Telegram Web Link
#Tecno #Camon30Pro5G

ልዩ ዲዛይን እና ቴክኖሎጂ አጣምሮ የቀረበዉ Tecno Camon30 Pro 5G ምርጫዎ ያድርጉ!

#Camon30Et #Camon30Pro5GEt #Camon30 #Camon30Pro5G #TecnoEt
በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለሺ በቀለ ያቀረቡት መልቀቂያ ተቀባይነት ማግኘቱ ተሰማ

በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው እያገለገሉ የሚገኙት የቀድሞው የውኃ ሀብት ሚኒስትር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) ከተሾሙበት የመንግሥት የሥራ ኃላፊነት ለመልቀቅ ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቱን ምንጮች ገለጹ።

ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደርነት ሹመታቸው ብቻ ሳይሆን ሙሉ በሙሉ ከመንግሥት መዋቅር በመልቀቅ በግል ተቀጥረው በሙያቸው ለማገልገል ማቀዳቸውንም ምንጮቹ ገልጸዋል።

ስለሺ (ዶ/ር) በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የሥልጣን ዘመን ወቅት የፓርቲ አባል ሳይሆኑ የመንግሥት መዋቅርን መቀላቀላቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ከዚያ አስቀድመው በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በውኃ ምኅንድስና ሙያቸው በግል ተቀጥረው ሲያገለግሉ ነበር።

ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) ከአሜሪካ አምባሳደርነታቸው በመልቀቅ ወደ ቀደመ የግል ሥራቸው ለመመለስ መፈለጋቸውን የጠቀሱት የሪፖርተር ምንጮች፣ ጥያቄያቸውንም ለመንግሥት አቅርበው ተቀባይነት ማገኘቱን ገልጸዋል።

አምባሳደር ስለሺ በቀለ መልቂቂያ ስለማቅረባቸውና መልቀቂያውም ተቀባይነት ማግኘቱን በመጥቀስ መረጃውን እንዲያረጋግጡ የጠየቅናቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ነብዩ ተድላ (አምባሳደር)፣ ስለዚህ ጉዳይ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ገልጸዋል ሲል የዘገበው ሪፖርተር ጋዜጣ ነው።

@ethio_mereja_news
ኦሮሚያ ባንክ ለብድር ካቀረበው 43.5 ቢሊዮን ብር 26 በመቶ የሚሆነውን ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች በብድር ማቅረብን አስታወቀ!

ከተመሰረተ 15 ዓመታት ያስቆጠረው ኦሮሚያ ባንክ 54 ቢሊዮን ብር በቁጠባ መልክ ማሰባሰቡን፤ ከዚህ ውስጥም ለብድር ካቀረበዉ 43.5 ቢሊዮን ብር ዉስጥ በነፍስ ወከፍ ሲሰላ በአማካይ አንድ ተበዳሪ 1.5 ሚሊዮን ብር ከባንኩ ማግኘቱ ተገልጿል።ይህም የብድር ስርጭቱ ከባንኩ ደንበኞች ምጣኔ አኳያ 92 በመቶ ይይዛል እንዲሁም ከተበደሩት ብድር አንፃር ደግሞ 26 በመቶ ይሸፍናሉ ተብሏል።

ቀሪው የብድር አቅርቦት ለከፍተኛ ተበዳሪዎች ማቅረብን የገለፀዉ የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተፈሪ መኮንን ይህም የብድር አቅርቦት በአማካይ አንድ ተበዳሪ 5 ሚሊዮን ብድር መውሰዱ ተናግረዋል።የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተፈሪ መኮንን ጨምረዉ እንደተናገሩት የባንኩ የተበላሸ የብድር መጠኑ ከ1.6 በመቶ እስከ 2 በመቶ የሚደርስ እንደሆነ ገልፀዋል።

በብሔራዊ ባንክ መመሪያ መሰረት የተበላሸ ብድር መጠን ጣሪያ 5 በመቶ መሆኑን የጠቀሱት ፕሬዝዳንቱ አሁን ላይ በዘርፉ ያለው አማካይ የተበላሸ የብድር መጠን 3.6 በመቶ መሆኑን አብራርተዋል።አሁን ላይ ቅርንጫፎችን ከመክፈት ወደ ዲጂታል የባንክ አገልግሎት ፊቱን ያዞረዉ ባንኩ "ኦሮ ዲጂታል" በተሰኘው አገልግሎት ቴሌግራምን ጨምሮ በ7 አማራጮች አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።

Via Capital
@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
መንግስት  እየፈጸመብኝ  ያለው ከፍተኛ ጥቃትና ጫና አስጊ ደረጃ ላይ ደርሷል ሲል ኢሰመጉ ገለፀ።

ኢሰመጉ ይህን ያለው አሁን አመሻሽ ላይ ባወጣው መግለጫው ላይ ነው።

በመግለጫውም እንዳሰፈረው ኢሰመጉ፣ በስራ ኃላፊዎች፣ ሰራተኞችና አባላት ላይ በፌደራልና በክልል መንግስታት እንዲሁም በከተማ አስተዳደሮችና በሌሎች የመንግስት አካላት እየደረሱ ያሉ ጥቃቶች አስጊ ደረጃ ላይ ደርሷል ብሏል።

እየደረሱ ካሉት መካከል ግድያዎች፣ ህገ ወጥ እስሮችን፣ ጥቃቶችን፣ ከፍተኛ ጫናዎች፣ማስፈራሪያዎች፣ ዛቻዎች፣ ማሸማቀቆች፣ እንግልቶች፣ ስልታዊ የስራ ገደቦች፣ የምርመራ ፈቃድና የመረጃ ክልከላዎች፣ ህገ ወጥ ከትትሎች፣ ቢሮ ሰበራዎች፣ የንብረት ነጠቃ እና መውሰድ፣ ስም ማጥፋትና ውንጀላና እየደረሰብኝ ነው ሲል ገልጿል ።

የተገለጹት ጫናዎች  በሌሎች መሰል የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች እንዲሁም ተቋማት ላይ እየተፈጸሙ ያሉ ጫናዎች ሲሆኑ በአገሪቱ ያለው የሲቪል ምህዳር ምን ያክል አሳሳቢ ሁኔታ ላይ መድረሱን የሚያሳይ ነው ሲልም ተችሏል ።

በመሆኑ መንግስት ለሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች የሚያደርገውን ጥበቃ ምቹና አስቻይ የሆኑ የህግና የፖሊሲ ማዕቀፎችን በመዘርጋትና በመተግበር በአገሪቱ ያሉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች እንዲሁም ተቋማቶቻቸው በነጸነት ተንቀሳቅሰው ደኅንነታቸው ተጠብቆ የሰብዓዊ መብቶች የማስከበር ስራዎችን የሚሰሩበት ሁኔታ እንዲፈጥር ጠይቁል።


በዓለም አቀፍ፣ በአህጉር አቀፍና በአገር አቀፍ ደረጃ ሰብዓዊ መብቶች ላይ የሚሰሩ ተቋማትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በኢሰመጉ ላይ በመንግስት አማካኝነት እየደረሱ ያሉ አስጊ ደረጃ ላይ የደረሱ ጥቃቶችና ከፍተኛ ጫናዎችን በመገንዘብ እነዚህ ጥቃቶችና ከፍተኛ ጫናዎች እንዲቆሙና ተጠያቂነት እንዲሰፍን እንዲያደርጉ እንዲሁም ከለላን በማቅረብ የበኩላቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ሲል አሳስበዋል ።

ኢሰመጉ ከምስረታው ጊዜ አንስቶ በርካታ የሰብዓዊ መብቶችን የማስከበር ስራዎችን ሲሰራ የቆየ መንግስታዊ ያልሆነ ተቋም ነውም ተብሏል።

Ethio FM
@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የሕገመንግሥት አጣሪ ጉባዔ፣ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከኅዳር 26 ቀን ጀምሮ ተግባራዊ ባደረገው አዲስ ደንብ ዙሪያ ምላሽ እንዲሰጥ መጠየቁን ሪፖርተር ዘግቧል።

ደንቡ እንዲሻር ለጉባዔው የሕገመንግሥት ትርጉም ጥያቄ ያቀረበው "ቅድሚያ ለሰብዓዊ መብቶች" የተባለ ሲቪክ ድርጅት ነበር።

አቤቱታው፣ ደንቡ በሕግ የፈረሰው የክልሉ ምክር ቤት ያወጣቸው ሕጎች ተፈጻሚነታቸው እንዲቀጥል አድርጓል የሚል ነው።

ደንቡ ካስቀጠላቸው አዋጆች መካከል፣ የክልሉን ፖሊስ ኮሚሽን አፍርሶ ሌላ ኮሚሽን ያቋቋመውና በጦርነቱ አንሳተፍም ያሉ በርካታ ፖሊሶች የተባረሩበትና የጡረታ መብታቸው የታገደበበት አዋጅ እንደሚገኝበት ዘገባው አመልክቷል።

ከጥቅምት 24 ቀን 2013 እስከ ኅዳር 30 ቀን 2015 ዓ፣ም ሠራተኞች በውዝፍ ደመወዝ ዙሪያ የሚያቀርቡት አዲስ ክስ ታግዶ እንዲቆይ መደረጉም ሌላኛው አቤቱታ ነው ተብሏል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የሶማሌላንድ ራስ ገዝ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ፣ ሶማሊላንድ ከኢትዮጵያ ጋር የተፈራረመችው የባሕር በር የመግባቢያ ስምምነት የዓለማቀፍ የንግድ መርከቦችን እንቅስቃሴ ደኅንነት አስተማማኝ ለማድረግ ያስችላል ማለታቸውን ፋይናንሻል ታይምስ ጋዜጣ አስነብቧል።

በስምምነቱ መሠረት፣ ኢትዮጵያ ሶማሊላንድ ውስጥ የባሕር ኃይል ጣቢያ ከመገንባት በተጨማሪ የንግድ መርከቦች እንደሚኖሯትና ሶማሊላንድም ከኢትዮጵያ የአገርነት እውቅና እንደምታገኝ ቢሂ መናገራቸውን ዘገባው አመልክቷል።

ቢሂ፣ ስምምነቱ ተግባራዊ ከኾነ፣ በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል በባሕር በር ሳቢያ ግጭት እንዳይቀሰቀስ ያደርጋል ማለታቸውም ተገልጧል።

በመግባቢያ ስምምነት ውስጥ ተሳታፊ የኾኑ አንድ የኢትዮጵያ ባለሥልጣንም፣ ስምምነቱ ተግባራዊ ይኾናል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ጠቁመዋል ተብሏል።

@ethio_mereja_news
በነፃ ዱባይ ሄደው መዝናናት ይፈልጋሉ? 😎

ቀላል ነው! ከግንቦት 7- ሰኔ 7 የYangoን መተግበሪያ ከAppstroe ወይም Playstore አውርደው፣ የመጀመሪያ ጉዞዎን ያድርጉ። 🚗

አሸናፊው በዕጣ ይመረጣል፤ ውድድሩ እንደተጠናቀቀ አሸናፊውን እናሳውቃለን። መልካም ዕድል!
ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በዓለም አቀፍ የአይሲቲ ፍጻሜ ውድድር አሸነፉ

ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በቻይና በተካሄደው የሁዋዌ ዓለም አቀፍ የአይሲቲ ፍጻሜ ውድድር ሦስተኛውን ሽልማት አሸነፉ።በቻይና ሼንዘን ከተማ በኮምፒውቲንግ ትራክ የተሳተፉት ሦስት ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ሦስተኛውን ሽልማት ከማሌዢያ፣ ሜክሲኮ እና ኬንያ ቡድኖች ጋር ተጋርተዋል።

ውድድሩ ከግንቦት 14 እስከ 18 ቀን 2016 ዓ.ም ከመላው ዓለም የተውጣጡ ተማሪዎች በተሳትፉበት በሦስት የውድድር ትራኮች ተከፋፍሎ የተካሄደ መሆኑ ተገልጿል፡፡በውድድሩ ከአርባ ምንጭና ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች በተገኙ ተማሪዎች የተወከለው የኢትዮጵያ ቡድን በኮምፒውቲንግ ትራክ ውድድር ሽልማት አሸንፎ ዛሬ ወደ ሀገሩ መመለሱን የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

ሚኒስቴሩ የተማሪዎችን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት እድል የሚፈጥሩ ውድድሮች ላይ ተሳትፎውን በማሳደግ ከዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች ጋር መስራቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጾ÷ ውድድሩን ላሸነፉ ተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፏል።

@ethio_mereja_news
Public Holidays draft law.pdf
420.3 KB
ግንቦት 20 ስራ ዝግ ይሆናል⁉️

ግንቦት 20 ለአመታት በህዝባዊ በዓላት ዝርዝር ዉስጥ ተካትቶ በህግ ሳይጸድቅ ሲከበር ቆይቷል። ግንቦት 20 የያኔዉ ኢህአዴግ የደርግ መንግስትን ገልብጦ ስልጣን የያዘበት ወይንም ማዕከላዊ መንግስትን የተቆጣጠረበት እለት ሆኖ በየአመቱ ስራ እና ትምህርት ዝግ ሆኖ ሲከበር ቆይቷል።

የህግ ባለሙያዎች ግንቦት 20 ለአመታት ሲከበር የቆየበት መንገድ ህጋዊ መሰረት የሌለዉ መሆኑን ሲናገሩ ይደመጣል። በአሉ በልማድ በህዝብ በዓላት ዝርዝር ዉስጥ ቢገባም በም/ቤት ጸድቆ እንዲከበር ግን አልተወሰነም ይላሉ። የሆነዉ ሆኖ ግንቦት 20 በተለይም ላለፉት 29 አመታት በድምቀት ሲከበር ቆይቷል። ከኢትዮጵያ በተጨማሪም የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ባሉባቸዉ ሀገራትም ቀኑ ታስቦ ይዉል ነበር።

ኢህአዴግ ከመፍረሱ ጥቂት አመታት በፊትም ሆነ ከፈረሰ በኋላ ቀኑ በተቀዛቀዘ መልኩ ሲከበር እና ኋላ ላይም ሲቀር ተመልክተናል። እለቱ ትምህርት እና ስራ ዝግ ሆኖ ይከበር በመሆኑ ኢህአዴግ ስልጣኑን ካጣ በኋላ የቀኑ መከበር እና አለመከበር ፤ ስራና ትምህርት ዝግ መሆን እና አለመሆኑ በየአመቱ ለሰዎች አዲስ ሆኖ ጥያቄ ይፈጥራል። ከዚህ ቀደም በአሉ ሲከበርበት የቆየበት መንገድ ህጋዊ መሰረት የሌለዉ መሆኑን ያነጋገርናቸው የህግ ባለሙያዎች ነግረዉናል። በተጨማሪም በቅርቡ በቀረበዉ ረቂቅ አዋጅ ላይም በአሉ አለመካተቱን ነግረዉናል። ይህንንም ጥያቄ ለመመለስ በቅርቡ በሚኒስሮች ም/ቤት እና በፍትሕ ሚኒስቴር ተዘጋጅቶ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የተመራዉን የሕዝብ በዓላትን እና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ዳጉ ጆርናል ለመመልከት ሞክሯል።

በቅርቡ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ይጸድቃል የሚባለዉ ረቂቅ አዋጅ ላይ ታድያ ግንቦት 20 ከህዝባዊ በዓላት ዝርዝር ዉስጥ አልተካተተም። በዚህም መሰረት አዋጁ ሲጸድቅ ግንቦት 20 በህዝባዊ በአልነት የማይከበር እና ስራም ሆነ ትምህርት ዝግ የማይደረግበት ቀን ነዉ ለማለት ያስችላል።

አሁን ላይ አዋጁ ባይጸድቅም ቀድሞዉንም ሆኖ በአሉ የሚከበርበት መንገድ ህጋዊ መሰረት የሌለዉ በመሆኑ በእለቱ ስራም ሆነ ትምህርት እንዲዘጋ የሚያስገድድ አግባብ የለም።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
"ነገ ተቋማት ዝግ ሆነው ይውላሉ"

የመንግስት ኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ "አዲሱ የበዓላት ሕግ ገና አልጸደቀም፤ ስለዚህ ዝግ ነው" ብለዋል።

የኮሙኒኬሽን ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ከበደ ደሲሳ <<በካላንደር ላይ የተለወጠ ነገር ስለመኖሩ እርግጠኛ አይደለሁም።ካላንደር ይዘጋዋል።ካላንደር እንደሚዘጋው ነው የምናውቀው ለምን እንዳወዛገበ አይገባኝም ። መስሪያ ቤቶች በራሳቸው ውሳኔ ሥራዎችን ሊያቅዱ ይችላሉ። ከሠራተኞቻቸው ጋር ተስማምተው>> ሲሉ አስረድተዋል።

ሁለቱም የስራ ኃላፊዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሰጡት ቃል የተወሰደ ነው።

@ethio_mereja_news
ጥቆማ‼️

Hamster‼️

Guys ይህ ትልቅ ብር ማግኛ ኤርድሮፕ ነው እየተባለ ይገኛል
ምንም ብር ስለማታወጡበት ብትሞክሩት አይከፋም ባይ ነን

ያልጀመራቹ ጊዜው ሳይረፍድ አሁንኑ በዚ ሊንክ ጀምሩት👇

ለመጀመር👇👇
https://www.tg-me.com/hamster_kombat_bot/start?startapp=kentId769729488


አጨዋወቱን ለከበዳቹ ዝርዝሩን በዚ ቻናል ያገኙታል👇👇
https://www.tg-me.com/sheger_crypto
ፍርድ ቤቱ የዋስትና ጥያቄውን በድጋሚ ውድቅ አደረገ

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቤተክህነት ጽሕፈት ቤት ሥራ አስኪያጅ የኾኑት ቀሲስ በላይ መኮንንና ግብረ አበሮቻቸው ማረሚያ ቤት ኾነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ወስኗል፡፡

ፍርድ ቤቱ ትናንት ሰኞ ብይኑን የሰጠው፣ ተከሳሾቹ የተከሰሱበት ከባድ የሙስና ወንጀል ከ10 ዓመት በላይ የእስር ቅጣት ሊያስጥል እንደሚችል በመግለጽ ነው።
ከምዝበራ መኩራው ጋር በተያያዘ የተከሰሱት
1ኛ. ቀሲስ በላይ መኮንን፣
2ኛ. በግብርና ኢንቨስትመንት ላይ የተሰማራው እያሱ እንዳለ ወ/መስቀል፣
3ኛ. በኮሚሽን ስራ ላይ የተሰማራው በረከት ሙላቱ ጃፋር፣
4ኛ. አለምገና ሳሙኤል ዲንሳ
5ኛ. የኒሞና ንግድ ስራ ኃላ/የተ/የግል ማህበር ስራ አስኪያጅ አበራ መርጋ ተስፋዬ ናቸው።

ከ1ኛ እስከ 3ኛ ያሉ ተከሳሾች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር።

ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄም ውድቅ ተደርጎ በማረፊያ ቤት እንዲቆዩ ታይዟል።

ፍርድ ቤቱ፣ የተከሳሾች ጠበቆች ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄም በድጋሚ ውድቅ አድርጓል። ኾኖም ፍርድ ቤቱ የቀሲስ በላይን የጤና ኹኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት እስከ ቀጣዩ ተለዋጭ ቀጠሮ ግንቦት 29 ድረስ በፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ እንዲቆዩ አዟል።

ቀሲስ በላይ ባለፈው ሚያዝያ በቁጥጥር ሥር የዋሉት፣ በአፍሪካ ኅብረት ግቢ ውስጥ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ሐሰተኛ ሰነዶችን በመጠቀም፣ ከኅብረቱ የባንክ ሒሳብ  ከስድስት ሚሊዮን ዶላር በላይ ወደ ሌላ የባንክ ሒሳብ ለማዛወር ሙከራ አድርገዋል ተብለው ነበር።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
አሜሪካ ለግንቦት 20 እንኳን አደረሳችሁ አለች

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ግንቦት 20ን አስመልክቶ በዛሬው ዕለት“መልካም ምኞታቸውን" ለኢትዮጵያ ገልፀዋል።
ግንቦት 20 ቀን 1983 በኢህአዴግ ጥላ ስር የታጠቁ ሃይሎች ጥምረት ከ17 አመት የትጥቅ ትግል በኋላ የደረግ አገዛዝ እንዲወድቅ የተረገበት ዕለት ነው። በዚህም በሀገራችን በተለይ በእህአዴግ የስልጣን ዘመን በድምቀት ከሚከበሩ በዓላት አንዱ ግንቦት 20 ነበር። ግንቦት 20 ዛሬ ላይ ላለንበት የብሄር ፖለቲካ የቀውስ ምንጭ ነው የሚሉም አሉ።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሆኑት ብሊንከን ግንቦት 20ን አስመልክቶ የሚከተለውን ብለዋል👇
"በኢትዮጵያውያ እና በአሜሪካ መካከል ያለውን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር እንሰራለን።
ዩናይትድ ስቴትስ ለኢትዮጵያ ሰላምን በውይይት ለማምጣት፣የጋራ ኢኮኖሚያዊ ደህንነትን ለማረጋገጥ እና እንደ የአየር ንብረት ለውጥ እና ጤና ያሉ ዓለም አቀፍ ጉዳዮችን በትብብር ለመፍታት የሚደረገውን ጥረት እንደምትደግፍ ቃል ገብተዋል።
"ኢትዮጵያ አሁን የገጠሟትን ፈተናዎች ለማሸነፍ እና ለወደፊት ብሩህ ተስፋን ሰንቃ እያደረገች ያለውን ጉዞ እና ጥረት የአሜሪካ ህዝብ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጎን ይቆማል"ሲሉ በመግለጫቸው ላይ ማንሳታቸውን አዩዘሀበሻ ተመልክቷል።

@ethio_mereja_news
መንግስታት የተቀያየሩበትና ስልጣን የያዙበት ቀን እንደ ሕዝባዊ በዓል ሊቆጠር እንደማይገባ ተገለጸ

መንግስታት ከስልጣን የወረዱበትም ይሁን ወደ ስልጣን የመጡበትን ቀን ህዝባዊ በዓል ሁኖ ሊከበር እንደማይገባ መናኸሪያ ሬዲዮ ያነጋገራቸው የታሪክ ባለሙያ ተናግረዋል፡፡

ግንቦት 20 ለአመታት በህዝባዊ በዓላት ዉስጥ ሳይካተት በህግ ሳይጸድቅ ሲከበር የቆየ ቢሆንም የህዝብ በአል ሊደረግ እንደማይችልና ኢህአዴግ የደርግ መንግስትን ገልብጦ ስልጣን የያዘበት ወይንም ማዕከላዊ መንግስትን የተቆጣጠረበት እለት ሆኖ በየአመቱ ስራ እና ትምህርት ዝግ ሆኖ ሲከበር መቆየቱ አግባብነት እንዳልነበረው የታሪክ ባለሙያው አቶ ደረጄ ተክሌ ተናግረዋል፡፡

ግንቦት 20 ለአመታት ሲከበር የቆየበት መንገድ ህጋዊ መሰረት የሌለዉ መሆኑን የሚናገሩት ባለሙያው በዓሉ በልማድ በህዝብ በዓላት ዝርዝር ዉስጥ ቢገባም በምክር ቤት ጸድቆ እንዲከበር ያልተወሰነና የጥቂት ሰዎች መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ከአንደኛው የመንግስት ስርዓት ወደ ሌላኛው ሽግግር ሲደረግ ስህተቶች ሊደገሙ እንደማይገባና ልዩነቶችን ያጠበበ ሊሆን እንደሚገባ የሚናገሩት ደግሞ ሌላኛው የታሪክ ባለሙያ አቶ በላይ ስጦታው ናቸው፡፡

የታሪክ ቅብብሎሽ በትኩረት ካልተጠና ሃገራዊ ማንነቶች እየጠፉና እየተሸረሸሩ እንደሚያልፉ የሚናገሩት ባለሙያው ከአንዱ ወደ ሌላኛው የመንግስት ስርዓት ሽግግር ሲደረግ በመሪው እና ተመሪው መካከል ያለው መተማመን እንዳይጠፋ ነው በትኩረት መሰራ ያለበት ብለዋል፡፡

መንግስታት ስልጣን የተቆጣጠሩበትን ቀን ከመዘከር ይልቅ ካለፈው ስርዓት በቅብብሎሽ ሊማሩትና ሊያስቀጥሉት የሚገባ የስራ ባህል ሊኖራቸው እንደሚገባ ባለሙያዎቹ አመላክተዋል።

መናኸሪያ ሬዲዮ
@ethio_mereja_news
ጥቆማ‼️

Hamster‼️

Guys ይህ ትልቅ ብር ማግኛ ኤርድሮፕ ነው እየተባለ ይገኛል
ምንም ብር ስለማታወጡበት ብትሞክሩት አይከፋም ባይ ነን

ያልጀመራቹ ጊዜው ሳይረፍድ  አሁንኑ በዚ ሊንክ ጀምሩት👇

ለመጀመር👇👇
https://www.tg-me.com/hamster_kombat_bot/start?startapp=kentId769729488


አጨዋወቱን ለከበዳቹ ዝርዝሩን በዚ ቻናል ያገኙታል👇👇
https://www.tg-me.com/sheger_crypto
ትናንት ምሽት በኤርትራ መንግሥት ደጋፊዎች እና ተቃዋሚዎች መካከል በእስራኤሏ ቴላቪቭ ከተማ በተፈጠረ የቡድን ጠብ አንድ ሰው እንደተገደለ የእስራኤል ዜና ምንጮች ዘግበዋል።

በብጥብጡ አምስት ሰዎች እንደቆሰሉና ከእነዚህ ውስጥ ሦስቱ ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው ዘገባዎቹ አመልክተዋል። 20 ያህል ኤርትራዊያን ደሞ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውለዋል ተብሏል።

ብጥብጡ የተፈጠረው፣ የመንግሥት ተቃዋሚዎች የመንግሥት ደጋፊዎች ስብሰባ ወደሚያደርጉበት አዳራሽ ሂደው ተቃውሞ ባሰሙበት ወቅት እንደኾነ ተገልጧል።

@ethio_mereja_news
ባለሃብቱ አብነት ገብረመስቀል ዓቃቤ ሕግ የመሠረተባቸው ክስ ተቋርጦ ከስምንት ወራት እስር በኋላ ትናንት ከቀትር በኋላ ከእስር መፈታታቸውን ዋዜማ ተረድታለች።

የጸረ-ሙስና ዓቃቤ ሕጎች በአብነትና ሌሎች አራት ግለሰቦች ላይ የመሠረቱትን የሙስና ክስ ያቋረጡት፣ አብነት ከባድ የጤና እክል ስላጋጠማቸው እንደኾነ ታውቋል።

ዓቃቤ ሕግ አብነትና ግብረ አበሮቻቸው አዲስ አበባ ወሎ ሠፈር አካባቢ የሚገኝ ቦሌ ታዎርስ በሊዝ የያዘውን 1 ሺህ 972 ስኩዌር ሜትር መሬት በተጭበረበረ መንገድ ለሌላ ግለሰብ አስተላልፈዋል፤ ሕጋዊ ያልኾነ ገንዘብን ሕጋዊ አስመስለው አቅርበዋል በማለት ነበር ክስ የመሠረተባቸው።

አብነት በመሬቱ ላይ የ40 በመቶ ድርሻ የነበራቸው ሲኾን፣ ሼክ መሃመድ አል አሙዲን ደሞ የ60 በመቶ ድርሻ ነበራቸው።

@ethio_mereja_news
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)፣ በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች በግጭት ተሳታፊ የኾኑ ኹሉም አካላት ያለምንም ቅድመ ኹኔታ ተኩስ አቁም እንዲደረጉ ዛሬ ባወጣው ሪፖርት ጠይቋል።

ኢሰመኮ፣ የግጭት ተሳታፊ አካላት በማናቸውም የግጭት ሂደት ዓለማቀፍ የሰብዓዊ መብቶችና የሰብዓዊነት ሕጎች ጥሰትን ከመፈጸም እንዲቆጠቡ፣ ተጠያቂነትን እንዲያረጋግጡ፣ በሲቪሎች ሕይወት፣ አካል እና ንብረት ላይ ጥቃት ከማድረስ እንዲቆጠቡም ጥሪ አድርጓል።

ኮሚሽኑ፣ መንግሥት በኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች በትጥቅ ግጭቶቹ ዓለማቀፍ የሰብዓዊ መብቶችና የሰብዓዊነት ሕጎችን በጣሱ አካላት ላይ የወንጀል ምርመራና የክስ ሂደት እንዲጀመር እና ከግጭቶቹ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ሥር ውለው እስካሁን ክስ ያልተመሠረተባቸው ግለሰቦችንም እንዲለቅ አሳስቧል። 

ኢሰመኮ፣ ከሕግ ውጭ ግድያ፣ የሲቪል ሰዎች ሞት፣ የአካል ጉዳት፣  የዘፈቀደ፣ የጅምላ እና የተራዘመ እሥራት፣ አስገድዶ መሰወር እንዲሁም እገታ አሳሳቢነታቸው እንደቀጠለ መኾኑን ገልጧል።

ኢሰመኮ ይህን ጥሪ ያቀረበው፣ በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ከግጭቶች ጋር በተያያዘ እንዲኹም በሌሎች ክልሎች በቅርብ ወራት ውስጥ የመንግሥት ኃይሎች፣ ታጣቂ ቡድኖችና ሌሎች ማንነታቸው ያልታወቁ ኃይሎች በሲቪሎች ላይ የፈጸሟቸውን ግድያዎችና ያደረሷቸውን አካላዊ ጉዳቶች አስመልክቶ ባወጣው ሰፊ ሪፖርት ነው።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
We call to our Investors!
Just one step: From purchasing NFTs to creating and co-founding the bank of the future: TLVD Trusty Bank!
Closed listing by founders from May 9, 2024!
Open sale of NFTs on the DeFi marketplace OpenSea begins on June 10, 2024!
UNION IS STRENGTH!
+372 5837 7377
https://tlvd.uk
https://opensea.io/collection/tlvd
https://www.tg-me.com/nftttbank
2024/11/18 15:43:44
Back to Top
HTML Embed Code: