁሉን የፈጠረው በማሕፀንሽ የተቀረጸብሽ የብርሃን እናት ሆይ እሰግድልሻለሁ። ረቂቅ ድንቅ ምሥጢርን ዓለምንም ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣውን እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ እለምንሻለሁ። በመንፈሳዊ ልደት ይወልደኝ ዘንድ ወደ እርሱ ዓለምና አዳኝ ወደ ሆነች ዕውቀት ከፍ ያደርገኝ ዘንድ ወደ እርሱ እንድትለምኝልኝ እለምንሻለሁ፣ አማጸንሻለሁ።

የሕይወት መገኛ የነገሥታት ንጉሥ የባለሥልጣናቱ ባለሥልጣን የአምላኮችን አምላክ በበረት ያስተኛሽው እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ። አዳኝ ስለሆነው ስለስምሽ እንዲረዳኝ ትለምኝልኝ ዘንድም ወደ አንቺ እለምናለሁ፤ እማልዳለሁም። በማየቱ አዳምንና ከእርሱ ጋር ያሉትን ሁሉ ነጻ ያወጣውን በክንድሽ የታቀፍሽው እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ።

በረቂቅ መመልከቱ እንዲመግበኝ ከሰይጣን መሰናክልም እንዲያድነኝ ትለምኝልኝ ዘንድ እለምንሻለሁ፤ እማጸንሽማለሁ። ዓለማትን ሁሉ ለሚመግበው ጡትሽን ያጠባሽው የመድኃኒት እናት እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ እሰግድልሻለሁ፤ የሰማይ ኃይላት የሚመገቡትም ከእርሱ ነው። ነፍሴን በፈቃዱ ከጸጋው ይመግባት ዘንድ ወደ እርሱ እንድትለምኝልኝ እማጸንሻለሁ።

እመቤቴ ድግል ማርያም ሆይ ተወዳጁ ልጅሽ እንደ ፍጹም ፈቃዱ እንዲመግበኝ በየጊዜው በየሰዐቱ አማላጅ ሁኚኝ። ይህችም ወደ እርሱ የምትለምኝውን ልመና የተመላች መጽሐፍ ናት ። የለመንሁትን ሁሉ እርሱ ያደርግልሻልና። ኃጢአቴን ይቅር ይለኝ ዘንድ ወደ እርሱ እንድትለምኝልኝ እማጸንሻለሁ። ሰላምን ስለሰጠሽ ስለ አብ ከአንቺ ስለተወለደው አንቺንም ስለተዋሐደው ከአንቺም ሰው ስለሆነው ስለወልድ፣ ስለቀደሰሽ፣ ከሦስቱ ቅዱስ ለአንዱ ማደሪያ ለመሆን እስከሚገባሽ ድረስ ስላነጻሽ ስለመንፈስቅዱስም እለምንሻለሁ። አገልጋይሽን ተወዳጁ ልጅሽ እንዲመግበኝ ትለምኝልኝ ዘንድ እማጸንሻለሁ። ለዘለዓለሙ አሜን።

#ቅዱስ_ባስልዮስ_ዘቂሳርያ
(Deacon Birhanu Admass የተረጎመው)

@finote_tsidk ♻️ @finote_tsidk
@finote_tsidk  ♻️  @finote_tsidk
የቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ጸሎት

አምላኬ ሆይ ክፉ የማያስብ ምኞቶችም የማይጠጉት ንፁህ እና ቅን ልብን ፍጠርልኝ። ንፁህ ልብ መጥፎ ጨዋታን የማያውቅ ባልንጀራውን የማይነቅፍ ነው። ንፁህ ልብ ሁል ጊዜ በፍቅር የተሞላ እና ለእያንዳንዱ ሰው ደህንነትን እና ሰላምን የሚፈልግ ነው። ንፁህ ልብ መጾምን፣ መጸለይን፣ ማረፍን፣ አካልን ማዋረድን፣ ሁልጊዜ መሥራትና መድከምን ይወዳል።


@finote_tsidk ♻️
@finote_tsidk
@finote_tsidk  ♻️ 
@finote_tsidk
2024/09/21 07:49:41
Back to Top
HTML Embed Code: