Telegram Web Link
#THEY ASKED HER : "WHY DON'T YOU HAVE A BOYFRIEND? "Listen

She replied with confidence and eyes full of love for her Creator:"in my religion it is haram to have a boyfriend and I prefer to die then to anger my creator and disobey him the one who provide for me and love me and gave me life! I would never enter a cursed relation and date the futur husband of another woman while my lord already wrote for me 50000 years ago before I existed if I would get married or not and to whom I would get married so why gain useless sins?!"

They said:"but how will you find a husband if you don't date?"
*
She smiled and replied:"the one meant for me will find me even if I'm hidden inside a mountain..that is called:destiny! And I trust my creator!"

They said :"time has changed so be modern!"

She replied :"but the words of my creator didn't!..they remained the same and I say to him:"I heard and I obey!"

They said:"but everyone is doing it!"

She replied:"should I stop praying if everyone stop praying? Haram remain haram even if the whole world do it! And my Allah said:"if you follow most of people on earth they would turn you away from the truth and lead you astray!"

She added:"I would never shame my father or my brother who are proud of my purity and piety I was raised by a good woman who taught me that I was the futur wife of a pious man how could I cheat on my futur husband?how would I cheat on the man who will make me his and make me take his name and cherish my beauty? My beauty is only for him and I am worth more than being a girlfriend and let a man who is nothing for me have me that easy and touch me that easy as if I was a cheap stone found everywhere!no! I am a pearl in it's shell reserved only for my husband and I will wait for him until Allah send him to me!

@fezekiru
እውነተኛ ደስታን ለማግኘት ከፈለጋችሁ

አላህን ከሚያፈቅሩት ሰዎች ውስጥ ሁኑ።

እጅግ ባለ ፀጋ ብሎ ማለት የመኖሩ አላማ የአላህን ፍቅር❥  ማግኘት የሆነ ሰው ነው» ።

@fezekiru
ፍቅር ማለት ልብን እንድታፈቅር አድርጎ የፈጠራትን ጌታ ማፍቀር ነው ለኔ ፍቅር ማለት እኛ እያመፅነው ወንጀላችንን የሚሠትርልንን ጌታ ማፍቀር ነው ለኔ ፍቅር ማለት ሁሌም ስጠራው አቤት የሚለኝን ሰጨቀጭቀው የሚወደውን እኔ በስንዝር ስቀርበው እሱ በክድ እኔ በክድ ስቀረብው እሱ በእርምጃ እኔ በእርምጃ ስቀርበው እሱ እየሮጠ የሚቀርበኝን ጌታ ማፍቀር ነው::

@fezekiru
👆👆👆
🕊..ሹራ 34..🕊
(ሱመይራ አብዱ)

<<አያቴ ሰው ጎድቶሽ ያውቃል>>
<<በጥቂቱ!!>>
<<ከዛ ምን አደረግሽ?>>
<<ከሰው ምንም መጠበቅ አቆምኩ የኔ ልጅ>>አለችኝ ሙስባሀባውን እየቆጠረች
<<እሱን ካደረግን አንጎዳም?>>
<<እንዴታ የኔ ልጅ ሰው በብዙ ሚጎዳው በብዙ ከሰው ልጅ ሲጠብቅ ነው።ሰው ላይ መመካት ሀረግን ይዞ ለመንጠላጠል መሞከር ነው ሀረግ ምንም አቅም የለውም።በአፀፋው ተበጥሶ መሬት ላይ ይጥልሀል የሰው ልጅም እንደዛው ነው።መመካትህን በጀሊሉ ካደረግክ የሰው ልጅ ነገር እሱ የፈቀደው ቢሆን እንጂ አይነካህም።>>
<<መርሀባ አያቴ>>
<<አላህ ሰው ልብ ላይ ተንጠልጥላ የማትጎዳ የሆነች ልብን ይስጥህ የኔ ልጅ!!>>

👇👇👇

@fezekiru

>>@wezekirsumeyriandhayuna
የስነ ልቦና ውቅራችንን የገነቡ ለስላሳ መገፋቶች አሉ። ፍርሀታችንን የገነቡ ትንንሽ ድፍረቶች አሉ። በአንድ በተከፋ ልብ ውስጥ ምንም ቦታ ያልተሰጠው ትዝታ አለ። የአድናቆትትና የሙገሳ ቃላት በለመደ ማንነት ውስጥ የቃላት ግለትን ላለማጣት የመፍጨርጨር ድብቅ እንቅስቃሴ አለ።
ኢምንት የሚመስሉ ነገሮች ትልልቅ ነገሮችን ይገነባሉ። ኢምንትነት ወደ ትልቅ ነገር መሸጋገርያ ድልድይ ነው።

@fezekiru
የአላህ ዉዴታ ያሳሰበው አንድ ደረሴ፦

❝ ሸይኻችን ሆይ አላህ ከሚወዳቸው መካከል መሆኔን እንዴት ላውቅ እችላለሁ?❞  አላቸው።

❝ ልጄ ባይወድህማ ኖሮ ስለ ዉዴታው አያሳስብህም ነበር።❞ አሉት።
 
አላህ ከወደዳቸው ባሮቹ ያድርገን 🤲

👇👇👇

@fezekiru
  ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
አሁን ሰዓት አልፏል... በዚህ ወቅት ውስጤ የሚተራመሱ መዓት ሃሳቦችን ቃል አሰባጥሮ ፡ ውል ባለው መንገድ ማፍሰስ እንዴት ይከብዳል?
ጊዜ በገፋ ቁጥር ወደ ውስጥ ማመቅን እየተማርን እንመጣለን መሰል ኣ?

@fezekiru
ነፃነታችን በደም የተገዝዛ ነው። ሐገራችን፣ መላእክት የሸሒድ ድግስ የሚያሰናዱባት ቅድስት መሬት ናት። ልባችን በምላስ ያልተንጠለጠለች አኺራን ብቻ የምታይበት ቁዋ ያላት ጀግናችን ናት። ጀሰዳችን ፍርሐት የማያውቅ ወደጀነት አድራሽ-ኣችን ነው። በተበደልነው እና በተገፍፋነው ቁጥር ዱንያ ላይ መልካም እናጭዳለን። በተሰዋው ነፍሳችን ምትክ ዳግም መስሰዋትን እስክንመኝ ድረስ ተድላ ፊታችን ነው። የኖርነውም፣ የታገልነውም፣ የሞትነውም ለስኬት ነው!!🇵🇸one day insha Allah free Palestine



@fezekiru
ጌታዬ…
መሄጃ እንዳለኝ ካንተ ብሸሽም
ትዕዛዝህን ጥሼ ራሴን ብዋሽም
አላውቅበትም ያወቅኩ ቢመስለኝ
አስችለኝ እንጂ ምን አቅም አለኝ።

@fezekiru
@fezekiru
አንዳንዴ ምንም ያህል ጥሩ ሰው ቢሆንም እንኳን ትንሽ ጥሩ ያልሆነ ጎን ሊኖረው ይችላልና ችሎ ማሳለፍ ነው አለበለዚያ ግን ለትንሹ ጥሩ ላልሆነው ነገር ብለን ትልቁን መልካም ነገር እናጣለንና።
ምክንያቱም እጅግ የሚያምረው የፅጌሬዳ አበባ 🥀እንኳን ያለ እሾህ አልተፈጠረምና።

@fezekiru
👆👆👆
ካንተ ውጪ ማንም የማያውቀው ብቸኛው ምስጢር "ከአላህ ጋር ያለህ ትስስር ምስጢር ነው"።

..  .  አሞጋሾች አይሸንግሉህ፤ ወቃሾችም አይጉዱህ። በቃ ስለራስህ ስራ! ስለራስህ ኑር!

👇👇👇
@Dinel_islam.

@fezekiru
ሰላም ለእነዚያ ፍቅራቸውን ክብራችንን በመጠበቅ ለሚገልፁት፣ ስሜቶቻቸውን ከፍላጎታችን ባላይ ለማያስበልጡት።
ሰላም ለሷ ፍቅራችንን ልንነግራት ላልቻልንበት፣ እሷም ላልተረዳችን።
ሰላም ለሱ የሆነ ወቅት ላይ ተደናቅፎ አሁንም ድረስ የእንቅፋቱ ህመም ለሚጠዘጥዘው፣ እንደ ቀድሞው መሆን ለተሳነው።
ሰላም ላንቺ እንደ ልብሽ ላልሆንሽው፣ የልብሽን በልብሽ አፍነሽ ለምትስቂው።
ሰላም ላንተ ኃላፊነቶችህ ላጎበጡህ፣ እንደ ልፋትህ የልፋትህን ያህል ለማታገኘው።
ሰላም ለእናንተ ከህይወት ጋር ለምትታገሉት።

@fezekiru
@fezekiru
አንዳንዴ ሽንፈትን፣ ስብራትን መቀበል እና ማመን ተገቢ ነው። ጥንካሬ ማለት ሽንፈትን ወይም ህመምን መካድ ማለት አይደለም። ከህመም እና ሽንፈቱ ገዝፎ መገኘት እንጂ! ባልነቁ ሀሳቦች ለማነቃቃት የሚዳክሩ ብዙ ናቸው። አሸናፊነት ሁሌም አሸናፊ ነኝ፣ እችላለሁ በማለት ብቻ አይገኝም። ተጎድተህ ከነበር ጉዳትህን አምነህ ለማገገም ተጣጣር እንጂ አልተጎዳሁም በማለት ከጎዳህ ነገር በላይ እራስህን አትጉዳ! ጥለውሽ ሄደዋል ወይም የሆነ ክብርሽን ዝቅ ባደረገ ምክንያት ከተለዩሽ አምነሽ ተቀበይ። እኔ እራሴ ተውኳቸው፣ አልፈለግኳቸውም እያልሽ በውሸት ምክንያቶችሽ ጭስ አትታፈኝ።
ሰው መሆናችንን አንዘንጋ እንጂ! ሰው የከፍታ እና ዝቅታ ቅይጥ ነው። እንባሽን ዋጥ አድርገሽ መሳቅ መቻልሽ አይደለም ጠንካራ የሚያስበብልሽ፣ ዘውትር የሚያስለቅስሽን ነገር አውቀሸወ መፍትሄ መፈለግሽ እንጂ! በአንድ ሰው ሰበብ ሁሉም ሰዎች ቆሻሻ እየመሰሉህ እንደ ዝንብ ማረፍ መቻልህ አይደለም ህመምህን የሚያስታግስልህ፣ የነጀሰህን ሰው ቆሻሻ አፅድተህ አንተም ሌሎችን ከመነጀስ ለመታቀብ መጣጣርህ ነው ህመምህን በደንብ የሚያሽረው።
እረፉ! አጓጉል ጠንካራ ነኝ በሚል ውስጥ ውስጡን አትሰበሩ። ሰላም ነኝ ምንም አልሆንኩም እያላችሁ የዛፍ ላይ እንቅልፍ አትተኙ! በቃ አጉል ሽንፈትና ጉዳታችሁን ላለማመን ችክ እያላችሁ የፈውሳችሁን ጊዜ አታርቁት! አንዳንድ ህመምና ጉዳቶች ተቀብለን ካላመንናቸው አይሽሩም። ግድየላችሁም በአጓጉል ያለማመን ትግላችሁ የተነሳ ወደ ጌትየው የምትዘልቁበትንም ጊዜ እርም አታድርጉት። ልብ በሉ አዕምሮ ደጋግመው የነገሩትን ሁሉ ፍፁም ሁሌም አይቀበልም። ልብም ደጋግመው ያሰቡትን ሁሉ አያፈቅርም። #አብሽሩ! ብቻ እንዲህ ይሰምማኛል!

@fezekiru
@fezekiru
Forwarded from ሀላል መረዳጃ ዲላ (Abuki)
ለነፍስህ እዘንላት ፣ ልብህ በግርግር እንዳትጠፋ ጠብቃት።
አላህ ነፃ አድርጎ ለትልቅ አላማ ከፈጠረህ በኋላ ስለምን የአጀንዳ ተጠቂ ትሆናለህ?
አንተ ቆሻሻ መጣያ አይደለህም ፣ ሚናህን ለይተህ እወቅ የሚመለከትህ ነገር ላይ አተኩር ፣ ማንም በየቀኑ አዳድስ አጀንዳ እየፈጠረ እርጋታህን እንዳይቀማህ።

የተፃፈውን ሁሉ እያነበብክ ነፍስህን እረፍት አትንሳት ፣ timelineህን ስርኣት አስይዘው ማንን መከተል እንዳለብህ በደንብ አስብበት ፣ ለጀሰድህ ምግብ መርጠህ እንደምትመግበው ሁሉ ለሩህህ እየመገብከ ያለውን ነገር አጢነው ፣ የቁርጥራጭ ሀሳቦች ማከማቻ አትሁን ፣ አላህ አክብሮ እንደፈጠረህ ሁሉ ራስህን አክብረው ፣ ልብህ የአላህ ቤት ናት ወደሷ ሚሄደውን ነገር ተቆጣጠር ፣ አቅልህን የአጀንዳ ፈጣሪዎች መደበሪያ አታድርጋት🙏

በተለይ የሰዎችን ድንበር ከመንካት ተቆጠብ ፣ የተላላቆች ክብር ላይ መረማማድንም እንደቀልድ አድርገው እንዳያለማምዱህ እምቢ በላቸው ፣ ህይወት አለብን ፣ የኑሮ ውድነቱ የቤተሰብ ሀላፊነት ጭንቀቱ ፣ ከምትኖርበት ቤት ጀምሮ ምን አልባት ክፍያ ይጠበቅብሃል ፣ ታድያ ስለምን በማይመለከትህ ጉዳይ ከግራ ወደ ቀኝ ስትሮጥ ቀንህ ይመሻል?
ሁሉም ነገር አህል አለው ባለቤቱ ይጨነቅበት ፣ ይመለከተኛል የምትለው ነገር ካለ ደግሞ ስራዬ ብለህ በደንብ ያዘው ፣ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው አካላት መረጃ አደራጅ ፣ እርግጠኛ ባልሆንከው ነገር ላይ የሰዎችን ክብር ከማጉደፍ ተጠንቀቅ ፣ karma መጥፎ ነው ነገ ዙሮ ቤትህ ይገባል።

ኣዒሻ ረ.ዐ በውሸት ስሟ የጠፋበት ክስተት ሀዲሰል ኢፍክ ተብሎ በስርኣት ተሰንዶ በቁርኣን ተደግፎ ታሪኩ ለእኛ የተላለፈው እንድንማርበት እንጂ ለመረጃነት ብቻ አይደለም።
ሃሻ በላቸው ፣ ባልተሟላ መረጃ ላይ ተመርኩዘህ የማንንም ሀሳብ አታስተጋባ።
አንተ ክቡር ሰው ነህ ፣ ክቡር ሰው ነሽ። ኢኮኖሚካሊ ባደጉት ሀገራት ላይ የሰዎችን concentration ለማጥፋት ወጣቱ በእርጋታ እንዳያስብ ለማድረግ በጀት የሚመደብበት ዘመን ላይ ነን፣ ኢልሃድን ለማስፋፋት የሚንቀሳቀሱ አካላት የመጀመርያ እርምጃቸው ልቦች ላይ ብዥታን መፍጠር ፣ ስክነትን ከወጣቱ ላይ ማጥፋት ነው ፣ ከዛ ሀይማኖቶች በራሳቸው ጊዜ ፎርሙላ ብቻ ይሆናሉ ፣ እምነት የሚባለው ነገር ይጠፋል ፣ ዝምብለህ አስብ አንዳንዴ ከነፍስህ ጋር ኸልዋ ግባ ከቻልክ በዚህ ዘመን ከማንም የቤት ስራ አትቀበል።

አንተ የምታያቸው ነገሮች ጥርቅም ነህ ፣ ማንነትህ ከአዋዋልህ ይቀዳል ፣ ስርኣትህ ከምታነበው ነገር ይገነባል ፣ ሁሌ ክርክር ፣ ሁሌ ጭቅጭቅ ..
አላህ የሰጠህን energy በማይጠቅምህ ነገር ላይ አታባክን ፣ ልብህን አታድክማት ለነፍስህ እዘንላት።

"እናንተ ያመናችሁ ሰዎች ሆይ ነፍሶቻችሁን አደራ"🙏
ወሰላሙን ዐላ መኒተበዐል ሁዳ
Abas✍️
Forwarded from ሀላል መረዳጃ ዲላ (ye zd Lij)
"የልጅነት-ውጥን፤ የአፍላነት-ጥረት፤ የወጣትነት-ስኬት"

🌹 ክብር ለሚገባው ክብርን ምስጋና ለሚያሻውም ምስጋናን እንቸራለን። እኛ ከራሳችን አንዳች ነገርን ለማድረግ አቅሙም ብልሀቱም የለንም የአላህ መልካም ፍቃድ ቢታከልበት እንጂ። ይህን ድንቅ ስኬትም ላሳየን አምላክ የሚገባውን ያህል ምስጋና እናደርሳለን፥ አልሀምዱሊላሒ-ረቢል አለሚን።

🌹 በያዝነው ሳምንት በከተማችን ዲላ ብሎም በአካባቢያችን ታይቶም ሆነ ተሰምቶ የማይታወቅ ድንቅ ተግባር በጌታችን ይሁንታ ለመሳካት ችሏል። ለአመታት በሌሎች አካባቢዎች ሲከወን ተመልክተን እንከጅለው የነበረን መልካም ስራ ተራው ደርሶን እኛም የእድሉ ተካፋይ ለመሆን በቅተናል።

🌹 "ሀላል" የተሰኘው የልበ-ቀናዎች ስብስብ ልግስናና ቸርነት ከሞላቸው ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች ጋር በፈጠረው ጠንካራ ግንኙነት ከ200 በላይ ወይፈን እና ቁጥራቸው ሰባት የሚደርሱ በጎችን ለተከበረው የአረፋ በዓል መስዋዕት በማድረግ ከሰባት ያላነሱ ከተሞችን፤ 12 ወረዳዎችን እንዲሁም በከተማችን ዲላ የሚገኙ ነዋሪዎችና ተቋማትን (ዩኒቨርሲቲ፣ ማረሚያ እና መሳጂዶችን) ጨምሮ ቁጥራቸው ከ3,000 ለሚልቁ ቤተሰቦች በዓሉን በደስታ ያሳልፉ ዘንድ የስጋ እደላ ፕሮግራም ሲያከናውን ውሎ አምሽቷል።

🌹 "ሀላል መረዳጃ ማህበር" በአስደናቂ የአመራር ብቃት፤ በቀልጣፋ አገልግሎት፤ አክብሮት በተሞላው መስተንግዶ እንዲሁም ጨዋነትን በተላበሰ አፈፃፀም የ1445ኛውን ዓመተ-ሒጅራ የአረፋ በዓል ታሪክ በሚያወሳው መልኩ በሰደቃ አድምቀውት ውለዋል፥ ይህን ሰናይ ተግባር አድንቀናል አመስግነናልም።

🌹 "ሀላል" ዛሬ ላይ ከሚፈፅማቸው ግሩም ተግባራት በተጨማሪ በቀጣይም ለመስራት ያሰባቸው በርካታ ውጥኖች አሉት። እነኚህ ታላላቅ ፕሮጀክቶች ዛሬ ላይ የማይቻሉ መስለው ቢታዩም በአላህ ፍቃድ ሁሉም እውን እንደሚሆን ባለሙሉ ተስፋ ነን፥ ኢንሻአላህ።

👉 በመጨረሻም "ሀላል" የወጣቶች ስብስብ እንደመሆኑ በርካታ እገዛዎችን ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ይሻል። ይህን መሰል ባለራዕይ፤ ትጉህ እና ቆራጥ ስብስብ ወደ ተሻለ ደረጃ ማድረስ የሁሉም ሀላፊነት ሊሆን ይገባዋል።

🥀 ስለሆነም ማህበሩን በተለያየ መልኩ ለማገዝና ከወጣቶቹም ጎን በመሆን የቻላችሁትን አስተዋፆ ማበርከት የምትሹ አካላት በሚከተሉት አድራሻዎች ልታገኙዋቸው ትችላላችሁ።

👉 አድራሻ፦ ቢላል_መስጂድ_ህንፃ_አንደኛ_ፎቅ
ስልክ፦ 09-12-33-00-91
09-10-88-30-37
09-30-66-66-13

#ሀላል_በጎ_አድራጎት_ማህበር
#ኑ_በጋራ_ሆነን_የተሻለ_ማህበረሰብ_ለመፍጠር_እንትጋ!
https://www.tg-me.com/halale_merdaja_dilla

By:-Arefate abdulgefar
Forwarded from ሀላል መረዳጃ ዲላ (ye zd Lij)
በቅርቡ በሀላል በጎ አድራጎት አማካኝነት ለመመረቅ ቀናቶች ብቻ የቀሩት መስጂድ ኢንሻ አላህ በቅርብ ቀን 💪💪💪


ስለሆነም ማህበሩን በተለያየ መልኩ ለማገዝና ከወጣቶቹም ጎን በመሆን የቻላችሁትን አስተዋፆ ማበርከት የምትሹ አካላት በሚከተሉት አድራሻዎች ልታገኙዋቸው ትችላላችሁ።

👉 አድራሻ፦ ቢላል_መስጂድ_ህንፃ_አንደኛ_ፎቅ
     ስልክ፦ 09-12-33-00-91
               09-10-88-30-37
               09-30-66-66-13

#ሀላል_በጎ_አድራጎት_ማህበር
#ኑ_በጋራ_ሆነን_የተሻለ_ማህበረሰብ_ለመፍጠር_እንትጋ!
https://www.tg-me.com/halale_merdaja_dilla
2024/06/28 09:35:28
Back to Top
HTML Embed Code: