Telegram Web Link
የኢትዮጵያ አወ‍እሮፕላን በሱማሌላንድ አየር ክልል እየበረረ በሌላ አቅጣጫ ሲመጣ ከነበረ የኤሚሬትስ አውሮፕላን ጋር ለሁለተኛ ጊዜ ከመጋጨት ለጥቂት ተርፏል ተባለ

በ 37,000 ጫማ ከፍታ ላይ ሲበር የነበረዉ የኤምሬትስ  አየር መንገድ በተመሳሳይ ርቀት ላይ ከነበረው ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በድጋሚ ከመጋጨት ለጥቂት መትረፍ ተሰማ።

ከሞቃዲሾ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች በተሰጠዉ ትዕዛዝ በተመሳሳይ የጫማ ከፍታ ላይ ሲበሩ የነበሩት ንብረትነታቸው የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና የኢትዮጵያ መንግስት የሆኑት አዉሮፕላኖች በድጋሚ ከመጋጨት አደጋ መትረፋቸው የሶማሌላንድ ሲቪል አቪዬሽን እና ኤርፖርቶች ባለስልጣን ማስታወቁን ዳጉ ጆርናል ሰምቷል። ባለፈው የካቲት ወር በተመሳሳይ አጋጣሚ የኢትዮጵያ እና የኳታር አየር መንገዶች ንብረት የሆኑ አውሮፕላኖች ከመጋጨት ለጥቂት መትረፋቸው ይታወሳል።

እሁድ መጋቢት 15 ቀን 2016 ዓ.ም. በ 37,000 ጫማ ከፍታ ላይ ሲበር የነበረዉ የኤምሬትስ አየር መንገድ አዉሮፕላን UAE722 እና በተመሳሳይ በ 37,000 ከፍታ ላይ ከነበረዉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ETH690 ለመጋጨት ጥቂት ደቂቃዎች ሲቀራቸዉ የሶማሊላንድ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን አብራሪ ባደረጉት ጥረት አብራሪው በፍጥነት ከፍታውን በመቀየር ወደ 39, 000 ጫማ ከፍ እንዲል በማድረግ የተፈራው አደጋ ለጥቂት ሳይደርስ እንዲቀር አድርጓል።

በድጋሚ ለተፈጠረዉ ክስተት የሶማሌላንድ የሲቪል አቪዬሽን እና አየር ማረፉያዎች ባለስልጣን  የሞቃዲሾ ትራፊክ ተቆጣጣሪዎችን የወቀሰ ሲሆን።

መሰል ቸልተኝነት እና የእውቀት ማነስ ሞቃዲሾ በሚገኙ የሱማልያ የአቪዬሽን ባለሞያዎች በተደጋጋሚ እየተፈጠረ መሆኑን አለም ይወቅ ሲል አክሏል።

ሁኔታውም የአየር ደህንነትን አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑን አፅንኦት በመስጠት ሁኔታውን ኮንኗል።

Via ካፒታል

@ethio_mereja_news
“ ህወሓት የፕሪቶርያውን ስምምነት በግልፅ በመጣስ ራያ ላይ ጦርነት ከፍቷል ” - የአላማጣና አካባቢው አመራር‼️
የትግራይ እና አማራ ክልሎች የይገባኛል ጥያቄ ከሚያነሱበት አንዱ በሆነው ራያ አላማጣ አካባቢ ትላንትና " ህወሓት " ተኩስ መክፈቱን፣ በዚህም በሰው ሕይወት ላይ ሞትና የአካል ጉዳት ሙድረሱን አካባቢውን ከሚያስተዳድሩ አመራሮች (ባለስልጣን) አንደኛው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

አንድ የአካባቢው አመራር (ባለስልጣን) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ “ ራያ ላይ  አዲስ ነገር አለ። ህወሓት የፕሪቶሪያውን ስምምነት በግልፅ በመጣስ ራያ ላይ ጦርነት ከፍቷል ” ብለዋል።

“ ቀን ላይ አንድ ሰው ሕይወቱ አልፏል። ሁለት ቆስለው ወደ ደሴ ሪፈር ተብለዋል። ደንበሩን በማለፍ የራያ አላማጣ ወረዳ አዳዲስ ቀበሌዎች ተቆጣጥሯል ” ሲሉ አክለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጦርነቱ የተከፈተው በምን ሰዓት ነው ? በዬት በኩል ነው የተከፈተው ? አሁን ተኩስ አለ ? በቁጥጥር ስር የሆኑት ቀበሌዎች እነማን ናቸው ? ከሰሞኑን ለጦርነት አመላካች ጉዳዮች ነበሩ ? ሲል ለአመራሩ ጥየቄ አቅርቧል።

አመራሩም ፣ “ ጦርነቱን የጀመሩት ሰኞ ሌሊት 6:00 አከባቢ ሲሆን፣ እስከ ቀን 6:30 ድረስ ነበር። መከላከያ ለራያ ምሊሻ ‘ወደ ኋላ ተመለሱ እነርሱም ይመለሳሉ’ በማለቱ ምክንያት ጦርነቱ ቁሞ የራያ ምሊሻ ወደ ኋላ ቢልም TDF መልሶ ቦታውን ተቆጣጥሮታል ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ተኩሱ የተጀመረበትን ልዩ ቦታ በተመለተ በሰጡት ምላሽም ፣ “ የተጀመረበት ቦታው ‘ጮጓራ’ ይባላል። የራያ አላማጣ ቦታ ነው። አሁንም እሱን በማለፍ ወደ ‘ኮስም’ የሚባል አከባቢ እየተጠጉ ነው። ተጨማሪ ኃይልም እያስጠጉ ይገኛሉ ” ብለዋል።

የአካባቢው አመራር የተኩሱን መነሻ በገለጹበት አውድ ፣ “ የዚህ ዋናው መንስኤ አማራ ክልል #ወልቃይት እና #ራያ በስርዓተ ትምህርቱ ካርታ ላይ ተካተዋል በሚል በወጣው መግለጫ ነው ” ሲሉ አስረድተዋል።

“ የራያ ህዝብ የዘመናት ትግሉ በህጋዊ መንገድ ፍትህ ማግኘት እንጂ ጦርነት አይፈልግም። እነሱ እየተከተሉ ደጋግመው እያቆሰሉት ነው ” ሲሉም አክለዋል።

በህወሓት ተከፈተ ስለተባለው ተኩስ በትግራይ ክልል በኩል እስካሁን በይፋ የተባለ ነገር የለም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በትግራይ ያሉ አስታዳዳሪዎችን አግኝቶ የነበረ ሲሆን ስብሰባ ላይ እንደሆኑና ወደ በኃላ ማብራሪያ እንደሚሰጡን ገልጸዋል።

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ካቢኔ ሰሞኑን በሰጠው መግለጫ፣ “ የአማራ ክልል የትግራይ መሬት በካርታው በማስፈር የትምህርቱ ሰርዓቱ አካል በማድረግ እያስተማረበት ይገኛል " ማለቱ አይዘነጋም።

አስተዳደሩ ፤ በአማራ ክልል መንግሥት በኩል በትግራይ ህዝብ ላይ ግፍ እና በደል ሲፈፀም እንደቆየ አሁንም እንደቀጠለ ገልጾ ክልሉ የሰላም ስምምነቱን የሚያናጋ ጠብ አጫሪ ተግባራትን እየፈፀመ እንደሆነ ከሶ ነበር።

የፌደራል መንግስት በካርታው ላይ ምንም አይነት እርማት እንዳልሰጠ ፣ የአማራ ሕዝብም ሆነ ሌለው የኢትዮጵያ ህዝብ ከጊዚያዊ አስተዳደሩ ጎን እንዲቆሙ ይህ ሳይሆን ቀርቶ ለሚከተለው ነገር ሁሉ ግን የአማራ ክልል ሙሉውን ኃላፊነት ይወስዳል " ሲል አስጠንቅቆ ነበር።

@ethio_mereja_news
በኢትዮጵያ የኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚዎች ቁጥር 41 ሚሊዮን ደረሰ 

በኢትዮጵያ የኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚዎች ቁጥር 41 ሚሊዮን መድረሱን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች በተገኙበት ዲጂታል ኢትዮጵያን ለማሳካት የተከናወኑ ተግባራትና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ውይይት ተደርጓል።

በመድረኩ በነበረው የፓናል ውይይት ላይ የተሳተፉት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ በቴሌኮም ዘርፉ የተደረጉ ማስፋፊያዎችና ለውጦችን ዘርዝረዋል።

በዚህም በግልና በመንግስት የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢዎች የሞባይል አገልግሎት ደንበኞች ቁጥር 85 ሚሊዮን መድረሱን ተናግረዋል።

@sheger_press
@sheger_press
ያሳዝናል‼️

የአለልኝ የሞቱ መንስኤ ከቤተሰብ ጋር በትዳሩ ምክንያት አለመግባባት ነው !

የካናል ፕሉሱ ጋዜጠኛ አብዱ ሞሀመድ

"...ለእረፍት ወደ ቤተሰቦቹ ቤት አርባምንጭ ባለቤቱን ይዞ እንደሄደና ፡ ቤተሰቦቹ ትዳሩን እንዳልወደዱለትና ጭቅጭቅ እንደነበር፡ ከዛም ሞተሩን አሰነስቶ አዲስ ወደሚያሰራው የግል ቤቱ በመሄድ የኤልትሪክ ምሰሶ ላይ ራሱን አጠፋ " ብሏል በዘገባው

ከመሰረተው ትዳር ጋር በተገናኘ ተደጋጋሚ ጭቅጭቆች እንደነበሩ በዩቲዩብ ቻናሉ አጋርቷል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
መንግሥት በዋና ከተማ አዲስ አበባ የሚከናወኑ የቤት ፈረሳዎች ከተማዋን ለማዘመንና ለነዋሪዎቿም ምቹ ለማድረግ የታሰበ የልማት እቅድ መሆኑን ይገልጻል። መኖሪያ ቤታቸው ለፈረሰባቸው ወገኖችም ምትክ ቦታ እንደሚሰጥም እንዲሁ። በዛሬው ዕለትም በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ሥራ ሂደት መገምገሙንም ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ በማኅበራዊ መገናኛ ገጻቸው አመልክተዋል። በዚህም ቀዳሚ ዓላማቸው አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ የተመቸች ሳቢ ከተማ ለማድረግ ያላቸውን ቁርጠኝነት ማሳካት መሆኑንም ገልጸዋል። «የማልማት ሥራ ሂደቱ በግሉ ክፍለ ኢኮኖሚና በመንግሥት ብሎም አነስተኛ ገቢ ባላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች እና የተለያዩ አካላት የተያዙና የተከራዩ ንብረቶችን የነካ ሊሆን ቢችልም ይህ ለረዥም ጊዜ ፋይዳ ትልም ይዞ የተነሳ ሥራ ሲጠናቀቅ ለሁሉም ባለድርሻ አካል ብሎም ለሰፊው ሕዝብ የሚሰጠው ጥቅም ትልቅ ነው»ም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
ከተማን ለማዘመን በማሰብ የነባር ቤቶች እና መንደሮች መፍረስ አስቀድሞ ከሌሎች ሃገራት ተሞክሮ ቢወሰድበት መልካም እንደነበር የሚጠቁሙ በበኩላቸው ለታሪካዊ ሕንጻዎችና ቅርሶች ተገቢና ሞያዊ ጥንቃቄ እያሳሰቡ ነው። ከበቂ መተላለፊ መንገድ አንስቶ የመጸዳጃ ቤቶች እና የፍሳሽ ማውረጃ መስመሮች ጉድለት የሚታይባቸው ጭርንቁስ መንደሮችን የዋና ከተማዋን ደረጃ በጠበቀ መልኩ ማሻሻል እንደሚያስፈልግ የሚገልጹ ወገኖች ጥንታዊ የከተማ ገጽታዎችን ጠብቆ ማቆየት በሌሎች ሃገራት ለቱሪዝም መስህብነት አይነተኛ ሚና እንዳለውም ያነሳሉ። እርስዎስ ምን ይላሉ?

@ethio_mereja_news
#Notcoin

የመጨረሻ እድል ነው 3 ቀን ነው የቀረው ፍጠኑ! ትንሽም ቢሆን ለመጫወት ሞክሩ👇

https://www.tg-me.com/notcoin_bot?start=r_573809_33859156

3 ቀን ብቻ ነው የቀረው ሁላችሁም የአቅማችሁን coin ሰብስቡ Tap Tab ማረግ ነው! ምንም ልፋት የለወም እዚሁ ቴሌግራም ቦት ላይ coin ሰለምሰበሰቡ ደህንነቱ 100% የተጠበቀ ነው! እንዳይቆጫቹ አሁኑኑ ጀምሩ

ግድ የላችሁም
ችላ አትበሉት👇

Start በማረግ
አሁንኑ ጀምሩ👇👇

https://www.tg-me.com/notcoin_bot?start=r_573809_33859156
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ትናንት ምሽት ባወጣው መግለጫ ከሰሞኑ በህውሃት በኩል እየተፈፀሙ ነው ያላቸውን ትንኮሳዎች አንስቶ ለአማራና ለትግራይ ህዝብ እንደዚሁም ለአማራ ክልልና ፌደራል መንግስት መልዕክት አስተላልፏል።ከመግለጫ የተወሰዱት 3 ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው።

"የተከበርከው የአማራ ሕዝብ…ትሕነግ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ጠላት ቢሆንም ፣ በተለይ የአማራ ህዝብ የቡድኑ ወረራ ቀጥተኛ ሰለባ እና ገፈት ቀማሽ በመሆኑ ጦርነቱን የመመከት ድርብ ኃላፊነት ያለበት መሆኑ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም በሁሉም አካባቢዎች የሚገኝው ሕዝባችን ካለፈው የጥፋት ግዜ በመማር ለታሪካዊ ጠላቱ ፕሮፖጋንዳ ጀሮ ባለመስጠት ራስህን ከአራተኛ ዙር ጥፋት ለመከላከል ከመቸውም ጊዜ በላይ በአንድነት እንድትቆም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡"

"የተከበርከው የትግራይ ሕዝብ በስምህ የሚነግደው … ቡድን ፣ ከመላው ኢትዮጵያውያን ጋር ያለህን ትስስር ለመበጠስ እና ከኢትዮጵያዊ ማንነትህ ለመንቀል በማያባራ የጦርነት አዙሪት ውስጥ እንዳስገባህና አምራች ሀይልህን ፍትሀዊ ባልሆነ ጦርነት ማግዶ ማስፈጀቱ ይታወቃል፡፡ ልጆችህን ከጉያህ እየነጠቀ ፣ ጥሪትህን እያሟጠጠ እና አግቶ በመያዝ ከሌሎች ኢትዮጵያውን ጋር በአንድነት እና በሰላም እንዳትኖር ጋሬጣ የሆነብህን ደም-የማይጠግብ የሽብር ቡድን ከራስህ ላይ አሽቀንጥረህ በመጣል ራስህን ነጻ እንድታወጣ ጥሪያችንን እያስተላለፍን ፣ ከሽብር ቡድኑ እገታ ነጻ ለመውጣት በምታደርገው ተጋድሎ ድጋፋችን እንደማይለይህ ከወዲሁ እናስታውቃለን፡፡ "   

"የአማራ ክልል መንግስትና የፌዴራል መንግስት ትህነግ ወያኔ ተደጋጋሚ ወረራ በመፈጸም ታሪክ ይቅር የማይለው ሰፊ ጥፋት በሀገርና በህዝብ ላይ የፈጸመ ሆኖ ሳለ ይህ አልበቃው ብሎ አሁንም ሌላ ዙር ጦርነት ቀስቃሽ ፕሮፓጋንዳ ውስጥ የገባ በመሆኑ ይህንን የወያኔን ጠብ አጫሪነት በትኩረት እንዲከታተሉ በጥብቅ እያሳሰብን ከዚሁ ጋር በተያያዘ በአማራ ክልል ውስጥ የተፈጠረውን ችግር ልዩ ትኩረት ሰጥተው በውይይትና ድርድር ሰላም የማስፈን ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሁንም ጥሪ እናቀርባለን።"
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)
መጋቢት 17/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ!

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፤ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በተወሰኑ የክልሉ አካባቢዎች ላይ ትንኮሳ መጀመሩን ገለጸ፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግሥት ከሰሞኑ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ያወጣውን መግለጫ ተከትሎ ምላሽ ሰጥቷል። ሙሉ መግለጫዉ እንደሚከተለው ቀርቧል...

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ.ም የአማራ ክልል ተማሪዎች መማሪያ መጻህፍትን እንደሰበብ ተመርኩዞ ያወጣውን የዛቻ እና የጠብ አጫሪነት መግለጫ ተመልክተናል፡፡ ጊዜያዊ አስተዳደሩ የአማራ ክልል የትምህርት ሥርዓትን በማጣቀስ የተሳሳተ ካርታ ተሰርቷል ሲል ያወጣው መግለጫ በተሳሳተ ካርታ ወደ አማራ ክልል ተካተዋል ያላቸውን አካባቢ ሕዝቦች ታሪካዊ እውነታን፣ ተጨባጭ ማስረጃዎችን እና ነባራዊ ሐቅን የካደ፣ አሳሳች እና የጠብ አጫሪነት ፍላጎትን የተሸከመ መግለጫ በመሆኑ እና በትናንትናው እለት ማለትም መጋቢት 18 ቀን 2016 ዓ.ም ደግሞ ከነበረበት አካባቢ በመንቀሳቀስ የራያ አላማጣ ወረዳ ቀበሌዎችን በመያዝ ነዋሪዎችን በመግደል እና በማሰቃየት ላይ ይገኛል፡፡

ጊዜያዊ አስተዳደሩ የአማራ ክልል የተማሪዎች የመማሪያ መጻሕፍ ውስጥ የተሳሳተ ካርታ ተሰርቷል ሲል ባወጣው መግለጫ ሊያመላክታቸው የተፈለጉት አካባቢዎች ካለፉት 30 ዓመታት በፊት ጀምሮ የወልቃይት ጠገዴ፣ ጠለምት እንዲሁም የወፍላ ወረዳዎች እና የራያ የማንነት ጥያቄ ያሉባቸው ወረዳዎች የማንነት እና ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄዎችን ሲያቀርቡባቸው በነበሩ ቦታዎች ላይ መኾኑ ግልጽ ነው፡፡

አሁን በሥራ ላይ የሚገኘው የሀገሪቱ ሕገ መንግሥት ከመጽደቁ በፊት በተስተዋሉት የአስተዳደራዊ መዋቅሮች እና አደረጃጀት ቅመራ ጅማሬ አንስቶ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በሰሜን ዕዝ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ አሰቃቂ ጥቃት በመፈጸሙ ምክንያት ጦርነት እስከተቀሰቀሰበት ግዜ ድረስ የወልቃይት ጠገዴ፤ ጠለምት እንዲሁም የወፍላ ወረዳዎች እና የራያ የማንነት ጥያቄ ያለባቸው ወረዳዎች በወቅቱ ለነበረው መንግስት የማንነትና ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄዎችን በማንሳት መብቶቻቸው እንዲከበሩላቸው ሲጠይቁ የነበሩ መሆኑን በበርካታ ታሪካዊ ሁነቶችና ተጨባጭ ማስረጃዎች የተረጋገጠ ጉዳይ ነው፡፡

ይሁን እንጂ እነዚህ የማንነትና ራስን በራስ የማስተዳደር መብቶቻቸው እንዲከበሩላቸው ሲጠይቁ የነበሩ ሕዝቦች እና አካባቢዎችን ለበርካታ ዘመናት በኃይል ሲገዛ የነበው የቀድሞው የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የወልቃይት ጠገዴ፤ ጠለምት እንዲሁም የወፍላ ወረዳዎች እና የራያ የማንነት ጥያቄ ያለባቸው ወረዳዎች ላነሱት ታሪካዊና ሕጋዊ ጥያቄዎች ሕጋዊ አሰራርን የተከተለ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ የአካባበው ተወላጆችን፣ የሀገር ሽማግሌዎችን፣ የማንነትና የአስተዳደር ጥያቄ አስተባባሪዎችን በማሰር፣ በማሰደድ እና በመግደል የሕዝቡ ጥያቄ ምላሽ ሳያገኝ እስከ ሰሜኑ የህግ ማስከበር ጊዜ ድረስ እንዲገፋ አድርጎታል ብሏል።


የማንነት እና የአስተዳደር መብት ዙሪያ ላነሳቸው ጥቄዎች የወልቃይት ጠገዴ፣ ጠለምት እንዲሁም የወፍላ ወረዳዎች እና የራያ የማንነት ጥያቄ ያለባቸው ወረዳዎች ትግል በተፋፋመበትና ከፍተኛ መስዋዕትነት ጭምር እየከፈለ በሚገኝበት ወቅት ህወሓት የሠሜን ዕዝ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን አሰቃቂ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ሁሉንም ኢትዮጵያዊያንን በማቀናጀት ለሁለት ዓመታት የቆየ የሕግ ማስከበር እርምጃ ለመውሰድ የተገደደበት ሁኔታ መፈጠሩ ይታወሳል፡፡

የማንነትና የአስተዳደር ጥያቄዎቹ ለዘመናት የታፈኑበት ሕዝብም ከማዕከላዊው መንግስት ጎን ተሰልፎ በህ.ወ.ሓ.ት የክህደት ተግባር በኢትዮጵያ ሕልውና እና ሉአላዊነትት ላይ የተጋረጠውን ግልጽ አደጋ እንዲቀለበስ የበኩሉን አስተዋጽዖ ከማበርከቱ ባሻገር በሂደቱ ህወሓት በኃይል ተገፍፎባቸው የነበረውን የማንነትና ጥያቄና ራስን በራስ የማስተዳደር ነጻነት የተቀዳጁበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡

በዚህም ምክንያት የወልቃይት ጠገዴ፣ ጠለምት እንዲሁም የወፍላ ወረዳዎች እና የራያ የማንነት ጥያቄ ያለባቸው ወረዳዎች ህዝብ እንደማንኛውም የሀገሪቱ ሕዝብ ሁሉ የልማቱ ተሳታፊና ተጠቃሚነት መብቱ ሊቀለበስ የማይችል በመሆኑ በቀድሞው የህ.ወ.ኃ.ት እና በኢ.ፌ.ዲ.ሪ መንግስት መካከል የፕሪቶሪያው ስምምነት ከመፈረሙ በፊት ጀምሮ የአማራ ክልል እንደሌሎቹ ዞኖችና የልማት ትሩፋቶች ሁሉ የአካባቢው ሕዝብም በትምህርቱም መስክ ተጠቃሚ እንዲሆኑ አድርጓል፡፡

አካባቢዎቹን በተመለከተ የነበረው፣ ያለው እና የሚኖረው እውነታ ይሄ ሆኖ ሳለ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ/ም ከፕሪቶሪያው ስምምነት ከመፈረሙ በፊት በስራ ላይ የዋሉ የአማራ ክልል ተማሪዎች እንደሌሎቹ አካባቢዎች የነዚህ አካባቢ ህፃናትም የመማራ መብታቸው እንዲከበር የአማራ ክልል መንግስት ግዴታውን መወጣቱን ሰበብ በማድረግ በአማራ ክልል ላይ ጥቃት ከመፈጸም የማይመለስ መሆኑን የሚገልጽ የጠብ አጫሪ መግለጫ ማውጣቱ ካለፉት ድርብርብ ውድቀቶች ትምህርት አለመውሰድን ከማሳየት የዘለለ ፋይዳ አይኖረውም፡፡

የተፈጠሩ ችግሮችን በህግ አግባብ እንዲፈታ እተደረገ ያለውን ጥረት የአማራ ክልል መንግስት የራሱን ድርሻ እየተወጣ ባለበት ሁኔታ በህዝብ መጎሳቆልና በወጣቶች እልቂት ትምህርት አለመወሰዱና የተለመደ ትንኮሳ በማድረግ ላይ መሆኑ እጅጉን አሳዝኖናል፡፡

ስለሆነም የትግራይ ክልል ግዜያዊ አስተዳደር ለሀገሪቱ ቋሚ ቀውስ ምንጭ ከሚያደርጉት ተግባራት እንዲታቀብ፣ ሀገራችንንና ሁለቱን ክልሎች ወደ ቀውስ ከሚያስገቡ ተግባራት በመቆጠብ ከለመደው አጓጉል የካርታ ፖለቲካ ጨዋታ እንዲወጣና የህዝብን ፍላጎት ማዕከል ባደረጉ ውይይቶች ላይ እንዲያተኩር እንዲሁም አንድ ሀገር ለመገንባት ለሚፈለገው ዘላቂ ሠላም እና ለሕዝቦች አንድነት መጽናት በሚበጅ ሐሳብና ተግባር ላይ እንዲያተኩር እንመክራለን ሲል መግለጫውን አጠናቅቋል፡፡

@ethio_mereja_news
በኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚሰሩ የጉምሩክ ሰራተኞች እንደአዲስ ሊዋቀሩ ነው ተባለ‼️

በቅርብ ጊዜያት በርካታ ቅሬታዎችን ያስተናገደው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጉምሩክ የስራ ክፍል፤ ሰራተኞች በአዲስ መልክ እንደሚደራጁ የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ።

የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ በ2016 ስምንት ወራት ውስጥ 49 የጉምሩክ ሰራተኞች እና ከፍተኛ አመራሮች  ላይ አስተዳደራዊ እና ሕጋዊ እርምጃ ተወስዷል ብለዋል።

ኮሚሽኑ በሰራተኝኞቹ ላይ የሚቀርቡትን ቅሬታዎች ለመቅረፍ "ረጅም ጊዜ" የወሰደ ጥናት መካሄዱ ታውቋል።

በጥናቱ መሰረት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ የሚሰሩ የጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞን ለመቀየር፣ ለማሸጋሸግ እና በድጋሚ ለማዋቀር ዝግጅት ተደርጓል ተብሏል።

@ethio_mereja_news
ጌታቸው ረዳ‼️

የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በድጋሚ የሚያገረሽበት ዕድል ዝግ ነው ሲሉ አቶ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ ፣ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በድጋሚ የሚያገረሽበት ዕድል ዝግ ነው በማለት ትናንት ከቻይናው ሲጂቲኤን ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል።

ያለፈው ጦርነት የትግራይ ሕዝብ ፍላጎት አልነበረም ያሉት ጌታቸው ፣ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደርና የትግራይ ሕዝብ ድጋሚ ጦርነት እንዳያገረሽ የተቻላቸውን ጥረት ኹሉ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል።

ጌታቸው ይህን ያሉት ፣ በአላማጣ አቅራቢያ በትግራይ ኃይሎች እና ባካባቢው ሚሊሻዎች መካከል የተኩስ ልውውጥ በተደረገ ማግስት ነው መባሉን ዳጉ ጆርናል ከዋዜማ ዘገባ ተመልክቷል።

አቶ ጌታቸዉ ይህንን ይበሉ እንጂ አብን፣ ሕወሃት ለአዲስ ዙር ጦርነት ቅስቀሳ እያደረገ ነው ሲል ትናንት ምሽት ባወጣው መግለጫ ከሷል። ፓርቲው፣ በግጭት ማቆም ስምምነቱ መሠረት የሕወሃት ተዋጊዎች ሙሉ በሙሉ ትጥቅ ሳይፈቱና መከላከያ ሠራዊት በትግራይ ክልል ጸጥታ ለማስከበር ሳይሠማራ ሕወሃት ለሌላ ዙር ጦርነት ፕሮፓጋንዳ በመለፈፍ ተጠምዷል ብሏል።

የፌደራሉና የአማራ ክልል መንግሥታት የሕወሃትን የጠባጫሪነት ቅስቀሳ በትኩረት እንዲከታተሉና በአማራ ክልል የሚካሄደው ግጭት "በንግግር" እና "ድርድር" እንዲፈታም አብን ጠይቋል። የአማራ ሕዝብ ሕወሃት ሊያደርስበት የሚችለውን ጥቃት ለመከላከል በአንድነት እንዲቆም የጠየቀው ፓርቲው፣ የትግራይ ሕዝብም ራሱን ከሕወሃት ቀንበር እንዲያላቅቅ ጥሪ አድርጓል።

@sheger_press
@sheger_press
መርጌታ ቃለ ህይወት  የባህል መዳኒት ቀማሚ እና መስተፋቅር እንሰራልን በሁሉም ከተሞች ያላችሁ አናግሩኝ:

መርጌታ ቃለ ህይወት የባህል መድህኒት አስማት እና ጥበብ ይፈልጋሉ:
የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል
1 ለመፍትሔ ስራይ
2 ለህማም
3 ጋኔን ለያዘው ሰው
4 ቡዳ ለበላው
5 ለቁራኛ
6 የዛር ውላጅ ለተዋረሰው
7 ለአይነ ጥላ
8 ነገረ ራዕይ(ራዕይ የሚያሳይ)
9 ለዓቃቤ ርዕስ
10 ለመክስት
11 ለቀለም(ለትምህርት)
14 ለመስተፋቅር
15 ለሁሉ ሠናይ
16 ለገብያ
17 ለአምፅኦ ብእሲት(ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች የሚሰራ)
18 ለመድፍነ ፀር
19 ሌባ የማያስነካ
20 ለበረከት

ውድ  ቤተሰቦች  ለማንኛውም ነገር ያማክሩን    ከስላምታ ጋር።
ከምሰጣቸው በትንሹ ይህን ይመስላል 
ለጥያቄወ 09 75-90-23-15
#የካፒታል ገበያ ነገር፡-

የካፒታል ገበያ  ወደስራ መግባቱን ተከትሎ በካፒታል ገበያው ውስጥ ስላለው  የኢንቨስትመንት ባንክ ዋና ዋና ተግባራት ከፕራግማ ኢንቨስትመንት አማካሪ ዋና ስራ አስፈፃሚ  ከአቶ  መርዕድ ብርሀን  ጋር የተደረገ ቆይታ።

# የኢንቨስትመንት ባንክ ማለት ምን ማለት ነው?

በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን አዋጅ ቁጥር 1248/2021 አንቀፅ 34 መሰረት  ኢንቨስትመንት ባንክ ተቀማጭ ገንዘብ የማይሰበስብ የገንዘብ ተቋም ነው፡፡

በግልም ይሁን በመንግስት የሚሸጡ የሰነደ መዋዕለ ነዋይ ሽያጮችን በውክልና የሚሸጥ ገዢ እና ሻጭን የማገናኘት ስራ የሚሰራ ተቋም እንደሆነም አቶ መርዕድ ይገልፃሉ። 

ኢንቨስትመንት ባንክ የአማርኛ ፍቺው መዋዕለ ነዋይ ባንክ ሲሆን በሰነደ መዋዕለ ገበያ ውስጥ ሰነደ መዋዕለ ነዋይ አቅራቢዎችን ከገዢዎች ጋር በማድረግ የግብይት ስርዐቱ እንዲፋጠን የሚያደርግ ተቋም ነው።

# የኢንቨስትመንት ባንክ ዋና ዋና ተግባራት ምን ምን ናቸው ?

•  የመዋዕለ ነዋይ  ገበያው አማካሪ  በመሆን ያገለግላል ይህም ማለት ድርጅቶች በካፒታል ገበያው ውስጥ ጥሩ ሆነው  እንዲቀርቡ ማብቃት

•  የሰነደ መዋዕለ ነዋዮችን የመግዛት እና የማሻሻጥ ስራም ይሰራል  በዚህም ሰነዶችን ቀድሞ በመግዛት ለድርጅቶች  የማከፋፈል ስራ ይሰራል

•  የድርጅቶችን ሰነዶችን ለመጀመሪያ ጊዜ ከገዢ ጋር እንዲገናኙ ሰነዱን ያዘጋጃል

•  እንዲሁም ለድርጅቶች ትላልቅ የሆነ የብድር  ሰነዶችን በማገናኘት ብድር ያመቻቻሉ፡፡

# አንቨስትመንት  ባንክ ከሌሎች ባንኮች የሚለይባቸው ባህሪያትስ ምን ምን ናቸው

ንግድ ባንክም ይሁን የግል ባንኮች ተጠሪነታቸው ለብሄራዊ ባንክ ሲሆን የኢንቨስትመንት ወይም የሰነድ መዋዕለ ባንክ ተጠሪነት ግን ለኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ሲሆን የሚመራውም በካፒታል ገበያው ነው።

ሌሎች ባንኮች ውስጥ ተቀማጭ የሚሆነው ገንዘብ ሲሆን ኢንቨስትመንት ባንክ ውስጥ ግን ተቀማጭ የሚሆነው ከሌሎች ባንኮች በተለየ መልኩ ሰነድ እንደሆነ አቶ መርዕድ ያስረዳሉ

ኢንቨስትመንት ባንክ የሰነደ መዋለ ነዋይነ ገዢ እና ሻጭን  ከማገናኘት ባለፈም በካፒታል ገበያው ውስጥ ጥናት በማዘጋጀት ለድርጅቶች የማቅረብ ሂደት መሰራቱም ልዩ እንደሚያደርገውም ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ነዋይ ገበያ ከእቅዱ ቀድሞ ለማሰባሰብ ካቀደው የመመስረቻ ካፒታል በላይ መሰብሰቡን   ሲነሳ  መስራች የሚያደርገው የአክሲዮን ሽያጭ ቀነ ገደብም በቅርቡ እንሚጠናቀቅም  በውይይቱ ተነስቷል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምግብ እና መድሃኒት ባለስልጣን ባለፈው ሰድስት ወር ውስጥ ምግቦች ላይ በአድ ነገር ጨምረው የተገኙ 18 ተቋማት ላይ እርምጃ ወስጃለው አለ፡፡

ላለፉት ስድስት ወራት በተደረገ የምግብ ቁጥጥር ልክ ባልሆነ መንገድ ሲሸጡ የተገኙ 18 ተቋማት ላይ የማሸግ እርምጃ መውሰዱን ባለስልጣኑ ለጣቢያችን አስታዉቋል፡፡

የባለስልጣኑ የቁጥጥር ዘርፍ ምክትል ስራ አስኪያጅ አሰፋ ተሬሳ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት እንደዚህ አይነት ክስተቶች በተለይ የተለያዩ በአላትን ተገን በማድረግ የሚደረጉ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

እንደ አብነትም አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ እንዲሁም መርካቶ አካባቢ እርምጃ ከተወስድባቸው አካባቢዎች መካከል መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡

በአላት ላይ እንደዚህ አይነት ተግባራት እንደሚበራከቱ በማወቃችን ከመደበኛው ጊዜ በበለጠ በአላት ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር ይደረጋልም ብለዋል፡፡

በቀጣይም የዒድ እንዲሁም የፋሲካ በዓላት እየመጡ ስለሆነ ከወዲሁ እቅዳቸው ውስጥ በማስገባት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጀመራቸውን ና የቁጥጥር ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አንስተዋል፡፡

ነገር ግን እንደዚህ አይነት ስራዎች የምግብ እና መድሃኒት ባለስልጣን ብቻ የሚቆጣጠራቸው ባለመሆኑ የሁሉም ትብብር እና በተለይ የፀጥታ አካላት ቁጥጥር እንደሚያስፈልግ አቶ አሰፋ ተናግረዋል፡፡

ማህበረሰቡም በዚህ ድርጊት ላይ የተሰማሩ አካላትን በሚያይበት ጊዜ ጥቆማ እንዲሰጥ ጠይቀዋል፡፡

@ethio_mereja_news
#ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኀበር (ኢሕባማ) በፆታዊ ጥቃት ለሚፈጸሙ ወንጀሎች ሲወሰን የሚስተዋለውን ፍፁም ያልተመጣጠነ ቅጣት በተመለከተ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ማብራሪያ ሰጥቷል።

ማኅበሩ የቅጣት ዋነኛ ዓላማ ወንጀል ፈጻሚዎች ተጸጽተው እንዲማሩ ፣ ሌሎችም ተመሳሳይ ድርጊት ላለመፈጸም ትምህርት እንዲወስዱ ለማድረግ ቢሆንም አሁን እየሆነ ያለው ግን ከዚህ በተቃራኒው እንደሆነ ገልጿል።

የማኀበሩ ምክትል ዳይሬክተር ወ/ሮ ቤተልሄም ደጉ ምን አሉ ?

“ አሁን አሁን የምንሰማቸው ውሳኔዎች ይበልጥ እንዲያውም የልብ ልብ የሚሰጡና ‘ምንድነው ይህን ያክል ጊዜ ነው ብታሰር’ የሚሉ አይነት አስተሳሰቦችን በሰዎች ላይ Create የሚያደርጉ ናቸው ” ብለዋል።

ሰሞንኛውን የወምበራ ወረዳ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የ6 ወራት የቅጣት ውሳኔ በተመለከተ በሰጡት ቃል ፦

“ በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ዝቅተኛው ተብሎ የሚቀመጠው እንኳ 5 ዓመታት ነው።

በልዩ ሁኔታዎች ተብሎ የተቀመጠው እንኳ፣ የወንጀለኛ መቅጫ 620ንና ከዚያ ቀጥሎ ያሉትን ብናይ ከ3 ዓመታት በታች የሚያስወስን የወንጀል ጥቃት የለም።

ከ6 ወራት እስከ 4 ዓመታት የሚወሰኑ ቅጣቶች አሉ። ለችግሩ ዋነኛ ክፍተቱ ምን ላይ እንደሆነ የሚያመላክት ጥናት ግን ገና የለም።

የማስረጃ ሕግ አለመኖር፣ ነገር ግን የማስረዳት ሸክም ጋር ተያይዞ ያሉት ከፍተኛ የሆኑ የማስረጃ ስታንዳሮዶች ራሱን በቻለ መልኩ ፆታን መሠረት ላደረጉ ጥቃቶች Contribute እያደርጉ መሆኑን መረዳት ይቻላል።

ክፍተት ያለው የቱ ጋር ነው ? ከዳኞች መረዳትና ግንዛቤ ነው ?፣ ከሕግ ማዕቀፎች ነው ? የሚለውን ለመለየት ጥናት ያስፈልጋል።

ቅጣት በሚወሰንበት ጊዜ ዳኞች ሚያስቀምጡት የቅጣት አወሳሰን መመሪያዎችና ደንቦች አሉ። እዚህን መመሪያዎችና ደንቦችን በደንብ መቃኘት ያስፈልጋል " ብለዋል።

... የ3 ዓመቷን ህፃን ላይ በፈፀመው ወንጀል ተላለፈ የተባለው የ6 ወራት የእስራት ቅጣትን በተመለከተ በመነሻው ምናልባት ጉድለት ሲኖር ፣ የማስረዳት ሸክምን ዐቃቢ ሕግ በአግባቡ ሳይወጣ ሲቀር ዝቅተኛ ቅጣት ሊወሰን ይችላል። ግን ጨቅላ ህፃን የደፈረን ሰው 6 ወራት ሊያስወስን የሚችል የህግ መነሻና መንደርደሪያ የለም።

ቅጣቱ የ3፣ 4 ዓመታት እንኳ ቢሆን ዝቅተኛው መንደርደሪያ ላይ አረፈ ብለን፣ በቂ አይደለም ልንል እንችላለን። ይሄ 6 ወራት የሚለው ግን ቅጣት ነው ወይ ? ራሱ፣ የሚለውን ጥያቄ አብሮ ያስነሳል። ስለዚህ የሕግ ማዕቀፋችን እንደገና ሊታይ ይገባል ” ብለዋል።

መፍትሄውን ምንድነው ?

“ ሁላችንም በዘርፉ ያለን ተቋማት ሁሉ የሕግ ማዕቀፎችን Re evaluate ማድረግና ክፍተቶች ካሉ ደግሞ መንግሥት እንዲያስተካክል የAdvocacy ስራዎችን መስራት ይጠበቅብናል ” ብለዋል።

መረጃው በአ/አ ቲክቫህ ኢኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ኢዮብ ትኩዬ የተዘጋጀ ነው።

@sheger_press
@sheger_press
የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ከታጣቂዎች ጋር ለመነጋገር “የሰላም መንገድ” እንደሚያመቻች ገለጸ

ከመንግሥት ጋር የትጥቅ ግጭት ውስጥ የገቡ ታጣቂ ቡድኖች “ነፍጣቸውን ወደ ጎን አድርገው” ደኅንነታቸው በተጠበቀ መልኩ እንዲነጋገሩ “የሰላም መንገድ” እንደሚያመቻች የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ገለጸ።

የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን “ሁሉም አሸናፊ ይሆንበታል” ለሚለው ምክክር ከታጣቂ ኃይሎች ጋር የመነጋጋገር ፍላጎት እንዳለው በተደጋጋሚ ቢገልጽም፤ ለዚህ ውይይት ግን ታጣቂዎች ‘ነፍጥን ማስቀመጥ’ አለባቸው ብሏል።

ታጣቂዎች ነፍጣቸውን አውርደው ለመነጋገር ከመንግሥት ስጋት እንዳለባቸው ያነሳሉ ሲሉ የገለጹት የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መሥፍን አርአያ፤  እስካሁን የኮሚሽኑን ጥሪ ተቀብለው የመጡ ታጣቂ ኃይሎች እንደሌሉ ተናግረዋል።

ኮሚሽኑ ከታጣቂዎች ጋር ተገናኝቶ ለመነጋገርና ስጋቱን ለመቅረፍ “የሰላም መንገድ” (ደኅንነት ዋስትና) እንደሚያመቻች ፕ/ር መሥፍን ለቢቢሲ ተናግረዋል።
በእነ ክርስቲያን ታደለ መዝገብ የተከሰሱ ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ

ተከሳሾቹ በአቶ ዩሃንስ ቧያለው አማካኝነት ላለፉት ስምንት ወራት የደረሰባቸውን በደል ለችሎቱ አስረድተዋል። በእነ ክርስቲያን ታደለ መዝገብ የተከሰሱ ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡
የፍትህ ሚኒስቴር በእነ ክርስቲያን ታደለ መዝገብ ባሉ 52 ተጠርጣሪዎች ላይ የፖለቲካ ርዕዮትን በሀይል ለማስፈጸም ተንቀሳቅሰዋል፣ በ1996 ዓም የወጣውን የወንጀል ህግ እንዲሁም የሽብር ወንጀሎችን ለመከላከል የወጣውን ህግ ጥሰዋል በሚል ክስ መስርቷል፡፡

በዚህ ክስ መዝገብ ስርም ክርስቲያን ታደለ፣ ዮሀንስ ቧያለው፣ ካሳ ተሸገር (ዶ/ር) ጫኔ ከበደ፣ እስክንድር ነጋ፣ ዘመነ ካሴ፣ አበበ ፈንታው፣ አሰግድ መኮንን፣ መከታው ማሞ፣ ፈንታሁን ሙሃባ እና ሌሎችም ተካተዋል፡፡ከ52ቱ ተከሳሾች መካከል 14ቱ ተጠርጣሪዎች ልደታ በሚገኘው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ህገ መንግስት እና ሽብር ወንጀሎች ችሎት የቀረቡ ሲሆን የተጠርጣሪዎቹ ጠበቃ እና ቤተሰቦች መገኘታቸው ተገልጿል፡፡

ያለመከሰስ መብት ያላቸው ሰዎች በአስቸኳይ አዋጁ ከታሰሩ በኋላ ለምን በቀጥታ ክስ መመስረት አልተቻለም?የተጠርጣሪዎች ጠበቃ ሰለሞን ገዛኸኝ ለአልዐይን እንዳሉት በችሎቱ መገኘታቸውን ገልጸው ፍርድ ቤቱ የተከሳሾችን ማንነት ካረጋገጠ በኋላ የተለያዩ ትዕዛዞችን አስተላልፏል ብለዋል፡፡

በችሎቱ ከተላለፉ ትዕዛዞች መካከልም አቃቢ ህግ ተከሳሾች አሁን ካሉበት የፌደራል ፖሊስ ጊዜያዊ ማቆያ ወደ ማረሚያ ቤት ይዛወሩ፣ ክሱም መታየት ይጀምር ብሎ ለፍርድ ቤት ዳኞች አቅርቦ እንደነበር ተገልጿል፡፡የተከሳሾች ጠበቃም ተከሳሾች ላለፉት ስምንት ወራት በተለያዩ ቦታዎች በእስር ላይ ከህግ ምክር እና አገልግሎት ተገልለው በመቆየታቸው ያሉበት ሁኔታ ሳይረጋገጥ ወደ ማረሚያ ቤት መዛወር እና የክስ ሂደቱም ለተለዋጭ ቀጠሮ ችንዲተላለፍ ችሎቱን ጠይቀዋል፡፡

እንዲሁም ዛሬ ችሎት የቀረቡት ተከሳሾች በአቶ ዩሃንስ በኋያለው አማካኝነት የነበሩበትን ሁኔታ ለችሎቱ እንዲያስረዱ ችሎቱ እንዲፈቅድላቸው እና ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው ጠይቀው ፍርድ ቤቱም ይህን እድል ሰጥቷቸዋል ተብሏል፡፡አቶ ዩሃንስ ቧያለውም ላለፉት ስምንት ወራት በአዋሽ አርባ እና አዲስ አበባ በጨለማ ክፍል ውስጥ እንደታሰሩ፣ ለመንቀሳቀስ አመቺ ባልሆነ ስፍራ መታሰራቸውን፣ ህክምናን ጨምሮ የሀይማኖት አባት፣ ቤተሰብ እና የህግ ማማከር አገልግሎት ተከልክለው መቆየታቸውን ለችሎቱ አስረድቷል፡፡

ፍርድ ቤቱም ተከሳሾቹን አጅቦ ወደ ፍርድ ቤት ያመጣቸውን የፌደራል ፖሊስ ሀላፊ በተከሳሾች በተነሱ ቅሬታዎች ዙሪያ ምላሽ እንዲሰጥ መጠየቁን፣ የፖሊስ ሀላፊውም በተከሳሾች ከተነሱት መካከል የተወሰኑ አገልግሎቶችን የከለከልናቸው አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ስለማይፈቅድላቸው በመሆኑ እንደሆኑ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ግራ እና ቀኙን ያዳመጠው ችሎቱም ተከሳሾች ፍርድ ቤት ከቀረቡበት ጊዜ ጀምሮ ጉዳያቸው በመደበኛ የህግ አሰራር መሰረት የሚዳኝ በመሆኑ ማንኛውም ተጠርጣሪ እና ተከሳሽ በህጉ መሰረት የተፈቀደለትን መብት መከልከል እንደማይቻል ትዕዛዝ መስጠቱን የተከሳሾች ጠበቃ ሰለሞን ነግረውናል፡፡

እንዲሁም ተከሳሾች ተጨማሪ ጥያቄ ካላቸው በጠበቃቸው በኩል ለፍድ ቤቱ ማቅረብ እንደሚችሉም ችሎቱ ትዕዛዝ እንደሰጠ ተገልጿል፡፡ከዚህ በተጨማሪም ተከሳሾቹ ወደ ማረሚያ ቤት ሳይሄዱ አሁን ባሉበት የፌደራል ፖሊስ ጊዜያዊ ማቆያ እንዲቆዩ ቀጣይ የክስ ሂደቶችን ለማየትም ለመጋቢት 27 ቀን 2016 ዓ.ም መቀጠሩን ጠበቃ ሰለሞን አክለዋል፡፡

የፌደራል ፖሊስም በአቃቢ ህግ ክስ መዝገቡ ከተጠቀሱት 52 ተጠርጣሪዎች መካከልም እስካሁን ያልተያዙ ቀሪ 38 ተጠርጣሪዎችን ይዞ እንዲያቀርብም ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Notcoin Mining Airdrop

3 ቀን ቀረው‼️

በዚህ ሊንክ በመግባት
#Start በሉት👇

https://www.tg-me.com/notcoin_bot?start=r_573809_33858216

1) Start earn more የሚለውን ተጫኑ ( ወይንም Play የሚል አለ )
2) ስክሪናችሁን Tap Tap በማድረግ ብዙ Token ሰብስቡ ( Energy ስለሚያልቅ በየተወሰነ ሰዓት ነው የምትሞክሩት ሲያልቅባችሁ )
3) Earn & Boost Section ውስጥ በመግባት ተጨማሪ ስራ እና ተጨማሪ Bonus ማግኘት ትችላላችሁ

በተረፈ ቀላል ስለሆነ ብትሞክሩት አሪፍ ነው ፣ ለአዲስ ገቢ 2.5k Free Token & ለTelegram Premium ተጠቃሚ ደግሞ 50k Free Token በመስጠት ይጀምራል.

https://www.tg-me.com/notcoin_bot?start=r_573809_33858216
በአፋር ክልል፣ በአፋር እና ኢሳ ሱማሌ ጎሳዎች መካከል በድጋሚ በተያዘው ሳምንት ግጭት ማገርሸቱን ዋዜማ ሰምታለች።

ግጭቱ የተከሰተው፣ በገቢ ረሱ ዞን (ዞን ሦስት) አሚባራ ወረዳ ውስጥ አፋርና ሱማሌ ክልሎች በሚወዛገቡበት ገዳማይቱ ቀበሌ እንደኾነ ታውቋል።

በግጭቱ ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰዎች ሳይገደሉና ሳይቆሰሉ እንዳልቀሩ ተነግሯል። ካለፉት ጥቂት ወራት ወዲህ፣ በአፋሮች እና ኢሳ ሱማሌዎች መካከል የሚደረጉ በትጥቅ የተደገፉ ግጭቶች ተበራክተዋል።

@ethio_mereja_news
" የሟች ወንድም እና እህትን በቁጥጥር ስር አድርገን ምርመራ እያካሄድን ነው " - የአርባ ምንጭ ከተማ ፖሊስ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንና የባህር ዳር ከተማ የመሀል ሜዳው ተጫዋች አለልኝ አዘነ ለህልፈት መዳረጉን ተከትሎ ቤተሰቦቹ  በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰምቷል።

የአርባ ምንጭ ከተማ ፖሊስ  " አሟሟቱ ድንገተኛና አሰቃቂ መሆኑን ተከትሎ የቅርብ ግንኙነት ያላቸዉን አካላት ይዤ ምርመራ ጀምሪያለሁ " ብሏል።

የወጣቱ ህይዎት ይቀጠፍ ዘንድ ምክኒያት የሆኑ ጉዳዮችን ለማወቅ የስልክ ልውውጦችን ከመመርመር በተጨማሪ በዙሪያው የነበሩ አካላትንም በቁጥጥር ስር እንዳዋለ ገልጿል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ እነማን ተያዙ ? የምርመራዉ አካሄድስ ምን ይመስላል ? ሲል ለአርባምንጭ ከተማ ፖሊስ አዛዥ የለሆኑት ኢንስፔክተር አብርሀም ሙሄ ጥያቄ አቅርቧል።

" የተጫዋቹ መሞት በተሰማበት ወቅት አጠራጣሪ ጉዳዮች ስለነበሩ ፖሊስ የምርመራ እንቅስቃሴ ጀምሯል " ያሉት ኢንስፔክተር አብርሀም " በዚህ ወቅት ወንድም እና እህቱን በቁጥጥር ስር አድርገን ምርመራ እያካሄድን ነው ።አሁን ላይ ከእህት እና ወንድሙ ዉጭ የተያዘ አካል የለም በማለት ወደፊት ግን ከተያዙት የሚለቀቅ ካልተያዙት ደግሞ የሚያዝ ሊኖር ይችላል " ብለዋል።

" አሁን ላይ ምርመራዉን በፍጥነትና በጥንቃቄ እያካሄድን ነው " ያሉት ኢንስፔክተር አብርሀም ሙሄ ውጤቱን ለመላ የኢትዮጵያን ህዝብ ለማድረስ ማሰባቸዉን  ጠቁመዋል።
         መረጃው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ነው።

@ethio_mereja_news
2024/10/01 22:29:53
Back to Top
HTML Embed Code: