Telegram Web Link
ማራቶን‼️

የሴቶች ማራቶን ከተጀመር ትንሽ ቆይቷል።

ሀገራችንን ሶስት ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ይወክሏታል።

ትዕግስት አለሙ
አማኔ በሬሶ
መገርቱ አለሙ

መልካም ዕድል
#Ethiopia

የሴቶች ማራቶን ሊጠናቀቅ ወደ 2 ኪሎ ሜትር አካባቢ ቀርቶታል።
ኢትዮጵያ በትግስት አሰፋ አማካኝነት በፓሪስ ኦሎምፒክ ሶስተኛውን ብር አግኝታለች።

🥇ሲፋን ሀሰን
🥈ትግስት አሰፋ
🥉ሄለን ኦብሪ

@ethio_mereja_news
ኢትዮጵያ የፓሪስ ውድደሯን ጨርሳለች !

በ 2024 የፓሪስ ኦሎምፒክ የተሳተፈው የ ኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ቡድን በድምሩ አራት ሜዳሊያዎችን ብቻ በመሰብሰብ ቆይታውን አጠናቋል።

ሜዳሊያ ያስገኙ አትሌቶች :-

🥇 ታምራት ቶላ
🥈 በሪሁ አረጋዊ ፣ ጵጌ ድጉማ እና ትግስት አሰፋ ናቸው።

ሀገራችን አሁን ባለው ወቅታዊ የሜዳሊያ ሰንጠረዥ ከአለም 4️⃣5️⃣ኛ ላይ ትገኛለች።

ቀሪ የኦሎምፒክ ውድድሮች ስላሉ ደረጃው የሚለዋወጥ ይሆናል።

ኢትዮጵያ በተከታታይ ሶስት ኦሎምፒኮች በሪዮ ፣ ቶኪዮ እና ፓሪስ አንድ ወርቅ ብቻ አግኝታለች።

በዘንድሮው የፓሪስ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያ ሁለት ሪከርዶቿ ( በቀነኒሳ በቀለ ) እና ( ቲኪ ገላና ) ተይዞ የቆዩ ሪከርዶቹ በዩጋንዳ እና ኔዘርላንድ አትሌቶች ተሰብረዋል።Tikvahsport

@ethio_mereja_news
Dogs ‼️

List ሊደረግ ሶስት ቀን ቀረው።

100% የተረጋገጠና ሌላኛው ኖትኮይን የተባለለት።

Dogs ቢያንስ 5 ሰው ካስገባቹ 20,000 Dogs ማግኘት ትችላላቹ።

በርግጠኝነት ሌላኛው ኖትኮይን ማለት ይቻላል።

ያልጀመራቹ ቶሎ ጀምሩ👇👇

https://www.tg-me.com/dogshouse_bot/join?startapp=zBY7jyJYQW6OF9Sjuhm7mA
መንግሥት ለግል ሠራተኞች የደመወዝ ማስተካከያ እንዲደረግ አቅጣጫ እንዲሰጥ ጥያቄ ቀረበ

የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) መንግሥት ከሰሞኑ ይፋ ያደረገውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተከትሎ ለመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ማስተካከያ ይደረጋል በተባለው ልክ፣ ለግል ድርጅቶች ሠራተኞችም ማስተካከያ የሚደረግበት አቅጣጫ እንዲሰጥ ጥያቄ አቀረበ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በቅርቡ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ፣ ለመንግሥት ሠራተኞች አስከ 300 ፐርሰንት የደመወዝ ጭማሪ እንደሚደረግ ገልጸው፣ ለዚህም መንግሥት ለደመወዝ ጭማሪ ከ90 ቢሊዮን ብር በላይ መመደቡን ገልጸው ነበር፡፡

አስተያታቸውን ለሪፖርተር የሰጡት የኢሠማኮ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አያሌው አህመድ፣ በመንግሥት በጀት ለሚተዳደሩት የመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ማስተካከያ እንደሚደረግ ቢገለጽም፣ የግል ድርጅቶችና ተቋማት በራሳቸው በጀትና ትርፍ የሚንቀሳቀሱ በመሆኑናቸው፣ በትርፋቸው ላይ ተመሥርተው ለሠራተኛ የደመወዝ ማስተካከያ እንዲያደርጉ ከመንግሥት አቅጣጫ እየተጠበቀ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ‹‹የሠራተኞችና የደመወዝ ዝቅተኛው ወለል እንዲወጣ እየወተወትን ነው፤›› ብለዋል፡፡ የመንግሥትና የግል ሠራተኞች አንዱ የተሻለ አንዱ የወደቀ የሚባል ክፍያ ሊኖር አይገባም ብለዋል፡፡

‹‹መንግሥት ጉዳዩን ሊዘነጋው አይችልም የሚል እምነት ቢኖረንም፣ መሰል አገራዊ አጋጣሚዎችና ቀውሶች በሚኖሩበት ጊዜ ባለሀብቶችንና ተቋማትን የሚመለከቱ ማሻሻያዎች በማድረግና ውይይቶች በማካሄድ አቅጣጫዎች ሊሰጡበት ይገባል፤›› ብለዋል፡፡ ‹‹ይህ የማይሆን ከሆነ ግን ለአገርም አይጠቅምም፣ የኢንዱስትሪ ሰላም አይኖርም፣ ሠራተኛውም ተረጋግቶ ሥራውን ማከናወን አይችልም፤›› ያሉት አቶ አያሌው፣ ጉዳዩ በጣም አሳሳቢ ስለሆነ መንግሥት አቅጣጫ የማይሰጥበት ከሆነ ኢሠማኮ ጥያቄውን በጽሑፍ ለመንግሥት ያቀርባል፤›› በማለት አስረድተዋል፡፡

‹‹ሠራተኛው በከፍተኛ የኑሮ ውድነት ምክንያት በልቶ ማደር አልቻለም፣ የኑሮ ውድነቱን መቋቋም አልቻለም፣ ይህን ማንም ያውቀዋል ሚስጥር አይደለም፣ አሠሪዎቹ ለሚያሠሯቸው ዜጎች ተመጣጣኝ የሆነ ክፍያ መክፈል አለባቸው፤›› ብለዋል፡፡

የሠራተኛ መብት መከበር እንዳለበት ‹‹የሚያረጋግጥ ወጥ የሆነ ሕግ ያስፈልጋል›› ያሉት አቶ አያሌው፣ የሠራተኞች ዝቅተኛ የደመወዝ ወለልና ሌሎች የሠራተኞች መብቶችና ጥቅማ ጥቅሞች ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን መንግሥት ለምን እንዳዘገያቸው አልገባኝም፤›› ሲሉም አክለዋል፡፡

የዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ጉዳይ ላይ አሁንም መንግሥት የዘነጋው ይመስላል ያሉት ምክትል ፕሬዚዳንቱ፣ ኢሠማኮ ተጨማሪ ጥያቄ ሊያቀርብ እንደሚችል ተናግረዋል፡፡

አክለውም ከመንግሥት ተቋማት በተሻለ የሚያተርፉት የግል ተቋማት፣ ከመንግሥት የደመወዝ ጭማሪ ጋር እኩል ላለመጨመር ትልቁ ችግር የአስተሳሰብ ጉዳይ እንጂ፣ የገንዘብ እጥረት አይደለም በማለት ለዜጎች ማዘን እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡  ለራስ ብቻ ከማግበስበስ ዕሳቤ በመውጣት ምርታማ ሠራተኛን ለማፍራት፣ አሁን  ተመጣጣኝ የደመወዝ ጭማሪ ማድረግ ብዙ ነው የሚያሰኝ አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የአሠሪዎች ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ዳዊት ሞገስ በበኩላቸው፣ ለዋጋ መጨመር አንዱ ምክንያት የደመወዝ ጭማሪ ነው ይላሉ፡፡ ደመወዝ ከመጨመሩ በፊት የምርት ማደግ መፍትሔ መሆኑን የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ፣ ለሠራተኛ 300 ፐርሰንት እንዲጨመር ከተፈለገ ምርታማነቱ በዚያው ልክ ማደግ አለበት ብለዋል፡፡ ለሠራተኛ ደመወዝ መጨመር እሰየው የሚያስብል ቢሆንም፣ ምርታማነት ዝቅተኛ ከሆነባቸው አገሮች መካከል አንዷ በሆነችው ኢትዮጵያ ከመንግሥት ጋር እኩል 300 ፐርሰንት ደመወዝ ጭማሪ አድርጉ ማለት ይከብዳል ብለዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ በአሠሪዎች ዘንድ የታሰበ ነገር ባይኖርም ሠራተኛው ሥራ ጥሎ እንዳይሄድ ምን እናደርግ የሚል ውይይት መጀመሩን ጠቅሰው፣ ደመወዝ ቢጨምር የባሱ ችግሮች ሊፈጠሩ ስለሚችሉ መጠንቀቅ ያስፈልጋል  ሲሉ ተናግረዋል፡፡

‹‹በቀጣይ ሠራተኞች ደመወዝ ይሻሻል ብለው መጠየቃቸው አይቀርም፡፡ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባትና ጥናት በማድረግ ጥንቃቄ ተደርጎበት ሊሠራ የሚገባ ጉዳይ ነው፤›› ሲሉ አክለዋል፡፡

ሰው በችግር ውስጥ ሆኖ መኖርና መሥራት የለበትም ያሉት ፕሬዚዳንቱ ነገር ግን አንዳንድ የግሉ ዘርፍ አባላት በዋጋ ንረት፣ በዶላር እጥረትና በመሰል ማነቆዎች እየተንገዳገዱ ናቸው ብለዋል፡፡ በመሆኑም በዚህ ችግር ላይ ደመወዝ ጨምሩ ማለት ሊከብድ ቢችልም፣  ምናልባት የመንግሥት የደመወዝ አጨማመር ታይቶ ሊታሰብበት የሚገባ ጉዳይ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የኢሠማኮ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አያሌው፣ አሠሪዎች ደመወዝ እንጨምር ካሉ ሁለትና ሦስት ሠራተኛ ይሠራው የነበረውን ለአንድ ሠራተኛ በማሸከም፣ ሠራተኛ ወደ መቀነስ ሊገቡ እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡ አቶ ዳዊት ግን፣ ‹‹የመንግሥትን አጨማመር ተመልክተን የምንሄድበት ይሆናል፤›› ብለው፣ ዋናውና መወሰድ ያለበት በየተቋማቱ ባሉ የቢሮክራሲ ማነቆዎች የጉዳይ መጓተት ባለበት ሁኔታ፣ ሥራ በታቀደው ጊዜ ማስኬድ በማይቻልበት ደመወዝ ጨምሩ ማለት አስቸጋሪ ነው ብለዋል፡፡ መንግሥት አምራቹን መደገፍ በሚገባው ልክ አቅጣጫ በመስጠት ድጋፍ ሊያደርግ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል፡፡
(ሪፖርተር)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
መቀሌ

" የህዝብ ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል ላለልተወሰነ ጊዜ የድጋፍም ይሁን የተቋውሞ ሰልፍ ማድረግ ተከልክሏል " - ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር፣ ምክትል ፕሬዜዳንት ሌ/ጀነራል ታደሰ ወረደ ዛሬ ከሰዓት መግለጫ ሰጥተዋል።

በዚህም ፤ " ፓለቲካዊ አለመግባባት ወደ ማንኛውም የፀጥታ አደጋ እንዲሸጋገር አንፈቅድም " ሲሉ አጠንቅቀዋል።

" የህዝብ ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል ላለልተወሰነ ጊዜ የድጋፍም ይሁን የተቋውሞ ሰልፍ ማድረግ ተከልክሏል " ያሉት ጀነራል ታደሰ ወረደ " ፓለቲካዊ ልዩነት በሰላማዊ መንገድ ብቻ መፈታት አለበት " ሲሉ ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም ጊዜያዊ አስተዳደሩ ፤ በቀላል እና ከባባድ ወንጀሎች ተሳትፈዋል ያላቸውን ግለሰቦች በቁጥጥር ስር የማዋል ኦፕሬሽን መጀመሩ ይታወሳል።

ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረዳ በዛሬ መግለጫቸው ላይ በህግ ቁጥጥር ስር የዋሉት ግለሰቦችና ብዛታቸውን ባይገልጹም " የህግ የበላይነት ለማስከበር የተጀመረው እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል " ሲሉ አሳውወዋል።

የዘንድሮ የአሸንዳ በዓል አከባበርና የህወሓት ጉባኤ ከመካሄድ ጋር ተያይዞ የፀጥታ ችግር እንዳይፈጠር ተገቢ እና ጥብቅ የፀጥታ ስራ ይሰራል ሲሉም ተናግረዋል።

በህወሓት አመራሮች መካከል ያለው ልዩነት እየሰፋ እና እየከረረ መሄዱ በርካቶችን ያሳሰበ ጉዳይ ሆኗል።

ሁኔታው የፀጥታ ስጋት ደቅኗል የሚሉ አልጠፉም።

ሌ/ጄነራል ታደሰ ግን ፓለቲካዊ ልዩነት በሰላማዊ መንገድ ብቻ መፈታት እንዳለበት ፤ ማንኛውም ልዩነት ወደ ፀጥታ አደጋ እንዲሸጋገር የጸጥታ አካሉ እንደማይፈቅድ አጠንቅቀዋል።
(Tikvahethiopia)

@ethio_mereja_news
የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ሁለተኛ ዙር ውይይት ነገ በአንካራ ሊካሄድ ነው

በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል የተፈጠረውን ውጥረት ለመፍታት በቱርክ የተጀመረው ሽምግልና ሁለተኛ ዙር ንግግር ከታቀደለት ጊዜ አስቀድሞ ሊካሄድ ነው። በቱርክ ዋና ከተማ አንካራ በሚካሄደው እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ታዬ አጽቀሥላሴ እንዲሁም የሶማሊያ አቻቸው አህመድ ሙዓሊም ፊቅ የሚሳተፉበት ውይይት፤ ነገ ሰኞ እንደሚካሄድ ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ አንድ የዲፕሎማቲክ የመረጃ ምንጭ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

@ethio_mereja_news
#TPLF : " ህወሓትን ለማፍረስ አልሞ በሚካሄደው ጉባኤ አንሳተፍም " ያሉት ምክትል ሊቀመንበሩ አቶ ጌታቸው ረዳ የሚገኙባቸው 14 የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት " ጉባኤውን ተከትሎ ለሚመጣው ነገር እኛ የለንበትም " ብለዋል።

ጉባኤው " በጥቂት ቡድኖች ማን አለበኝነት " የተዘጋጀ ፦
- የጉባኤው ከፍተኛ ስልጣን ያለው የማእከላዊ ኮሚቴ አመራር ያልወሰነው
- የድርጅቱ የማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን ውድቅ ያደረገው
- ከኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ መግባባት ያልተደረሰበትና
- ትግራይ ከጫፍ አስከ ጫፍ ያልተወከለበት፤ ነጻ ያልወጡ አካባቢዎች ባሉበት ነው ብለዋል።

" ጉባኤው የጠባብ ቡድን ጥቅም ለማስከበር ብቻ ያለመ ነው ፤ እኛ ደግሞ በዚህ ላይ አንሳተፍም " ሲሉ ገልጸዋል።

" ህወሓትን እና የትግራይ ህዝብ ወደ ከፋ አደጋ የሚያጋልጥ ያልተረጋጋ ጉባኤ ማካሄድ የጠባብ ቡድኑ ጥቅምን ከማረጋገጥ ያለፈ እርባና የለውም " ሲሉም ገልጸዋል።

14ቱ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት " ህወሓትን እና የትግራይ ህዝብ ወደ ሌላ የተወሳሰበ ቀውስ በሚከት በጠባብ ቡድን የተዘጋጀው ጉባኤ አንሳተም " ብለው " ጉባኤውን ተከትሎ ለሚፈጠረው ማንኛውም ነገር ተጠያቂው ይኸው ቡድን መሆኑ እናስታውቃለን " ብለዋል።

አቶ ጌታቸው ረዳ ያሉበት 14 የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት " ጠባብ ቡድን " እያሉ የገለጻቸውን ጥቂት ቡድኖች በስም አልገለጿቸውም።

#Tikvah

@ethio_mereja_news
Dogs ‼️

ሊጠናቀቅ ሁለት ቀን ቀረው።

100% የተረጋገጠና ሌላኛው ኖትኮይን የተባለለት።

Dogs ቢያንስ 5 ሰው ካስገባቹ 20,000 Dogs ማግኘት ትችላላቹ።

በርግጠኝነት ሌላኛው ኖትኮይን ማለት ይቻላል።

ያልጀመራቹ ቶሎ ጀምሩ👇👇

https://www.tg-me.com/dogshouse_bot/join?startapp=u5TqlMD7SJ-O9LXqqn3Qjg

https://www.tg-me.com/dogshouse_bot/join?startapp=u5TqlMD7SJ-O9LXqqn3Qjg
የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ዛሬ በአዲስ አበባ ስብሰባ ያካሂዳል።

በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮችና በመጭው ጥቅምት ሊያካሄደው ላቀደው የፓርቲው ጉባዬ ጠቅላላ አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል።

@ethio_mereja_news
አወዛጋቢው የህወሓት ጠቅላላ ድርጅታዊ ጉባኤ ነገ ይጀመራል‼️

👉በጉባኤው የሚሳተፉ አባላቱን ወደ መቀሌ ከተማ ሲገቡ ዛሬ አቀባበል ሲደረግ ውሏል።

የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ(ህወሓት) ምክትል ሊቀ መንበርን ጨምሮ 14 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት እንደማይሳተፉ የገለጹበት 14ኛው የፓርቲው ድርጅታዊ ጠቅላላ ጉባኤ፣ ነገ ማክሰኞ፣ ነሐሴ 7 ቀን 2016 ዓ.ም.፣ በመቐለ የሰማዕታት ሐውልት አዳራሽ እንደሚጀምር፣ የፓርቲው ጽሕፈት ቤት እና የጉባኤው አዘጋጅ ኮሚቴ ገልጿል፡፡

ድርጅታዊ ጠቅላላ ጉባኤው፣ “ጉባኤ ድኅነት” (የመዳን ጉባኤ) ተብሎ መሰየሙን፣ ፓርቲው በፌስቡክ የማኅበራዊ ትስስር ገጹ ላይ አስታውቋል፡፡

የፓርቲው ሊቀ መንበር ዶር. ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል፣ ትላንት እሑድ፣ ነሓሴ 5 ቀን 2016 ዓ.ም. ለብዙኀን መገናኛ በሰጡት መግለጫ፣ “ትልቅ ብልሽት ውስጥ ያለውን የህወሓት አመራር በማስተካከል ፓርቲውን ለማዳንና ሕዝቡ እንዲክስ ለማድረግ ጉባኤው አስፈላጊ ነው፤” ብለዋል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በነገው ዕለት ለሚካሄደው የህወሓት ጠቅላላ ጉባኤ፤ ምርጫ ቦርድ “እውቅና አልሰጥም” አለ!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፤ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በነገው ዕለት ለሚያካሄደው ጠቅላላ ጉባኤም ሆነ በጉባኤው ላይ ለሚተላለፉ ውሳኔዎች በሙሉ "እውቅና እንደማይሰጥ" አስታወቀ።

ህወሓት ጠቅላላ ጉባኤ ከማድረጉ 21 ቀናት በፊት ለምርጫ ቦርድ ማሳወቅ እና ፓርቲው በሚያደርገው ጠቅላላ ጉባኤ የቦርዱ ታዛቢዎች መገኘት እንደነበረባቸውም አስታውቋል።

ብሔራዊው ምርጫ ቦርድ ይህን ያስታወቀው፤ ዛሬ ሰኞ ነሐሴ 6፤ 2016 ለህወሓት በጻፈው ደብዳቤ ነው። የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ ፊርማ ያረፈበት ይህ ደብዳቤ፤ ህወሓት “ጠርቶታል” የተባለውን ጠቅላላ ጉባኤ የሚመለከት እንደሆነ በመግቢያው ላይ ተቀምጧል።

ይኸው ደብዳቤ፤ ህወሓት በቦርዱ “በልዩ ሁኔታ” እንዲመዘገብ ከተደረገ በኋላ ከቦርዱ የህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት እንደተሰጠው አስታውሷል። ህወሓት ይህ የምስክር ወረቀት ከደረሰው በኋላ የሚተዳደረው፤ በ2011 ዓ.ም በወጣው እና ባለፈው ግንቦት ወር በተሻሻለው፤ የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ ምግባር አዋጅ መሰረት መሆኑንም ቦርዱ ጠቅሷል።

(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

@sheger_press
በእጅዎ ያለው ጥሬ ገንዘብ ዋጋ እያጣብኝ ነው ብለው ተጨንቀዎል?
የብር ዋጋ መቀነስ ወይም የዶላር ጭማሪ ሳያሳስብዎ የሚፈልጉትን ቤት ከ ዲኤምሲ ሪልስቴት ያግኙ

ዲኤምሲ ወቅቱን ባገናዘበ በከፍተኛ ዋጋ ቅናሽ ጥራታቸውን የጠበቁ ቤቶችን በተለያዩ ካሬ አማራጮች አቅርቦሎታል

በእጆ የያዙት ብር ዋጋ ከማጣቱ በፊት በቋሚ ንብረት ይቀይሩት።
  -በ10% ቅድመ ክፍያ
  -50/50 የብድር አማራጭ
  -ከ8-25% ቅናሽ
  -ከስቱዲዮ እስከ ባለ 4 መኝታ ቤቶች እና ከተጨማሪ የሰራተኛ ክፍልና መታጠቢያ ጋር
❇️ለበለጠ መረጃ 0977190118 ይደውሉ
በፓሪስ ኦሎምፒክ የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልኡካን ቡድን አዲስ አበባ ገባ

በፓሪስ ኦሎምፒክ ድል ያስመዘገቡ እና የተሳተፉ የኢትዮጵያ ልኡካን ቡድን ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገብተዋል።

የልኡካን ቡድኑ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

በዛሬው እለት ከሰዓት በኋላ በብሔራዊ ቤተ-መንግስት ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ በተገኙበት ለልዑካን ቡድኑ የክብር ሽልማት፣ የማበረታቻ እና የእራት ግብዣ መርኃ-ግብር የሚካሄድ መሆኑንም ተገልጿል።

ኢትዮጵያ በ33ኛው የፓሪስ ኦሊምፒክ 1 የወርቅ እና 3 የብር በአጠቃላይ 4 ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ ከዓለም 47ኛ ከአፍሪካ ደግሞ 4ኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋ ይታወቃል።

@sheger_press
@sheger_press
2024/10/01 22:31:58
Back to Top
HTML Embed Code: