Telegram Web Link
የገበታ ለሀገር አካል የሆነው ወንጪ-ደንዲ ኢኮ ቱሪዝም
የፓኪስታን ባለሀብቶች በኢንዱስትሪ ፓርኮች ኢንቨስት ማድረግ እንፈልጋለን አሉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የፓኪስታን ባለሀብቶች ድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጣናን ጨምሮ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ኢንቨስት ማድረግ እንደሚፈልጉ ገለጹ፡፡ በኢንዱስትሪ ልማት ኮርፖሬሽን የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሽፈራው ሰለሞን ከፓኪስታን ባለሃብቶች ጋር ተወያይተዋል፡፡ በዚሁ ወቅት ኮርፖሬሽኑ በሚያሥተዳድራቸው 13 ኢንዱስትሪ ፓርኮችና ድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጣና ያሉ መሠረተ-ልማቶችን እና የኢንቨስትመንት ማበረታቻዎችን…

https://www.fanabc.com/archives/263528
ኢትዮጵያ በ79ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እየተሳተፈች ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በኒውዮርክ እየተካሄደ በሚገኘው 79ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ጠቅላላ ጉባኤ እየተሳተፈች ነው። በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሤ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በመድረኩ በመሳተፍ ላይ ይገኛል። በልዑካን ቡድኑ ውስጥ የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)፣ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ…

https://www.fanabc.com/archives/263532
የዓለም ባንክ ለገጠሩ ማህበረሰብ የጤና አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት እንደሚደግፍ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ባንክ ከከተማ ርቀው በገጠር ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች የጤና አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ በመንግስት የሚደረገውን ጥረት እንደሚደግፍ ገለጸ። የዓለም ባንክ ከፍተኛ ሃላፊዎች በጤና ሚኒስቴር እየተተገበሩ የሚገኙ ማህበረሰብ አቀፍ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን የሚያረጋግጡ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል፡፡ ሃላፊዎቹ በቢሾፍቱ የሚገኘውን የጨለለቃ ጤና ጣቢያን በጎበኙበት ወቅት የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ሃላፊ…

https://www.fanabc.com/archives/263537
አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከኡጋንዳ እና ርዋንዳ አቻቸው ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኒውዮርክ እየተካሄደ ከሚገኘው 79ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (የተመድ) ጠቅላላ ጉባዔ ጎን ለጎን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከኡጋንዳ እና ርዋንዳ አቻቸው ጋር ተወያይተዋል።

አምባሳደር ታዬ ከኡጋንዳ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢሊቪየር ኑሁንጊሬሄ እና የርዋንዳ ውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ጄጄ ኦዶንጎ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

ከርዋንዳው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጄጄ ኦዶንጋ ጋር በነበራቸው ውይይት በናይል የውሃ ሃብት ፍትሃዊ አጠቃቀም ላይ ሁለቱ ሀገራት ስላላቸው የጋራ አቋም ዙሪያ ሀሳብ ተለዋውጠዋል።

ከኡጋንዳው አቻቸው ጋር በነበራቸው ውይይትም በምስራቅ አፍሪካ ቀጣና የሰላም ሁኔታ ላይ የመከሩ ሲሆን፤ በድህረ በሶማሊያ ከአፍሪካ ኅብረት የሽግግር ሰላም ማስከበር ተልዕኮ (አትሚስ) መደረግ ስላለባቸው ጥንቃቄዎች እና አጠቃላይ ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።

ኢትዮጵያና ኡጋንዳ በሶማሊያ ሰራዊት አሰማርተው የነበሩ በመሆናቸው ድህረ አትሚስ ሽብርተኝነትን በመዋጋት የተመዘገበው ውጤት ወደኋላ በማይመልስ መልኩ መፈጸም እንዳለበት መክረዋል።

በጥቅምት ወር አጋማሽ ላይ ኡጋንዳ የምታስተናግደው የናይል ጉባዔ የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ወደ ተግባር እንዲገባ የሚያስችሉ ውሳኔዎች የሚተላለፉበት እንደሚሆን ያላቸውን እምነት አምባሳደር ታዬ ገልጸዋል።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
‹‹የጨበራ የዝሆን ዳና ሎጅ ሰባተኛው የኢጋድ የቱሪዝም ሻምፒዮን ስያሜን ያገኘንበት ማሳያችን ነው - ከማህደራችን።

ጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክ ደጃፍ እንደደረሱ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገበታ ለሀገር ፕሮጀክት አካል የሆነው የጨበራ የዝሆን ዳና ሎጅ ይቀበልዎታል።

ወደ ዐሥር ሄክታር የሚጠጋ የተንጣለለ ቦታ ላይ የተንሰራፋው ይህ ሎጅ ፕሬዘዳንሺያል ማረፊያዎች ከራሳቸው የግል የመዋኛ ገንዳዎች ጋር ፤ቪአይፒ ቪላዎች ፤ ደረጃቸውን የጠበቁ የመኝታ ክፍሎች፤ የስብሰባ ማዕከል እና ሙዚየም ፤ መንፈስን የሚያድስ የመዋኛ ገንዳ ፤ ምግብ እና መጠጥ ቤት ፤ የውበት መጠበቂያ እና የመዝናኛ ማዕከላት አሉት፡፡

በዚህ ሁሉ ጸጋው የጨበራ የዝሆን ዳና ሎጅ የተፈጥሮ ውበትን ከነሙሉ ግርማው የሚያጣጥሙበት መዳረሻ ነው።›› - የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት
በአዲስ አበባ ከነገ እስከ ዓርብ ማለዳ ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር ተከለከለ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በመስቀል ደመራ በዓል ምክንያት በአዲስ አበባ ከተማ ከነገ ማለዳ 12 ሠዓት እስከ ዓርብ ማለዳ 12 ሠዓት ድረስ ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር ተከለከለ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ እንዳስታወቀው÷ ለመስቀል ደመራ በዓል አከባበር የመንገድ ትራንስፖርት ደህንነት ሲባል ከመስከረም 16 እና 17…

https://www.fanabc.com/archives/263551
የመስቀል ደመራ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለትራፊክ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) መስከረም 16 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል ምክንያት የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ ተገለፀ።

በዚህም ነገ ከረፋዱ 5 ሰአት ጀምሮ እስከ መርሀ ግብሩ ፍፃሜ ድረስ ለተሽከርካሪዎች ዝግ የሚደረጉ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል። በዚህም መሠረት ፦

• ከቅዱስ ኡራኤል አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል አደባባይ ላይ፣
• ከቦሌ አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ኦሎምፒያ አደባባይ ላይ፣
• ከመስቀል ፍላወር ወደ ኦሎምፒያ የሚወስደው መንገድ ጋዜቦ አደባባይ ላይ፣
• ከአጎና ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ለከባድ ተሽከርካሪ አጎና ሲኒማ አጠገብ እንዲሁም ለቀላል ተሽከርካሪ ጥላሁን አደባባይ (አራተኛ ክፍለ ጦር ላይ)፣
• ከለገሀር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ለገሀር መብራት ላይ፣
• ከቴሌ ማቋረጫ ወደ ስታዲየም ለሚጓዙ ቴሌ ማቋረጫ፣
• ከራስ ሆቴል ወደ ስታድየም ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ራስ ሆቴል ላይ፣
• ከሃራምቤ መብራት ወይም ከአምባሳደር ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ሃራምቤ መብራት ላይ፣ ..............

https://www.fanabc.com/archives/263562
በትራፊክ አደጋ የ28 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ከወላይታ ሶዶ ከተማ ወደ ዳውሮ ዞን ሲጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ተገልብጦ የ28 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

በወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ የትራፊክ አደጋ መከላከልና ቁጥጥር ዲቪዥን ኃላፊ ኢንስፔክተር ወልዴ ቢሊሶ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ ከሟቾች በተጨማሪ በ19 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡

አደጋው ዛሬ ቀን 7 ሠዓት ላይ በወላይታ ዞን ኪንዶ ዲዳዬ ወረዳ ፋታታ ቀበሌ መከሰቱንም አረጋግጠዋል፡፡

የተከሰተው አደጋ ከባድ መሆኑን ጠቅሰው የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል አመላክተዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው
የመስቀል ደመራ በዓል ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከበር በቴክኖሎጂ የታገዘ ዝግጅት መደረጉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስቀል ደመራ በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር በቴክኖሎጂ የታገዘ ዝግጅት መደረጉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ገለጹ፡፡ በዓሉ ያለምንም የጸጥታ ችግር በድምቀት እንዲከበር ሁሉም የጸጥታ አካላት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡ የአዲስ አበባ ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ሀሰን ነጋሽ በበኩላቸው÷ በዓሉን በሰላም ለማሳለፍ…

https://www.fanabc.com/archives/263568
2024/09/28 10:19:36
Back to Top
HTML Embed Code: