Telegram Web Link
ለግብርናው ዘርፍ ትልቅ ፋይዳ ያላቸው ኤርትራክተሮችን ወደ ስራ አስገብተናል – ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) እጅግ ዘመናዊ የሆኑ፣ ለግብርናው ዘርፍ አገልግሎት ትልቅ ፋይዳ ያላቸው ኤርትራክተሮችን ዛሬ ወደ ስራ አስገብተናል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ግብርናችን የህልውናችን እና የሉዓላዊነታችን መሰረት ነው ብለዋል። ዘርፉን ከሚገጥሙት ፈተናዎች ለመታደግ ዘመኑ የደረሰባቸውን የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ…

https://www.fanabc.com/archives/249914
የሀገራችን ሙስሊም ማኅበረሰብ የመደጋገፍ ባህል ከተረጂነት ለመላቀቅ ወሳኝ ዕሴት ነው – ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ለዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት አስተላልፈዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ኢድ አል አድሃ (አረፋ) በሙስሊም ማኅበረሰቡ ዘንድ ከፍተኛ ክብር ያለው በዓል ነው ብለዋል። ዐቅሙ እና ሁኔታው የፈቀደላቸው ምዕመናን የሐጅ ሥነ…

https://www.fanabc.com/archives/249917
የዒድ አል-አድሃ በዓልን ለማክበር ህዝበ ሙስሊሙ በአዲስ አበባ ስቴዲየም እየተሰባሰበ ነው

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓልን ለማክበር ህዝበ ሙስሊሙ በአዲስ አበባ ስቴዲየም እየተሰባሰበ ይገኛል። 1ሺህ 445ኛውን የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላት እና በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓቶች በጋራ ለማክበር ህዝበ ሙስሊሙ ከማለዳው ጀምሮ ነው እየተሰባሰበ የሚገኘው።

https://www.fanabc.com/archives/249920
የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 1 ሺህ 445ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በተለያዩ ከተሞች በድምቀት መከበር ጀምሯል።

በዓሉ በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በመላ ሀገሪቱ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓቶች ነው እየተከበረ የሚገኘው፡፡

በበዓሉ አከባበር ሰላት እና ተክቢራን ጨምሮ የተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓቶች በመከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡
የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በጅማ ከተማ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 1ሺህ 445ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በጅማ ከተማ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓቶች እየተከበረ ይገኛል፡፡

የ1ሺህ 445ኛው ዓመተ ሒጅራ የዒድ ሰላት በጅማ ከተማ አዌ ፓርክ አካባቢ ሕዝበ ሙስሊሙ በተገኘበት ነው እየተከበረ የሚገኘው፡፡

በአከባበር ሥነ- ሥርዓቱ የጅማ ከተማና አካባቢዋ የሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች ተገኝተዋል፡፡

በአብዱራህማን መሃመድ እና ሙክታር ጠሃ
የአረፋ በዓል ተግባራት

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሕዝበ ሙስሊሙ ዘንድ የመስዋዕት በዓል ተብሎ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓቶች ተከብሮ ይውላል፡፡ ሐይማኖታዊ ምክንያቱም ነብዩ ኢብራሂም ፈጣሪያቸውን የመስማትና ለዚያም እስከልጅ መስዋዕት ማድረግ የደረሰን ፍቅር እንደሚያሳይ የሃይማኖት አባቶች ይናገራሉ፡፡ ነብዩ ኢብራሂም በህልማቸው አላህ ልጃቸው እስማኤልን እንዲሰው ሲጠይቃቸው በማየታቸው ፈቃዱን ለመሙላት አላንገራገሩም ይላሉ የኃይማኖቱ…

https://www.fanabc.com/archives/249926
የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 1 ሺህ 445ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በአዲስ አበባ ስታዲየም በድምቀት እየተከበረ ነው፡፡

በዓሉ ሰላት እና ተክቢራን ጨምሮ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓቶች ነው እየተከበረ የሚገኘው፡፡
የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሐዋሳ ከተማ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 1ሺህ 445ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሐዋሳ ከተማ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓቶች እየተከበረ ነው።

በበዓሉ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የሲዳማ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ፕሬዚዳንት ሼክ አብዱልሸኩር አብዱልቃድር ፥ የአረፋ በዓልን ስናከብር የተቸገሩትን በመርዳት ሊሆን ይገባል ብለዋል።

በዓሉ በሐዋሳ ከተማ ሚሊኒየም አደባባይ ህዝበ ሙስሊሙ በተገኘበት በሰላትና በበተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓቶች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል፡፡

በብርሃኑ በጋሻው
2024/11/16 03:14:59
Back to Top
HTML Embed Code: