Telegram Web Link
አስታውስ
ሰዎችን በሂወታቹ ውስጥ መቀበል ያለባቹ እንደ ጠዋት ፀሀይ ነው ። እንዴት? ሁል ጊዜ አይቆዮም .......ግን ሂወታቹን ውብ አርገው ያልፋሉ 👇👇👇 @fezekiru
ትላንት የጠለቀችው ፀሀይ በማለዳ መመለሷ አይቀርም። ምታስፈልገንን ሰዓት ትጠብቃለች እንጅ ሁሌም አብራን ነች። ከመኖሯ አለመኖሯ በሚጠቅመን time ለኛ የተሻለ ጥቅም በማሰብ ነው ምትሸሸገው! እና ብቅ ስትል ዳግም እስክትገባ ለዛሬ ልዩ ሽልማት ተሰጥቶናል። የህይወትህ መሪ ልታዞርበት ና ስኬትን ልታገኝ የንድትችልበት!....

አብሽር ነገን ናፍቃ ጓግታ ሳትቀር ብርሃንን ይዛ ብቅ ትላለች እያመሰገንክ ጠብቃት🥰

@fezekiru
ታውቃለህ/ሽ ??👐

የተደገፍከው ያ እንዳንተ ስጋ ለባሽ ሰው የህይወትህን መንገድ ያካሂድህ (አብሮህ ይጏዝ) ይሆን ይሆናል እንጂ ... ያንተን ጉዞ አይጏዝልህም!!

ልበ-ቀና ከሆነ መንገድህ ያዛለህ ጊዜ ያበረታሃል!! ...ስጠፋ ይፈልግሃል የወደቅህ ሰዓት ደግፎ ያነሳሃል!! ....

የፍቅር ሰው ከሆነ በመንገድህ ስታነክስ ትከሻውን አስደግፎህ በምትጎትተው እግርህ ልክ የራሱን መንገድ ፍጥነት ገትቶ አብሮህ ይጏዛል::

በጣም ለፅድቅ የቀረበ ከሆነ እስከሚችለው ድረስ ያዝልህ ይሆናል:: .... (አንተ ጀርባው ላይ ሀሳብህንም ክብደትህንም ጥለህ ለሽ ብለህ እያንቀላፋህ ... ፈሱ እስኪያመልጠው አይሸከምህም!! ... 🤷‍♂️🤷‍♂️)

በተረፈው ሁሉም ልክ እንዳንተው የራሱ ሩጫ.. የራሱ መውደቅ እና መነሳት ... የራሱ ጉድለት አለው እና የራሱን አቁሞ እንዲያቋቁምህ መጠበቅም የዋህነት ነው!!!

ወደቅህም ተነሳህም .. ፈረጥክም ... ቀደምህም ... ዘገየህም ...ህይወቱኮ ያንተ ነው!! እገሌ እንዲህ አላደረገልኝም ... እገሊት ረሳችኝ ጠፍቼ ሳትፈልገኝ... ታምሜ ሳይጠይቁኝ ... ሞቼ ሳያለቅሱልኝ ... እያልክ የምታላዝነው ምን ሆነህ ነው??

ለራስህ ህይወት ሀላፊነቱን ራስህ ውሰድ እንጂ 🙄ምን ሆነህ ነው ቤተሰብ .. ጎደኛ .. ፍቅረኛ ... ደርበው ያንተን ስንክሳር እንዲኖሩልህ ቁጭ ብለህ የምትጠብቀው??

እንኳን ሰው አምላክ ራሱ ሲረዳህኮ የምትጏዝበትን ጉልበት እና ጥበብ እንጂ የሚሰጥህ በአስማት ነገር እንደንፋስ አያስወነጭፍህም!!

እንዳልኩህ ነው!! ማንም ቢሆን አብሮህ ይሮጥ ይሆናል እንጂ ያንተን ሩጫ አይሮጥልህም!! ...

ሰው እንዲረዳህ ከመጠበቅህ በፊት በራስህ የምትችለውን አድርግ !!! ሰው እንዲወድህ ከመጠበቅህ በፊት ራስህን ውደድ !! ሰው እንዲያከብርህ ከመጠበቅህ በፊት ራስህን አክብር!!)

Join @fezekiru
ክቡር እንባ ከሚፈስበት ቀዬ ተገኝተን አላነባንም። ከተቀደሰው ስፍራ ሆነን እስካሁን ዱዓን ለማድረግ አልታደልንም። ግና ባለንበት ከዝንጉዎች አልሆንም። እንኛ ከውድ ጊዜያቸው ላይ ሰውተው ያስታወሱን።
እንዴት ያለ ውዴታ ነው በክቡር  ዱዓ መታወስ። አላህ አላህ! 🥺🥺
በሩቅ መናፈቅን ናፋቂው ካልሆነ ሁሉም አይረዳውም። በዱዓችሁ አስታውሱን ያልናቸው አልዘነጉንም?። ልባችን ይደሳ ዘንድ ከማስታወሻቸው ውስጥ ምልክትን አሳዩን..ትንሽ የሚመስል ግና በትውስታችን ውስጥ በክብር የሚመዘገብ ትልቅ ስጦታን ሰጡንሳይዘነጉ...በዱዓ ሳይዘነጉን። የልብን ለባለቤቱ ይነግሩታል እንጂ ልብ የያዘውን ሁሉ አይዘረዝሩትም። አላህ ልንከትበው የቸገረንን የደስታ ስሜቶች ሁሉ ከበረካ ጋር ለአስታዋሾቻችን ይለግሳቸው። አሚን ለዛች ልብ ተስፍን ለጣልኩባት ወንድሟን በዱዓዋ ላልዘነጋችው! 🥰

@fezekiru
@fezekiru
ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚታወቀው መውሊድ የሚያከብርም የማያከብርም ሙስሊም ማህበረሰብ አለ። በኢትዮጵያ የሚገኙ ዑለሞችም በዚህ ጉዳይ እየተወያዩ ብዙ መድረኮችን አሳልፈዋል! ሚያዚያ 23 በተግባቡበት ሰነድም ላይ በዚህ ጉዳይ ላይ ፅንፍ መደራረስ እንደሌለባቸው ተማምነው ማለፋቸው የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው!

ከአንድ አመት በፊት መጅሊስ ይከፈል የሚሉ ሰዎች ድምፅ በጎላበት ሰዓት

"መውሊድ አክባሪውም ጋር አንድ ነን፣ መከፈል የለብንም፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ኺላፍ ትልቅ የሚባል አይደለም፣ እየተመካከሩ መቀጠል ይቻላል"
ሲሉ የነበሩ ሰዎች፣ዛሬ ላይ ይህን አጀንዳ ከመጠን በላይ ሲለጥጡት እያየን ነው!

በማህበረሰባችን ውስጥ መውሊድ የሚያከብርም የማያከብርም ወገን አለ። የሚያከብረውም ሆነ የማያከብረው በመረጃ ሀሳቡን መግለፁ መልካም ነው! ክርክሩም በዚህ መልኩ ወደ ፊት ክፍለ-ዘመናትን ሊሻገር ይችላል!

አመት በመጣ ቁጥር ግን ወንድምን የመጥላት መሳሪያ፣ የመበያያ መድረክ ማድረግ ግን ሁላችንም ልንፀየፈው ይገባል! በመውሊድ ላይ ባንስማማም በዚህ ላይ ግን መስማማት ግድ ይለናል! ውይይቱ ይቀጥላል፣ የልብ ጥላቻ ግን ይቆማል!
ሳትዘልፍ መውሊድ ቢድዓ ነው በል፣ ሳትሳደብ መውሊድን አከብራለሁ በል! አለበለዚያ፣ ይህ አጀንዳ ከወንድም ጋር የመጠያያ ጉዳይ ነው ብለህ ምታስብ ከሆነ፣ "አንድ ነን" ሚለውን መሸንገያ ቃል ጣልና አቋምህን ቀጥታ አስቀምጥ! በዚያም መንገድ ላይ ጉዞህን ቀጥል!
ali amin✍️✍️
Forwarded from ሀላል መረዳጃ ዲላ (Abuki)
አልሃምዱሊላህ ሀላል መረዳጃ ለ 9ኛ ዙር ያደረገውን የትምህርት ቁሳቁስ እደላ ፕሮግራም በተሳካ ሁኔታ አካሂዷል
መስከረም 17/1/2016
😍😍

እኛ እያለን አንድም ተማሪ ከትምህርት ገበታው አይቀረም በሚል መሪ ቃል   ከ600 በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ማድረስ ችለናል።😍

ሀላል መረዳጃ ዲላ  በዘንድሮ አመት ለ9ኛ ዙሩ ባደረገው የደብተር እደላ ፕሮግራም ካቀደው በላይ እዲሰራ የበኩላችሁን  አስተዋፆ ላበረከታች ሁሉ እናመሰግናለን ።🙏🙏

የ ሀላል መረዳጃ አባላት ሀላል ሁሌም ካሰበው በላይ እንዲሰራ እናንተ የጀርባ አጥት ናችሁ :: አላህ የከይር ስራ ምንዳችሁን ይክፈላችሁ 🤲


እነኝህን እና መሰል ስራዎችን  ለማገዝ:-ዲላ ቢላል መስጂድ ህንፃ ላይ ሀላል መረዳጃ ቢሮ ወይንም 0935511930/0930666613/ 0922837632 በነኚ ስልኮች ቢደውሉ ያገኙናል።
https://www.tg-me.com/halale_merdaja_dilla
<< አንቱ ሰው ስለ ደስታ ንገሩኝ? >>
የኔ ልጅ ደስታ ልቦችን በፍቅር መዳበስ ነው። ልብህን አፅድተህ ፍቅርን መስጠት ነው ደስታ። የኔ ልጅ በንፁህ ልብ ፍቅርን ስትሰጥ በዙርያህ የሚገኝ ሁሉ ሰላም ይሰማዋል። የኔ ልጅ ለጌታህ የምትመች ስትሆን ፍጥረታት አንተ ዘንድ ይመቻቸዋል። ደስታህም በረካ ይኖረዋል። >>
<< አንቱ ሰው እወዶታለሁ! >>
<< የሚያስደስተኝ ጌታዬ ያስደስትህ። >>
(ኢብን ሰፋ)
@fezekiru
@fezekiru
« ልጄ ሆይ… » አሉ አንድ በእድሜ ጠና ያሉ አዛውንት። ወደ ሕይወት ትግል ገና እየተቀላቀለ የሚገኝ ጎረምሳ ወጣትን እየተመለከቱ።
« ልጄ ሆይ… መጠበቅህን አደብ አሲዘው። የመጠበቅ ልጓምህን ተቆጣጠረው።
የኔ ልጅ ሰዎች መጥፎ ነገር በማድረግ ብቻ አይጎዱህም። ልብህን በአጉል ተስፋ አንጠልጥለው ከጌታህ ጋር ሊያጣሉህ ይችላሉና ተጠንቀቅ።
ልጄ ሆይ… ሕይወት እንደ እናትህ ልብ አይደለችም። አትራራልህም። እንደ አባትህም እቅፍ አይደለችም። እንዳይበርድህ ሙቀት አታቀብልህም። ሕይወት የወቅት ዘመድ ነች። የአሁን ሁኔታ ነች። »
ወጣቱ የአዛውንቱን ንግግር በጥሞና ማዳመጡን ቀጠለ።
« ልጄ ሆይ ወደ ልብህ የዘለቀን አክብር። የተለየህን አትጥላ።
ልጄ ሆይ… ሰዎች በመጥፎ ምግባር ላይ ስላየሀቸው ብቻ አትፍረድባቸው። በምታውቀው እኩይ ምግባር ላይ ስለተገኙ አትጠየፋቸው። ይህን ልብ አድርግ አላህ ምርጥ ነብያቶቹን በእጅጉ ቆሽሸው ለነበሩ ሰዎች ልኮ የቆሸሹትን አፅድቶ እንዳስከበራቸው።
ልጄ ሆይ ወንድሞችህ ከፊርዓውን የባሱ አይሆኑምና ከፊርዓውን ያነሰ ክብር ሰጥተህ አታዋርዳቸው። የአላህ ነብይ ሙሳ ፊርዓውንን በለዘብታ ቃል እንዲያናግረው መታዘዙን ዘንግተህ በወንድሞችህ ላይ አጉል አትጩህ! »
ንግግራቸውን በድንገት አቁመው ዝም አሉ። ንግግራቸውን ባያቋርጡ ይመኝ ነበር። ግና አዛውንቱ በዝምታ ረጉ። ከወጣቱ አንደበት አንዲት ንግግር ብቻ ተሰማች። እንዲህ የምትል
« አንቱ ሰው እወዶታለሁ! »
ፈገግ ብለውለት
« በሕይወት ውስጥ ከጌታህ ከመለየት ጌታዬ ይጠብቅህ! » አሉት።
« አሚን! »ብሎ ወደ ሕይወት ትግሉ አመራ።

@fezekiru
@fezekiru
Forwarded from ሀላል መረዳጃ ዲላ (Abuki)
https://vm.tiktok.com/ZMj4XcWGt/ይህ የሀላል በጎ አድራጎት የtiktok አካወንት ነው follow አድርጉ🙏🙏🙏
ልባችሁ ውስጥ የዩሱፍ ታሪክ ያለ አይመስላችሁም?  ሩ…ቅ ህልሞች፣  አጥር የተሻገሩ ምኞቶች…  እና ደግሞ "ዩሱፍ ሊመለስ አይችልም" ብለው የሚምሉ የመንደሩ ሰዎች አሉ። እዚያ ደግሞ የያዕቁብን የለቅሶ ዓለም እንደ ንጭንጭ የሚቆጥሩ  ዘላኖች አሉ።  በህይወት ኖረም አልኖረም ለሩቅ ሰዎች በባርነት እንደሸጡት እርግጠኛ የሆኑ ወንድሞቹም አሉ።
አንዳንዴ… እዚህ መሀል ነው  የአላህ ፍላጎት ጣልቃ የሚገባው።
وَمَن يُهِنِ اللَّهُ فَمَا لَهُ مِن مُّكْرِمٍ ۚ إِنَّ اللَّهَ يَفْعَلُ مَا يَشَاءُ ۩
አላህ የሚያዋርደውም ሰው ለእርሱ ምንም አክባሪ የለውም፡፡ አላህ የሻውን ይሠራልና፡፡(ሱረቱል ሀጅ 18)

"የማይሆን" ብለው የማሉለት ጉዳይ መሀል "የፈለኩትን አድራጊ ነኝ" ሊል ይመጣል። ሊቀየር የማይችል የሚመስለን ሁሉ ይቀየራል። ተበትነው የነበሩ ምኞቶች ይሰበሰባሉ።  ህልም የነበረው በገሀዱ ዓለም ይታያል። አጠገብህ ላሉት ሰዎችም “አላህ እንደሚቀበለኝ በእርግጠኝነት ምዬ አልነገርኳችሁም ነበር ወይ?" ትላቸዋለህ። ዓጂብ።

👇👇👇
@fezekiru

@Halal_Fkr
#አንብቤው_ከተመቸኝ_ላካፍላችሁ!

🔙 ሀዘን እና ትካዜ ወደ ኋላ ጣላቸው!

🌱ኢብኑል ቀይም አላህ ይዘንለት እንዲህ ይላል፦
"ሀዘን ቁርኣን ውስጥ በክልከላ መልኩ ወይም በማራቅ መልኩ ቢኾን እንጂ አልተጠቀሰም
ልክ አላህ እንዳለው

{ وَلَا تَهِنُوا وَلَا تَحْزَنُوا }
{አትስነፉ አትዘኑም}


{ فَلَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ }
{ፍርሃት የለባቸውም፤ እነርሱም አያዝኑም}"

🔵የዚህ ሁሉ ሚስጥሩ
👉🏽 ሸይጣን ከሚያስደስተው ነገር ሁሉ ትልቁ ሙዕሚን የኾነ ሰው አዝኖ ማየቱ ነው። ከዚያም ከመንገዱና ከጉዞው ሊገታው።

🔵በእርግጥም ነብዩ ሙሐመድ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከሐዘን ተጠብቀዋል
"اللهم إني أعوذ بك من الهم والحزن"
[አላህ ሆይ እኔ ከሀዘንና ከጭንቀት በአንተ እጠበቃለሁ] በማለት


🌱ኢብኑል ቀይም በድጋሚ እንዲህ ይላል፦
"ሀዘን ብሎ ማለት
ቀልብን ያደክማል፣ ቆራጥነትን ያከሽፋል፣ ፍላጎትን ይጎዳል፣ ወደ ሸይጣንም ምንም ተወዳጅ ነገር የለም ሙዕሚን አዝኖ እንደ ማየት"


💡ስለኾነም፦
🍎ሀዘንን ራቁ!
   መልካምን ከጅሉ!
      በአላህ ላይ መልካም ግምት ይኑራችሁ!
       አላህ ዘንድ ባለው ተማመኑ
          በአላህም ላይ ተመኩ
              በአላህ ፍቃድ በሁሉም ሁኔታ ደስተኞች ትኾናላችሁ

@fezekiru

@yasin_nuru 
ያ ረብ በፍትሐዊነትህ ላይ ቅንጣትም ጥርጣሬ የለንም ይብቃችሁ የምትለን ጊዜ እስኪመጣ ግን በእጅጉ ተቻኮልን።
የበዳዮችን ውርደት አይተናል፣ ስራዎቻቸው የተዋረዱ እንደሆኑም አረጋግጦልናል። ካንተ ውጪ በዳይን ተገቢውን ቅጣት የሚቀጣ የለምና በደለኞችን አንተው ተበቀልልን።
ጌታዬ እዝነትህን! ችላ ካልናቸው ወንድሞቻችን አንተ ዘንድ ከመጠየቅም መሀርታህን። እናንተ ፍልስጤማውያን ልቦች ሆይ አላህ ይዘንላችሁ።የአላህ እርዳታው እገዛው አብሯቹ ይሁን::
@fezekiru
@fezekiru
2024/06/30 17:55:16
Back to Top
HTML Embed Code: