Telegram Web Link
ኢትዮጵያ መድንና አርባምንጭ ከተማ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ሣምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ኢትዮጵያ መድንና አርባምንጭ ከተማ ያለ ምንም ግብ አቻ ተለያዩ፡፡

በሌላ በኩል ምሽት 1 ሠዓት ላይ ሊደረግ የነበረው የወልቂጤ ከተማ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጨዋታ÷ የወልቂጤ ከተማ ክለብ ማሟላት የሚጠበቅበትን ባለማሟላቱ ምክንያት ንግድ ባንክ በፎርፌ 3 ነጥብ አግኝቷል፡፡

ወልቂጤ ከተማ ባለፈው ሳምንትም ከመቻል ጋር መጫወት ሳይችል ቀርቶ በፎርፌ መሸነፉ ይታወሳል፡፡
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ሀጋ ገራድ… - በየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር)
እሁድ ረፋድ በፋና ከዋክብት ይጠብቁን
ዋሊያዎቹ የ2025 የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታቸውን ኮትዲቯር ላይ ያደርጋሉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከጊኒ ጋር የሚያደርጋቸውን የ2025 የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ 3ኛ እና 4ኛ የምድብ ጨዋታዎች ኮትዲቯር ላይ እንደሚያደርግ ታውቋል፡፡

በዚሁ መሠረት ዋሊያዎቹ 3ኛውን ጨዋታ ጥቅምት 1 ቀን 2017 ዓ.ም ምሽት 1 ሠዓት ላይ ጊኒ የሜዳ ጨዋታዋን ለማድረግ ባስመዘገበችው በኮትዲቯር ያሞሱክሩ በሚገኘው ስታድ ኮናን ባኒ ስታዲየም ይጫወታሉ፡፡

በተመሳሳይ ብሔራዊ ቡድኑ ከጊኒ ጋር ጥቅምት 4 ቀን 2017 ዓ.ም የሜዳውን ጨዋታ ለማከናወን ባስመዘገበው አቢጃን በሚገኘው ስታድ ደ ኢቢምፔ ስታዲየም ምሽት 4 ሠዓት ላይ የሚያደርግ ይሆናል፡፡
ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ የተመድ ዋና ጸሐፊ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛን አመሰገኑ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሃና ቴቴህ በቀጣናው ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቀረቡ፡፡ መልዕክተኛዋ በቀጣናው የነበራቸውን የሥራ ጊዜ ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ በፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ ስንብት ተደርጎላቸዋል፡፡ በዚሁ ወቅትም ለኢትዮጵያና ለአፍሪካ ቀንድ ላበረከቱት ከፍተኛ ድጋፍ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ አመስግነዋል፡፡

https://www.fanabc.com/archives/263619
ኢትዮጵያ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን በመከላከልና መቆጣጠር ላስመዘገበችው አመርቂ ውጤት እውቅና አገኘች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ኢትዮጵያ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን በመከላከልና መቆጣጠር ላስመዘገበችው አመርቂ ውጤት እውቅና ሰጥቷል።

በአሜሪካ ኒውዮርክ እየተካሄደ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 79ኛው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ነው የተመድ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች መከላከል እና መቆጣጠር ግብረ ሃይል (ኤንሲዲ) ለኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ሽልማት ያበረከተው።

እውቅናው የተሰጠው ኢትዮጵያ የተቀናጀ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች መከላከል እና መቆጣጠር ስራዎችን በማከናወን እና ማህበረሰቡን ያማከለ አገልግሎት መስጠት በመቻሏ ነው።

በተለይም የማህፀን ጫፍ ካንሰርን በመከላከል ላስመዘገበችው ውጤት እውቅናው መሰጠቱን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት 79ኛው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ሽልማቱን ተቀብለዋል።
ተመድ ኢትዮጵያ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ያላትን አስተዋፅኦ አደነቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከተመድ የሰላም ኦፕሬሽን ረዳት ዋና ፀሐፊ ዣን ፒዬር ለክሮይ ጋር በሰላም ማስከበር ተልዕኮ አብይ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።

ረዳት ዋና ፀሐፊው ኢትዮጵያ ለተመድ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ያላትን አስተዋፅኦ እና ከድርጅቱ የሰላም ኦፕሬሽን ጋር የፈጠረችውን ጠንካራ ግንኙነት አድንቀዋል።

አምባሳደር ታዬ በበኩላቸው ፥ ኢትዮጵያ ሽብርተኝነትን በመዋጋት ዙሪያ ያላትን ቁርጠኝነት ገልጸው በሶማሊያ ከድህረ አትሚስ በኋላ የሚኖረው የኃይል ስምሪት በቂ ጊዜ ተወስዶ በጥንቃቄ መከናወን እንዳለበት ትኩረት ሰጥተው ገልፀዋል።

ሚኒስትሩ አሁን ላይ ባልተረጋጋ የደኀንነት ሁኔታ ውስጥ የውጭ ኃይላት የሚያቀርቦት ጦር መሣሪያ አሸባሪዎች እጅ ላይ የመውደቁ እድል ከፍተኛ እንደሆነ ያላቸውን ስጋት ለረዳት ዋና ፀሐፊው ገልፀዋል።

ውይይቱ ኒውዮርክ እየተካሄደ ከሚገኘው 79ኛ የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ጎን ለጎን የተደረገ መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።
የዕለቱ የምንዛሪ ዋጋ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት በምስል
2024/11/16 10:52:44
Back to Top
HTML Embed Code: