Telegram Web Link
የፍልስጤም እግር ኳስ ማህበር በጋዛ ወረራ የተነሳ ፊፋ እስራኤልን እንዲያገል ጠየቀ

   👉 የፍልስጤም የተባበሩት መንግስታት ሙሉ አባልነት ጥያቄ ላይ አርብ እለት ድምጽ ይሰጣል


የፍልስጤም እግር ኳስ ማህበር (ፒ ኤፍ ኤ) ለዓለም እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ፊፋ ባቀረበው ጥያቄ መሰረት በእስራኤል እግር ኳስ ማህበር ውስጥ ያሉ ባለስልጣናት "በጋዛ ውስጥ ለተፈጸመው የዘር ማጥፋት ከፍተኛ ድጋፍ እንደሚሰጡ የሚያመለክቱ" የማህበራዊ ሚዲያ ጽሁፎችን አጋርቷል፡፡

"በጋዛ ውስጥ ያሉት ሁሉም የእግር ኳስ መሠረተ ልማቶች ወድመዋል ወይም በከባድ ሁኔታ ተጎድተዋል፣ በእስራኤል ወረራ ወደ ማጎሪያ ካምፕ የተቀየረውን የአል-ያርሙክን ታሪካዊ ስታዲየም ጨምሮ ከአንድ በላይ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ጉፋትን በሰነድ በማስደገፉ ማቅረቡን" የፍልስጤም እግር ኳስ ማህበር  ተናግሯል።

የእስራኤል እግር ኳስ ማህበር በሊጋው ውስጥ የሚደርሰውን አድልዎ እና ዘረኝነት ላይ እርምጃ መውሰድ አልቻለም፣ይህም የፊፋ ህግጋትን አንቀጽ 3 በቀጥታ የሚጥስ ነው ሲል አክሏል።ከኢየሩሳሌም የመጣ አንድ የእስራኤል ቡድን “እስራኤል ውስጥ እጅግ ዘረኛ ቡድን እንዴት እንደሆነ በኩራት ይዘምራል። ለተቃዋሚ ቡድኖች በሚጫወቱት አረቦች ላይ እንደ ‘አሸባሪ’ ያሉ ፅሁፎችን ያሰማሉ” ሲል የፍልስጤም እግር ኳስ ማህበር ተናግሯል።

በሌላ በኩል የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ቤጂንግ ፍልስጤም የተባበሩት መንግስታት ሙሉ አባል እንድትሆን ትደግፋለች ሲሉ ተደምጠዋል።ዋንግ ከኢንዶኔዥያ አቻቸው ጋር በጃካርታ ያደረጉትን ቆይታ ተከትሎ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ ለፍልስጤም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባልነት እንደሚደግፉ አስታውቀዋል ሲል በቻይና መንግስት የሚደገፈው ዲጂታል የዜና ማሰራጫ ዘ ፔፐር ዘግቧል።

ዋንግ በተጨማሪም እስራኤል በጋዛ ላይ ያካሄደችው ጦርነት ሰብአዊ አደጋ ፈጥሯል እና "ምንም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የተኩስ አቁም" በአስቸኳይ ተግባራዊ መሆን አለበት ማለታቸዉን የዜና ማሰራጫው ዘግቧል።የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት አርብ  እለት የፍልስጤም የተባበሩት መንግስታት ሙሉ አባልነት ጥያቄ ላይ ድምጽ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ይህ እርምጃ ዩዩናይትድ ስቴትስ የእስራኤል ጠንካራ አጋርነትን  ሊያግደው ይችላል ተብሎ ይጠበቃል ።
#ኢትዮጵያ

ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያዎች አንድ አባት  በጎረምሶች ተከበው ሲመቱ ፣ ሲሰደቡ ፣ ሲዘለፉ ፣ ሲዋከቡ በቪድዮ ታይቷል።

ይህን እጅግ አሳፋሪና በምን አይነት ሁኔታ ላይ እንዳለን ሚያሳይ ቪዲዮ ያጋሩት ደግሞ እራሳቸው የድርጊቱ ፈጻሚዎች ናቸው።

ድርጊቱ ብዙዎችን ክፉኛ አስቆጥቷል። በርካቶች ስለ ነገ በማሳብ ፍርሃት ውስጥ ከቷቸዋል።

በእርግጥ በሀገራችን ያላየነው ግፍ ፣ ያልሰማነው ክፉ ተግባርና ጭካኔ ምን አለ ? እንዘርዝር ብንልስ ቦታው፣ ጊዜው  ይበቃናል ? በፍጹም !

ከዚህ በፊትም እንደምንለው በቪዲዮዎች ተቀርጾ የምናየው ምናልባትእድለኞች ሆነን ከብዙ አንዱ እንጂ ስንት ያላየነው ይኖራል።

ወደ ቪድዮው ስንመለስ ተከበው ሲመቱ፣ ሲዋከቡ ፣ ሲዘለፉ የነበሩት አባት ' እንጀራ ፍለጋ እግር ጥሏቸው እንደመጡ ' ይገልጻሉ የሚጠይቀን የለም ባዮች ጎረምሶች ' እዚህ አካባቢ ምን ትሰራለህ ? ለምን እዚህ መጣህ ? ከመጣህበት ቦታስ እንጀራ የለም ? ' ሲሉ እጅግ በንቀት ያዋክቧቸዋል።

ይህን ተግባራቸውን እንደ በጎ ስራ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ አጋርተውታል።

የትኛውም ዜጋ በገዛ ሀገሩ የመንቀሳቀስ መብት አለው ? ካልሆነ ስለምን #ኢትዮጵያዊ ይባላል ? ጥፋት ካለበት ፣ ከተጠረጠረ የሚጠይቀው ህግ እንጂ የሰፈር ጎረምሳ አይደለም። ግለሰቦቹ ጥርጣሬ አለን ካሉ ህግን ማሳወቅ እንጂ ማነው ፤ የትኛው ህግ ነው ይህንን መብት የሰጣቸው ? 

ይህ ተግባር በተለይ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ እየተነዛ ያለው የጥላቻ ስብከት ምን ያህል ስር እንደሰደደ እንደሆነ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ሲሆን ነገን እጅግ አስፈሪ ያደርገዋል።

ግልጽ የሆነ የብሄርና የግለሰቦች ጥላቻ ፣ ልብም አእምሮም በጥላቻ መሞላት፣ አይንም በጥላቻ መታወር ፦
- ሌላው ይቅር ታላላቆቻችን እንዳናከብር
- ለእምነታችን ፣ ለሃይማኖታችን ቦታ እንዳይኖረን
- ለሰው ልጅ ትንሽ እንኳን ቦታ እንዳንሰጥ
- ለህግ እና ስርዓት ቅንጣት ታክል ደንታ እንዳይኖረን
- ባህል፣ ወግ ፣ አብሮነት ለሚባለው ጉዳይ ቦታ እንደሌለን
- ነገ እኔስ ምን ይገጥመኛል ? ምን እሆን ይሆን ? በህይወት አጋጣሚ የት እሄዳለሁ ፣ ምን አካባቢ እገኛለሁ የሚለውን ለማገናዘብ እንኳን እንዳንችል ያደርገናል።

ሰዎች ወደው ሳይሆን በስርዓት፣ በግለሰቦች፣ በአንቂዎች ፣ በሚዲያዎች... አማካኝነት ነው ጥላቻ እንዲውጣቸው እና ማገናዘብ ፣ ቆም ብሎ ማሰብ የሚባለውን መሰረታዊ ነገር እንዲያጡት የሚሆነው።

ሰዎች ከመሰል ድርጊታቸው እንዲታቀቡ አብሮነት ፣ ፍቅር ፣ መግባባት፣ መከባበር ፣ ህግ ፣ ስርዓት፣ ወንድማማችንነትን ከማስተማር ባለፈ በህግ ማረም ፣ ነገ መዘዙ የከፋ እየሆነ ስለሚሄድ ከወዲሁ እንዲገታ በአንድ ላይ ማውገዝ ፣ ተበዳይን መካስ ፣ እውነት ህግ የበላይ ነው የምንል ከሆነም ለራሳችን ስንል ህግን ሁሌም ማስከበር ነው።

ዛሬ ላይ እንዲህ ያሉና ከዚህ ቀደምም በየሀገሪቱ ክፍሎች የሰማናቸው ፍጹም አደገኛ የሚባሉ ጉዳዮች የሳምንት አጀንዳ እየሆኑ እያለፉ ይመስለን ይሆናል ግን በእርግጠኝነት መዘዛቸው የከፋ ሊሆን ይችላል።

ውጤታቸው ዛሬ ሳይሆን ውሎ አድሮ ምናልባትም አመታትን አልፎ ይታይ ይሆናል ስለሆነም እናስብበት ! ትውልዱን ከስህተቱ እናርመው ፤ ወገኑን እንዲጠላ ሳይሆን እንዲወድ ፣ እንዲያከብር እናስተምረው።

በሁሉም ዘንድ አውቀናል ታውቀናል ፣ ዛሬ ስልጣን አለን፣ ሚዲያውም የኛው ነው የምንል ሰዎችም ' አይ የኔ ወገን ስለሆነ ፍጹም ጻዲቅ ነው ፣ አይሳሳትም ፣ ጀግና ነው ፣ ቢሳሳትም ምንም ችግር የለውም እኔ እከላከልለታለሁ ' ከሚል አደገኛ እና ብዙ መዘዘ ካለው አመለካከት መራቅ ይገባናል።

#Tikvah

@ethio_mereja_news
በጃኔቫ ፤ በመንግስት ላይ የተቃዉሞ ድምጽ ያሰሙ ሰዎችን የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ ጽሕፈት ቤት አወገዘ

በጃኔቫ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ ጽሕፈት ቤት፣ ማክሰኞ'ለት ለኢትዮጵያዊያን ተረጂዎች ገንዘብ ለማሰባሰብ ጄኔቫ ውስጥ በተካሄደው ዓለማቀፍ መርሃ ግብር ላይ የተወሰኑ ኢትዮጵያዊያን ተቃውሞና ጩኸት ማሰማታቸውን አውግዟል።

አራቱ ትዉልደ ኢትዮጵያዊያን ሰዎች በጉባኤው ተገኝተዉ በኢትዮጵያ እየደረሱ ናቸዉ ያሏቸዉን ጉዳዮች በመጥቀስ በጭኸት ስብሰባውን አዉከዉ እንደነበር ሸገር መዘገቡ አይዘነጋም።

ፖሊስ ጩኸት ያሰሙትን ኢትዮጵያዊያን ይዞ ከአካባቢው እንዳራቃቸው ጽሕፈት ቤቱ ገልጧል። ጽሕፈት ቤቱ፣ ለድርቅ ተጎጂዎች ዓለማቀፉ ኅብረተሰብ እርዳታ በሚያሰባስብበት መድረክ ላይ ጩኸት ማሰማት፣ የአገር ጠላትነት ፖለቲካ እንጂ የተቃውሞ ፖለቲካ አይደለም በማለት ተችቷል።

የኢትዮጵያዊያን ዲያስፖራ ማኅበረሰብ፣ ባልተገባ ቦታ ጩኸት በማሰማት "አገር አዋራጅ" የኾነ ድርጊት የሚፈጽሙ ግለሰቦችን ሊቃወማቸው እንደሚገባም ጽሕፈት ቤቱ አሳስቧል።

ቋሚ መልዕክተኛ ጽሕፈት ቤቱ፣ በአገር ክብር ላይ እጃቸውን የሚዘረጉ ግለሰቦችን በሕግ አግባባብ የምጠይቅበትን አሠራር እከተላለሁ በማለትም አስጠንቅቋል።

Via ዋዜማ
@ethio_mereja_news
ብልፅግና ፓርቲ ‘የሚዲያ ሠራዊት’ አቋቁሞ በሚቃወሙት እና በሚተቹት ላይ ስም ማጥፋት ዘመቻ እንደሚያካሂድ ተገለጸ‼️

በገዢው ብልፅግና ፓርቲ ‘የሚዲያ ሠራዊት’ የሚል መጠሪያ ያላቸው የፓርቲው አባላት፤ መንግሥትን በሚተቹ እና በሚቃወሙ ግለሰቦች ላይ በፌስቡክ በተደረጉ የሐሰተኛ መረጃ እንዲሁም ‘የጥላቻ ንግግር’ ተብለው ሊቆጠሩ የሚችሉ ጽሑፎች እና ምስሎች ሥርጭት ላይ እንደተሳተፉ ቢቢሲ ባደረገው ምርመራ ማረጋገጡን አስታወቀ።

#የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ አቡነ ጴጥሮስ ከአዲስ አበባ ወደ አሜሪካ መጓዛቸውን ተከትሎ በወቅቱ የተሰራጩ መረጃዎችን ቢቢሲ በማሳያነት አቅርቧል።

በቤተክርስቲያኗ እና በገዢው ፓርቲ መካከል የተፈጠረውን ቅራኔ ተከትሎ “ሰበር መረጃ፤ አቡነ ጴጥሮስ ከሀገር ኮበለሉ”፣ “አሜሪካዊው አቡነ ጴጥሮስ ከሀገር ኮብልለዋል!” እና “ከአሜሪካዊ አቡነ ጴጥሮስ ኩብለላ ጀርባ ያሉ እውነታዎች!” የሚል መግቢያ ያላቸው መረጃዎች በወቅቱ ተሰራጭተው እንደነበር አውስቷል።

“ለምንድነው ላይክ፣ ሼር የማታደርጉት?” የሚል ጥያቄ ለተሳታፊዎቹ እንደሚያቀርብ፤ የሚዲያ ሠራዊት አባላት ላክይ፣ ኮሜንት እና ሼር ማድረጋቸውን የሚያሳይ “ስክሪን ሻት” እንዲልኩ እንደሚጠየቁ ቢቢሲ በግሩፑ የተደረጉ የመልዕክት ልውውጦችን ዋቢ በማድረግ አስታውቋል።

መንግስትን የሚቃወሙ ጽሁፎችን ባጋሩ የፌስቡክ ገጾች ላይ ‘የሚዲያ ሠራዊቱ’ አባላት ተዘጋጅቶ የተሰጣቸውን ጽሁፎች ኮሜንት እንደሚያደርጉ አረጋግጫለሁ ብሏል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
🛒ታላቅ ቅናሺ ከሸገር ገበያ📣

✔️m13 Samsung 📱
✔️4ram
✔️64Gb

        ዋጋ 13200

እዚህ ላይ ያናግሩን 👇👇
                  @ethio_sellerr

አዲስአበባ ያሉበት እናደርሳለን 🛵🚵
ክፍለሀገር በፖስታ ይደርሷታል።📩📮
የቻይና ከተሞች እየሰመጡ ነው❗️

ከቻይና ዋና ዋና ከተሞች ግማሽ ያህሉ ላይ የመስመጥ አደጋ መጋረጡ ተሰምቷል።  በበሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በተለይ የባህር ከፍታ ሲጨምር ለጎርፍ አደጋ እየተጋለጡ ነው ሲል በአገር አቀፍ ደረጃ የወጣው የሳተላይት መረጃ  አመልክቷል። በሳይንስ ጆርናል የታተመው ይኸው ጥናት 45 በመቶው የቻይና የከተማ መሬት በአመት ከ3 ሚሊ ሜትር በላይ በፍጥነት እየሰመጠ ነው ያለ ሲሆን 16 በመቶው ደግሞ በዓመት ከ10 ሚሊ ሜትር በላይ መስመጡን ገልጿል።  በከተሞቹ የሚገኙ በርካታ ሰማይ ጠቀስ ህንፃዎች  ምክንያት መሆናቸውን ሮይተርስ በዘገባው አመልክቷል።

@ethio_mereja_news
ተቀጥተዋል😁

በቤጂንግ ግማሽ ማራቶን ከስፖርት ጨዋነት ባፈነገጠ መልኩ ቻይናዊውን አትሌት ሆን ብለው እንዲያሸንፍ አድርገዋል የተባሉ የኬንያ እና የኢትዮጵያ አትሌቶች ያገኙት ሜዳሊያና የገንዘብ ሽልማት ተነጥቀዋል።

ባልተገባ መንገድ ውድድሩን እንዲያሸንፍ የተደረገው ቻይናዊ አትሌትም ሽልማቱን ተነጥቋል።

ኬንያውያኑ አትሌቶች ዊሊ ምናንጋት እና ሮበርት ኬተር እንዲሁም ኢትዮጵያዊው ደጀኔ ሃይሉ ቢቂላ ማሸነፊያው መስመር ላይ ሆን ብለው ቻይናዊው እንዲያሸንፍ ፍጥነታቸውን ሲገቱ እንደነበር መታየታቸው ተገልጿል፡፡

ባለፈው እሁድ በተካሄደው የግማሽ ማራቶን ሩጫ ውድድር ላይ የተፈፀመውን ያልተገባ ድርጊት የተመለከተው የውድድሩ አዘጋጅ ኮሚቴ ጉዳዩን እየመረመረ መቆየቱን ገልጿል፡፡

ኬንያዊው ምናንጋት መጀመሪያ ላይ የእስያ ጨዋታዎች ሻምፒዮናን እንዲያሸንፍ ያደረገው ጓደኛው በመሆኑ ነው ቢልም፤ ነገር ግን በኋላ ላይ ለማሯሯጥ እንደተቀጠረ ተናግሯል።

ይህንንም ተከትሎ የቤጂንግ ግማሽ ማራቶን ውድድር አዘጋጁ የአሸናፊውን ሂ ጄ እና የሦስቱን አትሌቶች ሜዳሊያና የገንዘብ ሽልማት መንጠቁን ሳውዝ ቻይና ሞርኒንግ ፖስት ዘግቧል፡፡

Via:- FBC

@ethio_mereja_news
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Who's here? 
We've asked for a free link to a paid channel, for our subs.
x2-x3 Signals here

👉 CLICK HERE TO JOIN 👈
👉 CLICK HERE TO JOIN 👈
👉 CLICK HERE TO JOIN 👈

❗️JOIN FAST! FIRST 1000 SUBS WILL BE ACCEPTED
#Update

የ " ቲክቶክ " እገዳ በኪርጊስታን ተግባራዊ ሆነ።

ኪርጊስታን " ቲክቶክ " በመላ ሀገሪቱ  እንዲታገድ ውሳኔ ማስለፏ ይታወሳል በዚሁ ውሳኔ መሰረት የቴሌኮም አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች ትዕዛዙን ወደ መፈጸም #እርምጃ ገብተዋል።

በሀገሪቱ " ቲክቶክ " መስራት እንዳቆመም ተነግሯል።

ሰዎች መተግበሪያውን ሲከፍቱን የሚያገኙት መልዕክት " Unable to load, please try again." የሚል ነው።

ውሳኔው በሀገሪቱ ብሔራዊ ደህንነት መ/ቤት የተላለፈ ነው።

የኪርጊስታን ዲጂታል ሚኒስቴር ቲክቶክን የሚያስተዳድረው ' ባይት ዳንስ ' ኩባንያ ፥ " #የልጆችን
- አእምሯዊ፣
- አካላዊ፣
- መንፈሳዊ እና #ሥነምግባራዊ እድገትን ለመጠበቅ በህግ የተዘረዘሩ ህጋዊ መስፈርቶችን ማክበር አልቻለም " ብሏል።

በዚህም ምክንያት " ቲክቶክ " በሀገሪቱ እንዳይሰራ ተደርጓል።

ውሳኔው የተቃወሙ አካላት ይህ ተገቢ እንዳልሆነ በመግለጽ ገደቡ እንዲነሳ ጠይቀዋል። ከገደብ ይልቅ ቁጥጥር ይደረግበት ብለዋል።

ከዚህ ቀደም የኪርጊስታን የባህል፣ ወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ፥ " ቲክቶክ " የተሰኘው መተግበሪያ ለልጆች አእምሯዊ እድገት እና አጠቃላይ ደህንነት ጠንቅ እየሆነ ነው " ማለቱ ይታወሳል።

መተግበሪያው #ህጻናት እጅግ ጎጂ ሊሆኑ የሚችሉ ይዘቶችን እንዳያገኙ ለመከላከል በቂ #መቆጣጠሪያ እንደሌለው ነበር የገለጸው።

በተጨማሪም ለተጠቃሚዎቹ ትክክለኛ የዕድሜ ማረጋገጫ እርምጃዎች እንደለለው እና ተጠቃሚዎችን በአጫጭር የቪዲዮ ክሊፖች ወደ ምናባዊ ግዛት በመሳብ #ሱስ የሚያስይዝ ይዘት እንዳለው አስረድቶ ነበር።

ሚኒስቴሩ " ቲክቶክ " በወጣቱ ትውልድ ደህንነት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንዳለው በአጠቃላይም ለትውልዱ ጠንቅ እየሆነ እንደመጣ አሳውቆ ነበር።

በሌላ በኩል ፤ አሜሪካ ውስጥ ከመረጃ ደህንነት ጋር በተያያዘ መተግበሪያው እንዲታገድ ከፍተኛ ግፊት እየተደረገ ሲሆን  " ቲክቶክ " ከቻይናው ኩባንያ ካልተፋታ / አሜሪካ የምትቆጣጠረው አይነት ካልሆነ በመላ ሀገሪቱ መታገድ ዕጣ ፋንታ ሊገጥመው ይችላል ተብሏል።

via tikvahethiopia

@merkato_media
This is 100% REAL!  

Ethiopians this service is for you 🔥

We offer you a unique opportunity to open VIP Offshore bank accounts in US Dollars and Euros in Panama.

Enjoy the security of one of the best banking jurisdictions worldwide and get approved by one of the TOP 3 best banks in Panama City!

🍀 Receive your Visa/Mastercard in 2 weeks via FedEx or DHL in Ethiopia or anywhere in Africa.

Book your free call with our experts Today! 📞

Join our Official Channel NOW! ⤵️⤵️⤵️

👉 https://www.tg-me.com/myafricanwealthofficial
👉 https://www.tg-me.com/myafricanwealthofficial
እስራኤል በኢራን ላይ የአጸፋ ጥቃት ሰነዘረች

እስራኤል ከኢራን ለተቃጣባት የሚሳኤልና ድሮን ጥቃቶች የአጸፋ እርምጃ መውሰዷ ተገለጸ።

እስራኤል ኢስፋሃን በተባለ የማዕከላዊ አራን አካባቢ ባሉ ወታደራዊ ካምፖች ላይ በድሮኖች ጥቃት መሰንዘሯ ነው የተጠቀሰው።

ይህን ተከትሎ ኢራን የጸረ-ሚሳኤል መከላከያ ማስወንጨፏንና የተተኮሱባትን ሦስት ድሮኖች መታ መጣሏን አስታውቃለች።

ኢስፋሃን የኢራን አየር ኃይል እና የኒዩክሌር ጣቢያ የሚገኝ ከተማዋ ሲሆን በአካባቢው የተሰማው ፍንዳታ ኢራን ያስወነጨፈቻቸው የጸረ ሚሳኤል መከላከያ መሆኑን አገሪቱ ባወጣችው መረጃ ገልጻለች።

የእስራኤልን ጥቃት ተከትሎ የአየር በረራዎች ተስተጓጉለው እንደነበርና በአሁኑ ሰዓት በረራ መጀመሩን እንዲሁም አካባቢው ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ መመለሱን የአልጃዚራ ዘገባ አመላክቷል።

በፈረንጆቹ ሚያዝያ 1 ቀን እስራኤል ሶሪያ በሚገኘው የኢራን ቆንስላ ጽሕፈት ቤት ላይ ባደረሰችው ጥቃት 13 ዜጎቿ መገደላቸውን ተከትሎ በእስራኤል ላይ ባሳለፍነው ቅዳሜ 300 ሚሳኤልና የድሮን ጥቃት ማድረሷ ይታወሳል። ለኢራን ጥቃት እስራኤል አጸፋዊ እርምጃ እንደምትወስድ ዝታ እንደነበርም የሚታወስ ነው።የሁለቱ አገራት የሰሞኑ ግጭትን ተከትሎ አገራት ዜጎቻቸውን ወደ እስራኤል እንዳይጓዙ እያስጠነቀቁ ነው።

ከስውር ጦርነት አልፎ ወደ ይፋዊና ቀጥተኛ ግጭት ውስጥ የገባው የሁለቱ አገራት የሰሞነኛ ፍጥጫ በቋፍ ላይ የነበረ የአካባቢውን ሰላምና ጸጥታ ወደለየለት ጦርነት እንዳይከተው ተሰግቷል።

 
የቡድን-7 አገራት ውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች፣ በኢትዮጵያ የሰፈነው ውጥረትና ኢትዮጵያ ከሱማሌላንድ ጋር የተፈራረመችው የባሕር በር መግቢያ ስምምነት እንደሚያሳስባቸው ትናንት ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

አገራቱ፣ ኢትዮጵያ እና ሱማሊያ "ኹሉንም የንግግር መስመሮች" ክፍት በማድረግ ውጥረቶችን እንዲያደርግቡ ጠይቀዋል። በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች፣ የኢኮኖሚ ቀውስና የምግብ ዋስትና ማሽቆልቆል አሳሳቢ እንደኾኑም አገራቱ ገልጸዋል።

የቡድኑ አባል አገራት፣ የመንግሥት የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ ዘላቂ እንዲኾን፣ ሲቪሎችን ከጥቃት እንዲጠበቁ፣ ውጥረቶች በፖለቲካዊ ንግግር እንዲፈቱ፣ እርቅ፣ የሽግግር ፍትህና ተጠያቂነት እንዲሰፍን ጥሪ አድርገዋል።

በተያያዘ ዜና

የቡድን-7 አገራት፣ ሱማሊያና ኢትዮጵያ በባሕር በር መግቢያ ዙሪያ የገቡበትን ውጥረት ለመፍታት "ኹሉንም የንግግር መስመሮች ክፍት እንዲያደርጉ" ላቀረቡት ጥሪ፣ የሱማሊያ መንግሥት ትናንት እኩለ ሌሊት ላይ ባወጣው መግለጫ አሉታዊ ምላሽ ሰጥቷል።

የሶማሊያ መንግሥት፣ ኢትዮጵያ ከሰሜናዊቷ ግዛቴ ሶማሊላንድ ጋር የደረሰችበትን የባሕር በር መግቢያ የመግባቢያ ስምምነት እስካልሰረዘችና የሱማሊያን አንድነት፣ ሉዓላዊነትና በውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ያለመግባት መርህ ሙሉ በሙሉ እስካላረጋገጠች ድረስ፣ ንግግር ማድረግ የሚሳካ ነገር አይደለም ብሏል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ኢዜማ፣ የመንግሥት አመራሮች፣ ካድሬዎችና የሜዲያ ተቀጣሪዎች "ሐሰተኛ መረጃ" እና "የጥላቻ ንግግር ሊባሉ የሚችሉ" ንግግሮችን በፌስቡክ ላይ በማሠራጨትና ስም በማጥፋት ዘመቻ ስለመጠመዳቸው ቢቢሲ ባደረገው ምርመራ መረጋገጡ፣ "ፍጹም ተቀባይነት የሌለው" እና ሥልጣን ከያዘ መንግሥት የማይጠበቅ ድርጊት መኾኑን ትናንት ምሽት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ኢዜማ፣ ይህ "አምባገነናዊነት" እና ራስን "በአሸዋ መሠረት" ላይ የማቆም አካሄድ የዲሞክራሲ እንቅፋት በመኾኑ በጥብቅ አወግዘዋለሁ ብሏል። ፓርቲው፣ መንግሥት ከመሰል ድርጊቱ እንዲቆጠብና ለእስካኹኑ ድርጊቱ ሕዝቡን ይቅርታ እንዲጠይቅ አሳስቧል።

ፓርቲው፣ የመንግሥት መገናኛ ብዙኀን መንግሥትንና ፓርቲን በማይለዩ ሃላፊዎች በመያዛቸው ሕዝቡ በመንግሥት ላይ እምነት እንዲያጣና ማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን የመጀመሪያ የመረጃ ምንጭ አድርጎ እንዲቆጥር ተደርጓል ብሏል።

@sheger_press
@sheger_press
እናንተ ደጋግ ኢትዮጵያውያን እባካችሁ‼️

ድምፅ ሁኗት 🙏😭

ቪድዮውን ማየት ያልቻላቹ የመልክተኛው የቲክቶክ ገፅ ላይ አለላቹ

ሼር አድርጉት እባካችሁ 🥹

እናት እና አባቷ ለስራ በሌሊት ሲወጡ ጠብቀው 3 ጎረምሶች በራቸውን በርግደው ገቡ። እቺ የ 17 ዓመት ልጅና ታናሿ የ4 ዓመት ልጆች ቤት ውስጥ ብቻቸውን ነበሩ።

ጎረምሶቹም እቺን ልጅ ሊደፍሯት አባቷ ተኝቶበት የነበረው ፍራሽ ላይ ገፍትረው ጣሏት። አፏን በጨርቅ አፍነው ይታገሏት ጀመር። በዚህ ውስጥ ሆና እንኳን የታናሽ እህቷ ጉዳይ አስጨንቅዋት ወደ እህቷ ሊሄድ የሚታገለውን ጎረምሳ በእጅም በምልክትም መማፀን ጀመረች።

ጎረምሳዎቹም ስታስቸግራቸው ራስን የሚያስት መዳኒት አፍንጫዋ ላይ ነፉባት። ራሷንም ሳተች። ሶስቱም ጎረምሶች እስኪበቃቸው ከደፈርሯት በኃላ ጥለዋት ወጡ።

ስትነቃ ራሷን ያገኘችው ሆስፒታል ተኝታ ነው! ጉዳዩ ለሕግ አካላት ተነገረ። ሕጉም ምንም ማስረጃ የለም አርፈሽ ኑሪ ብለው ሸኟት። በስንት መከራ ከህመሟ እና ከስብሯቷ አገግማ entrance ስላልመጣላት የሜካፕ ኮርስ መውሰድ ትጀምራለች።

ይሄንን ያዩ ደፋሪዎች እንዴት እኛ ደፍረንሽ ከቤት ወጣሽ አርፈሽ ቤት ተቀመጪ የሚል ማስፈራሪያ ይደርሳት ጀመር።

ጭራሽ 2መቶ ብር እና እንገልሻለን የሚል ደብዳቤ ይላክላት ጀመር። ሁኔታው ያስፈራቸው ቤተሰቦች አሁንም ደብዳቤውን ይዘው ወደህግ ይሄዳሉ። የሕግ አካላትም አታካብዱ ይሄ እኮ ቀላል ነው be2መቶ ብሩ ቡና አፍሉበት በሚል ስላቅ ይመልሷቸዋል።

ካስፈራሯት ከቀናት በኃላ የሆነች ሴትዮ መጥታ ሰው የምትጠይቃት አስመስላ አዘናግታ ከደፋሪዎቹ ጋር አፍነው ወሰዷት። ስትነቃ መኪና ውስጥ እራሷን አገኘችው። ደፋርዎቹም መንቃቷን ሲያዩ ድጋሜ መድሃኒቱን ነፍተውባት ራሷን ከሳተች በኃላ እንደፈለጉ ተጫውተውባት እንዳስፈለጋቸው አድርገው ጫካ ውስጥ ጥለዋት ሄዱ!

ቤተሰቦቿም እሷን በማሳከም ያላቸውን ጨርሰው ሸራ ወጥረው መኖር ከጀመሩ ሰነባብተዋል። ደፋርዎቹም ማንም ስለማይጠይቃቸው የፈለጉት ቤት እየገቡ የፈለጉዋትን ሴት መድፈራቸውን ቀጥለዋል ። የሕግ አካላቱም በተጎጂዎች ቁስል እየተሳለቁ የወንጀሉ ተባባሪ ሆነዋል ።

ነግ በኔ ነው! ለዚች ሴት ፍትህ እንጠይቅ እንደሷ ድምፃቸው ላልተሰማ ተሰብረው ቤት ለቀሩት ሴቶች ፍትህ እንጠይቅ ሕግ የለም አትበሉ ሚዲያ የያዘው ጉዳይ ሕግ አለው ለማለት ይሰራል ጫና እናድርግ ፍትህ እንበል ፍትህ እንሻለን

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Forwarded from Bura - collection
m14 Samsung 📱
✔️6ram
✔️128 GB

📌ዋጋ=16500

@ethio_sellerr   
@Birukepromo
           ላይ  ያናግሩን።
በስልክ ቁጥራችን 0946159797 ይደዉሉልን ።

አዲስአበባ ያሉበት እናደርሳለን 🛵🚵
ክፍለሀገር በፖስታ ይደርሷታል።📩📮

ተጨማሪ እቃዎችን ለመሸመት የቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ👇👇
https://www.tg-me.com/bura_collection
በአዲስ አበባ ከተማ በተገነቡ ማዕከላት ከመደበኛው ገበያ የጤፍ ዋጋ ላይ የ3 ሺ ብር ቅናሽ እንዳለው ተገለፀ

በአዲስ አበባ ከተማ ተገንብተው አምራችን ከሸማቾች የሚያገናኙ ሶስት ማዕከላት ሙሉ በሙሉ ስራ መጀመራቸውን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታውቋል።

ቢሮው አሁን ላይ በዋነኛነት የገበያ ማዕከላት ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ እንደሚገኝ ለብስራት ሬድዮና ቴሌቭዥን የተናገሩት የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ ከ3.3 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ተደርጎባቸው እንደተገነቡ ተናግረዋል።

ከተማ አስተዳደሩ በእነዚህ ማዕከላት አምራቾችን ሙሉ በሙሉ አስገብቶ ለሸማቾች ከማሳ የተሰበሰቡ ምርቶችን በቅናሽ ዋጋ እያቀረበ ነው ብለዋል።እነዚህ ማዕከላት በሸማቹ እና በአምራቹ መሀል የነበረውን ህገ ወጥ ደላላን መስበር የቻለ ነው።

ከዋጋም አኳያ ከእሁድ ገበያ አንፃር የተሻሉ መሆናቸውን ገልፀዋል።ምርቶች በበቂ ሁኔታ በገበያ ማዕከላት ቢገቡም ህብረተሰቡ ስለ ማዕከላቱ በቂ ግንዛቤ ስሌለው የሚበላሹ  ምርቶች አሉ በተለይ ደግሞ  የአትክልት እና ፍራፍሬ ምርቶች ብልሽት እንደሚገጥማቸው ተናግረዋል።

ሸማቹ ወደ እነዚህ ማዕከላት በመምጣት ሁሉንም ምርቶች በአንድ እንዲሁም በቅናሽ ዋጋ ማግኘት እንደሚችል ገልፀዋል።ከመደበኛ ገበያዎች የጤፍ ዋጋ በእነዚህ ማዕከላት ውስጥ የ3ሺ ብር ቅናሽ እንዳለው አንስተዋል። እንዲሁም አትክልት እና ፍራፍሬ ምርቶችም ከእሁድ ገበያው ቅናሽ እንዳለውም አቶ ሰውነት አየለ ጨምረው ለብስራት ሬድዮና ቴሌቭዥን ተናግረዋል።

ማዕከላቱ በኮልፌ ፣በአቃቂ እና በለሚ ኩራ ክፍለ ከተሞች ይገኛሉ ተብሏል።

ዳጉ_ጆርናል
ሶሻል ሚዲያ ይሺጡ ይግዙ

✔️የቴሌግራም ግሩፕ እና ቻናል
✔️የዩትዩብ ቻናል
✔️የፌስቡክ ፔጅ
✔️የቲክቶክ ገፅ

መግዛት እና መሸጥ የምትፈልጉ አናግሩን ሁሉም እኛ ጋር አለ።
    @ethio_sellerr
@birukpromo ላይ አናግሩን

በስልክ ቁጥራችን 0946159797 ይደዉሉንን::
ኢራን አፋጣኝ የበቀል እርምጃ ለመውሰድ እቅድ የላትም ሲሉ አንድ የኢራን ባለስልጣን ተናገሩ

አንድ የኢራን ከፍተኛ ባለስልጣን ለሮይተርስ የዜና ወኪል እንደተናገሩት "ኢራን በእስራኤል ላይ አፋጣኝ የበቀል እርምጃ ለመውሰድ እቅድ የላትም" ሲሉ እስራኤል በኢራን ኢስፋሃን ከተማ ላይ ጥቃት መሰንዘሯ ተከትሎ ተናግረዋል፡፡

ሁለት የአሜሪካ ባለስልጣናት ጥቃቱ ከእስራኤል የመጣ መሆኑን ለመገናኛ ብዙሃን ቢናገሩም እስራኤል ኃላፊነቱን ለመዉሰድ ወዲያዉ መግለጫ አላወጣችም ነበር።አንድ ኢራናዊ ተንታኝ ለኢራን መንግስት ቲቪ እንደተናገሩት "በኢስፋሃን በአየር መከላከያ የተተኮሱ ሚኒ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ወደ ኢራን ውስጥ ሰርጎ ገቦች ገብተዋል" በማለት እስራኤል ጥቃቱን ፈጽማለች የሚለውን ዘገባ አሳንሰዉ ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል እስራኤል በኢራን ላይ የበቀል ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ ዩናይትድ ስቴትስ በእስራኤል ለሚገኙ የኤምባሲ ሰራተኞቿ እና ቤተሰቦቻቸው “ከከፍተኛ ጥንቃቄ የተነሳ” የጉዞ ገድብ ጥላለች።ኤምባሲው ሰራተኞቹ ከታላቋ ቴል አቪቭ ክልል ውጭ  ወደ ሄርዝሊያ ፣ ኔታንያ እና ዩሁዳን ጨምሮ ወደ እየሩሳሌም እና ቢየር ሼቫ አካባቢዎች እንዳይጓዙ አስጠንቅቋል፡፡
ራያ‼️

ከአላማጣ እና አካባቢው 29 ሺህ ህዝብ መፈናቀሉ ተገለጸ

ተፈናቃዮቹ በቆቦ፣ወልዲያ እና ሰቆጣ ከተሞች መጠለላቸው ተገልጿል
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ባወጣው ሪፖርት 29 ሺህ ዜጎች ከራያ እና አላማጣ አካባቢዎች መፈናቀላቸውን አስታውቋል፡፡

እንደ ድርጅቱ ሪፖርት ከሆነ ከሰሞኑ በትግራይ እና አማራ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች ላይ ባገረሸው ግጭት ምክንያት ዜጎች ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለዋል ብሏል፡፡
ተፈናቃዮቹ በቆቦ፣ወልዲያ እና ሰቆጣ ከተማ በሚገኙ መጠለያዎች ላይ እንደተጠለሉም ድርጅቱ አስታውቋል፡፡

በአካባቢው ባለው አለመረጋጋት ምክንያት ተጨማሪ ዜጎች ሊፈናቀሉ እንደሚችሉ የገለጸው ድርጅቱ ለተፈናቃዮች ውሃ፣ ምግብ እና ሌሎች ህይወት ማቆያ ድጋፍ በማድረግ ላይ መሆኑንም ገልጿል፡፡

አሁን ላይ ከለጋሽ ተቋማት እና ሀገራት የሚገኘው ድጋፍ እየተሟጠጠ በመሆኑ በአካባቢው ያለው ማህበረሰብ የሚችለውን ድጋፍ እያደረገ እንደሆነም ተገልጿል፡፡

ለተፈናቃዮቹ መጠለያ፣ የሕክምና አገልግሎት እና ሌሎች መሰረታዊ ድጋፎችን ማድረግ ይገባል ያለው ድርጅቱ የኢትዮጵያ አደጋ መከላከል እና ዝግጁነት ኮሚሽን ሰራተኞች ወደ ስፍራው ተሰማርተዋልም ተብሏል፡፡

ተፈናቃዮቹ ከአንድ ሳምንት በፊት በሚኖሩባቸው አካባቢዎች የህወሃት ታጣቂዎች ወደ ራያ እና አላማጣ አካባቢዎች መምጣታቸውን ተከትሎ ቤታቸውን ጥለው ለመሰደድ እንደተገደዱ ተገልጿል፡፡
ከተፈናቀሉት 29 ሺህ ዜጎች ውስጥ 70 በመቶዎቹ ህጻናት እና ሴቶች ሲሆኑ ቀሪዎቹ አዛውንቶች እና ታዳጊዎች ናቸው ተብሏል፡፡

በአላማጣ ከተማ የፌደራል የጸጥታ ሀይሎች መግባታቸውን ተከትሎ ተቋርጦ የነበረው ከቆቦ-አላማጣ ትራንስፖርት ዳግም መከፈቱ ተገልጿል፡፡

@sheger_press
@sheger_press
2024/11/06 02:00:02
Back to Top
HTML Embed Code: