Telegram Web Link
በመርዝ የተለወሰዉ 100 ሚሊዮን ዶላር

መሰሪዋ ፈረኦኗ ግብፅ በመርዝ የተለወሰ የ100 ሚሊዮን ዶላር ገፀ በረከት ይዛ ኡጋንዳ ገብታለች፡፡በአባይ ተፋሰስ ላይ ያቀደችዉን ሴራ ከግብ ለማድረስ ግብፅ ባለስልጣኖቿን 100 ሚሊዮን ዶላር አሳቅፋ ወደ ኡጋንዳ ልካለች፡፡

ከዚህ በላይደግሞ
ዝርዝሩን በዚህ ያንብቡት👇👇
https://www.tg-me.com/+gPveFwjiiXdiMDE0
https://www.tg-me.com/+gPveFwjiiXdiMDE0
መረጃ‼️

ናይጄሪያ የኑሮ ውድነት ቀውስ በመቃወም ሰልፍ የወጡ ዜጎች በሞት ልትቀጣ እንደምትችል ተነገረ።

ከእነዚህ መካከል ከ14 -17 አመት እድሜ ላይ የሚገኙ 29 ህጻናትን ይገኙበታል ተብሏል።

የሀገሪቱን የኑሮ ውድነት ቀውስ በመቃወም ሰልፍ ከወጡ ናይጄሪያውያን መካከል ክስ የተመሰረተባቸውን ዜጎች በሞት ልትቀጣ እንደምትችል ነው የተገለፀወው፡፡

ከነዚህ መካከል በትላንትናው ዕለት ፍርድ ቤት የቀረቡት 29ኙ ህጻናት መሆናቸው የተነገረ ሲሆን፥ በፍርድ ቤት በቀረቡበት ወቅት አራቱ በጭንቀት እራሳቸውን ስተው መውደቃቸው ተዘግቧል፡፡

በአጠቃላይ 76 ሰላማዊ ሰልፈኞች በ10 የወንጀል ክሶች የተከሰሱ ሲሆን ከነዚህም መካከል የሀገር ክህደት፣ ንብረት ማውደም፣ በህዝባዊ ብጥብጥ እና ጥቃት መከሰሳቸውን ኤፒ ዘግቧል፡፡

በዚህ የክስ መዝገብ ውስጥ ከተከሰሰሱ ሰዎች መካከል እድሜያቸው ከ14 - 17 የሆኑ 29 ህጻናት ይገኙበታል ተብሏል፡፡

የኑሮ ውድነት በፈጠረው ተጽእኖ የተነሳ የተሻለ የኑሮ ሁኔታ እንዲሻሻል እና ለወጣቶች የስራ እድል የሚጠይቁ የተቃውሞ ሰልፎች ባለፉት ወራት ናይጄሪያ እና ኬንያን ጨምሮ በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ተካሄደዋል፡፡

በነሀሴ ወር በናይጄርያ የተለያዩ አካባቢዎች በተካሄደው ተቃውሞም 20 ሰዎች በጥይት ሲገደሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ለእስር ተዳርገዋል፡፡

የሞት ቅጣት በናጄርያ ከ1970 ጀምሮ ተግባራዊ መሆን የጀመረ ቢሆንም ከ2016 ወዲህ አንድም ሰው በሞት ተቀጥቶ አያውቅም፡፡



@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
መረጃ‼️

የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት 120 የመንግስት ፀጥታ ሃይሎችን ደምስሻለሁ ሲል  አስታወቀ

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ዉጫሌ በሚባል አካባቢ ላይ በሁለት አካባቢዎች የተሳካ ዘመቻ አድርጌ 120 የመንግስት የፀጥታ አካላትን ገድያለሁ ሲል ነዉ ኦነግ በመግለጫዉ ያስታወቀዉ ፡፡

ካራ በሚባል ወታደራዊ ካምፕ ላይ በፈፀመዉ ጥቃት 67 ወታደሮች መግደሉን ሲናገር በተመሳሳይ በደፈጣ እየተጎዙ ባሉ የሰራዊቱ አባላት ላይ ተኩስ በመክፈት 53 ወታደሮችን ገድያለሁ ብሎል ፡፡

ሰሞኑን በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች ንፁሃን በአሰቃቂ መንገድ ሲገደሉ እንዲሁም የሀይማኖት አባት እስከ ቤተሰቦቻቸዉ ታግተዉ ተገድለዉ መገኘታቸዉ የሚታወስ ነዉ ፡፡

ፊልድ ማርሻሉን ጨምሮ ከፍተኛ የሰራዊቱ አመራሮችን ኦነግ ሸኔ እየጠፋ ነዉ ቆሞ መዋጋት አይችልም ቢሉም ከ4ኪሎ 100 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ኦነግ የሚፈልገዉን  እየገደለ የሚፈልገዉን እየዘረፈ ይገኛል፡፡

@Sheger_press
@Sheger_press
የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ኢትዮጵያ ላይ ዛቱ

ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ ለሁለቱ የአገሪቱ ምክር ቤቶች ባደረጉት ንግግር በቅርቡ ከግብፅ እና ቱርክ ጋር የተፈራረሙትን የመከላከያ ትብብር ስምምነቶችን ከኢትዮጵያ ለሚመጣ ስጋት እንደሚጠቀሙባቸው ጠቁመዋል።

እነዚህ ስምምነቶች የአፍሪካ ቀንድ መረጋጋትን አያሳጡም፣ ነገር ግን ዓለም አቀፍ ህግን የሚቃረን የኢትዮጵያን ምኞት ያስቀራል ሲሉም አረጋግጠዋል።

የፕሬዝዳንቱ ንግግር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከሰሞኑ ለፓርላማው ባደረጉት  ንግግር፣ ኢትዮጵያ በቀይ ባህር ላይ  መዳረሻ ለማግኘት ያላትን እና  የማይናወጥ ያሉትን ፍላጎት በድጋሚ ካረጋገጡ በኋላ የተሰማ ነው።


@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
#ጠብታው ሲጠራቀም  

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምስራቅ በለሳ ወረዳ የሚገኘው ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም ልዩ በረከት ያለበት ስፍራ ነው፡፡

ከዓለት መሀል በመነኮሳት ፀሎት ብቻ በሚቆረጥ የማር እምነትና ድውያን ከመፈወስ አልፎ ሙት ያስነሳ ድንቅ ጸበል ያለበት፤ ከዘጠና በላይ ገዳማውያን የተጠለሉበት፣ ስለ ዓለምና ስለ ሀገራችን ሌት ተቀን የሚጸልዩበት ቅዱስ ስፍራ ነው፡፡

ይሁንና መነኮሳቱና ገዳማውያኑ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ችግሮች እየተፈታተኗቸው ነው፡፡ አከባቢው ተፈጥሮ ፊቷን አዙራበት ድርቅ በመኖሩ ጭው ያለ ምድረ በዳ ሆኋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በአካባቢው ያለው ጦርነት በየጊዜው ይጎበኟቸው የነበሩ ፀበልተኞች ፈጽመው እንዲሸሹና ገዳማውያኑ ያለምንም ጠያቂ በትልቅ ችግርና ፈተና ውስጥ እንዲገኙ አድርጓቸዋል፡፡

ከፀሎትና ከድካም መልስ የሚጠለሉበት በአታቸውን ማጽናት የሚችል እገዛ፣ ከፆም መልስ የሚቀምሱትን አፍ መሻሪያና የአመት ልብስ ልናቀርብላቸው ይገባል። በዚህ የበረከት ስራ ገዳሙንና አባቶችን ብቻ ሳይሆን በጸሎታቸው ሀገራችንንም ለመጠበቅ አስተዋጽኦ እናደርጋለን፡፡ የእያንዳንዳችን ጠብታ ድጋፍ ሲጠራቀም ዋጋ አለው፣ የሕሊና እርካታም እናገኛለን፡፡
 
ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
#የሀዘን_መግለጫ

በኦሮሚያ ክልል፣ ሰሜን ሸዋ ዞን፣ ደራ ወረዳ፣ አድዓ መልኬ ቀበሌ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በኦነግ ሸኔ(ኦ.ነ.ሠ) ታግተው በግፍ ለተገደሉት የገንዳ አረቡ መስጅድ ኢማም ሼህ ሙሐመድ መኪን ሀጂ አረፉ ፓርቲያችን የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልጻል።

ኢማሙ በአካባቢያቸው የተፈሩና የተከበሩ፣ የተጣላ አስታራቂ እንደነበሩና በመስጅድ ውስጥ ሳሉ ከሌሎች 12 የቅርብ ሰዎች ጋር ታግተው በቅድሚያ ለመልቀቅ መደራደሪያ 3ሚሊዮን ብር ተጠይቆ 1.4ሚሊዮን ሰጥተው መሣሪያ ጭምር ካላመጣችሁ በማለትና ቀሪውን ገንዘብ ሲፈልጉ በግፍ ኹሉንም እንደገደሏቸው ለማወቅ ችለናል። ኢማሙ የታገቱት ከወር በፊት እንደነበርና ለማስልቀቅም ከፍተኛ ርብርብ እንደነበር ሰምተናል። በሣምንት ልዩነት እንዲሁ አንድ የቤተክርስቲያን አገልጋይ 800ሺህ ብር ተጠይቆባቸው ብሩንም ከፍለው ከብዙ እንግልት በኋላ በአሰቃቂ ኹኔታ ገድለዋቸዋል። አካባቢው ከፍተኛ ማንነት ተኮር ጭፍጨፋ የሚዘወተርበት በአንጻሩ ግፉ እንዳይነገር በሚዲያ በታገዘ ፕሮፓጋንዳ ጭምር የሚድበሰበስበት ነው።

ፓርቲያችን ደጋግሞ እንዳሳሰበው እንዲህ ከነባር ሃይማኖት ኢትዮጵያን ለማፋታትና ወደአዲሱ የዓለም ሥርዓት/New world order/ ለመውሰድ በሚደረገው ጥድፊያና ርብርብ መንግሥታዊ መዋቅር ጭምር ተከትሎ እየተሠራበት እንደሆነ ለዚህም በዋናነት የሃይማኖት ተቋማትን በቃልም በተግባርም መዳፈር፣ የሃይማኖት አባቶችን እያሳደዱ መግደል፣ ምዕመናንን ማሳሳት፣ ማፈናቀል፣ ዕምነት ተኮር ጭፍጨፋ የስልት ትግበራውና መንገድ ጠረጋው አካል ተደርጎ የሚወሰድ መሆኑን ደጋግመን ገልጸናል።

እንዲህ ያለው ተግባር በጥንቃቄ የሚፈጸም በመሆኑ ዛሬ ክርስቲያኑን ነገ ሙስሊሙን ቦታ እየቀያየረ የሚደረግ ነው። እንዲያውም በታሪክ፣ በባህል እንደምናውቀው አንዱ የሌላው መከታና ጠባቂ እንዳይሆን እርስ በእርስ ለማፈጀትም ሴራ ሲጠምቅ ይታያል። ውጤቱ ውሎ አድሮ ያለ ተው ባይና አስታራቂ፣ በጎውን መንገድ ከነውሩ ለይተውና አበጥረው በቃልም በጽሑፍም የሚያመላክቱንን ጠቋሚ አባቶች የሚያሳጣ አካሄድ መሆኑን በውል መረዳት ይገባል።

ፓርቲያችን እንዲህ ያለውን እኩይ ተግባር በጽኑ ያወግዛል፤ ባለ በሌለ ኃይሉም ይታገለዋል።
በድጋሚ በኢማሙ ግፍ ግድያ የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጥን ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን እንመኛለን።

እግዚአብሔር ሀገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!

እናት ፓርቲ
ጥቅምት ፳፫ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ጊዜው የመረጃ ነው ❗️
ለዚህ ደግሞ እውን የቴሌግራም ቻናል ልጠቁማችሁ ሁላችሁም የምትመርጡት ቻናል ይሆናል ወቅታዊ ፤ትኩስና የጦርነቱን ድባብ የሚዘግብ ምርጥ ቻናል 👇👇👇
https://www.tg-me.com/+gPveFwjiiXdiMDE0
https://www.tg-me.com/+gPveFwjiiXdiMDE0
ተጠያቂዉ ማነዉ⁉️

ለሙከራ በተተኮሰ ከባድ መሳሪያ የአንድ ገበሬ ህይወት አለፈ

ዛሬ ጠዋት በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን የከሚሴ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ለሙከራ ከባድ መሳሪያ ሊተኮስ እንደሚችልና እንዳትደነግጡ የሚል  መልዕክት አስተላልፎ ነበር።

ከባድ መሳሪያዉ ወደ  ሰሜን ሸዋ ዞን
መኮይ አምቧሀ አካባቢ የተተኮሰ ሲሆን የተተኮሰው መድፍ የአንድ ገበሬ ህይወት ማጥፋቱን ተዘግቦል።

አዉሮፓዉያን ለአንድ ዜጋቸዉ ህይወት ሙሉ የሃገራቸዉን ጦር ያዘምታሉ ፡፡

እኛ ጋር በግዴለሺነት ቦታዉ ከሰዉ እና ከእንሰሳት ነፃ መሆኑ ባልታወቀበት ከባድ መሳሪያ ተተኩሶ የሰዉ ህይወት ይጠፋል ፡፡

ለዚህ ንፁህ አርሶ አደር ገበሬ ደም ተጠያቂዉ ማነዉ?


@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ኢትዮጵያ ውስጥ፣ በጋራዦችና መለዋወጫዎች እጥረት ሳቢያ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ባለቤቶች ከፍተኛ ችግር እንደገጠማቸው መረዳቱን ጠቅሶ የፈረንሳይ ዜና ወኪል ዘግቧል።

አዲስ አበባ ውስጥ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ መጠገን የሚችሉ ጋራዦች ከሦስት እንደማይበልጡ ዘገባው ጠቅሷል።

የትራንስፖርት ሚንስቴር ሃላፊዎች በበኩላቸው፣ መንግሥት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ባትሪ ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎች እንዲቋቋሙ ገንዘብ እንደሚመድብ እንደነገሩት የዜና ምንጩ አመልክቷል።

ሃላፊዎቹ፣ መንግሥት የኤሌክትሪክ ባትሪዎችን የሚያመርት ፋብሪካ የማቋቋም ዕቅድ እንዳለውም ሃላፊዎቹ ተናግረዋል ተብሏል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
እናት ፓርቲ፣ በኦሮሚያ ክልል፣ ሰሜን ሸዋ ዞን፣ ደራ ወረዳ፣ አድዓ መልኬ ቀበሌ ባለፈው ሳምንት በገንዳ አረቡ መስጅድ ኢማም ሼህ ሙሐመድ መኪን ሐጂ አረፉ ላይ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች ፈጸሙት የተባለውን እገታና ግድያ ትናንት ባወጣው መግለጫ አውግዟል።

ኢማሙ ከ12 የቅርብ ሰዎቻቸው ጋር ታግተው ለማስለቀቂያ 3 ሚሊዮን ብር ተጠይቆባቸው፣ 1 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር ተከፍሎ እንደነበር መረዳቱን ፓርቲው ገልጧል።

አካባቢው ከፍተኛ "ማንነት ተኮር ጭፍጨፋ" እንደሚዘወተርበት የጠቀሰው ፓርቲው፣ ግፉ እንዳይነገር በመገናኛ ብዙኀን ፕሮፓጋንዳ አማካኝነት ጭምር ይድበሰበሳል ብሏል።

የኃይማኖት አባቶች ግድያ፣ የምዕመናን መፈናቀልና የዕምነት ተኮር ጭፍጨፋ የሚካሄደው፣ በመንግሥታዊ መዋቅሩ ጭምር በመታገዝ ኢትዮጵያን ከነባር ኃይማኖቶች በማፋታት ወደ አዲሱ የዓለም ሥርዓት ለመውሰድ ነው በማለት ፓርቲው ከሷል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የREMEDIALፕሮግራም ምደባ ይፋ ሆነ።

በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የREMEDIAL ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ተደርጓል።

ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ተማሪዎች ምደባቸውን ፦

በWebsite: https://placement.ethernet.edu.et 

በTelegram: https://www.tg-me.com/moestudentbot ላይ መመልከት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

@Sheger_press
@Sheger_press
ትራምፕ ዴሞክራቶችን የአጋንንት ፓርቲ ነው ሲሉ ተናገሩ

ዴሞክራቷ ካማላ ሃሪስ በታሪካዊው የጥቁሮች ቤተክርስትያን እና ከፍተኛ ትንቅንቅ በሚደረግባት ሚቺጋን ውስጥ እሁድ እለት ለአሜሪካ ፕሬዝዳንትነት የመዝጊያ የምረጡኝ ቅስቀሳ ስታደርግ የሪፐብሊካኑ ተቀናቃኛቸው ዶናልድ ትራምፕ በፔንስልቬንያ በተካሄደው የድጋፍ ሰልፍ ላይ ሃይል የተቀላቀለበት ንግግርን አድርገዋል።

የሕዝብ አስተያየት እንደሚጠቁሙት የ60 ዓመቷ ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስ በሴት መራጮች ዘንድ ጠንካራ ድጋፍ ስተገኝ የ78 አመቱ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ደግሞ በሂስፓኒክ መራጮች በተለይም በወንዶች ዘንድ ድል እንደሚቀናቸው ይጠበቃል።ሪፐብሊካኖች በሴኔቱ ውስጥ አብላጫውን ወንበር ለመያዝ ሲወዳደሩ ዲሞክራቶች በተወካዮች ምክር ቤት የሪፐብሊካኑን አብላጫ ድምጽ የመገልበጥ እድል እንዳላቸው እየታየ ይገኛል። ፓርቲያቸው ሁለቱንም ምክር ቤቶች መቆጣጠር ያቃታቸው ፕሬዚዳንት ወደ ስልጣን ቢመጡ እንኴን ትልቅ ህግ ለማውጣት ይቸገራሉ።

"በቀናት ውስጥ ብቻ የሀገራችንን እጣ ፈንታ ለትውልዱ ጭምር የመወሰን ስልጣን አለን" ሲሉ ሃሪስ በዲትሮይት በሚገኘው በታላቁ የአማኑኤል ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ለታደሙ ምእመናን ተናግረዋል። "መተግበር አለብን፤ መጸለይ እና ማውራት ብቻ በቂ አይደለም።" ሲሉ ለታዳሚዎች ተናግረዋል።በኋላም ላይ በምስራቅ ላንሲንግ ሚቺጋን በተካሄደው ሰልፍ ለ200 ሺ የሚጠጉ አረብ አሜሪካውያን ንግግር ያደረገችው ካማላ ሀሪስ በጋዛ እና ሊባኖስ በእስራኤል ጦርነት ለተጎዱ ሲቪል ሰዎች ይህ አመት ከባድ ነበር ብላለች። በጋዛ በደረሰው የሞት እና ውድመት መጠን እንዲሁም በሊባኖስ በሲቪሎች ላይ ለደረሰው ጉዳት እና መፈናቀል እንደ ፕሬዝዳንት የጋዛን ጦርነት ለማስቆም የተቻለኝን ሁሉ አደርጋለሁ ስትል ሃሪስ ተደምጣለች።

በጋዛ እና ሊባኖስ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሲቪሎች ሲሞቱ እና በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ መፈናቀል ባለበት በዚህ ወቅት በርካታ አረብ እና ሙስሊም አሜሪካውያን እንዲሁም ፀረ-ጦርነት አክቲቪስቶች አሜሪካ ለእስራኤል የምታደርገውን ድጋፍ አውግዘዋል። ትራምፕ አርብ ዕለት የአረብ አሜሪካውያን ማህበረሰብ እምብርት በሆነችው ዴርቦርን ሚቺጋን በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ግጭት እንደሚያስቆሙ ቃል ገብተዋል። ትራምፕ ዴሞክራቶችን “የአጋንንት ፓርቲ” በማለት የዲሞክራቲክ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ላይ ተሳልቀዋል። በሐምሌ ወር በፔንስልቬንያ በትለር ከተማ በታጣቂ ከተተኮሰ ጥይት ጆሮአቸውን ተመተው ከግድያ ሙከራ የተረፉት ትራምፕ እሁድ እለት ነፍሰ ገዳይ ከሆኑ የዜና ማሰራጫዎች በኩል የሚተኮስ የውሸት ዜና ያን ያህል አያሳስበኝም ብለዋል።
የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ የሆነውን የሰው ልጅ በእናትነት እቅፏ ታቅፋ ዘወትር ስለልጆቿ ለምትማፀነው ፣ የህይወት ውሀ ምንጭ  የሆነው ወንጌልን የሚወዱ ፍለጋ ሳይሰደዱ ፣ እናት ቤተክርስቲያን ለዘመናት የጠበቀቻቸውን ልጆቿን ሳታጣ  ከአስራታችን ፣ ከዕለት ቁርሳችን በመስጠት የሐዋርያት መሰብሰቢያ የጻድቃን ከተማ የሆነችውን ቅድስት ቤተክርስቲያንን እንታደግ።

ድጋፍ ለማድረግ :-ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
የሩሲያ ጦር ደምስሶ ተቆጣጠረ

ሩሲያ ሁለት ተጨማሪ የዩክሬን መንደሮችን እንደተቆጣጠረች የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡የሩሲያ ወታደሮች በካርኪቭ ግዛት ፔርሾትራቭኒቭ እና በዶኔስክ ግዛት ኩራክሂቭካ የተሰኙ የዩክሬን መንደሮችን ነው የተቆጣጠሩት፡፡

በአካባቢው ሲደረግ በቆየው ፍልሚያ በርካታ የዩክሬን ጦር መሳሪያዎች መማረካቸውና መውደማቸውም ተገልጿል፡፡በዚህም በርካታ ተዋጊ አውሮፕላኖች፣ ሄሊኮፕተሮች፣ ድሮኖች፣ ታንኮች፣ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችና የሮኬት ማስወንጨፊያዎች መውደማቸው ተጠቁሟል፡፡

በአንጻሩ በጉዳዩ ላይ ከዩክሬን መንግስት በኩል የተባለ ነገር አለመኖሩን የቲ አር ቲ ዘገባ አመልክቷል፡፡
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በሶማሌ ክልል የኔትዎርክ ተደራሽነቱን ማስፋቱን ገለጸ፡፡

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በሶማሌ ክልል ጎዴ፣ ቀብሪደሃር፣ ቀብሪበያ፣ ደጋሃቡር፣ ዋጃሌ እና አዉባሬ ከተሞች እንዲሁም በመሃል ያሉ ከተሞች ላይ የኔትዎርክ ተደራሽነቱን ማስፋቱን አስታዉቋል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ጊዜው የመረጃ ነው ❗️
ለዚህ ደግሞ እውን የቴሌግራም ቻናል ልጠቁማችሁ ሁላችሁም የምትመርጡት ቻናል ይሆናል ወቅታዊ ፤ትኩስና የጦርነቱን ድባብ የሚዘግብ ምርጥ ቻናል 👇👇👇
https://www.tg-me.com/+gPveFwjiiXdiMDE0
https://www.tg-me.com/+gPveFwjiiXdiMDE0
ካማላ ሀሪስ እና ዶናልድ ትራምፕ ፕሬዝደንት ለመሆን የትኞቹን ግዛቶች ማሸነፍ አለባቸው?

አሜሪካ 50 ግዛቶች አሏት። ሁለቱ አውራ የፖለቲካ ፓርቲዎች ማለትም ዲሞክራት እና ሪፐብሊካን እኒህን ግዛቶች ተቀራምተዋቸዋል።

ይህ ማለት የትኛው ግዛት ለየትኛው ፓርቲ ድምፁን እንደሚሰጥ ይታወቃል ማለት ነው።

ነገር ግን ሰባት ግዛቶች ለየትኛው ፓርቲ ድምፃቸውን እንደሚሰጡ አይታወቅም፥ ለዚህ ነው ወላዋይ የሚባሉት።

እኒህ ግዛቶች ኔቫዳ፣ አሪዞና፣ ኖርዝ ካሮላይና፣ ጆርጂያ፣ ዊስኮንሲን፣ ሚሺጋን እና ፔንሲልቬኒያ ናቸው።

በአሜሪካ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ዕጩዎች በርካታ ድምፅ ስላገኙ መንበረ-ሥልጣኑን ማግኘት ይችላሉ ማለት አይደለም።

ሁለቱ ዕጩዎች የሚፎካከሩት በ50ዎቹ ግዛቶች የሚደረጉትን ምርጫዎች ለማሸነፍ ነው የሚታገሉት።

እያንዳንዱ ግዛት ኢሌክቶራል ኮሌጅ የሚባል ቁጥር አለው። ይህ የሚሆነው በሕዝብ ቁጥር ብዛት ላይ ተመስርቶ ነው።

በአጠቃላይ 538 ኢሌክቶራል ኮሌጆች አሉ፤ ዕጩዎቹ ከእነዚህ መካከል 270 እና ከዚያ በላይ ማግኘት አለበባቸው።

ይህ እንዲሆን ደግሞ ከሰባቱ ወሳኝ ግዛቶች ቢያንስ በሶስቱ ማሸነፍ ይጠበቅባቸዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ኢትዮጵያ ካላት 120 ሚልዮን ህዝብ 86 ሚልየኑ በድህነት ውስጥ እንደሚኖር አንድ ጥናት አረጋገጠ

(መሠረት ሚድያ)-  የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና ኦክስፎርድ በጋራ ያዘጋጁት ይህ ጥናት እንደጠቆመው ህንድ 234 ሚልዮን በድህነት የሚኖሩ ዜጎችን በመያዝ በአለም በአንደኝነት ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

ፓኪስታን በ93 ሚልዮን ሁለተኛ፣ ኢትዮጵያ በ86 ሚልዮን ሶስተኛ፣ ናይጄርያ በ74 ሚልዮን አራተኛ እንዲሁም ዴሞክራቲክ ኮንጎ በ66 ሚልዮን አምስተኛ ደረጃን ይዘዋል።

እነዚህ አምስት ሀገራት ከአለማችን 1.1 ቢልዮን ድሀ ህዝቦች መሀል 48 ፐርሰንቱን እንደሚይዙ የተጠቀሰ ሲሆን ከእነዚህ የአለማችን ህዝቦች መሀል 455 ሚልዮኑ ጦርነት በሚካሄድባቸው ሀገራት ይገኛሉ ብሏል።

ኢትዮጵያ ካላት 120 ሚልዮን ህዝብ 86 ሚልየኑ ወይም 72 ፐርሰንት ገደማው በድህነት ውስጥ እንደሚኖር ቢረጋገጥም ከመንግስት የሚወጡ ተከታታይ ሪፖርቶች ኢኮኖሚው እንዳደገ የሚጠቁሙ ናቸው።

Via ከመሠረት ሚዲያ

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2024/11/06 01:30:15
Back to Top
HTML Embed Code: