Telegram Web Link
የግብፁ ፕሬዝዳንት አልሲሲ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከንን አነጋገሩ

የግብፁ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከንን በካይሮ ተቀብለው አነጋግረዋል ። ይሁን እንጂ በምን ጉዳይ ላይ እንደ ተነጋገሩ የተባለ ነገር የለም ።

አንቶኒ ብሊንከን ግብፅ ካይሮ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሹክሪ ተቀብለዋቸዋል ። አንቶኒ ብሊንከን በእስራኤል እና በሃማስ መካከል ጦርነት ከጀመረ በኋላ ስድስተኛው የመካከለኛው ምስራቅ ጉዟቸው እንደሆነ ተጠቁሟል ።

በተያያዘ የአውሮጳ ህብረት እና ግብፅ በንግድ እና በፀጥታ ዙሪያ ያላቸውን ትብብር ለማሳደግ እንዲሁም ወደ አውሮጳ የሚደረገውን የስደተኞች ፍሰት ለመግታት ያለመ የ7 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዩሮ ወይም የ8 ቢሊዮን ዶላር ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል ።

ስምምነቱ የአውሮፓ ህብረት ከግብፅ ጋር ያለውን ግንኙነት ወደ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ከፍ ያደርገዋል የተባለ ሲሆን የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ውድቀት ለመደገፍ በሚቀጥሉት ሶስት አመታት እርዳታ፣ ብድር እና ሌሎች ድጋፎችን እንደሚያገኙ ተጠቁሟል ።

@ethio_mereja_news
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በድጋሜ የድርድር ጥሪ አቀረበ

"የኦሮሞ ሕዝብ አሁን ያለበት ተጨባጭ የትግል ምዕራፍ ለትጥቅ ትግል የሚያነሳሳም አይደለም" ሲል የኦሮሚያ ክልል ኮምኒኬሽን ቢሮ ገለጸ።

ቢሮው ትላንት ምሽት ባወጣው መግለጫ የኦሮሞ ሕዝብ ሲታገልላቸው የነበሩ "ዋና ዋና ጥያቄዎች" ተመልሰዋል ብሎ የቀሩትም በሂደት እየተፈቱ ይገኛሉ ሲል አስታውቋል።

"ከለውጡ" ወዲህ የትላንቱን የፖለቲካ ኋላ ቀርነት ለማስወገድ እና ሰላምን ለማረጋገጥ እየተሰራ ነው ያለው የክልሉ መንግስት፤ የሰላም በሮችን ክፍት አድርጓል ማለቱን አዲስ ማለዳ ከመግለጫው ተመልክታለች።

"የተለያዩ አካላት ነጠላ ትርክት እየተከተሉ የትናንቱ ኋላ ቀርነት አብሮን እንዲቀጥል እየሠሩ ነው" ያለው መግለጫው፤ እስካሁን ከ3 ሺህ 500 በላይ "የሸኔ" ታጣቂዎች የሰላም ጥሪ ተቀብለው 1 ሺህ 500 የሚሆኑት ተዋጊዎች የመልሶ ማቋቋም ስልጠና ወስደው ወደ ሕብረተሰቡ ተቀላቅለዋል።

የኦሮሚያ ክልል ኮምኒኬሽን ቢሮ በመግለጫው "ለኦሮሞ ሕዝብ የሚበጀው የተገኘውን ድል ተባብሮ በመጠበቅ ለተሻለ ነገ በሕብረት መሥራት እንጂ እርስ በርስ መፋለም እና መጠፋፋት አይደለም" ብሎ መጠፋፋትና መጠላለፍ "እንደአገር ያገኘነውን ድል" ለማስቀጠል ፈተና ሆኗል ብሏል።

የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እና የኢትዮጵያ መንግስት ኤርትራ ውስጥ  ከስድስት ዓመታት ገደማ በፊት የተፈራረሙት ስምምነትን ተከትሎ ወደ አገር ወስጥ የገባው ታጣቂ ቡድን ወደ ኦሮሚያ ክልል ከገባ በኋላ ላለፉት ዓመታት የግጭት ቀጠና ሆኗል።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ)ን ጨምሮ ሌሎችም የፖለቲካ ድርጅቶች በኦሮሚያ ክልል ያለው ግጭት ያላባራ እና ያልተቋረጠ በመሆኑ ከፍተኛ ውድመት እና የሰው ህይወት መጥፋት እያስከተለ እንደሆነ በተደጋጋሚ ይገልጻሉ።

@ethio_mereja_news
የአዲስአበባ ፖሊስ በማህበራዊ ሚዲያ አውቶቡስ ላይ ቦንብ ማፈንዳቱን የሚገልፅ የፈጠራ ወሬ እያሰራጩ ያሉ ሰዎችን አስጠነቀቀ

በማህበራዊ ሚዲያ ፈፅሞ ያልተፈጠረን ነገር የሆነ በማስመሰል ህዝብን ለማደናገር እየሞከሩ ይገኛሉ ሲል የአዲስአበባ ፖሊስ አስታዉቋል።

ሰሞኑን አዲስ አበባ ውስጥ ጥቃት ለመፈፅም በህቡዕ የተደራጀ ቡድን እንዳለ በማስመሰል ሳር ቤት አካባቢ አውቶቡስ ላይ ቦንብ ማፈንዳቱን የሚገልፅ የፈጠራ ወሬ እያሰራጩ ይገኛሉም ብሏል። ይህ ከእውነታ የራቀ በአዲስ አበባ ሰላም የለም ለማስባል ሆን ተብሎ የተሰራጨ የሀሰት መረጃ መሆኑን ሁሉም የከተማችን ነዋሪዎች ሊገነዘቡ ይገባል ብሏል ፖሊስ።

መረጃዉ የተሰራጨዉ ቲክ ቶክ በተባለው ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሲሆን በከተማችን አዲስ አበባ ያለው ሰላም አስተማማኝ ሆኖ እንዲቀጥል ፖሊስ ከመቼውም ጊዜ በላይ የፀጥታ ስራውን እያከናወነ እንደሚገኝ አስታዉቋል።

ህብረተሰቡም ትክክለኛ መረጃዎችን ከትክክለኛው ቦታ የማግኘት ባህሉን ሊያዳብር እንደሚገባ ፖሊስ አሳስቦ ሀሰተኛ መረጃን በማህበራዊ ሚዲያ በሚያሰራጩ አካላት ላይ በህግ አግባብ ተገቢው እርምጃ እንደሚወስድ የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በአማራ ክልል በርካታ አካባቢዎች በመንግሥት ኃይሎችና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ግጭት ተባብሶ መቀጠሉን ዋዜማ ከምንጮች ሰምታለች።

የመንግሥት ኃይሎች በደቡብ ጎንደር ዞን ደራ ወረዳ ውባንተ አባተ የተባለ የፋኖ ታጣቂዎች አመራር መግደላቸውን ትናንት ገልጠው ነበር።

ይህንኑ ተከትሎ፣ በደቡብ ጎንደር ዞን ጋይንት፣ እስቴ ወረዳ እና ሐሙሲት እንዲኹም በምሥራቅና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች አንዳንድ አካባቢዎች በኹለቱ ወገኖች መካከል ውጊያዎች እንደተካሄዱ ተሰምቷል።

@ethio_mereja_news
ፖሊስ በቀድሞው የሰላም ሚንስትር ደዔታ ታዬ ደንደአ ላይ ምርመራውን በማጠናቀቅ ለዓቃቤ ሕግ ማቅረቡን ለፍርድ ቤት እንዳሳወቀ "ኢትዮጵያ ኢንሳይደር" ዘግቧል።

የፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ችሎት ትናንት የተሰየመው፣ የታዬን አካልን ነጻ የማውጣት አቤቱታ ለመመልከት ነበር።

ታዬ በአቤቱታቸው፣ ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንደታሠሩ በመግለጽ፣ ፖሊስ ፍርድ ቤት እንዲያቀርባቸውና ፍርድ ቤቱም ጉዳያቸውን አጣርቶ አካላቸውን ነጻ እንዲያወጣላቸው መጠየቃቸውን ዘገባው አመልክቷል።

ፖሊስ ተጠርጣሪውን ፍርድ ቤት ያላቀረብኳቸው፣ ባስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አማካኝነት በቁጥጥር ሥር ስላዋልኳቸው ነው ማለቱ ተጠቅሷል።

@sheger_press
የሕዝብ ተመራጮች የኾኑት ክርስትያን ታደለ፣ ዮሃንስ ቧያለው፣ ካሳ ተሻገርና ሌሎች እስር ቤት የሚገኙ 11 ተጠርጣሪዎች "አካላዊ፣ ሞራላዊና ሥነ ልቦናዊ ጥቃት" እየተፈጸመባቸው እንደኾነ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ለጠቅላይ ፍርድ ቤትና ለፍትህ ሚንስቴር በደብዳቤ አቤቱታ ማቅረባቸውን ዶይቸቨለ ዘግቧል።

ተጠርጣሪዎቹ በደብዳቤያቸው፣ ለከፍተኛ የምግብ እጥረትና ለጊዜያዊና ቋሚ በሽታዎች ተጋላጭ እንድንኾንና ከቤተሰብ፣ ከጠበቃ፣ ከኃይማኖት አባቶች፣ ከመብት ድርጅቶችና ከሌሎች ጠያቂዎች ጋር እንዳንገናኝ ተደርገናል ማለታቸውን ዘገባው አመልክቷል።

ዘገባው፣ ተጠርጣሪዎቹ ማንነትን መሠረት ያደረጉ ስድቦች፣ ዘለፋዎች፣ ዛቻዎችና ድብደባዎች እንደተፈጸሙባቸው ጠቅሰዋል ብሏል።

ፌዴራል ፖሊስ ጉዳዩ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መርማሪ ቦርድን እንደሚመለከት በመግለጽ፣ በአቤቱታው ዙሪያ ምላሽ እንዳልሰጠ ዜና ምንጩ ጠቅሷል።(DW)

@ethio_mereja_news
በጋምቤላ ክልል ለሚነሱ ግጭቶች ዋነኛ ተዋናዮቹ በውጪ የሚኖሩ ሰዎች ናቸው:-ክልሉ!!

በውጭ የሚኖሩ የሁለቱ ብሔረሰብ ተወላጆች በሚያሰራጩት ግጭት ቀስቃሽ መልዕክት የተነሳ የአከባቢውን የጸጥታ ችግር በዘላቂነት መፈታት እንዳልቻለ የጋምቤላ ክልል አስታወቀ።

በክልሉ ኢታንግ በተሰኘ አከባቢ በተደጋጋሚ የሚከሰቱ የፀጥታ ችግሮችን በቋሚነት ለመፍታት ጥረት እየተደረገ መሆኑን የክልሉ ሠላምና ፀጥታ ቢሮ አስታውቋል፡፡

በክልሉ በተለያዩ አከባቢዎች በተደጋጋሚ በግለሰቦች መካከል የሚፈጠሩ ፀቦችን መነሻ በማድረግ የሚያጋጥሙ ግጭቶችን ለማስቆም ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር በመሆን እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ሠላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ - አቶ ቻውል ኩን ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ቀደምም በተመሳሳይ ምክንያት በተፈጠረ ግጭት ከፍተኛ ቀውስ ማጋጠሙን ያስታወሱት ኃላፊው፤ በወቅቱ ክልሉ በሁለት ብሔረሰቦች መካከል የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ተጠያቂነትን በማስፈን ሁለቱ ብሔሮች ተቀራርበው ችግሮቻቸውን በቋሚነት እንዲፈቱ መደረጉንም አስታውሰዋል፡፡

ይሁን እንጅ ዘላቂ መፍትኤ ማምጣት እንዳልተቻለ እና ዛሬም ድረስ ችግሮቹ መቀጠላቸውን  ያመላከቱት ኃላፊው፤ የክልሉ መንግስት በቋሚነት ችግሮቹን ለመፍታት እየሰራ ነው ብለዋል፡፡

በአከባቢዎቹ በአንጻራዊነት ሠላም ከሰፈነ በኃላ፤ ከሀገር ውጭ የሚኖሩ የሁለቱ ብሔረሰብ ተወላጆች በማህበራዊ ሚዲያ በሚያሰራጬት ግጭት ቀስቃሽ መልዕክቶች ዳግም ግጭቶች እያገረሹ ነው ያሉት ኃላፊው በዚህም ምክንያት ቀጣይነት ያለው ሠላም ማስፈን እንዳልተቻለ ጠቁመዋል፡፡

የክልሉ መንግስት ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በመሆን በቋሚነት ችግሩን ለመፍታት እየሰራ መሆኑን የክልሉ ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊው ጠቁመዋል፡ (መናኸሪያ ሬዲዮ)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የምክር ቤት አባላት ያለመከሰስ መብታቸው ቢነሳም እስካሁን ድረስ ፍርድ ቤት አለመቅረባቸውን ቤተሰቦቻቸው እና ጠበቃቸው ተናገሩ

በአማራ ክልል የተደነገገውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተከትሎ በቁጥጥር ሥር የዋሉት የምክር ቤት አባላት ያለመከሰስ መብታቸው ቢነሳም እስካሁን ድረስ ፍርድ ቤት አለመቅረባቸውን ቤተሰቦቻቸው እና ጠበቃቸው ተናገሩ።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ ክርስቲያን ታደለ፣ የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባል ዶ/ር ካሳ ተሻገር እና የአማራ ክልል ምክር ቤት አባል አቶ ዮሐንስ ቧያለው ያለ መከሰስ መብታቸው ሳይነሳ ከስድስት ወራት በላይ በአዋሽ ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ በሚገኝ ጊዜያዊ ማቆያ ታስረው ቆይተዋል። ቢቢሲ አማርኛ ከሁለት ወር ገደማ በፊት ደግሞ ወደ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ተዛውረው በዚያ ታስረው እንደሚገኙም የቤተሰብ አባሎቻቸቸው እና ጠበቃቸው ነግረዉኛል ማለቱን ዳጉ ጆርናል ከዘገባዉ ተመልክቷል። የምክር ቤት አባላቱ ለምን ወደ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን እንደተዛወሩ ምክንያቱን እንደማያውቁ ከጠበቆቻቸው አንዱ የሆነት አቶ ሰለሞን ገዛኸኝ ገልጸዋል።

ሆኖም ያለመከሰስ መብታቸው በተነሳበት ወቅት በምክር ቤቶቹ ከተሰጡት ማብራሪያዎች በመነሳት ወደ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ያመጧቸው ክስ ለመመሥረት አስበው ሳይሆን እንደማይቀር ግምታቸውን አስቀምጠዋል።

ያለመከሰስ መብታቸው በተነሳበት ወቅት የተሰጠው ማብራሪያ ተጠርጣሪዎቹን በሽብር አዋጅ እና በወንጀል ሕግ ክስ ለመመሥረት የሚያስችል መረጃዎችን ማግኘታቸውን መጠቆሙን ጠበቃው አስታውሰዋል።

እስካሁን ድረስ ፍርድ ቤት ያልቀረቡት የምክር ቤት አባላቱ፣ አዋሽ አርባ በነበሩበት ወቅት በተደጋጋሚ ለሕክምና ይመጡ እንደነበር እና አሁንም በከፋ የጤና ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ከቤተሰቦቻቸው መረዳታቸውንም ጠበቃ ሰለሞን ተናግረዋል።

“አቶ ዮሐንስ ቧያለው ለሕክምና በመጣበት ወቅት ሌላ እስረኛ ለመጎብኘት ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ስሄድ አይቻቸዋለሁ። አካላቸው ተጎሳቁሏል። የአካባቢው የአየር ሁኔታ ሁለመናቸውን እንደቀየራቸውም ከቤተሰባቸው ሰምቻለሁ” ብለዋል።

ለወራት በእስር ላይ የቆዩት የምክር ቤት አባላቱ ለከባድ የጤና እክል መዳረጋቸውንም ቢቢሲ ከቤተሰቦቻቸው ሰምቷል። ጠበቃቸውም ደንበኞቻቸውን አግኝተው ለማነጋገር እና ስላሉበት ሁኔታ ለመረዳት ሜክሲኮ ወደሚገኘው የፌደራል ወንጀል ምርመራ ክፍል ሄደው ቢጠይቁም ፈቃድ እንዳላገኙ ተናግረዋል።

“ይሄ የእኛ ሥልጣን አይደለም። ስለዚህ ጠበቃ እንዲያገኙ የሚፈቅደው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መርማሪ ቦርድ አሊያም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን የሚመለከተው አካል እንጂ እኛን አይመለከተንም። እኛ አቆዩ ነው የተባልነው። የማገናኘት ፈቃድ አልተሰጠንም” የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው ገልጸዋል።

የምክር ቤት አባላቱ በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን እንደሚገኙ እና በቀን አንድ ጊዜ ምግብ እንዲያቀብሏቸው እንደተፈቀደላቸው የሚገልጹት የቤተሰብ አባሎቻቸውም እንግልትና ማዋከብ እንደሚደርስባቸው ተናግረዋል።

ከአራት ቀናት በፊት አቶ ዮሐንስ ቧያለውን በስልክ እንዳነጋሯቸው የሚገልጹት የቤተሰብ አባል “ስላለባቸው የጤና ችግር እና እንግልት በነጻነት ለመናገር እንኳን ተቸግረዋል” ብለዋል። የምክር ቤት አባላቱ ከዚህ ቀደም አዋሽ አርባ በነበሩበት ወቅት የሚደርሰባቸውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት በመቃወም የረሃብ አድማ አድርገው ለጤና ችግር ተዳርገው እንደነበርም ተገልጿል።

ከሦስት ቀናት በፊት እንደተጻፈ በሚገልጽ እና የምክር ቤት አባላቱን ጨምሮ በ14 እስረኞች ፊርማ በወጣ በእጅ የተጻፈ ደብዳቤ ላይ፣ በእስረኞቹ ላይ ከፍተኛ እንግልት እና የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንደተፈፀመባቸው ይገልጻል። ከታሳሪዎቹ የቤተሰብ አባል ለቢቢሲ የተላከው ይህ ደብዳቤ ማንነትን መሠረት ያደረገ ስድብ፣ ዛቻ፣ ማስፈራራት እና ድብደባ እንደተፈፀመባቸው፤ እንዲሁም ከታሰሩ ከሰባት ወራት በላይ ቢሆናቸውም ከጠበቃ፣ ከሃይማኖት አባቶች፣ ከቤተሰብ፣ ከሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ጋር እንዳይገናኙ መደረጋቸውን ይገልጻል።

ከዚህም በተጨማሪ ለምግብ እጥረት እና ለተለያዩ በሽታዎች መዳረጋቸው፣ ታስረው በቆዩበት የአዋሽ ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ በመቃብር ቦታ እና የዱር አውሬዎች በሚገኙበት ስፍራ መታሰራቸው ሞራላዊ እና ሥነ ልቦናዊ ተፅዕኖ እንዳደረሰባቸው፣ እንዲሁም በጨለማ ክፍል ውስጥ ተዘግተው እንደሚውሉ ያትታል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው ቤተሰቦቻቸውም የጨለማ ክፍል ውስጥ ታስረው እንደሚገኙ እንደገለጹላቸው ተናግረዋል።

የአቶ ዮሐንስ ቧያለው የቤተሰብ አባል የሆኑት ግለሰብ “ምግብ ሊቀበለኝ ሲመጣ ለማየት ሲቸገር አየሁት። ምን ሆነህ ነው? ብዬ ስጠይቀው ‘በጨለማ ክፍል ውስጥ እያስገቡን ስለነበር ዐይኔ ችግር አለበት’ አለኝ” ብለዋል።

በአማራ ክልል የተከሰተውን አለመረጋጋት ተከትሎ በክልሉ ውስጥ እና እንዳስፈላጊነቱ በመላው አገሪቱ ተግባራዊ እንዲሆን ለስድስት ወራት የተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጥር 24/2016 ዓ.ም. ለተጨማሪ አራት ወራት መራዘሙ ይታወሳል።

Via ቢቢሲ አማርኛ

@ethio_mereja_news
በሞስኮ በደረሰው የሽብር ጥቃት የሟቾች ቁጥር ከ60 ተሻገረ! ለጥቃቱ አይ ኤስ ሀላፊነት ወስዷል!!

ሩሲያ በሞስኮ ጥቃት የፈጸሙትን ሰዎች እያደነች ትገኛለች!

በሩሲያ ዋና ከተማ ሞስኮ በተዘጋጀ የሙዚቃ ድግስ ላይ ታጣቂዎች ትናንት ምሽት ባደረሱት ድንገተኛ ጥቃት በርካታ ሰዎች ላይ ጉዳት አድርሰዋል። ታጣቂዎቹ በአውቶማቲክ የጦር መሳሪያ እና በቦምብ ባደረሱት ጥቃት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ60 የተሸገረ ሲሆን፤ የቆሰሉ ሰዎች ቁጥር ደግሞ ከ145 ማለፉ ነው የተነገረው።

በተጨማሪም ጥቃቱን የፈጸሙ ሰዎች የእጅ ቦምብ እና ሌሎች ተቀጣጣይ ፈንጂዎችን በመወርወር 12 ሺህ 900 ስኩዌር ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የአዳራሹን ክፍል በእሳት ማጋየታቸውም ተነግሯል። የሩሲያ የምርመራ ኮሚቴ፤ ከፍተኛ የመንግስት የወንጀል ምርመራ ኤጀንሲ በጥቃቱ ላይ "የሽብር" ምርመራን ከፍቷል።

የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቤተ መንግስት ክሬምሊን በጥቃቱ ዙሪያ እስካሁን ተጠያቂ ያደረገው አካል የለም ተብሏል።

የዩክሬን ፕሬዝዳንት አማካሪ መይክሃይሎ ፖዶልያክ፤ ዩክሬን በዚህ ተግባር ውስጥ እጇ የለበትም ሲሉ አስተባብለዋል።

በሽበርተኘት የተፈረጀው ኢስላሚክ ስቴት (አይ.ኤስ) ለጥቃቱ ኃላፊነት እንደሚወስድ ያስታወቀ ሲሆን፤ የአይ ኤስ ክንፍ የሆነው የአፍጋኒስታኑ የኮርሳን ፕሮቪንስ ኢስላሚክ ስቴት ጥቃቱን ያደረሱት አባላቱ እንደሆኑ ገልጿል።

አይ ኤስ በጉዳዩ ላይ በሰጠው አጭር ማብራሪያ፤ ተዋጊዎቹ በሞስኮ ዳርቻ ላይ ጥቃት በመሰንዘር፣ “በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ገድለዋል፣ አቁስለዋል፣ በቦታው ላይ ከፍተኛ ውድመት አድርሰዋል፤ ከዚያ አምልጠዋል” ብሏል።አሜሪካ ባሳለፍነው ሳምንት ላይ ጽንፈኞች በሞስኮ የማይቀር የሽብር ጥቃት ሊያደርሱ ይችላሉ በማለት ማስጠንቀቋ አይዘነጋም።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
#Update

" ምዕመናን #ክርስቲያናዊ_አለባበስ ለብሳችሁ እንድትገኙ እና የአቅማችሁን ያህል እድትለግሱ ጥሪ እናቀርባለን " - ማህበረ ቅዱሳን

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን " ኑ ቸርነትን  እናድርግ " በሚል መሪ ቃል ነገ እሁድ ከቀኑ 7:00 ላይ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር በሚሊኒየም አዳራሽ ያካሂዳል።

ገቢ ማሰባሰቢያው በሀገራችን ኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች ባጋጠመው ማኅበራዊ ቀውስና ድርቅ የተጎዱ ወገኖቻችንን፣ ገዳማትና አብነት ት/ቤቶችን ለመደገፍ የሚውል እንደሆነ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከአዘጋጆቹ ያገኘው መረጃ ያሳያል።

የመግቢያ ትኬቶች በ100 ብር እየተሸጡ ሲሆን ትኬቶቹን ፦
1. በማኅበረ ቅዱሳን ሕንጻ 4ኛ ወለል (ቤተ አብርሃም)
2. በወረዳ ማዕከላት ጽ/ቤቶች  
3. በማኅበረ ቅዱሳን ንዋያተ ቅድሳት መሸጫ ሱቆች
4. በማኅበረ ቅዱሳን ሕንጻ የዕለት ገንዘብ መሰብሰቢያዎች
5. በአሐዱ ባንክ ሁሉም ቅርንጫፎች
6. በሰ/ት/ቤት ጽ/ቤቶች ማግኘት ይቻላል ተብሏል።

ነገ በመግቢያ በር ላይም ትኬት ማግኘት እንደሚቻል ተገልጿል።

ሁሉም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች / ምዕመናን ነገ ወደ ሚሊኒየም አዳራሽ ሲሄዱ ክርስቲያናዊ አለባበስ እንዲለብሱ እና የአቅማቸውን ያህል እንዲለግሱ ጥሪ ቀርቧል።

@ethio_mereja_news
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ተጨማሪ 100 'ሙርከኞች' በይቅርታ መልቀቁን ገለፀ!!

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ተጨማሪ 100 የኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት እስረኞችን በዛሬው ዕለት መጋቢት 14 ቀን መፍታቱን ይፋ አድርጓል።

በትላንትናው ዕለት 112 እስረኞችን የለቀቀው አስተዳደሩ እስካሁን ለ212 'ሙርከኞችን' ይቅርታ ማድረጉን ነው የተገለፀው።

@ethio_mereja_news
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጋርዱላ ዞን አስተዳደር፣ አማራ ክልል ውስጥ ታጣቂዎች አግተዋቸው የቆዩ የደራሼ ወረዳ ተወላጅ የኾኑ የጉልበት ሠራተኞች ትናንት ምሽት በሰላም እንደተለቀቁና ዛሬ አዲስ አበባ እንደገቡ አስታውቋል።

የዞኑ አስተዳደር 246 የወረዳው ተወላጆች ኒኮትካ ኮንስትራክሽን የተባለ የግል ኩባንያ ለሕዳሴ ግድብ ሐይቅ ማረፊያ ለጫካ ምንጣሮ ቀጥሯቸው ወደ አካባቢው ሲጓዙ በክልሉ ውስጥ በታጣቂዎች እንደታገቱ ባለፈው ወር አስታውቆ ነበር።

የዞኑ አስተዳደር፣ ታጣቂዎቹ ታጋቾቹን እንዲለቋቸውና ፌደራል መንግሥቱና የደቡብ ኢትዮጵያና የአማራ ክልላዊ መንግሥታት ታጋቾቹን ለማስለቀቅ ጥረት እንዲያደርጉም መጠየቁ ይታወሳል።

ታጋቾቹ የተለቀቁት፣ ቀጣሪው ድርጅት፣ መንግሥትና የሐይማኖት አባቶች ባደረጉት ጥረት እንደኾነ ዞኑ ገልጧል።

@ethio_mereja_news
አስቸኳይ አሁን የደረሰ ሰበር የጥንቃቄ መረጃ

አዳማ (ናዝሪት ) የሀገረ ስብከቱ መቀመጫ ኢየሱስ ቤተክርስቲያንን ለማቃጠል የኦነግ ሸኔ ቡድን በአካባቢው መሽጎ እንደሚገኝ ከዉስጥ የመረጃ ምንጭ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ቀበሌ 12 ። ወደ ማጥቃት ለመግባት ጥቂት ሰአታት ብቻ ይቀሩታል ።

ሼር አድርጉት በፍጥነት የ(አዳማ(ናዝሬቱን ኢየሱስ  ቤተክርስቲያን እንታደግ 🙏

@ethio_mereja_news
የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በግፍና በኢ-ፍትሀዊነት ከቀየው ፊንፊኔ (አዲስ አበባ) እንዲሰደድ የተደረገውን የኦሮሞ ሕዝብ ወደ ቀደመ ስፍራው እንዲመለስ እያደረግን ነው አሉ ።

@ethio_mereja_news
" ከእንግዲህ በሽፍትነት / rebel በመሆን መንግሥትን መጣል አይደለም ፤ መነቅነቅ አይቻልም " - ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፤ " ከእንግዲህ በኃላ በሽፍትነት / rebels በሚመስል ነገር መንግስትን መጣል አይደለም መነቅነቅ እንኳን አይቻልም " አሉ።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ይህን ያሉት በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ ከፍተኛ እና ታማኝ ግብር ከፋይ ባለሀብቶችን ሰብሰበው በመከሩበት ወቅት ነው።

ታማኝ ከፍተኛ ግብር ከፋዮቹ ለጠ/ ሚኒስትሩ በዛ ያሉ ጥያቄዎችን ያቀረቡላቸው ሲሆን በየአካባቢው ከሚታየው ሁኔታ አንፃር #የሰላም ጉዳይ ከጥያቄዎቹ አንዱ ነበር።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፤ " እኛ የምንፈልገው ሰላም ነው " ብለዋል።

ሰላምን በተመለከተ ያነሷቸው ሃሳቦች ሁሉ ጥሩ እንደሆነ ገልጸው " ሽማግሌ ነን እድሜያችን ልምዳችን ያላችሁ #ሸምግሉ " ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

" እኔ የማረጋግጥላችሁ ግን በሽፍትነት / rebels በሚመስል ነገር ከእንግዲህ በኃላ የኢትዮጵያን መንግስት መጣል ሳይሆን መነቅነቅ አይቻልም። በጣም የተለያየን ነን ብቃታችን አይደለም የሚለያየው ያለን conviction ይለያያል እሱ ብር ነው የሚሰበስበው እኛ ስራ ነው የምንሰራውን እናውቃለን እያደረግን ያለነውን በቀላሉ የሚሆን አይመስለኝም " ሲሉ ተደምጠዋል።

" እነሱ ሰዎች ልብ ገዝተው ከመጡ በጣም በጣም በደስታ ነው የምንቀበለው ፤ እናተም ሞክሩ በሁሉም በምትችሉት መንገድ ሞክሩ " ብለዋል።

@ethio_mereja_news
2024/10/03 21:32:39
Back to Top
HTML Embed Code: