Telegram Web Link
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር የጦር ካቢኔያቸውን በተኑ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የሀገሪቱን ጦር ካቢኔ መበተናቸው ተሰምቷል፡፡ ውሳኔው የእስራኤል የጦር ካቢኔ ሚኒስትር ቤኒ ጋንትዝ ሥልጣን መልቀቃቸውን ተከትሎ የተደረገ መሆኑ ተመላክቷል፡፡ የጦር ካቢኔው መበተን ውሳኔ የእስራኤል የፖለቲካ እና ደህንነት ካቢኔ በጉዳዩ ላይ ከመከረ በኋላ የተላለፈ መሆኑንም አልጀዚራ ዘግቧል፡፡ የእስራኤል ጦር ካቢኔ ስድስት አባላት…

https://www.fanabc.com/archives/250097
በኦሮሚያ ክልል ከ20 ሺህ በላይ ፕሮጀክቶች ተጠናቀዋል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዘንድሮ በጀት ዓመት በኦሮሚያ ክልል ከ79 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው 20 ሺህ 664 አዲስና ነባር ፕሮጀክቶች መጠናቀቃቸውን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አወሉ አብዲ ገለጹ። በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ተገንብተው የተጠናቀቁና ፕሮጀክቶችን አስመልክቶ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አወሉ አብዲ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል። አቶ አወሉ በመግለጫቸው…

https://www.fanabc.com/archives/250096
Live stream finished (37 minutes)
በካሊፎርኒያ 50 ኪሎ ሜትር ካሬ የሸፈነ ሰደድ እሳት ተቀስቅሶ ጉዳት እያደረሰ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ ከሎስ አንጀለስ ሰሜን ምዕራብ የተቀሰቀሰ ሰደድ እሳት 50 ካሬ ኪሎ ሜትር ካሬ ቦታ እንደሸፈነና ነዋሪዎች እንዲለቁ ማስገደዱ ተገለጸ። ሰደድ እሳቱ ከአንድ ሺህ በላይ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን እንዲለቁ ማስገደዱን የአካባቢው ባለስልጣናት ተናግረዋል። የካሊፎርኒያ የደን እና የእሳት አደጋ መከላከል ክፍል (ካል ፋየር) እንደገለጸው÷ 400 የሚሆኑ የእሳት አደጋ…

https://www.fanabc.com/archives/250104
የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ከ23 ቢሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ምርቶችን ማገበያየቱን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በ2016 በጀት ዓመት 11 ወራት 23 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ዋጋ ያላቸው ምርቶችን ማገበያየቱን አስታወቀ። የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ በኃይሉ ንጉሴ፤ ተቋሙ በሀገሪቱ ባሉት 25 ቅርንጫፎች ከ200 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ ምርት መቀበሉን ተናግረዋል። በዚህም 23 ነጥብ 6 ቢሊየን…

https://www.fanabc.com/archives/250111
ማስታወቂያ!

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ እንኳን ለ1445ኛው ዓመተ ሒጅራ የዒድ- አልአድሃ (አረፋ) የዓል በሰላም አደረሳችሁ ሲል መልካም ምኞቱን ይገልጻል፡፡

ኢንተርፕራይዛችን በግንባታው ዘርፍ ግንባር ቀደም በመሆን ደረጃቸውን የጠበቁ የህንጻ፣ የመንገድ፣ የመስኖና ግድብ፣ የኤርፖርት እና መሰል ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ይገነባል፡፡

በኮንስትራክሽን ዘርፍ ጥራትን መለያው አድርጎ ዘላቂና አስተማማኝ የግንባታ ሥራዎችን በመሥራት በግንባታው ዘርፍ የልማት አጋርነቱን እያስመሰከረ ይገኛል፡፡

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1445ኛው ዓመተ ሒጅራ የዒድ - አልአድሃ (አረፋ) በዓል አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የደስታና የመተሳሰብ እንዲሆንላችሁ የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ይመኛል!!

ዒድ ሙባረክ!

መከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
ስለ ድርጅቱ የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦
https://www.dce-et.com/
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/defenseconstruction
ቴሌግራም፦
https://www.tg-me.com/www.tg-me.com/DCE2020
ትዊተር፦
https://twitter.com/
በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
“መስፈርት አላሟሉም” የተባሉ 41 ትምህርት ቤቶች ፈቃድ ተሠረዘ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) “የሚጠበቅባቸውን መስፈርት አላሟሉም” የተባሉ 41 ትምህርት ቤቶች ፈቃድ መሠረዙን የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

ፈቃዳቸው የተሠረዘው የትምህርት ፖሊሲውን ባለመጠበቅና መስፈርቱን ባለማሟላታቸው ነው ብሏል ባለስልጣኑ፡፡

ባለስልጣኑ በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን መዝግበው የሚያስተምሩ ትምህርት ቤቶችን እና ፈቃዳቸው የተሠረዘ የትምህርት ተቋማትን ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህም በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን መዝግበው የሚያስተምሩ ትምህርት ቤቶች 1 ሺህ 332 ሲሆኑ÷ የማስተማር ፈቃድ እንደተሰጣቸውም ገልጿል፡፡

በሌላ በኩል 43 ትምህርት ቤቶች በራሳቸው ጊዜ መቀጠል ስላልቻሉ ፈቃዳቸው ተሠርዟል መባሉን የባለስልጣኑ መረጃ አመላክቷል፡፡

እንዲሁም 150 ትምህርት ቤቶች ጉዳያቸው በሂደት ላይ መሆኑና ወደፊት እንደሚገለጽ ተጠቁሟል፡፡

41 ትምህርት ቤቶች ደግሞ የትምህርት ፖሊሲውን ባለመጠበቅና መስፈርቱን ባለማሟላታቸው ፈቃዳቸው መሠረዙን ነው ባለስልጣኑ ያስታወቀው፡፡
አምባሳደር ታዬ ከተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ፕሬዚዳንት ዴኒስ ፍራንሲስ ጋር ተወያዩ። አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴና ፕሬዚዳንት ዴኒስ ፍራንሲስ በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮችና በአፍሪካ ቀንድ አገራት የሰላም ማስከበር ጉዳዮች ዙሪያ ላይ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብዩ ተድላ ተናግረዋል። የተባበሩት መንግስታት…

https://www.fanabc.com/archives/250124
የአየር ብክለት ሁኔታ ጠቋሚ ዘመናዊ የራዳር መቆጣጠሪያ ለመትከል እየተሠራ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአየር ብክለት ሁኔታ ጠቋሚ ዘመናዊ የራዳር መቆጣጠሪያ ጣቢያ ለመትከል እየተሠራ መሆኑን የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡

ጣቢያዎቹ በተለያዩ አካባቢዎች እንደሚተከሉ የገለጹት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ፈጠነ ተሾመ÷ 250 ኪሎ ሜትር ራዲየስ ውስጥ መረጃዎችን በፍጥነት መሰብሰብ እንደሚያስችሉ አስታውቀዋል፡፡

የአየር ጠባይና ሁኔታ አመላካች የትንበያ መረጃዎችን ሰብስቦ በመተንተን ለቅድመ ማስጠንቀቂያና ልማት ሥራ እገዛ እንዲኖራቸው ለማድረግ ቀጣይነት ያለው ሥራ እየተሠራ መሆኑንም ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

ዓለም አቀፍ የአየር ጠባይ ክስተቶችን ከግምት በማስገባት የትንበያና የቅድመ ማስጠንቀቂያ አገልግሎት…

https://www.fanabc.com/archives/250136
በ2017 የትምህርት ዘመን የትምህርት አገልግሎት እንዳይሰጡ የታገዱ የትምህርት ተቋማት ዝርዝር ይፋ ሆነ

https://www.fanabc.com/archives/250141
ኮሪያ ሪፐብሊክ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የልማት ትብብር አጠናክራ ትቀጥላለች – አምባሳደር ጃንግ ካንግ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኮሪያ ሪፐብሊክ ከኢትዮጵያ ጋር ያላት የልማት ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በኢትዮጵያ የሀገሪቱ አምባሳደር ጃንግ ካንግ ተናገሩ። አምባሳደሩ ÷ኢትዮጵያና ኮሪያ ሪፐብሊክ በተለያዩ የትብብር መስኮች ጠንካራ የሁለትዮሽ ግንኙነት እንዳላቸው ተናግረዋል። ሁለቱ ሀገራት በፖለቲካ፣ በምጣኔ ኃብትና በልማት ዘርፎች ያላቸው ታሪካዊ ግንኙነት በሌሎች የትብብር ዘርፎችም እየሰፋ መምጣቱንም ነው ያነሱት። በቅርቡ…

https://www.fanabc.com/archives/250158
2024/11/16 08:42:34
Back to Top
HTML Embed Code: