Telegram Web Link
ሀይሌ ያሰጀመረው የፓሪሱ ማራቶን 30ኪሜ አልፏል።

ይቅናን
አትሌት ታምራት ቶላ እየመራ ይገኛል

@ethio_mereja_news
አትሌት ታምራት ቶላ አሁንም እየመራ ይገኛል። 4KM አካባቢ ይቀራል

መጨረሻው ያሳምርልን

@ethio_mereja_news
1KM ቀርቷል
እንኳን ደስ ያላቹ ።
እንኳን ደስ ያለን ።

እልልልልልል እናት ሀገር አሸነፈች🇪🇹🇪🇹

Congraaaaaaaa🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

በመጨረሻም ስናፍቀው የነበረው ወርቅ ወደ ቤቱ ተመልሷል።

ታምራት ቶላ ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ወርቅ አስገኝቷል።

ጀግና

ዛሬ የድል ቀን ነው🇪🇹🇪🇹🇪🇹

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
እልህ ፣ወኔ ፣ አልበገር ባይነት ያሸናፊነት መንፈስ ሁሉንም የያዘ የሀገራችን ምርጥ እንቁ አትሌት ታምራት ቶላ!!

በነገራችን ላይ ሪከርድ በመስበር ጭምር ነው ያሸነፈው።

የኦሎምፒክ ሪከርድን በስድስት ሴኮንዶች ያሻሻለ ጀግና!

ታምራት ቶላ ከ 24 አመታት በኋላ በኦሎምፒክ ማራቶንን ያሸነፈ ኢትዮጵያዊ ሆነ።

ተጠባባቂ ተብሎ በደል የደረሰበት አትሌት በተጎዳ ሰው ተተክቶ ለሀገሬ በማራቶን የመጀመሪያ ወርቅ አስገኘ 💪💪💪

ታምራት ቶላ ይገባሀል 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

@ethio_mereja_news
ለሕዝባችን የሚገባውን ደስታና ኩራት አመጣህለት!! የዛሬው ድል ልዩ ትርጉም አለው።

ፈጣሪ ይባርክህ!!"

ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ

@sheger_press
@sheger_press
ክቡር ጠ/ር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ያስተላለፉት የእንኳን ደስ ያላቹ መልክት

በፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ ጀግናው አትሌት ታምራት ቶላ በማራቶን ውድድር ላይ ወርቅ በማግኘት ሰንደቅ አላማችንን በድጋሚ ከፍ አድርጓል።

እንኳን ደስ አላችሁ!

@ethio_mereja_news
ጀግናው አትሌት ታምራት ቶላ ከድሉ በኋላ ለሲዲ ስፖርት በሰጠው አጭር ቃል በእንባ ታጅቦ በደስታ ሲያለቅስ ታይቷል ።

ከድሉ በኋላ የመጀመሪያ በሆነው ቃሉ ''ደስታ ነው ያስለቀሰኝ እግዚአብሔር ይመስገን '' ብሏል

በድጋሚ እንኳን ደስ አለን‼️

@ethio_mereja_news
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በጎፋ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ ለተፈናቀሉ ዜጎች የ5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በጎፋ ዞን በድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ የሚውል የ5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ በዛሬው እለት አሰረክቧል፡፡

የገንዘብ ድጋፉን የኮርፖሬሽኑ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ኃይለብርሀን ዜና በቦታው በመገኘት አስረክበዋል፡፡ አቶ ኃይለብሀን ዜና በወገኖቻችን ላይ በደረሰው ድንገተኛ አደጋ የኮርፖሬሽኑ አመራሮችና ሠራተኞችን ማዘናቸውን ገልጸዋል፡፡

ኮርፖሬሽኑ በመላ አገሪቱ የሚከሰቱ ሰው ሠራሽ እና ተፍጥሯዊ አደጋዎች ምክንያት ጉዳት ለደረሰባው ወገኖች የገንዘብ ድጋፍ ሲያደርግ መቆቱን አስተውሰው በ6 ዓመታት ብቻ ኮርፖሬሽኑ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ታሳቢ በማድረግ ያደረገው ድጋፍ ግማሽ ቢሊየን ብር መሻገሩን ተናግረዋል፡፡

በጎፋ ዞን በድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ ለተፈናቀሉ ዜጎች መልሶ ለማቋቋም እየተደረገ ያለውን አንቅስቃሴ መደገፉን አጠናክሮ ይቀጥላልም ነው ያሉት አቶ ኃለብርኃን ዜና ፡፡

የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ በበኩላቸው ከፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ለተደረገው የገንዘብ ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበው ፣ ድጋፉ በአደጋው ለተጎዱ እና የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም የሚደረገውን ጥረት የሚያግዝ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

በአደጋው ለተጎዱና ለተፈናቀሉ ወገኖች ተገቢው የሆነ ሰብዓዊ ድጋፍ እየተደረገ እንደሆነ ጠቁመው ተፈናቃዮችን ከአደጋ ስጋት ነጻ ወደ ሆነ ቦታ የማስፈር ሥራ እየተሰራ እንደሆም ገልጸዋል፡፡
ኮርፖሬሽኑ ያደረገው የገንዘብ ድጋፍም ለመልሶ ማቋቋም ሥራው ትልቅ አጋዥ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Dogs‼️

Dogs ያልጀመራቹ ብዙዎች መቆጨታቹ አይቀርም እያሉ ነው

ስለዚ ጀምሩ ያልጀመራቹ 👇👇

https://www.tg-me.com/dogshouse_bot/join?startapp=qA4t5KguQWKX0tWVVEhxSQ

https://www.tg-me.com/dogshouse_bot/join?startapp=qA4t5KguQWKX0tWVVEhxSQ
በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን በኮምቦልቻ ከተማ ዛሬ ጠዋት ልዩ ስሙ ዶሮ እርባታ አካባቢ አንድ ግለሰብ ውሻ አርዶ በመግፈፍ ላይ እያለ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን ጥቆማዎች ደርሰውኛል።

ከዚህ በፊት የውሻ ስጋን ወደ ሽያጭ ሲያወጣ እንደነበር ከግለሰቡ ቃል ለመገንዘብ ተችሏል ሲሉ ምንጮች ገልጸዋል።(ayu)

@ethio_mereja_news
የ 5000ሜ ወንዶች ፍፃሜ ውድድር ከጀመረ 5 ያህል ደቂቃዎች አልፈውታል

ሀገራችን ኢትዮጵያ በርቀቱ

🇪🇹 በአትሌት ሀጎስ ገብረ ህይወት
🇪🇹 በአትሌት አዲሱ ይሁኔ
🇪🇹 በአትሌት ቢኒያም መሀሪ ተወክላለች።

መልካም እድል ለአትሌቶቻችን 🇪🇹
ሜዳሊያ ውስጥ አልገባንም።

ኢትዮጵያ በ 5000ሜ የፍፃሜ ውድድር ሜዳሊያ ማግኘት አልቻለችም።

ጆኮብ ኢንግብርስቴን ለኖርዌይ የወርቅ ሜዳሊያ ሲያስገኝ ኬንያ ብር እንዲሁ አሜሪካ ነሐስ አግኝተዋል።

5ኛ ሀጎስ ገብረ ሂወት
6ኛ ቢንያም መሀሪ
14ኛ አዲስ ይሁኔ በመሆን ውድድራቸውን አጠናቀዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በድጋሚ አሁን በተደረገው የሴቶች 1500ሜትር ፍፃሜ የሜዳሊያ ሰንጠዥ ውስጥ መግባት እንዳማረን ቀርቷል።

@ethio_mereja_news
ህውሀት‼️

ህወሓት ህጋዊ ሰውነቴ እንዲመለስ እንጂ በአዲሱ አዋጅ በልዩ ሁኔታ መመዝገቡን አልቀበልም ብሏል‼️

ሙሉ መግለጫው👇

"የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በሀምሌ 19 ቀን 2016 ዓ.ም የቀረበለትን የተሰረዘውን የህወሓት ህጋዊ ሰውነት ወደ ነበረበት የመመለስ ጥያቄ ተከትሎ በነሓሴ 03 ቀን 2016 ዓ.ም ለህወሓት የፖለቲካ ፓርቲዎች በልዩ ሁኔታ ሲመዘገቡ የሚሰጥ የህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት” እና ”ህወሓት በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ ምግባር አዋጅን ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁጥር 1332/2016 መሰረት በልዩ ሁኔታ የተመዘገበ መሆኑን ስለማሳወቅ” የሚል አርእስት የተሰጠውን በቁጥር አ1162/11/15180 የተፃፈ ህወሓት ስላቀረበው ጥያቄና ቦርዱ የሰጠውን ውሳኔ የያዘ ደብዳቤ ደርሶናል።

በዚህ መሰረት፤ ህወሓት ያቀረበው ጥያቄ በቦርዱ ውሳኔም በግልፅ እንደተቀመጠው ከፕሪቶሪያው ስምምነት፣ ከህግ እና ህወሓት እያደረገ ካለው ተጨባጭ እንቅስቃሴ አንፃር የተሰረዘውን ህጋዊ ሰውነታችን ወደነበረበት እንዲመለስልን የሚል ብቻ ነው። የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ከዚህ በፊት የህወሓት ህጋዊ ሰውነት ወደ ነበረበት ስለመመለስ እና ለዚህ ጉዳይ መፍትሄ ተብሎ በፌደራል መንግስት የቀረበውን አዋጅ ቁጥር 1162/2011 የሚያሻሽል አዲስ አዋጅ ይዘት አስመልክቶ ውይይት በማድረግ አዋጁ የህወሓትን ህጋዊ ሰውነት እንደማይመልስ በመገንዘብ ከሚመለከታቸው የፌደራል አካላት ጋር ውይይት እንዲደረግ ወስኗል።

በዚህ መሰረት የህወሓት የስራ ሀላፊዎች ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩና ከሚመለከታቸው የፌደራል መንግስት የስራ ሀላፊዎች ጋር ተደጋጋሚ ውይይቶችን በማካሄድ የህወሓት ሕጋዊ ሰውነት እንዲመለስ መግባባት ላይ ተደርሷል። በአፍሪካ ህብረት ፓነል ውይይትም ይህ ጉዳይ ተነስቶ ህጋዊ ሰውነቱ መመለስ እንዳለበት ስምምነት ተደርሶበታል። ይህንን ተከትሎም ህወሓት ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ህጋዊ ሰውነቱን ወደነበረበት እንዲመለስለት ብቻ በሀምሌ 19 ቀን 2016 ዓ.ም ጥያቄ አቅርቧል።

ሆኖም ቦርዱ የፕሪቶሪያውን ስምምነት፣ ከዚህ በፊት በሌሎች የፌደራል ተቋማት የተሰጡትን ውሳኔዎች፣ ሌሎች ህጎች እና ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የተደረሱ መግባባቶች ወደጎን በመተው ጥያቄውን ”በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ ምግባር አዋጅን ለማሻሻል በወጣው አዋጅ” መልሷል። ከዚህ የተነሳም ጥያቄው ሌላ መልሱ ሌላ ሆነዋል።

ከዚህ ባሻገር፤
1) ምንም እንኳን ቦርዱ የህወሓት ጥያቄ ህጋዊ ሰውነት መመለስ ብቻ እንደሆነ በግልፅ ያስቀመጠ ቢሆንም ከህወሓት ጥያቄ እና እውቅና ውጪ በፍትህ ሚኒስቴር የተፃፈውን ደብዳቤ በአባሪነትና መነሻነት ጠቅሷል።

2) ህወሓት ባቀረበው ማመልከቻ ላይ በማሻሻያ አዋጁ አንቀፅ 2(2) ላይ የተቀመጡትን መቅረብ አለባቸው ተብለው የተቀመጡትን ዝርዝሮች በማሻሻያ አዋጁ መሰረት እንደቀረቡ ገልጿል። ሆኖም የፍትህ ሚኒስቴሩ ደብዳቤ ከፍ ብሎም እንደተገለፀው በህወሓት በኩል ምንም ዐይነት ጥያቄ ሳይቀርብና ከህወሓት እውቅና ውጪ የተፃፈ ነው። በይዘቱም ህወሓት አይስማማም። በህወሓት የቀረበውን ማመልከቻ እና አባሪዎቹ የሚመለከትም ህወሓት የተሰረዘውን ህጋዊ ሰውነቱ ወደነበረበት እንዲመለስ የሚያግዙ ሰነዶች ማለትም የፓርቲው ፕሮግራም፣ መተዳደሪያ ደንብ እና የጠቅላላ አመራሮቹ ዝርዝር የያዘ ሰነድ እንጅ በማሻሻያ አዋጁ መሰረት እንዲሁም አዋጅ ቁጥር 1162/2011 ዐንቀፅ 2(14) መሰረት የስራ አስፈፃሚ አባላት ስም፣ አድራሻ እና በተለየ ሁኔታ ሀላፊነት ወስደው ቃል የሚገቡበትን የተፈረመ ሰነድ ለቦርዱ አላቀረበም።

በነበረው ሂደት ቦርዱ በአዲሱ ማሻሻያ ህግ መንፈስ የራሱ ፎርም አዘጋጅቶ የህወሓት ስራ አስፈፃሚ አባላት ስም፣ ፌርማ፣ አድራሻ ሞልተው ሀላፊት ወስደው እንደሚሰሩ የሚገልፅ ሰነድ እንዲቀርብለት ጠይቆ በህወሓት በኩል ከማመልከቻው የሚጣጣም ሰነድ ካልሆነ በስተቀር በአዲሱ ህግ ወይም ቦርዱ ባቀረበው ፎርም መሰረት የተለየ ሀላፊነት ወስዶ የሚፈርምበት ምክንያት እንደሌለ ገልፆ ሳይስማማ በመቅረቱ ቦርዱ በቀረበለት ማመልከቻ ብቻ ውሳኔውን እንደሰጠ ይታወቃል።

በአጠቃላይ በቦርዱ ውሳኔ ላይ የተካተቱት ዝርዝር ይዘቶች አዲስ በወጣው ማሻሻያ ህግ መሰረት የተቀመጡና ህወሓት ካቀረበው ጥያቄ ጋር የማይገናኙ ናቸው። ስለሆነም ምንም እንኳን ቦርዱ ህወሓት በልዩ ሁኔታ ተመዝግቧል ቢልም ውሳኔው በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ ምግባር አዋጅን ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁጥር 1332/2016 መሰረት በልዩ ሁኔታ የተመዘገበ መሆኑን ገልጿል። ስለሆነም ድርጅታችን ህጋዊ ሰውነቱ ወደነበረበት እንዲመለስ ያቀረበውን ጥያቄ የማይመልስ በመሆኑ አልተቀበለውም። ውሳኔው በፕሪቶሪያው ስምምነት ያልተመሰረተ፣ ከዚህ በፊት በሌሎች የፌደራል ተቋማት የተሰጡትን ውሳኔዎች እንዲሁም የነበሩ ውይይቶችን የሚቃረኑ ዝርዝር ይዘቶች በህወሓት ላይ የሚጭን በመሆኑ የቀረበውን ጥያቄ እስኪመለስ ድረስ ህወሓት የፓርቲው ሕገ ደንብ በሚፈቅድለት መልኩ ተያያዥ ስራዎች ያከናውናል። የፌደራል መንግስቱም የማስተካከያ እርምጃ እንዲወስድ ጥሪ ያቀርባል"ሲል በመግለጫው ጠይቋል።

@ethio_mereja_news
2024/10/01 19:28:04
Back to Top
HTML Embed Code: