Telegram Web Link
አረጋዊ ካህን ዐራት ቤተሰባቸውን ጨምሮ ማንነታቸው ባልታወቁ ኃይሎች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ

መልአከ/መ/ ቀሲስ ወልደ ኢየሱስ አያሌው የተባሉ በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሉሜ ( ሞጆ ) ወረዳ ቤተ ክህነት በቢቃ ደ/መ/ቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ለ 41 ዓመታት ያህል ከዲቁና እስከ ደብር አስተዳዳሪነት ድረስ በትሕትና ሲያገለግሉ መቆየታቸው ተገልጿል፡፡

ካህኑ ከባለቤታቸውና ከሦስት ልጆቻቸው ጋር ባሰቃቂ ሁኔታ ማንነታቸው ባልታወቁ ኃይሎች በግፍና በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን የሉሜ ወረዳ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የገለጸ ሲሆን ልጃቸው ዲ/ን መልአክ ወልደ ኢየሱስም የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ እንደነበር ተጠቅሷል፡፡

ጸሎተ ፍትሐት ሥርዓቱም የሞጆ ሉሜ ወረዳ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ሰላም ቆሞስ አባ ሰይፈ ገብርኤል ገረመው፣ የአድባራት አስተዳዳሪዎች ፣ አበው ካህናት ሊቃውንት ፣ በርካታ ምእመናን በተገኙበት በሞጆ ደ/ብ/ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን በብፁዕነታቸው መሪነት እየተከናወነ ይገኛል።

ዘገባው የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሚዲያ ነው

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የሸዋ አማራ የጦር ግንባር ዉሎዎችን በሚዛናዊነት እየተከታተለ የሚያቀርብ ቻናል ልጠቁማችሁ👇👇
https://www.tg-me.com/SNN_merja
እስራኤል በዛሬው እለት በደቡባዊ ቤይሩት ከተማ የሂዝቡላህ ዋና መስሪያቤትን ጨምሮ ሶስት ህንፃዎችን ሙሉ በሙሉ በማውደም በርካታ ሰዎች ህይወት አልፏል።

የጥቃቱ ኢላማ የሂዝቡላሁ መሪ ሰይድ ሀሰን ነስረላህ የነበረ ሲሆን ኢላማዋ አለመሳካቱን ቡድኑ አስታውቋል።

ሂዝቡላህ ከጥቃቱ በሗላ በሰጠው አጭር መግለጫ ሰይድ ሀሰን ነስረላህ ደህንነቱ በተጠበቀ ቦታ ነው ብሏል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) 79ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ተገኝተው ስሜት የተሞላበት ንግግር አድርገዋል፡፡ 

“ዘንድሮ በጉባኤው የመሳተፍ እቅድ አልነበረኝም፤ ሀገሬ በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ በምትገኝበት ጊዜ እዚህ የተገኘሁት በመድረኩ ከተለያዩ አካላት ለቀረበብን ወቀሳ ምላሽ ለመስጠት ነው” በሚል ንግራቸውን የጀመሩት ጠቅላይ ሚንስትሩ እየተዋጋን ያለነው ከምድረ ገጽ ሊያጠፉን ከሚሹ “አረመኔ ጠላቶች” ጋር ነው ብለዋል።

“እስራኤል ኢራን በከፈተችው 7 አውደ ውግያዎች እየተዋጋች ትገኛለች፤ ተሄራን ከምታሰማራቸው ርህራሄ የለሽ ገዳዮች እራሳችንን መከላከላችንን እንቀጥላለን፡፡ ይህ ሲሆን በኢራን ውስጥ የእስራኤል ረጅም ክንድ የማይደርስበት ቦታ አለመኖሩ ሊታሰብበት ይገባል” ነው ያሉት

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ኢትዮጵያ በሶማሊያ የደረሰውን የሽብር ጥቃት አወገዘች

የኢትዮጵያ መንግሥት በሶማሊያ ሞቃዲሾ የደረሰውን የሽብር ጥቃት አወግዟል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው የሐዘን መግለጫ÷ በተፈጸመው የሽብር ጥቃት ሕይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝቷል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት የተፈጸመውን ጥቃት በማውገዘ ሽብርተኝነትን በመታገል ረገድ ከሶማሊያ መንግሥትና ሕዝብ ጎን መሆኑንም አረጋግጧል፡፡
ወልቂጤ ከተማ በይፋ ከሊጉ ተሰርዟል

የወልቂጤ ከተማ እግር ኳስ ክለብ አስፈላጊው የመወዳደሪያ መስፈርት ባለሟሟላቱ በሊጉ የመጀመሪያ ሳምንታት ሁለት ጨዋታዎች ላይ ሳይካፈሉ ቀርተዋል።

የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አክስዮን ማህበር የውድድር ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ባስተላለፈው ውሳኔ ክለቡ “ ከ 2017 የ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ እንዲሰረዝ “ ወስኛለሁ ብሏል።

የወልቂጤ ከተማ ክለብ ለውድድር ዓመቱ የሚያስፈልገውን የክለብ ላይሰንሲንግ የምዝገባ ሂደት ማሟላት ሳይችሉ መቅረታቸው የሚታወስ ነው።

የወልቂጤ ከተማን ከሊጉ መሰረዝ ተከትሎ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ በቀጣይ በአስራ ስምንት ክለቦች መካከል የሚካሄድ ይሆናል።

@sheger_press
@sheger_press
በሲዳማ ክልል ደቡባዊ ዞን ዳራ ወረዳ በዚህ ወር ብቻ ከ25 በላይ ህፃናት በጅብ ተበልቷል ይለናል የዳውሮ ኮሚኒኬሽን‼️

ለዚህም የክልሉ መንግሰት ልዩ ትኩረት እንዲሰጥ ተጠይቋል።

ጅቦቹ በአካባቢው በቀን እየወጡ በተደጋጋሚ ጥቃት እያደረሱ መሆኑን በመጠቆም የክልሉ መንግሰት ልዩ ትኩረት እንዲሰጥ ተጠይቋል።
በሲዳማ ክልልም በቀን ጭምር የጅብ ጥቃት እንደቀጠለ ነው።

@sheger_press
@sheger_press
ሰበር መረጃ  ..🇩🇯

የጂቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌ በጠና እንደታመሙና ለህክምና ወደ ፈረንሳይ ፓሪስ መወሰዳቸው ተሰምቷል። አቶ እስማኤል ጂቡቲን ከሩብ ክፍለዘመን በላይ የመሩ አምባገነን መሪ ናቸው። ኢስማኤል ኦማር ሀገራችን ኢትዮጵያ የባህር በር እንዳታገኝ  በፊትለፊትም ከመጋረጃ ጀርባ ከሶማሊያ ኤርትራና ግብፅ ጋር ሆነው ከፍተኛ ሴራ እየሰራ የሚገኝ ጠላት ነው። እናም በአሁን ሰአት ኮማ ላይ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆኔ አንዳንድ ህይዎታቸው አልፏል የሚል  ያልተረጋገጠ መረጃዎች እየወጡ ነው...

@sheger_press
@sheger_press
#FakeNewsAlert በአርቲስት ቴዎድሮስ ታደሰ ህልፈት ዙርያ እየተሰራጨ ያለው መረጃ የተሳሳተ ነው

'Yehabesha' የተባለው እና ከ1.9 ሚልዮን በላይ የፌስቡክ ተከታዮች ያሉት ገፅን ጨምሮ በርካታ የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ታዋቂው ድምፃዊ ቴዎድሮስ ታደሰ ህይወቱ እንዳለፈ ዛሬ መረጃ ሲያጋሩ ውለዋል።

እነዚህ ፅሁፎች ምንም አይነት ምንጭ ሳይጠቀስባቸው ለህዝብ የተጋሩ ሲሆን በርካታ ሰዎችም መልሰው ሲያጋሩት (ሼር ሲያደርጉት ተመልክተናል)፣ በርካታ የኢትዮጵያ ቼክ ተከታታዮችም ፅሁፉን እንድናጣራ ጥያቄ አቅርበዋል።

የመረጃ ማጣርያ ዴስካችን በዚህ ዙርያ አንድ የአርቲስቱ ጓደኛን እና አንድ የቅርብ ቤተሰብን ያነጋገረ ሲሆን በማህበራዊ ሚድያ የተሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን ተናገረዋል።

"እኛም ከመሸ አይተነው ነበር፣ በርካታ ሰው ተደናግጦ ሲደውል ነበር፣ ወሬው ግን ውሸት ነው። ከእንዲህ አይነት በሬ ወለደ ፅሁፍ ምን እንደሚጠቀሙ አይገባኝም" ብለው ምላሽ የሰጡን ምንጫችን ይህ በአርቲስቱ ዙርያ ሲወራ ለሶስተኛ ግዜ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ማህበራዊ ሚድያ ላይ የሚሰራጩ መረጃዎችን ትክክለኛነት ሳናጣራ፣ የምናምናቸው ምንጮች ሳይዘግቡት እንዲሁም ማስረጃዎችን ሳንመለከት ባለማመን እና መልሰን ለሌሎች ባለማጋራት የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን እንከላከል።

Via:- ኢትዮጵያ ቼክ

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር የወደብ የመግባቢያ ስምምነትን በመከተል ክልላዊ መንግስታትን በማስታጠቅ ለተወሰኑ ጎሳዎች ስልጣን በመስጠት እና በጌዲኦ ክልል የሚገኙ የአየር ማረፊያዎችን በመቆጣጠር እና በማስፋፋት ሶማሊያ ከግብፅ ጋር ለገባችው ወታደራዊ ውል የበቀል እርምጃ ነው ሲሉ ከሰሱ‼️
👉"የውክልና ጦርነት በሃገሬ እንዲሆን አልፈቅድም"
ፕሬዝደንቱ አያይዘውም ግብፅ ሶማሊያን ለመቆጣጠር ነው የጦር መሳሪያ ያስገባችው የሚለው ፍፁም ውሸት ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ሶማሊያ ግብፅን አዲስ የአፍሪካ ህብረት ተልዕኮ እንድትቀላቀል የጋበዘችው የኢትዮጵያን ሰላም አስከባሪ ሃይል በግብፅ ወታደሮች ለመተካት ታስቦ ነው ብለዋል።

ሀሰን ሼክ "ኢትዮጵያን ጦርነት መግጠም አንችልም"፣"የውክልና ጦርነት በሃገሬ እንዲሆን አልፈቅድም"ብሏል።
ኢትዮጵያ ከሱማሊላንድ ጋር ያደረገችውን የወደብ ስምምነት በዲፕሎማሲ መፍታት ካልቻልን እና ቱርክ እያደራደረች ያለችው ድርድሩ ጥሩ ውጤት እንጠብቃለን። ያሳይሆን ቀርተው የባህር በር  ስምምነቱ ቢተገበር እንኳን ከኢትዮጵያ ጋር አንዋጋም። የውክልና ጦርነት በሱማሊያ ምድር አይታሰብም ብሏል።
ኢትዮጵያ ብቻዋን አይደለችም ከኋላ በኢኮኖሚ ጠንካራ እና ሃያላን ሃገራትም አሏት። ግን ሃገራቶችን ለመጥቀስ አልፈለጉም።
መረጃውን የወሰድኩት ከአልጀዚራ ጋር ካደረጉት ቃለምልልስ ነው።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ትራምፕ እንዲህ አሉ " ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ከጦርነቱ ጠብቀን"

" ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ከጦርነቱ ጠብቀን። ከዲያብሎስ ክፋትና ወጥመዶች ከልለን። በትህትና እንጸልያለን እግዚአብሔር ይገስጸው፣ አንተ የሰማይ ሠራዊት አለቃ ሆይ፣ በእግዚአብሔር ኃይል፣ የነፍስን ጥፋት እየፈለጉ በዓለም ላይ የሚንከራተቱትን ርኩሳን መናፍስትን ሁሉ ወደ ሲኦል ጣላቸው"

ይህ የቀድሞው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ በትዊተር ገፃቸው ያሰራጩት መልዕክት ነው።

@sheger_press
@sheger_press
ንግድ ባንክ በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ታሪፍ ተግባራዊ አደረገ!

ግዙፉ መንግስታዊ ባንክ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚያደርግ አስታዉቋል ።

ባንኩ ከመስከረም 21፤2017 ዓ.ም. ጀምሮ ምርትና የአገልግሎት ዓይነቶች ላይ በሚከፈል የአገልግሎት ክፍያ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ታሪፍ የተጨመረባቸው መሆኑን እንሳዉቃለን ቢልም በምን ያህል መጠን እንደሆነ ግን አልገለፀም።

የገንዘብ ሚኒስትር አዋጁ ተግባራዊ እንዲደረግ ለመንግሥት ፋይናንስ ተቋማት በሐምሌ 1 ቀን 2016 ዓ.ም. በፃፈው ደብደቤ ላይ እንደገለፀው ከሰኔ 27 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ በተደረገው የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ላይ ሙሉ በሙሉ በፌዴራል መንግስቱ በጀት የሚተዳደር የመንግስት መስሪያቤቶችን እንደሚያካትት ገልፆ ነበር ።

ይህን ተከትሎ መንግስት በቅርቡ ባወጣው አዲስ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሕግ ቁጥር 1341/2016 መስረት ባንኮች በሚሰጧቸው አገልግሎቶች ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲጣል በመታወጁ ንግድ ከዛሬ ጀምሮ የተጨማሪ እሴት ታክስ ታሪፍ የተጨመረባቸው መሆኑን ነዉ ያስታወቀው።

ከአዲሱ የዉጪ ምንዛሪ ለዉጥ ጋር ተያይዞ መንግስት ከያዛቸው ስር ነቀል ለዉጦች መካከል የታክስ ዘርፉ አንደኛው መሆኑ ይታዉቃል። በዚህ በበጀት ዓመት በታክስ 1.15 ትሪሊየን ብር ለመሰብሰብ ያቀደ ሲሆን ይህ ደግሞ የበጀት ዓመቱ ሲጀመር ለመሰብሰብ ታቅዶ ከነበረው 502 ቢሊየን ብር አንፃር ከእጥፍ በላይ የጨመረ እንዲሆን አድርጓታል ።

በዚህም በቅርቡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልን ጨምሮ ኢትዮቴሌኮም እንዲሁም ሌሎች የመንግስታዊ ተቋማት በሚሰጧቸው አገልግሎት ላይ የታሪፍ ማሻሻያ እያደረጉ እንደሚገኙ ይታወቃል ።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Breaking

አሁን ማምሻውን ኢራን እስራኤል ላይ የባለስቲክ ሚሳኤል ጥቃቶችን አድርሳለች::

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
#ሰበር

እስራኤል ከኢራን ሚሳኤሎች መወንጨፏቸውን አስታወቀች

የእስራኤል ጦር በመላ ሀገሪቱ የሚሳኤል ሳይረን እየተሰማ መሆኑን ያሳወቀ ሲሆን ከኢራን ሚሳኤል ተወንጭፋል ብሏል።

@sheger_press
@sheger_press
የእስራኤል መከላከያ ኃይል ጥቃቱ መጀመሩን ተከትሎ ለዜጎቹ ባስተላለፈው መልዕክት “የሚወጡ መመሪያዎችን በንቃት እንዲከታተሉ” አሳስቧል።

የኢራን የሚሳዔል ጥቃት መጀመሩ ተከትሎ የእስራኤል ጦር የአገር ውስጥ ዕዝ በአንዳንድ አካባቢዎች ለሚኖሩ ዜጎች ወደ መከላከያ ስፍራዎች እንዲገቡ የሚያዝ “ነፍስ አድን” ያለውን መመሪያ በአጭር የጽሁፍ መልዕክት አስተላልፏል።

የጦሩ ቃል አቀባይ ዳንኤል ሃጋሪ ደግሞ በቪዲዮ ባስተላለፉት መልዕክት፥ ነዋሪዎች በአቅራቢያቸው ወደሚገኙ ከጥቃት የመሸሸጊያ ስፍራዎች በመግባት ተጨማሪ መመሪያዎችን እንዲጠባበቁ መክረዋል።

ቃል አቀባዩ ጨምረውም የእስራኤል የአየር ጥቃት መከላከያ ሥርዓት “ሙሉ ለሙሉ በስራ ላይ ሆኖ የሚተኮሱ ሚሳዔሎችን በመለየት እያከሸፈ” መሆኑን ተናግረዋል።

@sheger_press
@sheger_press
ባይደን እስራኤል ራሷን ከኢራን ጥቃት ለመከላከል አሜሪካ ለመርዳት ዝግጁ መሆኗን ተናገሩ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እስራኤል ራሷን ከኢራን የሚሳኤል ጥቃት ለመከላከል እና በአካባቢው የሚገኘውን የአሜሪካን ጦር እገዛ ለማድረግ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ እስራኤልን ከእነዚህ ጥቃቶች ለመከላከል እና በአካባቢው የሚገኙ የአሜሪካን ሰራተኞችን ለመጠበቅ እንዴት እንደተዘጋጀች ከምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስ እና ከዋይት ሀውስ ብሔራዊ ደህንነት ቡድን ጋር ተወየይተናል ሲሉ በኤክስ ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።

@sheger_press
@sheger_press
ኢራን በእስራኤል ላይ ከ 240 በላይ የባለስቲክ ሚሳኤሎችን መተኮሷ ተዘገበ

ምሽቱን ኢራን በእስራኤል ላይ ከፍተኛ የሚሳኤል ድብደባን ፈጽማለች። ኢራን ከ 240 እስከ 250 የባለስቲክ ሚሳኤሎችን ተኩሳለች የተባለ ሲሆን ብዙዎቹ ቢከሽፉም በእስራኤል ምድር ላይ የወደቁ ሚሳኤሎች መኖራቸዉን ግን ዳጉ ጆርናል ከስፍራው የቀጥታ ስርጭት ዘገባ ከሚሰሩ የዜና አዉታሮች ታዝቧል።

አሁ ላይም ኢራን ሌላ ዙር ጥቃት በእስራኤል ላይ ካልፈጸመች የአየር ጥቃቱ ቆሟል የተባለ ሲሆን በጥቃቱ የደረሰዉ ጉዳት ግን እስካሁን አልታወቀም። ኢራን ጥቃቱን በእስራል ላይ ያደረገችዉ በሁለት አቅጣጫዎች ነዉ ተብሏል።

ቴልአቪቭ ፤ ለቴርሃን ጥቃት ምን አይነት ምላሽ ትሰጣለች የሚለዉ አሳሳቢዉ ጉዳይ ሲሆን ጦርነቱን ሀያላኑ ሀገራት እንዳይቀላቀሉት አስግቷል። የእስራኤል መከላከያ ሀይል በበኩሉ ከ 180 በላይ ሚሳኤሎች መተኮሳቸዉን እንዳረጋገጠ ኤቢሲ ኒዉስ ዘግቧል።

እስራኤል የኢራን የአየር ጥቃት መቆሙን ተከትሎ ዜጎች ከሚሳኤል መሸሸጊያዎች እንዲወጡ መልዕክት አስተላልፋለችም ተብሏል። እስራኤል ሶስት የአየር ጥቃት መከላከያ ያላት ሲሆን ሶስቱን የጸረ ሚሳኤል መከላከያን የጣሱ የኢራን ሚሳኤሎች ግን በእስራል ላይ ቀላል የማይባል ጉዳት እንደሚያደርሱ ዳጉ ጆርናል ታዝቧል።

@sheger_press
@sheger_press
በእስራኤል ዋና ከተማ ቴላቪቭ በተከፈተ የጅምላ ተኩስ ስድስት ሰዎች ተገደሉ

ኢራን በእስራኤል ላይ ከፈፀመችው የሚሳኤል ጥቃት በተለየ ሁኔታ፣ በቴል አቪቭ የጅምላ ተኩስ ተከስቷል።

ዛሬ ማምሻውን ታጣቂዎች በከተማው ጎዳና ላይ በሰዎች ላይ ተኩስ ከፍተዋል ሲል ፖሊስ የገለፀ ሲሆን የእስራኤል መገናኛ ብዙሃን ቢይንስ ስድስት ሰዎች መሞታቸውን ዘግበዋል። ቢያንስ ሰባት ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸው የተዘገበ ሲሆን አንዳዳዶቹ በአስጊ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ መባሉን ዳጉ ጆርናል ዘግቧል።

በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ የተለጠፉት ምስሎች እንዳሳዩት ታጣቂው በጃፋ አካባቢ በሚገኝ የባቡር ጣቢያ ላይ መሬት ላይ ተኝተው በተሰበሰቡ ሰዎች ላይ ሲተኩስ ታይቷል። ፖሊስ የጥቃቱን ምክንያት “ሽብር” ሲል ገልጾታል።
2024/10/02 00:25:32
Back to Top
HTML Embed Code: