Telegram Web Link
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለቱሪዝም ዘርፍ በተሰጠው ልዩ ትኩረት በገበታ ለሀገር ከተገነቡ የቱሪስት መዳረሻዎች መካከል አንዱ - ወንጪ-ደንዲ ኢኮ ቱሪዝም ፕሮጀክት

👉 ፕሮጀክቱ ከወሊሶ አምቦ፤ ከወንጪ ደንዲ፤ ከደንዲ አስጎሪ ሰፊ የሆነ ቦታ ላይ በምዕራፍ ተከፋፍሎ እንዲገነባ የተቀረጸ ሰፊ ራዕይ ያለው ትልቅ ሀገራዊ የልማት ዐሻራ ነው፡፡

👉 የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት አካል የሆነው የወንጪ-ደንዲ ኢኮ ቱሪዝም ፕሮጀክት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ጥር 4 ቀን 2016 ዓ.ም ተመርቋል።

👉 በግንባታ ሂደት ብቻ ከ10 ሺህ ለሚበልጡ የአካባቢው ነዋሪዎች የሥራ ዕድል ፈጥሯል፡፡

👉 ፕሮጀክቱ ከቱሪስት መዳረሻነት ባሻገር ለአካባቢው የማያቋረጥ የሥራ ዕድልና ልማት ማስገኘቱን ይቀጥላል፡፡ ለአብነትም በ22 ማኅበራት ለተደራጁ ከ560 የሚበልጡ ወጣቶች በተለያዩ ዘርፎች የሥራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ መሠራቱ ይታወቃል፡፡

👉 ከአዲስ አበባ 135 ኪሎ ሜትር ርቀት ከወሊሶ-አምቦ መንገድ መሃል ላይ በእሳተ ጎመራ የተፈጠረ ነው፡፡

👉 ወንጪ ሐይቅ ዙሪያ ገባውን አረንጓዴ በለበሱ ድንቅ ተራራዎች የተከበበ ውብ ስፍራ ነው።

https://www.fanabc.com/archives/263481
በትራፊክ አደጋ የ7 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል በጂካዎ ወረዳ ትናንት ምሽት በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሰባት ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡ አደጋው የደረሰው ትናንት ምሽት 1 ሰዓት አካባቢ ከጋምቤላ ከተማ ወደ ኑዌር ዞን በመጓዝ ላይ የነበረ አምቡላንስ በጂካዎ ወረዳ የባሮ ወንዝ ጊዜያዊ ድልድይን ጥሶ ወንዝ ውስጥ በመግባቱ መሆኑ ተገልጿል፡፡ በዚህም የሰባት ሰዎች ህይወት…

https://www.fanabc.com/archives/263486
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የጥላሁን ገሠሠ ማስታወሻ- በፋና ቴሌቪዥን ብቻ

የመስቀል ዕለት ይጠብቁን
በአማራ ክልል ከ8 ሚሊየን ኩንታል በላይ የሩዝ ምርት ይጠበቃል ተባለ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በዘንድሮው የምርት ዘመን በሩዝ ሰብል ከለማው መሬት ከስምንት ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠበቅ የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ። በቢሮው የሩዝ ሰብል ልማት አስተባባሪ ወይዘሮ እንየ አሰፋ እንደገለጹት÷ በምርት ዘመኑ 150 ሺህ 226 ሄክታር መሬት በሩዝ ሰብል ለምቷል። በማዕከላዊ፣ ምዕራብና ደቡብ ጎንደር፣ በአዊና ሰሜን ጎጃም…

https://www.fanabc.com/archives/263489
የመስቀል ደመራ በዓልን በድምቀት ለማክበር ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስቀል ደመራ በዓልን በድምቀት ለማክበር ዝግጅት መጠናቀቁን የሐረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ረምዚ ሱልጣን አስታወቁ፡፡ በዓሉን በድምቀት ለማክበር ኮሚሽኑ ከሀገር መከላከያ፣ ፌደራል ፖሊስ፣ ከጸጥታ አካላት እና ከክልሉ ሕዝብ ጋር በቅንጅት እየሠራ ነው ማለታቸውን የሐረሪ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

https://www.fanabc.com/archives/263496
በተሳትፏዊ አነስተኛ የመስኖ ልማት ፕሮግራም 112 የመስኖ ግድቦች ለአገልግሎት መብቃታቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በተሳትፏዊ አነስተኛ የመስኖ ልማት ፕሮግራም ዝናብ አጠር በሆኑ አካባቢዎች 112 የመስኖ ግድቦች ተገንብተው ለአርሶ አደሮች አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ። የፕሮግራሙ ማጠናቀቂያ መርሐ ግብር የሚኒስቴሩ ከፍተኛ አመራሮች፣ ተጠቃሚ አርሶ አደሮችና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ተካሂዷል። የተሳትፏዊ አነስተኛ መስኖ ልማት ፕሮግራም አስተባባሪ ኑረዲን አሳሮ በዚህ ወቅት…

https://www.fanabc.com/archives/263499
ዓለም ለጦርነት የምታባክነውን ሀብት የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቋቋም ማዋል አለባት – ፕሬዚዳንት ሉላ ዳ ሲልቫ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም ለጦርነት የምታባክነውን ሀብት የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቋቋም ማዋል አለባት ሲሉ የብራዚል ፕሬዚዳንት ሉዊስ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ ገለጹ። በኒውዮርክ እየተካሄደው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) 79ኛው ጠቅላላ ጉባዔ መካሄዱን እንደቀጠለ ነው። በመድረኩ ንግግር ያደረጉት ፕሬዚዳንት ሉላ ዳ ሲልቫ፤ የዓለም መሪዎች ሰላም በመፍጠር የአየር ንብረት…

https://www.fanabc.com/archives/263502
በደቡብና በምሥራቅ ሊባኖስ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ እና በምስራቅ የሊባኖስ አካባቢዎች የፀጥታ ችግር እየተጠናከረ መምጣቱን ተከትሎ በሀገሪቱ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄኔራል ጽሕፈት ቤት ለዜጎቹ ጥሪ አቅርቧል፡፡ ጽሕፈት ቤቱ ባወጣው መረጃ በተለይም በደቡብ እና በምስራቅ የሊባኖስ አካባቢዎች የፀጥታ ችግር እየተጠናከረ መሆኑን ገልጾ÷ በእነዚህ አካባቢዎች ያሉ ዜጎችን ለይቶ ማወቅ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ብሏል፡፡ በመሆኑም…

https://www.fanabc.com/archives/263492
ማስታወቂያ

የነዳጅ ክፍያ
በሲቢኢ ብር ፕላስ ቀላል ነው!
*********
የሲቢኢ ብር ፕላስ መተግበሪያን ተጠቅመው
ከሲቢኢ ብር ሂሳብዎ ወይም ከባንክ ሂሳብዎ ጋር በማገናኘት በቀላሉ የነዳጅ ክፍያዎን መፈፀም ይችላሉ፡፡
**********
አሁኑኑ ወደ Google Play ወይም App Store በመግባት የሲቢኢ ብር ፕላስ መተግበሪያ ይጫኑ/ያዘምኑ፡
• ለአንድሮይድ ስልኮች፡
https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr
• ለአፕል ስልኮች፡
https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787
#cbe #cbebirr #ethiopia #digitalbanking #banking #business #fuel #payment
99 ኢትዮጵውያን ፍልሰተኞች ከጅቡቲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ 99 ህገ ወጥ ፍልሰተኞች ከነጋድ ባቡር ጣቢያ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ማድረጉን ገለፀ። ዜጎቹን የመመለሱ ስራ ጅቡቲ ከሚገኘው የዓለም አቀፍ ፍልሰተኞች ድርጅት ጋር በመተባበር የተደረገ መሆኑ ተመላክቷል። ኤምባሲው በየጊዜው ፍልሰተኞች ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እየሰራ ቢሆንም በህገ-ወጥ ስደት ምክንያት በየቀኑ የሚጠፋውን የሞት…

https://www.fanabc.com/archives/263511
ራፋዬል ቫራን ጫማ ሰቀለ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የሪያል ማድሪድ እና ማንቼስተር ዩናይትድ የቀድሞ ተከላካይ ሥፍራ ተጫዋች ራፋዬል ቫራን እግር ኳስ ማቆሙን አስታውቋል፡፡

ቫራን ባለፈው ክረምት የዝውውር መስኮት ማቼስተር ዩናይትድን በመልቀቅ የጣሊያኑን ኮሞ እግር ኳስ ክለብ መቀላቀሉ ይታወሳል፡፡

በአዲሱ ክለቡ በነበረበት ጊዜ ያጋጠመው ጉዳት ተከትሎም በ31 ዓመቱ ጫማ መስቀሉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በተጫዋችነት ዘመኑ ሀገሩ ፈረንሳይ የዓለም ዋንጫ ስታነሳ የራሱን አስተዋጽኦ ያበረከተው ቫራን÷ በቀድሞ ክለቡ ሪያል ማድሪድ በነበረው ስኬታማ ጊዜም ላሊጋን ጨምሮ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ማሳካት ችሏል፡፡
የመስቀል በዓልን ለማክበር ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ወደ ጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ እየገቡ የሚገኙ የበዓሉ ተሳታፊዎች -በምስል
በእስራኤልና ሂዝቦላህ መካካል የሚካሄደውን ጦርነት የማስቆም አቅም ያላት አሜሪካ ብቻ ናት ስትል ሊባኖስ ገለጸች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በእስራዔልና ሂዝቦላህ መካካል የሚካሄደውን ጦርነት የማስቆም አቅም ያላት አሜሪካ ብቻ እንደሆነች የችግሩ ሰለባ የሆነችው ሊባኖስ አስታወቀች። የሁለቱ ወገኖች ጦርነት መነሻ አጋርነቱን ለሃማስ ለማሳየት ሚሳዔሎችን ወደ እስራዔል ማስወንጨፍ በጀመረው ሂዝቦላህ ላይ እስራዔል አመራሮች ላይ የታለመ እርምጃ መውሰዷ እንደሆነ ተነግሯል። እስራኤል ለሂዝቦላህ ጥቃት በሰጠችው ምላሽና በወሰደችው የአየር…

https://www.fanabc.com/archives/263517
Live stream finished (36 minutes)
2024/09/28 08:17:05
Back to Top
HTML Embed Code: