Telegram Web Link
በአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታ ሮማንያ ዩክሬንን 3 ለ 0 አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) እየተካሄደ በሚገኘው የአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታ ቀደም ብሎ የአሸናፊነት ግምት ያልተሰጣት ሮማንያ ዩክሬንን 3 ለ 0 ረትታለች፡፡

ኳስ ተቆጣጥሮ በመጫወት ብልጫ የነበራት ዩክሬን÷ ስታንቺዩ በ29ኛው፣ ማሪን በ53ኛው እና ድራጉስ በ57ኛው ደቂቃ ከመረብ ባሳረፏቸው ጎሎች ሽንፈት አስተናግዳለች፡፡

ውጤቱን ተከትሎም ሮማንያ ሦስት ነጥብ በመያዝ በምድብ አምስት ቁንጮ ላይ ተቀምጣለች፡፡

17ኛው የ2024 የአውሮፓ ዋንጫ መርሐ-ግብሮች ሲቀጥሉ÷ በምድብ አምስት የሚገኙት ቤልጂየም እና ስሎቫኪያ ምሽት 1 ሠዓት ላይ ይጫወታሉ፡፡

እንዲሁም በምድብ አራት የሚገኙት ኦስትሪያ እና ፈረንሳይ ምሽት 4 ሠዓት ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ ከፍተኛ ትኩረትን ስቧል፡፡

ትናንት በተካሄዱ ጨዋታዎች እንግሊዝ ሰርቢያን 1 ለ 0 እንዲሁም ኔዘርላንድስ (ሆላንድ) ፖላንድን 2 ለ 1 ሲረቱ ስሎቬኒያ ከዴንማርክ አንድ አቻ መለያየታቸው ይታወሳል፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን አሶሳ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የልማት ሥራዎችን ለመጎብኘት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ ገብተዋል፡፡

አሶሳ ከተማ ሲደርሱም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አሻድሊ ሃሰንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እና የከተማዋ ነዋሪዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የማዕድን ሚኒስትር ሐብታሙ ተገኝ (ኢ/ር) እና ሌሎች የፌደራል የሥራ ኃላፊዎችም ከአቶ ተመስገን ጋር አሶሳ ተገኝተዋል።

በክልሉ በሚኖራቸው ቆይታ የግብርና እና የአረንጓዴ ዐሻራ ሥራዎችን ጨምሮ ሌሎች የልማት ሥራዎችን እንደሚጎበኙ ይጠበቃል፡፡

አቶ ተመስገን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ “የታላቁ ህዳሴ ግድብ መገኛ፣ የንጉስ ሼህ ሆጀሌ ሀገር፣ የወርቋ ምድር ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ገብተናል፤ በቆይታችንም በክልሉ የሚገኙ ልዩ ልዩ የልማት ስራዎችን የምንጎበኝ ይሆናል” ብለዋል፡፡

በአሶሳ የሞቀ አቀባበል ላደረጉላቸው የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር እና ካቢኔያቸው እንዲሁም የአሶሳ ከተማ ሕዝብም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በፍሬሕይወት ሰፊው
የሠራዊቱን ኑሮ ለመደጎም እየተሠራ ነው -ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሠራዊቱን ኑሮ ለመደጎም እንደተቋም አመርቂ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገለጹ፡፡

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ በመከላከያ ጠቅላይ መምሪያ ጠቅላላ አገልግሎት ዋና ዳይሬክቶሬት የቤቶችና ካምፕ አሥተዳደር ዳይሬክቶሬት የሥራ እንቅስቃሴን ጎብኝተዋል።

በጉብኝታቸውም÷ በቁርጠኛ የመከላከያ አመራሮች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተቋማችን የጀመረው የዕድገት ጉዞ በተፈለገው ልክ ውጤት እያመጣ ነው ብለዋል፡፡

በተለይም አሁን ላይ የሠራዊቱን ኑሮ ለመደጎም እንደተቋም አመርቂ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ተቋማዊ የሪፎርም ሂደታችን ከዕቅድ አንፃር በሚፈለገው ልክ ግቡን እንዲመታ በመከላከያ ጠቅላይ መምሪያ የጠቅላላ አገልግሎት ዋና ዳይሬክቶሬት ኃላፊነቱን በሚገባ እየተወጣ ነው ሲሉም አረጋግጠዋል፡፡

ዳይሬክቶሬቱ በውስጡ የነበሩ ችግሮችን በመቅረፍ በሠራዊቱ ውስጥ ዘርፈ ብዙ የሆኑ ችግር ፈቺ ተግባራትን መሥራቱን እና ለሌሎቹም አርአያ እየሆነ ያለ ክፍል መሆኑንም በጉብኝታቸው ማረጋገጣቸውን ተናግረዋል፡፡

በሁሉም የመከላከያ ክፍሎች ውጤታማ የለውጥ ሥራዎች እየተሠሩ ነው ማለታቸውን የመከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ መረጃ አመላክቷል፡፡
በ23ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለሚካፈለው የኢትዮጵያ ልዑክ ሽኝት ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በካሜሮን ዱዋላ ከተማ በሚደረገው 23ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ለሚካፈለው የኢትዮጵያ ልዑክ ቡድን በዛሬው ዕለት ሽኝት ተደርጓል። በ23ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከተዘጋጁት 45 የሜዳ ላይ ተግባራት ኢትዮጵያ በ41ዱ የምትሳተፍ ሲሆን÷34 ሴት እና 43 ወንድ አትሌቶችም ኢትዮጵያን ወክለው ይሳተፋሉ። የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ…

https://www.fanabc.com/archives/250184
1 ሺህ 172 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 172 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል። የዛሬ ተመላሾች ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ÷ከእነዚህ ውስጥም 2 ጨቅላ ሕጻናትና ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ 29 ታዳጊዎች አንደሚገኙ ተገልጿል፡፡ ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን ድጋፍና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ሥራ እየተከናወነ መሆኑንም የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ…

https://www.fanabc.com/archives/250189
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በኦሮሚያ ክልል የቡና ችግኝ ተከላ ሥራ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች የቡና ችግኝ ተከላ ሥራ መጀመሩን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷የኦሮሚያ ክልል የቡና ምርትን ጥራትና ብዛት በመጨመር የውጭ ምንዛሬንና የአርሶ አደሩን ገቢ በማሳደግ ላይ በትኩረት እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

ከኦሮሚያ ዞኖች በብዛትና በጥራት ቡናን የማምረት ዓላማን በማሳካት ላይ ከሚገኙት ውስጥ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች በቀዳሚነት እንደሚጠቀሱ አንስተዋል፡፡

በ2016 ዓ.ም እንደ ክልል ከተዘጋጀው 2 ነጥብ 6 ቢሊየን የቡና ችግኝ ውስጥ ከ120 ሚሊየን የሚልቀው በሁለቱ ጉጂ ዞኖች መዘጋጀቱን ጠቁመዋል፡፡

አሁን ላይም በጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች የቡና ችግኝ ተከላ ሥራ መጀመሩን ነው ርዕሰ መስተዳድሩ የገለጹት፡፡

ያለውን ሰፊ እድል በመጠቀም የቡና ልማት በማስፋፋት ረገድ ጠንከር ያለ እንቅስቃሴ ቢታይም ያለውን እምቅ አቅም አሟጦ ለመጠቀም እጅግ ከፍ ያለ ቁርጠኝነት እንደሚጠይቅ አሳስበዋል፡፡

የቡና ኢኒሼቲቭን ያስተዋወቀው የ"ነቀምቴ አዋጅ" በ2011 ዓ.ም ይፋ ከተደረገ ወዲህ የተያዘውን ዓመት ጨምሮ በአጠቃላይ 8 ቢሊየን የቡና ችግኝ በመልማት ላይ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል፡፡

በዚሁ መሠረት ለቡና ምርት ጥራትና ብዛት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ሀገራችንና አርሶ አደሮች ከአረንጓዴው ወርቅ ማግኘት ያለባቸውን ጥቅም ይበልጥ የምናረጋግጥ ይሆናል ሲሉም ገልጸዋል።
Live stream finished (1 hour)
2024/11/16 09:33:05
Back to Top
HTML Embed Code: