Telegram Web Link
ሰበር ፍልስጤም

አየርላንድ እና ስፔንን ጨምሮ ሶስት የአውሮፓ ሀገራት ፍልስጤምን እንደ ሀገር እውቅና ሰጥተዋል።

ኖርዌይ ለፍልስጤም መንግስት በይፋ እውቅና ሰጥታለች፣ ሲሉ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር በይፉ ተናግረዋል።

ይህንን ተከትሎ የእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሀገራቱ ለፍልስጤም ሉዓላዊነት እውቅና የሰጡትን ውሳኔ በመቃወም የአየርላንድ እና የኖርዌይ አምባሳደሮች በአስቸኳይ እንዲጠሩ አዝዟል።

@ethio_mereja_news
ኢትዮጵያ በሶማሊላንድ፣ ሃርጌሳ የሚገኘውን የቆንስላ ጽህፈት ቤቷን ሙሉ አገልግሎት ወደሚሰጥ ኤምባሲ ማሳደጓን የሶማሊላንድ ሚኒስትር ገለጹ‼️

የሶማሊላንድ የመረጃ፣ የባህል እና የብሔራዊ መመሪያ ሚኒስትር አሊ ሐሰን መሐመድ (አሊ ማርሃን) ለቢቢሲ ሶማሊኛ ከቀናት በፊት ራሷን በነጻ አገርነት ያወጀችው የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት ሙሳ ቢሂ አብዲ ቆንስላው ወደ ኤምባሲ ማደጉን አስመልክቶ የተናገሩትን አረጋግጠዋል።

ከአንድ ወር በፊት ሶማሊያ በሶማሊላንድ እና በቱንትላንድ ግዛት የሚገኙ የኢትዮጵያ ቆንስላ ፅ/ቤቶች እንዲዘጉ ውሳኔ ማሳለፏ የሚታወስ ነው።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ትናንትና ከትናንት ወዲያ ሪያድ ውስጥ ስድስተኛው የኢትዮጵያና ሳዑዲ ዓረቢያ የሚንስትሮች ኮሚሽን ስብሰባ ተካሂዷል።

ኹለቱ ወገኖች በጸጥታ፣ ሰላም፣ ንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ እንስሳት፣ ግብርና፣ መሠረተ ልማት፣ ኢነርጂና ማዕድን ዘርፎች የኹለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር እንደተስማሙ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል።

የኢትዮጵያን ልዑካን ቡድን የመሩት፣ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ታዬ አጽቀሥላሴ እንደኾኑና ከአገሪቱ የውሃ፣ አካባቢና ግብርና ሚንስትር ጋር ጭምር እንደተወያዩ ተገልጧል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ትናንትና ከትናንት ወዲያ ሪያድ ውስጥ ስድስተኛው የኢትዮጵያና ሳዑዲ ዓረቢያ የሚንስትሮች ኮሚሽን ስብሰባ ተካሂዷል።

ኹለቱ ወገኖች በጸጥታ፣ ሰላም፣ ንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ እንስሳት፣ ግብርና፣ መሠረተ ልማት፣ ኢነርጂና ማዕድን ዘርፎች የኹለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር እንደተስማሙ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል።

የኢትዮጵያን ልዑካን ቡድን የመሩት፣ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ታዬ አጽቀሥላሴ እንደኾኑና ከአገሪቱ የውሃ፣ አካባቢና ግብርና ሚንስትር ጋር ጭምር እንደተወያዩ ተገልጧል።

@ethio_mereja_news
#Tecno #Camon30Pro5G

ፍጥነት እና ቅልጥፍና መገለጫው የሆነውን MediaTek Dimensity 8200 ፕሮሰሰር አካቶ Tecno Camon 30 pro 5G ቀርቦሎታል

#Camon30Et #Camon30proEt #Camon30 #Camon30Pro #TecnoEt
ለአሸከርካሪዎች ዝግ የተደረጉ መንገዶች‼️

ዛሬ ከ11:00 ጀምሮ ከፖሊስ ስራ ጋር በተያያዘ ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት ፕሮግራም ይካሄዳል፡፡

👉 ከልደታ በላይኛው መንገድ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ

👉 ከአፍሪካ ህብረት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ

👉 ከጠማማ ፎቅ በንግድ ምክር ቤት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ

👉 ከገነት መብራት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ

👉 ከሰንጋ ተራ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ

👉 ከዲአፍሪክ ሆቴል ወደ ሜክሲኮ አደባባይ

👉 ከቡናና ሻይ በላይኛው መንገድ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ

ፕሮግራሙ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ ስለሆኑ አሽከርካሪዎች የትራፊክ መጨናነቅ እንዳያጋጥማቸው አማራጭ መንገዶች እንዲጠቀሙ አዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

@sheger_press
"ዘንድሮ በወረቀት ከሚሰጠው ፈተና ጎን ለጎን ለመጀመሪያ ጊዜ በኦንላይን የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መንግሥት በሚያዘጋጃቸው ኮምፒውተሮች ይከናወናል፡፡" - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

በዚህ ዓመት የ12ኛ ክፍል ፈተና በወረቀት እንዲሁም በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወቃል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ በተለይ የግል ትምህርት ቤት ተፈታኞች የራሳቸውን ላፕቶፕ እንዲያዘጋጁ ተወስኗሉ የሚሉ መረጃዎች ሲዘዋወሩ ታይቷል፡፡

"ይህንን በተመለከተ ለትምህርት ቤቶች የተላለፈ መልዕክት አለመኖሩንና ወላጆች ኮምፒውተር እንዲያዘጋጁ መጠየቃቸውም ተገቢ አለመሆኑን" የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) ለኢቢሲ ተናግረዋል፡፡

"ፈተናው መንግሥት በሚያዘጋጀው የኮምፒውተር አቅርቦት ይከናወናል" ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፤ "ተማሪዎች አንብበውና በቂ ዝግጅት አድርገው የተመዘገቡበትን መታወቂያ ብቻ ይዘው መምጣት ነው የሚጠበቅባቸው" ብለዋል፡፡ "ሆኖም ትምህርት ቤቶችም ሆኑ ተማሪዎች የግል ኮምፒውተሮቻቸውን ለፈተናው መጠቀም ከፈለጉ እንደማይከለከሉ" ተናግረዋል፡፡

በኦንላይን ፈተና የሚወስዱ ተፈታኞች ካሳለፍነው ሳምንት ጀምሮ በልምምድ ላይ እንደሚገኙ ያነሱት ኃላፊው፤ 156 የኮምፒውተር ባለሙያዎች ሰልጥነው በክልሎች ስልጠና እንዲሰጡ መሰማራታቸውን ጠቁመዋል፡፡

በዘንድሮው ፈተና ልምዶችን በመያዝ፤ በሚቀጥሉት ከ3 እስከ 5 ዓመታት ጊዜ ውስጥ የ12ኛ ክፍል ፈተናን ሙሉ በሙሉ በኦንላይን የመስጠት ዕቅድ መኖሩን ገልፀዋል፡፡

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሐምሌ 3-5/2016 ዓ.ም ለማኅበራዊ ሳይንስ እንዲሁም ከሐምሌ 9-11/2016 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ይሰጣል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ሰከላ ከግንቦት 5-7 ወደ ቤተክርስቲያን ሲሄዱ የነበሩ እና የሰርግ ስነስርዓትን ታድመው ይመጡ የነበሩትን ጨምሮ አጠቃላይ 40 ሰዎች በፀጥታ ሀይሎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎችንና የተጎጂ ቤተሰቦችን አነጋግሮ አሻም ቲቪ ዘግቧል።

ከዚህ ቀደም ብሎ ግንቦት 4 በፋኖ ሀይሎች እና በመከላከያ ሰራዊት መካከል ውጊያ እንደነበር ተገልጿል።

የአካባቢው ነዋሪዎች በስጋት ምክንያት አካባቢያቸውን ለቀው ወደ ባህርዳር እና ወደ ገጠራማ አካባቢዎች መሰደዳቸውን ዘገባው ጠቅሷል።

የምዕራብ ጎጃም ዞን ኮማንድ ፖስት ም/ሰብሳቢ አቶ እእድሜአለም አንተነህ በበኩላቸው በአካባቢው ውጊያ እንደነበር ገልፀው ነገርግን አንድም ንፁሃን አልሞቱም ሲሉ ለጣቢያው መናገራቸውን ሸገር ተመልክቷል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
#Tecno #Camon30Pro5G

ቴክኖ ሞባይል በአይነቱ የተራቀቀውን አዲሱን Tecno Camon 30 pro 5G ምርጫዎ ያድርጉ ሲል ይጋብዛል!

#Camon30Et #Camon30pro5GEt #Camon30 #Camon30Pro5G #TecnoEt
በአዲስ አበባ የመንደር ንግድ ቁጥጥር የአሰራር ስርዓት መመሪያ ሊተገበር ነው ተባለ 🥹

የንግድ ስርዓቱን ፍትሃዊና ቀልጣፋ ለማድረግ የሚያግዝ የመንደር ንግድ ቁጥጥር የአሰራር ስርዓት መመሪያን ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጅት ማጠናቀቁን የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ አስታወቀ።

መመሪያውን አስመልክቶ ቢሮው በሰጠው መግለጫ እንዳመለከተው መመሪያ ቁጥር 159 /2016 ተግባር ላይ ሲውል የንግድ ስርዓቱን ፍትሃዊና ቀልጣፋ ለማድረግ እገዛ ያደርጋል ብሏል።

መመሪያው በወረዳ ደረጃ ያሉ የንግድ ተቆጣጣሪዎች ቁጥጥር የሚያደርጉበትን ስርዓት ያመላከተ ነው ተብሏል።

እንዲሁም የንግድ ፍቃድ ሳይኖራቸው የሚሰሩትን ከአስተዳደራዊ እስከ ህጋዊ እርምጃ የሚወሰድበት አግባብ ላይ አፅንኦት የሰጠ መሆኑም ተገልጿል።

መመሪያው ህግና ስርአትን የተከተለና ወጥነት ያለው አሰራር በሁሉም ወረዳዎችና ክፍለ ከተሞች ለመዘርጋትም እድል ይፈጥራል ተብሏል።(Arada_Fm)

@ethio_mereja_news
በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን ከሚገኘው ኦላላ መጠለያ ጣቢያ ከኹለት ሺህ በላይ የሱዳን ስደተኞች ከሐሙስ ጀምሮ የርሃብ አድማ ማድረጋቸውን የሱዳን ዜና ምንጮች ዘግበዋል።

ስደተኞቹ የርሃብ አድማ ያደረጉት፣ በመጠለያ ጣቢያው የደኅናነት ስጋት በመባባሱና የአገልግሎቶች አቅርቦት በማሽቆልቆሉ እንደኾነ ዘገባዎቹ አመልክተዋል።

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኩርሙክ የስደተኞች መጠለያም፣ ሱዳናዊያን ስደተኞች በተመሳሳይ ምክንያት የርሃብ አድማ ማድረጋቸው ተነግሯል።

በኹለቱ ክልሎች ከ47 ሺህ በላይ የሱዳን ስደተኞች እንደሚገኙ የተመድ ስደተኞች ኮሚሽን መረጃ ያመለክታል።

@ethio_mereja_news
#Tecno #Camon30Pro5G

Tecno Camon 30 pro 5G እያንዳንዱ ፎቶ እና ቪድዮ ከፍተኛ ጥራት እንዲላበሱ የSony IMX890 ካሜራ ሴንሰር ገጥሞ ቀርቧል!

#Camon30Et #Camon30Pro5GEt #Camon30 #Camon30Pro5G #TecnoEt
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር፣ ከአላማጣ አካባቢ ገርጃለ እና በቅሎ ማንቂያ ከተባሉ ቦታዎች "የተወሰኑ" የትግራይ ተዋጊዎች እንዲወጡ ማድረጉን የክልሉ ቴሌቪዥን ትናንት ምሽት ዘግቧል።

ጊዜያዊ አስተዳደሩ ተዋጊዎች ከተጠቀሱት አካባቢዎች እንዲወጡ ያደረገው፣ በፕሪቶሪያው የግጭት ማቆም ስምምነት የትግበራ እቅድ መሠረት ወደ ቀያቸው ለሚመለሱ ተፈናቃዮች ደኅንነት ሲል እንደኾነ ዘገባው አመልክቷል።

ጊዜያዊ አስተዳደሩ ከኹለቱ አካባቢዎች ምን ያህል ተወጊዎች እንዳስወጣ ግን ዘገባው አልጠቀሰም።

የትግራይ ኃይሎች እና የአማራ ክልል ታጣቂዎች ከሳምንታት በፊት በተጠቀሱት አካባቢዎች መጋጨታቸውና የትግራይ ኃይሎችም አካባቢዎቹን መቆጣጠራቸው እንደተዘገበ አይዘነጋም።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን ከሚገኘው ኦላላ መጠለያ ጣቢያ ከኹለት ሺህ በላይ የሱዳን ስደተኞች ከሐሙስ ጀምሮ የርሃብ አድማ ማድረጋቸውን የሱዳን ዜና ምንጮች ዘግበዋል።

ስደተኞቹ የርሃብ አድማ ያደረጉት፣ በመጠለያ ጣቢያው የደኅናነት ስጋት በመባባሱና የአገልግሎቶች አቅርቦት በማሽቆልቆሉ እንደኾነ ዘገባዎቹ አመልክተዋል።

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኩርሙክ የስደተኞች መጠለያም፣ ሱዳናዊያን ስደተኞች በተመሳሳይ ምክንያት የርሃብ አድማ ማድረጋቸው ተነግሯል።

በኹለቱ ክልሎች ከ47 ሺህ በላይ የሱዳን ስደተኞች እንደሚገኙ የተመድ ስደተኞች ኮሚሽን መረጃ ያመለክታል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ኩዌይት የገጠማትን የቤት ሠራተኞች እጥረት ለመቅረፍ፣ ሰሞኑን አንድ ልዑካን ቡድን ወደ ኢትዮጵያ እንደምትልክ የአገሪቱ ጋዜጣ ኩዌይት ታይምስ አስነብቧል።

ከኢትዮጵያ ሠራተኞችን መቅጠር በሚችልበት ኹኔታ ዙሪያ ለመምከር በመጪው ሳምንት ሰኞ ወደ ኢትዮጵያ የሚጓዘው ልዑካን ቡድን፣ የመንግሥት ባለሥልጣናትንና የሠራተኛ ቅጥር ቢሮዎችን ሃላፊዎች ያካተተ እንደኾነ ዘገባው አመልክቷል።

ኩዌይት የቤት ሠራተኞች እጥረት የገጠማት፣ የፊሊፒንስ መንግሥት በኹለቱ አገራት መካከል የተፈረመውን የሠራተኛ ቅጥር ስምምነት አላከበረም በማለት ካለፈው ዓመት ግንቦት ጀምሮ ከፊሊፒንስ ሠራተኞችን መቅጠር በማቆሟ እንደሆነ ተገልጧል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሰኔ 10 ጀምሮ ወደ ኦሮሚያ ክልል ነቀምቴ ከተማ አቋርጦት የነበረውን በረራ እንደገና እንደሚጀምር ማስታወቁን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘግቧል።

አየር መንገዱ ወደ ነቀምቴ በድጋሚ በረራ የሚጀምረው፣ በሳምንት አራት ጊዜ እንደኾነ መናገሩን ዘገባው አመልክቷል።

አየር መንገዱ የበረራ ብዛቱን ለማሳደግ የአውሮፕላን ማረፊያውን የቀድሞ የመንገደኞች ተርሚናል የማደስ ሥራ በቅርቡ ይጀምራል መባሉንም ዘገባው ጨምሮ ጠቅሷል።

አየር መንገዱ ከጥቂት ሳምንታት በፊት፣ ለዓመታት አቋርጦት የቆየውን የደምቢዶሎ በረራ በድጋሚ መጀመሩ አይዘነጋም።

@ethio_mereja_news
ኢትዮጵያ፣ በአውሮፓ ኅብረት አዲስ የደን ጥበቃ ሕግ መሠረት የቡና ምርቷን ሰንሰለት ወደምታስተካክልበት ደረጃ ለመሸጋገር ፍላጎት ካሳየች ኅብረቱ የገንዘብ ድጋፍ ሊያደርግ እንደሚችል ከኅብረቱ ምንጮች መስማቱን ጠቅሶ ሊ ሞንድ ጋዜጣ ዘግቧል።

በቀጣዩ የፈረንጆች ዓመት ተግባራዊ የሚኾነው የኅብረቱ አዲስ ሕግ፣ አባል አገራት ደኖችን በመጨፍጨፍ የተመረተ ቡና ከውጭ አገራት ገዝተው እንዳያስገቡ የሚያግድ ነው።

ኢትዮጵያ በዚህ ረገድ ከሌሎች ቡና አምራችና ላኪ የአፍሪካ አገራት ወደኋላ እንደቀረች የኅብረቱ ምንጮች መጠቆማቸውንም ዘገባው አመልክቷል።

አንዳንድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች ኢትዮጵያ የቡና ምርቷን ሰንሰለት ከኅብረቱ አዲስ ሕግ ጋር ለማጣጣም በትንሹ አምስት ዓመት ያስፈልጋታል ብለዋል ያለው ዘገባው፣ አንድ የሆላንድ ኩባንያ በደን ጭፍጨፋ የተመረተ የኢትዮጵያ ቡና ካለ በሳተላይት የመለየት ሥራ መጀመሩ አገሪቱን ከችግር ሊታደጋት ይችል ይኾናል ብሏል።

@ethio_mereja_news
የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ከመጽደቁ ከኹለት ወራት በፊት ያቀረብኳቸው አብዛኞቹ ምክረ ሃሳቦች ወደ ጎን ተገፍተዋል በማለት ለፍትህ ሚንስቴር ቅሬታ ማቅረቡን ከኮሚሽኑ ሚስጢራዊ ሰነድ መመልከቱን ጠቅሶ ሪፖርተር ዘግቧል።

በሽግግር ፖሊሲው ውስጥ ሳይካተት ከቀረው የኮሚሽኑ ምክረ ሃሳብ አንዱ፣ ፖሊሲው "ለሰብዓዊ መብት ጥሰት ተጎጂዎች" የሰጠው ትርጉም አብዛኛውን የኅብረተሰብ ክፍል አግልሏል የሚል እንደኾነ ዘገባው አመልክቷል።

የባለሥልጣናት የሕግ ከለላ፣ ከመብት ጥሰት ተጠያቂነት እንደማያድናቸው በፖሊሲው ውስጥ በግልጽ እንዲጠቀስና ፖሊሲው ግልጽና ተዓማኒ እንዲኾን የዓለማቀፍ ፍርድ ቤቶች ትብብር እንደሚያስፈልግ እንዲያካትት ኮሚሽኑ ያቀረባቸው ምክረ ሃሳቦችም በተመሳሳይ አልተካተቱም ተብሏል።

ኮሚሽኑ፣ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲው ለኹሉም ጥሰቶች "ኹሉን ዓቀፍ የሕግ መሠረት" ሊኾን እንደማይችል የሚገልጽ ሌላ ሕግ እንዲወጣ መጠየቁንም ዘገባው ጠቅሷል።

@ethio_mereja_news
2024/11/18 17:21:21
Back to Top
HTML Embed Code: