Telegram Web Link
Live stream finished (29 minutes)
ዴንማርክና ስሎቬኒያ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጀርመን አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው 17ኛው የ2024 የአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታ ዴንማርክ እና ስሎቬኒያ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡

የዴንማርክን ጎል ክርስቲያን ኤሪክሰን በ17ኛው ደቂቃ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል፡፡

የስሎቬኒያን የአቻነት ጎል ጃንዛ በ77ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል።

ቀደም ብሎ 10 ሠዓት ላይ በተካሄደ ጨዋታ ኔዘርላንድስ (ሆላንድ) ከመመራት ተነስታ ፖላንድን 2 ለ1 አሸንፋለች፡፡

እንዲሁም ቀሪ የዛሬ የጨዋታ መርሐ-ግብር ሲቀጥል በምድብ ሦስት የሚገኙት ሰርቢያ እና እንግሊዝ ምሽት 4 ሠዓት ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር ያላትን የቆየ ግንኙነትና ትብብር አጠናክራ ትቀጥላለች – አቶ አደም ፋራህ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር ያላትን የቆየ ግንኙነትና ትብብር በሁሉም ዘርፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ ገለጹ። በአቶ አደም ፋራህ የተመራ ልዑክ ከሰኔ 9 እስከ 12 ቀን2016 በሚካሔደውና “ዎርልድ ማጆሪቲ ፎር መልቲፖላር ኦርደር” በሚል…

https://www.fanabc.com/archives/250050
በሩዋንዳ በተካሄደ የቦክስ ውድድር ኢትዮጵያ 2 የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሩዋንዳ ኪጋሊ በተካሄደ የቦክስ ውድድር ኢትዮጵያ ሁለት የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች፡፡ በውድድሩ ገነት ፀጋዬ በ57 ኪሎ ግራም የሩዋንዳ ተጋጣሚዋን በብቃት በማሸነፍ የወርቅ ሜዳሊያና የውድድሩ ድንቅ እንስት ቡጢኛ በመባል የዋንጫ ተሸላሚ ሆናለች፡፡ በወንዶች ምድብ ደግሞ በ63 ነጥብ 5 ኪሎ ግራም ኢ/ር አብርሃም ዓለም የሩዋንዳ አቻውን በሰፊ ልዩነት…

https://www.fanabc.com/archives/250055
አቶ እንዳሻው የ #ጽዱኢትዮጵያ ንቅናቄን በሆሳዕና ከተማ አስጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው “ጽዱ ከተሞች ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ሃሳብ የ #ጽዱኢትዮጵያ ንቅናቄን በሆሳዕና ከተማ አስጀምረዋል፡፡ ርዕሰ መስተዳድሩ በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ እንዳሉት÷ አካባቢን ፅዱና አረንጓዴ በማድረግ ድርቅን መከላከልና የከተማ ውበትን መጠበቅ ይገባል። የዞኑ መንግስት መላውን ህብረተሰብ በማሳተፍ ከተማዋን ፅዱና…

https://www.fanabc.com/archives/250065
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ማስታወቂያ!

ጤናችን በምርታችን !


በሀገራችን የመጀመሪያ የሆነው የሀገር ውስጥ የህክምና ግብዓት ምርትና ኢኖቬሽን ኤግዚብሽን ከ ሰኔ 15 - 20 /2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል፡፡

በዚህ ታላቅ ኤግዚብሽን ፤-

• በሀገራችን በባህላዊ እና በዘመናዊ መድሀኒት፤
• በህክምና መገልገያ መሳሪያ
• የጤና እና የግል ንጽህና መጠበቂያ ማምረት ላይ የተሰማሩ ከአነስተኛ አስከ ከፍተኛ አምራች ድርጅቶች ምርቶቻቸውን ያስተዋውቃሉ፤
• የቴክኖሎጂ እና የፈጠራ ውጤቶች ይቀርባሉ
• የሀገር ውስጥና አለም ዓቀፍ የንግድ ትስስሮች እና የልምድ ልውውጦች ይደረጋሉ፡፡
• ዓለም ዓቀፋዊ ተሞክሮዎችና አሰራሮችላይ ያተኮረ የፓናል ውይይቶች ይካሄዳሉ፤

እርስዎ፡- መጥው ሲጎበኙ ሀገራችን እያከናወነች ያለውን እና ወደፊት የምትደርስበትን የህክምና ግብዓት አምች ኢንደስትሪ ዘርፍ ሁለንተናዊ እድገት ይመለከታሉ፤ በርካታ ኢንቨስትመንት እድሎችም እንዳሉ ይገነዘባሉ፡፡

ይምጡ፤ ይካፈሉ፤ ይጎብኙ

ጤና ሚኒስቴር ከመድኃኒትና የህክምና መገልገያ አምራች ዘርፍ ማህበራት ጋር በመተባበር
ለበለጠ መረጃ 011 518 6262 / 952 ላይ ይደውሉ!! ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ!!
https://pharma-exhibition.moh.gov.et/

#ጤናችን በምርታች
#our health by our products
Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: twitter.com/FMoHealth
YouTube: @FMoHealthEthiopia
Tiktok: @mohethiopia
አፍሪካና ላቲን አሜሪካ ድምጻቸው እንዲሰማ በዓለም አቀፍ ተቋማት የተሻለ ውክልና ሊኖራቸው ይገባል – አቶ አደም ፋራህ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አፍሪካና ላቲን አሜሪካ ድምጻቸው እንዲሰማ በዓለም አቀፍ ተቋማት የተሻለ ውክልና ሊኖራቸው እንደሚገባ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ ገለጹ፡፡ በአቶ አደም ፋራህ የተመራ ልዑክ ከሰኔ 9 እስከ 12 ቀን2016 በሚካሔደውና “ዎርልድ ማጆሪቲ ፎር መልቲፖላር ኦርደር”…

https://www.fanabc.com/archives/250072
በአውሮፓ ዋንጫ ፈረንሳይ ከኦስትሪያ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 17ኛው የ2024 የአውሮፓ ዋንጫ መርሐ-ግብሮች ሲቀጥሉ ዛሬ ሦስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡

በዚሁ መሠረት በምድብ አምስት የሚገኙት ሮማንያ እና ዩክሬን ቀን 10 ሠዓት እንዲሁም ቤልጂየም ከስሎቫኪያ ምሽት 1 ሠዓት ላይ ይጫወታሉ፡፡

በሌላ በኩል በምድብ አራት የሚገኙት ኦስትሪያ እና ፈረንሳይ ምሽት 4 ሠዓት ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ ከፍተኛ ትኩረትን ስቧል፡፡

ዛሬ በሚካሄዱ ጨዋታዎች ዩክሬን፣ ቤልጂየም እና ፈረንሳይ የማሸነፍ ዕድል እንዳላቸውም ቅድመ ጨዋታ ግምቶች እየተሰነዘሩ ነው፡፡

ትናንት በተካሄዱ ጨዋታዎች እንግሊዝ ሰርቢያን 1 ለ 0 እንዲሁም ኔዘርላንድስ (ሆላንድ) ፖላንድን 2 ለ 1 ሲረቱ ስሎቬኒያ ከዴንማርክ አንድ አቻ መለያየታቸው ይታወቃል፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የፍትሕ ተቋማት ትራንስፎርሜሽን ንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የፍትሕ ተቋማት ትራንስፎርሜሽን ክልላዊ የንቅናቄ መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡ በመድረኩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ፣ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎችና የፍትሕ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች መገኘታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡ በቅርቡ የሚኒስትሮች ም/ቤት በሀገሪቱ የተቀናጀና የተናበበ የሽግግር ፍትሕ ሒደት የሚመራበት ሥርዓት መዘርጋት…

https://www.fanabc.com/archives/250075
የቦረና ከብት እርባታ ዲዳ ጡዩራ እርባታ እና ማሻሻያ ማዕከል- በምስል
2024/11/16 10:37:06
Back to Top
HTML Embed Code: