Telegram Web Link
የዕለቱ የምንዛሪ ዋጋ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ቦክሰኛ ማይክ ታይሰን በጄክ ፖውል ተሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የ58 ዓመቱ አሜሪካዊ የከባድ ሚዛን ቦክሰኛ ማይክ ታይሰን ከ27 ዓመቱ ጄክ ፖውል ጋር ባደረገው ግጥሚያ ተሸንፏል፡፡

ታይሰን ዛሬ ማለዳ ያደረገው ግጥሚያ ራሱን ከፕሮፌሽናል ውድድር ካገለለ ከ19 ዓመታት በኋላ የተከናወነ ነው፡፡

የግጥሚያውን ውጤት ተከትሎም ታይሰን 20 ሚሊየን እና ጄክ ፖውል 40 ሚሊየን ዶላር አግኝተዋል፡፡
የኤሌክትሪክ መኪኖችን ለመገጣጠም ያለመ ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኤሌክትሪክ መኪኖችን ለመገጣጠም እና በቴክኒክ ጉዳዮች ላይ አብሮ ለመሥራት ያለመ የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ፡፡

የመግባቢያ ስምምነቱን የተፈራረሙት ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ፣ ኤስ ጂ አውቶሞቲቭ ግሩፕ እና ሚስተር ሉታ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ናቸው፡፡

https://www.fanabc.com/archives/271171
ኢትዮጵያ ከታንዛኒያ ዛሬ ጨዋታዋን ታደርጋለች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2025 የሞሮኮ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ አምስተኛ የምድብ ጨዋታ ኢትዮጵያ ታንዛንያን ትገጥማለች። ጨዋታው ምሽት 1 ሠዓት ላይ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በሚገኘው ስታድ ደ ማርትየርስ ስታዲየም ይደረጋል።

https://www.fanabc.com/archives/271184
የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀንን ለማክበር ተዘጋጅተናል- የዲላ ከተማ ነዋሪዎች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) 19ኛውን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል በድምቀት ለማክበር መዘጋጀታቸውን ፋና ብሮድካስቲንግ ከኮርፖሬት ያነጋገራቸው የዲላ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ። የዘንድሮው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል “ሀገራዊ መግባባት ለኅብረ-ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ሐሳብ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አርባምንጭ ከተማ ይከበራል። ክልሉ በአዲስ መልክ በተደራጀ ማግስት ለመጀመሪያ…

https://www.fanabc.com/archives/271187
ማስታወቂያ

#InfinixEthiopia

የዛንዚባር የቢዝነስ ክላስ ደርሶ መልስ የአውሮፕላን ቲኬት፣ የኢንፊኒክስ ስማርት ቲቪ፣ የኢንፊኒክስ ላፕቶፕ እንዲሁም ሌሎች አጓጊ ሽልማቶችን ኢንፊኒክስ ስማርት ስልኮች የሆኑትን ሆት 40 ፣ ኖት 40 ፣ ዜሮ 40 እና የኢንፊኒክስ ስማርት TVን ሲገበያዩ ኩፖን በመውሰድ አብሮት ካለ ወዳጅ ዘመድ ወይም ጓደኛ ጋር በመረጡት ስፍራ ፎቶ በመነሳት #InfinixEthiopia የሚለውን ሃሽ ታግ በመጠቀም እና ማህበራዊ ሚዲያ ላይ በመለጠፍ ማሸነፍ ይችላሉ ይፍጠኑ የዚህ ልዩ የሽልማት ፕሮግራም አካል ይሁኑ፡፡

መመሪያ

1. የኢንፊኒክስ ኢትዮጵያን ፌስ ቡክ ፣ ኢንስታግራም እና ቲክቶክ ገጾችን ፎሎው ያድርጉ፡፡
2. የተነሱትን ፎቶ በመረጡት ማህበራዊ ሚዲያ ሲለጥፉ የኢንፊኒክስ ኢትዮጵያን ገፅ ከፖስቶት ጋር ታግ ያድርጉ፡፡

3. #InfinixEthiopia የሚለውን ሃሽታግ መጠቀሞን አይርሱ፡፡

Tag ሲያደርጉ ለ Facebook @InfinixMobileEthiopia ፣ ለ Instagram @infinixethiopia ለ TikTok @Infinixet እና ለ Telegram @Infinixeth ሜንሽን ማድረግ እንዳይረሱ።
የዓለም ጤና ድርጅት የኩፍኝ በሽታ እየጨመረ ሊሄድ እንደሚችል አመላከተ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ጤና ድርጅት የኩፍኝ በሽታ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ20 በመቶ መጨመሩን አስታውቋል፡፡

ድርጅቱ በፈረንጆች 2023 ከ10 ሚሊየን በላይ ሰዎች በኩፍኝ መያዛቸውን አስታውሶ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር ዘንድሮ ከ20 በመቶ በላይ መጨመሩን አስታውቋል፡፡

በሽታው ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ107 ሺህ በላይ ሰዎችን ሕይወት መቅጠፉን እና አብዛኞቹ ሕጻናት መሆናቸውን አብራርቷል፡፡

https://www.fanabc.com/archives/271198
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ምርጥ የአፍሪካ ካርጎ አየር መንገድ ሽልማትን አገኘ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ በ ዓረቢያን ካርጎ አዋርድስ ምርጥ የአፍሪካ ካርጎ አየር መንገድ ሽልማት አገኘ፡፡

የሽልማት አሰጣጥ መርሐ-ግብሩ በዱባይ ከተማ ተካሂዷል፡፡

አዋርዱ በገልፍ ሀገራት ለሚሰጡ ምርጥ የአየር ዕቃ ጭነት አገልግሎቶች ዕውቅና የሚሰጥበት መሆኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ መረጃ አመላክቷል፡፡
የውጭ ምንዛሪ ማሻሻያ ትግበራ ሲዳሰስ
https://www.youtube.com/watch?v=2R1z7J8Rc2s
Live stream finished (39 minutes)
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ ሚሆኑ መንገዶች ይፋ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ነገ የሚካሄደው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡ የውድድሩ መነሻ እና መድረሻ መቀስል ዐደባባይ መሆኑን ያስታወቀው ፖሊስ÷ ሩጫው እስከሚጠናቀቅ ድረስ ከታች የተዘረዘሩት መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ ብሏል፡፡ -ከኦሎምፒያ ዐደባባይ ወደ መስቀል ዐደባባይ (ኦሎምፒያ ዐደባባይ ) – ከጥላሁን…

https://www.fanabc.com/archives/271206
2024/11/16 11:36:22
Back to Top
HTML Embed Code: