Telegram Web Link
በአውሮፓ ዋንጫ ቤልጂየም በስሎቫኪያ ያልተጠበቀ ሽንፈት አስተናገደች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታ ስሎቫኪያ ቤልጂየምን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፋለች፡፡

የስሎቫኪያን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ኢቫን ሽራንዝ በ7ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡

የአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታ መርሐ ግብር ሲቀጥል ምሽት 4 ሰዓት ላይ በምድብ አራት ፈረንሳይና ኦስትሪያ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡
ም/ጠ/ሚ ተመስገን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሌማት ትሩፋትና የአረንጓዴ አሻራ ልማትን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሌማት ትሩፋትና የአረንጓዴ አሻራ ልማትን ጎብኝተዋል።

በጉብኝት መርሐ ግብሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን እና ሌሎች የሥራ ሃላፊዎችም ተገኝተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በማዕድን፣ በለም አፈር፣ በመልካም የአየር ጠባይ የታደለ መሆኑን ጠቅሰው÷ ይህም ለክልሉ ትልቅ የመልማት አቅም ነው ብለዋል።

ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ በግብርና ሥራ ለውጥ ካመጡ ክልሎች አንዱ እንደሆነ በማንሳት÷ ተዘዋውረው የተመለከቷቸው የሌማት ትሩፋት ሥራዎች በአጭር ጊዜ አበረታች ውጤት ማምጣታቸውን ገልጸዋል።https://www.fanabc.com/archives/250203
Live stream finished (35 minutes)
ፖርቹጋል የምትጠበቅበት የአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታ ዛሬ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ17ኛው የ2024 የአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታ ፖርቹጋል ከቼክ ሪፐብሊክ የሚያደርጉት ፍልሚያ ይጠበቃል፡፡

የመጀመሪያው ዙር የምድብ ማጣሪያ የመጨረሻ ጨዋታዎች ዛሬ ይካሄዳሉ፡፡

በዚህም በምድብ ሥድስት የሚገኙት ቱርክ እና ጆርጂያ ምሽት 1 ሠዓት ላይ የሚጫወቱ ሲሆን÷ ጨዋታውን የማሸነፍ ዕድሉ ለቱርክ ተሰጥቷል፡፡

እንዲሁም በቅድመ ጨዋታ ግምት እንደምታሸንፍ የተገመተችው ፖርቹጋል ምሽት 4 ሠዓት ላይ ከቼክ ሪፐብሊክ ጋር የምታደርገው ፍልሚያ ትኩረት ስቧል፡፡

ትናንት በተካሄዱ ጨዋታዎች ፈረንሳይ ኦስትሪያን እንዲሁም ስሎቫኪያ ቤልጂየምን በተመሳሳይ 1 ለ 0 ሲያሸንፉ÷ ሮማንያ ዩክሬንን 3 ለ 0 መርታቷ ይታወሳል፡፡
በጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) አቅጣጫ መሰረት በጎንደር እየተገነቡ ያሉ ፕሮጀክቶች አፈጻጸም አበረታች መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሰጡት አቅጣጫ መሠረት በጎንደር ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ግንባታ አፈጻጸም አበረታች መሆኑ ተመላከተ፡፡ በክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር የተቋቋመው ግብረ-ኃይል በጎንደር ከተማ በፌደራል መንግሥት እየተገነቡ ያሉ ፕሮጀክቶችን አፈፃፀም ሂደት ከጎንደር ከተማ አሥተዳደር ጋር ገምግሟል፡፡ በግምገማውም የአስፋልት መንገድ የሥራ እንቅስቃሴን ጨምሮ የጎንደር…

https://www.fanabc.com/archives/250217
የክልሉ የአደጋ ስጋት አመራር ም/ቤት ምስረታ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአደጋ ስጋት አመራር ምክር ቤት የምስረታ መርሐ-ግብር በወላይታ ሶዶ ከተማ በመካሄድ ላይ ነው፡፡ በምስረታ መድረኩ ላይ÷ የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር ጥላሁን ከበደ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች መገኘታቸውን የርዕሰ መሥተዳድር ጽ/ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡ ከምክር ቤቱ ምስረታ በተጨማሪ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ፖሊሲ በተመለከተ እና…

https://www.fanabc.com/archives/250228
ለሀገራዊ ምክክር አጀንዳ በመቅረፅ ሂደት የሚተኮርባቸው ጉዳዮች :-

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የምክክር አጀንዳዎችን በማሰባሰብ እና በመቅረፅ ሂደት ውስጥ ዘርፈ-ብዙ ተግባራትን ያከናውናል፡፡ ከሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎችና ከዳያስፖራው ማኅበረሰብ÷ ግልፅ፣ አካታችና አሳታፊ በሆነ መንገድ የተሰበሰቡ አጀንዳዎችን ለኮሚሽኑ ምክር ቤት በየፈርጁ ተለይተው ይቀርባሉ፡፡ ከቀረቡ በኋላም ለሀገራዊ ምክክር ጉባዔ የሚሆኑ አጀንዳዎች እንደሚቀረጹ የኮሚሽኑ መረጃ አመላክቷል፡፡ በአጀንዳ ቀረፃ…

https://www.fanabc.com/archives/250235
በህዳሴው ግድብ ላይ የመገናኛ ብዙኃን ሚናን በተመለከተ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ የመገናኛ ብዙኃን ሚናን የተመለከተ መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡ በመድረኩ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሕዝብ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አረጋዊ በርሄን (ዶ/ር) ጨምሮ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች፣ ጋዜጠኞችና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል። በውይይቱም የመገናኛ ብዙኃን ባለፉት ዓመታት…

https://www.fanabc.com/archives/250238
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የጨዋታ መርሐ-ግብር ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ2024/25 የውድድር ዓመት የጨዋታ መርሐ-ግብር በዛሬው ዕለት ይፋ ተደርጓል።

በዚሁ መሠረት የ2024/25 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በፈረንጆቹ ነሐሴ 16 ቀን 2024 ማንቼስተር ዩናይትድ ከፉልሃም በሚያደርጉት ጨዋታ የሚጀመር ይሆናል፡፡

በሊጉ የመጀመሪያ ሣምንት ጨዋታዎችም÷ የ2023/2024 የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን ማንቼስተር ሲቲ ከቼልሲ የሚያደርጉት ጨዋታ ከወዲሁ ይጠበቃል።

እንዲሁም÷ አርሰናል ከዎልቭስ፣ ዌስትሃም ከአስቶን ቪላ፣ ኢፕስዊች ከሊቨርፑል፣ ኤቨርተን ከብራይተን፣ ኖቲንግሃም ፎረስት ከቦርንመዝ፣ ኒውካስል ዩናይትድ ከሳውዛምፕተን፣ ሌስተር ሲቲ ከቶተንሃም፣ ብሬንትፎርድ ከክሪስታል ፓላስ ጋር በመጀመሪያው ሣምንት ይፋለማሉ፡፡
በባሕር ዳር የኮሪደር ልማት ሥራ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል የባሕርዳር ከተማ አሥተዳደር የኮሪደር ልማት መርሐ-ግብር በዛሬው ዕለት ተጀምሯል። ከተሞችን ጽዱና ለነዋሪዎች ምቹ የማድረግ ሀገራዊ መርሐ-ግብር አካል የሆነው የባሕር ዳር ከተማ የኮሪደር ልማት የዲዛይን ጥናት ሥራ ተጠናቅቆ ርዕሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ በተገኙበት ተጀምሯል፡፡ አቶ አረጋ በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷ ልማቱ የክልሉ ከተሞች ራሳቸውን የሚያድሱበት፣…

https://www.fanabc.com/archives/250247
2024/09/27 22:28:44
Back to Top
HTML Embed Code: