ኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊ ጉዞ ወደ ቅዱስ ላሊበላ!
በነፍሳችን ዲያብሎስ ፣ በስጋችን ቄሳር እንዳይነግስ፣ ያለወንድ ዘር በረቂቅ ሚስጥር ከብጽዕት ማርያም የተወለደውን ወልድ እግዚአብሔርን ኑ በምስጋና እናንግሰው።
ንጉሧን ያላወቀች እስራኤል ከምድር ያሳደደችው ፣ በመስቀል ሆኖ "ንጉሥ" የተባለ ፣ በመላእክት የተበሰረ ዜና ልደቱን፣ በያሬዳዊ ዝማሬ በታሪካዊው ቅዱስ ላሊበላ በማክበር በረከተ ነፍስ በረከተ ስጋን እናትርፍ።
ለአረጋውያን ፣ ለነፍሰጡር ፣ ለህፃናት እና ለአካል ጉዳተኞች በጤና ባለሙያዎች ልዩ እንክባቤ እንሰጣለን። ስለማረፊያዎ አያስቡ፤ያሉን ቦታዎች ውስን ናቸውና ፈጥነው በመመዝገብ ቦታ ይያዙ።
የጉዞ መነሻ ቀን:- 24/04/17
የጉዞ መመለሻ ቀን:- 02/05/17
የጉዞ ዋጋ:- ምግብን ፣ ማረፊያን ፣ መስተንግዶን እና አስጎብኚን ጨምሮ :-6,500
ለበለጠ መረጃ:-0938944444
አዘጋጅ:- ማኀበረ ቁስቋም

የደቡብ ኮሪያ ገዢው ፓርቲ መሪ የፕሬዝዳንት ዮን ስልጣን እንዲታገድ ጠየቀ
የደቡብ ኮሪያ ገዥ ፓርቲ መሪ የፕሬዚዳንት ዩን ሱክ-ዮል ስልጣን በፍጥነት እንዲታገድ የጠየቁ ሲሆን ፕሬዝዳንቱ የማርሻል ህግን ማወጃቸውን ተከትሎ የፖለቲካ መሪዎችን ለማሰር እንደፈለጉ "ተአማኒ ማስረጃ" አለ ብለዋል።
ቀደም ሲል ዮንን ለመክሰስ የሚደረገውን ጥረት እንደሚቃወሙ የገለፁት የፒፕል ፓወር ፓርቲ መሪ ሃን ዶንግ-ሁን “አዲስ እየወጡ ባሉ መረጃዎች ግን በፕሬዚዳንቱ ላይ ከፍተኛ ተቃውሞን እያሳዩ ይገኛል። ፕሬዚዳንቱ የመከላከያ ኢንተለጀንስ አዛዥ ዋና ዋና የፖለቲካ መሪዎችን እንዲይዝ ፀረ-መንግስት ሃይሎች እንደሆኑ በመግለጽ እና የስለላ ተቋማትን በሂደቱ እንዲያንቀሳቅስ እንዳዘዙ ተረድቻለሁ ሲሉ ሃን ተናግረዋል። ሃን አክለውም “ይህች አገር ወደ ሌላ ትርምስ እንዳትገባ ለመከላከል፣ የክስ መቃወሚያ ሂደት እንዳይቋሩጥ ለማድረግ እሞክራለሁ ሲሉ ተናግረዋል። ደቡብ ኮሪያን እና ህዝቦቻችንን ለመጠበቅ ፕሬዝዳንት ዩን እንደ ፕሬዝደንት ስልጣናቸውን በፍጥነት እንዳይጠቀሙ ማስቆም አስፈላጊ ነው ብዬ አምናለሁ ብለዋል።
ሃን ፕሬዝዳንት ዩን የማርሻል ህግ መግለጫው ህገወጥ እና ስህተት መሆኑን አምነው መቀበል አልቻሉም ሲሉ አክለዋል። በስልጣን ላይ ከዚህ በላይ ከቆዩ እንደገና ተመሳሳይ ጽንፍ ያለው እርምጃ ሊወስዲ ይችላል የሚል ትልቅ ስጋት አለኝ ሲሉ አክለዋል።ደቡብ ኮሪያ ማክሰኞ ምሽት ላይ ለስድስት ሰአታት ያህል በማርሻል ወይም ወታደራዊ ህግ ስር ወድቃ የነበረች ሲሆን ፕሬዝዳንት ዮን እርምጃው መተግበሩን ለህዝቡ ያሳወቁት በድንገተኛ በቴሌቭዥን ላይ ቀርበው ነው።ለእርምጃው ምክንያት ሲሉ የገለፁት ከ"ፀረ-መንግስት ኃይሎች እና ከሰሜን ኮሪያ ደጋፊዎች የሚሰነዘሩ ዛቻዎችን ጠቅሰዋል። የብሄራዊ ምክር ቤቱ የዩኑን ትዕዛዝ በ190 ተቃውሞ ያለ አንዳች ድጋፉ በፍጥነት ውሳኔው እንዲሻር አድርገዋል።
ዩን በአሁኑ ወቅት ከስልጣን ከተነሱት የመከላከያ ሚኒስትር ኪም ዮንግ-ህዩን ፣የጦር ኃይሎች አዛዥ ጄኔራል ፓርክ አንሱ እና የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ሊ ሳንግ ሚን ጋር በመሆን በሀገር ክህደት ወንጀል ምርመራ እየተካሄደባቸው እንደሚገኝ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።የፍትህ ሚኒስትር የሆኑት እና በገዢው ፒ.ፒ.ፒ. ውስጥ የፕሬዝዳንት ዮን ከፍተኛ ተቀናቃኝ አንዱ የሆኑት ሃን ተቃውሞ ገዥው ፓርቲ ለችግሩ የሚሰጠውን ወሳኝ ምላሽ ለውጥ ያሳያል ተብሏል። ተቃዋሚው ዴሞክራቲክ ፓርቲ ፕሬዝዳንት ዮንን ለመክሰስ ቅዳሜ ምሽት ድምጽ እንዲሰጥ ጠይቋል።
ነገር ግን 300 አባላት ባለው የብሄራዊ ምክር ቤት ውስጥ አስፈላጊውን ሁለት ሶስተኛ ደረጃ ላይ ለመድረስ ከገዥው ፓርቲ ቢያንስ ስምንት ድምጽ ያስፈልገዋል።አቤቱታው ከተሳካ፣የደቡብ ኮሪያ ሕገ-መንግሥታዊ ፍርድ ቤት ዮንን ከስልጣን እንዲወገዱ ውሳኔ ይሰጣል።እ.ኤ.አ. በ2016 የቀድሞ ፕሬዚደንት ፓርክ ጊዩን ሃይ ከስልጣን መነሳቷን ተከትሎ እንደተከሰችው አሁን ላይ ገዢው ፒፒፒ ፓርቲ የዮንን መከሰስ እንደሚቃወም አንዳንድ ተንታኞች ጠቁመዋል።ፓርክ ባምህረት ከመለቀቋ በፊት በሙስና ወንጀል የ20 አመት እስራት ተፈርዶባት እንደነበር ይታወሳል።ዩን ሳይጨምር፣ በ1980ዎቹ መገባደጃ ላይ ሀገሪቱ ወደ ዲሞክራሲ ከተሸጋገረችበት ጊዜ አንስቶ ከነበሩት ሰባት ፕሬዚዳንቶች አራቱ በሙስና ተከሰው ወይም በሙስና ተጠርጥረው ታስረዋል።

መረጃ‼️
የአዲስአበባ እግርኳስ ፌደሬሽን ዛሬ ከሰዓት በኋላ አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቷል።
የፌደሬሽኑ ም/ፕሬዝዳንት በመሆን ትናንት የተመረጠችው አርቲስት ማስተዋል ወንዶሰን
የመልቀቂያ ደብዳቤ እንደምታስገባ የሚጠበቅ ሲሆን
በምትኳም የፕሪምየር ሊጉ አክሲዮን ማህበር አመራር የሆኑት ዶ/ር ወገኔ ዋልተንጉስ እንደሚተኩ ይጠበቃል።
Via ዳጉ ጆርናል
@Sheger_press

ምክትል ፕሬዝዳንቷ በኃላፊነታቸው ይቀጥላሉ !!
የኣዲስ ኣበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን ለዛሬ የጠራው ስብሰባ ኣዲስ የተመረጠው ስራ ኣስፈፃሚ ለትውውቅ የጠራው እንጂ ምንም ሹም ሽር ሀላፊነት መልቀቅ ምናምን የለውም ፤ ትናንት የተመረጡት ይቀጥላሉ በሀረገወይን ቦታ ብቻ ሰው ሊተካ ይችላል።
[ኤርምያስ በላይነህ]
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news

''ከባለሀብቶችና ኤምባሲዎች ጋር በመነጋገር ገቢ አመጣለው''
ተዋናይነት ማስተዋል
አዲሷ የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት ማስተዋል ወንደሰን ከምርጫው በኋላ ለአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ጋዜጠኛ ዮናስ ሞላ ሀሳቧን ሰጥታለች።
በጣም ደስ ብሎኛል አልጠበኩም ነበር ያለችው ተዋናይነት ማስተዋል አዲስ አበባ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መስራች እንደመሆኗ አሁን ያለችበት ሁኔታ ደስ አይልም ብላለች።
ዋና ከተማ ላይ በርካታ ኤምባሲዎች አሉ እኔ ከነሱና ባለሀብቶች ጋር በመነጋገር ጥሩ ገቢ በመነጋገር ለማምጣት እጥራለው ስትል ተደምጣለች።
በአለም ላይ ከ4 ቢሊዮን በላይ ተከታታይ ያለው የስፖርት አይነት በመሆኑ ሁሉም ይደግፈኛል ሁላችንም ይወክላል ፣ሴቶችንም እናበረታታለን ይደግፉናል ስትል ከምርጫው በኋላ አስተያየት ሰጥታለች።

#እስከ ሞት ያስጨከነው ደብዳቤ
በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን በቀድሞዋ ፋርስ በአሁኗ ኢራን በቀድሞዋ ፋርስ በአንድ ወገን እጅግ ጠንካራ ክርስቲያኖች፣ በሌላ ወገን ደግሞ ጣዖት የሚያመልኩ እጅግ ጨካኝ ነገስታት ነበሩባት፡፡
በርካታ ክርስቲያኖችም ክርስቶስን አንክድም፣ ለጣኦት አንሰግድም በማለት በሰማዕትነት አርፈውባታል፡፡ ከእነዚህ አንዱ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከዓበይት ሰማዕታት ወገን የሚቆጠረው ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ ነው፡፡ በዘመኑ ከነበረው ንጉስ ሠክራድ ጋር እጅግ ይዋደዱ ነበር፡፡ ይሁንና ቅዱስ ያዕቆብ ከክርስቲያን ቤተሰቦች የተወለደ በትምህርተ ሃይማኖት ያደገ፣ በክርስትና ስርዓት ሚስት አግብቶ የሚኖር ፍጹም ክርስቲያን ነበር፡፡
ንጉሱም ከፍቅሩ ብዛት የተነሳ በቤተ መንግስት ሹመት ሰጥቶ ከእርሱ ጋር እንዲኖር አደረገው፡፡
ቅዱስ ያዕቆብም በቤተ መንግስቱ ያለው የስጋው ምቾት መንፈሳዊ ሕይወቱን እያስረሳው ከጾምና ከጸሎት አራቀው፡፡ በሒደትም ንጉሱ ያለውን ሁሉ እንደ ክርስቲያን ሳይመዝን ይሁን እሺ የሚልና ተግቶ የሚፈጽምም ሆነ፡፡
ነገሮች ከልክ ማለፍ ጀመሩ፡፡ ንጉሱ ሠክራድ “እኔ እኔ ለማመልካቸው ለእሳትና ለፀሐይ ስገድ አምልካቸውም” አለው፡፡ እርሱም በተለመደ እሺታው ሊያስደስተው ፈልጎ ሰገደ፤ ማምለክም ጀመረ፡፡ በስጋችን ምቾት፣ በወንድማዊነት ፍቅር ሰበብ፣ ሃይማኖት ከምግባር መግባ ያሳደገችንን ቅድስት ቤተክርስቲያን የተውን “በክፉ ባልንጀርነት መልካሙን አመላችንን ያጠፋን ስንቶች ነን? ለክብር ያበቃችንን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ያናነናቅንስ? ገዳማትን የረሳን፣ ትጋታችንን የተውን፣ ለባልንጀሮቻችን ፍቅር የክርስቶስን ፍቅር የተውን፣ ከቅዳሴው ይልቅ ሌላ ድምጽ እየሰማን ያለን ራሳችንን እንመርምር፡፡
ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስ፡፡ ቅዱስ ያዕቆብ ያደረገውን ነገር በዘመኑ የነበሩ ክርስቲያኖች ሰምተው እጅግ አዘኑ፡፡ እህቱ ሚስቱና እናቱ ግን ለሐዘናቸው ዳርቻ አልተገኘለትም፡፡
በእንባና በለቅሶም ደብዳቤ ጻፉለት፡፡ "አንተ ክርስትናህን መካድህን ሰምተን አዘንን:: በዚህም ምክንያት ከዚህ በሁዋላ በአካባቢህ መኖርን አንፈልግም:: ለሞተልህ ለክርስቶስ ካልታመንህ እኛ አንተን እንደ ወንድም፣ እንደ ባልና እንደ ልጅ ልናምንህ ይከብደናል::" ይላል ደብዳቤው፡፡ እዳሉትም ከአካባቢው ለቀቁ፡፡
ቅዱስ ያዕቆብ ደብዳቤውን ሲያነበው ደነገጠ፤ በምድር ያሉት ብቸኛ የስጋ ዘመዶቹ እንርሱ ናቸውና፡፡
ከንጉሱ ጋር በነበረው ያልተገባ አካሔድ የደም ዋጋ ከፍሎ ያዳነውን ጌታ መካዱ ሲገባውም "ጌታ ሆይ! በምድር ካሉ የሥጋ ዘመዶቼ መለየት እንዲህ ካሸበረኝ: ካንተ ፍቅር መለየትማ እንደ ምን ይጨንቅ ይሆን! በሰማያዊ ዙፋንህ ፊትስ እንዴት ብዬ እቆማለሁ!" ብሎ መሪር እንባ አለቀሰ፡፡
ሌሊቱን ሙሉ በእንባና በለቅሶ አሳልፎ በጠዋት ንስሐ ገባ፡፡ በጾምና ጸሎት ጸንቶ ከንጉሱ አደባባይ ራቀ፡፡ ንጉስ ሠክራድም አስጠርቶ "ምን ሆነሃል? ስለ ምንስ በአምልኮ ከእኔ ተለየህ?" ሲል ጠየቀው፡፡ ቅዱስ ያዕቆብም "የፈጠረኝን ክርስቶስን ትቼ አንተን በባዕድ አምልኮ አስደስትህ ዘንድ የሚገባ አይደለም" ሲል መለሰለት፡፡
ንጉሱ ሊያባብለው ሞከረ እንደማይሆን ሲገባው በደም እስኪነከር አስደበደበው፡፡ በክርስቶስ ፍቅር እንደጸና ሲገባውም ከጣቶቹ ጀምሮ አካሉን እንዲቆራርጡት ነገር ግን ቶሎ እንዳይገድሉት ወሰነ፡፡ ሰውነቱ ሲቆራረጥ መከራው ሲጸናበት እርሱ ግን ያመሰግን ነበር፡፡
በመጨረሻም ከወገቡ በላይ ያለ አካሉና ራሱ ብቻ ነበር የቀረው፡፡ ይሕም ሆኖ ይጸልይ ያመሰግን ነበር፡፡ 42 ቦታ የተቆራረጠው ሰውነቱን ረስቶ በቀረው አካሉ ያመሰግን ነበር፡፡
በመጨረሻም አንገቱን በሰይፍ መተው ገድለውታል፡፡ እስከ ሞት ያስጨከነውን ደብዳቤ የጻፉለት እናቱ፣ እህቱና ሚስቱ በሰማዕትነት በማለፉ በደስታ እየዘመሩና በስጋ ስለተለያቸው እያለቀሱ ሽቱ ቀብተው ቀብረውታል፡፡
ሰማዕታት የዚህ ዓለምን ክብር ንቀው አንገታቸውን ለሰይፍ እንደሰጡ፣ ገዳማውያን አባቶችና እናቶች የዓለምን ጣዕም ንቀው በበረሀ ወድቀዋልና በአታቸውን እናጽና ገዳማቸውን እናግዝ፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

ቱርክ፣ ኢራን እና ሩሲያ በሶሪያ ጉዳይ በዶሃ ሊወያዩ መሆኑ ተገለጸ።
የቱርክ፣ የኢራን እና የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ፈጣን በሆነው የሶሪያ አማጺያን ግስጋሴ ጉዳይ በነገው እለት በኳታር ዶሃ ተገናኝተው እንደሚወያዩ ሮይተርስ ዘግቧል።
አማጺያኑ የሶሪያ የእርስበርስ ጦርነት ከተጀመረ ከ13 አመታት በኋላ በጦር ሜዳ ከፍተኛ ድል በመጎናጸፍ፣ በበሽር አላሳድ አገዛዝ ላይ ከፍተኛ ኪሳራ አድርሰዋል።
ለበርካታ አመታት በሀገሪቱ ሰሜን ምዕራብ ክፍል ለበርካታ አመታት መሽገው የነበሩት አማጺያኑ በሀያት ታህሪር አል ሻም በተባለው ቡድን በመመራት ባለፈው ሳምንት የሶሪያን ትልቅ ከተማ አሌፖን ተቆጣጥረው፤ በደቡብ በኩል ወደ ሀማ ከተማ መግፋት ችለው ነበር።
አማጺያኑ በትናንትናው እለት ደግሞ ሁለተኛዋን ትልቅ ከተማ ሀማን ተቆጣጥረዋል።
ቱርክ፣ ሩሲያ እና ኢራን 'አስታና ፒስ ፕሮሰስ' በተባለ ማዕቀፍ በሶሪያ የወደፊት እጣፊንታ ላይ የሶስትዮሽ ምክክር ያደርጋሉ።
የኔቶ አባሏ ቱርክ ተቃዋሚዎችን የምትደግፍ ሲሆን ሩሲያ እና ኢራን ደግሞ የአሳድ አገዛዝን እንደሚደግፉ ይገለጻል።
ሮይተርስ ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው ከሆነ ሶስት ሚኒስትሮች ከዶሃ ፎረም ጎንለጎን በነገው እለት ይገናኛሉ።

ከሰሞኑ የሰማነው የተወሰኑ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (መንግስት ኦነግ ሸኔ የሚለው) አባላት ሰላም መምረጥ ተስፋ ይሰጣል
አካሄዱ ላይ ግን ጥንቃቄ ካልተደረገበት ውጤቱ ከታሰበው በተቃራኒ እንዳይሆን ያሰጋል።
ዛሬ ጠዋት ስልኬን ስከፍት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ልብስን የለበሱት ጃል ሰኚ ነጋሳ መግለጫ ሲሰጡ ተመለከትኩ። "በምን አግባብ?" የሚለው ትልቁ ጥያቄዬ ነበር፣ ምክንያቱም የሰራዊቱ አባል ያልሆነ ሰው ልብሱን ለብሶ ከተገኘ እንደ ከፍተኛ ወንጀል ስለሚቆጠር።
በርካቶች ይህን ሁኔታ አይተው "ቀድሞውም እኮ አንድ ነበሩ" እና "ቁስል እንኳን ሳይደርቅ እንዴት እንዲህ ይደረጋል?" የሚሉ አስተያየቶችን እየሰጡ እንደሆነ ታዘብኩ።
መንግስት ከጥቂት ሳምንታት እና ወራት በፊት በግድያ፣ በዝርፊያ፣ በእገታ እና በሽብር ሲከሰው ከነበረው አካል ጋር ስምምነት ሲፈፅም ረጋ ተብሎ እና በሰከነ ሁኔታ ካልተያዘ ጉዳት የደረሰባቸው እና በተለይ አሁን ድረስ ከታጣቂዎቹ ጋር በዱር በገደሉ ተፋጠው ላሉ የመንግስት ፀጥታ አካላት የሚያስተላልፈው መልዕክት ያሰጋል።
አለም አቀፍ ልምዶች እንደሚያሳዩት ከሁሉም በፊት የሚቀድመው የተሀድሶ ፕሮግራም ነው።
ሰላም ለሀገራችን።
Via ኤልያስ መሰረት

ህወሓት በመቐለ ከተማ የጠራው ሰልፍ ፍቃድ ሳያገኝ ቀረ
የመቐለ ህወሓት ፅሕፈት ቤት "የጊዝያዊ አስተዳደሩን ህገ ወጥ" አሰራር በመቃወም በመቀለ ከተማ ሰላማዊ ሰለፍ ለማድረግ የከተማ አስተዳደሩን ፍቃድ መጠየቁ ይታወሳል።
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
የመቐለ ህወሓት ፅሕፈት ቤት "የጊዝያዊ አስተዳደሩን ህገ ወጥ" አሰራር በመቃወም በመቀለ ከተማ ሰላማዊ ሰለፍ ለማድረግ የከተማ አስተዳደሩን ፍቃድ መጠየቁ ይታወሳል።
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
ሼኽ መሐመድ ሁሴን አል-አሙዲ፣ አብነት ገብረ መስቀል በፍርድ ቤት የተወሰነባቸውን ከ852 ሚሊዮን ብር በላይ መክፈል ካልቻሉ፣ በናሽናል ኦይል ኢትዮጵያ ኩባንያ ውስጥ ያላቸው የ15 በመቶ የአክሲዮን ድርሻ ተሽጦ እንዲከፈላቸው ለፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባስገቡት ማመልከቻ መጠየቃቸውን ዋዜማ ተረድታለች።
ከኅዳር 27፣ 2014 ዓ፣ም እስከ ኅዳር 12፣ 2017 ዓ፣ም የተሰላውና አብነት እንዲከፍሉ የተወሰነባቸው የ9 በመቶ ሕጋዊ ወለድ ደሞ፣ 226 ሚሊዮን 968 ሺሕ ብር ነው።
ሼክ አል-አሙዲ በፍርድ ቤቱ ውሳኔ ላይ ይግባኝ ስለመባሉ እንደማያውቁ ለፍርድ ቤቱ በላኩት ማመልከቻ ላይ ጠቅሰዋል። ፍርድ ቤቱ ጥቅምት 5 የሰጠውን ውሳኔ አብነት የማይፈጽሙበት ምክንያት ካለ፣ ታኅሳስ 18 ቀርበው እንዲያስረዱ ታዘዋል።
ገዥው ብልጽግና ፓርቲን ጨምሮ ከአብነትና ከሚድሮክ ኩባንያ አመራሮች ከፍተኛ የገንዘብ ሥጦታ የተቀበሉት የተለያዩ መንግሥታዊ ተቋማት አል-አሙዲን ይመለስልኝ ያሉትን ገንዘብ መቀበላቸውን አምነው፣ ገንዘቡን የተቀበሉባቸውን የባንክ ደረሰኞች ፍርድ ቤቱ ላዘጋጀው ገለልተኛ ኦዲተር ማረጋገጣቸውን ዋዜማ የተመለከተቻቸው የተቋማቱ ደብዳቤዎች አረጋግጠዋል።

ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል የሚመሩት የሕወሓት ክንፍ፣ በመቀሌ ከተማ ኅዳር 29 የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ለከተማዋ ምክር ቤት በደብዳቤ ጥያቄ አቅርቧል።
ቡድኑ ሰልፉን የሚያካሂደው፣ ሕዝባዊ ምክር ቤቶችን በኃይል ለማፍረስ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ለመቃወም እንደኾነ ገልጧል። ቡድኑ፣ የክልሉ ጸጥታ ኃይል ለሰልፉ ጥበቃ እንዲያደርግም ጠይቋል።
ጊዜያዊ አስተዳደሩና ቡድኑ መቀሌን ጨምሮ በከተሞች፣ ዞኖችና ወረዳዎች የራሳቸውን ሹሞች በመሾም ርስበርስ ሲወነጃጀሉ ቆይተዋል።
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
ቡድኑ ሰልፉን የሚያካሂደው፣ ሕዝባዊ ምክር ቤቶችን በኃይል ለማፍረስ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ለመቃወም እንደኾነ ገልጧል። ቡድኑ፣ የክልሉ ጸጥታ ኃይል ለሰልፉ ጥበቃ እንዲያደርግም ጠይቋል።
ጊዜያዊ አስተዳደሩና ቡድኑ መቀሌን ጨምሮ በከተሞች፣ ዞኖችና ወረዳዎች የራሳቸውን ሹሞች በመሾም ርስበርስ ሲወነጃጀሉ ቆይተዋል።
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
“በሶስት ወራት ብቻ በህገወጥ መንገድ ለስደት ከተዳረጉ 6ሺ ወጣቶች 294ቱ ህይወታቸው አልፏል” - የትግራይ ክልል
ባለፉት ሶስት ወራት በህገወጥ መንገድ ለስደት ከተዳረጉ ከስድስት ሺ በላት ወጣቶች ውስጥ 294 የሚሆኑት ህይወታቸው ማለፉን የትግራይ ክልል የወጣቶችና ስፖርት ጉዳይ ቢሮ አስታወቀ።ህገወጥ ስደት የበርካታ የክልሉን ወጣቶች ህይወት እየቀጠፈ ነው፣ የወጣቶች ህገወጥ ስደት የሁሉም ሰው አጀንዳ መሆን አለበት ሲሉ የቢሮው ሃላፊ አቶ ሓይሽ ስባጋድስ አሳስበዋል።
ይህ የተገለጸው የወጣቶች ህይወት በመቅጠፍ ላይ ያለውን ህገወጥ ስደት በጋራ መከላከል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ለመምከር በመቀለ ከተማ ትላንት ህዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም በተዘጋጀው በመድረክ ላይ ነው።የቢሮው ሃላፊ አቶ ሓይሽ ስባጋድስ መንግስት እና ሁሉም አጋር አካላት ህገወጥ ስደትን የሚያባብሱ ተግባራትን በማስወገድ ሚናቸውን እንዲወጡ ጠይቀው በተለይም ዋነኛ ተዋናይ የሆኑትን የደላሎችን ሰንሰለት ለመበጣጣስ መስራት ይኖርበታል ሲሉ አሳስበዋል፤ መንግስት ለወጣቶች በቂ ድጋፍ ማድረግ ይገባዋል ሲሉም ጠይቀዋል።
በክልሉ እስከ ቀበሌ ድረስ ያለው የመንግስት አካል የጉዳዩ ክብደት በመረዳት እርብርብ ሊደረግ ይገባዋል ብለዋል፤ ቤተሰብ የልጆቹ ጉዳይ እንዲያሳስበው እየሰራን ነው ሲሉ ጠቁመዋል።በመድረኩ ላይ የተገኙት የመንግስታቱ ድርጅት ተወካይ ፀሃየ ወ/ጊዩርጊስ በኢትዮጵያ ከሚሰደዱ ወጣቶች መካከል 46 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው ሲሉ መግለጻቸውን ከትግራይ ቴሌቪዥን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

በሰሜን ወሎ ሲኖትራክ ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት በርካቶች መገደላቸውን የዓይን እማኞች እና የተጎጂ ቤተሰቦች ተናገሩ!
በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ባለፈው ሳምንት 'ሲኖ ትራክ' በተባለ የጭነት ተሽከርካሪ ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት 50 የሚሆኑ ሰዎች እንደተገደሉ የዓይን እማኞች እና የተጎጂ ቤተሰቦች ለቢቢሲ ተናገሩ።
ጥቃቱ የደረሰው ዞኑ ዳውንት ወረዳ ውስጥ ባለፈው ሐሙስ ኅዳር 19/2017 ዓ.ም. ቀትር 8፡00 አካባቢ መሆኑን የተናገሩት የአካባቢው ነዋሪዎች የጥቃቱ ሰለባዎች ከተለያዩ ጉዳዮች ወደ ኩርባ ከተማ ሲመለሱ የነበሩ ሰዎች ናቸው ብለዋል።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ስለ ጥቃቱ ጥቆማ እንደደረሰው እና መረጃ እያሰባሰበ እንደሆነ ለቢቢሲ ተናግሯል። ሐሙሲት የተባለ ገበያ ከሚውልበት ሾጋ አካባቢ ወጣ ብሎ ልዩ ስሙ ሰጎራ በተባለ አካባቢ ጥቃቱ መድረሱንም የዓይን እማኞች ተናግረዋል።
በአካባቢው ባለው የትራንስፖርት ችግር ምክንያት በጭነት ተሽከርካሪዎች መጓዝ የተለመደ መሆኑን የተናገሩት ነዋሪዎች፤ ያለፈው ሳምንት ጥቃት አሸዋ እና ሰዎችን በጫነ 'ሲኖ ትራክ' በተባለው ተሽከርካሪ ላይ መድረሱን ተናግረዋል። ገበያ ውለው ሲመለሱ የነበሩ ገበያተኞች፣ አርሶ አደሮች፣ ለሥራ ፍላጋ ከአጎራባች ዋድላ ወረዳ ሲመለሱ የነበሩ ወጣቶች እንዲሁም ከደላንታ ወረዳ ክርስትና ደርሰው ሲመለሱ የነበሩ ሰዎች የጥቃቱ ሰለባዎች እንደሆኑ ተናግረዋል።

በመላው ሀገሪቱ የኃይል መቋረጥ አጋጥሟል ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ
ዛሬ ማምሻውን በሲስተም አለመረጋጋት በተፈጠረ ችግር የተነሳ በመላው ሀገሪቱ የኃይል መቋረጥ አጋጥሟል ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል።
ችግሩን በመፍታት የተቋረጠውን ኃይል ወደነበረበት ለመመለስ በኃይል ማመንጫዎች እና በማከፋፈያ ጣቢያዎች ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ነው ብሏል።
የተፈጠረው ችግር እስኪፈታ ድረስ ደንበኞች በትዕግስት እንዲጠባበቁ ጠይቆ፤ ያሉትን መረጃዎች በፍጥነት የሚያሳውቅ መሆኑንም ገልጿል።
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
ዛሬ ማምሻውን በሲስተም አለመረጋጋት በተፈጠረ ችግር የተነሳ በመላው ሀገሪቱ የኃይል መቋረጥ አጋጥሟል ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል።
ችግሩን በመፍታት የተቋረጠውን ኃይል ወደነበረበት ለመመለስ በኃይል ማመንጫዎች እና በማከፋፈያ ጣቢያዎች ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ነው ብሏል።
የተፈጠረው ችግር እስኪፈታ ድረስ ደንበኞች በትዕግስት እንዲጠባበቁ ጠይቆ፤ ያሉትን መረጃዎች በፍጥነት የሚያሳውቅ መሆኑንም ገልጿል።
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ግማሽ ክፍለ ዘመን እንቅልፍ ያላዩ ዓይኖች
ስምንት መቶ ሰባት ዓመታትን ወደኋላ ስንመለስ “ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን” “የአእላፍ ቅዱሳን አባት” በመባል የሚታወቁት ታላቁ ጻድቅ የተወለዱበት ዓመት 1210 ዓ.ም ላይ እንገኛለን፡፡
ጎንደር ስማዳ ዳሕና ሚካኤል የተወለዱት አባት ገና በጉብዝናቸው ወራት በ30 ዓመታቸው ዓለምና አምሮቷን ንቀው ወደ ትግራይ “ደብረ ዳህምሞ” የአባታችን አቡነ አረጋዊ ገዳም ደብረ ዳሞ በመግባት ከጻድቁ አምስተኛ የቆብ ልጅ አባ ዮሐኒ ካልዕ ደቀ መዝሙር ሆኑ፡፡
በደብረ ዳሞም ቀኑን ለመነኮሳት በመታዘዝ፣ በመፍጨትና ውሃ በመቅዳት ሌሊቱን ደግሞ እኩሉን በጸሎት እኩሉን ቅዱሳት መጻሕፍትን በመገልበጥ ያሳልፉት ነበር፡፡ ከሰባት ዓመታት ተጋድሎ በኋላም በ37 ዓመታቸው ምንኩስና ተሰጣቸው፡፡
በዚው ዓመትም መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ብዙ ተአምራትና አገልግሎት የምትሰራበት ስፍራ እግዚአብሔር አዘጋጅቶልሀልና ወደ ወሎ ሐይቅ ሒድ አላቸው፡፡ ምንም እንኳን ደብረ ዳሞና ሐይቅ እስጢፋኖስ እጅግ የተራራቁ ቢሆኑም መልአኩ ነጥቆ የተፈቀደላቸው ስፍራ ላይ አደረሳቸው፡፡
በዚም ለሰባት ዓመታት ከሐይቁ በስተሰሜን በሚገኘው የጴጥሮስ ወጳውሎስ ገዳም በማስተማርና በማገልገል ስራቸውን ጀመሩ፡፡ በእነዚህ ዓመታት ሌሊቱን በሐይቁ ውስጥ ገብተው በመጸለይ ያሰዳልፉ ነበር፡፡ በኋላም ቅድስናቸውን የተመለከቱ አበው በብዙ ትግል አበምኔት አደርገው ሾሟቸው፡፡ ይህም የታላቁ ስራቸው መጀመሪያ ሆነ፡፡
አባታችን አቡነ ኢየሱስ ሞአ ከደሴ ከተማ በ30 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም 800 ደቀ መዛሙርትን በመሰብሰብና በማስተማር ዮዲት ጉዲት ለ40 ዓመታት ያፈረሰቻትን ቤተ ክርስቲያን ይገነቡ ጀመር፡፡
ታላላቅ መጻሕፍትን በማሰባሰብ የመገልበጥና የማባዛት ስራ ያሰሩ ሲሆን ደቀ መዛሙርቶቻቸውንም በማስተማር በመላው ሀገሪቱ ለሐዋርያዊ አገልግሎት አሰማርተው ቃለ እግዚአብሔር እንዲስፋፋ፣ ትምህርት ወንጌል እንዲሰርጽ አድርገዋል፡፡
ለ45 ዓመታት በዘለቀው የገዳሙ አበምኔትነት አገልግሎታቸው አይናቸው ከእንቅልፍ ጋር ተገናኝቶ እንደማያውቅ ገድላቸው ያስረዳል፡፡ እግዚአብሔር አምላክም ይህን ተጋድሏቸውን ለፍሬ አድርጎላቸው ታላላቅ ጻድቃን አባቶችን አፍርተዋል፡፡
ከእነዚህም መካከል የደብረ ሊባኖስ ኢትዮጵያዊው ሐዋርያ አቡነ ተክለ ሃይማኖት፣ አባ ኂሩተ አምላክ ዘጣና ሐይቅ፣ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ፣ አባ ዘኢየሱስ፣ አባ በጸሎተ ሚካኤል፣ አባ አሮን ዘደብረ ዳሬት ጥቂቶች ናቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ንጉሱ አፄ ይኩኖ አምላክንም በትምህርተ ሃይማኖት አንጸው ለክብር ያበቋቸው እርሳቸው ናቸው፡፡ የሚያርፉበት ጊዜ ሲደርስም ጌታችን ወርዶ ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል፡፡
በተወለዱ በ82 ዓመታቸው በ1292 ዓ.ም ሕዳር 26 ቀን ወደ ማያልፈው ክብር ጌታችን ጠርቷቸዋል፡፡ አስገራሚው ነገር አበምኔት ከመሆናቸው በፊት ለሰባት ዓመታት በገዳሙ አስተዳዳሪነት ደግሞ ለ45 ዓመታት በጠቅላላው ለ52 ዓመታት በቆየው ተጋድሏቸው እንቅልፍ የሚባል በአይናቸው አልዞረም፡፡
ገዳማውያን ዓለምንና አምሮቷን ትተው ሲመንኑ የበለጠውን ክብር ሽተው፣ ከአምላካችን ከእግዚአብሔር ጋር ሰፊ ጊዜ ለማሳለፍ ፈልገው እንጂ ተሞኝተው አይደለም፡፡ መስቀሉን ተሸክመው ሲከተሉት ዓለም እንደ ሞኝነት ይቆጥርባቸዋል፡፡
በረከታቸው ግን ምዕተ ዓመታትን ተሻግሮ ድንቅ ይሰራል፡፡ አሁን በዘመናችን ያሉትን ገዳማትና መናንያን ስንደግፍም ይህ ቃል ኪዳንና በረከት ከኛ ጋር ይሆናል፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:-ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም