በአቶ አደም ፋራህ የተመራ የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ ልዑክ ሩሲያ ገባ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ የተመራ ከፍተኛ ልዑክ ሩሲያ ቭላዲቮስቶክ ከተማ ገብቷል። የልዑካን ቡድኑ አባላት ሩሲያ ቭላዲቮስቶክ ከተማ የገቡት በብሪክስ ሀገራት የፖለቲካ ፓርቲዎች ዓለም አቀፍ ፎረም ላይ ለመሳተፍ ነው። ፎረሙ ከሰኔ 9 እስከ…
https://www.fanabc.com/archives/249933

የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በአሰላና ማያ ከተሞች እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 1 ሺህ 445ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በአሰላ እና ማያ ከተሞች እየተከበረ ነው፡፡
በዓሉ ሰላት እና ተክቢራን ጨምሮ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓቶች ነው እየተከበረ የሚገኘው፡፡
በሒርፖ ሽቦ እና ያሲን ሸምሰዲን

የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሐረር እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል 1ሺህ 445ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሐረር ከተማ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶች በድምቀት እየተከበረ ነው።
በክልሉ በገጠርና ከተማ ወረዳዎች የሚገኘው የእምነቱ ተከታቶች ከማለዳው ጀምሮ ሐረር በሚገኘው ኢማም አህመድ ስታድየም በመሰባሰብ በዓሉን እያከበሩ ይገኛሉ።
በአከባበር ሥነ-ሥርዓቱም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ፣ የክልሉ ም/ቤት አፈጉባዔ ሱልጣን አብዱሰላም፣ የሃይማኖት አባቶችና ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች መገኘታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በደሴና ወልድያ ከተሞች እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በደሴ እና ወልድያ ከተሞች በተለያዩ ሃይማታዊ ሥነ-ስርዓቶች እየተከበረ ይገኛል፡፡
በደሴ እና ወልድያ ከተሞች ህዝበ ሙስሊሙ በጋራ በመሰባሰብ ሰላት በመስገድ እና ሌሎች ሃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓቶችን በመከወን ነው በዓሉን እያከበረ የሚገኘው፡፡
በበዓሉ ላይ የተገኙት የደሴ ከተማ ተቀዳሚ ም/ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ ፥ ህዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር ሰላምን በማስጠበቅና በመረዳዳት ሊሆን ይገባል ብለዋል።
የደሴ ከተማ አስተዳደር እስልምና ጉዳዮች ም/ ቤት ፕሬዚዳንት ሼህ እንድሪስ በሽር በበኩላቸው ፥ ህዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከበር አንድነቱን በማስጠበቅ ሊሆን እንደሚገባ አንስተዋል።
በከድር መሃመድ