Telegram Web Link
የትግራይ ነጻነት ፓርቲ፣ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን የትግራይ የጦርነት ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንደተመለሱና የተቋረጡ መሠረተ ልማቶች አገልግሎት እንደጀመሩ አድርገው የፕሪቶሪያውን ግጭት ማቆም ስምምነት ሁለተኛ ዓመት በማስመልከት ሰሞኑን የሰጡትን አስተያየት ነቅፏል።

እንዲህ ያለው አስተያየት "አሳሳች ነው" ያለው ፓርቲው፣ የምዕራብ ትግራይ እንዲኹም አብዛኞቹ የምሥራቅ እና ደቡባዊ ትግራይ የጦርነት ተፈናቃዮች እስካኹን ወደ ቀያቸው እንዳልተመለሱ ገልጧል።

የብሊንከን አስተያየት፣ በትግራይ ባኹኑ ወቅት ያለውን ሰብዓዊ ቀውስ የሚያጣጥልና አኹንም ተፈናቅለው የሚገኙ ዜጎችን አደጋ ላይ የሚጥል ነው በማለት ተችቷል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
አዲሱ የደመወዝ ጭማሪ ሙሉ አዋጅ (1).pdf
14.9 MB
ደመወዝ‼️

በዚህ ወር ተግባራዊ ይደረጋል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው የመንግስት ሰራተኞች #
የደመወዝ_ጭማሪ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ

የጥቅምት ወር ደመወዝ እየተከፈለ ያለው በነባሩ ደመወዝ ነው።
መንግሥት ከጥቅምት ወር ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ያለው የመንግሥት ሠራተኞች የደሞዝ ጭማሪ፣ በዚህ ወር ተግባራዊ አለመሆኑን ተሰምቷል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ መንግሥት ሠራተኞች በተወሰኑ ወረዳዎች ከሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ጋር ውይይት ማድረጋቸውን እና ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል።

ቢሮው፣ ለከተማ አስተዳደሩ የመንግሥት ሰራተኞች ጭማሪው የሚከፈልበት ጊዜ የተራዘመው የሰራተኞችን መረጃ ለማደራጀት ጊዜ ስለሚያስፈልግ ነው የሚል ምላሽ ሰጥቷል ።

ሆኖም ሰራተኞቹ ቢሮው እስካሁን ምን ያህል የመንግስት ሰራተኛ እንዳለ እና ሌሎች ከደሞዝ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን አያውቅም ወይ? የሚል ጥያቄ ማንሳታቸው ተሰምቷል ።

ሰራተኞቹ እስካሁን የተጨመረላቸውን ደሞዝ የሚገልጽ ይፋዊ ደብዳቤ አልደረሳቸውም።

በተጨማሪም ከተማ አስተዳደሩ አዲስ የመዋቅር ማሻሻያ አደረጃጀት ጥናት አድርገው የብቃት መመዘኛ ፈተና ለሰጡት ተቋማት ሰራተኞች የደሞዝ ጭማሪው ይዘገያል መባሉንም ዋዜማ ተገንዝባለች። ጭማሪው የሚዘገየው ተቋማቱ የሰራተኞችን የሥራ ደረጃ ምደባ ገና ስላልጨረሱ ነው ተብሏል። 

ከተማ አስተዳደሩ በመጀመሪያው ዙር የብቃት ምዘና ፈተና የተሰጠው ለቤቶች ልማት አስተዳደር ጽህፈት ቤት፣ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ጽህፈት ቤት፣ የሥራ ኢንተርፕራይዝ ኢንዱስትሪ ልማት ፅሕፈት ቤት፣ የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ፅሕፈት ቤት፣ ኅብረት ሥራ ፅሕፈት ቤት እና የመሬት ልማት አስተዳደር ፅሕፈት ቤት መሆኑ ይታወሳል።

ዋዜማ በክልሎች የተወሰኑ ቦታዎች ባደረገችው ማጣራትም፣ የፋይናንስ ተቋማት እስካሁን ስለደሞዝ ጭማሪው የደረሰን መመሪያ የለም በማለት የዚህን ወር ደሞዝ በነባሩ መደብ እንደሚከፍሉ መናገራቸውን ተገንዝባለች።

የፋይናንስ ቢሮዎቹ ደሞዝ ጭማሪው ተግባራዊ የሚደረግ ከሆነ ከጥቅምት ወር ጀምሮ ያለው ወደፊት ሊከፈል ይችላል የሚል ምላሽ እንደሰጧቸውም የጠየቅናቸው የመንግሥት ሠራተኞች ነግረውናል።

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የሚኖሩ አንድ የመንግሥት ሰራተኛ ነባሩ የጥቅምት ወር ደሞዝ እንደተከፈላቸው ገልጸው፣ ጭማሪው የሰራተኞች መረጃ ወደ ዞን ተልኮ ክልል ከደረሰ በኋላ ኅዳር ላይ ሊመጣ ይችላል የሚል ግምት እንዳላቸው ነግረውናል።

የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ በጀቱን ለክልሎች ልከናል በማለት ክፍያ ያልተፈጸመው ክልሎች የሚያጣሩት ነገር ኖሯቸው ሊሆን እንደሚችል ለዋዜማ ተናግረዋል።  ከጥቅምት ጀምሮ ያለውን የደሞዝ ጭማሪም ወደፊት ሊከፍሉ እንደሚችሉም ተናግረዋል።

የገንዘብ ሚንስትር አህመድ ሽዴ ጥቅምት 09/2017 ዓ. ም ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ አዲሱ የመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪ ከጥቅምት ወር ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን ገልጸው ነበር።
ሚንስትሩ፣ የደመወዝ ጭማሪውን ተግባራዊ ለማድረግ የገንዘብ ሚንስቴር እና ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኹሉንም ቅድመ ዝግጅቶች አድርገዋል ብለውም ነበር።

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ በተመሳሳይ ባለፈው ሳምንት ለሕዝብ እንደራሴዎች በሰጡት ማብራሪያ ለደሞዝ ጭማሪው 91 ቢሊዮን ብር ስለተመደበ ከጥቅምት ወር ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ማለታቸው ይታወሳል።

#ዋዜማ

@Sheger_press
@Sheger_press
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን 738.2 ሚሊዮን ዶላር ብድር አፀደቀች

የኢትዮጵያ መንግሥት ለጎረቤት ደቡብ ሱዳን 738.2 ሚሊዮን ዶላር ብድር ለማቅረብ ያደረገውን ስምምት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፀደቀ።

ብድሩ ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳንን በመንገድ ለማስተሳሰር የሚውል ሲሆን በዋናነትም ከኢትዮጵያ ድንበር አንስቶ ወደ ደቡብ ሱዳን እስከ 220 ኪሎ ሜትር የሚዘልቅ ነው።

የብድር ስምምነቱ የአምስት አመት የችሮታ ጊዜን ጨምሮ በ10 ዓመት የሚመለስ ነው። ብድሩ የሚመለሰው ባከሽ ወይም በድፍድፍ ነዳጅ ሲሆን ተበዳሪው አገር በድፍድረፍ ነዳጅ የሚመልስ ከሆነ በራሱ ወጪ እስከ ፖርት ሱዳን ድረስ ማቅረብ ይጠበቅበታል።
ሪፖርተር

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
አሜሪካውያን ቀጣይ ፕሬዚዳንታቸውን እየመረጡ ነው
የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እየተካሄደ ነው።

አሜሪካውያንም ቀጣዩን 47ኛ ፕሬዚዳንታቸውን እየመረጡ ሲሆን ከ83 ሚሊየን በላይ መራጮች ድምጻቸውን ሰጥተዋል።

ምርጫው እስከሚጠናቀቅ ድረስም መራጮች ድምጻቸውን የሚሰጡ ሲሆን፥ በዋናነት የየትኛው ፓርቲ መራጮች እንደሆኑ ባልለየላቸውና በሚዋዠቅ የመራጭነት ሚና ባላቸው ሰባት ግዛቶች የሚገኘው ድምጽ ከወዲሁ አጓጊ ሆኗል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በአማራ ክልል ያለውን ችግር ለመፍታት መንግሥት ቁርጠኛ ሆኖ ተኩስ አቁም ማድረግ አለበት ሲሉ ፓርቲዎች ገለጹ

በኢትዮጵያ በተለይም በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በየዕለቱ እየተከሰተ ያለዉን የሕጻናትና እናቶችን ሞት ለማስቆም፤ የፌደራሉ መንግሥት ቁርጠኛ በመሆን የተኩስ አቁም ሊያደርግ ይገባል ሲሉ ፓርቲዎች ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባሳለፍነው ሳምንት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመቅረብ ከአባላቱ ለተነሱላቸው ጥያቄ ምላሽ በሰጡበት ወቅት፤ ለሰላም ቁርጠኝነት እንዳለ በመግለጽ "አግዙን" ሲሉ ጥሪ አቅርበው ነበር፡፡

አሐዱም ይህንን የጠቅላይ ሚኒስትሩን ንግግር መነሻ በማድረግ፤ የፖለቲካ ፓርቲዎችን "መንግሥት እውነት ቁርጠኛ ነው ወይ?" ሲል ጠይቋል፡፡

የእናት ፓርቲ አባል አቶ ጌትነት ወርቁ "መንግሥት የተኩስ አቁም ማድረግ አለበት" ያሉ ሲሆን፤ 'ቁርጠኛ መሆን አለበት' ሲባልም "በሌላው ወገን ያሉትም ጦር በማዉረድ ወደ ሌላ አሸናፊ መንገድ ለመምጣት ቁርጠኛ መሆን አለባቸው" ብለዋል፡፡

"መንግሥት ለሰላም ቁርጠኛ ነኝ እያለ ይናገር እንጂ በእውነት መሬት ላይ የወረደ የተተገበረ ነገር ግን ማግኘት አይቻልም" ያሉት ደግሞ፤ የነፃነትና እኩልነት ፓርቲ የአደረጃጀትና አቅም ግንባታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙባረክ ረሽድ ናቸው፡፡

"አሁንም ግጭት ውስጥ ነው የምንገኘው" ያሉት አቶ ሙባረክ፤ "ለሰላም ዝግጁ የሆነ አካል ቢያንስ ወደ ሰላም የሚያመጡ አስቻይ ሁኔታዎችን መፍጠር አለበት" ብለዋል፡፡

ይሁን እንጂ የሰላም ፍላጎት መታየቱ በራሱ ግን የሚያስደስትና አንድ ደረጃ ችግሩን አምኖ የሰላም ጥሪ ማድረጉ በበጎ የሚወሰድ መሆኑን ፓርቲዎቹ ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጥሪያቸው 'እናንተም አግዙ' የሚል ጥሪ ስለማድረጋቸው በሚመለከት ሀሳባቸውን የሰጡት ፓርቲዎቹ፤ "ችግሩ ከእኛም ከመንግሥትም በላይ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል" ብለዋል፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት መካሄዱ የሚታወስ ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰላም ፀጥታ ዙሪያ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሳላቸው ጥያቄ መንግሥታቸው "ከኃይል ይልቅ ሰላም እጅግ በጣም አዋጭ ነው" ብሎ እንደሚያምን መናገራቸው ይታወሳል፡፡

አሃዱ ራዲዮ

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በሸገር ከተማ በዛሬው እለት በደረሰ የእሳት አደጋ እናት ከስድስት ወር ልጇ ጋር ህይወታቸው አለፈ

ጥቅምት 26 ቀን 2017 ዓ.ም በሸገር ከተማ ፉሪ ክፍለ-ከተማ በመስሪያና መሸጫ ሼድ ላይ በተነሳ የእሳት አደጋ እናት ከስድስት ወር ልጇ ጋር ህይወቷ  ማለፋን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

በእሳት አደጋዉ በሼድ ዉስጥ ካሉ  ሱቆች መካከል ስድስት የንግድ ሱቆች ተቃጥለዋል። የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር ሶስት የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪና ሁለት አምቡላንሶች ከሰላሳ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጋር የተሰማራ ሲሆን የእሳት አደጋዉ ወደሌሎች ንግድ ሱቆች ተዛምቶ ተጨማሪ ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠር መቻሉን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።

ከንግድ ሱቆቹ መካከል በአንደኛዉ ነዳጅ በፕላስቲክ ጠርሙስ በችርቻሮ የሚሸጥበት ሱቅ በመሆኑ ለሽያጭ የተዘጋጀዉ ነዳጅ ለቃጠሎው መከሰትና መባባስ ምክንያት ሆኗል።

ከስድስት ወር ልጇ ጋር ህይወቷ ያለፈችዉ እናት በእሳት አደጋዉ ከተቃጠሉት የንግድ ሱቆች ዉስጥ በአንደኛዉ ሱቅ የንግድ ስራ ላይ የነበረች መሆኗን አቶ ንጋቱ ጨምረው ለብስራት ተናግረዋል።

ነዳጅ ማከማቸትም ሆነ መሸጥ ያለበት በተፈቀደለትና የአደጋ ደህንነት መስፈርትን ባሟሉ የነዳጅ መሸጫ ጣቢያዎች ዉስጥ ብቻ መከናወን ያለበት በመሆኑ በተለያዩ የንግድ ሱቆች ዉስጥ ነዳጅ ማከማቸትም ሆነ መሸጥ መሰል አደጋዎችን የሚያስከትል በመሆኑ የንግድ ፈቃድ የሚሰጡ አካላት ተገቢዉን ቁጥጥር ማድረግ ይኖርባቸዋልም ሲሉ አክለዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ልጄ ሆይ ልብህን ስጠኝ ያለህ እግዚአብሔር ቸርነትህን ይጠብቃል!
ከአለም ርቀው ስለፍቅሩ ሲሉ በየበርሀው እና በየገዳማቱ ባዕታቸውን ቀልሰው ሌት ከቀን ለሚማፀኑልን ሰርክ የሚጸልዩ ስለ ዓለሙ ምልጃ የሚተጉ የሚያነቡ  ገዳማውያን የልጆቻቸውን እጅ ናፍቀው ተጨነቁ ቢባል እግዜሩስ እንዴት ያየናል?!
ስለእኛ ለነፍሳችን በመድከም በመንፈሳዊ ህይወት መምህር የሚሆኑን የክርስቶስ እውነተኛ ሙሽሮች ገዳማውያን፣ ዛሬ ላይ ባለው  ሰው ሰራሽም ሆነ ተፈጥሯዊ ነባራዊ ሁኔታዎች የሚቀመስ እፍኝ ቆሎም ጠፍቶ ረሀብ ጥማቱ በብርቱ እየተፈታተናቸው ለጾም ለጸሎት መቆም ተስኗቸው  ከተፈጥሮ ጋር ግብ ግብን ይዘዋል።
እግዚአብሔርን የምትወዱ እርሱን ለመምሰል የምትተጉ ብጹዓን  ጥቂት በመራራት የቸርነት እጃችሁን ለእነዚህ  ገዳማውያን በመዘርጋት በረከተ እግዚአብሔርን ታገኙ ዘንድ እንጠይቃቹኋለን፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
                       
በአዲስ አበባ ለስኳር ህመምተኞች የሚያገለግለውን ኢንሱሊን ለተጠቃሚዎች ማቅረብ እንዳልቻሉ ፋርማሲስቶች ተናገሩ

የስኳር ህመም በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን በማሳደግ እድሜ ልክ የሚዘልቅ የህመም ስያሜ ያለው ነው ። በዚህም መሠረት የስኳር ህመምተኞች በተገቢው ሰዓት ኢንሱሊን መውሰድ አለባቸው ፡፡ ይሁን እንጂ ከፍተኛ የሆነ የኢንሱሊን እጥረት እንዳለ ተነግሯል ።

በተለይም አስተያየታቸውን ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን የተናገሩ የመድሃኒት መደብር ባለቤቶች ኢንሱሊን መጥፋቱን ይናገራሉ ። አስተያየታቸውን ከሰጡት መካከል በመድኃኒት መደብሬ ውስጥ የሚገኘውን አነስተኛ ኢንሱሊን ለተጠቃሚዎች እንዲዳረስ በሚል ለአንድ ሰው አንድ ኢንሱሊን እየሸጥኩ እገኛለሁ ብለዋል ።

ፋርማሲስቱ አክለውም ምንም እንኳን ከተማ ወስጥ ኢንሱሊን እንደጠፋ ባውቅም ሃላፊነት ስላለብኝ ዋጋ ጨምረን ብዛት እንውሰድ ቢሉኝም ይህንን ከማድረግ ተቆጥቤያለሁ ብለዋል ። ከስኳር ህመምተኞች መካከል አነስተኛው ቁጥር የሚይዙት የአይነት አንድ ህመምተኞች ሲሆኑ ሰውነታቸው ኢንሱሊን ማመንጨት እንደማይችል ተመላክቷል። በተጨማሪም በኢትዮጵያ ውስጥ አይነት አንድ የሚባለው የስኳር ህመም በህፃናት እና ወጣቶች ላይ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ይገኛል።

አይነት ሁለት በሚባለው የስኳር ህመም የተያዙ ሰዎች ደግሞ ሰውነታቸው በተገቢው መንገድ ኢንሱሊን አያመርትላቸውም ፡፡ ስለሆነም የስኳር ህመምተኞች በተገቢው ሰዓት ኢንሱሊን መውሰድ ቢኖርባቸውም የምርት እጥረት ማጋጠሙ አሳሳቢ ያደርገዋል ።የስኳር ህመምተኞች ለልብ ችግር የመጋለጥ አዝማሚያቸው ከፍተኛ በመሆኑ የደም ግፊታቸውንና የኮሌስትሮል መጠናቸውን በየጊዜው መከታተል እንዳለባቸው የዘርፉ ባለሙያዎች ይመክራሉ ።

የተለመዱ የስኳር ህመም ምልክቶች ቶሎ ቶሎ መሽናት፣ ብርቱ የውሃ ጥም እና ረሃብ፣ ክብደት መጨመር ወይም ያልተለመደ መቀነስ፣ ድካም፣ የማይድን ቁስል የእግር እና እጅ ጣቶች መደንዘዝ ናቸው ፡፡ በኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመሩ እንደሆነና 43 በመቶ የሞት ምጣኔን የሚይዙት ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች መሆናቸውን ጤና ሚኒስቴር ማስታወቁ ይታወሳል ።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቤቶን እና ቢሮዎን እናሳምርልዎ

ሳንፎርድ ፈሪኒቸር

👉🏼 ለልጆዎ ምቾት ጥራት ያላቸው አልጋዎች፣
👉🏼 ለቤትዎ ዘመናዊ እና ውብ ቲቭ ስታንዶችን፣
👉🏼 ለቢሮዎ ውበትን ከጥራት ጋር ያዋሃዱ ጠረጴዛ እና ወንበሮች፣
👉🏼 እንዲሁም ለኪችኖ ፤ በፈለጉት ድዛይን የሚያምሩ ኪችን ካቢኔቶችን፣ በተመጣጣኝ ዋጋ ሰርተን እናስረክብልዎ!!!

ወርክ ሾፕአችንን ጦር ሀይሎች ወደ ቤተል በሚወስደው መንገድ ድሪም ታወር አጠገብ ያገኙታል።

ለበለጠ መረጃ፡ 0978777775/0976777775 አሁኑኑ ይደውሉ!
Forwarded from Sheger Press️️
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቤቶን እና ቢሮዎን እናሳምርልዎ

ሳንፎርድ ፈሪኒቸር

👉🏼 ለልጆዎ ምቾት ጥራት ያላቸው አልጋዎች፣
👉🏼 ለቤትዎ ዘመናዊ እና ውብ ቲቭ ስታንዶችን፣
👉🏼 ለቢሮዎ ውበትን ከጥራት ጋር ያዋሃዱ ጠረጴዛ እና ወንበሮች፣
👉🏼 እንዲሁም ለኪችኖ ፤ በፈለጉት ድዛይን የሚያምሩ ኪችን ካቢኔቶችን፣ በተመጣጣኝ ዋጋ ሰርተን እናስረክብልዎ!!!

ወርክ ሾፕአችንን ጦር ሀይሎች ወደ ቤተል በሚወስደው መንገድ ድሪም ታወር አጠገብ ያገኙታል።

ለበለጠ መረጃ፡ 0978777775/0976777775 አሁኑኑ ይደውሉ!
በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላን አዲስ አበባ ሲደርስ የተደረገ የአቀባበል መርሐ ግብር በምስል

@Sheger_press
@Sheger_press
ጊዜው የመረጃ ነው ❗️
ለዚህ ደግሞ እውን የቴሌግራም ቻናል ልጠቁማችሁ ሁላችሁም የምትመርጡት ቻናል ይሆናል ወቅታዊ ፤ትኩስና የጦርነቱን ድባብ የሚዘግብ ምርጥ ቻናል 👇👇👇
https://www.tg-me.com/+gPveFwjiiXdiMDE0
https://www.tg-me.com/+gPveFwjiiXdiMDE0
መረጃ‼️

መከላከያ ሰራዊቱ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ከፍተኛ  አመራርን ገድያለሁ አለ

የኢፊዴሪ መከላከያ ሰራዊት የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሸኔ  አመራርን  የነበሩትን   ጃል እንሰርሙ ከነግብረ አበሮቹ  ደምስሻለሁ ሲል ጃል ኦብሳ የተባለው ደግሞ በቁጥጥር ስር አዉያለሁ አለ ፡፡

ሰራዊቱ ይሄን ያለዉ የመከላከያ ሰራዊቱ 6ኛ ዕዝ ዋልታ ክፍለጦር በወረ ጃርሶ ወረዳ በአቡ ኬኮ ቀበሌ በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ላይ ወሰድኩት ባለዉ ጥቃት ነዉ ፡፡

የማዕከላዊ ዕዝ ክፍለ ጦር በተሰማራበት የግዳጅ ቀጠና አሸባሪው የሚሉትን  የኦነግ ጦር  በማሳደድ የመደምሰስ ስራ እየሰራ መሆኑን  የክፍለ ጦሩ አዛዥ ኮሎኔሌ ደጀኔ ፈይሳ ተናግረዋል ፡፡

ኮሎኔሉ ይሄን ይበሉ እንጂ ኦነግ ሸኔ በቅርቡ ብዛት ያላቸዉን የመንግስት የስራ አመራሮች የፀጥታ ሀይሎች እንዲሁም ንፁሃን ገበሬዎችን ከአዲስ ቅርብ እርቀት መግደሉ አይዘነጋም ፡፡

Sheger Press


@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በሀዲያ ዞን በጣለ ከባድ ዝናብ በሰብል እና በመኖሪያ ቤት ላይ ጉዳት ደረሰ

በሀዲያ ዞን ሸሾጎ ወረዳ በጣለ ወቅቱን ያልጠበቀ ከባድ ዝናብ በወረዳዉ የሚገኘዉ አብዛኛዉ ምርት ከጥቅም ዉጭ መሆኑ ተነግሮል ፡፡

አንኳር መረጃ ያነጋገረቻቸዉ የወረዳዉ አስተዳዳሪ እንዳሉት  ከ16 ሺህ በላይ አባዎራዎች ሙሉ በሙሉ ሰብላቸዉ ወድሞል ብለዋል ፡፡

ነዋሪዎቹም ጎርፉ በመሙላቱ እና መኖሪያ ቤታቸዉ ጉዳት ስለደረሰበት መፈናቀላቸዉ ተገልፆል ፡፡

ወገኖቻችን ሀብት ንብረታቸው ወድሟል
መንገድ ላይ ወድቀዋል

እባካችሁ ሼር አድርጉት ለሚመለከተው አካላት🙏

@Sheger_press
@Sheger_press
2024/11/06 01:26:27
Back to Top
HTML Embed Code: