Telegram Web Link
በእነ ዳንኤል ዮሐንስ ላይ አቃቤ ህግ ክስ መሰረተ

የፍትህ ሚኒስቴር አቃቤ ህግ ዳንኤል ዮሐንስን ጨምሮ በስድስት ግለሰቦች ላይ ሦሥት ክሶችን መሰረተ፡፡

አቃቤ ህግ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ግለሰቦቹ ላይ የመሰረተው ክስ አውሮፕላንን አላግባብ በመያዝ፣ በማህበራዊ ሚደያ አማካኝነት በቀጥታ በማስተላለፍ መልካም ስም የሚያጎድፍ ተንቀሳቃሽ ምስል በኮምፒዩተር ስርአት አማካኝነት በማሰራጨት እና የመንግስት ሰራተኛ ኦፊሻላዊ የስራ ግዴታውን እንዳይፈፅም መቃወም እና አለመታዘዝ የሚሉ ናቸው፡፡

በሁለቱ ወንጀሎች ሁሉም ሲከሰሱ የመዝገቡ መጠሪያ የሆነው በቲክክቶክ የሚታወቀው ዮሀንስ ዳንኤል በሶስቱም ተከሷል፡፡

ለሁለት ሰአታት ሙሉ ከአውሮፕላን አንወርድም፤ ይከስከስ በማለት ሌሎችም እንዳይወርዱ በማሳደም በቲክቶክ ቀጥታ በማሰራጨት ሳይታገት ታግቻለሁ በማለት በቲክቶክ ስሙ ዮኒ ማኛን ቀጥታ በማስገባት የአየር መንገዱ ስም እንዲጎድፍ አድርጓል የሚለውንም አቃቤ ህግ ዘርዝሮበታል፡፡

@sheger_press
@sheger_press
በአፋሮችና ሶማሌዎች መካከል ሲካሄድ የቆየው የጎሳ ግጭት እንደቆመ ለግጭቱ መፍትሄ ለመስጠት የተቋቋመው ብሄራዊ ኮሚቴ መግለጡን ፋና ብሮድካስት ዘግቧል።

ብሄራዊ ኮሚቴው፣ በግጭት አካባቢዎች በመከላከያና ፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ሥር የኾነ ነጻ ቀጠና እንደተቋቋመና ግጭቶችን ማስቆ እንደተቻለ ኮሚቴው መናገሩን ዘገባው አመልክቷል።

የሰላም ሚንስትር ብናልፍ አንዷለም፣ ከነጻ ቀጣናው ያልወጡ ቀሪ ታጣቂ ኃይሎች ባስቸኳይ እንዲወጡ ማድረግና በአወዛጋቢ አካባቢዎች ሠፈራዎችን ማቆም እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል ተብሏል።

@sheger_press
@sheger_press
#በኦሮሚያ ክልል መቂ ከተማ‼️

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን በመቂ ከተማ ጳጉሜ 2/2016 ዓ.ም በተፈጸመ ጥቃት ቢያንስ የ4 አሽከርካሪዎች ሕይወት ሲያልፍ ከ30 በላይ ተሸከርካሪዎች ደግሞ ጉዳት ማስተናገዳቸውን ከጥቃቱ ያመለጡ እማኞች ተናገሩ፡፡

ጥቃት አድራሾቹ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ታጣቂዎች እንደሆኑ ቢገለፅም ጥቃት ያደረሱት የኦሮሚያ ክልል ልዩ ሀይል መለዮ የለበሱ ናቸው ሲሉ ከጥቃቱ ያመለጡ አሽከርካሪዎች ተናግረዋል።

@sheger_press
@sheger_press
ሚድሮክ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ 400 ሰራተኞቹ ለእያንዳንዳቸው ከ100 እስከ 500 ሺህ ብር ስጦታ አበረከተ

👉 ሼህ መሀመድ ሁሴን አላሙዲን ለሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ሰራተኞችና አመራሮች ምስጋና አቅርበዋል



ሼህ መሀመድ ሁሴን አላሙዲን የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ሰራተኞች እና አመራሮች ላከናወኑት ተግባር ምስጋና አቅርበዋል።

የሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በዛሬው ዕለት በሚሊኒየም አዳራሽ የላቀ አፈጻጸም ላሳዩ አመራሮችና ሰራተኞቹ እውቅና ሰጥቷል።

በዚሁ ወቅት ሼህ መሀመድ ሁሴን አላሙዲን በዙም ባስተላለፉት መልዕክት፤ የተቋሙ ሰራተኞች እና አመራሮች ላከናወኑት ተግባር ምስጋና አቅርበዋል።

ሼህ መሀመድ ሁሴን አላሙዲን በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡም ገልፀዋል።

በመድረኩ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በ2016 በጀት ዓመት የዕቅዱን 90 በመቶ ማሳካቱ ተጠቅሷል፡፡

ተቋሙ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ 400 ሰራተኞቹ ለእያንዳንዳቸው ከ100 እስከ 500 ሺህ ብር ስጦታም አበርክቷል።

#ዳጉ_ጆርናል

@sheger_press
@sheger_press
በመዲናዋ የ2017 የትምህርት ዘመን በመጪው ሰኞ ይጀመራል

በአዲስ አበባ ከተማ የ2017 የትምህርት ዘመን የፊታችን ሰኞ መስከረም 6 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚጀመር የከተማው ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ የ2017 የትምህርት ዘመን በመጪው ሰኞ በሁሉም ት/ቤቶች የሚጀመር መሆኑንም የቢሮው መረጃ ያመላክታል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ሸኽ መሀመድ ሁሴን አላሙዲን ለ400 ሠራተኞቹ ከ100 ሺ ብር እስከ 500 ሺ ብር ሰጥተዋል!

ሸኽ መሀመድ ሁሴን አላሙዲን ለሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ሰራተኞች እና አመራሮች ላከናወኑት ተግባር ምስጋና አቅርበዋል።

የሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በዛሬው ዕለት በሚሊኒየም አዳራሽ የላቀ አፈጻጸም ላሳዩ አመራሮችና ሰራተኞቹ እውቅና ሰጥቷል።

በዚሁ ወቅት ሼህ መሀመድ ሁሴን አላሙዲን በዙም ባስተላለፉት መልዕክት፤ የተቋሙ ሰራተኞች እና አመራሮች ላከናወኑት ተግባር ምስጋና አቅርበዋል። ሼህ መሀመድ ሁሴን አላሙዲን በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡም ገልፀዋል።

በመድረኩ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በ2016 በጀት ዓመት የዕቅዱን 90 በመቶ ማሳካቱ ተጠቅሷል፡፡ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ 400 ሠራተኞቹ ለእያንዳንዳቸው ከ100 ሺ ብር እስከ 500 ሺ ብር ስጦታ ተበርክቷል።

@sheger_press
@sheger_press
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1 ሺህ 499ኛው የነብዩ መሀመድ ልደት (መውሊድ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ነገ ጀምሮ በቱርክ አንካራ ከተማ በሶማሊያ መንግስት እና ኢትዮጵያ ሊያደርጉት የነበረው ውይይት ሊራዘም እንደሚችል መረጃዎች እየወጡ ነው::

ይህ ስብሰባ ለሌላ ጊዜ የተራዘመበት ምክንያት ሁለቱም ወገኖች በአቋማቸው ላይ እስካሁን ምንም አይነት ለውጥ ባለማሳየታቸው ነው ተብሏል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በካዛንችስ እና አዋሬ ፥ ከህንፃዎች እና አንዳንድ በደንብ ከተያዙ መኖርያ ቤቶች በቀር ሁሉም ፈራሽ ናቸው መባሉ ተሰማ

የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር አመራሮች ባሳለፍነው ሳምንት ካዛንችስ ተገኝተው ነዋሪዎችን ባነጋገሩበት ወቅት ካዛንችስ እና አዋሬ ውስጥ ከህንፃዎች እና አንዳንድ በደንብ ከተያዙ መኖርያ ቤቶች በቀር ሁሉም ፈራሽ መሆናቸው እንደተነገራቸው ዳጉ ጆርናል ከመሠረት ሚዲያ ሰምቷል። ይህን የሚያስረዳ የድምፅ ሪከርድ ደርሶኛል ሲልም የዜና ምንጩ ዘግቧል።

ከበርካታ ነዋሪዎች የደረሰን መረጃ እንደሚጠቁመው በቅርብ ቀናት ካዛንችስ ከስድስተኛ ፖሊስ ጣብያ ጀርባ ያለው አካባቢ ሙሉ በሙሉ ሊፈርስ እንቅስቃሴ ተጀምሯል።

"መቼ እንደሚፈርስ ግን ትክክለኛው ግዜ አልተነገረንም" ያሉት ነዋሪዎቹ ይህም "እንቅልፍ ነስቶናል፣ ከዛሬ ነገ መጥተው ውጡ ሊሉን ይችላል" ብለው ከፍተኛ ስጋት እንዳደረባቸው ተናግረዋል።

Via መሠረት ሚዲያ

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ዶናልድ ትራምፕ በነበሩበት አካባቢ የተኩስ እሩምታ እንደተሰማ ተገለፀ

የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ፍሎሪዳ በሚገኘው የትራምፕ አለም አቀፍ የጎልፍ ክለብ ውስጥ ጎልፍ እየተጫወቱ በነበረበት ወቅት በአካባቢው ድንገተኛ የተኩስ እሩምታ እንደተሰማ ተገልጿል፡፡

የዶናልድ ትራምፕ የምርጫ ዘመቻ ግንኙነት ኃላፊ ስቴቨን ቼዌነግ፤ ትራምፕ በቅርበት በነበሩበት አካባቢ የተኩስ ድምፅ እንደተሰማ አረጋግጠዋል፡፡

ከክስተቱ በኋላ ዶናልድ ትራምፕ ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ የገለፁት ኃላፊው፤ አሁን በጉዳዩ ላይ ዝርዝር ማብራሪያ ማቅረብ እንደማይቻል ተናግረዋል፡፡

የአሜሪካ የሚስጥራዊ ደህንነት ተቋም (ሰክሬት ሰርቪስ) ጉዳዩን ከምዕራብ ፓልም ቢች ከተማ ፖሊስ ጋር በመሆን እየመረመረ መሆኑን ገልፆ፤ አሁን ላይ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ደህና መሆናቸውን ማስታወቁን ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡

ከሁለት ወራት ገደማ በፊት በዶናልድ ትራምፕ ላይ የግድያ ሙከራ ከተደረገ በኋላ ለሊት ያጋጠመው ክስተት በትራምፕ ላይ ያነጣጠረ ይሁን አይሁን እስካሁን ግልጽ አለመሆኑም ነው የተገለፀው፡፡

ዶናልድ ትራምፕ በፈረንጆቹ ህዳር ወር ለሚደረገው የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በፔንሲልቬንያ የምረጡኝ ቅስቀሳ እያደረጉ በነበሩበት ወቅት የግድያ ሙከራ እንደተሰነዘረባቸው የሚታወስ ነው፡፡

የBernstein ተንታኞች ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ካሸነፉ የ bitcoin ዋጋ በአመቱ መጨረሻ ላይ 90,000 ዶላር ሊደርስ እንደሚችል ተንብየዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
“በጦርነቱ ከአንድ ሚልዮን በላይ ትግራዋይ አለቀ  ተብሎ የሚወራው ማስረጃም ሆነ ጥናት የለውም።ለፖለቲካ ፉጆታ የተፈበረከ ነው።
ከተኩስ ማቆም ውጭ ያለውን የፕሪቶሪያ ስምምነት አንቀበለውም ብሏል። ትጥቅ መፍታትም ሆነ ሌላው በስምምነቱ ላይ መቀመጡንና መፈረማቸውን ቢያምንም  ከተኩስ ማቆም ውጭ ያለውን "እንታገለዋለን" ብሏል። " መጀመሪያ ስንሰማ ሁሉንም ያስደነገጠ ነው" ብሏል።
- ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ለሆራይዘን ሚዲያ ከተናገሩት የተወሰደ

@sheger_press
@sheger_press
የኢትዮጵያ አየር መንገድን በፑንትላንድ እንዳያርፍ ተከለከለ‼️
👉ይህ ክልከላ ሌሎች አውሮፕላንችንም ያካትታል።
ይህንን ክልከላ የጣለው የሱማሊያ ፌዴራል መንግስት ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ በመንግስትና በፑንትላንድ አስተዳደር መካከል በተፈጠረው ውዝግብ የተነሳ ነው፡፡ ውዝግቡን ተከትሎ የሱማሊያ ሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን ከዛሬ ጀምሮ በፑንትላንድ የሚገኘው የቦሳሶ አየር ማረፊያ ዝግ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የፑንትላንድ የፀጥታ አካላት የቦሳሶ አየር ማረፊያ አስተዳደርና ደህንነት ከቁጥጥራቸው ውጭ መሆኑን በመግለፅ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ በዚያ ለሚጠቀሙ አውሮፕላኖች ማስጠንቀቂያ ሰጥተው እንደነበር ተዘግቧል፡፡ ይሁንና ይህንን ማስጠንቀቂያ ቸል በማለት በረራቸውን የቀጠሉት የኢትዮጵያ አየር መንገድና የዳሎ አየር መንገድ ብቻ የነበሩ ሲሆን ዛሬ እነዚህም ቦሳሶ እንዳያርፉ ከሱማሊያ ሲቪል አቪየሽን እገዳ ተጥሎባቸዋል፡፡

ይህ የዛሬው እገዳ በሱማሊያና በፑንትላንድ መካከል ያለውን የፖለቲካ ሽኩቻ አንድ ደረጃ ከፍ ያደረገ መሆኑን የፖለቲካ ታዛቢዎች ተናግረዋል፡፡ የአየር ማረፊያው በመዘጋቱ በርካታ መንገደኞች ለእንግልት የተዳረጉ ሲሆን ሲቪል አቪየሽኑ ሌላ ማስታወቂያ እስከሚያወጣ ድረስ ዝግ ሆኖ እንደሚቆይ አስታውቋል፡፡

@sheger_press
@sheger_press
በአዲሱ ዓመት በአዲስ ክህሎቶች ራሳችሁን ብቁ አድርጉ። በሳፋሪኮም ታለንት ክላውድ ላይ የ 20% ቅናሽ ለወንዶች : 5,706 ብር የነበረው አሁን በ 1,141 ብር ብቻ ያግኙ።

- 6000+ tech and non tech ኮርሶች
- በ ቀጣሪዎች ዘንድ ተቀባይነት ያላቸው ሰርተፍኬቶች
- በተለያዩ ፕሮጀክቶቻችሁ ላይ ከአቻ ባልደረቦቻችሁ ጋር አብራችሁ የምትሰሩበት እድል
- ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች የሚመሩ የስልጠና ቡድኖችን
- በየወሩ ነጻ የ6 GB የኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚም ይሆናሉ

በዚህ አዲስ ዓመት ግቦችን ብቻ አታስቀምጡ፣ ግቦቹን አሳኩት። አሁኑኑ ይመዝገቡ : https://bit.ly/4cQrem2

ለተጨማሪ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ: https://www.tg-me.com/+3nNaOCMHiXgyMTA0
Forwarded from Sheger Press️️
Make the most of the New Year with New Skills. Invest in your future with Safaricom Talent Cloud’s exclusive 80% scholarship for women, originally 5,706 birr, now just 1,141 birr.

Build your future with:
- 6,000+ tech and non tech courses
- Certifications recognized by top employers
- A supportive learning community
- Expert coaching at every step
- 6 GB free internet monthly

Don’t just set goals this New Year, achieve them. Register now at https://bit.ly/4cQrem2 and make 2017 your year of success!

For more information, join our Telegram channel: https://www.tg-me.com/+3nNaOCMHiXgyMTA0
በ2017 ዓ/ም መማር ለምትፈልጉ አመልካቾች በሙሉ

በአንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በቀን በመደበኛ መርሃ ግብር በመንግስት ስኮላርሺፕ እና በግል በመጀመሪያ ዲግሪ በ2017 ዓ/ም መማር ለምትፈልጉ አመልካቾች በሙሉ፤

በ2017 ዓ/ም በቅድመ ምረቃ መደበኛ መርሃ ግብር በትምህርት ሚኒስቴር ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምደባ እንደማይኖር ይታወቃል።

በመንግስት ስኮላርሺፕ እንዲሁም በግል ከፍላችሁ በዩኒቨርሲቲያችን መማር ለምትፈልጉ በሙሉ የአ.አ.ዩ የሚያወጣውን የመግቢያ ፈተና (UAT) እንዲሁም ሌሎች መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባችኋል፡፡

በዚህም መሠረት በዩኒቨርሲቲያችን ድረ ገጾች
(www.aau.edu.et ወይም https://portal.aau.edu.et) ላይ የተመለከቱትን ዝርዝር የማመልከቻ መስፈርቶች በማሟላት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

• የመመዝገቢያ ቀናት እስከ መስከረም 8/ 2017 ዓ.ም ድረስ ይሆናል

• የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀናት ወደፊት በ ዩኒቨርሲቲያችን ዌብ ሳይት፤ የምዝገባ ፖርታል እንዲሁም በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ የሚገለጽ ይሆናል::

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
‹‹ የእነ ዶ/ር ደብረጺዮን ቡድን ከፍተኛ የስልጣን ጥመኛ ነው ›› ባይቶና

በህወሃት ነባር አመራሮችና በጊዚያዊ አስተዳደሩ ሃላፊዎች መካከል የተፈጠረውን ውዝግብ ተከትሎ የተለያዩ አስተያየቶች መሰጠታቸው እንደቀጠለ ነው፡፡

የባይቶና አባይ ትግራይ ፓርቲ ምክትል ሊመንበር የሆኑት አቶ ዮሴፍ በርሄ በትግራይ እየተከሰቱ ላሉ ፖለቲካዊ ቀውሶች የአንበሳውን ድርሻ የሚወስደው ነባሩና በዶክተር ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ቡድን ነው ብሎ ፓርቲያቸው እንደሚያምን ገልጸዋል፡፡

በክልሉ ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ እንዳይኖር፣ስርአት አልበኝነት እንዲበራከትና መሰል ችግሮች እንዲፈጠሩ በታችኛው መዋቅር ያሉና ነባሩን የህወሃት መዋቅር የሚደግፉ አመራሮች ፈተና ሆነዋል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ከዚህ አንጻር ጊዚያዊ አስተዳደሩ የተሻለ የፖለቲካ አመለካከት አለው ለማለት ያስደፍራል ያሉት ምክትል ሊቀመንበሩ ያም ቢሆን ግን ችግሮችን ከመፍታትና የህዝብን ጥያቄ ከመመለስ ይልቅ ሁለቱ ቡድኖች ስልጣንን የመጀመሪያ ጉዳይ አድርገው መሻኮታቸው ግባቸው ምን እንደሆነ ቁልጭ አድርጎ ያሳየ ነው ብለዋል፡፡

ላለፉት 50 ዓመታት ትግራይን ወጥሮ የያዘው የአንድ ፓርቲ አስተሳሰብ መወገድ እንዳለበት እናምናለን ያለው  ፓርቲው ይህንን ለማድረግም የሚጠበቅብኝን የቤት ስራ እየሰራሁ ነው ሲል ገልጿል፡፡
አዲስ ማለዳ

@sheger_press
@sheger_press
2024/10/02 08:16:13
Back to Top
HTML Embed Code: