Telegram Web Link
የደብረፂዮኑ የህወሓት ክፋይ ዛሬ ባወጣው መግለጫ "ይቅርታ ጠይቀው ወደ ፓርቲው እንዲቀላቀሉ የሰጠኋቸውን የአንድ ወር ጊዜ ሳይጠቀሙበት ወሩ በመገባደዱ ከፓርቲው አባርሬያቸዋለው" ያላቸውን ሰዎች ስም ዝርዝር ይፋ አድርጓል !

ከተባረሩት ውስጥ አቶ ጌታቸው ረዳም ይገኙበታል።

@sheger_press
@sheger_press
ጥቆማ‼️

ቴሌግራምን በመጠቀም ብቻ በርካቶች በርካታ ብር በማግኘት ላይ ናቸው።

እናንተም ይህን ቻናል በመቀላቀል ሙሉ ትምህርት ማግኘት ትችላላቹ።

Join us👇👇👇👍
https://www.tg-me.com/+fzeZ2gn56UE3NTI0
https://www.tg-me.com/+fzeZ2gn56UE3NTI0
አስቸኳይ ስብሰባ በሶማሊያ እየተካሄደ ነው‼️

የሶማሊያ የፌደራል መንግስት ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ ፣የፓርላማ አፈ ጉባኤ ሼክ አዳነ ማዶቤ እና ጠቅላይ ሚንስትር ሃምሳ አብዲ ባሬ አስቸኳይ ስብሰባ እያካሄዱ መሆኑን ዘገባዎች አመልክተዋል። ይህ ስብሰባ በሶማሊያ እና በደቡብ ምዕራብ አስተዳደር መካከል ባለው ውጥረት ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል።

ዛሬ ከሰአት በኋላ የደቡብ ምዕራብ ፕሬዝዳንት አብዲካሲስ ላፍታጋሬን እና የሶማሊያ ፓርላማ አፈ-ጉባኤ ሼክ አዳነ ማዶቤ በስልክ ተወያይተው የነበረ ቢሆንም ያለስምምነት መጠናቀቁ ተዘግቧል።

መረጃው እንደሚያመለክተው ሼክ አዳነ ማዶቤ ላፍታጋሪን ወደ ሞቃዲሾ እንዲመጡ ቢጠይቁም ላፍታጋሬን ጥያቄውን ውድቅ ማድረጉን ነው የተገለፀው።

በውይይታቸውም ሁለቱ ባለስልጣናት እላፊ ቃላት መለዋወጣቸው የተነገረ ሲሆን የሁለቱ ወገኖች ግጭት ምን ያህል የሰፋ እንደሆነ ያሳያል ተብሏል::

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ዜና ዕረፍት‼️

ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

ከንቲባ አዳነች በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት የሀዘን መልዕክት ሀገራቸውን በሞያቸውና በሚፈለግባቸው መስክ ሁሉ ሲያገለግሉ በኖሩት ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገልጸዋል።

ፈጣሪ ነብሳቸውን በአጸደ ገነት ያኑር፤ ለቤተሰቦቻቸው፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸዉ መጽናናትን እመኛለሁ ብለዋል።

በየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር) በፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት በዋና ዳሬክተርነት ሲያገለግሉ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ፍርድ ቤቱ እነ ዮሀንስ ዳንኤል የጠየቁትን የዋስትና መብት ከለከለ

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተረኛ የግዜ ቀጠሮ የወንጀል ችሎት እነ ዮሀንስ ዳንኤል የጠየቁትን የዋስትና መብት ከልክሏል።

ተጠርጣሪዎቹ የዋስትና መብት እንዲፈቀድላቸው በጠበቆቻቸው አማካኝነት ጠይቀው የነበረ ሲሆን፤ ፍርድ ቤቱም በዛሬው ችሎት የዋስትና መብቱን ከልክሏል።

ችሎቱ የክስ መዝገቡን ለመመልከት ለጥቅምት 4 ቀን 2017 ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል፡፡

የፍትህ ሚኒስቴር አቃቤ ህግ ዳንኤል ዮሐንስን ጨምሮ በስድስት ግለሰቦች ላይ ሶስት ክሶችን መመስረቱ ይታወሳል፡፡

@sheger_press
@sheger_press
📍ጎንደር ከተማ

ከሌሊት ጀምሮ በጎንደር አንዳንድ የከተማው ክፍል አካባቢዎች በመከላከያ ሰራዊትና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ውጊያ መኖሩን ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡

ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች እንዳሉት በጎንደር ከተማ “ገንፎ ቁጭ”ና ማራኪ በተባሉ አካባቢዎች ከባድ ጦር መሣሪያ ጭምር ከሌሊት ጀምሮ እየተተኮሰ ነው፡፡

አንድ የከተማዋ ነዋሪ እርሳቸው ባሉበት ቀበሌ 18 በሚባለው አካባቢ የቀላል መሣሪያ ድምፅ እንደሚሰማ አመልክተው፣ ራቅ ብሎ ደግሞ የከባድ መሣሪያ ድምፅ ይሰማል ብለዋል፡፡ ሌላ ነዋሪ በተመሳሳይ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች የተኩስ ልውውጥ የሚመስል ድምጽ ይሰማል ብለዋል፡፡ ትናንትና በአዘዞና በጎንደር ሆስፒታል አካባቢ ተኩስ እንደነበርም ገልጠዋል፡፡ የዛሬው ከባድ እንደሆነ ያመለከቱት እኚሁ ነዋሪ የከባድ መሣሪያው የተኩስ ድምፅ (እርሳቸው እንደገመቱት የመድፍ ድምፅ) መሬት ያንቀጠቅጣል ሲሉ ነው የተናገሩት፡፡ ሱቆችና የከተማ ውስጥ እንቅስቃሴዎች በከተማዋ የተገቱ ቢሆንም ፒያሳ በተባለው የከተማው ክፍል የተወሰኑ ባለሦስት እግር ተሸከርካሪዎች ሲንቀሳቀሱ ማየታቸውን አስረድተዋል፡፡

ባለፉት ሁለት ሳምንታት በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ዮሐንስ፣ ሽንፋ፣ ኮኪትና ገንዳ ውኃ ዙሪያ ተመሳሳይ ውጊያዎች በመንግስትና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ሲካሄዱ እንደነበር መዘገቡ ይታወሳል፡፡(DW-Amharic)

@sheger_press
@sheger_press
መንገድ መዝጋት   ህዝብን ለመከራና ለስቃይ የሚዳርግ ተቀባይነት የሌለዉ ተግባር ነዉ ሲሉ የመንዝ እና አካባቢዉ ነዋሪዎች ገለፁ

አዲስአበባን ከመንዝ የሚያገናኘዉ ዋና መስመር ከተቆረጠ አምስት ቀን እንደሆነ የገለፁት ነዋሪዎች ህዝቡ በከፍተኛ ስቃይ እና እንግልት ዉስጥ መሆኑን አስረድተዋል ፡፡

እንደሚታወሰው በአልን አስመልክቶ ከሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ወደ መንዝ እና ሸዋ የተለያዩ ቦታዎች ተወላጆች መግባታቸዉ የሚታዉስ ሲሆን አስቸኮይ የስራ ፍቃድ ያላቸዉ ዉስብስብ የጤና ክትትል ያላቸዉ እና ለህዝቡ መሰረታዊ ፍጆታ የሚያመላልሱ ተሽከርካሪዎች ባሉበት መንገድ መዘጋቱ ህዝብን እያማረረ  መሆኑ ይነሳል ፡፡ ( SNN)

@sheger_press
@sheger_press
""ወልዲያ"‼️

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን በወልዲያ ከተማ የተከሰተው የኮሌራ ወረርሽኝ በፍጥነት እየተዛመተ መሆኑ ተነገረ

<<ወረርሽኙ በፍጥነት በመዛመቱ 85 ሰዎች ታመው በሦስት ጤና ተቋማት ሕክምና እየተደረገላቸው ሲሆን ከታማሚዎቹ መካከል 11 ያህሉ በፅኑ መታከሚያ ከፍተኛ ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።እስከ ትናንት ማክሰኞ መስከረም 7 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ የአንድ ሰው ሕይወት አልፏል።

የኮሌራ በሸታው ጳጉሜን 4 ቀን 2016 ዓ.ም. በእቴጌ ጣይቱ ብጡል ክፍለ ከተማ አድማስ ባሻገር ተክለ ሃይማኖት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው የተከሰተው።

በሚመለከተው አካል ርብርብ ካልተደረገ ውጤቱ ጥሩ አይሆንም፡፡>>
የወልዲያ ከተማ ጤና መምርያ ሜዲካል ኦፊሰር ሲስተር ዘሬ በቀለ ለሪፖርተር ከተናገሩት የተወሰደ

@sheger_press
@sheger_press
በአማራ ክልሰ በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ በፋኖ ሀይሎች እና በመንግሥት የፀጥታ ሀይሎች ውጊያ በርካታ ሰዎች መሞታቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት አስታወቁ::

በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ከተማ በመንግስትና በፋኖ ሀይሎች መካከል ከትላንት በስተያ በነበረው ግጭት ወደ ደባርቅ አጠቃላይ ሆስፒታል ቆስለው ከገቡት ውስጥ ሁለት ሰዎች ሲሞቱ የሶስት አመት ህፃንን ጨምሮ 28 ሰዎች መቁሰላቸውን የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አስታውቀዋል፡፡

ስራ አስኪያጁ አቶ አለ አምላክ ሲናገሩ ከሟቾቹ ውስጥ አንድ ታጣቂና አንድ ሲቪል ናቸው ብለዋል ::

ወደ ሆስፒታል ሳይደርሱ የህፃኑን አባት ጨምሮ ከ7 በላይ ስዎች መሞታቸውን አክለው ገልፀዋል፡፡
VOA

@sheger_press
@sheger_press
መፈንቅለ መንግሥት‼️
መፈንቅለ መንግስት ሊያደርግብኝ ነው>>የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር‼️
የደብረፅዮን ቡድን ለስልጣኑ ሲል የትግራይ ህዝብ ላይ ተደጋጋሚ ክህደት እየፈፀመ ይገኛል ሲል የጌታቸው ረዳ ቡድን ባወጡት መግለጫ ገልጸዋል።

አባላቱ አክለውም የትግራይ ህዝብ ላይ የተፈፀመውን ጄኖሳይድ ለስልጣኑ ሲል ወደ መካድ ደርሷል ሲል ከሰዋል። 

የጌታቸው ቡድን መግለጫው የደብረፅዮን(ዶ/ር) ቡድን ማንኛውም አካል ላይ ውሳኔ የማሳለፍ ሆነ እርምጃ የመውሰድ ፖለቲካዊ፣ ሞራላዊ እና ህጋዊ ስልጣን እንደሌለው ለህዝባችን እና ለአባላቶቻችን ማሳወቅ እንወዳለን ብሏል።

የአቶ ጌታቸው ቡድን ከፌደራል መንግስት ጋር የህወሓት ህጋዊ ሰውነትን ለመመለስ በምናደርገው ፓለቲካዊ ድርድር መላው አባላችን እና ደጋፊ ከጎናችን እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።

@sheger_press
@sheger_press
በአማራ ክልል በደቡብ ጎንደር ዞን የፋኖ ሀይሎች አምስት ወረዳዎችን መያዛቸውን ተከትሎ ፖሊሶች፣ ሚሊሻዎችና የወረዳና ቀበሌ አመራሮች ወረዳዎቹን ለቀው ከዞኑ ዋና መቀመጫ ደብረታቦር መግባታቸውን ዋዜማ ሬዲዮ ዘግባለች።

የፋኖ ሀይሎች ከጳጉሜ መጨረሻ ጀምሮ ባሉት ቀናት በተቆጣጠሯቸው ታች ጋይንት፣ እስቴ፣ አንዳቤት፣ መካነእየሱስ፣ ስማዳ እና ስዴ ሙጃ ወረዳዎች፣ የራሳቸውን አስተዳደራዊ መዋቅሮች የመዘርጋትና ግብር የመሰብሰብ ሙከራ እያደረጉ እንደኾነም በዘገባው ተካቷል።

@sheger_press
@sheger_press
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🏃‍♂️🏃🏃‍♂️በመሃል ፒያሳ ሊሴገብረማርያም ት / ቤት ዘመናዊ ቤት ከ ቴመር ፕሮፐርቲ

👉ስቱዲዮ .....48 and 46
ባለ አንድ መኝታ.....66...64....71...75
ባለ ሁለት መኝታ.....75....78...71....99...92...91
ባለ ሶስት .....111....106
🏠 ተጨማሪ የንግድ ሱቅ ፒያሳ አድዋ ሙዝየም ፊትለፊት በሚኒሊክ አደባባይ ከ12 ካሬ እስከ 22 ካሬ
ለወርቅቤት #ቡቲክ #ፋርማሲ #office .....የሚውሉ

💴 483,000 ብር ቅድመ ክፍያ ብቻ የቤት ባለቤት ይሁኑ!!!

ለተጨማሪ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡ https://www.tg-me.com/+33kkNORhQ_JmMDlk
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ ፡
☎️0904657777/0902597777 ያግኙን
ለታጋቾች ማስለቀቂያ ብር ለመክፈል የሄዱ ግለሰቦች እራሳቸው በታጣቂዎች መታገታቸው ተሰማ‼️
ከሳምንት በፊት በአርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ 38 ሰዎች በጉዞ ላይ እያሉ በሸኔ ታጣቂዎች ታግተው መወሰዳቸው ይታወሳል፡፡

ታጣቂዎቹ ታጋቾችን ለመልቀቅ ከ250ሺህ እስከ 1 ሚሊየን ብር ድረስ የማስለቀቂያ ገንዘብ እንዲከፈላቸው መጠየቃቸውን ተከትሎም አንዳንድ የታጋች ቤተሰቦች ገንዘቡን ለመክፈል ወደ ተባሉበት ቦታ ማቅናታቸውን የሚገልጹት የመረጃ ምንጮች ገንዘብ አቀባዮቹ በቦታው ሲደርሱ ግን እራሳቸው በታጣቂዎቹ መታገታቸውን ነው የገለጹት ፡፡

‹‹ካሉበት ቦታ ሆነው ስልክ ደውለው እኛም ታግተናል›› አሉን የሚሉት አንድ ምንጭ የታገቱትን አስፈትተው ይመጣሉ ብለን ተስፋ ስናደርግ እነሱም መያዛቸው ሌላ ጭንቀት ፈጥሮብናል ይላሉ፡፡

ታጋቾችን ለማስለቅ የሚያስችል ገንዘብ አሁን ላይ እንደሌላቸው የሚገልጹት እነዚህ የታጋች ቤተሰቦች የቀደሙትንም ለማስፈታት በገበያ ቦታ፣ በእድርና በመሰል ማህበራዊ አደረጃጀቶች በኩል ጥረት ተደርጎ ገንዘቡ እንደተሰበሰበ ገልጸዋል፡፡

መንቀሳቀስና መስራት ውድ እየሆነ መጥቷል፤ መንግስትም የህግ የበላይነት የሚባለውን መሰረታዊ ግዴታውን ሊወጣ ይገባል በማለትም አካባቢው ላይ የሚታይ ስጋት አሁንም እንዳለ ነው ያስታወቁት፡፡

በሌላ በኩል ታግተው ከነበሩ 38 ሰዎች ውስጥ 5 ያህል ታጋቾች ማምለጣቸውንም እነዚህ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ ምንጮች አሁን ላይ ያመለጡት ታጋቾች በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ ግን ተጨማሪ መረጃዎችን ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡

የሸኔ ታጣቂ ቡድኖቹ በአርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ከጎቤሳ ከተማ ወደ ተለያዩ ከተሞች በመጓዝ ላይ የነበሩ አጠቃላይ 8 የህዝብ ማመላለሻዎችን ጋለማ በሚባል ጫካ ውስጥ በማስቆም 38 ሰዎችን በመምረጥ ማገታቸው የሚታወስ ነው።

አዲስ ማለዳ

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ሰበር
አርቲስት አዜብ ወርቁ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለች። ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ አርቲስቷ በ3ኛ ፖሊስ ጣቢያ እንደምትገኝ የፖሊስ ምንጮች ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ይዘን እንመጣለን።
አርቲስቷ ሰሞኑን "ልማት የሰውን ልጅ ሲያፈርስ በዓይኔ አየሁት!" የሚል ጽሁፍ በማህበራዊ ሚዲያዎች ካጋራች በኋላ ጽሁፉ መነጋገሪያ ሆኖ እንደነበርና በኋላም ከማህበራዊ ገጿ ጽሁፉን ማንሳቷን ማስታወቋ አይዘነጋም።

ምንጭ ዘሀበሻ

@sheger_press
@sheger_press
ተፈታለች‼️
ደራሲ እና አርቲስት አዜብ ወርቁ መታሰሯ ከሰዓታት በፊት ተዘግቦ ነበር‼️
ዛሬ በቁጥጥር ስር ውላ የነበረችው አዜብ ወርቁ ለግማሽ ቀን ያህል በእስር ከቆየች በኋላ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ተለቃለች።
አርቲስቷ ሰሞኑን "ልማት የሰውን ልጅ ሲያፈርስ በዓይኔ አየሁት!" የሚል ጽሁፍ በማህበራዊ ሚዲያዎች ካጋራች በኋላ ጽሁፉ ብዙዎች ተጋርተውት እንደነበርና በኋላም ከማህበራዊ ገጿ ጽሁፉን ማንሳቷን ማስታወቋ አይዘነጋም።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ፕሪሚየር ሊጉ መቐለ 70 እንደርታ እና ሀዲያ ሆሳዕና በሚያደርጉት ጨዋታ ዛሬ ይጀመራል

የ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መቐለ 70 እንደርታ እና ሀዲያ ሆሳዕና በሚያደርጉት ጨዋታ ዛሬ ይጀመራል፡፡

በሊጉ የመክፈቻ ጨዋታ ሁለቱ ቡድኖች የሚያደርጉት መርኃ ግብር 10 ሰዓት ላይ በድሬዳዋ ስታዲየም ይካሄዳል።

በዛሬው የጨዋታ መርኃ ግብር ከምሽቱ 1 ሰዓት አርባ ምንጭ ከተማ ከድሬዳዋ ከተማ የሚከናውኑት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።

በዘንድሮው ፕሪሚየር ሊግ መቐለ 70 እንደርታ፣ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ እና ስሑል ሽረ ዳግም ወደ ውድድር መመለሳቸውን ተከትሎ በዚህ የውድድር ዘመን በ19 ክለቦች መካከል ውድድር ተደርጎ 5 ክለቦች ወደ ከፍተኛ ሊግ እንደሚወርዱ ተጠቅሷል።

ፕሪሚየር ሊጉ በቀጣይ ዓመት ወደነበረው ፎርማት የሚመለስ ሲሆን፤ በዚህ ዓመት ግን በየሳምንቱ አንድ አራፊ ቡድን ኖሮ ውድድሩ በ19 ክለቦች መካከል እንደሚከናወን የሊጉ አክሲዮን ማህበር መረጃ ያመለክታል።

@sheger_press
@sheger_press
ንግድ ባንክ ቪዛ ካርድን በአለም አቀፍ ደረጃ መጠቀም የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ!!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደንበኞቹ ካርዶችን በአለም አቀፍ ደረጃ መጠቀም የሚያስችላቸዉን ስምምነት ከቪዛ ኢንተርናሽናል ጋር ተፈራረመ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳት አቤ ሳኖ እንደገለጹት ፤ባንኩ ከቪዛ ኢንተርናሽናል ጋር ለረጅም አመታት የዘለቀ አጋርነት ያለዉ ሲሆን የሚጠቀምባቸዉ ካርዶችም የቪዛ ኢንተርናሽናል ናቸው።

በዛሬዉ ዕለት ባንኩ ያደረገው ስምምነት ወደ ዉጭ የሚጓዙ ደንበኞች በውጭ ምንዛሬ በአለም አቀፍ ደረጃ መጠቀም የሚያስችላቸው ነው ብለዋል። ስምምነቱ ለአምስት አመት የሚቆይ ሲሆን ቪዛ ለባንኩ ድጋፍ እንደሚያደርግም ገልጸዋል።

@sheger_press
@sheger_press
News‼️

ኢትዮጵያ ወደ ሶማሊያ ፑንትላንድ ግዛት የምታጓጉዘው ያልተፈቀደ የጦር መሳሪያ ዝውውርን በጽኑ አወግዛለሁ አለ

ይህ ድርጊት በሶማሊያ ሉዓላዊነት ላይ ከፍተኛ ጥሰትን የሚፈጥር እና ከባድ የብሄራዊ እና ክልላዊ ደህንነት አንድምታዎችን ይፈጥራል ብሏል።
ከኢትዮጵያ ወደ ፑንትላንድ የጦር መሳሪያ ሁለት መኪናዎች ያለምንም ዲፕሎማሲያዊ ተሳትፎ እና ፍቃድ የጦር መሳሪያ ሲያጓጉዙ በሰነድ የተገኙ መረጃዎች ያረጋግጣሉ፣ ይህም የሶማሊያን የግዛት ሉዓላዊነት በግልፅ መጣሱን ያሳያል ብሏል። የሶማሊያ መንግስት ኢትዮጵያ ለአለም አቀፍ ህግጋት የምታደርገውን ጥረት እና ለቀጣናው መረጋጋት ያላትን ቁርጠኝነት በእጅጉ እንዳሳሰበው ገልጿል። አሁን በሁለቱ ሀገራት መካከል የተፈጠረው ውጥረት በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እንዲፈቱ ቁሮጠኛ ነን ብሏል።

@sheger_press
@sheger_press
2024/11/19 23:39:32
Back to Top
HTML Embed Code: