Telegram Web Link
በአዲስ አበባ ከተማ በመስቀል ዐደባባይ የተከናወነው የመስቀል ደመራ በዓል በምስል
የቡድን 7 አባል ሀገራት በኢትዮጵያ በግብርና ዘርፍ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የቡድን ሰባት አባል ሀገራት በኢትዮጵያ በግብርና ዘርፍ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ፡፡

ኢትዮጵያ በጣሊያን ሲራኩስ እየተካሄደ በሚገኘው የቡድን ሰባት አባል ሀገራት የግብርና መድረክ ላይ እየተሳተፈች ነው፡፡

የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በመድረኩ ላይ የኢትዮጵያን የግብርና ኢንቨስትመንት ልምድ ማካፈላቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

ኢትዮጵያ በዘርፉ ያላትን ከፍተኛ ጸጋ እንድትጠቀም የኢትዮጵያን የግብርና ፖሊሲ ከፍተኛ ዕገዛ ማድረጉን የገለጹት ሚኒስትሩ÷ ከዚህ ጋር በተያያዘም በሜካናይዝድ እርሻ እያስመዘገበች ያለውን አበረታች ውጤት አብራርተዋል፡፡

የምግብ ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ሂደት ኢትዮጵያ ስንዴን ጨምሮ በሌሎች የግብርና ምርቶች ስኬታማ ተግባራትን እያከናወነች መሆኗን ጠቅሰው÷ ለበለጠ ውጤት በትብብር መሥራት እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡

በዚሁ መሠረት የኢትዮጵያን የግብርና ትራንስፎርሜሽን ፍኖተ-ካርታ ጨምሮ በዘርፉ ያሉ ምቹ ሁኔታዎችን እና እየተመዘገቡ ያሉ አበረታች ውጤቶችን በመረዳት የቡድን ሰባት አባል ሀገራት ኢንቨስት እንዲያደርጉ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በጎንደር ከተማ እየተከበረ የሚገኘው የደመራ እና የመስቀል በዓል -በምስል
2024/11/16 09:48:52
Back to Top
HTML Embed Code: