Telegram Web Link
በአማራ ክልል ከ 4መቶ ሺህ በላይ የወባ ህሙማን ሪፖርት መደረጉ ተነገረ

በአማራ ክልል የተለያዩ ቦታዎች በተከሰተዉ የወባ በሽታ በሀምሌ እና ነሀሴ ወራት ከ 4መቶ ሺህ በላይ የወባ ህሙማን ሪፖርት መደረጋቸዉ ተነግሯል ፡፡

የአማራ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የወባ መከላከል እና መቆጣጠር ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ዳምጤ ላንከር ለጣቢያችን እንደተናገሩት ፤ አዊ ዞን፡ደቡብ ጎንደር ዞን እና ማእከላዊ ጎንደር ዞኖች  በክልሉ በቀዳሚነት   የበሽታዉ ስርጭት ተጠቂዎች ሆነዋል ሲሉ ጠቅሰዋል  ፡፡

የበሽታዉን ስርጭት ለመቆጣጠር ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመሆን የሳምንታዊ ክትትል ስራ እና በ22 ወረዳዎች እንዲሁም በ 233 ቀበሌዎች የኬሚካሌ እርጭት መደረጉን የፕሮግራሙ አስተባባሪ አንስተዋል ፡፡

በተጨማሪም ከ1ሚሊዮን 1መቶ ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍል በኬሚካል እርጭት ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሎ እንደሚገመት ተናግረዋል ፡፡

የላብራቶሪ መመርመሪያ ቁሳቁሶች እና ለእርጭት የሚሆኑ ኬሚካሎች  የግብአት እርዳታ መንግስት እንዲደረግላቸዉ  የፕሮግራሙ አስተባባሪ አቶ ዳምጤ ላንከር ጠይቀዋል ፡፡

አቤል እስጢፋኖስ ] ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በሊባኖስ ባለዉ ግጭት ምክንያት በሀገሪቱ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉን ዜጎች ስጋት ዉስጥ መሆናቸዉ ተነገረ

በቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንፅላ ፅ/ቤትም በሊባኖስ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን የጥቃት ዒላማ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሎ ከሚታሰቡ ቦታዎች ራሳቸውን እንዲያርቁ አሳስቧል፡፡

ሀገረ ሊባኖስ የጋዛዉ እጣፋንታ ደርሶባት ዜጎቿን በአሰቃቂ ጥቃት እየተነጠቀች ስለመሆኑ ከስፍራዉ የሚወጡ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
የሊባኖስ ባለስልጣናት፤ እስራኤል ሂዝቦላ ላይ ያነጣጠረ ነዉ ባለችዉ ጥቃት በአንድ ቀን ብቻ 500 የሚጠጉ ሰዎች እንደተገደሉ ተናግረዋል።

ቀጣይ ደረጃ ብላ እስራኤል በሰየመችዉ እስራኤል በሊባኖስ ሄዝቦላን ለማጥቃት እንደምትገፋበት እየገለጸች ነዉ፡፡

ይህ ብቻ አይደለም በደቡባዊ ሊባኖስ የሚገኙ ዜጎች አካባቢያቸዉን ለቀዉ እንዲወጡ በሚል ለ80 ሺህ ዜጎች በእጅ ስልካቸዉ የማስጠንቀቂያ መልዕክት ማስተላለፏም ተሰምቷል፡፡

በሀገረ ሊባኖስ ከ 50 ሺህ በላይ ዜጎች እንደሚኖሩ መረጃዎች ያሣያሉ፡፡

የተለያዩ ሀገራት ሁኔታዉ ከዚህ የከፋ ሊሆን ይችላል በሚል ስጋት ዜጎቻቸዉ ሊባኖስን በአስቸኳይ ለቀዉ እንዲወጡ እያስጠነቀቁ ይገኛሉ፡፡

በተለይም በደቡባዊ ሊባኖስ የሚኖሩ ዜጎች ወደተያዩ ስፍራዎች በፍጥነት እየተመሙ ነዉ ተብሏል፡፡
ይሁንና ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ በመፈጠሩ አካባቢዉን ቶሎ ጥሎ ለመዉጣት አስቸጋሪ መሆኑም እየተነገረ ነዉ።
በቤይሩት የሚገኙ ኢትዮ ኤፍ ኤም ያናገራቸዉ ነዋሪዎችም ይህንኑ አረጋግጠዋል፡፡

በመካከለኛዉ ምስራቅ የሚታየዉ ግጭት እና ዉጥረት እየሰፋ እንዳይሄድ የዓለምን ህዝብ አስግቷል።
በደቡባዊ ሊባኖስ በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ንብረቶቻቸዉን በመኪና እየጫኑ ወደ ሰሜን የአገሪቱ ክፍል ለማቅናት እየሞከሩ ነዉ።

በሊባኖስ በአስር ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን በሊባኖስ ይኖራሉ።

በሊባኖስ ያለዉን ስጋት አስመልክተዉ ማብራሪያ የሰጡት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያተ ጌታቸዉ የዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ ነዉ ብለዋል፡፡

በቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንፅላ ፅ/ቤት በበኩሉ በሊባኖስ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን የጥቃት ዒላማ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሎ ከሚታሰቡ ቦታዎች ራሳቸውን እንዲያርቁ አሳስቧል፡፡

በሊባኖስና በቀጠናው ያለው ወቅታዊ የፀጥታ ስጋት እንዲሁም ውጥረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ መጥቷል ያለው ቆንፅላ ፅህፈት ቤቱ በተለይ በደቡባዊ ሊባኖስ እና በቤይሩት አንዳንድ አካባቢዎች ላይ የሚደርሰው ጥቃት ተጠናክሮ ቀጥሏል ብሏል፡፡

ቆንፅላ ፅህፈት ቤቱ ጉዳዩ አሳሳቢ መሆኑ ተረድቶ የዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር እየሰራ እንዳለ በፌስ ቡክ ገጹ ላይ ባወጣው መግለጫ አስረድቷል፡፡

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የሊባኖስ ህዝብ “ጥቃት ከሚሰነዘርባቸው አካባቢዎች በፍጥት እንዲወጡ አሳስበዋል።
ለረዥም ጊዜ ሄዝቦላህ እናንተን እንደ ጋሻ ሲጠቀምባችሁ ቆይቷል። በመኖሪያ ክፍሎቻችሁ ውስጥ ሮኬቶችን እና ሚሳኤሎችን አስቀምጧል።
ህዝባችንን ከሄዝቦላህ ጥቃት ለመከላከል እነዚህን መሳሪያዎች ማስወገድ አለብን ብለዋል።

በቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንፅላ ፅ/ቤት ከሊባኖስ መንግስት የሚሰጡ መመሪያዎችን መተግበር የከፋ ነገር በሚያጋጥምበት ወቅት ደግሞ በቆንፅላው የቀጥታ የስልክ መስመር ዜጎች እንዲደውሉ ፅህፈት ቤቱ ጠይቋል፡፡

ችግሩ እየከፋ የሚሄድ ከሆነ ወደፊት የሚወሰዱ እርምጃዎችን በፌስ ቡክ የማህበራዊ ትስስር ገፅ ላይ የማሳውቅ ይሆናል ብሏል፡፡

አባቱ መረቀ
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8
በትራፊክ አደጋ የ28 ሰዎች ሕይወት አለፈ

ከወላይታ ሶዶ ከተማ ወደ ዳውሮ ዞን ሲጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ተገልብጦ የ28 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

በወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ የትራፊክ አደጋ መከላከልና ቁጥጥር ዲቪዥን ኃላፊ ኢንስፔክተር ወልዴ ቢሊሶ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ ከሟቾች በተጨማሪ በ29 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡

አደጋው ዛሬ ቀን 7 ሠዓት ላይ በወላይታ ዞን ኪንዶ ዲዳዬ ወረዳ ፈታታ ቀበሌ መከሰቱንም አረጋግጠዋል፡፡

የተከሰተው አደጋ ከባድ መሆኑን ጠቅሰው የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል አመላክተዋል፡፡

Via fbc

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ።

መልካም በዓል!

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ፎቶ ፦ የ2017 ዓ/ም የመስቀል ደመራ አከባበር በዓል በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ።

photo - tikvah

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
አረጋዊ ካህን ዐራት ቤተሰባቸውን ጨምሮ ማንነታቸው ባልታወቁ ኃይሎች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ

መልአከ/መ/ ቀሲስ ወልደ ኢየሱስ አያሌው የተባሉ በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሉሜ ( ሞጆ ) ወረዳ ቤተ ክህነት በቢቃ ደ/መ/ቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ለ 41 ዓመታት ያህል ከዲቁና እስከ ደብር አስተዳዳሪነት ድረስ በትሕትና ሲያገለግሉ መቆየታቸው ተገልጿል፡፡

ካህኑ ከባለቤታቸውና ከሦስት ልጆቻቸው ጋር ባሰቃቂ ሁኔታ ማንነታቸው ባልታወቁ ኃይሎች በግፍና በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን የሉሜ ወረዳ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የገለጸ ሲሆን ልጃቸው ዲ/ን መልአክ ወልደ ኢየሱስም የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ እንደነበር ተጠቅሷል፡፡

ጸሎተ ፍትሐት ሥርዓቱም የሞጆ ሉሜ ወረዳ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ሰላም ቆሞስ አባ ሰይፈ ገብርኤል ገረመው፣ የአድባራት አስተዳዳሪዎች ፣ አበው ካህናት ሊቃውንት ፣ በርካታ ምእመናን በተገኙበት በሞጆ ደ/ብ/ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን በብፁዕነታቸው መሪነት እየተከናወነ ይገኛል።

ዘገባው የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሚዲያ ነው

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የሸዋ አማራ የጦር ግንባር ዉሎዎችን በሚዛናዊነት እየተከታተለ የሚያቀርብ ቻናል ልጠቁማችሁ👇👇
https://www.tg-me.com/SNN_merja
እስራኤል በዛሬው እለት በደቡባዊ ቤይሩት ከተማ የሂዝቡላህ ዋና መስሪያቤትን ጨምሮ ሶስት ህንፃዎችን ሙሉ በሙሉ በማውደም በርካታ ሰዎች ህይወት አልፏል።

የጥቃቱ ኢላማ የሂዝቡላሁ መሪ ሰይድ ሀሰን ነስረላህ የነበረ ሲሆን ኢላማዋ አለመሳካቱን ቡድኑ አስታውቋል።

ሂዝቡላህ ከጥቃቱ በሗላ በሰጠው አጭር መግለጫ ሰይድ ሀሰን ነስረላህ ደህንነቱ በተጠበቀ ቦታ ነው ብሏል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) 79ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ተገኝተው ስሜት የተሞላበት ንግግር አድርገዋል፡፡ 

“ዘንድሮ በጉባኤው የመሳተፍ እቅድ አልነበረኝም፤ ሀገሬ በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ በምትገኝበት ጊዜ እዚህ የተገኘሁት በመድረኩ ከተለያዩ አካላት ለቀረበብን ወቀሳ ምላሽ ለመስጠት ነው” በሚል ንግራቸውን የጀመሩት ጠቅላይ ሚንስትሩ እየተዋጋን ያለነው ከምድረ ገጽ ሊያጠፉን ከሚሹ “አረመኔ ጠላቶች” ጋር ነው ብለዋል።

“እስራኤል ኢራን በከፈተችው 7 አውደ ውግያዎች እየተዋጋች ትገኛለች፤ ተሄራን ከምታሰማራቸው ርህራሄ የለሽ ገዳዮች እራሳችንን መከላከላችንን እንቀጥላለን፡፡ ይህ ሲሆን በኢራን ውስጥ የእስራኤል ረጅም ክንድ የማይደርስበት ቦታ አለመኖሩ ሊታሰብበት ይገባል” ነው ያሉት

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2024/09/28 23:21:34
Back to Top
HTML Embed Code: