Telegram Web Link
''ተመስገን''


መላእክቱና እረኞች በአንድነት ሆነው ''በሰማያት ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን...'' ብለው ያመሰገኑትን ጌታ እኛም  እንዲሁ እሁድ ታኅሣሥ 27 ከቀኑ 6:00 በቦሌ ደ/ሳ መድኃኔዓለም ካቴድራል አዳራሽ ተሰብስበን ''ተመስገን'' በተሰኘው የዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ ቁጥር 2  የዝማሬ አልበም የተወለደውን አምላክ እናመሰግናለን::

በዕለቱም 16 መዝሙራትን የያዘው የዝማሬ አልበም ለሽያጭ ይቀርባል::


መዝሙራቱ በማኅቶት ቲዩብ የሚለቀቁ ሲሆን በሁሉም የCD Distribution  አማራጮችና  (spotify, itunes…) በተለያዩ መተግበሪያዎች ይገኛሉ::


በመላው ዓለም ለማከፋፍል በ+251941518851/ +1 469 733 0150 ይደውሉ ወይም [email protected] ይጻፉልን::


ተመስገን ተመስገን
ለምስጋና ስላሰባሰብከን
እግዚአብሔር ተመስገን
በዉስጥ የደረሰን👇

በእንደዚህ ሁኔታ በድልድይ ላይ carve የሠሩ ባለሙያዎች እና ርክክብ አርገው የወሰዱ አካላት ነው መንስኤ ስለዚህ በዬ ዓመት የሚጠፋ ነፍስ እየጨመረ ስለሆነ መንግስት ለዚህ ድልድይ ጉዳይ በአስቸኳይ መብቴ መፈለግ ያስፈልጋል 😭😭

@Sheger_press
@Sheger_press
የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ፣ ኢትዮጵያና ሱማሊያ በቱርክ አሸማጋይነት የደረሱበትን የባሕር በር ስምምነት አገራቸው በቅርበት እየተከታተለች መኾኗን መናገራቸውን የአገሪቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል።

አል ሲሲ፣ ስምምነቱ በቀጠናው ሰላምና መረጋጋት ለማስፈን ሊረዳ ይችላል ብላ ግብጽ ተስፋ እንደምታደርግ ገልጸዋል ተብሏል።

ሲሲ ይህን የተናገሩት፣ ከፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በስልክ በተወያዩበት ወቅት እንደኾነ ተገልጧል።

ግብጽ በኹለትዮሽ ትብብርም ይኹን በአፍሪካ ኅብረት የሰላም አስከባሪ ተልዕኮ በመሳተፍ፣ በሱማሊያ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ድጋፍ እንደምትሰጥ አል ሲሲ ማረጋገጣቸውንም ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
#ገዳሙን ከነረበት ችግር አላቃ ወደ ገነትነት ለውጣዋለች

ገና በትንሽ እድሜዋ ለምንኩስና ልዩ ፍቅር ያደረባት፣ የበጎ ነገር ጠላት የሆነው ጠላታችን ያደረሰባትን ፈተና ተቋቁማ ያሸነፈችው፣ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምና ቅዱስ ጊዮርጊስ ልዩ በረከት ያደሏት፣ የግብጽ ኦርቶዶክሳውያን 6ኛ ፓትርያርክ ቅዱስ ቄርሎስ ታላቅ እመምኔት እንደምትሆን ገና በመጀመሪያ የምንኩስና ዘመኗ የተበዩላት ድንቅ ገዳማዊት ናት፡፡ በርካቶች ስለ ቅዱሳን ጻድቃን እናቶች የሚነገረውን ገድልና ተአምራት ለመንቀፍ ከሚሞክሩበት ምክንያት አንዱ ከምዕተ ዓመታት በፊት የነበሩ፣ ታሪኮች ናቸው የሚል ነው፡፡ ይሁንና በአውሮፓውያኑ 1999 ጥቅምት 21 ቀን ያረፈችው እማሆይ ጣማፍ ኡምና ኤሬን (ሔራኒ) በዘመናችንም ቅድስና እንዳለ ያሳየች ድንቅ ገዳማዊት ናት፡፡

ግብጽ ጊጋር በተባለ ስፍራ የተወለደችው ቅድስት የልደት ስሟ ፋውዚያ ነበር፡፡ በስጋዊው ዘመናዊ ትምህርት ቤት የተማረች፣ በመኪናና በአውሮፕላን የተጓዘች፣ አብረዋት የተማሩና የሚያውቋት ሰዎች አሁን ድረስ በሕይወት ያሉና የሚመሰክሩላት፤ በመንፈሳዊው ደግሞ ገና በትንሽነቷ ምንኩስናን የመረጠች፣ በግብጻውያን “አቡ ሰይፈን” የሚባለው የሰማዕቱ ቅዱስ መርቆሬዎች የሴቶች ገዳም እመ ምኔት የነበረች፣ የሰራቻቸው አስደናቂ ተአምራቶች በአል-አህራም ጋዜጣ ሳይቀር ታትሞ የወጣላት፣ እግዚአብሔር በሰጣት ጸጋ እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት በቅጽበት ከአንዱ ስፍራ ወደ ሌላው የምትጓዝ ነበረች፡፡ የቅዱስ መርቆሬዎስ ገዳምን እስከ ዕለተ ሞቷ በእመ ምኔትነት በመራችበት ወቅት በችግር ውስጥ የነበረውን ገዳም በርካታ ልማት ወደ ሚሰራበት ስፍራም ቀይራዋለች፡፡

በረከቷን ሽተው የሚመጡ ክርስቲኖች በሚያደርጉት ድጋፍ ገዳሙን ከነበረበት ችግር አላቃ የበረሃው ገነት፣ ትልቅ የቅድስና ስፍራ አድርጋው ነው ያረፈችው፡፡ የግብጹ አልአህራም ጋዜጣ ይዟቸው ከወጣ ተአምራቶቿ አንዱ “አጊባ” ወደ ተባለ አካባቢ በአውሮፕላን ስትጓዝ፣ የተፈጠረውን ብልሽት ተከትሎ ሙሉ መንገደኞች ሊያልቁ የነበረበትና በአፍንጫው ከተከሰከሰው አውሮፕላን አንድም ሰው ሳይጎዳ በጸሎቷ ያዳነችበት፣ በዘመናችንም የቅዱሳን ጸሎት በስራዋ ኃይል እደምታደርግ ያሳየ ነው፡፡ ገዳማውያንን ማሰብ እጅግ ማትረፊያና የበረከታቸው ተሳታፊ መሆኑን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የምትነግረንም ይህንን መሰረት አድርጋ ነው፡፡

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምስራቅ በለሳ ወረዳ የሚገኘው ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም ከዘጠና በላይ ገዳማውያን መነኮሳት ያሉበት ልዩ ስፍራ ነው፡፡ ከዓለት መሀል በመነኮሳት ፀሎት ብቻ በሚቆረጥ የማር እምነትና ድውያንን የሚፈውስ ድንቅ ጸበል ያለበት፤ ስለ ዓለምና ስለ ሀገራችን ሌት ተቀን የሚጸልዩበት ቅዱስ ስፍራ ነው፡፡ በተደጋጋሚ ባደረግነው ጥሪ መሠረትም የዘረጋችሁት እጃችሁ ድንቅ ነገር ሰርቷል፡፡ የሴቶች ገዳማውያን መኖሪያ ባማረና በዘመነ ሁኔታ ተሰርቶ፣ የሶላር ኃይል ተገጥሞለት ጭምር ተጠናቋል፡፡ ለዚህም ባወጣችሁት አብዝቶ ይተካ፣ በዘረጋችሁት እጅ ማለቂያ የሌለው በረከት ያሳፍሳችሁ ለማለት እንወዳለን፡፡ አሁንም ይህ ልግስናችሁ ተጠናክሮ ይቀጥል፡፡ አንድ ትልቅ ምዕራፍ ብንጓዝም ለመስራት ከታሰበው ግማሽ ያህል እንኳ አልተጠናቀቀምና ገዳማውያኑ ልገሳችሁን ይሻሉ፡፡ አካባቢውን የበረሃ ገነት የማድረግ እድል አለንና እንጠቀምበት፡፡              

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
በኢትዮጵያ ሁለት ሚሊዮን ዜጎች በዝሆኔ በሽታ የመያዝ ስጋት ተደቅኖባቸዋል ተባለ

በኢትዮጵያ በርካታ ዜጎች  ትኩረት ለሚሹ ሀሩራማ በሽታዎች የተጋለጡ ናቸው ሲል የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡በሚኒስቴሩ ትኩረት የሚሹ ሀሩራማ በሽታዎች ቡድን መሪ አቶ ተስፋሁን ቢሻዉ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት በኢትዮጵያ 13  ትኩረት የሚሹ ሀሩራማ በሽታዎች የተመዘገቡ ሲሆን በዋናነት በአስሮቹ ላይ ትግበራ እየተደረገ ይገኛል።

የሀሩራማ በሽታዎችን ለማጥፋት፣ ለመቆጣጠርና ለመከላከል በተለይ በውሃ አቅርቦትና ንፅህና አጠባበቅ ላይ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባም ተጠቁሟል፡፡አቶ ተስፋሁን አክለውም ትኩረት የሚሹ ሀሩራማ በሽታዎች ከሚባሉት መካከል አንዱ ዝሆኔ መሆኑን ገልፀዉ በአሁኑ ወቅት 2 ሚሊዮን ዜጎች በበሽታዉ የመያዝ ስጋት ተደቅኖባቸዋል ብለዋል።የዝሆኔ በሽታ በወባ ትንኝ አማካኝነት የሚተላለፍ ፣ እግርና ሌሎች የሰውነት ክፍሎችን የሚያሳብጥ እንዲሁም ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍ በሽታ መሆኑን ገልፀዋል።

በደቡብ፣ኦሮሚያ፣ጋምቤላ፣ቤኒሻንጉል እና አማራ ክልሎች ላይ  የበሽታዉ ስርጭት ከፍተኛ እንደሆነ የገለፁት ቡድን መሪዉ በትግራይ ጭምር በተወሰኑ ወረዳዎች ላይ በሽታው ይስተዋላል ብለዋል።በሽታው ጾታ የማይለይ እና አስከፊ የጤና ችግርን የሚያስከትል ነው ያሉት አቶ ተስፋሁን በወንዶች ላይ የማህደረ ቆለጥ እብጠትን ሊያስከትል ይችላል።ህመሙ ሲጀምር በሴቶች ላይ እንዲሁ የጡት እብጠትን ሊያስከትል ይችላል በማለት የገለፁ ሲሆን እየቆየ ሲሄድ የእግር ቅርፅ እየተቀየረ የመምጣትና ከፍተኛ የጤና ችግርን ያስከትላል ሲሉ አስረድተዋል።

ሰዎች የበሽታውን ምልክትን ሲያዩ ፈጥነዉ ወደ ሀኪም ዘንድ ቀርበው ተገቢውን ህክምና ማድረግ እንደሚኖርባቸዉ አቶ ተስፋሁን ተናግረዋል።የዝሆኔ በሽታን ለመከላከል የትንኝ መራቢያ ቦታዎችን የማጥፋት፣ ህብረተሰቡን የማስተማር፣ የማከምና የመድሐኒት እደላ ስራዎች እንደሚከናወኑ ጨምረው ለጣቢያችን ገልጸዋል፡፡

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
በሲዳማ ክልል ሰርገኞች ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ ከ50 በላይ የሚሆኑት ተጎጂዎች የአንድ ቤተሰብ አባላት እንደሆኑ ተነገረ

በሲዳማ ክልል ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ሰርገኞች ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ ሕይወታቸው ካለፈ 71 ሰዎች ውስጥ ከ50 በላይ የሚሆኑት የአንድ ቤተሰብ አባላት እና ዘመዳሞች መሆናቸው ተነግሯል።

አደጋው የደረሰው በዞኑ ቦና ዙሪያ ወረዳ ትናንት ዕሁድ ታኅሳስ 20 ሲሆን ሰርገኞቹ ወራንቻ ወደ ተባለ አካባቢ ሲጓዙ ጋለና ወንዝ ድልድይ ላይ ተሽከርካሪው መስመር በመሳት ወደ ወንዙ መግባቱን የአካባቢው ባለስልጣናት ተናግረዋል።

በአደጋው ሙሽራውን ጨምሮ የ71 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የተናገሩት ኃላፊው፤ አስከሬን እስከ ሌሊቱ 9፡00 ድረስ እንደተነሳ ተናግረዋል።

የአካባቢው ማኅበረሰብ ትብብር 73 የአደጋው ተጎጂዎች ወደ ቦና አጠቃላይ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ለማ ለጊዴ ገልጸዋል።

በአስከሬን ምርመራ በአደጋው 66 ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉን እንዳረጋገጡ ሜዲካል ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

ከሟቾቹ ውስጥ ሙሽራውን ጨምሮ 61 ወንዶች እና አራቱ ሴቶች መሆናቸውን ጠቁመዋል።

ሰባት ሰዎች ቆስለው ህክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝ የተናገሩት ዶ/ር ለማ አምስቱ ተጊጂዎች መጠነኛ ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑን ተናግረዋል።

ሁለቱ ተጎጂዎች ደግሞ የዳሌ፣ የእጅ እና እግር ስብራት እንዳጋጠማቸው ገልፀው፤ ወደ ሀዋሳ ለሪፈር ህክምና መወሰዳቸውንም አክለው ተናግረዋል።

ከ50 በላይ የሚሆኑት ሟቾች የሚሪዴ ቀበሌ ነዋሪዎች የሆኑ የአንድ ቤተሰብ አባላት እና ዘመዳሞች መሆናቸውን ምክትል ኢንስፔክተር ሹመቴ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

አንድ ቤተሰብ አባለትን ጨምሮ ሰርጉን ለማጀብ የወጡ ጎረቤቶችም የአደጋው ተጎጅዎች እንደሆኑ ገልጸዋል።

"አብዛኞቹ ወጣቶች ናቸው" ሲሉ ስለ ተጎጂዎች ማንነት የተናገሩት የቦና አጠቃላይ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር፤ ተጎጂዎቹ ከ15 ዓመት እስከ 30 ዓመት የሚሆኑ ወጣቶች መሆናቸውን ገልጸዋል።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
ጥቆማ‼️

በሀገራችን እዉቅ ጋዜጠኞች የተመሰረተና የመረጃ አነፍናፊና አዲሱ tikvah የተባለለት የቴሌግራም ቻናል እናስተዋዉቃችሁ

እውነተኛ መረጃ ከፈለጋቹ በፍጥነት ይህን ቻናል መቀላቀል ይኖርባችኋል።

በዚ LINK ግቡ👇
👇👇👇
https://www.tg-me.com/+gPveFwjiiXdiMDE0
https://www.tg-me.com/+gPveFwjiiXdiMDE0
ወጣትነቷን በሙሉ ለበጎ ስራ ያዋለችዋ ወ/ሮ ሙዳይ ተሸለመች

ለበርካታ አመታት በርካታ ህጻናትን እየረዳችና እያሥተማረች እንዲሁም ስራ ለሌላቸው እናቶች የስራ እድልን እየፈጠረች እና እያገዘች የቆየችዋ ይህን በጎ ተግባሯን አሁንም በርካቶችን በማቀፍ አየቀጠለች የምትገኛዋ የወጣትነት ዘመኗን በመልካም ስራ ስታሳልፍ የቆየችዋ የድሆች እህትና እናት የሆነችዋ የሙዳይ በጎ አድራጎት መሥራች የሆነችው ወይዘሮ ሙዳይ ምትኩ ታላቅ ሽልማት እና እውቅና ተሰጣት።

ሁሌ በእየ አመቱ ለሀገር ጥሩ የሠሩና በጎ የሰሩ ሴት እህቶቻችንን በመሸለም እና እውቅና በመሥጠት የሚታወቀው እንቁ ኤቨንት በትላንትናው ዕለት በአዲስ አበባ ባካሄደው "እንቁ ሴት, ንቁ ሴት, ጠንካራ ሴት" በተሰኜው 6ኛው ዙር የሽልማት ስነ ስርአቱ ከሸለማቸው ጠንካራ እና ንቁ ኢትዮጵያውያን ሴቶች መካከል ሙዳይ ምትኩ አንዷ ሆናለች።

ወይዘሮ ሙዳይ ይህን ሽልማት የሸለሟትን አዘጋጆች ካመሠገነች በኋላ መላ ኢትዮጵያውያን ድርጅታችን በአሁን ሰአት ካለው የኑሮ ውድነት አንጻር በርካታ በልተው የማያድሩ ህጻኖችና እናቶች እየበዙብን ስለሆነ እና የቤት ኪራያችንን ጨምሮ በርካታ ወጪዎች ስላሉብን ሁሌም ከጎናችን የማይለየው የኢትዮጵያ ህዝብ አሁንም ከጎናችን ይሆን ዘንድ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ ብላለች።

ከእዚህ ጋር ተያይዞም ሁሌ በእየአመቱ እንደምናደርገው ሁሉ የገናን በአል ምክንያት በማድረግ ለአንድ ልጅ አንድ እንቁላል እንድታግዙን በማለት መልዕክቷን አስተላልፋለች።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
🔴 በአዲስ አበባ አቆጣጠር ከሌሊቱ 7:13 (01:13 am)፣ በአፋር ክልል አዋሽ አካባቢ ከሰሞኑ ከደረሱት የመሬት መንቀጥቀጥ ክሰተቶች በመጠኑ ከፍተኛ የሆነ መንቀጥቀት ተከሰተ።

በአካባቢው ሌሊት 7:ሰዓት ከ13 ላይ የደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ፤ በሬክተር ስኬል 5.2 የደረሰ እንደሆነ የጀርመን የጂኦሳይንስ የምርምር ማዕከል (The German Research Centre for Geosciences | GFZ) አስታውቋል።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለው የሰሞኑ የመሬት መንቀጥቀጥ 47 ቤቶችን ሲያፈርስ ከ2,500 በላይ አባዋራ አፈናቅሏል ተባለ።

ታህሳስ 21/2017 ዓ.ም ለሊቱን ከእስከ ዛሬው ከፍተኛ የተባለ(5.2 በሬክተር ስኬል) ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል።

የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት የተሰማባቸው ሰዓታት
4:30 5:29 5:33 5:58
6:22 7:13 9:02 ናቸው።

ይህ የመሬት መንቀጥቀጥ መነሻው አፋር ክልል ሲሆን በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ በሰው ህይወት ላይ የደረሰ አደጋ ባይኖርም በገቢ ረሱ ዞን 47 መኖሪያ ቤቶችን ላይ ጉዳት ማድረሱ ታውቋል።30ዎቹ ቤቶት ከትናንት በፊት ሲሆን 17ቱ ትናንት ምሽት ጉዳት ደርሶባቸው አጠቃላይ ከ2500 በላይ አባዎራ ተፈናቅሏል።

የመሬት መንቀጥቀጡ በአዋሽ አካባቢ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን እያፈናቀለ በሚገኝበት ወቅት ፣በርካታ ህንፃዎች፣ የመኖርያ ቤቶች እና መንገድ ጭምር እየተሰነጣጠቀ ባለበት ሰዓት፣አዳዲስ እሳት ገሞራ እየተፈጠረ(ፈንታሌ) ባለበት ሰዓት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሴስሞሎጂ ትምህርት ክፍል ኃላፊ ፕ/ር አታላይ አየለ ከሰሞኑ ህዝቡን እየረበሸ እና እያሳሰበ በሚገኘው የመሬት መንቀጥቀጥ ዙርያ ለቲክቫህ በሰጡት አስተያየት "መሬት በራሷ ጉዞ እየሄደች የምታስተነፍሰው ሃይል ነው ምንም የሚያስደንቅ ነገር አይደለም ቦታውም፣ በምን ያህል ርቀት ላይ እንደሆነ ይታወቃል በተለይ አዲስ አበባ ያለ ሰው ምንም ሊደነግጥ አይገባም" የሚል አስገራሚ ምላሽ ሰጥተው ተመልክተናል።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
''ተመስገን''

መላእክቱና እረኞች በአንድነት ሆነው ''በሰማያት ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን...'' ብለው ያመሰገኑትን ጌታ እኛም  እንዲሁ እሁድ ታኅሣሥ 27 ከቀኑ 6:00 በቦሌ ደ/ሳ መድኃኔዓለም ካቴድራል አዳራሽ ተሰብስበን ''ተመስገን'' በተሰኘው የዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ ቁጥር 2  የዝማሬ አልበም የተወለደውን አምላክ እናመሰግናለን::

በዕለቱም 16 መዝሙራትን የያዘው የዝማሬ አልበም ለሽያጭ ይቀርባል::


መዝሙራቱ በማኅቶት ቲዩብ የሚለቀቁ ሲሆን በሁሉም የCD Distribution  አማራጮችና  (spotify, itunes…) በተለያዩ መተግበሪያዎች ይገኛሉ::


በመላው ዓለም ለማከፋፍል በ+251941518851/ +1 469 733 0150 ይደውሉ ወይም [email protected] ይጻፉልን::


ተመስገን ተመስገን
ለምስጋና ስላሰባሰብከን
እግዚአብሔር ተመስገን
ዜና፡ በ #ቡግና እና #ላስታ ወረዳዎች “በታጣቂዎች በተጣለ ገደብ” 77 ሺህ ሰዎች ላይ ሰብዓዊ ቀውስ እንዲባባስ ማስቻሉን ሪፖርት አመላከተ

#አማራ ክልል ሰሜን ወሎ በቡግና እና ላስታ ወረዳ “በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ” በተጠሉ ገደቦች ምክንያት ቀድሞውኑ አስከፊ የሆነውን የሰብአዊ ሁኔታ በማማባስ 10 ሺህ ተፈናቃዮችን ጨምሮ 77 ሺህ ሰዎች ላይ ተጽዕኖ ማድረሱን የአውሮፓ ሲቪል ጥበቃ እና የሰብአዊ እርዳታ ኦፕሬሽንስ (ECHO) ባወጣው ሪፖርት አስታወቀ።

ሪፖርቱ “የቴሌኮሙኒኬሽን እና ባንክ አገልግሎቶች ስራ ላይ አለመሆናቸውንና የመንግስት መዋቅሮችም ለሶስት ወራት በስፍራው እንዳልነበሩ” ገልጿል።

79 በመቶ የሚሆኑ ነፍሰ ጡር እና የሚያጠቡ ሴቶች እንዲሁም 70 በመቶ የሚሆኑ ሕፃናት ከፍተኛ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት እንዳለባቸው የገለጸው ሪፖርቱ ከዚህ ውስጥ 9 ነጥብ 2 በመቶ የሚሆኑት ህጻናት ደግሞ እጅግ ከባድ የሆነ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት አለባቸው ገልጿል።
2025/01/08 21:53:24
Back to Top
HTML Embed Code: